Monday, December 29, 2014

የኢሳት 4ኛ አመት በበርገን ከተማ ኖርዌይ ተከበረ

 የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የተመሰረተበትን አራተኛ አመት በዓል ምክንያት በማድረግ ተጋባዥ የኢሳት ጋዜጠኞች ከእንግሊዝ አበበ ቶላ እና ፍስሐ ተገኝ ከአመስተርዳም ገሊላ መኮንን እንዲሁም በኖርዌይ የሚኖሩ የኢሳት ቤተሰቦች በተገኙበት “ኢሳት ይቀጥላል”  በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ ዲሴምበር 13 . 2014 በደመቀ ሁኔታ በኖርዌይ በርገን ከተማ ተከብሮ ውሏል ፡፡


             
በእለቱ የነበረውን ፕሮግራም የኢሳት በርገን ቅርጫፍ ድጋፍ ሰጭ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አሸናፊ እና ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በአማረ መልኩ መርተውታል ፡፡ ዝግጅቱን በንግግር የከፈተው የኢሳት በርገን ፀሐፊ የሆነው ወጣት ሺበሺ ጌታቸው ሲሆን ንግግሩም ያተኮረው  “ኢሳት ይቀጥላል”  ስንል ምን ማለታችን ነው በማለት ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርቧል በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት ነፃ ሚዲያ ባለመኖሩ ይህንን ክፍተት ለመሸፈን ኢሳት የኢትዮጵያን ህዝብ በመረጃ ሙሉ ከማድረግ አንፃር እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል ፡፡  ኢሳት የህዝባችን አንደበት፣አይን እና ጆሮ ስለሆነ ኢሳትን ለመርዳትና ቋሚ አባል በመሆን የዜግነት ግዴታችንን በመወጣት  በመረጃ እጦት ውስጥ ላለው ወገናችን አለኝታ እንድንሆንና የኢሳትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ  የኛ ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው አስገንዝበዋል ፡፡
               
      በቀጣይነትም  የኢሳትን ስራ የሚዘክር የኢሳት መዝሙር በአቶ ማርቆስ አብይ ተደርሶ በቶማስ  አለባቸው ዜማው ተሰርቶ በአቶ ኢሳያስ አዘጋጅነት ተዘጋጅቶ ቀርቧል ፡  የመዝሙሩ መጠሪያ “ኢሳት ይቀጥላል በፍጹም አይቆምም ” የሚል ሲሆን በህብረት ዘማሪያን ለታዳሚው ቀርቦ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል ፡፡ መዝሙሩም በሲዲ ተቀርፆ ለኢሳት ኖርዌይ በስጦታ ተበርክቷል ፡፡
       በመቀጠል ተጋባዥ የኢሳት እንግዶች ጋዜጠኛ አበበ ቶላ እና ጋዜጠኛ ፍሰሐ ተገኝ በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች እና በኢሳት ዙሪያ  አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ገጠመኞቻቸውን ለታዳሚው እያዋዙ አቅርበዋል ፡ በተጨማሪ ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን  በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ የሚያተኩር ስሜትን የሚነካ ግጥም ያቀረበች ሲሆን ታዳሚውም  በአፀፋው ለሶስቱ ጋዜጠኞች ያለውን ፍቅርና አክብሮት በጭብጨባ ገልፀውላቸዋል ፡፡

 ሌላው በእለቱ ለየት ያለ ዝግጅት የቀረበው የኢሳት የሶስቱም ስቱዲዮ ጋዜጠኞች የሚያቀርቧቸውን ዝግጅቶች የሚዘክር የፎቶ  ኤግዚብሽን  ለእይታ የቀረበ ሲሆን በእያንዳንዱ ስቱዲዮ የሚቀርቡትን ዝግጅቶች ማለትም አቶ ሚካኤል አቦዬ  የአመስተርዳም ስቱዲዮን ፣ አቶ አሰግድ ታመነ  የዋሽንግተን ስቱዲዮን እና አቶ ዳዊት ዮሐንስ የለንደን ስቱዲዮን ዝግጅቶች ለጎብኚዎቹ በስፋት አብራርተዋል ፡፡
   
ሌላው በዝግጅቱ ላይ የቀረበው “የሳኦል ፍሬዎች” የሚል በአቶ አይንሸት ገበያው ተደርሶ በገሊላ መኮንን አዘጋጅነት በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ለእይታ የሚቀርበው ፊልም የተመረቀው በዚሁ እለት ነበር ፡፡ ይህ ፊልም  በሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሲሆን በአጭሩ ለተመልካች ቀርቧል ፡፡ በተጨማሪም በኢሳት ላይ የሚያተኩር እና መሳጭ ግጥም በወጣት ዳዊት እዮብ ቀርቦ ከተመልካች አድናቆትን አትርፏል ፡፡

 በመጨረሻም የቀረበው የአትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ በኖርዌይ “በርገን ሲቲ” በሚል የሚዘጋጀውን የግማሽ ማራቶን  ውድድር  የኢሳትን ቲሸርት በመልበስ   ሮጦ ያሸነፈበትን ዋንጫ ለጫረታ አቅረቦ በተለይም በኦስሎ እና በበርገን ከተሞች የመጡ የኢሳት ቤተሰቦች ከፍተኛ የሆነ ፉክክር ያደረጉበት ሲሆን በመጨረሻም ከኦስሎ የመጣው አቶ ፋንታሁን ተሰማ  በከፍተኛ ገንዘብ ጨረታውን አሽንፎ ዋንጫውን የግሉ አድርጓል በተጨማሪም  አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ  “በበርገን ፋና ግማሽ ማራቶን” ያሸነፈበትን ዋንጫ ለኢሳት በስጦታ መልክ አበርክቷል ፡፡ በዕለቱ ከጫረታ፣ ከትኬት እና ከመስተንግዶ ከ 100000.00 / ከመቶ ሺህ ክሮነር/ በላይ መስብሰቡን በበርገን የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ባጫ ደበሌ ለተሰብሳቢው ይፋ አድርገዋል ፡፡
       
 የዝግጅቱም ፍፃሜ ለተጋባዥ ጋዜጠኞች እና ለኢሳት ቤተሰቦች  እንኳን ለ4ኛ አመት አደረሳችሁ በሚል የተዘጋጀውን ኬክ የመቁረስ ስነ ስርዓት ተካሂዶ  “ኢሳት ይቀጥላል በፍጹም አይቆምም “ በሚለው መዝሙር ታጅቦ በተሳካ እና አስደሳች በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል  ፡፡
                                                   
                                                                                             ኢሳት ይቀጥላል
                                                                                               ዳዊት እያዩ
                                                                               በኖርዌይ የኢሳት በርገን ቅርጫፍ  ድጋፍ ሰጪ  




Friday, December 12, 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና (ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ  (ከዝዋይ እስር ቤት)
መሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሰነዘረው የቦንብ ጥቃት ተሳትፈሃል በሚል ለእስር በመዳረጉነው፡፡ ይህንን ተከትሎምከምድራችን አስከፊ ማሰቃያዎች መካከል ግንባር ቀደም በሆነውና የክልሉ
ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ  እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡
ከፍርዱ በኋላም በተመ

Monday, December 1, 2014

ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተቋማት ፕሬዚዳንቶች ለአመጽ ተነሱ!

ዘረኛውና አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከላትነት ለይቶ የማያይ ስለመሆኑ በተቋማቱ ውስጥ የሚደረጉ ተግባራት ማረጋገጫዎች ናቸው። ለዚህ ተግባሩ በሰነድ ደረጃ መቅረብ ከሚችሉት የቅርብ ጊዜ ማስረጃዎች ዋነኛው በህዳር 2007 ዓ.ም. በሥራ ላይ የዋለው “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል” የተሰኘው በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላለፈው ሰነድ ነው። ይህ ሰነድ፣ የህወሓት አሳፋሪ የትምህርት ፓሊሲ ባፈጠጠ መልኩ የተገለፀበት፤ የኢፌዴሪ መንግሥት ተብሎ በሚጠራው የህወሓት አገዛዝ ተቋም እና በህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲ መካከል ለይምሰል እንኳን ልዩነት አለመኖሩ በግላጭ የሚታይበት ሰነድ በመሆኑ በዚህ ርዕሰ አንቀሳችን በስፋት ልንዳስሰው ወስነናል።

ሰነዱ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ መርዙን መርጨት የሚጀምረው ገና በመግቢያው ስለማንዋሉ አስፈላጊነት ሲገልጽ ነው። ማንዋሉ “ከምንም በላይ የብጥብጥና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢህአዴግ አመራር አባላት እየታገዙ ለመያዝ የሚያስችል ነው” በማለት ህወሓት ተማሪውን የሚመለከተው “ከምንም በላይ በብጥብጥ መንስኤነት” መሆኑ፤ ለዚህ መድሀኒቱ ደግሞ ተማሪውን በኢህአዴግ አመራር አባላት “መያዝ” መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ይገልፃል። ቀጥሎም “በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም በማደራጀት መረጃ ለመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል” በማለት መረጃ መጥለፍ የዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ሚኒስቴር ሥራ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል።

Wednesday, November 19, 2014

ህወሓትን በማስወገድ አገራችንን እና ህዝባችንን ከውርደትና ባርነት እንታደግ!!

በዳዊት ዮሃንስ

ላለፉት 24 አመታት በሕወሓት አምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ ስር የወደቀችው አገራችን ኢትዮጵያ ስላለችበት ጭንቅ እና መከራ፤ ህዝባችን ስለሚኖርበት የምድር ሲኦል ብዙ ብዙ ተብሏል። የሕወሓት መሪዎችና የቡድኑ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት አቋም፤ በአገር እና በወገን ላይ የፈፀሙትን በደልና ግፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ ያውቀዋል ብየ በፅኑ አምናለሁ። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚፈልገውንና የሚመኘው ነገር ቢኖር በአገራችን ላይ ሰላም ሰፍኖ፣ የህዝብ መብት ተጠብቆ፣ የዜጎች አንድነትና የአገር ህልውና ተከብሮ፣ በአለም እያዋረደን ካለው የድህነት ችግራችን ተገላግለን ማየት እንደሆነ እሙን ነው።

ይሁን እንጂ በዚህ አስከፊ ክፉ ዘመን፤ ከረሃቡም፣ ከችግሩም፣ ከግድያውና ከእስራቱ በላይ፣ የኢትዮጵያችን ህልውና፣ የአገዛዙን ስልጣን በያዙ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ምክንያት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡ በተጨማሪም በሕወሃት መሪዎች እብሪትና ማናለብኝነት የጠፋው የህዝብ ህይወት፣ የተዘረፈው የአገር ሃብት፣ የባከነው እውቀት እና ጉልበት በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ይታወቃል።  

በነገራችን ላይ ባለፉት 24 የጨለማ አመታት በአገራችን ለደረሰው ውርደትና ጥፋት የሕወሓት ቡድን የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ እንጂ የተቃዋሚ የፖለቲካ ሰዎች ነን የምንል ሁሉ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ ለተፈፀመው ጥፋት ተገቢ የሆነውን የየራሳችንን የጥፋት ድርሻ መቀበል ይኖርብናል፡፡ ህዝብም ቢሆን በተለይ አቅሙና ችሎታው የነበረው ሁሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን መረን በመልቀቅ እና መሪዎችን በማቅበጥ ለደረሰው ጥፋት እራሱ ሃላፉነት መቀበል የሚገባው መሆኑን ሳልጠቁም ማለፍ አልፈልግም። በስልጣን ላይ ያለው አስከፊው የሕወሓት አገዛዝ የሚያዋርደን እኛ እስከፈቀድንለት ድረስ እንደሆነ ሁሉ ፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችም በህዝብ ላይ መቀለድ የሚችሉት ህዝብ እስከፈቀደላቸው ድረስ መሆኑን ልናውቀው ይገባል። የፖለቲካ ድርጅቶች የህዝብን አደራ እንዳይበሉ፣ የህዝብ ቅስም እንዳይሰብሩ፤ በማን አለብኝነት ያሻቸውን እንዳይፈፅሙም ምን ያህሎቻችን ነን ከዳር ቆመን ከማውራት አልፈን በውስጣቸው ገብተን ልንቆጣጠራቸው፤ በህዝብ ስሜት መቀለድ አትችሉም ብለን የሞገትናቸው?
 
ስንቶቻችን ነን ሁሉንም የፖለቲካ ሰዎች በድፍን ከማማትና አይረቡም ከማት አልፈን ከግብዝነት እና ከአድር ባይነት በላይ ተሻግረን  አጥፊዎቹን ፊት ለፊት መናገር ድፍረቱን የተላበስን? ስንቶቻችን ነን ሊደገፉ የማይገባቸውን ድርጅቶችና የፖለቲካ መሪዎች አገራዊና ህዝባዊ ከሆነ ጉዳይ ምክንያት ውጭ በጭፍን በመደገፍ የጥፋት ስራ የሚሰሩበት እድሜያቸውን እየቀጠልንላቸው ያለነው? ለዚህ ደግሞ እያመንን ተከዳን ብቻ እያልን ማማረር ሳይሆን ሁሉም ይህንን የእምነት ክህደት አዙሪት ለመስበር ምን ሰርቻለሁ የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው፡፡

ስለዚህ አሁን ሁላችንም የህወሃትን የጥላቻና ንቀት ፖለቲካ በመስበር፤ ለአገዛዙ የአንድ ቀን የስልጣን እድሜ መስጠት የኢትዮጵያውያን ውርደት ማስቀጠል መሆኑን በማወቅ ለራሱ ክብር የሚሰጥ እና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራው ዜጋ ሁለ በያለበት ኢትዮጵያችንን ከጥፋት ቡድኖች ለመታደግ ሊንሳ ይገባል። ህወሃት የሃገራችንን ውበቷን፣ ክብሯን እና ግርማዋን ከማንም በላይ አዋርዷዋል፡፡ የዜጎቿም መታወቂያ እስር እና ስደት ሆኗል። ደምና አጥንት ቆጥሮ ተደራጅቶ ደምና አጥንት እየቆጠረ ዜጎችን የሚያዋርድ እና የሚያሰቃይ ዘረኛ ቡድን በኢትዮጵያችን ራስ ላይ ተቀምጦ እያየን እስከ መቼ ዝም ብለን በባርነት እንገዛለን። የስልጣን ህልውናውን ለማርዘም እንዲረዳው አስጠያፊ ዘረኝነትንና ጎሰኝነትን በኢትጵያ ላይ የዘረጋውን የህወሃት ዘረኛና ጠባብ ቡድን ከአገራችንና ከህዝባችን ጫንቃ ለማውረድ በያለንበት ተደራጅተን ልንፋለመውይገባል። ኢትዮጵያ የእኔም ሃገር ነች ማለት መጀመር አለብን፡፡ በዘረኝነት በሽታ የናወዙት የህወሃት ሹማምንት አገሪቷን እንደፈለጉ ሲያደርጓት ዕያዩ ዝም ማለት አገር እና ክብርን ከማሳጣት በተጨማሪ ለጥፋቱ ተባባሪ በመሆን ከመጠየቅ አያድንም።

ዛሬ ኢትዮጵያችን ከጥፋት የሚታደጓት ከደም እና ከአጥንት ልቆ ማሰብ የሚችሉ ዜጎቿን ከምንጊዜውም በላይ ትፈልጋለች። አሁንም አገራችን ለፍትህ፣ ለእኩልነት እና ነፃነት ዘብ መቆም የሚችሉ ዜጎቿን አድኑኝ ስትል ትጣራለች። ለሚመጣው ትውልድ ጥቂቶች ብዙሃኑን ተጭነው፤ ብዙሃንም ጥቂቶችን ተሸክመው መከራቸው በዝቶ የሚኖሩበት አገር ትተንላቸው እናልፍ ዘንድ ፈጽሞ አይገባም። በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑና የዘረኛው ቡድን ግፍና በደል ያንገፈገፋቸውና እያንገፈገፋቸው ያሉ የሰራዊቱ አባላት ከታሪክ ተወቃሽነት ለመዳንና የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መነሳትና አገር አድኑን የነፃነት ትግል መቀላቀል ያለባቸው ጊዜም ዛሬ ነው። በተጨማሪም ጥቂት ዘረኞችና ዘራፉዎች አገሪቷን እንደፈለጉ ሲቀራመቱ እያየን እኔ ምን አገባኝ የሚባልበት ጊዜ ላይ እንዳልሆንን ሁሉም ዜጋ ሊገነዘብ ይገባል።

ስለዚህም ከአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ ከእምነት ማካሄጃ ስፍራዎች እስከ የአገዛዙ መስሪያ ቤቶች፤ ከአርሶ አደሩ መንደር እስከ ምሁራኑ ሰፈር፤ ከአገር ቤት እስከ ውጭ ሃገረት ያለው ዜጋ ሁሉ የሕወሓት አገዛዝን በማስወገድ አገሩንና ህዝቡን ከጥፋት ለመታደግ በያለበት የነፃነት ትግሉን ልንቀላቀል ይገባል ስል ወገናዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።

ድል የህዝብ ነው!



Friday, October 31, 2014

ህወሃትና የጦር አበጋዞቹ እሴቶች

ህወሃት የትግሬ ተወካይ ብቻ ሳልሆን ለትግራይ ህዝብ የሚያመልከውን አምላክም ጭምር የምመርጥለት እኔ ነኝ በሚል እብሪት ውስጥ ይገኛል። በዚህ እብሪቱም እየተመራ የምታመልኩትን ልመርጥላችሁ ብሎ አጠቃላይ ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም እያመሰው እንደሆነ እያየን ነው። እኔን የማይቀበል እጣ ፈንታው ከመታመስ በላይ የሆነ ወዮታ ነው የሚል ያልተፃፈ አዋጅም አለው። ህወሃት በትግራይ ትከሻ ላይ ተፈናጦ፤ ትግራይን ምርጫ አሳጥቶ እኔን እምኑ መንገዳችሁም ህይወታችሁም እኔ ብቻ ነኝ ብሎ ራሱን የትግራይ ጣዖት አድርጎ ሹሟል። ይሄን ጣዖት አንቀበልም፤ እኛ የራሳችን ሂሊና ያለን እንደ ሰው ማሰብ የምንችል ነን ያሉ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ባልታወጀው አዋጅ መሠረት አብዮታዊ ፀሎት እየተፀለየላቸው አፈር ለብሰው ቀርተዋል።የህወሃት የእብሪቱ መጀመሪያ “እኔ ያልኩት ካልሆነ ሁሉም ገደል ይግባ” ማለቱ ነው። የትግራይ ተወካይ እኔ ብቻ ነኝ ሌላው ሁሉ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው የሚል እምነቱ የድርጅቱን ሥር የሰደደ መሠሪነትና እብሪት የሚያሳይ ነው።

ብዙ ኢትዮጵያዊያን ህወሃት የቆመው ለትግራይ ህዝብ ነው የሚል ዕምነት አሳድረዋል። ይሄን አስተሳሰብ መቀበል የሚጠቅመው ለህወሃት ብቻ ነው።ህወሃት ለትግራይ ህዝብ ክብርም ፍቅርም ያለው ቡድን አይደለም። ለትግራይ ህዝብ በጎ ምኞት እና ክብር ያለው ቢሆን ኑሮ የትግራይ ህዝብ የወደደውን እንዲመርጥ፤ ያልወደደውን እንዲተው ያልተሸራረፈ ነፃነት እንዲኖረው ያደርግ ነበር። እኛ እንደምናየው ግን የትግራይ ህዝብ የወደደውን ለመምረጥ፤የጠላውን ለመተው እንዲችል ነፃነትያለው ህዝብ አይደለም። የትግራይ ህዝብ ነፃነቱን በነፃነት ሥም ያጣ ህዝብ ሁኗል። ህወሃቶች የትግራይን ህዝብ ነፃነት ሸራርፈው ሸራርፈው ህዝቡን በሙሉ መያዣ አድርገውና ከወገኑ ለይተውት እየገዙት ይገኛሉ። የትግራይም ህዝብ ሳይወድ በግዱ ህወሃቶችን ተሸክሞ መከራው በዝቶ እየተገዛ ይገኛል።

