December 30, 2013
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ
Monday, December 30, 2013
Wednesday, December 25, 2013
በደቡብ ሱዳን ተገደው የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጁባ ገቡ
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የተደፈሩ 4 ሴቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል በሚገኝበት ጁባ ደርሰው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። ሴቶቹ መደፈራቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ለማረጋገጥ የቻለ ሲሆን፣ ሴቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ያደረገው ጥረት በመስመር ግንኙነት የተነሳ ሊሳካለት አልቻለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ታውቋል። አምባሳደሩ በዚህ አስቸጋሪ ሰአት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በአገሪቱ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተችተዋል።
በሌላ በኩል ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም የኢትዮጵያን ስደተኞች በተመለከተ ኢምባሲው በቅርበት ጉዳዩን እየተከታተለ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ ለሱዳን ችግር የኢጋድ አገሮች የሽምግልና ጥረት መጀመራቸውንም ገልጸዋል። በሽምግልና ጥረቱ ስለተገኘው ውጤት ግን ያሉት ነገር የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የተፈጠረውን የ እርስበርስ ግጭት ተከትሎ ጎሳ ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ግድያ እንደተፈፀሙ የሚያሳዩ አዳዲስ መረጃዎች በመውጣት ላይ ናቸው።
ጋዜጠኞች ከጁባ የዓይን ምስክሮችን ዋቢ አድርገው እንደዘገቡት ግጭቱን ተከትሎ ከ200 በላይ የሚሆኑ የንዌር ጎሳ ተወላጆች በደህንነት ሀይሎች በጅምላ ተገድለዋል።
ሌላ የጁባ ነዋሪም ሲናገር ብዙዎቹ የጸጥታ ሀይሎች ከዲንካ ጎሳ አባላት ስለሆኑ ኑዌሮችን እየለዩ ይገድሉ ነበር ብሏል።
ከሳምንት በፊት በጁባ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደተለያዩ ቦታዎች ተሸጋግሮ በሪክ ማቻር የሚመሩት አማጽያን “ቦር” እና “ቤንትዩ” የተሰኙ ቁልፍ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል።
ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር የቀድሞ ምክትላቸው መፈንቅለ መንግስት ሊፈፅሞባቸው እንዳሰቡ ክስ ቢያሰሙም፤ ሪክ ማቻር ግን በተቃውሞ የተነሱት በስርዓቱ እየተፈፀመ ባለው ጎሳ ላይ ያነጣጠረ የመብት ረገጣ እና ጥሰት ተከፍተው እንደሆነ በመግለጽ ነው ክሱን ያስተባበሉት።
በቀድሞ ሁለት የትግል ጓደኛሞች መካከል በስልጣን ማግስት የተከሰተው ይህ ግጭት በኑዌር እና ዲንካ ጎሳዎች መካከል ሙሉ ጦርነት በማስነሳት ደቡብ ሱዳንን ዳግም መውጫ ወደሌለው የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳይከታት ከፍተኛ ስጋት ማሳደሩን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ሰሞኑን በአማጺዎች ቁጥጥር ስር ውላ ነበረችው ቦር በመንግስት ሀይሎች እጅ መውደቋን ቢቢሲ ዘግቧል። የመንግስት ቃል አቀባይ እንደሉት ጦራቸው ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ከአማጽያን እጅ አስለቅቀዋል። አማጽያኑንም እግር በግር እየተከተሉ እየወጉዋቸው ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ማምሻውን እንዳስታወቁት ደግሞ በአገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሳይገደሉ አልቀረም። በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች በጅምላ የተቀበሩባቸውን ቦታዎች ማግኘታቸውን ባለስልጣኑ ገልጸዋል።

Friday, December 20, 2013
አቶ አያሌው ጎበዜም የድል አጥቢያ አርበኛ እንደ ውሃ ላይ ኩበት እመሀል ላይ እንደዋለሉ የማይቀረውን ስንብታቸውን ተሰናበተዋል
አቶ አያሌው ጎበዜም እንደምንም የመምህርነት ስራቸውን ትተው የድል አጥቢያ አርበኛ በመሆን ገብተው ወይ ራሳቸውን ነፃ ሳያወጡ ወይ ህዝቡን በትክክል ሳያገለገሉ እንዲሁ እንደ ውሃ ላይ ኩበት እመሀል ላይ እንደዋለሉ የማይቀረውን ስንብታቸውን ተሰናበተዋል፡፡ወያኔ እንደ ሸንኮራ ምጥጥ አድርጎ ተፋቸው፡፡እኔ እስከማውቃቸው አቶ አያሌው ከሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የሚለዮት በሙስና አለመጠርጠራቸው፤ብዙ ማውራት የማይወዱ ሲናገሩም ከባህል እና ከሞራል የማያፈነግጡ፤ለሚኖሩበት ማሀበረሰብ ክብር በመስጠት ሚስታቸው ሳይቀር አብረዋቸው ከሚኖሩት እድርተኞች እኩል መሳተፋቸው ነው፡፡ አቶ አያሌው እንደአባዱላ ገመዳ ብዙ ቤት ገንብተው ለትግሉ ስላስቸገረኝ ውሰዱልኝ ሲሉ አልተደመጡም፡፡እስካሁን ባለኝ መረጃ መሰረት አቶ አያሌው ባህርዳር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 14 አካባቢ በማህበር ተደራጅተው በወሰዱት አንድ ቦታ ቤት እንደገነቡ ነው ፡፡ ዘመድ አዝማዳቸውን ስራ በማስገባት አይታሙም ፡፡የአቶ አያሌው ልጆች እንደ ሌሎች የባለስልጣን ልጆች አሜሪካ እና አውሮፓ ወይም አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ውድ የግል ትምህርት ቤቶች አይደለም የሚማሩት፡፡እንደማንኛውም ደሃ ቤተሰብ ባህርዳር ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርቤቶች ያስተምሩ ነበር፡፡
