Washington Post Editorial
“AFRICA DOESN’T need strongmen, it needs strong institutions.” Those were President Obama’s words when he addressed Ghana’s parliament in July 2009, during his first trip to sub-Saharan Africa as president. The historic speech, watched around the globe, was an optimistic clarion call to the leaders on the continent from the son of a Kenyan. “First, we must support strong and sustainable democratic governments,” Mr. Obama said.
The president seems to have forgotten that speech. Last week, the White House announced that, while traveling to Kenya next month, Mr. Obama also will stop in Ethiopia, the first such visit by a sitting U.S. president to the country of 94 million. It’s almost unfathomable that he would make time for an entrenched human rights abuser such as Ethiopia while cold-shouldering the nation that just witnessed a historic, peaceful, democratic change of power: Nigeria.
Administration officials justify the trip by citing the United States’ long-standing cooperation with Ethiopia on issues of regional security and the country’s accelerating economic growth. Ethiopia is a major recipient of U.S. development assistance, and the African Union has its headquarters there. But it also stands out in Africa for its increasingly harsh repression and its escalating chokehold on independent media and political dissent. Since June 2014, 34 journalists have been forced to flee the country, according to the Committee to Protect Journalists. Ethiopia is also one of the world’s leading jailers of journalists.
Saturday, June 27, 2015
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ከሰነዓ አለም አቀፍ አውሮፓላን ጣቢያ ታፍነው ከተወሰዱ በዛሬው ዕለት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ. ም፣ አንድ ዓመት ይሞላቸዋል። የወያኔ አረመኔዎች ይህን ዓይነት የውንብድና ተግባር ሲፈጽሙ በከፍተኛ ደረጃ ያሰሉት፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማፈን፣ ንቅናቄው ብሎም ሕዝቡ፣ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት፣ የሚያደርገውን ትግል ለማዳከምና ከተቻለም ደግሞ ለማጥፋት እንደሆነ፣ ምንም የማያጠራጥር ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ የወያኔዎች ስሌት በምን ያህል ትክክል ነበር ?
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ፣ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸመው የውንብድና አፈና ተግባር፣ ንቅናቄያችን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባለው ሕዝብ ልብ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ሌላው ቀርቶ ከአፈናው በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ንቅናቄያችንን በጥርጣሬ የሚመለከቱ ወገኖች በአደባባይ ወጥተው፣ ” እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” በማለት አቶ አንዳርጋቸውና ንቅናቄው ለሚታገሉለት ሕዝባዊና ሐገራዊ ዓላማ መቆማቸውን በግልጽ አሳይተዋል። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሐገር ውስጥ፣ በምድር ላይና በውጭ ሐገር የሚገኘውን የንቅናቄያችንን አካላት ተቀላቅለዋል። ቀደም ሲል በንቅናቄያችን በተለያዩ ደረጃዎች ይሰሩ የነበሩ ዓባላቶች ከአፈናው በኋላ ለትግሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት በከፍተኛ ደረጃ ጨምረዋል።
የአቶ አንዳርጋቸውን አፈና ተከትሎ፣ የንቅናቄው አመራር መሰረታዊ የትግል እንቅስቃሴዎቹን በስፋትና በጥልቀት በመፈተሽ አስፈላጊውን ማሻሻያዎችና ማስተካካያዎችን አድርጓል። ንቅናቄያችን አቶ አንዳርጋቸው ለረጅም ጊዜ የደከሙለትን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ የመታገለን ጥረት አሳክቶ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዓርበኞች ግንባር ጋር ሙሉ ለሙሉ ተዋህዷል። ከዚህም በተጨማሪ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ጨምሮ፣ ከሌሎች አምስት በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋራ በጥምረት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሷል።