Wednesday, October 22, 2014

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን የደኅንነት ማኔጅመንት ፈንድ አቋረጠ

በእንግሊዝ መንግሥት ገንዘብ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረው የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም ተቋረጠ:ሪፕሪቭ የተባለ ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጥ የእንግሊዝ ኩባንያና ሌሎች የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች፣ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት ይህንን ፕሮግራም እንዲያቋርጥ ግፊት ሲያደርጉ ነበር::
እነዚህ ወገኖች ይህንን ግፊት የጀመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ምክንያት ዜጐችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ያፈናቅላል በሚል ክስ ነበር:: ይሁን እንጂ የግንቦት ሰባት ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመንና
በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመን በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመንሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለው ወዲያውኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ከተላለፉ በኋላ፣ በእንግሊዝ መንግሥት ላይ ጫናው እንዲጠናከር ሲጥሩ ነበር::
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይልም ሆነ በተገኘው አማራጭ ለመለወጥ የሚታገለው የግንቦት ሰባት አመራር ይሁኑ እንጂ፣ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑ ተጨማሪ ግፊት ይፈጥራል ብለውም ነበር::
እሳቸው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በእንግሊዝ መንግሥት ላይም ሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ግፊት ከሚያደርጉት መካከል፣ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም የሆነው ሪፕሪቭና የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ይገኙበታል::
የሪፕሪቭ የሕግ ዳይሬክተር ቲኔክ ሀሪስ በነሐሴ ወር ለእንግሊዝ መንግሥት ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጀስቲገን ግሪንግ በጻፉት ደብዳቤ፣ ‹‹የእንግሊዝ ዜግነት ያለውን ግለሰብ ላገተውና ቶርቸር በማድረግ ለሚጠረጠረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊዎች ይህንን ፕሮግራም መስጠት ተገቢ ነው ወይ? ተገቢ ነው ብለው ካላመኑ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስካልተፈቱ ድረስ ምን ዕርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ቢያሳውቁን?›› በማለት ጥያቄ አቅርበው ነበር::
የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው ጉባዔው በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር ላይ የእንግሊዝ መንግሥት ምንም ዓይነት ጫና አለማሳደሩን በመውቀስ አስፈላጊ ነው የተባለ ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ የሁለት ወራት ጊዜ ቀጠሮ ወስዶ መበታተኑን መዘገባችን ይታወሳል::
ይህ ጫና ባለበት በአሁኑ ወቅት የእንግሊዝ መንግሥት ዲፓርትመንት ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት (ዲኤፍአይዲ) ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረውን የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም አቋርጧል::
ፕሮግራሙ የተመረጡ የኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች በእንግሊዝ አገር በደኅንነት ማኔጅመንት የማስትሬት ዲግሪያቸውን እንዲሠሩ የሚያግዝ ነበር::
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ወደ 70 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን፣ ለመጀመሪያው ዙር ፕሮግራም ሁለት ሚሊዮን ፓውንድ ያስፈልግ ነበር::
ለዚህ ዓመት ተይዞ የነበረው የሁለት ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ለአጠቃላይ ፕሮግራሙ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ::
የዲኤፍአይዲ የኢትዮጵያ ቢሮ ጉዳዩን በተመለከተ ከሪፖርተር በኢሜይል ለቀረበለት ጥያቄ ፕሮግራሙ መቋረጡን አረጋግጧል:: ነገር ግን ምክንያቱ ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስታውቋል::
‹‹ፕሮግራሙ የተቋረጠው የእንግሊዝ መንግሥት ለፕሮግራሙ የሚያወጣውና የሚያገኘው ምላሽ (ኢንቨስትመንት ሪተርን) የሚጣጣሙ ባለመሆናቸው ነው፤›› በማለት በደፈናው መልሷል::

Sunday, October 19, 2014

“እኔ ብቻ” ቢያክሙት የማይሽር የወያኔ በሽታ

ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና ዕብሪት የወያኔ አዲሰ ባህሪያት ሳይሆኑ አስራ ሰባት አመት ጫካ ዉስጥ በቆየባቸዉ አመታትና ዛሬም ከጫካ ወጥቶ አገር እየመራ በቆየባቸዉ ሃያ ሦስት አመታት አብረዉት የኖሩ መታወቂያ ካርዶቹ ናቸዉ። ዘረኝነት፤ አማራ ጥላቻና የትግራይ ሪፓብሊክ ህልም ዋና ዋናዎቹን የወያኔ መሪዎች ደደቢት በረሃ ከገቡ በኋላ በድንገት የለከፋቸዉ በሽታ ሳይሆን ከና ከልጅነታቸዉ ተጠናዉቷቸዉ አብሯቸዉ ያደገ በሽታ ነዉ። ወያኔ ጨካኝ ነዉ፤ ወያኔ ዉሸታም ነዉ፤ወያኔ ከሃዲ ነዉ፤ ወያኔ ለኢትዮጵያ ዳርድንበርና የግዛት አንድነት ደንታ የሌለዉ ባዕድ አካል ነዉ። እነዚህ ሁሉ የወያኔን ማንነትና ምንነት በትክክል የሚገልጹ የወያኔ በሽታዎች ናቸዉ። በዛሬዉ ቆይታችን በልዩ መነጽር አብረን የምንመለከተዉ የወያኔ በሽታ ግን በአይነቱ ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት በሽታዎቸ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም በጠባይና በአገላለጽ ግን ለየት ያለ ነዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለአመታት እንዳየዉም ሆነ ሀወሓትን መስረተዉ ለስልጣን ያበቁትና ህወሓት ለእነሱም አልበጅ ብሏቸዉ ጥለዉት የወጡት ግለሰቦች በቃልም በጽሁፍም እንደነገሩን ወያኔ የጫካ ዉስጥ ጠባዩን ዛሬም ያልለቀቀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዛሬማ ጭራሽ ብሶበት ያየዉን ነገር ሁሉ ነጥቆ የራሱ ካላደረገዉ ወይም ሙሉ ለሙሉ ካልተቆጣጠረዉ አርፎ የማይተኛ ድርጅት ሆኗል። ብዙዎቻችን የወያኔ ስም በተነሳ ቁጥር ትዝ የሚለን ዘረኝነቱ ነዉ። በእርግጥም ወያኔ ግለሰብንና ግለሰቦችን ወይም የተለያዩ ቡድኖችን በዘር መነጽር ብቻ የሚመለከት ዘረኛ ድርጅት ነዉ። ሆኖም ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት ለመደምሰስ የሚደረገዉ ትግል የወያኔን ዘረኛ ገጽታ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የወያኔ ገጽታዎች ማጋለጥና መዋጋት አስፈላጊ ነዉ። ለምሳሌ ወያኔ በፕሮፓጋንዳዉ ይዋጋናል፤ በዲፕሎማሲ ዘርፍ ይዋጋናል፤ በማህበራዊ ሜዲያዉ ዘርፍ ለተሳዳቢዎች ገንዘብ እየከፈለ ይዋጋናል፤ ከዚህ በተጨማሪ በቁጥጥሩ ስር ባደረጋቸዉ ፍርድ ቤቶች፤ ፖሊስ፤ መከላከያና የደህንነት ተቋሞች አማካይነትም ይዋጋናል። አዎ ! ወያኔ በቁጥጥሩ ስር ባደረጋቸዉ ተቋሞች አማካይነት እንቅልፉን ትቶ ቀንና ማታ ይዋጋናል። ዉድ አድማጮቻችን እቺን ወያኔ በቁጥጥሩ ስር ባደረጋቸዉ ተቋሞች አማካይነት ይዋጋናል የምትለዋን አባባል ጠበቅ ያደረግነዉ አለምክንያት አይደለም። ዛሬ ብዙ የምናወራዉ ስለዚሁ “ሁሉን ነገር መቆጣጠር” ስለሚለዉ የወያኔ አባዜ ነዉ።

በወያኔ የበላይነት የተጻፈዉ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት – የኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረሰቦች፤ ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸዉ ይላል። ሆኖም የዚህ ሉዓላዊነት መገለጫ በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ 38 መቀመጫዎች ብቻ ያለዉ ህወሓት 509 መቀመጫዎች ያላቸዉን ከትግራይ ዉጭ ያሉትን ሌሎቹን የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የፖለቲካ ህይወት ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራል። የሚገርመዉ ወያኔ የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያን ህዝብ የፖለቲካ ህይወት ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን የኤኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎችም ሙሉ በሙሉ በወያኔ ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸዉ። በአጠቃላይ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ በዬትኛዉም ዘርፍ ከላይ እስከታች እሱ የማይቆጣጠረዉ ምንም ነገር እንዲኖር አይፈለግም። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ዉሰጥ በወያኔና በሁለቱ ግዙፍ የአገራችን ሐይማኖቶች መካከል ለአመታት የዘለቀዉ ንትርክ፤ አተካሮና ፍጥጫም የዚሁ የወያኔ ሁሉንም ነገር እኔ ብቻ ካልተቆጣጠርኩት የሚል ክፉ አባዜ ዉጤት ነዉ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይበት ወቅት አሁን ነው!

ዘረኛውና ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት በመከፋፈል ሹመቱና ጥቅማ ጥቅሙን ለራሱ ወገን፣ ችግሩንና መከራዉን ግን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ያደለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሳይማሩና ሳይሰለጥኑ የጄኔራልነት ማዕረጎችን በሙሉ ሰብስበው የወሰዱት የህወሓት አባላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው።

በወያኔ መዳፍ ውስጥ እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ በዘርም ይሁን በፓለቲካ አመለካከት ከህወሓት የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ቢማሩም ቢሰለጥኑም ለከፍተኛ አመራርነት እንደማይበቁ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያየነው ነው። አገዛዙ ቅራኔ ውስጥ በገባባቸው ቦታ ሁሉ እየዘመቱ ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ግን በመካከለኛና ዝቅተኛ ማዕረጎች ያሉ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖችና ብዙሃኑ የሠራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮችናቸው። ብዙሃኑ የሠራዊት ክፍል አለቆቹን ከመጠበቅ ባለፈ ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመናገር እንኳን የማይፈቀድለት ሎሌ ተደርጓል።

ለኢትዮጵያዊ ወታደር ለህወሓት ሎሌ ከመሆን በላይ የሞት ሞት የለም። ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱ አባላት በጥቂት የወያኔ ሹማምንት የሚረገጥ መሆኑ የሠራዊቱን አባላት የግል ስብዕና ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሠራዊቱን ክብር ይነካል። የሠራዊታችን የህወሓት አገልጋይ መሆን የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ያዋርዳል። ይህ ዉርደት በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም።

ከእንግዲህ ጄኔራሎችና ሌሎችም የበላይ አዛዦች ሁሉ የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሆኑበት ሠራዊት ውስጥ ተስማምቶ መኖር መቀጠል እያንዳንዱን የመከላከያ ሠራዊት አባል ሊያሰፍር ይገባል። የህወሓት ጄኔራሎች ጮማ በውስኪ ሲያወራርዱ፤ በህንፃዎች ግንባታ፣ በባንኮች ንግድ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ቢዝነሳቸውን ሲያጧጥፉ፣ ምስኪኖቹ የሠራዊቱ አባላት በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወገኖቻቸውን የሚፈጁበት ሥርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ብዙሃኑ አባላት ቤተሰቦቻቸው በችጋር እየተቆሉ የአዛዦቻቸው ሀብት ጠባቂ መሆናቸው ማክተም አለበት።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የጭለማ ዘመን ታሪክ እያበቃ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው። መሣሪያዎቻቸውን እንደያዙ የነፃነት ኃይሎችን የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨረመ መጥቷል። ሠራዊቱ ከሕዝብ ጎን እንደሚቆም ውስጥ ውስጡን የሚላኩ መልዕክቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ አበረታች ዜና ነው፤ ግን በቂ አይደለም። ወያኔን ከውስጥም ከውጭም የምናጣድፍበት ጊዜው አሁን ነው። የነፃነት ኃይሎችን መቀላቀያ ጊዜ አሁን ነው፤ በሠራዊቱ ውስጥም በህቡዕ መደራጃ ጊዜ አሁን ነው። ይህን ጊዜ መጠቀም ብልህነት ነው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ጥቂት የህወሓት ጥጋበኞች በብዙሃኑ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት በደል ማብቃት አለበት ይላል። ግንቦት 7፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሙስና የደለቡት፣ ትዕቢተኛና ጨካኝ መሪዎቻቸው ፍጹም ኢትዮጵያዊ ባህርይ የሌላቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች እንደሆኑ በመረዳት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ክንዱን እንዲያነሳባቸው ጥሪ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕዝብም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አንድ ወጥ እንዳልሆነ እና በመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ መኮንኖችና አብዛኞዎቹ ወታደሮች የሕዝብ ወገን መሆናቸውን እንዲገነዘብ ያሳስባል። “አብረን ነው ዘረኛውና ፋሽስቱን ወያኔን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ አውርደን የምንጥለው” ስንል አብዛኛው የመከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊ ወገናችን እንደሆነ እና በወደፊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥም ጉልህ ሚና እንዲጫወት የምንፈልግ መሆኑን ግልጽ ማድረግ እንሻለን። የመከላከያ ሠራዊቱም የሕዝብ ወገንተኝነቱ በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ እናደርጋለን። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ አካል ነው፤ የሕዝብ ወገናዊነቱ በተግባር የሚያሳይበት ትክክለኛ ጊዜ ደግሞ አሁን ነው እንላለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!



Saturday, October 11, 2014

ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም (በኤፍሬም ማዴቦ)

ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ ለመሳ ለሁለት የተከፈለች ትመስላለች። እግዝአብሄር ይመሰገን እዉነቱ ግን ከዚህ እጅግ በጣም የተለየ ነዉ። ርዕሴን የጀመርኩት አሜን ብዬ ነዉና እስኪ አንባቢዉ አንተም አሜን በል። ባንዳነትና ከሃዲነት ኃብታምና በእድገት ወደፊት የገፉ አገሮችን እየዘለለ ደሃና ኋላ ቀር አገሮችን ብቻ የሚጠናወት ተራ በሽታ አይደለም። ብዙዎቻችን አምባገነን መሪዎቻችንን ሸሽተን የተጠለልንባት አገር አሜሪካ እነ ሄንሪ ቤስትንና ጆን ብራዉንን የመሳሰሉ ከሃዲዎችን እንዳበቀለች ሁሉ ኢትዮጵያችንም ትናንት እነ ኃ/ሥላሤ ጉግሳን ዛሬ ደግሞ የኃ/ሥላሤ ጉግሳ የልጅ ልጆች የሆኑትን እነ መለስ ዜናዊን፤ አባይ ፀሐዬንና ሰብሃት ነጋን የመሳሰሉ የለየላቸዉ ከሀዲዎችን አፍርታለች። በነገራችን ላይ ሙስሊሙ በዱአዉ፤ ክርስቲያኑ በፀሎት፤ ጠቢብ በጥበቡ ፤ፀሐፊ በምናቡ የባንዳዉንና የከሃዲዉን ብዛት ለመቀነስ ካልተባበሩ በቀር “ወላድ በድባብ ትሂድ” ብለን ባንመርቃቸዉም የባንዳ አባትና አናት አስካሉ ድረስ ባንዳም መወለዱ አይቀርም።

ጋጠ ወጡ ማን ነው?

የህወሃት ጉጅሌና ሎሌዎቹ መቼም ራሳቸውን የሚያይ አይንም መስታዎትም ያላቸው አይመስሉም። ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው የዘሩ የማይመስሉት ለዚህ ሳይሆን ይቀራል። ምናልባትም ብልግና፣ ጭካኔ፣ ግፍ፣ አውሪያዊ ስብእና፣ ወገን ካለህግ መግደልና ማዋረድ፣ የህዝብ ሃብት በጠራራ ጸሃይ መዝረፍ ለእነሱ የተፈቀደና የተሰጠ ጸጋ አድርገው ሳይቆጥሩት ይቀራሉ?

ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰለጠነና የዳበረ ስርዓት አከባበር በሰፈነበት ከተማ ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ በመዋላቸው ለደረሰባቸው ትዝብት የነውረኝነት ሀፍረት እንደማፈር ሰላማዊዎቹንና በሰላማዊ መንገድ እስከ ሲቪላዊ አልታዘዝም ባይነት መብት ያላቸውን ጠንቅቀው አወቀው የተንቀሳቀሱትን ዜጎች ጋጠ ወጥና ባለጌዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ትንሽ ሲቀዠብርባቸው ደግሞ ኦባማ ስላነጋገረን የቀኑ ተቃዋሚዎች፣ ይህ አልበቃ ሲል ደግሞ የሻእቢያ ተላላኪዎች ሲሉም ተደምጠዋል። ከአውሬነት ብዙ ያልተለዩት ደጋፊዎቻቸው ተኩሱን ሲያንጣጣ የነበረው የቀድሞ የስዩም መስፍን የግል አሽከርና ሹፌር የነበረው ወዲ ወይኒ ግደይ ስለተባረረ ንዴታቸውን ከአደባባይ እንኳን መደበቅ አልቻሉም። እናስ እዚህ ውስጥ ጋጠወጡ ማነው? ሀገሩን የሚያስተዳድርበትን አራዊታዊና ህግ አልባ ስርአት በሰለጠነ ህዝብ ሀገር በአደባባይ ለኤግዚብሽን የሚያቀርብ መደዴ ወይስ እስከ ሲቪል እምቢተኝነት ድረስ ሊደርስ የሚችል መብታቸውን ጥንቅቀው የሚያውቁና በግፍ ስርአት ለሚኖረው ወገናቸው ድምጽ ያሰሙ የህዝብ ልጆች?

በዘሩ ታማኝነት ተመርጦ ከስዩም መስፍን ሾፌርነት ውጪ ቅንጣት የዲፕሎማሲ እውቀት የሌለውን ደንቆሮ የዲፕሎማት ማእረግና ሽጉጥ አስታጥቆ ዋሽንግተን ከሚልክ መንግስት በላይ ጋጠወጥና አጉራ ዘለል ከየት ይገኛል።

እውነቱ ግን ወዲህ ነው ያለው። ቢያንስ በነጻው አለምየሚኖሩ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራቸውና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ስቃይ ውርደትና ግፍ ተንገፍግፈዋል። የወያኔ ሹማምንት ግፋቸውን እንዲያቆሙ ያሰሩዋቸውን እንዲፈቱና ሀገር ዝርፊያ እስኪያቆሙ ድረስ በገቡበት እየገባ ቁም ስቅላቸውን ማሳየትና ጋጠወጥና የነውረኛ ስርአት አገልጋዮች መሆናቸውን ማጋለጡን ይገፉበታል። በሰሩት ወንጀል አለምአቀፍ ፍርድቤቶች መድረክ ላይ እየጎተተ የሚያቀርብበት ጊዜም ሩቅ አይደለም።

የወጋ ይርሳ እንደሆነ እንጂ የተወጋ አይረሳም። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሰላማዊ ተቃዋሚውን ድርጅት አባል በብረት ሶዶማዊ ምግባር የፈጸሙትን ጋጠ ወጥ የወያኔ ተላላኪዎች ማን ይረሳል። በየቤቱና በየጎዳናው በዱላ የሚቀጠቀጡትና ደማቸውን ሲጎርፍ ያየናቸው አዛውንት ሙስሊም ወገኖቻችን ደም እንዴት እንረሳለን። ሬሳቸው እንኳን ክብር አጥቶ የጋጠወጥ ወያኔ መጫወቻ የሆኑትን የኦጋዴን ወገኖቻችንን ማን ይረሳል። ጋምቤላ ጫካ ውስጥ እንደደኑ ተጨፍጭፈው የተቆለሉትን አኙዋኮች ማን ይረሳል። ከየኖሩበት ቦታ በግፍ እየተፈናቀሉ የሚንከራተቱትን እና የሚሞቱትን አማሮች ማን ይረሳል። በቆራጥነት ብቻ በሰላም መንገድ እንታገላለን ብለው በተነሱ ወህኒ የተወረወሩትን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የታሰሩትንና የተሰደዱትን ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች የምንረሳቸው ስንሞት ብቻ ነው። ከየጎረቤት ሀገሩ እየታፈኑ የሚሰቃዩትን እነ አንዳርጋቸውን እና ሌሎች የሞቱትን ማን ይረሳል።

ህዝባችንን ወደ ሰላማዊ አመጽም ሆነ ወታደራዊ አመጽ እየገፋው ያለው ይህ የወያኔ ባህሪ ነው።

ግንቦት 7 ከዚህ አራዊታዊ ስርአት ጋር ሆናችሁ በተለያየ ምክንያት በህዝባችሁ ስቃይ ላይ የምትተባበሩ ወገኖች ሁሉ በአገኛችሁት አጋጣሚ ከእዚህ እኩይ ስርአት ተግባራት ራሳችሁን እንድታወጡ፣ ከቻላችሁ በውስጥም ሆናችሁ ወገናችሁን ሳትበድሉ ትግሉን እንድትቀላቀሉ ይመክራል።

መላው ህዝባችን በያለህበት ራስህን በራስህ እያደራጀህ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎችን ጀምር። በመላው አለም ዙሪያ ተሰደህ የምትኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለወገንህ ለራስህም ትንሳኤ ተነስ!!