አቶ አያሌው እንግዲህ እነዚህ መልካም ነገር ቢኖራቸውም የተሰጣቸውን መክሊት አባክነው የክልሉ ህዝብ በየቦታው ሲፈናቀል የክልሉ መሬት እንደዳቦ እየተሸነሸነ ሲታደል የተቀመጡባትን ወንበር ላለማጣት በዝምታ ማለፍን መርጠዋል፡፡ይህ ደግሞ በምንም መልኩ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ከሌባ ጋር አብሮ ስርቆት ሂዶ በቅርብ ርቀት ሲሰርቁ እያዩ ዝም ማለት እና የሰረቀው አብሮኝ ያለው ሰው ነው አንጂ እኔ ነፃ ነኝ ቢሉ ከቅጣት አያመልጡም፡፡እንግዲህ እርሳቸው በስልጣን ላይ በቀዮበት ጊዜ ለጠፋው ሀይወት፤ለወደመው ንብረት፤ለተፈጠረው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድቀት የድርሻቸውን ይወስዳሉ፡፡
መቼም በዘመኔ ወያኔ ስራና ሰራተኛ ተገናኝተው ባይውቁም እንደአማራ ክልል ባለስልጣናት በእውቀት ድርቅ የተጠቃ የለም፡፡”ሰው ሢታጣ ይመለመላል ጎባጣ” ነው ነገሩ፡፡ሰው ሲታጣ ማለቴ ለወያኔ በታማኝነት የሚያገለግል ማለቴ ነው፡፡አቶ አያሌውን የተኩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በርቀት ትምህርት በማኔጅመት የመጀመሪያ ዲግሪ ሲኖራቸው በ1998 ዓ.ም የብአዴን ቢሮ ውስጥ ይሰሩ ነበር፡፡የተኛው የተምህርት ዝግጅት ተዛምዶ የክልሉየግብርና ቢሮ ኃላፊ ሁነው እንዲሰሩ እንዳበቃቸው የሚያውቀው ወያኔ ብቻ ነው፡፡ይባስ ብሎ ክልሉን የመምራት ሀላፊነት ለሳቸው መስጠት ከምጡ ወደ ዳጡ ነው፡፡ አቶ ገዱን የአማራ ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርቶች ተመርቀው የፓሪቲ አባል ካልሆኑ ስራ እንዳይሰጣቸው በክልሉ ላሉ ሁሉም ዞኖች ትእዛዝ ሲያስተላልፉ በተቃራኒው አባል ለሆኑት ስልክ ብቻ በመደወል እንዲቀበሉዋቸው ያል ምንም ውድድር እና ማስታወቂ በደብዳቤ ብቻ ሲመድቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡በተለይ በ1998ዓ.ም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በወረዳዎች መከፈትን ተከትሎ በሁሉም ወረዳዎች የተመደቡ ፈላፊዎች በዚህ አይነት የተመደቡ ነበሩ፡፡አቶ ገዱ የክልል ፕሬዚዳንት ቀርቶ ለቀበሌ አመራርነት ሚያበቃ ስብእና እንደሌላቸው ሚያወቁዋቸው ሁሉ የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡ግን ምን ይደረግ ወያኔ በሚመራው ሀገር ውስጥ ለሀገር የሚጠቅም ነገር በነፃነት መስራት ስለማይቻል አንዴ አዲሱ ለገሰ፤አንዴ ደመቀ መኮነን፤አንዴ ገዱ አንዳርጋቸው እተፈራረቁ በህዝቡ ትክሻ ላይ ያለከልካይ ይጫናሉ፡፡
በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ የምናውቀው ደጉ አብረሀም የተወለደው ያደገው ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ ነበር፡፡ እግዚያብሔርም አብርሀምን “አብርሀም አብርሀም ውጣ !እኔ ወደማሳህም ወደዚያ ተራራ ሂድ አለው”፡፡አብርሀምም ቤተሰቡ የሚያመልከው ጣኦት አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው የማይሰማ “ልክ እንደ ኢህአዴግ” ነበርና ከፈጣሪው የመጣለትን ትእዛዝ ሳያመነታ ተቀበለው ፡፡በሀጢያት ከረከሰው አካባቢውም ተለይቶ ወጣ፡፡አብርሀም ያደረገው ከሚወደው ቤተሰቡ በባእድ አምልኮ አብሮ ላለመኖር የግድ መለየት ነበረበት ተለያም፡፡ዛሬ በተለያዮ የስልጣን እርከን በወታደራዊም ሆነ በሲቪል ተቋማት ከወያኔ ጋር እየሰራችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ አብረሀም በደም ከተበከለው ፤ህዝብን አፍኖ በችግር እየገደለ ካለው ስርኣት ራሳችሁ ለይታችሁ ውጡ፡፡አብርሀም ቅድስናን የተቀዳጀው ከባእድ አምልኮው ተለይቶ ነው፡ለጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ወዘተ ራሳችህን እስካሁን አስገዛችሁ፡፡መጀመሪያ እውነት አለ መስሎአችሁ ገብታችሁ ይሆናል፡፡ግን ወያኔ ጋ ቀርቦ ያላየ የለም ደረጃው ይለያ እንጂ ፡፡ አንድም እውነት የለም ሁሉም ነገር የውሸት የማስመሰል ነው፡፡ወያኔ ጣኦት ነው፡፡ህገ-መንግስቱ፤የመለስ ራዕይ፤የብሄር መብት፤እድገት እና ትርናስፎርሜሽኑ፤የሚወራው ዲሞክራሲ ሁሉም ባእድ አምልኮዎች ጣኦቶች ናቸው፡፡እውነታውን ታውቁታላችሁ፡፡ስለገባችሁበት ነው እንጂ ሁሉም የህወአትን እድሜ ማራዘሚያ ነው፡፡ማንም ከወያኔ ጋር ሁኖ ህሌናው ያመነበትን እንደማይሰራ እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ፍርድቤቶች የሚፈርዱት በህሌናቸው ነው?ጋዜጠኞች እየሰራችሁ ያላችሁት እውነታውን ነው? ወታደሩ የገንዛ ወንድሙን፣እህቱን በቆመጥ የሚቀጠቅጠው አምኖበት ነው?፤የሚስኪኑዋ እናትክን ቤት እላይዋ ላይ የምታፈርሰው ህሌናህ ፈቅዶ በችግር ለተቆራመደው ወገናችን መርዳት ስንችል ለምን ተጨማሪ እዳ እንሆንባቸዋለን፡፡ከወያኔ ፍርፋሪ መጠበቅ ለጣኦት የተሰዋ መብላት ነው፡፡ ነው?ከወያኔ አገልጋይነት ተለዩ!ከወያኔ መንደር ውጡ!