በሌላ በኩል ያለፈው አንድ አመት የወያኔ የዘረኛ ዓምባገነን ቡድን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን የአፈና፣ የግድያ፣ የዕስርና የድብደባ ውንብድና ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት ዓመት ነበር ። ለዚህም ጸረ ሕዝብ ተግባሩ፣ በባህርዳር ከተማ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደረሰውን ግድያ፣ በሰላም እንታገላለን ብለው ይንቀሳቀሱ የነበሩትን የአንድነትና የመኢሀድ ድርጅቶች ማፍረስ ብቻ ሳይሆን፣ ዓባሎቻቸው ላይ ያደረሰውን ከፍተኛ የድብደባና የዕስር ወንጀል መጥቀስ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ በኦሮምያ፤ በአፋር፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በትግራይና በደቡብ ክልሎች ይህ ነው የማይባል አፈና፤ ግድያና የሕዝብ መፈናቀል በሰፊው አከናውኗል:: ከምርጫው ጋር ተያይዞም በአደረበት ስጋት የተነሳ በርካታ፣ በተለይ ወጣቶች ላይ፣ የመደብደብ፣የማዋከብ የዕስርና የግድያ ተግባር የፈጸመው በዚሁ አቶ አንዳርጋቸውን ከአፈነበት ቀን ጀምሮ በተቆጠረው የአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነበር። በጣም የሚገርመው ለራሱ አመቻችቶ ያዘጋጅውን ምርጫ እንኳን ሙሉ በሙሉ አሸነፍኩ ብሎ ከአወጀም በኋላም፣ ከምርጫው በፊት በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ወንጀል አጠናክሮ መቀጠሉ ያለበትን የስጋትና ጭንቀት ደረጃ የሚያሳይ መረጃ ነው ።
የወያኔ በራስ የመተማመን ደረጃ ከመቼውም ወቅት ይልቅ እጅግ አሽቆልቁሎ የታየውም ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነበር። በሐገር ውስጥ ይነሳብኛል ብሎ በሚያስበው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ስጋት ምክንያት ይህን ስጋት ለመቀነስ በአንድ መንገድም ይሁን በሌላ ይረዱኛል ብሎ ያሰባቸውን በአካባቢው የራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ያላቸውን ቀደም ሲል ወቀሳ ቢጤ እንደመሰንዘርም ዕልህም እንደመጋባትም ይዳዳቸው የነበሩትን መንግስታት ባለሥልጣኖች በመማጸንና ሐገር ውስጥ በመጋበዝ ማንነቱን አበጥሮ ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአደባባይ ወጥተው ወያኔ ያልሆነውን ነው ብለው ምስክርነት እንዲሰጡለት ማድረጉ የወያኔ ስጋት የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ሌላው መረጃ ነው።
በዚህ አጋጣሚ ንቅናቄያችን አቶ አንዳርጋቸውን አፍነው ለወያኔ የሸጡትን የየመን ባለሥልጣኖች ድርጊት በሚመለከት በጊዜው በሰጠው መግለጫ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ “ጊዚያዊ ጥቅምን በማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት የሚያደርገውን ትግል ከወያኔ ጋር በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ በመተባበር ለማፋን መሞከር፣ ታሪካዊ ስህተት መስራት ነው!” እንዳለው ሁሉ፣ ዛሬም የሌሎች መንግስታት ባለ ሥልጣኖች እንደ ትላንትናዎቹ የየመን ባለሥልጣኖች ጊዚያዊ ጥቅምን ብቻ በማየት ሌላ ታሪካዊ ስህተት እንዳይደግሙ ከወዲሁ ለማሳሰብ ይወዳል።
በንቅናቂያችን እምነት ከዚህ በላይ በጥቂቱም ቢሆን ለማሳየት እንደተሞከረው ያለፈው አንድ ዓመት ያሉት መረጃዎች በሙሉ የሚያሳዩት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በማፈን ለማዳከም ያሰበው ትግል ይበልጥ ተጠናክሮና ተቀጣጥሎ በርካታ አንዳርጋቸውዎችን ከማፍራቱም በላይ ብዙዎች ለነጻነታቸው መተኪያ የሌላትን ህይወታቸውን እስከመስጠት የሚያደርስ ዕልህ ውስጥ ገብተዋል። ወያኔ እንዳሰበውና እንዳሰላው ትግሉ መዳከም ሳይሆን መሬት እያያዘና እየተጠናከረ በመምጣቱ የወያኔ ስጋት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እየጨመረ ሄዷል። ይህም ሁኔታ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ሲያፍን ያሰላው ስሌት እጅጉኑ የተሳሳተ እንደነበረ በግልጽ አረጋግጧል። የወያኔ የአፈና ተስፋ ገና በአፈናው ማግስት እንደ ጧዋት ጤዛ ተኗል። ከአለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በመላው ሀገሪቷ ተጠናክሮ የምናያቸው የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎች የሚያመለክቱት ይህንኑ ስጋትና ጭንቀት ነው። የወያኔ የቅዥትና የስጋት የዛፍ ላይ እንቅልፍ፣ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተሸጋግሮና ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ንቅናቄያችን፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ለዕኩልነት ለፍትህና ነጻነት የሚደረግ ትግል፣ በተለይ እንደወያኔ ባለ ዘረኛ አምባገነን ቡድን በበላይነት በሚዘወር ሐገራዊ ሁኔታ ውስጥ፣ ምን ያህል ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አስቀድሞ ጠንቅቆ ያውቃል። ይህም ሆኖ ግን ባለፈው አንድ ዓመት፣ የትግል ጓዳችን የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ እየደረሰባቸው ያለውን መከራና ስቃይ እንዲሁም ይህ ሁኔታ በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያስጀመረውን የጭንቀት ዘመን፣ ለአንድ ሴኮንድም ቢሆን መዘንጋት አይችልም።
ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በአፈናው የተነሳ የደረሰው መከራና ስቃይ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ለፍትህ ለዕኩልነትና ለነጻነት በመቆማቸው በወያኔ አረመኔዎች ቁም ስቅላቸውን የሚያዩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሰቆቃ የሚያበቃው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ በሚያደርገው ሁለ ገብ ትግል በመሆኑ ማንኛችንም በአቶ አንዳርጋቸውም ሆነ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንደራሳችን ጥቃት አድርገን የሚሰማን ወገኖች በሙሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከታፈኑበት አንድ አመት ወዲህ የተጀመረውን ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አጠናክረን ወደ ውጤት ደረጃ በማድረስ መጭው ዘመን የሕዝብ የፍትህ የእኩልነትና የነጻነት ተስፋ የሚለመልምበት ፣ የወያኔ አምባገነን ሥርዓት እድሜ የሚያጥርበት ዘመን እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ንቅናቄያን ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ክብር ለፍትህ ለእኩልነትና ነጻነት መስዋትዕነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ታጋዮች!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ
ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም.

Friday, June 26, 2015
Ethiopia: Dozens of journalists forced into exile, CPJ report shows
Dozens of journalists have been forced into exile in the last 12 months, fearing imprisonment or death at the hands of their own governments, according to a report released Wednesday.
The Committee to Protect Journalists (CPJ) issued its “Journalists in Exile” study on Wednesday, showing that at least 82 reporters were forced to flee to another country between May 2014 and June of this year.
According to CPJ figures, that number is the smallest since the press freedom advocacy group started keeping figures in 2010-2011, when 84 journalists went into exile. In 2012-2013, a record 97 journalists were forced out ot their home countries.
In the last five years, according to CPJ, at least 452 writers and photographers were exiled, mostly from Syria, Cuba, Mexico, Iran and Ethiopia.
The real figure is likely higher as the CPJ number represents only the reporters the organization tried to help through its Journalist Assistance Program, which finds refuge and funds for journalists in danger.
The report revealed about 50 percent of journalists exiled since May 2014 said the likelihood of imprisonment was the primary reason they fled with another 28 percent blaming threats of violence.
But the problems don’t end at the border, said Nicole Schilit, the author of the report.

Thursday, June 18, 2015
ለሰማዕታቱ አደራ የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው?
ኢትዮጵያ አንድ ተጨማሪ ወጣት ልጇን አጣች። ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም ማታ የደብረ ማርቆሱ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ኢሰብዓዊ በሆነ ድብደባ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ በጽናት ታግሏል። ለኢትዮጵያ ይበጃል ብሎ ባመነበት መንገድ ተጉዞ ለትግሉ ሕይወቱን ሰጥቷል። ሳሙኤል በሕይወቱ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በትክክል ያውቅ ነበር፤ ለህልፈት የዳረገው አደጋ በመድረሱ በፊት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሰውበታል፤ ሆኖም ግን ግንባሩን አላጠፈም። በሕይወቱ ላይ ያንዣንበበውን አደጋ ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ በመገመቱ “ከታሠሩኩም ህሊናዬ አይታሰርም፤ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ። በተለይ የኔ ትውልድ አደራ!”የሚል ኗሪውን እረፍት የሚነሳ ተማጽኖ በጽሁፍ አስቀምጦ የመጨረሻውን ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል። ለዚህ የሙት አደራ ምላሻችን ምንድነው?