ትግላችን የመጨረሻውን መጀመሪያ እየተያያዘ ነው። የትልቅ ሀገርና ትልቅ ህዝብ ባለቤቶች ስለሆንን ከወያኔ ወሮበላ ጉጅሌ በበለጠ የሚገባን ህዝብ ነን!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Monday, September 29, 2014

ህወሃቶች “አቅም ግንባታ” የሚሉት፤ እኛ ደግሞ “አቅም አድክም” የምንለው ሂደት

ህወሃት የመምህራንን፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችንና የመንግስት ሠራተኞችን ”አቅም እገነባለው” ብሎ ተነስቷል። ለዚህ “አቅም ግንባታ” እያሉ ለሚጠሩት አሰለቺ እና አደንቋሪ አቅም አድክም ፕሮፖጋንዳ እየወጣ ያለው ወጪ ለሌላ ተግባር ውሎ ቢሆን ኑሮ የተሻለ ይሆን ነበር። የተሻለ ነገር በህወሃቶች መንደር ይሠራል ብሎ መጠበቅ ግን ሞኝነት ነው። ህወሃት የተፈጠረው አገርን ለማፍረሰና ህዝብን ለማስጨነቅ እንጂ የተሻለ ሥራ ሠርቶ ህዝብን ለማስደስት አይደለም።

ህወሃቶች በአፍቅሮተ ንዋይ አብደው አቅላቸውን የሳቱ፤ ለእውቀትና ከእነርሱ በተሻለ ደረጃ ለሚያውቅ ቅንጣትም ታክል ክብር የሌላቸው፤ ውሸት የመኖሪያቸው ድንኳን ሁኖ ለብዙ ዘመን ያኖራቸው ቡድኖች ናቸው። በዚህ ሁኔታ ራሳቸውን የገነቡ ቡድኖች የሌሎችን አቅም እንገነባለን ብለው የመነሳታቸው ነገር አገራችን የገባችበትን የውርደት አዘቀት ፍንትው አድርጎ የሚያሳየን ነው።

የንዋይ ፍቅር የክፋቶች ሁሉ መሠረት ነው። ህወሃቶች በዚህ በክፋት ሁሉ መሠረት በሆነው በንዋይ ፍቅር ያበዱ በመሆናቸው ህወሃቶችን ከክፋት፤ ክፋትን ደግሞ ከህወሃት ለይቶ ለማየት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። እነዚህ ቡድኖች በአፍቅሮተ ነዋይ አብደው ለእብደታቸውም መድሃኒት ጠፍቶ እኛ ከሌለን አገሪቷን እንበትናታለን በሚል ቅዥት ውስጥ እንደሚኖሩም የታወቀ ነው። ህወሃቶች ገንዘብ ሊያሰገኝ የሚችለውን ማንኛውንም ዓይነት ወንጀል ለመፈፀም የሚያቅማሙ አይደሉም። ህዝቡን በሙሉ በገንዘብ የሚገዛ ቢያገኙ ህዝቡን በሙሉ ለመሸጥ ወደ ኋላ ይላሉ ብሎ ማሰብም አይቻልም። ይህን በመሰለ የሞራል ውደቀት ውስጥ የሚገኙ ህወሃቶች የህዝቡን አቅም እንገነባለን ሲሉ ትንሽም አለማፈራቸው አገራችን ከደረሰችባቸው የሞራል ውደቀቶች መካከል አንዱ ሁኖ ሊጠቀስ የሚችል ዓቢይ ጉዳይ ነው።

ህወሃቶች ለእውቀትና ከእነርሱ በተሻለ ደረጃ ማሰብ ለሚችል ሰው ያላቸው ጥላቻ ወደር የለውም። ለዚህም ነው ከእነርሱ መካከል ይሄ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል የተመሰገን የተማረ ሰው የማይገኘው። ለህወሃቶች የተማረ ማለት ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት እያለ ለሆዱ ያደረ እንጂ ለአገሬ፤ ለህዝቤ፤ ለወገኔ ምን በጎ ተግባር ልፈፀም የሚል አስተሳሰብ ያለው ሰው አይደለም። የህወሃቶች ዋነኛው ችግር የተማረ ሰው መጥላታቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉንም እኛ እናውቃለን ማለታቸውም ጭምር ነው።ሁሉን እኔ አውቃለሁ ማለት ደግሞ የድንቁርና ታላቅ ምልክት ነው። ከዚህ ድንቁርና ራሱን ማላቀቅ ያልቻለ ቡድን የዜጎችን አቅም እገነባለው ብሎ መነሳቱ ከአስገራሚ በላይ ሁኖብናል።

ውሸት ጥሩ ነገር እንዳልሆነ ከህወሃቶች በቀር ሌላው ሁሉ የሚስማማበት ነገር ነው። ህወሃቶች ግን ውሸትን እንደ ታላቅ የትግል ስትራቴጂ ይቆጥሩታል።ህወሃቶች በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በአገር ደረጃ ሲዋሹ ቅንጣት ታክል እፍረት አይሰማቸውም። እንዲያውም ውሸታቸውን እውነት እንደሆነ አድርገው ያምናሉ። ለምሳሌ ኢኮኖሚው ከ11% በላይ አድጓል ይላሉ። ይሄ አሃዝ እውነት እንዳልሆነ ይታወቃል። ህወሃቶችና የሰበሰቧቸው ኮተታም ካድሬዎች ይሄን ውሸት እውነት ነው ብለው ያምናሉ። በአጠቃላይ ህወሃቶች ስለራሳቸውም ሆነ ስለሚገዙት ህዝብ እውነቱን መናገር ሞኝነት ነው የሚል ፅኑ ዕምነት አላቸው። ይሄን ከመሰለ ፅኑ ደዌ ራሳቸውን ማላቀቅ ያልቻሉ ደካሞች የሌላውን አቅም እንገነባለን ሲሉ አለማፈራቸው ያሳፍራል።

የሰሞኑ አቅም ግንባታ ብለው የሚጠሩት ግርግር ዓላማው እና ግቡ በተሻለ ደረጃ ማሰብ የሚችሉ ዜጎች ልዩ ልዩ አማራጮችን ማየት አቁመው አካሄዳቸውን በሞራልም ሆነ በእውቀት ውዳቂ ከሆነው ከህወሃት ጋር እንዲያደርጉ ለማድረግ ነው። ብዙ ኮተታም ካድሬዎቻቸው ለራሳቸው እንኳ የማይገባቸውን አብዮታዊ ድሞክራሲ የሚባለውን ፍልስፍና አዘረክርከው ይዘው በተማሪዎችና በመምህራን ፊት ያለምንም ዕፍረት ተጎልተው እየዋሉ ነው። እነዚህ ቡድኖች ከእነርሱ በተሻለ ደረጃ የሚያስብውን ኃይል መፍራት ብቻ ሳይሆን ሥር የሠደደ ጥላቻም አላቸው። በዚህ በሚፈሩትና በሚጠሉት ዜጋ መሃል ተገኝተው ለሚጠየቁት ጥያቄ መልስ መስጠት ሲገባቸው ማስፈራራት ዛቻ እና ስድብን የመልሳቸው ማሳረጊያ አድርገውታል።

በመሠረቱ አቅም ግንባታ ሲባል ዜጎች ራሳቸውንም ሆነ አገራቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያደርሱ የሚችሉበትን ሁኔታ በራሳቸው ማመቻቸት የሚችሉበትን አስተሳሰብ እንዲያሳድጉ የሚያስችል ነው። አቅም የሚገነባው የዜጎችን የመጠየቅ እና የመመራመር ችሎታ አዳብሮ የተሻለ አማራጭ እንዲያፈልቁ እንጂ መንግስት የሚለውን ብቻ አምነው እንዲቀበሉ ለማድረግ አልነበረም። የህወሃቶች አቅም ግንባታ ግን ዜጎች ማሰብ አቁመው መጠየቅንም ፈርተው ምንሊክ ቤተ-መግስት ውስጥ ከተተከሉት ዛፎች እንደ አንዱ ሁነው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው። እነዚያ ዛፎች መጥረቢያውን ሥሎ ሊገነድሳቸው ለሚያንዥብበው ዛፍ ቆራጭ ገንድሶ እሰከሚጥላቸው ድረስ ጥላ ይሆኑታል። ያ መጥረቢያውን ስሎ የተከለላቸው ሰው ጠላታቸው መሆኑን የማወቅ አቅም ግን የላቸውም። የህወሃቶች የአቅም ግንባታ ግቡ ዜጎች እንደ ዛፉ እንዳያስቡ እና ጠላትን ከወዳጅ የሚለዩበትን አቅም ማዳከም ነው።

ህወሃቶች ከ11% በላይ አድገናል ይላሉ። እደገቱ እውነት ከሆነ ለምን እንራባለን? ለምንስ ዜጎች ስደትን ይመርጣሉ? ለምንስ የጨው፤ የሳሙና፤ የስኳር፤ የቲማቲም እና የሽንኩርት ዋጋ የማይቀመስ ሆነ? ብሎ የሚጠይቅ ዜጋ ጠፍቶ፤ የውሸቱን የ11% እድገት ተቀብሎ የሚኖር ዜጋ የመፍጠር ብርቱ ቅዥት አላቸው።በዚህ ቅዥት ውስጥ እንዳይኖሩ የሚያጋድቸው የለም፤ ውሸታቸውንም አምኖ መኖር የእነርሱ ችግር ነው። የእነርሱ ውሸት አምኖ መኖር አገር የሚያፍረሰው እና ዜጎችን የሚያሰጨንቀው የእኛን ውሸት እመኑ ብለው ወደ ማስገደድ ደረጃ ሲደርሱ ነው። አሁንም እያደረጉ ያሉት ይሄንኑ ነው። የመንግስት ሠራተኞች፤ መምህራንና ተማሪዎች ተገደው የህወሃቶችንን ውሸት እየተጋቱት ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊያን ህወሃቶችን ማመን ካቆሙ ብዙ ዘመን ተቆጥሯል። ህወሃቶች በእንግሊዘኛው “ፓቶሎጂካል ላየርስ” ተብለው የታወቁ ናቸው። ይሄ ደግሞ በሽታ ነው። የህወሃቶች ውሽት ወደ በሽታ የተሸጋገረ ስለሆነ በማንኛውም መድረክና ሁኔታ የሚናገሩትን ማመን አይቻልም።ለምሳሌ የአዜብን ስታይል እንመልከት በስልክ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ስትነጋገር መጀመሪያ “አዎን እኔ አዜብ ነኝ” አለች ከአንድ ደቂቃ በኋላ ተመልሳ ደግሞ “አይ እኔ አዜብ አይደለሁም“ አለች። ይሄ እንግዲህ ውሸት ወደ በሽታ ተሸጋግሮባቸው የመኖሪያቸው ድንኳን መሆኑን ያሰየናል። እንግዲህ ዜጎች የህወሃቶችን ውሸት አንሰማም፤የእናንተንም አቅም ግንባታ አንፈልግም ማለት የሚችሉበት አገር የላቸውም። ዜጎች ይሄን እሰማለሁ፤ ያንን ደግሞ መስማት አልፈልግም የሚባል መብታቸው በህወሃቶች ተገፏል። ይህ የዜጎችን የመምረጥ መብት የገፈፈ ገዥ ቡድን እያደረገ ያለው የዜጎችን አቅም ማዳከም እንጂ የዜጎችን አቅም መገንባት አይደለም።አቅም በግዴታ አይገነባምና።

ህወሃቶች የሙስና ምንጮች መሆናቸው የታወቀ ነው።ከህወሃት መንደር ከሌብነት የፀዳ ባለስልጣን አይገኝም።ሁሉም ሌቦች፤ ሁሉም ሥነ-ምግባር የጎደላቸው ሰው ምን ይለኛልን የማያውቁ ናቸው። እነዚህ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ሙስና ማስቆም አገሪቷ ከገጠሟት ፈተናዎች መካከል አንዱ ቢሆንም መቆም ይኖርበታል። ይሄን ሙስና የማስቆም ኃላፊነት ከህወሃቶች እና ከኮተታም ካደሬዎቻቸው ውጪ ያሉ ዜጎችን ሁሉ ትብብር የሚጠይቅ ነው። በዚህ ረገድ መምህራኑና ተማሪዎች ለህወሃቶች ያነሷቸው ጥያቄዎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል። ህወሃቶች በሙስና መጨማለቃቸውን ከሌቦቹ ህወሃቶች በቀር ሁሉም ያውቃል። ህወሃቶች ከእንቅልፋቸው ሲነቁ በሚሊዮን የሚቆጠር ሃብት በእጃቸው ሲገባ የትግሌ ውጤት ይላሉ እንጂ ሰርቄ ነው የሚል አስተሳሰብ በአእምሯቸው ዝር አይልም። የህወሃቶች ትልቁ ችግር የሚፈፅሙትን ዝሪፊያ ሁሉ የትግላችን ውጤት ነው ይገባናል ብለው ከልባቸው ማመናቸው ነው። በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ የተቃኘ ቡድን የዜጎችን አቅም ለመገንባት በሚል እያካሄደ ያለው አደንቋሪ ስልጠና ተብየው የዜጎችን አቅም ያዳክም እንደሆነ እንጂ በምንም መሠፍረት የማንንም አቅም አይገነባም።

እነዚህ ቡድኖች ያለ ምንም ዕፍረት ሙስናን እንታገላለን ይላሉ። በሙስና የተጨማለቁ ባላስልጣናት ሙስናን እንዋጋለን ብለው በድፍረት ሲናገሩም ይደመጣል።በሙስና የተዘፈቁ ባላስልጣናት መኖራቸው እየታወቀ ለምን ህግ ፊት አይቀርቡም ተብለው ሲጠየቁ መልስ የላቸውም። ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ ዋና ሌባ መሆኑ ይታወቃል፤ በዘረፈው የህዝብ ሃብት የባንክ ቤት ባለድርሻ እሰከመሆን ደርሷል። መላኩ ፈንቴን እንዲታሠር የበየነው ህግ ሳሞራ የኑስን አይነካም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህግ ፊት እኩል ነው ቢባልም ሳሞራ የኑስና መላኩ ፈንቴን እኩል የሚያይ ህግ በኢትዮጵያ የለም። በዚህ ዓይነት የሞራል ዝቅጠት ውስጥ የሚገኝ ቡድን የሚገነባው አቅም ምንድ ነው? ዜጎችን በምን አቅጣጫ ወደየት ለመውሰድ ያለመ ስልጠና ነው እየተሰጠ ያለው ተብሎ ቢጠየቅም የሚገኘው መልስ ዜጎች ሁሉ እንደ ህወሃት በጎጥ አስተሳሰብ ተተብትበው፤ ሰው ምን ይለኛል ማለትን ረስተው፤ እግዚአብሄርን መፍራት ትተው፤ ግራና ቀኝ ማየትን አቁመው ከአንድ ማሰብ ከማይችል እንስሳ ሳይለዩ እንዲኖሩ ማድረግ ነው።

የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ህወሃት የተባለውን ዘረኛና ዘራፊ ቡድን ከተቆናጠጠበት የሥልጣን ኮርቻ ላይ አውርዶ አገሪቷን የሁሉም ለማድረግ የሚችለውን እያደረገ ነው። ለኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከህወሃት የበለጠ ጠላት የለም። ህወሃት ዋነኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት መሆኑ ሊሠመርበት የሚገባ ነጥብ ነው። ይሄን ጠላት ሳያቅማሙ በሁሉም መስክ መታገል ግዜው የሚጠይቀው ከዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ነው።

ተከብሬ የምኖርበት አገር ያስፈልገኛል የሚል ሁሉ ንቅናቄያችንን እንዲቀላቀል ዛሬም ደግመን የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን። እኛ አገር ያሳጡንን ቡድኖች በሚገባቸው ቋንቋን ለማነጋገር ሳንቅማማ የትግሉን ባቡር ተሳፍረናል። የትግሉን ባቡር አሁኑኑ ተሳፈሩና ለሁላችንም የትሆን አገር እንፍጠር።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Tuesday, September 9, 2014

ወጣቱን ለማደንቆር ያለመው ስልጠና ህወሓትን ለመቅበሪያነት ይዋል

ህወሓት፣ ከሶስት መቶ ሺህ በላይ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በየቦታው ሰብስቦ እያሰለጠነ ነው። ይህ ሲያልቅ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ስልጠና ይቀጥላል ተብሏል። በድምሩ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ወጣት አንድ አይነት ሰነድ አንብቦ ለ2007 ትምህርት ይዘጋጃል ማለት ነው። ስልጠናው ወደ መንግሥት ሠራተኞችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም ይስፋፋል ተብሎ ይገመታል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በዚህ ሥልጠና ላይ ያለውን እይታ በነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓም ቁጥር 328 ርዕሰ አንቀጹ መግለጹ ይታወሳል። ግንቦት 7 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወያኔ ስልጠናዎች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት መድፈራቸው ወጣቱ ለለውጥ የተዘጋጀ እንደሆነ አመላካች መሆኑን ተገንዝቦ ይህ የለውጥ ፍላጎት በድርጅት እንዲታገዝ ወጣቱ በትናንሽ ሕዋሶች ራሱን እንዲያደራጅ መክሯል። ሆኖም ግን ህወሓት ለስልጠናው የሰጠው ትኩረት ቀድሞ ከታሰበው በላይ በመሆኑ ንቅናቄዓችን በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደገና ሊመለስበት ወስኗል።

ህወሓት፣ ይህንን ያህል መጠነ ሰፊ ስልጠና ማድረግ ለምን አስፈለገው? የዲሞክራሲ ኃይሎችስ ይህንን ስልጠና እንዴት ለራሳቸው ጥቅም ሊያውሉት ይችላሉ?

ህወሓት ይህንን ትርጉም የለሽ ስልጠና በአሁኑ ሰዓት ለመስጠት የፈለገበትን በርካታ ምክንያቶች ማቅረብ ቢቻልም የሚከተሉት ሁለቱ ግን ዋነኛዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።

አንደኛውና ዋነኛው ምክንያት ህወሓት የተከታዮች ድርቅ የደረሰበት መሆኑ አድርባይ መሪዎቹን ማሳሰቡ ነው። በሚሊዮን ይቆጠራሉ የሚባሉት የኢህአዴግ አባላት ልባቸው ከህወሓት ጋር አለመሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። በተለይ ደግሞ በተላላኪዎቹ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደህዴግ የተሰባሰቡ አባላት በግልጽ ህወሓትን መቃወም እየጀመሩ ነው። ህወሓት የራሱን መጥፊያ እያደራጀ መሆኑ የተሰማው በመሆኑ አዳዲስ “ምዕመናንን” ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ መመልመል ይፈልጋል። የመንግሥት ንብረትና መዋቅር ለፓርቲ ስልጠና የሚጠቀም በመሆኑ ከብዛት የሚገኝ ትንሽም ቢሆን ጥቅም የሚያገኝ ከሆነ የወጭው ጉዳይ ህወሓትን አያሳስበውም። ስለሆነም ይህ ስልጠና በተቻለ መጠን ብዛት ያላቸዉን የተማተሩ ወጣቶች በአድርባይነት ለህወሓት ማሰለፍን አላማዉ አድርጎ የተነሳ ስልጠና ነዉ።

ሁለተኛው አቢይ ምክንያት ደግሞ ህወሓት ለኢትዮጵያ ወጣት ለማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ወደ እያንዳንዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ጆሮ መድረሱን ማረጋገጥ መፈለጉ ነው። መልዕክቱም “ሜዳ ውስጥ ያለሁት ተጫዋች እኔ ብቻ ነኝ። ለሚቀጥሉት አርባና አምሳ ዓመታትም እኔን የሚገዳደረኝ አይኖርም፤ ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ ለለውጥ ያለህ ተስፋ ከንቱ ነው። አርፈህ ቁጭ ብለህ ተገዛ” የሚል መልክት ነው።

ስልጠናዎቹ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ዓላማዎችን በሚገባ ማስፈፀም ይችላሉ ብሎ መገመት ከባድ ነው። የስልጠናው ይዘት እጅግ የወረደ እና የሰልጣኞቹን ብስለት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑ ስልጠናውን ምፀት የበዛበት አድርጎታል፤ አሰልጣኞቹንም ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል። የስልጠናዎቹ ጽሁፎች (ማንዋሎች) ይዘት ደግሞ የአዘጋጆቹ የእውቀት ማነስ ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ ለተማሪዎቹ ተጨባጭ ማስረጃዎች ሆነውላቸዋል። በአጠቃላይ ስልጠናው ለአሰልጣኝ ካድሬዎች ያልተዘጋጁበት ፈተና ደቅኖባቸዋል። የኢትዮጵያ ወጣት ሲሞሉት የሚሞላ ባዶ ጋን አለመሆኑን እያዩት ነው። ወጣቶች ጠጣር ጥያቄዎችን ያነሱባቸዋል፤ አሰልጣኖች እነዚህ ጥያቄዎች እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ስለማያውቁ ይደናበራሉ። መልስ ሲጠፋ ቁጣ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ይከተላል።

ይህም ሆኖ እነዚህ ስልጠናዎች ለህወሓት ምንም ውጤት አያስገኙም ብሎ ማለፍ አይቻልም። የስልጠናዎቹ ውጤት የሚወሰነው ግን የኢትዮጵያ ወጣት ከህወሓት ውጭ ለሚመጣ መረጃ ባለው ቅርበት መጠን ነው። ሁሉም የመረጃ ምንጮች ተዘግተውበት የህወሓትን የእድገትና የሰላም መዝሙር ሲሰማ ለኖረ ሰው በስልጠናው የሚሰጡ ባዶ ፕሮፖጋንዳዎችን የመቃወሚያ ምክንያት አይኖረውም። ለተለያዩ የመረጃ ምንጮች ቅርበት ያለው ወጣት ግን የህወሓት መዝሙር ከግራዚያኒ የእድገትና የሰላም መዝሙር የተለየ አለመሆኑን ይረዳል። በፋሺስት ወረራ ወቅት ግራዚያኒም ኢትዮጵያን በመንገድና በህንፃ እየገነባሁ ነው፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ አውሮፓ የደረሰችበት ደረጃ ላይ አደርሳታለሁ ይል እንደነበር ይታወሳል።