ዳዊት
ዓረና መድረክ ከተምቤን ኗሪዎች ጋር ለመወያየት እሁድ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል (አብርሃ ደስታ ከመቐለ/ትግራይ
ዓረና መድረክ ከተምቤን ኗሪዎች ጋር ለመወያየት እሁድ ታህሳስ 13, 2006 ዓም በዓብይ ዓዲ ከተማ (ማዘጋጃቤት አዳራሽ) ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል። የዓረና አባላት ከትናንት ሐሙስ ጀምሮ በተለያዩ የተምቤን ከተሞች ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው። እስካሁን የተምቤን ህዝብ በጥሩ መንፈስ እየተቀበላቸው ሲሆን የአከባቢው አስተዳዳሪዎች ግን እያንገራገሩ ነው። አስተዳዳሪዎች ቅስቀሳ የሚያካሂዱ የዓረና አባላትን ይሰድባሉ፣ ዕንቅፋት ይፈጥራሉ። የዓረና አባላት ቅስቀሳ በማድረጋቸው በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። ቅስቀሳው ግን በሌሎች አባላትም ቢሆን ይቀጥላል። የማይጨው ከተማ አስተዳዳሪዎች በጥሩ መንፈስ ተቀብለውን ነበር። የተምቤኖቹ ግን ለምን አንገራገሩ? ህወሓት ምክንያት አለው።
ኢህአዴግን ሙሉ በሙሉ ለማሸነፍ በትግራይ ክልል መንቀሳቀስ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ትግራይ ክልል የህወሓት መሰረት ነው። ኢህአዴግ ያለ ህወሓት ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በህወሓት ጠመንጃ ድጋፍ የሚኖሩ እንጂ የህዝብ ድጋፍ የላቸውም። ስለዚህ የህወሓት የትግራይ መሰረት ከተናጋ ኢህአዴግ ይናጋል።
ከትግራይ ክልል ደግሞ ሁለት ቦታዎች በደምብ መያዝ በቂ ነው፤ ተምቤንና ዓጋመ። በፖለቲካ ዘርፉ የተምቤን ህዝብ ከጎንህ ማሰለፍ ከቻልክ መለው ትግራይ መቆጣጠር ቀላል ይሆናል። (ምክንያት ሌላ ግዜ)። ሁለተኛው ቁልፍ የትግል መሰረት የዓጋመ ህዝብ ነው (በኢኮኖሚ ዘርፍ)። (ምክንያት ሌላ ግዜ)። የዓጋመ ህዝብ ከጎንህ ለማሰለፍ ግዜ ሊወስድ ይችላል። የተምቤን ግን ትንሽ ጥረት ማድረግ በቂ ነው። እናም ጉዟችን ወደ ተምቤን ነው።
ህወሓትም ይሄ የተምቤን ጉዳይ በደምብ የተረዳው ይመስላል። በተምቤን ዓብይ ዓዲ ከተማ በምናደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ለመረበሽ የተዘጋጀ ይመስላል።
እሁድ በዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ ስለሚደረገው ስብሰባ ተጨማሪ ዘገባ በወቅቱ ይቀርባል።
ተጨማሪ ማብራሪያ፡ ከህወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ጀምሮ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ህዝቦች ዓቅሙ እያላቸው በህወሓት የተንኮል አገዛዝ ምክንያት ተጨቁነው (ታፍነው) የሚኖሩ ህዝቦች የተምቤንና የዓጋመ ናቸው። የተምቤን ህዝብ የፖለቲካ ዓቅም አለው። የዓጋመ ህዝብም የኢኮኖሚ ዓቅም አለው። ሁለቱም ህዝቦች (የተምቤንና ዓጋመ) መቀስቀስ ከተቻለና አብረው ከሰሩ መላው ትግራይ አንቀሳቅሰው ህወሓትን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ ይችላሉ። ህወሓት አሁንም የሁለቱም ህዝቦች መነሳት ያስፈራዋል። ተምቤኖች በፖለቲካ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፤ ዓጋሜዎቹም በኢኮኖሚ እንዲዳከሙ ይደረጋል። ተምቤኖች እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ለዚህም ነው የህወሓት አስተዳዳሪዎች በተምቤን ለሚደረግ የስብሰባ ቅስቀሳ ለመረበሽ የተነሱት (የተምቤን አስተዳዳሪዎች የተምቤን ተወላጆች አይደሉም)። ህወሓት በተምቤንና ዓጋመ ምንም ድጋፍ የለውም። በጠመንጃ ሃይል ነው የሚገዛው።

Thursday, December 19, 2013
የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን በማሰጠትና ለዜጎች ሞት የሚጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን ለቀቁ
(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ክልል መሬቶች ለሱዳን እንዲሰጡ ከገዢው ሕወሓት ጋር በመተባበር ወንጀል፣ እንዲሁም ከጉራፈርዳ ተባረው
ወደ አማራ ክልል የመጡ ዜጎች የሚቀበላቸው የክልል መስተዳድር ጠፍቶ ለርሃብና ለሞት በመዳረጋቸው በዚህም ወንጀል እንደሚጠየቁ የሚነገርላቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን አስረከቡ።
መንግስታዊ ሚድያዎች አቶ አያሌው ጎበዜ “በመተካካት” ሂሳብ ስልጣኔን ተረክበውኛል ሲሉ ይዘግቡ እንጂ የአማራ ክልል ምክር ቤት በአስቸኳይ ተሰብስቦ ይሄን ውሳኔ ማጽደቁ ከበስተጀርባው የተደበቀ ምስጢር ሳይኖር እንዳልቀረ ብዙዎች ይገምታሉ። በተለይም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ጋር የኢትዮጵያን መሬቶች አሳልፈው ለመስጠት ከተፈራረሙ በኋላ የአቶ አያሌው ስልጣኔን ልልቀቅ ጥያቄ ምንልባትም ለሱዳን ከሚሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ለዘ-ሐበሻ ሰጥተዋል።
የአማራ ክልል አስቸኳይ ስብሰባውን ከትናንት ምሽት ጀምሮ በባህር ዳር ያካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ክልሉን ላለፉት 8 ዓመት ተኩል የመሩትን የአቶ አያሌው ጎበዜን ጥያቄ ወዲያውኑ በመቀበል ከስልጣን ያወረዳቸው ሲሆን በምትካቸውም በሕወሓት ተላላኪነታቸው ከአቶ ደመቀ መኮንን አይተናነሱም የሚባሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተተክተው ተሾመዋል። አቶ ገዱ የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንትና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አቶ አያሌው አልፈጽምም ሲሉ የነበሩ ሥራዎችን ለሕወሓት በማደር ይሰሩ እንደነበር እርሳቸውን የሚያውቁ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል። በተለይም አምባገነንና እኔ ያልኩት ይድመጥ የሚል ባህሪይ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ የአማራ ክልል ስር ያሉ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለሱዳን በመስጠት ከሕወሓት ጋር አብረው እንደሚሰሩ ይጠበቃል።