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በወጣት ሳሙኤል አወቀ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ይመኛል።
ዛሬን እየኖርን ያለነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከሀቅ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠናል። እንዴት ነው የሳሙኤል አወቀ እና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት አደራ መወጣት የምንችለው? እንዴት ነው ይህንን የህወሓት ፋሽስታዊ ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድና በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነበት፤ የአገር አንድነት የተረጋገጠበት ሥርዓት መገንባት የምንችለው? እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለዚህ ትግል የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ምንድነው? ማንን ነው የምንጠብቀው?
አርበኞች ግንቦት 7 መፍትሔው ሁለገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። ሁለገብ ትግል ደግሞ ሕዝባዊ አመጽንና ሕዝባዊ እምቢተኝነትን አቀናጅቶና አስማምቶ ማራመድን ይጠይቃል። በሁለገብ ትግል እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ የሚያበረክተው ነገር አለ። ሁለገብ ትግልን የሆነ አካል የሆነ ቦታ እስኪጀምረው መጠበቅ አይገባም፤ እያንዳንዳንችን እንደሁኔታው በየአካባቢያችን ልንጀምረው የምንችለው የትግል ስትራቴጄ ነው። ሁለገብ ትግል በየአካባቢያችን በምስጢር በመደራጀት “እኔም ኃላፊነት አለብኝ” እንድንል የሚያደርግ አሳታፊ የሆነ የትግል ስትራቴጂ ነው። ሁለገብ ትግል ጥቂቶችን ሳይሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚያሳትፍ ሕዝባዊ ትግል ነው።
በየጊዜው በህወሓት ፋሽስቶች ለሚደርስብን በደል ምላሽ መስጠት የሚኖርብን በየአካባቢያችን በምስጢር በመደራጀት ለአምባገነን አገዛዝ ያለን ጥላቻ ስንገልጽ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከራሱ ይጀምር፤ ለህወሓት አምባገነን አገዛዝ ላለመንበርከክ ቃል ይግባ፤ ከሚመስለው ጋር ይቧደን፤ የትግሉን አቅም ይገንባ፤ በአቅሙ መጠን አምባገነኑን ሥርዓት ይገዳደር። ትግሉ እሆነ ቦታ እስኪጀመር መጠበቁን ትተን በሁሉም ከተሞችና በሁሉም የገጠር መንደሮች በአቅማችን መጠን ትግሉን እናፋፍም። እያንዳንችን ለነፃነታችን ኃላፊነት አለብን። የሰማዕታት አደራ የእያንዳንዳችን አዕምሮ እረፍት ሊነሳ ይገባል። ይህንን ስናደርግ ነው ለሰማዕታቱ አደራ ምላሽ ሰጠን ማለት የምንችለው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Monday, June 15, 2015
ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው ቁም ነገሮች
በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል።
ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር አንድነት ግድ ያለን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው በርካታ ቁም ነገሮች ያሉ ቢሆንም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።
1. “ጥቂቶች ነን፤ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለው ተስፋ ቆርጠው በደልን ለመቀበል አልመረጡም፤
2. ዓላማቸው ትልቅና ሀገራዊ ቢሆንም እርጃዎቻቸው አካባቢ ተኮር አድርገዋል፤