የህወሓትን ኢትዮጵያን ለአርባና አምሳ ዓመታት የመግዛት እቅድን ወጣቱ ምክንያታዊ ነው ብሎ ይቀበላል? የራሱን አፋኝ ህጎች አክብረው እየተፍጨረጨሩ ያሉ ተቀናቃኖቹን እንኳን በእንጭጩ እየደፈጠጠ ያለ ሥርዓት “ኃላፊነት የሚሸከም አጣሁ” የሚለው ሰበቡ በወጣቱ ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል? በግንቦት 7 እምነት ይኸኛው የስልጠና ዓላማ ሊሳካ የሚችለው በዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ድክመት ብቻ ነው። ዘረኛውንና ዘራፊውን ወያኔ መጣል ብቻ ሳይሆን ከወያኔ በኋላ ፍትህ፣ እኩልነትና ብልጽግና የሚሰፍኑበትን ስትራቴጄ ያዘጋጀና ለስትራቴጂዉ ክንዉንራሱን ያዘጋጀ ድርጅት መኖሩን የኢትዮጵያ ወጣት ማወቅ ይኖርበታል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ወደ ነፃነት፣ እኩልነትና ብልጽግና ጎዳና ለማስገባት እየታገለ መሆኑን ሁሉም ወጣት ሊገነዘብ ይገባል። ይህ ግንዛቤ ካለ የኢትዮጵያ ወጣት ለእብርተኛው፣ ዘረኛው፣ ሙሰኛውና ከፋፋዩ ህወሓት ተገዢ አይሆንም።

በስልት ከተጠቀምንበት ህወሓት ብዙ ሚሊዮኖች የሕዝብ ገንዘብ አውጥቶበት ያዘጋጀው ስልጠና ለራሱ ከሚሰጠው ጥቅም በላይ ለዲሞክራሲያዊ ኃይሎች የሚሰጠው ጠቀሜታ ይበልጣል። ለምሳሌ፣ ግንቦት 7 እነዚህን ስልጠናዎች የኢትዮጵያን ወጣት ለትግል ያላቸውን ዝግጁነት ለመገምገም ተጠቅሞበታል። “የኢትዮጵያ ወጣት ለትግል ዝግጁ ነው – የቀረው ድርጅት ነው” ሲል የግምገማውን ውጤት አሳውቋል። በዚህም ርዕሰ አንቀጽ ይህንኑ መልዕክት ማስረጽ ይፈልጋል።

በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ የሚኖሩ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ከተለመዱ አደረጃጀቾች መለየት አለባቸው። መደበኛ (Formal) አደረጃጀቶች አባላትን ለአደጋ ያጋልጣሉ። በዚህም ምክንያት ነው ግንቦት 7፣ ኢ-መደበኛ (Non Formal) አደረጃጀቶች የሚመርጠው። በእኛ ሁኔታ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀት” ስንል አራት ይሁን አምስት የሚተማመኑ ወጣቶች የሚፈጥሩት የግንቦት 7 ሴል ነው። ይህንን ሴል የፈለጉትን ስም ሊሰጡት ይችላሉ – እድር፣ ክበብ፣ የሆነ ስፓርት ቡድን ደጋፊ የተመቻቸውን ስያሜ ይስጡት። የተቋቋመበት ዓላማ ግን ግልጽ ነው – ለፍትህና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ማገዝ ነው። ይህ ኢ-መደበኛ ስብስብ ራሱን የግንቦት 7 አካል አድርጎ ይቁጠር። የግንቦት 7 ፕሮግራሞችንና ጽሁፎችን ያንብብ። ስብስቡ ለመረጃዎች ራሱን ቅርብ ያድርግ። መረጃዎችን ይለዋወጥ። በሂደት ቀጣዩ መንገድ ግልጽ እየሆነለት ይመጣል።

እየተካሄደ ያለው የህወሓት የጅምላ ስልጠና ለኢ-መደበኛ ድርጅቶች መስፋፋት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች እነዚህን ስልጠናዎች የግንቦት 7 ሴሎችን ለማደራጀት እንዲጠቀሙበት እንመክራለን። ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ወጣት የፈጠራ ችሎታ ላይ እምነት አለው። የኢትዮጵያ ወጣት አደንቁሮ ሊቀብረው የመጣውን ስልጠና ህወሓትን ለመቅበሪያነት እንደሚጠቀምበት የግንቦት 7 እምነት ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!



Saturday, July 26, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረዘይት አየር ሃይል ግቢ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥ
በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ የማሰቃያ መርፌዎችን እየተወጉና
በኤልክትሪክ ሾክ እየተሰቃዩ መረጃ እንዲያወጡ እየተገደዱ ነው።
መርማሪዎች ከአቶ አንዳርጋቸው የሚፈልጉት መረጃ ከግንቦት7 ጋር በጋራ የሚሰሩ  አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግን አመራሮችን እንዲሁም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ አዛዦችን ስሞች
ሲሆን፣ አቶ አንዳርጋቸው ግን እስካሁን ምንም አይነት መረጃ ባለመስጠታቸው ፣ መርማሪዎች ሲበሳጩ መታየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ለወትሮው አንድ መረጃ ሲያገኙ በታላቅ ደስታ
የሚፈነጩት መርማሪዎች፣ ምርመራቸውን ጨርሰው ሲወጡ የሚያሳዩት ብስጭት፣ እስካሁን ድረስ የሚፈልጉትን እንዳላገኙ የሚያሳይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ አንዳርጋቸው እንዳስፈላጊነቱ በቀን ሶስት ጊዜ ምርመራ እንደሚካሄድባቸው የሚናገሩት ምንጮች፣ ምርመራውን የሚያካሂዱት የተመረጡ የህወሃት የደህንነት ሰራተኞች መሆናቸውንና በግቢው
ለበረራ የሚሰለጥኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ወይም የደህንነት ሰራተኞች ወደ አካባቢው እንደማይሄዱ ገልጸዋል። ምሽት አካባቢ የሚሰማው የጣር ድምጽ የሚረብሻቸው የእለት ተረኛ ጠባቂ
መኮንኖች በሁኔታው እያዘኑ አንዳንዶች ስሜታቸውን መቆጣጠር እንደማይችሉ ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
ስለ አቶ አንዳርጋቸው የእለት ውሎ ማወቂያ ብቸኛው ዘዴ የመርማሪዎች ፊት ነው የሚሉት ምንጮች፣ እስካሁን ድረስ ምርመራ በሚያካሂዱ የህወሃት አመራሮች  ዘንድ የደስታ ፊት
እንደማይነበብ ገልጸዋል።
የኢህአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታሰሩበትን ቦታ ይፋ ለማድረግ እስካሁን ፈቃደኛ አልሆነም። የእንግሊዝ ባለስልጣናት ለአቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር የማማከር አገልግሎት ለመስጠት
ጥያቄ ቢያቀርቡም ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ከዚህ በተቃራኒ ኢህአዴግ በአቶ አንዳርጋቸው እና በግንቦት7 ላይ ለሚሰራው ድራማ ግብአት ይሆን ዘነድ የተለያዩ ሰዎችን ማሰማራቱን ምንጮች ገልጸዋል። ቀደም ብለው በአገዛዙ ለስለላ ወደ ኤርትራ ተልከው
እና ለተወሰኑ ወራት ግንቦት7 ትን ተቀላቅለው በመጨረሻ የኢህአዴግ የስለላ አባላት መሆናቸው ሲታወቅ የጠፉ እንዲሁም ፈንጅ ሊያፈነዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉ እና በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጠቀም
እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ያሳየው ቁጣ ያስደነገጣቸው ደህንነቶች ለማንኛውም በሚል በደንበር አካባቢ ጥበቃቸውን እያጠናከሩ ነው።
የአቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ግንቦት7ትን የሚቀላቀሉ ሰዎች መጨመራቸውንም ከድርጅቱ የወጣው መረጃ ያመለክታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤልጂየም ብራሰልስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸውን ለመያዝ የሄደበትን እርቀት ከማውገዝ በተጨማሪ የእንግሊዝ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ
አጥብቆ እንዲከታተል ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በአውሮፓ ህብረት ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን በከፍተኛ ቁጣ ከማሰማት በተጨማሪ፣ ያዘጋጁትን ደብዳቤ ለአውሮፓ ህብረት
ባለስልጣናትና ለእንግሊዝ መንግስት ኮንስላ ጽ/ቤት ሃላፊዎች አስረክበዋል።

Friday, July 25, 2014

ለብሔራዊ አንድነትና ነፃነት – ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል!!!

በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙ የእብደት ተግባራትን ስናጤን ከፊት ለፊት ኢትዮጵያችንን እየጠበቀ ያለው መንታ መንገድ አመላካች ነው። ይህ ከፊት ለፊት የሚጠብቀን መንታ መንገድ አንዱ ወደ ብሔራዊ አንድነት፣ ነፃነትና ብልጽግና ሌላው ወደ እርስ በርስ ትርምስና ውድቀት የሚያመሩ ናቸው። የአንድነት፣ የነፃነትና የብልጽግና መንገድ ለመያዝ መስመራችንን ማስተካከል ያለብን ከአሁኑ ነው።

ለመሆኑ ከላይ ያልነውን ለማለት ያስቻሉን በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙት ተግባራት ምንድናቸው?

አንደኛ፤ ወያኔ፣ ዓለም ዓቀፍ ህግንና ሥርዓትን በጣሰ መንገድ ከየመን ባለሥልጣናት ጋር በማበር የንቅናቄዓችንን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማፈኑ በአለፉት ጥቂት ሣምንታት ውስጥ ውስጥ የተደረገ አብይ ክስተት ነው። ይህ የወያኔ የውንብድና ተግባር ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ አስቆጥቷል። ወያኔ፣ ለሀገር ነፃነትና ለእኩልነት የሚታገልን አንድ ታላቅ ሰውን ማፈንኑና ከእይታ ከልሎ እያሰቃየው መሆኑ በሕዝቡ ውስጥ ያለው ቁጣ ወደ መገንፈል አስጠግቶታል። አቶ አንዳርጋቸው በጠላት እጅ ከወደቀም በኋላ ኢትዮጵያዊያንን አሰባሳቢ ኃይል ሆኗል።

ሁለተኛ፤ ሰላምተኞቹን ብሎገሮችንና ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት በመክሰስ በቋፍ ላይ የነበረውን የወጣቶች ትዕግሥት እንዲሟጠጥ አድርጓል። ስለኢንተርኔት አጠቃቀምና ጥንቃቄ ሥልጠና መውሰድ በክስ ቻርጁ ውስጥ መካከቱ ሥርዓቱ ከእውቀት ጋር የተጣላ መሆኑ በግልጽ አሳይቷል። ከዚህም በተጨማሪ በህጋዊ ፓርቲዎች ውስጥ በንቃት የሚሳተፉ ወጣት መሪዎችን መርጦ በማሠርና በሽብርተኝነት በመወንጀል የወያኔ የአፈና መዋቅር ወጣቱ ላይ ማነጣጠሩ ግልጽ ሆኗል።

ሦስተኛ፤ እጅግ ሰላማዊና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ አቤቱታቸውን በማቅረብ ላይ የነበሩትን ሙስሊም ወገኖቻችንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ እና በጅምላ በማሠር በወያኔ መድብለ ቃላት ውስጥ “ሰላማዊ ትግል” የሚባል ነገር አለመኖሩ፤ ተቃውሞ ሁሉ “ሽብር” እንደሚባልና በሽብርተኝነት እንደሚያስከስስ በማያሻማ ሁኔታ አረጋግጧል። ይህም የሥርዓቱ አውሬዓዊ ባህሪ መገለጫ ሆኗል።

አራተኛ፤ አፈናውና እስሩ ወደ ትግራይም በመዛመቱ ወያኔ የቆመበት ምድር እየራደ መሆኑ አመላካች ሆኗል። ትግራይ ውስጥ የነበረው አፈና ድብቅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ከወያኔ የውስጥ ሽኩቻ ጋር ሲያያዝ ቆይቷል። አሁን ግን ሁኔታዎች እየተቀየሩ ነው። አገራዊ ርዕይ ያነገቡ፤ ወያኔን በጽናት ለመታገል የቆረጡ የትግራይ ወጣቶች ወደፊት እየመጡ ነው። እነዚህ ወጣቶች የተጫነባቸውን ድርብርብ ጫና በመበጣጠስ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጎን መቆማቸውን በተግባር እያረጋገጡ፤ ለዚህም መስዋዕትነት እየከፈሉ ናቸው።

ከላይ የተዘረዘሩት አራት ጉዳዮች በጋራ ሲታዩ የተበታተነ የሚመስለው እና በተለያዩ ስልቶች የሚደረገው ትግል የሚሰባሰብበትና የሚቀናጅበት ወቅት ላይ መደረሱ አመላካቾች ናቸው። ዛሬ የምንገኘው የተለያዩ የትግል ስልቶች እንዲናበቡና እንዲደጋገፉ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ ነው።

በተለይም ወያኔ፣ መሸሸጊያ ምሽጉ አድርጎ በሚቆጥረው ትግራይ ውስጥ እየዳበሩ የመጡት የአመጽም አመጽ-የለሽ ትግሎችም አስተዋጽኦ ከፍተኛነት ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲረዳ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ነው። የወያኔ የአፈናና የመጨቆኛ መዋቅሮች የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ዘውጌ ማኅበረሰብ አባላት የሚዘወሩ መሆኑ እውነት ነው። ይህ ማለት ግን ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ወኪል ወይም ጠበቃ ነው ማለት አይደለም። ትግላችን ከወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ጋር መሆኑ እና የትግራይ ሕዝብ የዚህ ትግል አጋር፣ የውጤቱም ተጠቃሚ መሆኑ ማስረገጥ ተገቢ ነው።

ከፊት ለፊታችን ካሉት መንታ መንገዶች መካከል የአንድነትን፣ የነፃነትና የብልጽግናን መንገድ ለመምረጥ የትግራይ ሕዝብ በስፋት ትግሉን እንዲቀላቀል ማድረግ ተገቢ ነው። ትግራይ የህወሓት የግል ጓዳ መሆኗ የማብቂያ ጊዜ ማፋጠን ይቻላል። በዲሞክራሲያዊ ትግል ውስጥ ያሉ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ ግንዛቤ ከያዙ ወያኔን ማንሳፈፍ የሚቻልበት እድል በስፋት ተከፍቷል።

ስለሆነም፣ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዘረኛውና ፋሽስታዊው ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል አንዱ የትግላችን ስትራቴጂ ሊሆን ይገባል ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Monday, July 21, 2014

ምናምንቴዎች በሠለጠኑ ግዜ ህዝብ ያልቀሳል !!!

ኢትዮጵያ ላይ ጥቂት ምናምንቴዎች ሰልጥነው ህዝቡን እያስለቀሱት ነው። ኢትዮጵያዊያን ለብዙ ዘመን በብዙ ሃዘንና እንባ ውስጥ መኖራቸው የታወቀ ነው። የአሁኑ ሃዘን እንዲሁ ተራ ሃዘን፤ ልቅሶውም ተራ ልቅሶ አይደለም። መራር ሮሮ እንጂ። ይህን የህዝብ ሮሮ የሚሰማ መንግስታዊ አካልም የለም። በ“Global terrorist database” ውስጥ የሥም ዝርዝሩ ተመዝግቦ የሚገኘው “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ” ነኝ የሚለው ቡድን መንግስ ነኝ ቢልም የመንግስት መልክና ባህሪይ ሊኖረው አልቻለም። ህወሃት መንግስታዊ አሸባሪ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ለመሆን የሞራልም ሆነ የእውቀት ብቃት ያለው ቡድን አይደለም።

ህወሃት ከተፈጠረ ጀምሮ የብዙ ንፁህ ዜጎችን ደም አፍሷል። ብዙ ዜጎችን ለስቃይ እና ለስደት ዳርጓል። ብዙ ቤተሰብን በትኗል። በተለይ ጠላቴ ነው ብሎ የሚያምነውን የአማራ ህዝብ ለማጥፋት ሴቶችን መካን የሚያደርግ ክትባት እስከ መከተብ ደርሷል። በዚህም የአማራው ቁጥር ከነበረው ቀንሶ ተገኝቷል። ይህ አሸባሪ ቡድን በኦጋዴን፤ በአፋርና በጋምቤላ የፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም ያወቀው ነው። በኦሮሚያ የፈሰሰው የንፁሃን ዜጎች ደም ከምድር ወደ ሰማይ እየጮኸ ነው። በአዲስ አበባ እና በደቡብ የተበተነውን የቤተሰብ ብዛት ቆጥረን አንዘልቀውም። በትግራይ የሚገኙ ምርጥ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አልቀዋል። የተረፉ ጥቂቶች ቢገኙም መግቢያ መውጪያ አጥተው በሁለት ሰይፍ የሚቆረጡ ሁነዋል።

የትግራይ ነፃ አውጪዎች ያተረፉልን ነገር ቢኖር ውርደት ነው። ውረድቱ የከበዳቸው ዜጎች ራሳቸውን በእሳት አቃጥለዋል። ገደል ውስጥ ራሳቸውን ወርውረው የሞቱም አሉ። ህወሃቶች ባሉበት ከምንኖር ብለው ስደተን መርጠው የበርሃ ንዳድ፤ የባህር ዐዞ እራት የሆኑ ብዙ ናቸው። በባእዳን አገር ውስጥም ማረፊያ አጥተው የሚንከራተቱም ቁጥራችው በቀላል የሚገመት አይደለም። ይህ የህወሃት መራር ፍሬ ነው።

አዎን በአገራችን ላይ እነዚህ እግዜርን የማያውቁ የሰይጣን ድንኳኖች ከሰለጠኑ ዘመን ጀምሮ የንፁህ ሰው ደም ሳይፈስ የዋለበት ቀን የለም። ህወሃቶች የትልቁንም የትንሹንም ደም በማፈሰስ የሚረኩ፤ ቤተሰብንም በትነው ድሃ አደግ በማድረጋቸው የሚደሰቱ ፍጡራን ስለመሆናቸው የእስከዛሬው ምግባራቸው ቋሚ ምስክር ነው። ለስልጣን ካላቸው ሥሥት የተነሳም ከባዕዳን ጋር እየተመሳጠሩና ብዙ ሚሊዮን ገንዘብ እየከፈሉ ነፍሰ ገዳዮችንና አፋኞችን ቀጥረው ዜጎችን እስከማሳፈን ደርሰዋል። የዚህ ዕኩይ ተግባር ሰለባዎች ብዙ ናቸው። ታላቁ ሰው አንዳርጋቸው ፅጌ የዚህ እኩይ ተግባር ሰለባ ከሆኑ ብዙ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ነው።

ጠላቶቻችን(ህወሃቶች) እና ወዳጆቻችን በሙሉ ስሙን ! አንዳርጋቸው የተነሳው ፡

ሚዛኑን ስቶ መሳለቂያ የሆነው ፍትህ ወደ ሚዛኑ ለመመለስና ፍጹም የህግ የበላይነትን በአገራችን ለማስፈን ነው።
የነፃነት ትርጉም ሳይገባው ስለነፃነት ሊነግረን ሳይሆን የነፃነትን ጣዕም አጣጥሞና ተርድቶ ከምር ኢትዮጵያዊያን ያለፍርሃት በነፃነት እንዲኖሩ ለማስቻል ነው።
ጥቂቶች ብዙሃኑን ተጭነው፤ ብዙሃኑም ጥቂቶቹን ተሸከመው መከራቸው በዝቶ የሚኖሩበት ሥርዓት ተወግዶ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት እንዲኖሩ ለማደረግ ነው።
ጠባብ ጎሰኛነት ተወግዶ ሁሉም በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ በሠላም መኖር የሚችልበት ንፁህ አገር እንድትኖረን ለማድረግ ነው።
ከዚያች ድሃ አገር ላይ እየዘረፈ በውጭ አገራት ባንኮች ውስጥ የሚደብቅ ይሄን ማድረግ ካልቻለም መሬት ምሶ የዘረፈውን ገንዘብ የሚቀብር ዘራፊ ቡድን ሳይሆን ያለውን ሁሉ ለአገሩና ለህዝቡ ለመስጠት ከልቡ ያመነ መሪ አገሪቷን የሚመራበት ሥርዓት እንዲዘረጋ ለማድረግ ነው።
ኢትዮጵያችን በውሸታሞች፤ ለህዝባቸው ክብር በሌላቸው፤ህዝባቸውን በሚንቁ፤ ከራሳቸውው ፍላጎት ውጪ ሌላ ወገን ህዝብ ማለትን በማያውቁ ደካሞች መገዛቷ አክትሞ ህዝቡን ፈርቶና አክብሮ የሚመራ፤ ህዝብ ላይ የሚጫን ሳይሆን በህዝብ የተመረጠና የተወደደ መሪ እንዲኖራት ለማብቃት ነው።
ግንቦት ሰባትንና መሪውን አንዳርጋቸው ፅጌን በህወሃቶች ዘንድ አሸባሪ እንዲሆኑ ያደረጓቸው እነዚህ ከላይ ለመዘርዘር የሞከርናቸው ቁም ነገሮች ናቸው እንጂ እንደ ህወሃቶች ግንቦት ሰባት ባንክ ሲዘርፍ፤ የእምነት ሥፍራዎችን ሲያወድም፤ ትምህርት ቤቶችን ሲያፈራርስ፤ የቀደመው ትውልድ በደምና አጥንቱ ያቆየውን ድንበር ቆርሶ ሲሸጥ፤ የአገሪቷን ለም መሬት ለባእዳን ሲሸጥ፤ አንዱን ጎሳ ከሌላው ጋር አጋጭቶ ደም እንዲፈስ ሲያደርግ ተገኝቶ አይደለም።