አቤል የተባሉ በክልሉ የሚኖሩ በፌስቡክ ዘ-ሐበሻን የሚከታተሉ አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት አስተያየት “ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ ዛሬ በአቶ ደጉ አንዳርጋቸው የተተኩበት አስቸኳይ ጉባኤ አንደምታው ምን ይሆን? ምን አልባት ከሠሞኑ የሚሠሙ ወሬዎችን እልባት ለመስጠት ይሆን? ያ ማለt ዐድርቃይን ለትግራይ፣ መተማን ለሱዳን፣ ጃዊ አካባቢ ያለ የአማራ ክልል ግዛቶችን ለመስጠት መሠናክሉን ከወዲሁ ለማቅለል ይሆን እንዴ? ያ ምርጫ፣ ዘመን ሣይጠናቀቅ ከስልጣን አቶ አያሌውን ማንሣት ምን ማለት ነው? እርሣቸው ለክልሉ ልዑላዊነት መከበር ጥብቅና የሚቆሙ ታማኝ መሪ ስለነበሩ ገለል ለማድረግ የታለመ ሹም ሽር ነው የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።
ሌላው የዘሐበሻ የፌስቡክ ተከታይም እንዲሁ “የአማራን ክልል መሬት ለሌላ አሳልፌ አልሰጥም በማለታቸው ስልጣናቸውን እንደለቀቁ ነው” የማምነው ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተውናል።
አንድ ቀን በኢትዮጵያ ነፃነት ሲመጣ ምንም እንኳ እርሳቸው አልፈረሙም፤ የፈረሙት አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው የሚባል ወሬ ቢኖርም አቶ አያሌው ጎበዜ ለሱዳን በተሰጠው መሬት፣ በአማራ ክልል ለደረሱ ጭፍጨፋዎች፣ በዜጎች መፈናቀል ዙሪያ ላሳዩት ቸልተኝነት ለፍርድ ይቀርባሉ የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው።

Wednesday, December 18, 2013
ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኖርዎይ በርገን ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሔደ
በበርገን ከተማ ለመጀመርያ ግዜ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ በርገን ቅርንጫፍ አስተናጋጅነት በዲሴምበር 14፥2013 የተዘጋጀው ህዝባዊ ስብሰባ በደመቀ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ100 በላይ የሚገመት ህዝብ የተገኘ ሲሆን ከተለያዩ የኖርዎይ ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱም ላይ ተገኝተዋል፥፥
በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ እንግዶች የነበሩት
1ኛ. ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግንቦት7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ አባል
2ኛ. አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ ዋና ሊቀመንበር
3ኛ. ዶ/ር ሙሉአለም አዳም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ በኖርዎይ የድርጅት አባል ናቸው፥፥
የውይይት መድረኩ ከመጀመሩ በፊት በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ፥ እየተገደሉ እንዲሁም በግፍ ኢሰብአዊ ድርጊት ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ የበርገን ቅርንጫፍ ጽ/ት ሰብሳቢ አቶ ሹሜ ወርቁ አጭር የመክፈቻ ንግግር ካረጉ በኋዋላ ተጋባዥ እንግዶቹ በየተራ ስለሚመሩአቸው ድርጅቶችና የወቅቱን የሃገራችንን አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተና ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አብረው በስምምነት የሚሰሩበትን ሁኔታ ማምጣት እንዳለብን እንዲሁም ስለ መደራጀት አስፈላጊነት ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል፥፥
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ስለ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዓላማ ራእይና ግብ እንዲሁም ስለውጭ እምቢተኝነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ሁሉም ኢትዮያዊ ግንቦት7ትን እንዲቀላቀልና ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ተባብረን እንታደጋት በማለት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለያዩ ድርጅቶች ስር ተደራጅቶና ታቅፎ መንቀሳቀሱ ያለውን ጠቀሜታና የሐይማኖትና የሲቪክ ማህበራትን ማደራጀትና ማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን አሳስበዋል፥፥ ፥፥
አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ ዋና ሊቀመንበር ስለ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ አመሰራረትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ በሰፊው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከህዝቡም ለቀረበላቸው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል፥፥
በተጨማሪም ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም በኖርዎይ የስደተኞች አኗኗር ዙሪያ ያለውን ችግር እንዲሁም ሁሉም የተቃቃሚ ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ የበርገን ቅርንጫፍ በተቋቋመ በአጭር ግዜ ውስጥ የደረሰበት ደረጃም በእጅጉ አስደሳች እንደሆነ በመግለፅ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ህዝቡ ለነጻነት ለሚደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፥፥
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ በሐና ሰመረ ሐቅ ተሰደደ በሚል ርእስ አጭር ግጥም የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በሎሚታ ገብረሚካኤል በምስል በተደገፈ በቀረበው የኢትዮጵያ የታሪክ ጉዞ ከነገስታት ስርአት እስከ ሐገራችን በወያኔ አገዛዝ ስር ወድቃ አሁን የደረሰችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ዘገባ ለታዳሚው ቀርቧል፥፥
በመጨረሻም ለእንግዶቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ ዝግጅቱ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሐይል መዝሙርን በመዘበር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥፥
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ የበርገን ቅርንጫፍ ጽ/ት
ዲሴምበር 14፥2013

Thursday, December 12, 2013
በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ታሳሪዎች ላይ መንግስት የጥፋተኛነት ውሳኔ አስተላለፈ
መንግስት በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ የጥፋተኘነት ውሳኔ ማስተላለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ለታህሳስ 3 በተቀጠረው የብይን ቀነ ቀጠሮ መሰረት 10 ተከሳሾችን ነፃ ናቸው ሲል ፍርድ ቤቱ ያሰናበተ ሲሆን የተቀሩት ላይ ግን በሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ወንጀል ጥፋተኛ ናችሁ ሲል ብይን አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ሁሉም በዕድሜ የገፉት አባቶች ዶ/ር ከማል ገለቱ፣ሼህ አብዱረህማን፣ሼህ ሃጂ ኢብራሂም፣ ሼህ ጣሂር፣.ሼህ ሱልጣን አማን፣ ኡስታዝ ጀማል ያሲን ፣ኡስታዝ ሃሰን አሊ ፣ወንድም አሊ መኪ ፣ ወንድም ሀሰን አቢ እና ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ በነፃ ፍርድ ቤቱ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ተዘግቧል፡፤ በተቀሩት ላይ ደግሞ የጥፋተኘነት ክስ በማስተላለፍ ለጥር 22 የመከላከያ ምስክራቸውን እንዲያቀርቡ ውሳኔ በማስተላለፍ ችሎቱ ተጠናቋል፡፡
Tuesday, December 10, 2013
ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በአባይ ግድብ ዙሪያ እንደገና ጥናት እንዲካሄድ ተስማሙ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ እንደዘገበው ከአራቱም አገራት የተውጣጣ ኮሚቴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከተቋቋመ በሁዋላ፣ በግድቡ ላይ ጥናት የሚካሂዱ ምሁራንንና ይመርጣል። ይህ ቡድን ጥናቱን ሲያጠቃልል ለሶስቱም መንግስታት የጥናት ውጤቱን ያቀርባል።
ከዚህ ቀደም የተቋቋመው አንድ አለማቀፍ ቡድን በግድቡ ፕሮጀክት ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር። ባለፈው ወር በሚቋቋመው ኮሚቴ ላይ አለማቀፍ ተወካዮች እንዲገኙ ግብጽ ያቀረበችውን ጥያቄ ኢትዮጵአ አልተቀበለችውም ነበር። አሁን ግብጽ አቋሟን መቀየሩዋንና ኮሚቴውን በሶስቱ አገሮች ወኪሎች ለማካሄድ መስማማቷን ዘገባው አመልክቷል። የሶስቱም አገራት ወኪሎች በጥር ወር መግቢያ ላይ እንደገና ሱዳን ላይ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።

Monday, December 9, 2013
ማንዴላና የማንዴላ የማይመስሉ እዉነቶች
ባለፈዉ ዓመት ደግሞ ሳይንቲስቶች አንድ ግንደ ቆርቁር መሰል የጥንት ወፍ ዝርያ አገኙ። «ኔልሰንማንዴላ» ብለዉ ሰየሙት።ማንዴላ ጀርመናዊዉ ፖለቲከኛ እንዳሉት ታሪክን የዘወሩ ታላቅ ሰዉ ነበሩ።በዚያ ዘመን ግን ሰዉ መሆናቸዉን እንኳ ያወቁት ካንዲት የጥቁሮች ነፃ ሐገር ሲደርሱ ነበር።1962።
ማንዴላ እና ማንዴላን የማይመስሉ ማንዴላዎች።ሰዉዬዉ ሞቱ።ሐሙስ።ዕሁድ ይቀበራሉ።ሥራ ምግባራቸዉን እየጠቃቀስን፥ የማንዴላ የማይመስሉ ድርጊቶችን ባጭሩ እንቃኛለን።አብራችሁኝ ቆዩ።
ማንዴላ፥ አንዴ እንዲሕ ብለዉ ነበር አሉ።«እንዲያዉ ሁሌም የሚሞክርን ሐጢያተኛ እንደ ቅዱስ ካለሰብክ በስተቀር እኔ ቅዱስ አይደለሑም።» ይበሉ እንጂ በተለይ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ አብዛኛዉ ዓለም እንደ ከከሰዉ በላይ ሰዉ ይመለከታቸዉ ነበር።ሚሊዮኖች ሊያዩ፥ የተሳካላቸዉ ሊያነግሩ፥ ሊጨብጡ፥ ሊያቅፏቸዉ በሚመኙበት ወቅት ግን በቴሌቪዥን መስኮትም አልታይም አሉ።ግን በተቃራኒዉ እኔ እደዉልላችኋለሁ።
«የአደባባይ እንቅስቃሴዬ ከዛሬ ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።እንዳትደዉሉሉኝ። እኔ እደዉልላችኋለሁ።»