ባንክ መዝረፍ፤ የእምነት አምባዎችን ማርከስ፤ ትምህርት ቤቶችን ማውደም፤ የአገሪቷን ድንበር እያፈርሱ ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት፤ ለም መሬቶችን ለባዕዳን መቸብቸብ፤ በህዝቦች መካከል ጥላቻን መዝራት፤ ከድሃ ጉሮሮ ላይ ሠርቆ በውጪ አገራት ባንኮች ውስጥ ገንዘብ ማጠራቀም ህወቶች እንደ ሙያ የተያያዙት የእለት ተዕለት ተግባራቸው ነው። ግንቦት ሰባት የተነሳው እንዲህ ዓይነት ነውረኞችን ከተቆናጠጡበት የስልጣን ወንበር ላይ አውርዶ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊያን የምትሆን አገር እንድትሆን ለማድረግ ነው። የመሪያችን የአንዳርጋቸው ፅጌም ምኞት ይሄው ነው። ኢትዮጵያን ከጥቂት ዘረኞችና ዘራፊዎች እጅ አውጥቶ የብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ አገር እንድትሆን ማድረግ።

ይሄ የኢትዮጵያ ውድ ልጅ በነውረኞቹ የትግራይ ነፃ አውጪዎች እጅ ገብቷል። ነፃ አውጪ ነን ባዮቹ አንበሳውን ከበው ለመቦጫጨቅ እንደሚያጓሩ ጅቦች ዓይናቸውን አጉረጥርጠው እያሰቃዩት ይገኛሉ። ምንም እንኳ ይሄ ታላቅ ሰው በነፍሰ ገዳዮቹ እጅ ቢወድቅም እርሱ የጀመረው የነፃነት ጥያቄ የሚሊየኖች ጥያቄ ሆኖ ከመቸው ግዜ በላይ ሚሊየኖችን አስነስቷል። በዓለም ዙሪያ “እኔም አንዳርጋቸው ነኝ፤ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ” የሚሉ ድምፆች ከፍ ብለው እየተሰሙ ነው። አንዳርጋቸውን ማሰር እንጂ እርሱ የጀመረወን የነፃነት ጥያቄ፤ እርሱ የዘረጋውን የትግል መስመር ማሰር አይቻልም። ለዚህም ነው አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ፅኑ መንፈስ ነው የሚባለው።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ህወሃት የተባለው ዘረኛ እና የወሮበላዎች ቡድን የገነባው የሰይጣን ድንኳን ፈርሶ ፍትህ፤ነፃነት እና እውነተኛ ዴሞክራሲ ተገንብቶ እስከሚያይ ድረስ የጀመረውን ሁለ ገብ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል።

የተከበራችሁ ያገራችን ዜጎች ሆይ ስሙን ! እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ማለታችሁ አንድ በጎ እርምጃ ነው። እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ማለት አንዳርጋቸው ራሱን አሳልፎ ለሰጠው ድንቅ ዓላማ ራሳን አሳልፎ መስጠት ማለት መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል። አንዳርጋቸው የቆመለትን ዓላማ ለማስፈፀም እኛ ወደ እናንተ እሰከምንመጣ መጠበቅ የለባችሁም። በያላችሁበት አምስትም ስድስትም አስርም እየሆናችሁ የአርበኝነት ተግባር መፈፀም መጀመር አለባችሁ። የቀደመዉ ትውልድ ፋሽት ጣሊያንን በየመንደሩ እየተደራጀ እና የጎበዝ አለቃ እየመረጠ መፋለሙን አስታወሱ። እናንተም ከምታምኑት ጋር እየተደራጃችሁና የጎበዝ አለቃ እየመረጣችሁ የዘመኑን ፋሽስት ልትፋለሙት ይገባል። ዘመቻ አንዳርጋቸው ማለት እኔ ለነፃነቴ፤ እኔ ለፍትህ እና ለህግ የበላይነት፤ እኔ ከዘረኞቹና ከሌቦቹ ህወሃቶች የፀዳች አገር ለመፍጠር ተነስቼአለሁ ማለት ነው። ለዚህም ዓላማ ለመሞትና ለመግደል ዝግጁ ነኝ ልትሉ ግዜው አሁን ነው። እንደ ቀድሞ ዝም ብላችሁ የምትሞቱ ሳትሆኑ ለመግደልም የምትችሉ መሆኑን በተግባር ማሳየት መቻል አለባችሁ።

“ትግሬን ነፃ” እናወጣለን ብላችሁ የተነሳችሁ እናንት ነውረኞች ሆይ ስሙ ዓይናችሁ እያየ፤ ጆሯችሁም እየሰማ ከወገኖቻችን ጎን ሁነንና እጅ ለእጅ ተያይዘን ልትገነቡ የሞከራችሁትን የዘረኝነትና የዝሪፍያ መረብ እንበጣጥሰዋለን። እናንተ ዘረኞችና ዘራፊዎች ስሙ! ህዝብን እንዳስለቀስዋችሁ መቀጠል እንደማትችሉ እርግጠኛ ሁኑ። አገራችን ኢትዮጵያም እናንተን ከመሰሉ ምናምንቴዎች ፀድታ ህዝቦቿም በነፃነት የሚኖሩበት ግዜ እሩቅ አይደለም። ያን ግዜ በእናንተ ነውሮኞች ግፍ የሚያለቅስ ህዝብ አይኖርም። አበቃን!!!

ድል ለኢትዮጵያችን ይሁን !!!!



Friday, July 18, 2014

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።

የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ነው። እነዚህ የጦርና የፓሊስ ሹማምንት ኢትዮጵያን ወረው እንደያዙት አገር ሲዘርፉ፣ ሕዝቧንም ሲገሉና ሲገርፉ እንሆ 23 ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ 23 ዓመታት ትግራይን ጨምሮ በደል ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት እና የኅብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ፋሽስቶች ተረግጧል፣ ተዋርዷል፣ ተግዟል። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በእነዚህ እኩይ የሠራዊቱና የፓሊስ አዛዦች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። የወያኔ የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች አገራችን እያደሙ፤ ሕዝባችንን እያስለቀሱ ነው። በወያኔ ፋሽስት የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች ጥምረት ሰቆቃ የሚፈፀምበት የኅብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። የወያኔ ማሰቃያዎችን የሞሉት የፓለቲካና የሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች መሆናቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።

የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።

ግፍ መብቃት አለበት። በጥቂት የህወሓት ሹመኖች ትዕዛዝ በኢትዮጵያዊው ወታደር ላይ የሚደርሰው ውርደት ማብቃት አለበት። ሠራዊቱ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሓት ሠራዊት አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም። ሠራዊቱ ለራሱ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ለአገርና ለሕዝብ ደህንነት ዘብ የመቆም ኃላፊነት አለበት። የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት የባንዳ ሠራዊት ሆኖ ሕዝብን በማሰቃየትና ሀገርን በመበደል ተግባር ላይ ተሠማርቶ ማየት አንሻም። ይህንን ለራሱ ክብር ያለው፤ አገሩንና ሕዝቡን የሚወድ የሠራዊቱ አባልም የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም።

ስለሆነም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚከተለው ሀገራዊ ጥሪ ለመላው የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ያቀርባል።

ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ወይም የፓሊስ ሠራዊት አባል! በጥቂት የህወሓት ፋሽስቶች መዳፍ ውስጥ ሆነህ የገዛ ራስህን፣ የቤተሰቦችህን፣ የወገንህን እና የአገርህን ስቃይ ማራዘምህን አቁም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታ እንጂ የጥቂት ጎጠኞች ሎሌ ልትሆን አይገባም። አንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታ እንጂ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ስጋት መሆን የለብህም። አንተ የመጪው ትውልድ አርዐያ እንጂ ሕፃናትንና ወጣቶችን ማስፈራሪያ መሆን የለብህም።

የኢትዮጵያ ወታደር ሆይ! ራስህን ተመልከት! ራስህን ታዘብ! ዛሬ ያለህበት ሁኔታ አሳፋሪ ነው። አዛዦችህ አገርን፣ ትውልድንና ታሪክን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው። አንተን ተጠቅመው ነው ይህንን ዓላማቸውን የሚያስፈጽሙት። ይህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆችህ ውርደት ነው። ከወያኔ ባርነት ራስህን ነፃ አውጣና የነፃነት ታጋዮችን ተቀላቀል። ወያኔ መጥፋቱ አይቀርም። ወያኔ የቀድሞውን ጦር እንደበተነው አንተን ለመበተን የሚሻ የለም። አንተ ዛሬ ከወገን ጋር ወገንተኛነትህን ካሳየህ ከአገዛዙ ጋር እጠፋለሁ ብለህ አትስጋ። ለዚህም ነው አንተ ዛሬ በግልም ሆነ በቡድን የምትወስደው እርምጃ የአገራችንን ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱን እጣ ፈንታ ይወስናል ብለን ወገናዊ ጥሪ የምናቀርብልህ።

ውድ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ወገናችን!ከበዳዮች ጎን ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን ቁም። ከገራፊዎችና ገዳዮች ጎን ሳይሆን ከነፃነት ታጋዮች ጎን ሁን። ዛሬውኑ ወስን። አሁን የነፃነት ታጋዮችን መቀላቀል ቀላል ሆኗል። ያሉበትን ታውቃለህ፤ ተቀላቀል። አልያም የጠመንጃህን አፈሙዝ በፋሽስት አለቆችህ ላይ አዙር። ይህንን እርምጃ በመውሰድ ከታሪክ ተወቃሽነት እራስህን በመታደግ ለአገርህና ለወገንህ አለኝታህን አረጋግጥ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Saturday, July 12, 2014

ወያኔ አንዳርጋቸው ያፈነበት እለት የሚረግምበት ቀን ሩቅ አይደለም!

የህወሃት ጉጅሌ እንደማንኛውም አምባገነን ከፊት ከነበሩ አምባገነኖች ቅንጣት ትምህርት አልተማረም። ወያኔዎች በእብሪት የያዙት ስልጣንና ከህዝብ የዘረፉትን ንብረት የሚያጡት እየመሰላቸው በባነኑ ቁጥር የነጻነት አርበኞችን በማፈን በመግደልና በማሰቃየት ፍርሃታቸው የተወገደ ይመስላቸዋል።

ወያኔ የእኛ መሪና የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት አርበኛ በሆነው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያካሄደው አፈና ከአፈናውም በሆላ በሚያደርሱበት አካላዊ ስቃይ ፍርሃታቸው የሚወገድ ወይም ስርአታቸው ከሞት የሚተርፍ መስሏቸው ከሆነ በእጅጉ ተሳስተዋል። አንዳርጋቸው ዛሬ በእጃቸው ሆኖ በነጻነት ይኖር ከነበረበት በበለጠ የሚለበልባቸው የውስጥ እግር እሳት ይሆናል።

አንዳርጋቸው ሰበአዊ ምቾቱንና ለራሱና ለቤተሰቡ መኖርን አቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻነት በህይወቱ ሊጋፈጥ ከቆረጠ ቆይቷል። እኛ የትግል ጓዶቹና ለህዝብ ነጻነት የቆሙ ሃይሎች ሁሉ አንዳርጋቸውን እናውቀዋለን። ወያኔ በአካሉ ላይ የለመደውን ስቃይ ጀምሮበታል፣ ከዚህ የበለጠም ጉዳት እንደሚያደርስበትም እናውቃለን። የአንዳርጋቸውን ታላቅ የነጻነት ሰውነትና ክብረ ህሊናውን፣ በአርበኝነቱ የሚሰማውን የኩራት ስሜቱን ለግፈኞች ያለውን ንቀትና መጸየፍ ሊለውጡ እንደማይችሉ አስረግጠን እናውቃለን።

አንዳርጋቸው እንደሁላችን ሰው ነውና በፈሪዎች በትር የሚደርስበት አካላዊ ስቃይ ግን ለህዝባችን የገባነውን ቃል ውሳኒያችንን እና አቋማችንን እንደብረት ያጠነክረዋል እንጂ አያላላውም።ይልቁንም በአንዳርጋቸው መታፈን ምክንያት ከመላ ሀገራችን በአለም ዙሪያ ከተበተነው ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች የነሰታነት ሃይሎች የምንሰማውና እየሰማን ያለነው የሚያስገመግም ህብረ ድምጽ ከብረት የሚያጠነክር ሃይል ሆኖኗል።

አንዳርጋቸው የዘራው የነጻነት የአርበኝነት ዘር ከመብቀል አልፎ እየጎመራ በመሄድ ላይ ነው። አንዳርጋቸው ሺ አንዳርጋቸውን ተክቷል። ወያኔ አንዳርጋቸውን በማፈንና በእጁ አስገብቶ በራሱ መስኮት ቲቪ ስቃዩን እንግልቱን በማሳየት ሊያላምጠው የማይችል የብረት እንክብል ነው የነከሰው። ይህንንም ሳይውል ሳያድር ያየዋል፡፡

መላው ህዝባችን በእልህና በቁጭት ላይ ያለህ ወገናችን ና የሀገራችን የነሰታነትና የዴሞክራሲ ሃይሎች በሙሉ፡- በአንዳርጋቸው ላይ ወያኔ የፈጸመው የአሸባሪዎች ውንብድና በየአንዳንዳችን ላይ የተፈጸመ በደል ግፍ ነው።

ይህንን የሽብርና የውንብድና ስርአት ለማስወገድ አብረን ከመነሳት ውጪ አማራጪ የለንም። የልዩነታችንን አጥር አፍርሰን የወየኔን እድሜ እንድናሳጥር ግንቦት 7 ለሁላችንም ጥሪውን ያቀርባል።

አንድ ሆነን የአንዳርጋቸውን ስምና ምግባር እንሁን!

አንዳርጋቸው የዘራው እና እየጎመራ ያለው የአርበኝነት ንቅናቄ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ወያኔ አንዳርጋቸውን ያፈነበት ቀን የሚረግምበት ጊዜ ከዚህ በኋላ ሩቅ አይሆንም፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Tuesday, July 8, 2014

Ethiopia: Fears for Safety of Returned Opposition Leader

Yemen Unlawfully Deported Andargachew Tsige, Concerns over Possible
Mistreatment
JULY 7, (London) – An exiled Ethiopian opposition leader unlawfully deported by Yemen back to Ethiopia is at risk of mistreatment including torture. Andargachew Tsige is secretary-general of Ginbot 7, a banned Ethiopian opposition organization, and was convicted and sentenced to death in absentia in separate trials in Ethiopia in 2009 and 2012.

The current whereabouts of Andargachew, a British national, is unknown, raising concerns for his safety. The Ethiopian government should take all necessary steps to ensure Andargachew’s safety and his right to a fair trial. Many individuals arrested in politically related cases in Ethiopia are detained in Addis Ababa’s Maekelawi prison. In an October 2013 report, Human Rights Watch documented the use of torture by authorities against detainees in Maekelawi, including members of opposition political parties and organizations, as well as journalists.

“We are deeply concerned for Andargachew Tsige’s safety,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Ethiopia needs to demonstrate that it is holding Andargachew in accordance with its international obligations, and he should be allowed immediate access to a lawyer, his family, and to British consular officials.”

Yemeni officials arrested Andargachew at El Rahaba Airport in Sanaa, Yemen, on June 23 or 24, 2014, while he was in transit on a flight from Dubai to Eritrea. They did not permit him consular access to UK embassy officials and summarily deported him to Ethiopia, credible sources told Human Rights Watch, despite his being at risk of mistreatment.

Yemeni authorities initially denied any knowledge of Andargachew’s detention and transfer to Ethiopia. Ethiopian government officials publicly called for his extradition from Yemen on July 3.

Under the Convention against Torture, which Yemen ratified in 1991, a government may not “expel, return (‘refouler’) or extradite a person to another State where there are substantial grounds for believing that he would be in danger of being subjected to torture.” These protections override any extradition treaty or other security arrangement that may exist between Yemen and Ethiopia.

Trials in absentia generally violate the defendant’s right to present an adequate defense, concerns heightened in cases involving the death penalty.

“Yemen blatantly violated its international legal obligations by deporting someone to Ethiopia who not only is at serious risk of torture, but also faces the death sentence after being tried in absentia,” Lefkow said.

Ginbot 7, of which Andargachew is a founding member, was established in the aftermath of Ethiopia’s controversial May 2005 national elections. The Ethiopian government banned Ginbot 7, which has advocated the armed overthrow of the Ethiopian government, and officially considers it to be a terrorist organization.

The government has prosecuted Ginbot 7 members and leaders in trials that did not meet international fair trial standards. In November 2009, a court convicted Andargachew and 39 others under the criminal code on terrorism-related charges. Andargachew, who was tried in absentia, was sentenced to death. In June 2012, he was convicted again in absentia, this time under the abusive 2009 anti-terrorism law, along with 23 journalists, activists, and opposition members. Again, he was sentenced to death.

Human Rights Watch has repeatedly criticized provisions in Ethiopia’s anti-terrorism law that violate due process rights guaranteed under Ethiopian and international law. At least 34 people, including 11 journalists and four Ginbot 7 leaders, are known to have been sentenced under the law since late 2011 in what appeared to be politically motivated trials; the real number is likely much higher. Suspects held under the law may be detained for up to four months without charge, among the longest periods under anti-terrorism legislation worldwide.

Ethiopian courts have shown little independence from the government in politically sensitive cases. Defendants have regularly been denied access to legal counsel during pretrial detention, and complaints from defendants of mistreatment and torture have not been appropriately investigated or addressed – even when defendants have complained in court.

The Ethiopian government routinely denies that torture and mistreatment occurs in detention. It restricts access to prisons for international observers, monitors, and consular officials, making it difficult to monitor the number and treatment of prisoners. In several cases documented by Human Rights Watch, Ethiopian security officials have arrested foreign nationals, denied knowledge of their whereabouts, and delayed access for consular officials for long periods.

In 2007 Human Rights Watch documented the forced transfer of scores of men, women, and children from Somalia and Kenya to Ethiopia. One of the men, Bashir Makhtal, a Canadian citizen of Ethiopian origin who was accused of membership of the Ogaden National Liberation Front (ONLF), a banned armed movement in Ethiopia, was denied consular access for 18 months. Meanwhile in 2010 and again in 2012, refugees registered with the United Nations High Commissioner for Refugees in Kenya were unlawfully returned to Ethiopia and told Human Rights Watch that they were subsequently tortured in detention. In all of these cases, the individuals were accused of belonging to groups that the Ethiopian government has designated as terrorist groups.

“Given its appalling track record of mistreating members and perceived supporters of banned groups, Ethiopia should know that the world will be watching how it treats Andargachew Tsige,” Lefkow said.
2014

Saturday, July 5, 2014

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ገመዳ ልጅ አረፈ – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)




ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።
ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ቀን ቀን በዚህ ቢሮ ለብቻቸው ያሳልፉ የነበሩት አዜብ መስፍን በጠና ከታመሙ ወዲህ ላለፉት አምስት ሳምንታት ወደዚህ ቢሮ ገብተው እንደማያውቁና በቤታቸው እንደሚያሳልፉ ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም ፓርቲው በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች መገኘት እንዳቆሙና ለመጨረሻ ጊዜ የተገኙት ከሁለት ወር በፊት ኢህአዴግ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚሁ ጉባኤ ከተሰብሳቢው ኋላ ለብቻቸው ተቀምጠው የታዩት አዜብ ምንም ሳይናገሩና አስተያየት ሳይሰጡ ስብሰባውን ከመጨረሳቸው ባሻገር ከስተውና ተጐሳቁለው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰው ከዚያ ወዲህ ህመሙ እየጠናባቸው እንደሄደ አያይዘው ገለፀዋል። አዜብ የባለቤታቸውን ቦታ በመተካት የጠ/ሚ/ርነቱንና ፓርቲውን የመምራት እቅድና ምኞት በተቀናቃኛቸው ስብሃት ነጋ ከከሸፈባቸውና የሚተማመኑባቸው የደህንነት ባለስልጣናትና የፓርቲው ቁልፍ ሰዎች እስር ቤት መወርወርና መባበረር ለከፍተኛ የሞራል ድቀትና ለበሽታ እንደዳረጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። አዜብ የኤፈርት ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ተብለው ቢሰየሙም ምንም አይነት የአመራር ሚና እንደሌላቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በነስብሃት ተመድበው ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ወደ ራዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና ከርሳቸው በኋላ ደግሞ የአርከበ እቁባይ ታናሽ ወንድም ጌታቸው እቁባይ እየመሩት መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።
ከአዜብ ጋር በተፈጠረ ያለመግባባት ከኤፈርት ለቀው የቆዩት ጌታቸው እቁባይ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ እንዲመለሱ መደረጉን አመልክተዋል። አዜብ ወደ ትግራይ -መቀሌ ከተጓዙ 6 ወር እንዳለፋቸው አክለዋል። በኤፈርት ውስጥ የአዜብ ደጋፊዎች በነስብሃት ተለቅመው መውጣታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ በቅርቡ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር የሚለውን የአዜብ ስልጣን በመግፈፍ ሊያባርሯቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። …ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባዱላ ገመዳ ልጅ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ ከዚህ አለም በሞት እንደተለየ ታውቋል። የ26 አመቱ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ በጉበት በሽታ ምክንያት ወደ ታይላንድ- ባንኮክ ተልኮ ለአንድ አመት ሲታከም ከቆየ በኋላ ሊድን ባለመቻሉ ከአራት ሳምንት በፊት ህይወቱ አልፏል። በባንኮክ ለአንድ አመት የሆስፒታል ቆይታው ለህክምና ብቻ ከ880ሺህ ዶላር ወጪ እንደተረገለት ታውቋል። በተመሰሳሳይ ሶስተኛ ታናሽ እህቱ (የአባዱላና ራሄል ልጅ) ከአምስት አመት በፊት በገጠማት የሳንባ፣ የአንጀትና የአእምሮ በሽታ በባንኮክ ሆ/ል ለሁለት አመት ህክምና የተከታተለች ሲሆን፣ ለህክምናው ጠቅላላ የወጣው 2.5ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ከዚህ ቀደም ይፋ በተረገው መረጃ መገለፁ ይታወሳል። ይህ ሁሉ ገንዘብ ከህዝብ የተዘረፈ ለመሆኑ አያጠያይቅም። ይህቺ ናት አገሬ! ..ለማንኛውም የአባዱላ ወንጀል ልጁን አይመለከተውም። ወጣት ኮሚያስ በአባቱ ድርጊት ነፃናነት ስለማይሰማው – በየእለቱ አልኮል ይጠጣና ይበሳጭ እንደነበረ ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹ ተናግረዋል። የጉበት በሽታውም መንስኤ ይኸው ነው። ነፍስ ይማር!

Friday, July 4, 2014

አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም!!! – የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው ታላቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀስ የመንን እንደመሸጋገሪያ በሚጠቀምበት ወቅት በሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በየመን ሰንዓ ከተማ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሀገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል:: ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻ ምክንያት ለአቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግሥት መታገት እና መታሰር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል እንደማይገባም በመግለጽ የየመን መንግሥት የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ እንዲለቅ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤት አላስገኘም:: ከዚህም በመነሳት አቶ አንዳርጋቸው ለዘረኛው እና ከፋፋዩ የወያኔ ቡድን ሊሰጥ ይችላል የሚለው ስጋታችን ቀን በገፋ እና ምላሽ በራቀ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::

በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በኩል የነፃነት ታጋዩ ለወያኔ ተላልፎ መሰጠቱን መቶ በመቶ እስከምናረጋግጥበት ቅጽበት ታጋዩን የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እናምናለን:: አንዳርጋቸውን ማሰር ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውን ማሰቃየት ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤ አንዳርጋቸውን መግደል ይቻላል። ሞትን ፈርቶ ወደ ትግል አልገባምና አንዳርጋቸውን በማሰር የአንዳርጋቸውን እንደ እቶን የሚያቃጥል የፍትህ፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲና የእኩልነት መንፈስ ግን ለሴኮንዶች እንኳን ማሰር አይቻልም። አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ያን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ የትውልዱን መንፈስ የሚገዛ የሁላችንም የምትሆን የጋራ ኢትዮጵያን የመፍጠር ንጹህ ራዕዩን ግን ፈጽሞ ማቁሰል አይቻልም!!! አንዳርጋቸውን በመግደል ዕንቁ ዓላማውን መግደል ከቶ አይቻልም፤ የታሪክ መዛግብት ገጾች ለዚህ ሃቅ በሚመሰክሩ እውነታዎች የተሞላ ነውና። አንዳርጋቸውን በመግደል “ከአባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተፈጠረ ይቆጠራል፣ ልጅ አባቱን ሩጦ መቅደም አለበት፣ ስለዚህ እናንተ ወጣቶች እኛን ሩጡ እና ብለጡ ቅደሙን፣ ቀናዎች ሁኑ፣ ርስ በርስ ተዋደዱ፣ ያለፉት ትውልዶች የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ታሪክን ከስሩ ተረዱ፣ ያለማወቅ ጠንቅ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን ሁሌም ለእውቀት ጉጉዎች ሁኑ። ለማወቅ ጣሩ፣ የማይቀረው ሞታችሁ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ እና ለነፃ ኢትዮጵያ ይሁን” እያለ ላለፉት በርካታ አመታት ያስተማራቸው እና የኮተኮታቸው የነፃነት ታጋይ አርበኛ ወጣቶችን እና እሳት መንፈሳቸውን መግደል አይቻልም::

ታሪካዊ ስህተት በመሥራት በአዲሱ ትውልድ ልብ ውስጥ የበቀል እና የቂም ጓዝ ለማስቀመጥ እየተንደረደረ ያለው የየመን መንግሥትም ሆነ ወያኔ ሊያውቁት የሚገባው ተፈጥሯዊ ሃቅ ይህ ነው:: አንዳርጋቸውን በአንድ ካቴና በማሰር፤ በአንድ ክፍል ውስጥ በመዝጋት ወይም በአንድ ጥይት በመግደል “መገላገል” የሚቻል አንድ ግለሰብ አይደለም:: አንዳርጋቸው ለሽህ ካቴናዎች የማይታጠፉ እጆች፤ ለሽህ ማጎሪያዎች የገዘፈ ገላ፤ ለሽህ ጥይቶች የሰፋ እና ሽህ ጥይቶችን የሚተፋ ግንባር እና ደረት ያለው ብርቱ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው አንድ ግለሰብ አይደለም፤ የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጅ!!!

አንዳርጋቸው ለአርባ አመታት በሚጠጋ የፖለቲካ ሕይወቱ ሁሉ በረሃ የሚወረወረው አፈር ላይ የሚንከባለለው፤ በእሱ እድሜ በማይታሰብ ሁኔታ እንኳን የበረሃ ሃሩር፣ ጥም እና ረሃብ የሚያንገላታው ነገ ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ወይ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመምራት ካለው ሰዋዊ ፍላጎት አይደለም:: የሱ ምኞት የሁላችንም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው!!! ይህን በተለይ የግንቦት ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች እና መላው አባላት ጠንቅቀን እናውቃለን:: አንዳርጋቸው ሁሌ ለሚያልማት ንጽህት ኢትዮጵያ መሥራት የነበረበትን ፈታኝ እና ታሪካዊ ሥራዎች ቀድሞ አከናውኗቸዋል:: ላለፉት 6 እና 7 ዓመታት ከጥልቅ የፖለቲካ ተሞክሮው እየቀዳ ለወጣት ኢትዮጵያውያን በየበረሃው እየዞረ አስተምሯል:: እያማጠ አደራ ብሏል:: እያለቀሰ ምኞቱን፣ ፍላጎቱን እና ራዕዩን ከውስጡ አውጥቶ መዳፉ ላይ በማስቀመጥ ልቡን ለታዳጊዎች አሳይቷል:: ንጹህ ዓላማው ሽህ ባለ ራዕዮችን ፈጥሯል የተግባር ሰዎችን አምርቷል:: የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አንዳርጋቸው እንደመጥምቁ ዮሃነስ በበረሃ እየዞረ ሲያስተምር እና ሲሰብክ ከፈጠረው ንጹህ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ የበቀለ ኃይል ነው::

ትናንት አብሮ ውሎ ዛሬ በድንገት መተጣጣት የትግል አንዱ ባህሪው ነውና ዛሬ አንዳርጋቸው በአካል አብሮን ላይኖር ይችላል:: ነፍሳችን ውስጥ ያሰረፀው ዘላለማዊ መንፈስ ግን እስከመጨረሻ ህቅታችን ድረስ አብሮን ይዘልቃል:: አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን አቆማለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ዓለምን እና ሁኔታዎችን መገንዘብ የማይችል ከራሱ የተጣላ የወያኔ አይነት ቂል ብቻ ነው:: አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን ማስቆም አይቻልም:: መንፈስን ማስቆም ከቶ ማን ይቻለዋል?? አንዳርጋቸው እኮ መንፈስ ነው:: ሁሉም ቦታ፣ ሁሉም ጫፍ ፣ሁሉም ልብ ውስጥ የሚገኝ እና የሚንሳፈፍ መንፈስ::

የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ ስህተት መሆኑን ዘግይቶም ቢሆን ተረድቶ የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ ይለቀው ዘንድ አሁንም ደጋግመን እንጠይቃለን:: ይህ ሳይሆ ን ቀርቶ ታጋያችን ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ ግን የትውልዱ የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት እንፈልጋለን:: ወያኔም ይህ የቂል ድርጊት የነፃነት ታጋዮችን የበለጠ ቁጭት እና የበቀል እርምጃዎች ውስጥ የሚከት መሆኑን አብሮ ሊገነዘበው ይገባል:: ለዚህ ቃላችን ታሪክ ምስክር ይሁንብን::

ድል ለ ኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Sunday, June 29, 2014

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!

ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።

ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።

የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።

ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።

ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።

ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።

ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።

የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!



Wednesday, June 25, 2014

ቀና ብለን የምንሄድበት ጊዜ አየመጣ ነው! ጎበዝ ተነሳ!

ጉጅሌዎቹ አይገባቸውም እንጂ የኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች የለውጥን ደመና ኣርግዘዋል። ወንዞችም ተራሮችም የለውጥ ማዕበል ማቆብቆቡን አያበሰሩ ናቸው። የቀደሙት ገዢዎች መረጃ የሚያገኙት እረኛ ምን ይላል ብለዉ እየጠየቁ ነበር። የአሁኖቹ አገር አጥፊ ገዢዎች ምሳሌ ያደረጉት ካድሬዎቻቸውን ብቻ ሆነ እንጂ ዛሬም የአገራችን እረኞች የለውጥን መምጣት በሚያምር ቅላጽያቸው አያንጎራጎሩ እንዲህ አያሉን ነው፣

የሀገሬ ጉብል የሰማውን እንጃ

የጎንደሬው ጉብል የሰማውን እንጃ

ከብቱን አየሸጠ ገዛ ኣሉ ጠብመንጃ።

የወለጋው ጉብል የሰማውን እንጃ

ቡናውን ሻሽጦ ገዛ ኣሉ ጠብመንጃ።

መልእክቱ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች አገራቸውን በክቡር ደማቸው ሊታደጓት ቆርጠው በመነሳት ወያኔን በማስወገድ የሀገራቸው ባለቤት ለመሆንና ያልተከፋፈለች ውብ ኢትዮጵያን ማየትን ለማረጋገጥ ጥርጊያውን መጀመራቸው ነው።

ላለፉት ፵ አመታት አምባገነኖች ባደረሱብን ጭቆና እና እንግልት የተነሳ የራሳችን የሆነ መንግሥት ሳይኖረን አንገታችንን ደፍተን ጀግኖቻችንን ስንገብር ኖረናል። በተለይም ባለፉት ፪፫ አመታት ጉጅሌዎቹ በአራት ኪሎ ከነገብን ጀምሮ በአንድ ላይ አንዳንቆም በማድረግና እና አርስ በራሳችን በማጋጨት ሲያባሉን ኖረዋል።

ዛሬ ሁኔታዎች ተለውጠዋል፤ በውጭም በአገር ውስጥም ለውጥ አየታየ ነው። የእንቅስቃሴው ማእበል አይሎ እየመጣ ነው። ዛሬ ሁሉም የዴሞክራሲ ሀይሎች ማለት በሚቻል ደረጃ በሁለት ነገሮች ላይ ስምምነት አለ፣

፩. ተቃዋሚዎች በግል ከሚያደርጉት ትግል ይልቅ በጋራ የመሰባሰብን አስፈላጊነት ተረድትው መሰባሰብ መጀመራቸው

፪. በአንድ ላይ መሰባሰብ ካልቻሉም እርስ በራስ ላለመጠላለፍ መስማማት መቻላቸውና አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ግዜ ሁሉ መረዳዳት መጀመራቸውና በግልም ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትግል ማፋፋም የቻሉበት ሁኔታ አየታየ መሆኑ የሕዝብ ወገኖችን እያስደሰተ ይገኛል።

በአገር ቤት የሚገኙ የዴሞክራሲ ኃይሎችም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝቡ ከፍርሀት ተላቆ ለመብቱ አንዲነሳ የሚያደርጓቸው አንቅስቃሴዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከሩ መጥተዋል። ለዚህም በቅርቡ በአዲስ ኣበባ መድረክ፣ ኣንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች የጠሯቸው ሰልፎች ይበል የሚያስብሉ ናቸው።

ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በዚሀ ኣጋጣሚ ለዴሞክራሲና ለነፃነት ታጋዮች ሁሉ ያለውን አክብሮትና ኣድናቆት ይገልጻል።

በሌላም በተለያዩ አቅጣጫዎች ወያኔን በኣመጽ ለመፋለም የወሰኑ ኃይሎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ወያኔን ለመፋለም ቆርጠው በጋራ ክንዳቸውን ኣቀናጅተው ለመፋለም አየተዘጋጁ ያሉበት ሁኔታ አበራታች ነው። እነዚህ ኃይሎች አዳዲስ የነጻነት ታጋይ አርበኞችን በተከታታይ በማስመረቅ ያሉ መሆናቸውና ከዚህም በተጨማሪ ከመላው የአገሪቱ አካባቢዎች ወጣቶች በገፍ ትግሉን እየተቀላቀሉ መሆኑን ስንሰማ ልባችን በደስታ ይሞላል።

በወያኔ ጉያ ውስጥ ያሉ የሕዝብ ወገኖች ደግሞ የቻሉትን በውስጥ ሆነው መቃብሩን እይቆፈሩለት ሲሆን፣ ያልቻሉትም የወያኔን ሚስጢር ይዘው በመውጣት የሕዝብ ወገንተኝነታቸውን አየገለጹ ይገኛሉ።

ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ለመላው ሕዝባችንና በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በተደጋጋሚ አንደሚለው የሀገራችን ባለቤት ለመሆን የምናደርገውን ትግል ተቀላቀሉ!!! መቀላቀል ያልቻላችሁም በኣካባቢያችሁ ከምታምኗቸው ወገኖቻችሁ ጋር ተሰባሰቡ፣ በህዋስ ተደራጁ። ግንቦት 7 በዚህ ትግል የዳር ተመልካች ሳይሆን መሪ እንድትሆኑ ኣገራዊ ጥሪውን ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Saturday, June 14, 2014

የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ማን ይፈራቸዋል?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እስክንድር ነጋን፣
 ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን…ማን ይፈራቸዋል?
bloggersየኢትዮጵያ የነጻው ፕሬስ እና ጦማርያን ቁንጮ የሆነው እስክንድር ነጋ ሀሳቡን በነጻ በመግለጹ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስር ተበይኖበት በገዥው አካል የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር እንዲውል እና የ18 ዓመቱ የሸፍጥ እስራት እንዲበየንበት ተደርጓል፡፡ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ማናቸውም ጋዜጠኞች የበለጠ እስክንድር ነጋን ይፈራዉና ይጠላው ነበር፡፡ ዝሆን አይጦችን “ይፈራል” ከሚለው ኢ-ስነ አመክንዮ አንጻር በተመሳሳለ መልኩ መለስም እስክንድር ነጋን እንደጦር ይፈራው ነበር፡፡
በቅርቡ እስክንድር ከማጎሪያው እስር ቤት ለ8 ዓመት ልጁ ለናፍቆት እንዲህ የሚል ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል፣ “እንዲያው ሁኔታውን ሳየው እያለሁ የሌለሁ የዘፈቀደ አባት ሆኛለሁ፣ ምክንያቱም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፈረንሳዮች ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍቅር እያሉ ደጋግመው ይጠሯቸው የነበሩትን ሶስት ቀላል ቃላትን በመውሰድ እኔም በሀገሬ ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍቅር እንዲሰፍን በማሰብ እነዚህን ቃላት በማስተጋባቴ ነው በሸፍጠኞች ለእስር የተዳረግሁት“ ብሏል፡፡ እስክንድር ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለአብሮነት ፍቅር ጦማሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለእኔ የጀግናዬ ተምሳሌት የሚሆነው!
የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ጀግናዋ የ34 ዓመቷ ወጣት ርዕዮት ዓለሙ በተመሳሳይ መልኩ በአቶ መለስ ዜናዊ የ14 ዓመታት እስር በይኖባታል፡፡ ይህች ጀግና ወጣት በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ “እውነት ተናጋሪዋ ኢትዮጵያዊት እስረኛ” በመባል ትታወቃለች፡፡ ርዕዮት ለእስር የተዳረገችው የግድብ ፕሮጀክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በተመለከተ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችት በማቅረቧ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የሊቢያ አምባገነን መሪ ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ ከአንድ ባህር የሚቀዳ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው መሆናቸውን በይፋ በመግለጿ ነው፡፡ ርዕዮት በእስር ቤት ተዘግቶባት እና አፏን ተሸብባ ለመቀመጥ ባለመፍቀድ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ ስልጣኖቻቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥነት ለሚጠቀሙት ህገወጦች እና ትዕቢተኞች እውነት እውነቱን እንዲህ በማለት እቅጬን ተናግራለች፣ ”የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት እኔ በግሌ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ማበርከት አለብኝ የሚል እምነት አለኝ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎች ተንሰራፍተው ስለሚገኙ እነዚህን እኩይ ተግባራት በምጽፋቸው ትችቶቸ ማጋለጥ እና ከንቱ መሆናቸውን መቃወም አለብኝ… ለዚህ በጎ ዓላማ በድፍረት ትግል በማካሂድበት ወቅት ሊያስከፍለኝ የሚችለውን ዋጋ ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ“ በማለት ከእስር ቤት አፈትልከው በሚወጡ የእጅ ጽሁፎቿ ገልጻለች ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ፡፡ በማይበገረው እና በማይንበረከከው ትክክለኛ የጽናት አቋሟ ምክንያት ገዥው አካል ሰብአዊነት የሚባለውን ክቡር ነገር በመደፍጠጥ የህክምና አገልግሎት እንዳታገኝ ቅጣት ጥሎባታል፡፡ መቀመጫውን ሎንዶን ያደረገ የህግ መከላከል የተነሳሽነት ሜዲያ/Media Legal Defense Initiative የተባለ ተቋም በአልጃዚራ ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት “በሰውነት አካሏ ላይ የተከሰተ እብጠት የተገኘ ቢሆንም ተገቢ የሆነ ህክምና እየተሰጣት እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ ምንም ዓይነት የሰመመን መስጫ ማደንዘዣ ሳይሰጣት በጡቷ ላይ የቀዶ ህክምና ስራ በማከናወን የቀዶ ህክምና መስፊያ ክሩ ከጡቷ ሳይወጣ ከዓመት በላይ ከመቆየቱም በላይ ከደህረ ቀዶ ህክምናው በኋላም ቢሆን ተገቢ የሆነ ህክምና የተሰጣት አይደለም“ ብሏል፡፡ ለእኔ ርዕዮት የጀግና ተምሳሌታዬ ናት!
የማይበገረው ጋዜጠኛ እና አርታኢ ውብሸት ታዬ የመናገር አንደበቱን ተሸብቦ በመለስ ዜናዊ ዝዋይ በሚባል አስፈሪ እና ጭራቃዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በእርሱ ላይም የ14 ዓመታት እስራት ተበይኖበታል፡፡ ውብሸት የገዥውን አካል ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን አስመልክቶ በጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ትችቶች እና አስተያየቶች በፍጹም አያቋርጥም፡፡ ውብሸት ለሚጠዘጥዝ የኩላሊት ህመም ተጋልጦ የሚገኝ ቢሆንም እርሱም ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ በመሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ለሚገኙት የህሊና እስረኞች የህክምና አገልግሎት መንፈግ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እለት በእለት የሚፈጽማቸው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የቅጣት ወንጀሎች ናቸው፡፡ ፍትህ እየተባለ የሚጠራው የውብሸት የአምስት ዓመት ልጅ እንዲህ በማለት ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል፣ “ሳድግ እና ለአቅመ አዳም ስደርስ እኔም እንደ አባቴ ሁሉ ወደ እስር ቤት እጋዛለሁን?“ ሕፃኑ ፍትህ በአሁኑ ጊዜ አጥር የሌለው እስር ቤት ውስጥ እየኖረ መሆኑን ሊገነዘብ አይችልም፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “የኢትዮጵያ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች” (የፖለቲካ እስረኞችን ከያዘው ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው የ “መለስ ዜናዊ ታዋቂው የቃሊቲ እስር ቤት” ህንጻዎች ቀጥሎ የተሰየመ) እና ሌሎች ጋዜጠኞች በስም አጥናፍ ብርሀኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋቤላ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሳዬ የክሱ ጭብጥ ባልታወቀበት ሁኔታ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ውለው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ፖሊስ በእነዚህ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ላይ ምን ዓይነት ክስ መመስረት እንዳለበት ገና በመለግ ላይ ይገኛል፡፡
(የገዥው ቡድን ፖሊስ የሚጠረጥረውን ዜጋ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር አውሎ እና እስርቤት በማጎር እያሰቃዬ ተሰራ ለተባለው ጥፋት ማስረጃ እና መረጃ በመፈለግ በዜጎቿላይ ሰብአዊ መብትን በመደፍጠጥ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ብቸኛዋ አገር ናት!!!የይስሙላዎች የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች በዘፈቀደ ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስርለዋሉት ዜጎች ዋስትና በመንፈግ ፖሊስ እና አቃቤህግ የሚባሉ የገዥው አካልየማጥቂያ መሳሪያ ሎሌዎች የሚፈበረኩ የፈጠራ ውንጀላዎችን አቀነባብረውእስኪያቀርቡ ድረስ የተንዛዙ እና አሰልቺ የሆኑ ማያልቅ ቀጠሮዎችን በመስጠት እናየይስሙላውን ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ከሚገባው በላይ በማዘግየት በንጹሀን ዜጎችላይ የቁማር ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ነው አነዚህን ፍርድቤቶችን “የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች እያልኩ የምጠራቸው፡፡” እውነተኛው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ወንጀል ሀሳብን በነጻ በመግለጽ የሚያምኑበትን ነገር በነጻ ማራመዳቸው እና እነርሱ የተሻለች ኢትዮጵያ በማለት ስለሚጠሯት ኢትዮጵያ ህልም ማለማቸው ነው፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን ጉዳይ የሚመለከተው በቅርቡ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የዳኝነት ችሎት ለህዝቡ እና ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታተሉት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ዝግ ነበር፡፡
እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን…የሚፈሯቸው ለምንድን ነው?
ናፖሊዮን ቦና ፓርት የተባሉት የፈረንሳይ አምባገነን መሪ በዚያች አገር የነጻው ፕሬስ ላይ ጦርነት ባወጁበት ወቅት “ከአንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ አራት ተቃዋሚ ጋዜጦች የበለጠ ይፈራሉ“ የሚለውን እውነታ የበለጠ ግልጽ አድርጎታል፡፡ ላለፉት 23 ዓመታት በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር በስልጣን ላይ ተጣብቆ ለሚገኘው ገዥ አካል ኤኬ – 47 ከታጠቀ አንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ ብዕር እና የኮምፒውተር ኪይ ቦርድ የያዙ ጥቂት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የበለጠ ያስፈሩታል፣ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንዲወሸቅ ያደርጉታል፣ ያርዱታል፣ ያስደነብሩታል፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጡታል፣ የቀን ቅዠት ይፈጥሩበታል፣ በላብ እንዲጠመቅም ያደርጉታል፡፡ በታሪክ መነጽር ሲታይ እና ሲገመገም ሁሉም አምባገነኖች እና ጨቋኞች የነጻውን ፕሬስ የእውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈሩታል፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተንፈራጥጠው የሚገኙት አምባገነኖች ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ከታቀው እና በልዩ ልዩ የጦር ክፍሎች ተዋቅሮ በጠላት ላይ ቅጽበታዊ ድልን የመቀዳጀት አቅም ካለው እና የጠላትን ኃይል በማያንሰራራ መልኩ ከሚያደባይ የጦር ኃይል ይልቅ የነጻውን ፕሬስ የዕውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈራሉ፡፡
ጠቅላላ የብዙሀን መገናኛዎችን እና ነጻውን ፕሬስ መቆጣጠር የገዥዎች እኩይ ምግባር ነው፡፡ የመረጃ ፍሰቶችን በመቆጣጠር በኃይል የሚገዙትን ህዝብ ልብ እና አእምሮ የተቆጣጠሩ እንደሚመስላቸው እምነት አላቸው፡፡ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎችን በመቆጣጠር እንደ በቀቀን እየደጋገሙ ከሚቀፈቅፉት ነጭ ውሸታቸው እውነትን የሚፈበርኩ ይመስላቸዋል፡፡ ነጻውን ፕሬስ አፈር ድሜ በማብላት ሁሉንም ህዝብ ሁልጊዜ ማሞኘት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን “እውነት ለዘላለም ተቀብራ እንደማትቀር እና ግፈኞችም በጉልበት ነጥቀው በያዙት የስልጣን ዙፋን ወንበር ላይ ለዘላለም ተጣብቀው እንደማይቆዩበት ድንጋይ በሆነው ልባቸው ያውቁታል፡፡“ ሁልጊዜም ስልጣናቸውን የሚያጡ እየመሰላቸው እለት በእለት የውሸት ድሪቷቸውን እየደረቱ ኑሮ አድርገው ይዘውታል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቆ የሚገኘው አረመኔ አምባገነን ገዥ ከብዙ ዓመታት በፊት ናፖሊዮን ተጋፍጦት የነበረውን ዓይነት ሁኔታ ተጋፍጦ ይገኛል፡፡ “ጋዜጠኛ የህዝቡን እሮሮ የሚያሰማ፣ ስህተትን አራሚ፣ ምክርን የሚለግስ፣ የሉዓላዊነት ወኪል እና የአገሮች መምህር ነው፡፡“ ጋዜጠኛ “አገርን የሚያስተምር” ነው፣ መረጃን ለህዝብ የሚሰጥ ነው፣ ህዝቡን በእውቀት የማነጽ እና የማስተማር ኃላፊነት አለው፡፡ እንግዲህ እነዚህ እውነታዎች ነበሩ ናፖሊዮን ነጻውን ፕሬስ እንዲፈሩት ያስገደዳቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል የናፖሊዮንን አምባገነናዊ አገዛዝ ትርጉም ባለው መልኩ እንደሚያጋልጠው እና በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂ እንደሚያደርገው ናፖሊዮን ይገነዘቡ ነበር፡፡ ናፖሊዮን የፈረንሳይን ህዝብ ለማስፈራራት በማሰብ መጠነ ሰፊ የሆነውን የስለላ መረባቸውን በመዘርጋት ሲያካሂዱት የነበረውን ስለላ ሲያጋልጡ የነበሩትን ጋዜጠኞች ለማስፈራራት፣ በእስር ቤት ለማጎር፣ በስራዎቻቸው ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እና አንደበታቸውን ለመሸበብ ጊዜ አላባከኑም፡፡ ነጻው ፕሬስ የናፖሊዮን ወታደራዊ እቅድ መክሸፉን አጋልጧል፡፡ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ማንንም ሳይለይ በጅምላ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተካሄዱትን ጭፍጨፋዎች እና የእርሳቸው የፖለቲካ ተቀናቃኝ በሆኑት ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ የተካሄደውን እስራት፣ ማሰቃየት እና ግድያ አውግዟል፡፡ በኢትዮጵያ እንደ መዥገር በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው የሚገኙት አምባገነኖች በናፖሊዮን ቅዠት በመውደቅ በተመሳሳይ መልኩ ወጣት ጦማሪያንን እና የነጻው ፕሬስ አባላትን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፡፡ እውነታውን በመፍራት እንቅልፋቸውን አጥተው በነጭ ላብ ተዘፍቀው ያድራሉ!
የኢትዮጵያ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ልዩ የኢትዮጵያ ጀግናዎች እና ጀግኒቶች ናቸው፡፡ የእውነት ተናጋሪ ተዋጊዎች ናቸው፡፡ አረመኔ አምባገነኖችን በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይዋጋሉ፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ጥይቶች እውነት፣ ቃላት፣ ሀሳቦች፣ እውነታዎች እና እምነቶች ብቻ ናቸው፡፡ የተንሰራፉትን ውሸቶች በእውነት ጎራዴ ይከትፏቸዋል፡፡ መጥፎ እና መሰሪ ሀሳቦችን በጥሩ ሀሳቦች ያሳድዷቸዋል፣ እናም ያረጁ እና ያፈጁ፣ እንዲሁም የጃጁ፣ እና የበከቱ አሮጌ አስተሳሰቦችን በአዲስ እና ተራማጅ በሆኑ አስተሳሰቦች ለመተካት የማስተማር ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የህዝቦችን ተስፋቢስነት በመዋጋት በተስፋ ቃላት ያለመልማሉ፡፡ ፍርሀት በጀግንነት እና በደፋርነት ድል እንደሚመታ ለህዝቡ ያስተምራሉ፡፡ ድንቁርናን እና ኃይለኛ ደንቆሮዎችን በእውቀት እና በምክንያታዊነት ይዋጋሉ፡፡ በእብሪት እና ትእቢት ለተወጠሩት የገዥው አካል አባላት በሰለጠነ መልኩ ለማስተማር እና ለማግባባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ትዕግስትየለሽነትን በታጋሽነት፣ ጭቆናን ከመሸከም በጽናት ታግሎ በማስወገድ እና በጥርጣሬ ከመሸነፍ በሙሉ እምነት አሳድሮ ድል በመምታት ለመቀየር ይፈልጋሉ፡፡ የህዝቡን ልብ እና አእምሮ ለመያዝ በሚደረገው የትግል አውድ እንደ ወሮበላው የገዥ አካል ስብስብ በተራ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እና በኃይል በጉልበት ጨፍልቆ ለመያዝ ሳይሆን እውነታውን እና እውነቱን ብቻ ለወገኖቻቸው በማሳየት በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይታገላሉ፡፡
ክህደት፣ ውሸት እና ፍርሀት በተንሰራፋባት ምድር ላይ መኖር፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እውነት ውሸት በሆነባት፣ እውነት በእየለቱ በምትደመሰስባት እና ሸፍጠኛ አታላዮች በፍርሀት ተዘፍቀው የሚኖሩባት የእራሳቸውን ምድር ፈጥረዋል፡፡ ገዥው አካል እንዲህ የሚለውን የካርቴሲያንን መርህ አዛብቷል፣ “በኛ አስተሳሰብ ብቻ ነገሮች ሁሉ ህልውና ይኖራቸዋል ወይም ደግሞ ህልውና አልባ ይሆናሉ“፡፡ መለስ ዜናዊ የክህደት አለቃ ነበር፡፡ ሁልጊዜ በሱ የማጎሪያ አስር ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት ሽምጥጥ በማድረግ ይክድ ነበር፣ እንዲህ በማለት፣ “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም፡፡ በእስር ቤት ያሉት አመጸኞች እና አሸባሪዎች ናቸው፡፡ እናም በእስር ቤቶቻችን የፖለቲከ እስረኞች አሉ ብሎ ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው ምክንያቱም የፖለቲካ እስረኞች አይደሉምና፡፡ በሱ የንጉስነት ወቅት ምንም ዓይነት ረሀብ እና ቸነፈር እንዳልነበረ ሙልጭ አድርገው በመካድ እንዲህ ብሎ ነበር፣ በጣም ጥቂት የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ በምግብ እጥረት ጉዳት የደረሰባቸው በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የወረዳ ኪስ ቦታዎች እና በሶማሊ ክልል አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ብቻ ነው የነበሩት በማለት ዓይኔን ላፈር ብለዋል፡፡ በአገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ያፈጠጠ እና ያገጠጠ እውነታ ሙልጭ አድርገው በመካድ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት የለም“ ብለዋል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በማሰብ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኦጋዴን አካባቢ መንደሮችን አቃጥለዋል እየተባለ ውንጀላ ቀርቦብናል፡፡ ሆኖም ግን በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፤ ኑስ አንድ መንደር እንኳ አልተቃጠለም፡፡ እናም እኔ እስከማውቀው ድረስ አንዲት ጎጆ አልተቃጠለችም፡፡ እኛ እየተከሰስን ያለነው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቀድሞ ከነበሩባቸው መንደሮች በማንቀሳቀስ ወደ መጠለያ ካምፖች በማስገባታችን ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅንጣት መረጃ ሊቀርብ አይችልም“ ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ የሳይንስ እድገት ማህበር/American Association for the Advancement of Science በኦጋዴን መንደሮች ላይ የተካሄደውን የጅምላ የመንደሮች ማቃጠል ወንጀል በሳቴላይት ምስሎች የተረጋገጠው እውነታ ለመለስ ምድር ምናባዊ ህይወት ምንም አይደለም፡፡ አደናጋሪ የፕሬስ ህግ አዋጅ በማውጣት በደርዘን የሚቆጠሩ ምርጥ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለእስር እና ግዞት ሲዳረጉ የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ በሀሰት በነተበው አንደበታቸው መልሰው “ከዓለም የተሻለ ምርጥ የፕሬስ ህግ” በማለት ያደናግራሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የተካሄደውን አገር አቀፋዊ “ምርጫ” ተከትሎ መለስ ፓርቲው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ያሸነፈ መሆኑን በኩራት ተናግሮ ነበር፣ ምክንያቱም ህዝቡ ፓርቲያቸውን የሚወደው ስለሆነ ነው በማለት አፋቸውን ሞልተው ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ የኦርዌላን/Orwellian የእንስሳት ትረካ ዓይነት እውነታን የሚያራምድ ሰው ነበር፡፡ ውሸቱን ለመንዛት ሲፈልግ “የፖለቲካ ቋንቋን በመጠቀም የለየለትን ነጭ ውሸት እውነት እንዲመስል አድርገው በማቅረብ፣ ግድያ መፈጸም ወንጀል እና የስነምግባር ዝቅጠት መሆኑ ቀርቶ የሚያስከብር እንደሆነ አድርገው በማቅረብ ነጩን ውሸት የእውነት ቅርጽን እንዲላበስ አድርገው በማስመሰል የማቅረብ የባዶ ብልጣብለጥነት አካሄድ መንገድን ይጠቀሙ ነበር፡፡”
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጠው አገሪቱን እያተራመሱ በመግዛት ላይ ስለሚገኙት ስብስቦች አንድ የማይካድ ሀቅ አለ፡፡ ሁሉም በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ ያገጠጠውን እና ያፈጠጠውን እውነታ አየፈሩ ነው በመኖር ላይ ያሉት፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል እውነታውን የሚያጋልጥ ስለሆነ የነጻውን ፕሬስ ኃይል በመፍራት ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ በአንድ ወቅት የእነርሱ የአመለካከት ፍልስፍና አለቃ ቁንጮ የነበሩት ቪላድሚር ሌኒን አንዳለው “የመናገር ነጻነት እና የፕሬስ ነጻነት ለምንድን ነው የሚፈቀደው? ለምንድን ነው መንግስት ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሲሰራ ትችት እንዲቀርብበት የሚፈቅደው? ተቃዋሚዎችን የጠላት መሳሪያ እንዲሆኑ መንግስት መፍቀድ የለበትም፣ ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ የገዳይነት ባህሪ አላቸው፡፡ ለምንድን ነው ማንም ሰው የማተሚያ ቤት እንዲገዛ እና የሚቀርቡ ሀሳቦችን አትሞ በማሰራጨት በስልጣን ላያ ያለውን መንግስት በተቀነባበረ ስሌት ለመተቸት እና ለማሳፈር እንዲችል የሚፈቀደው?“ ፡፡
እውነታውን በሚገባ ያውቁታል ምክንያቱም እውነታው ህዝቡን ነጻ እንዲሆንያ ደርገዋል፡፡ ነጻነትን ይፈራሉ ምክንያቱም አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ፡፡ አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ ምክንያቱም ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ነጻ የሆነ ህዝብ የእውነትን ጥሩር ታጥቆ የሀሳብ ነጻነትን ተጎናጽፎ በእራሱ ፈቃድ የእራሱን የመንግስት ዓይነት ለመመስረት ሙሉ ነጻነት አለው፡፡