የመጨረሻቸዉ መጀመሪያ ነበር።ባንድ ወቅት ግን «ትምሕርት» አሉ «ዓለምን የምትለዉጥበት መሳሪያ ነዉ።» የሌላዉን አናዉቅም ወይም አያገባንም።እሳቸዉ ግን ያሉትን ከማለታቸዉ ከብዙ ዘመን በፊት ተማሩ።በሕዋላም ዓለምን በርግጥ ለወጡ።ዓለምን የለወጡበትን ትምሕርት በ1925 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ኤ ከማለታቸዉ በፊት ግን ወላጆቻቸዉ እንደ አፍሪቃዊ ባሕል-ወግ ያወጡላቸዉ ሥም ለአዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች እንዲመች፥ በአዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች ሲለወጥ መቀበል ግድ ነበረ ባቸዉ።

Sunday, December 8, 2013
የመለስ ጎጂ ሃሳቦችና ድርጊቶች
December 5, 2013
የኢትዮጵያ ሲቪክ ንቅናቄ
Ethiopian Civic Movement
Email: ethiocivic@gmail.com
ሕዳር 2006
Click here for PDF
የኢትዮጵያ አንድነትንና የመንግስት ስርዓቱን የሚመለከቱት የመለስ ሃሳቦችና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ከባድና አሳሳቢ ትርጉም አላቸው፡፡ የአንድነቱ ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሲሆን፣ ስርአቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ መብቶች ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያመለክታል፡፡ የአገር ህልውና እና የህዝብ መብትን ያህል ትልቅ ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ክብደቱና አሳሳቢነቱ አያጠያይቅም፡፡
መለስ አንድነትን በሚመለከተው ሃሳቡ ትግራይን ከመገንጠል ኣላማ ጀምሮ ሳይተገብረው ቢቀርም፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጓል፤ ህዝብን በቋንቋ ክልሎች ከፋፍሎ በጉራ ፈርዳና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ለተከሰቱት አማሮችን የማፈናቀል ግፍ መሰረት ጥሏል፤ የመገንጠል “ህገ መንግስታዊ” አንቀፅ አዘጋጅቷል፤ ለሱዳን መሬት አድሏል፤ ዜጎችን አፈናቅሎ ለም መሬት ለውጭ ድርጅቶች በርካሽ ለረዥም ጊዜ አከራይቷል፡፡
የመንግስት ስርዓቱ በቃላት መድብለ ፓርቲ በተግባር ያንድ ፓርቲ አፋኝ ስርዓት ነው፡ስለዚህም ስርዓቱ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ወሳኙ መለስ እንደነበረ ለ21 ዓመታት ደጋግሞ አረጋግጧል፡፡ ሰውየው በኢትዮጵያ በነበሩ መንግስታት በተለመደ መሳሪያ ማለትም የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣንን በመጠቀም፣ በኢትዮጵያ ግን ያልተለመደና በውጭ ሃይሎችም ያልተሳካ፣ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ ለመተግበር ሞክሯል፤ በከፊልም ተሳክቶለታል፡፡

Friday, December 6, 2013
ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!!
ecember 6, 2013
የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም ሲለዩ፤ የተለያዩ አገሮች እንደየራሳቸው ግንኙነት የራሳቸውን ታሪክ ሲያወሩ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሃዘናቸውን ሲገልጹ ከማንዴላ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመግለጽ ነበር። እኔ በምኖርበት አትላንታ ከተማ ዜናው ሲቀርብ፤ ኔልሰን ማንዴላ አትላንታ በመጡበት ወቅት፣ ከነአንድርው ያንግ ጋር ሆነው የማርቲን ሉተር ኪንግ ማዕከልን ስለመጎብኘታቸው ነበር – ዋናው ዜና። ሁሉም አገር ስለማንዴላ የየራሱ ትዝታ አለው። ኢትዮጵያውያንም ስለኔልሰን ማንዴላ የራሳችን ታሪክ እና ትዝታ አለን። እናም ማንዴላ የዛሬ 51 አመት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ስለነበረው ጉዳይ በማውጋት ታሪካችንን እንጀምራለን
በዳዊት ከበደ ወየሳ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ከተማ ይፍሩ በ1962 ዓ.ም አራተኛው የፓን አፍሪካ ስብሰባ በኢትዮጵያ እንዲደረግ ጃንሆይን ፍቃድ ጠየቁ። ጃንሆይ በጉዳዩ ተስማሙና በፌብሩዋሪ 1962 ዓ.ም የአፍሪካ ታዋቂ የነፃነት ታጋዮች ወደ ኢትዮጵያ መጡ። ከእነዚህም መሃከል ሚስተር ኦሊቨር ታምቦ፣ ሚስተር ሮበርት ሙጋቤ፣ ሚስተር ኬኔት ካውንዳ እና ሚስተር ኔልሰን ማንዴላ ይገኙበታል። (በኋላ ላይ እነዚህ ወጣት ታጋዮች የየአገራቸው ፕሬዘዳንት ሆነዋል) ይህ ጉዞ በተለይ ለኔልሰን ማንዴላ በህይወታቸው ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጡት ነው።

Thursday, December 5, 2013
ወያኔ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት መታሰብያ በዓል እንዳይከበር ፍቃድ ከለከለ
የሰማያዊ ፓርቲ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመትን በተለያዩ ዝግጅቶች አስቦ ለመዋል በጃንሜዳ የመሰብሰብ ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ ይሁንና መንግስት ጥያቄውን ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ውድቅ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ ልኳል።
brhanutekleyared
የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡
እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?
ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!
Wednesday, December 4, 2013
ኢህአዴግ ለግንቦት7 ያቀረበው የእንደራደር ጥያቄ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች በስልክ እየሰጡ ባለው አስተያየት ግንቦት7 ከኢህአዴግ ጋር መነጋገሩን አይደግፉም። አብዛኞቹ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ “ኢህአዴግ ተዳክሟል፣ ኢህአዴግ የሚታመን ድርጅት አይደለም” የሚሉ ናቸው። በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሰጡት አስተያየት የሚከተለውን ይመስላል
በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን የድርድሩ ዜና መልካም ወሬ መሆኑን ለኢሳት በላኩት የኢሜል መልክት አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ፓርቲዎች በሰላም ተነጋግረው ለአገራቸው ቢሰሩ መልካም መሆኑን የጠቀሱት እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ድርድሩ ከልብ የመጣና ኢህአዴግ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ ከሆነ፣ ለአገሪቱ መልካም ዜና ነው ብለዋል።
ኢህአዴግ ለግንቦት7 የድርድር ጥያቄ ማቅረቡን መዘገባችን ይታወቃል። ግንቦት 7 በተለያዩ ምክንያቶች የቀረበለትን ድርድር ሳይቀበለው ቀርቷል።
Tuesday, December 3, 2013
የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
Monday, December 2, 2013
አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ክፍል ሁለት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )
December 2, 2013
አበሻ ድግስ ይወዳል፤ ድግስ የሚወደው መብላትና ማብላት ስለሚወድ ነው፤ ለመብላት የአበሻ ምክንያቱ ብዙ ነው፤ ልጅ ተወለደ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ክርስትና ተነሣ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ አገባ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ሞተ ብሎ መብላት ነው፤ አበሻ ሰው ቀብሮ ሲመለስ በንፍሮ ይጀምርና ቀስ በቀስ ወደሌላው ይተላለፋል።
ሃይማኖትም ቢሆን ለመብላት ካልሆነ የነፍሱ ጉዳይማ በጣም ሩቅ ነው፤ ሕያዋን ለነገሥታት፣ ሙታን ለካህናት ይገብራሉ፤ በሚለው መመሪያ መሠረት
ግብር መቀበል ያለ ነው፤ ክርስቶስ ተወለደ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተጠመቀ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ሞተና ተቀበረ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተነሣ መብላት ነው፤ ማርያም አረገች መብላት ነው።
ማኅበርም የሚጠጣው (የሚበላው ለማለት ነው፤) ለመብላት ነው፤ አምላክ በተለያዩ ስሞቹ፣ ቅድስት ማርያም በተለያዩ ስሞችዋ፣ መላእክት፣ ቅዱሳን፣ ሰማዕታት ሁሉ ለመብላትና ለማብላት ያገለግላሉ፤ ወደመንግሥተ ሰማያት ለመግባት አማላጅ ሊሆኑ የሚችሉ ሁሉ ማኅበር ለመብላት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፤ የሌሎች አገሮች ክርስቲያኖች በመብል አይመለሱም፤ ገበያቸው በጠገራ ብር ነው፤ ስለዚህም አብሮ መብላት ብሎ ነገር የለም።
አበሻ የሚበላው የመጣውን ሲቀበል ብቻ አይደለም፤ የሚሄደውን ሲሰናበትም መብላት ይወዳል፤ ሞትም ቢሆን ለመብላት ምክንያት ነው፤ ቀብር ብሎ እዝን እያቀረቡ መብላት ነው፤ ሠልስት ብሎ መብላት ነው፤ ለሰባት መብላት ነው፤ ለዓርባው መብላት ነው፤ የሙት-ዓመት ደግሶ መብላት ነው፤ በቀብር ላይም ቢሆን ለቅሶውም ‹‹ሆዴ! ሆዴ!›› ነው።
ለአበሻ ጾምም ቢሆን ለመብላት ነው፤ የጾም ትልቁ ምሥጢሩ ምግብ እንዲናፍቅ ለማድረግ ነው፤ የፍስኩ የተትረፈረፈ ምግብና ጥጋብ ባይኖር ማን ይጾማል? የለየላቸው ጠጪዎች በሁዳዴ መለኪያውንና ብርጭቆውን አርግፍ አድርገው የሚተውት ሲፈሰክ በናፍቆት ዊስኪውንና ቢራውን ለመጋት ነውኮ! ይህ ባይሆን አንድ ጊዜ ሞጣ ያየሁትየበግ ሌባ ለምን ይጦም ነበር? ታሪኩ እንዲህ ነው፤ በሞጣ አውሮጵላን ማረፊያ አንድ የበግ ቆዳ የያዘ ሰውዬ በፖሊሶች ይጠበቃል፤ እንደሰማሁት በግ ሰርቆ ጫካ ይወስድና ቆዳውን ገፎ ለመሸጥ ወደገበያ ሲሄድ ተይዞ ነው፤ የሁዳዴ ጾም ስለነበረ ሥጋውን ለማይጾሙ አውሬዎች ጫካ ውስጥ ጥሎ ነው! አሁን ይህ ሰውዬ የሚጾመው ሲፈሰክ ደህና አድርጎ በናፍቆት ለመብላት ካልሆነ ለሌላ ለምንድን ነው ሊባል ነው?