በኢትዮጵያ ላይ ስላለው ገዥ አካል ያለው እውነታ ምንድን ነው? እውነታው በሰው ልጆች ላይ ግፍን የፈጸሙ ወንጀለኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ህጋዊነት የላቸውም፡፡ በጠብመንጃ ኃይል በጉልበት በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙ አምባገነኖች ናቸው፣ ምርጫዎችን በመስረቅ እና በመዝረፍ ተመርጠናል እያሉ በማታለል ተክነዋል፣ በጥልቅ የሙስና ማእበል ውስጥ ተዘፍቀው የአገሪቱን ሀብት በማውደም ላይ ይገኛሉ፣ ስልጣናቸውን በህገወጥ መንገድ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፣ የህግ የበላይነትን በመደፍጠጥ በጫካው ህግ የሚገዙ ህገወጦች ሆነዋል፣ እውነታው ሲታይ በአጠቃላይ በሸፍጥ የታወሩ የጫካውን አስተዳደር ወደ መንግስታዊ አስተዳደርነት አዙረው ህዝብን በማተራመስ ላይ የሚገኙ የስግብግብ ወሮበላ ቡድን ስብሰቦች ናቸው፡፡ እውነታው በአጠቃላይ ሲታይ የአፍሪካን የጨካኝ ዘራፊነት ስርዓት በሀገራችን ላይ የሚተገብሩ ወሮበላ ዘራፊዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን ይፈራሉ ምክንያቱም እነዚህ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪዎች አምባገነኖቹ የሚሰሯቸውን ወንጀሎች እና ሙስናዎች፣ የመከኑ እና የወደቁ ፖሊሲዎቻቸውን፣ የአቅም ድሁርነታቸውን እና ድንቁርናቸውን በማጋለጥ እውነታውን ያወጡባቸዋል፡፡ እነዚህ ጭራቃዊ ፍጡሮች በጫማቸው ስር እረግጠው የያዟቸው የግፍ ሰለባዎች ነጻ ቅዱስነት እና የያዙት ጸበል ስለሚያቃዣቸው ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን አጥብቀው ይፈራሉ፡፡ በያዙት ሁሉ ኃይል በመጠቀም እውነቱ ወጥቶ ለህዝብ እንዳይደርስ እና እንዳይታወቅባቸው ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡ የሳቴላይት ስርጭቶችን ሳይቀር አፍነዋል፣ የኢንተርኔት ግንኙነቶችን አቋርጠዋል፣ ጋዜጦችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን በእየእስር ቤቶች አጉረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የአረብሳት ለዓለም አቀፉ የግንኙነት ህብረት/International Communication Union እና ለአረብ ሊግ/Arab League ኢትዮጵያ ስርጭቱን ያፈነች መሆኗን እና “ወንጀለኛውን ለመቅጣት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ” እና በዚህ ህገወጥ ድርጊት ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ወይም በዚህ ህገወጥ የአፈና ተግባር ምክንያት ወደፊት ለሚደርስ ማንኛውም አደጋ ተገቢውን ካሳ እንድትከፍል እንዲደረግ ተማጽዕኖውን አቅርቧል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ገዥው አካል በገበያ ላይ የቀሩትን እና በገዥው አካል ላይ ጠንካራ ጥችት የሚያቀርቡትን ጥቂት ጋዜጦች በየመንገዶች እያዞሩ የሚሸጡትን ጋዜጣ አዟሪዎችን እያሳደደ፣ እያስፈራራ እና በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል፡፡
እውነታው በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ ከመግለጽ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እየተካሄደ ላለው ጭቆና እና አፈና የቻይናዎች ስውር እጆች ያሉበት መሆኑ ነው፡፡ ቻይናዎች ለገዥው አካል የማፈኛ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ማቅረብ ብቻ አይደለም የሚያከናውኑት፡፡ ሆኖም ግን ለተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ለኢንተርኔት አገልግሎት የመሰረተ ልማት ስራዎችም ግንባር ቀደም ተዋንያን ናቸው፡፡ የመረጃ ፍሰት ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እና ወደ ኢትዮጵያም እንዳይገባ ለመገደብ እና ለማቋረጥ የአንድ መስኮት ፈጣን የአግልግሎት መስጫ ኪቶችን ይዘዋል፡፡ ከዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ በፊት የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄላሪ ክሊንተን ዛምቢያን በመጎብኘት ላይ ሳሉ የቻይናውያን በአፍሪካ አህጉር ላይ ያላቸውን ሚና በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “በቅኝ ግዛት ዘመን ጊዜ መምጣት እና ለመሪዎቹ ገንዘብ በመስጠት የተፈጥሮ ሀብቶችን ከአፍሪካ መውሰድ ቀላል ነበር፣ በምትለቅቅበት ጊዜ እዚህ ላለው ህዝብ ምንም ነገር ትተህ አትወጣም፣ በአሁኑ ጊዜ አዲስ ቅኝ ተገዥነት በአፍሪካ ማየት አንፈልግም“ ብለው ነበር፡፡ እውነታው ግን ቻይናውያን በኢትዮጵያ መቆየታቸው እና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መያዛቸው ብቻ ሳይሆን ለገዥው አካል የቴክኒክ እገዛ በመስጠት፣ የኦዲዮ እና ቪዲዮ መሳሪያዎችን በማቅረብ የመረጃ ምርመራ በማድረግ እና በኤሌክትሮኒክ መገናኛ ብዙሀን ላይ አፈናዎችን በማካሄድ ነጻ አሰተሳሰብን በመጨቆን በዋናነት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ነጻነትን ይፈራሉ፡፡ ነጻነት ምንድን ነው? የሁሉም የሰው ልጆች ነጻነቶች ባህሪያት ከፍርህት የሚገኙ ነጻነቶች ናቸው፡፡ በተግባራዊ ሁኔታ ሲታይ አንድ ሰው ያሰበውን ለመናገር መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ደስ ያለውን መጻፍ መፍራት ወይም በአንድ ሀሳብ ማለትም ሀይማኖት ወይም ፍልስፍና ላይ ማመን እና አለማመንን መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ከመረጠው ሰው ጋር አብሮ መገናኘት መፍራት ማለት አይደለም፡፡ ዋናው እና የመጨረሻው የሰው ልጅ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባው ህዝቡ እራሱ ስልጣን የሰጣቸው በስልጣን ወንበር ላይ ያሉት ሰዎች ናቸው በህብረተሰቡ የኑሮ ሂደት ላይ መፍራት እና ህዝቡን ማክበር ያለባቸው፡፡
ሀሳብን ይፈራሉ፡፡ “ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ ገዳዮች ናቸው“ በማለት ሌኒን አስጠንቅቀዋል፡፡ ሀሳቦች ሳይንስን፣ ፖለቲካን እና ማናቸውንም የሰው ልጅ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ሁሉ የመለወጥ ኃይል አላቸው፡፡ ከምንም በላይ ዓለም ጠፍጣፋ አይደለችም፡፡ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያሉ ገዥዎች የአዲስ ጠፍጣፋ መሬት ባለቤቶች ናቸው፡፡ እንደ ጥንቱ ንጉሶች፣ ዛሮች፣ እና ማሃራጃሆዎች ሆነው ከህዝቡ ፈቃድ ውጭ ( በተሰረቀ ስምምነት) መሰረት መግዛት ይፈልጋሉ፡፡ ጥቂት ሞራላዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሀሳቦች ሲኖሯቸው ነገሮችን በቀላሉ ለመገንዘብ እና አዳዲስ ሀሳቦችንም ለማድነቅ እና ተቀብሎ ወደ ተግባር ለማዋል የምሁርነት አቅሙ የሌላቸው የመንፈስ የአስተሳሰብ ድሁሮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን የጎሳ ክፍፍልን ለማራመድ፣ ስግብግብነት እና ጥላቻን ለማምጣት፣ የጥላቻ ከባቢን የመፍጠር፣ ግጭትን የመጫር፣ ሙስናን ለማስፋፋት እና ለማጠናከር፣ ህብረትን በመናድና የጥላቻ መንፈስን በመዝራት እንዲሁም በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እና አለመተማመን እንዲነግስ በማድረግ ጭንቅላቶቻቸው ዋና የዲያብሎሳዊነት ቤተሙከራዎች ናቸው፡፡ ህዝብን ሊያስተባብሩ እና ሊያፋቅሩ የሚችሉ ሀሳቦችን ለማመንጨት፣ በጎሳዎች መካከል ፍቅርን የማስፈን፣ ብሄራዊ አንድነትን የማምጣት፣ የጋራ መግባባትን የመፍጠር፣ የጓዳዊነት መንፈስ የማጠናከር እና እምነትን የማራመድ አቅመቢሶች ናቸው፡፡
አዳዲስ ሀሳቦችን የሚፈሩ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቆናጥጠው የሚገኙ አምባገነኖች የአዲስ ሀሳብ አመንጭ እና ባለራዕይ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፡፡ ህዝቡ እና ዓለም ወደፊት ጥሩ ነገር የሚያስቡ መልካም ነገር አላሚዎችና ፈጣሪዎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲመለከታቸው እና እምነት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን በህልም የቅዠት ፍርሀት ተዘፍቆ ያለ ማንም ሰው መልካም አላሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ባለራዕይ መሪዎች ለሚያደርጓቸው ማለትም ታማኝነት፣ ኃላፊነትነትን የመሸከም ብቃት፣ ሌሎችን አነቃቅቶ እና አሳምኖ በስራ የማሳተፍ ችሎታ፣ ያለፉትን ስህተቶች በግዴለሽነት እንዳሉ ከመድገም ይልቅ ከስህተት እና ከውድቀት መማርን፣ ስህተት በሚሰሩበት ጊዜ ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ መጠየቅን፣ ግልጽነት፣ ትክክለኛውን ነገር ለመስራት ፍትሀዊነት እና በፍቅር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከመገኘት ተግባራት ጋር ሁሉ አይተዋወቁም፡፡ መጥፎ እና ዕኩይ ተግባራትን ለማድረግ ፍቅር ያላቸው መሰሪ መሪዎች ናቸው፡፡ ኪሶቻቸውን የሚወጥሩትን የተዘረፉ በርካታ ገንዘቦችን ዓይኖቻቸው በቀላሉ ማየት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን አሁን እየፈጸሟቸው ያሏቸው በርካታ ወንጀሎች በዘለቂነት ለወደፊት ሊያስከትሉት የሚችሏቸውን እንደምታዎች ለማየት የታወሩ ናቸው፡፡ ጠንካራን ሀሳብ ጊዜው እየመጣ ያለውን ሀሳብ የሚያቆመው ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት የሚያደርገውን ተጋድሎ የሚያቆመው ኃይል የለም፡፡ አንዴ ከተጀመረ በመንገዱ ላይ ያለውን ጋሬጣ ሁሉ እየጠራረገ ወደፊት ይገሰግሳል፡፡
ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ለውጥ ምንድን ነው? ለውጥ በሁሉም ነገር የሚከሰተውን የዕድገት እና የመበስበስ ዓለም አቀፋዊ ዘላለማዊ የለውጥ ህግ የሚገዛ ሂደት ነው፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ለውጥን አጥብቆ ይፈራል ምክንያቱም በህበረተሰቡ ላይ ያላቸውን የኢኮኖሚ እና የፖሎቲካ የበላይነት ቦታ ስለሚያሳጣቸው ነው፡፡ ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱትን ማናቸውንም ሙከራ ሁሉ ይደመስሳሉ፡፡ ከዚህ አንጻር “በሰላማዊ መንገድ የለውጥ አብዮት እንዳይመጣ የሚከለክሉ ሁሉ የአመጽ ለውጥ በኃይል እንዲመጣ ይገደዳሉ“ የሚለውን ሀቅ ለመገንዘብ የተሳናቸው ይመስላል፡፡
በፖለቲካ ህጋዊነት ማጣት እና በመንግስት አቅም ማጣት ምክንያት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ መበስበስ የመጨረሻ ጠርዝ ላይ ያለችበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ የጨነገፈ መንግስት ሆናለች፡፡ ባለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት የጎሳ ክፍፍል ፖሊሲ (የጎሳ ፌዴራሊዝም) “ልማታዊ መንግስት” ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዘገብን በማለት የሚራገበው እርባናየለሽ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም እንኳ ኢትዮጵያን በሁለት አማራጮች ላይ ጥሏታል፡፡ የእነርሱ ነጭ ውሸት ብቻ ነው በባሁለት እና በባለሶስት አሀዝ እድገት ያስመዘገበው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ እንደተባበረች ሀገር አንድ ሆና ወደፊት ትገሰግሳለች ወይም ደግሞ ወደተለያዩ ትናንሽ የተበጣጠሱ ክልሎች ትገነጣጠላለች፡፡ የአፓርታይድ ዓይነት ባንቱስታንስ በኢትዮጵያ ክልል እየተባለ በዘር እና በቋንቋ የተቀየደ የአገዛዝ ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተበጣጠሱ ግዛቶች ስብስብ የምትሆን ከሆነ የመጀመሪያው ቸግር ቀማሽ የሚሆኑት አሁን በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ገዥው አካል፣ የእነርሱ ጋሻጃግሬዎች እና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ በፖቲካ ስልጣን ማጣት ብቻ የሚቆም ሳይሆን ቢያንስ እስከ አሁን ድረስ በአገር ውስጥ የሚደረግ ለውጥ ዘግይቶ እንደደረሰ ባቡር ይቆጠራል፡፡ በምስራቅ አውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅ ሲነፍስ የነበረው የለውጥ ነፋስ ያለምንም ጥርጥር በኢትዮጵያም መንፈሱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛ ጥያቄ ግን እነዚህ ነፋሶች ተስማሚ እና በሰላም የሚያልፉ ወይስ ደግሞ ሁሉንም ነገር እየገነደሱ እና እየቦደሱ የሚጥሉ ኃይለኛ የሁሪኬን/hurricane-force ሞገዶች ይሆናሉ የሚለው ነው፡፡
እውነት ነጻ ያወጣሀል ነጻ አስከሆንክ ድረስ ሆኖም ግን ነጻ ያልሆኑት ይሰቃያሉ፣
“እውነት ነፃ ታወጣሀለች” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ነጻነት እና ፍርሀት ለእየራሳቸው ተነጥለው የሚኖሩ ናቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ እና ጦማሪያን ብቸኛው ተግባራቸው እንዳዩት እውነታውን ወዲያውኑ መናገር ነው፡፡ ስለ እውነታው ያላቸውን ሀሳብ የለምንም ፍርሀት የመግለጽ ነጻነት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ህዝቡ እውነታውን ቀድሞም ቢሆን ያውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች የሚለው ነጭ ውሸት ቢሆንም ህዝቦች እውነታውን ያውቁታል፡፡ የሚበላ በቂ ምግብ እንደሌለ ያውቃሉ፣ እናም ሚሊዮኖች በየቀኑ እየተራቡ እንዳሉ ያውቃሉ፡፡ እንዲሁም በቂ የውኃ አገልግሎት ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሌለ ያውቃሉ፡፡ አናሳ የህክምና አገልግሎት ነው እየተሰጠ ያለው፣ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት አያገኙም እናም ስራ አጦች ናቸው፡፡ ገዥው አካል በሙስና ማጥ ውስጥ የተዘፈቀ እና የበከተ ነው፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ይፈጽማል፡፡ ህዝቦች በግልጽ የአየር ድባብ ውስጥ እስረኛ ሆነው እንደሚኖሩ ያውቃሉ፡፡
የነጻ ጋዜጠኞች እና የጦማሪዎች ወንጀል የሚያውቁትን ነገር ለማያውቁት ወገኖቻቸው መግለጻቸው ብቻ ነው፡፡ የእነርሱ ወንጀል የማዕድን ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች እየቆፈሩ በማውጣት ማስረጃ በማቅረባቸው ነው፡፡ ለዚህም በስልጣን ላያ ያለው ገዥ አካል እየፈራቸው ያለው፡፡ ገዥው አካል እውነታው ሳይታወቅ ተቀብሮ እንዲቀር እና እንዲረሳ ይፈልጋል፡፡ ገዥው አካል እውነታው እንዳይታወቅ በመደበቅ፣ እውነት ተናጋሪዎችንም ጸጥ በማስደረግ እና በየእስር ቤቶች በማጎር ለዘላለም ጸጥ በማድረግ ትንፍሽ እንዳይሉ በማድረግ እውነትን የመግደል እምነት አለው፡፡ ጆርጅ ኦርዌል እንደጠቆሙት፣ ”የማጨበርበር እና የሀሰት ሸፍጥ በተንሰራፋበት ጊዜ እውነትን መናገር አብዮተኛነት ድርጊት ነው“ ብለው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ጦማሪያን የኢትዮጵያ የማይበገሩ አብዮተኞች ናቸው፡፡
ፍርሀትን በብዙሀን መገናኛ እንደ መሳሪያ መጠቀም፣
በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ዋና ድክመትን እንደ ትልቅ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል፡፡ ህዝብን ግራ ለማጋባት፣ እርስ በእርስ ለመከፋፈል፣ ለማታለል፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ሀሳብን ከዋናው ጉዳይ አቅጣጫውን ለማስቀየስ ፍርሀትን በዋና መሳሪያነት ይጠቀምበታል፡፡ ማቋረጫ የሌለው የፍርሀት ዘመቻ በህብረተሰቡ ላይ ለመንዛት ሲፈልግ፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ለማጠልሸት ሲፈልግ በህዝብ የግብር መዋጮ የሚተዳደረውን መገናኛ ብዙሀን ለእኩይ ምግባር ሌት ቀን ይጠቀማል፡፡ ገዥውን አካል የሚቃወሙትን ቡድኖች እና ግለሰቦች ጸጥ ለማድረግ ሲፈልግ እርባናየለሽ በውሸት ላይ ተመስርተው የተቀነባበሩ ዘጋቢ ፊልሞችን በመፈብረክ “አሸባሪ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በአሰልችው የመገናኛ ብዙሀን እንደበቀቀን ይደጋግማቸዋል፡፡ የውሸት ሸፍጥ በታጨቀበት እና ለመስማት እና ለማየትም አስቀያሚ በሆነው “አኬልዳማ” ብሎ በሰየመው ለምንም የማይውል እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ በዲያስፖራው ተቃዋሚ ኃይል እና በአገር ውስጥ ባሉ የእነርሱ የግብር ተመሳሳዮች አማካይነት እንዲሁም ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ትብብር እና ርብርብ አደገኛ የሽብር አደጋ ተደቅኖባት እንደሚገኝ አደንቋሪ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡ “አኬልዳማ” በዓለም ላይ የተደረጉትን በጣም አስፈሪ እና አስቀያሚ ምስሎችን ሁሉ ለቃቅሞ በቪዲዮ በማሳየት በቅርቡ በህይወት የተለዩት አቶ መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎቻቸውን ጥላሸት በመቀባትና በሶማሌ የሚንቀሳቀሰው የአልቃይዳ እና አልሻባብ ቅጥረኞች ናቸው ብለው በአሸባሪነት በመፈረጅ የጥቃት ብቀላቸውን በንጹሁነ ዜጎች ላይ በሰፊው ተግብረውታል፡፡
በሌላ “ጅሃዳዊ ሀራካት” በተባለ እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም በክርስቲያን እና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ፍርሀት እና ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ጸረ እስልምና እሳትን የመጫር ሙከራ አድርገው በህዝቡ አርቆ አስተዋይነት እና የንቃት ደረጃ ምክንያት እኩይ ምግባራቸው ሳይሳካ መክኖ ቀርቷል፡፡ ለዘመናት አብሮ እና ተከባብሮ እየኖረ ያለውን የክርስቲያን እና የሙሰሊም ማህበረሰቡን በማጋጨት የእስልምና አሸባሪዎች በድብቅ ጅሀዳዊ መንግስት ለመመስረት ዕቅድ አውጥተው ተንቀሳቅሰዋል በማለት በሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች እምነት ተከታዮች መካከል የማያባራ እልቂት እና የደም ጎርፍን ለማዝነብ የታቀደ ዲያብሎሳዊ የድርጊት ዕቅድ ነድፈው ነበር፡፡ አሁንም ህዝቡ የነቃባቸው እና ከእነርሱ እኩይ አስተሳሰብ ውጭ የመጠቀ ሀሳብ ስላለው እና ስላወቀባቸው ዕቅዳቸው አሁንም መክኖ ቀርቷል፡፡
ፍርሀት እና ጥላቻን በህዝቡ ውስጥ ለማስፋፋት እና ምናባዊ የሆነ የዘር እና የጎሳ እልቂት እንዲሁም የኃይማኖት ጽንፈኝነት እልቂት እንደሚከሰት በመስበክ ይህንንም እልቂት ለማስወገድ ብቸኛ ቅዱሶች እነርሱ እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ እና በማደናገር ጸረ ኢትዮጵያ እና ዘረኛ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ጎጠኞች መሆናቸውን በአደባባይ አስመስክረዋል፡፡ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ አንዱን ጎሳ በሌላው ላይ በማስነሳት ለማጋጨት ሌት ቀን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ “የጎሳ ፌዴራሊዝም/ethnic federalism” በሚል እኩይ ስልት የዘር ማጽዳት ዘመቻቸውን ቀጥለውበታል፡፡ የጎሳ ጥላቻን ለመቀስቀስ ታሪካዊ ብሶቶችን እየፈበረኩ እና ጥቃቅን ነገሮችን እያጋነኑ በህዝቡ ዘንድ አለመተማመን እና ግጭቶች እንዲነሱ አበርትተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝቡ ግን ስለነቃባቸው በባዶነታቸው ቀልበቢስ በመሆን እንደ አበደ ውሻ ከወዲያ ወዲህ በመቅበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ የእራሳቸውን ፍርሀት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ህዝቡን ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ትንታግ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ላይ የተከፈተው ጦርነት በእራሷ በእውነት ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፣
በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በጦማሪያን ላይ ያወጀው ጦርነት በእውነት በእራሷ ላይ ያወጀው ጦርነት ነው፡፡ ገዥው አካል ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት በተደረጉት ጦርነነቶች እና ግጭቶች ሁሉ በድል አድራጊነት ተወጥቷል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ጎራዴ እና ኤኬ 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃዎችን በታጠቁ አምባገነኖች እና ብዕሮች እና የኮምፒውተር ኪቦርዶችን በሚጠቀሙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መካከል የሚደረገው ወሳኙ ፍልሚያ ተቃርቧል፡፡ ያ ጦርነት እና ፍልሚያ በኢትዮጵያውያን/ት ልብ እና አእምሮ ውስጥ ሰርጾ ሁሉንም ዜጎች ለወሳኙ ፍልሚያ እና ለድል ጉዞ ጥርጊያ መንገዱን የሚያመቻች ይሆናል፡፡ የዚያ ጦርነት እና ፍልሚያ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ቢኖር ፍልሚያው የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል፡፡ በእርግጥ ያ ጦርነት በእውነት አራማጅ ወገኖች አሸናፊነት እንደተደመደመ እምነት አለኝ፡፡ ኤድዋርድ ቡልዌር ሊቶን የተባሉት ገጣሚ በትክክል እንዳስቀመጡት ጎራዴ በታጠቁት እና ብዕርን በጨበጡት ተዋጊዎች መካከል በሚደረግ የጦርነት ፍልሚያ በመጨረሻ ሁልጊዜ የወሳኙ ድል ባለቤት የሚሆኑት ብዕርን የጨበጡት ናቸው፡፡
እውነትን ጨብጠዋልና!
እውነት፣ ይህ!
ከሰዎች አገዛዝ ስር ሌላ ታላቅ ነገር አለ፣
ብዕር ከጎራዴ የበለጠ ኃይል አለው፡፡ አስተውል/ይ
ቀስት ተሸካሚዎች ይፈነድቃሉ፣ ግን ምንም የሚመጣ ነገር የለም!-
ልዩ ታምር ከጌታቸው እጀ ይቀበላሉ፣
እናም ቄሳሮችን በድን ለማድረግ ያምጻሉ
ታላቋ መሬት ትንፋሽ ያጥራታል!- ጎራዴውን ከዚህ ወዲያ ውሰዱ-
መንግስታት ከእርሱ ውጭ ሊጠበቁ ይችላሉና!
ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል ማዳን ወይስ ደግሞ የኢትዮጵያን ነጻ ፕሬስ እና ጦማሪያንን ማዳን የሚል ወሳኝ ጥያቄ ቢቀርብልኝ ቶማስ ጃፈርሰን እንደመረጡት ሁሉ እኔም የኋለኛውን ማዳን የሚለው እንዲጠበቅልኝ እመርጣለሁ፡፡ ቶማስ ጃፈርሰን እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው የሚከተለውን መልስ ሰጥተው ነበር፣ ”የእኛ መንግስት መሰረቱ የህዝብ ሀሳብ እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያው ዓላማ መሆን ያለበት ያንን መብት ማስከበር ነው፡፡ እናም ጋዜጦች የሌሉበት መንግስት ከሚኖር ወይም ደግሞ መንግስት በሌለበት ጋዜጦች ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ስል ማንኛውም ሰው እነዚህን ጋዜጦች መቀበል እና ማንበብ መቻል አለበት፡፡“
በተመሳሳይ መልኩ ለእኔም ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የሌሉበት ገዥ አካል ከሚኖር ወይም ደግሞ ገዥ አካል በሌለበት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ከሁሉም በላይ ለዓላማ በጽናት የቆምኩ፣ ለምሰራው ትክክለኛ ስራ ሁሉ ኩራት የሚሰማኝ፣ ላመንኩበት ዓላማ ከልብ እና በወኔ የቆምኩ፣ ዓላማየን ለማስፈጸም በከባድ እርምጃ ወደፊት የምገሰግስ፣ ላልሰራሁት ወንጀል ይቅርታን የማልጠይቅ፣ በምሰራው ስራ ሁሉ የማላፍር፣ ቆራጥ እና የማያወላውል ባህሪን የተላበስኩ የኢትዮጵያ ጦማሪ ነኝ!!!
ኃይል ለነጻ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ጦማሪያን!
ውድቀት እና ዉርደት ህዘብን በጠብመንጃ ኃይል አስገድደው ለመግዛት ለተነሱ የዕኩይ ምግባር አራማጆች!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!