ሥራም ቢሆን ለመብል ነው፤ ከመኝታው ሲነሣ ጀምሮ እስኪተኛ ቢበላ ደስታውን አይችለውም፤ለገና፣ ለፋሲካ፣ ለእንቁጣጣሽና ለመስቀል ለገናና ለፋሲካ፣ ለእንቁጣጣሽና ለመስቀልም ከሌሊት ጀምሮ ከአንዱ ቤት አንዱ ቤት እየተዘዋወሩ በመብላት ቀኑ ያልፍ የለም እንዴ! በእውነት አበሻ መብላት የሚወደውን ያህል ማብላትም ይወዳል፤ ስሞት! ስቀበር! አፈር ስገባ! … ወዘተ. እየተባባለ የጠገበውን ሰው በቁንጣን እንዲሰቃይ ማድረግ የአበሻ ልዩ የፍቅር መግለጫ ነው! መጎራረስም አለ፤ ፍቅርና ጉርሻ ሲያስጨንቅ ነው እየተባለ ፍቅርና ሆድን ያያይዛል፤ አነጋገሩ አበሻ ለመብላት ያለውን እንጂ ፍቅርን አይገልጽም፤ ማሰጨነቅንና ፍቅርን ምን አገናኛቸው! አበሻ ሌላም ተረት አለው፤ የወለዱትን ካልሳሙለትና የሠሩትን ካልበሉለት ደስ አይለውም ይባላል፤ የልጅ ፍቅር ከምግብ ፍቅር ጋር ተስተካክሎ የቀረበ ይመስላል፤ ደሞም ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል፤ ይላል፤ ጉድ ነው! ሲሞትም ተከተሉኝ የሚል ይመስላል!! ለነገሩማ ፍቅርምኮ አበሻ ዘንድ ምግብ ነው፤ ሆዴ! አንጀቴ! ጎንደሬዎች ሲያሳምሩት ደግሞ ራቴዋ! ይሉታል።
ዛሬ ዛሬ አበሻ ከማብላት ይልቅ ማጠጣት ይወዳል፤ እስቲ ሰዎች ሰብሰብ ብለው በሚጠጡበት ቦታ ብቅ በሉ፤ ያቺን የፈረደባትን ጉበት ለማቃጠል በአቦ፣ በሥላሴ የማይል የለም፤ ቸገረኝ ብሎ ገንዘብ የሚጠይቅ አይምጣ እንጂ ለማብላትና ለማጠጣት፣ ለአንድ ጥሪኝ ፈሳሽ አበሻ ቸር ነው፤ በላኤ ሰብስ በማርያም ስም አንድ ጥሪኝ ውሀ ሰጥቶ አይደለም እንዴ የበላው ሰው ሁሉ የተሰረዘለት? አበሻ በሆድ አይጨክንም።
ለአበሻ ምግብ ክቡር ነው፤ ስለዚህም ምንም ነገር ሲበላ ተቀምጦ ነው፤ ፈረንጅ ቂሉ በየመንገዱ እንደመጋዣ ያመነዥካል፤ በየመንገዱ ማመንዠክ ምግቡን ማዋረድ ነው፤ ከዚያም በላይ ቆመው ሲበሉ ወደጉልበት ይወርዳል ይላል፤ ለአበሻ ጨጉዋራና ጉልበት በቀጥታ የተገናኙ ናቸው፤ ሳይንሱ የሚለው ሌላ ቢሆንም አበሻ አበሻ ምን ቸገረው?
ለመሆኑ ከሆድ ጋር ያልተያያዘ ነገር አበሻ ምን አለው? ነገርን በሆድህ ያዘው ምን ማለት ነው? ነገርን ማብላላት የማሰብ ምትክ መሆኑ ነው፤ ልጆች ሆነን አይጥ አበላሁት እንል ነበር፤ አሸነፍሁት ለማለት ነው፤ ዛሬም ቢሆን ቁማርተኞች በላሁ-ተበላሁ ይባላሉ፤ አይጥ ከማብላት ገንዘብ ወደማብላት ተለወጠ እንጂ ከሆድ አልወጣም፤
አበሻ በሆዱ የማይዘው ምን ነገር አለ? ፍቅርም፣ ጥላቻም በሆድ ነው፤ ቂምም በሆድ ነው፤ ምኞትም ፍላጎትም በሆድ ነው፤ ተስፋም በሆድ ነው፤ መጥኔ ይስጠው የአበሻ ሆድ! ሁሉን ከተናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፤ አይ የአበሻ ሆድ! የነገር ስልቻ ከመሆኑ በላይ ነገር አልቆበት ‹‹ነገር እንዳይርበው(!)›› ጥንቃቄ ማድረግ አለበት! የአበሻ ሆድ እህል ቢያጣና ከእህል ባዶ ቢሆንም ከነገር ባዶ መሆን የለበትም፤ እህል ቢጠፋም ነገር አይጥፋ!
የአበሻና የሆድ ነገር በዚህ አያበቃም፤ አበሻ ሲያመው ቡዳ በልቶት ነው፤ ቆንጆውን ሁሉ ቡዳ ይበላዋል፤ ልብ በሉ ለአበሻ በዓይንም ይበላል ማለት ነው! አንዳንዴም ሲያመው መድኃኒቱ ምግብ ነው፤ ለሆድ ቁርጠት ብላበት፤ አበሻ ሲሞትም ለቅሶው ሁሉ ስለሆድ ነው፤ ‹‹የኔ ሆድ፣ ሆዴ እንዴት ይቻለው! ፋሲካን የት ልፈስክ?››
እስከናካቴው ‹‹ሆድ›› የሚባል ቃል ከአበሻ ቋንቋ ፈጽሞ ቢሰረዝ ቋንቋው ብቻ ሳይሆን አበሻም ጉድ ይፈላበታል፤ አእምሮ፣ ኅሊና የሚባሉትን ቃላት አበሻ አያውቃቸውም፤ ተግባራቸውንም ሁሉ ለሆድ ሰጥቶታል።

Subscribe to:
Posts (Atom)