3. የሚወስዷቸው እርምጃዎች በአቅማቸው መጠን እንዲሆኑ በማድረግ በራሳቸው ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ማድረግ ችለዋል፤
4. እንደሁኔታው በፍጥነት መሰባሰብና መበታተን የሚችል ቀልጣፋስብስብ ማደራደት ችለዋል፤ እና
5. በከፍተኛ ሥነሥርዓት በመታነጽ ከቴፒ ሕዝብ ጋር ያላቸውን ትስስር አጠናክረዋል።
ሁላችንም ከእነዚህ ወጣቶች ልንማር ይገባል። በአምባገነን አገዛዝ ጉያ ውስጥ የሚደራጅ የአመጽ ኃይል የተለያዩ አደረጃጀቶች ሊኖሩት ይችላል። አንዱ አደረጃጀት የቴፒ ወጣቶች በተግባር ያሳዩን ነው – ተንቀሳቃሽ፣ ለግዳጅ ተሰባስቦ በፍጥነት የሚበተን፤ መልሶ ደግሞ የሚሰባሰብ ቀልጣፋ ድርጅት።
በምርጫ 97 በሰላማዊ መንገድ የሰጡትን ድምጽ ይከበርን ያሉ ወገኖታችን በአዲስ አበባ ከተማ በግፍ የተጨፈጨፉበት ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም 10ኛ ዓመት በሀዘን አስታውሰናል። ከዚያ ወዲህ በርካታ ወገኖቻችንን በሰላማዊና ህጋዊ ትግል አጥተናል፤ ብዙዎች ቆስለዋል፤ በሺዎች የሚገመቱ በእስር እየማቀቁ ነው። ሆኖም ግን ያ የትግል መስመር የትም አላደረሰንም። የህወሓት አገዛዝ እንዲያበቃ እና በምትኩም ሕዝብ በነፃነት የመረጠው አስተዳደር እንዲኖር የምንፈልግ ወገኖች ሁሉ ወደግባች የሚያደርሱንን አማራጮችን መፈለግ ግዴታችን ሆኗል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ሁለገብ ትግልን” እንደ ትግል ስትራቴጂ ሲመርጥ በውስጡ ብዙ አማራጭ ስልቶች መኖራቸውን እግንዛቤ በማስገባት ነው። የቴፒ ወጣቶች በተግባር ያሳዩን የተለያዩ የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ አካል የሆኑ በርካታ የትግል ስልቶች መኖራቸውን ነው። ቴፔ የተደረገው እንዳለ ሌላ ቦታ ይደረጋል ማለት አይደለም። ከቴፒ የምንማረው ዋናው ቁምነገር በፈጠራ እና በአካባቢ እውቀት በታገዘ ስልት ወያኔ መፋለም ያለብን መሆኑ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የቴፒ ወጣቶች ላሳዩት ተግባራዊ መነሳሳት አድናቆት እና ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለውን ክብር እየገለፀ በሌላው የአገራችን ክፍሎች ያሉ ወጣቶችም ከቴፒ ወንድሞቻቸው ትምህርት እንዲቀስሙ ያበረታታል።
በዚህ አጋጣሚም በየቦታው በራስ አነሳሽነት የሚጀመሩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አካባቢ ተኮር ቢሆኑም እንኳን አገራዊ እይታ እንዲኖራቸው፤ ከሌሎች መሰል እንቅስቃሴዎች ጋር እንዲቀናጁና እንዲደጋገፉ ብሎም የሀገራዊ ትግሉ አካል እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ያስገነዝባል፤ ይህ ተግባራዊ እንዲሆንም ይሠራል።

Tuesday, June 9, 2015
ምርጫ ሲባል መሳይና አስመሳይ – መስፍን ወልደ ማርያም
ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ፡፡… ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል ይሆናል፤ አንድ የሁለት ጓደኞች የቆየ ቀልድ ትዝ አለኝ፤ አንዱ ስሙ መሳይ ነው፤ ፊታውራሪ ነው፤ ሌላው ስሙ በፈቃዱ ነው፤ ሀኪም ነው፤ አንድ ቀን በፈቃዱ መሳይን ሲያገኘው በፊታውራሪነቱ ለማሾፍ ፊታውራሪ መሳይ አለ፤ መሳይን ጫን ብሎ፤ መሳይም ሲመልስ በዶክተርነቱ እያሾፈ ዶክተር በፈቃዱ ብሎ ዶክተርን ጫን ብሎ መለሰለት! የኛን ምርጫ-መሳይ ምን ብለን፣ አንዴት ብለን እናሹፍበት? ያውም ማሾፍ ከተፈቀደ! በባህላችን በጣም የተወደደ ምግብ አለ፤ ያንን ምግብ አቅርበው መሣሪያው ሲነፍጉ ሥጋውን ሰጥቶ ቢላዋውን መንሣት ይባላል፤ ንፉግነት ብቻ አይመስለኝም፤ ክፋትም አለበት፤ የደርግና የወያኔ ምርጫ-መሳዮች በአለማወቅና በንፉግነታቸው ይመሳሰላሉ፤ በክፋት ግን አይመሳሰሉም፡፡ ደርግም ሆነ ወያኔ ከሌኒን ለመማር አልቻሉም እንጂ አስመስለዋል፤ ምርጫ-መሳዩንም ያገኙት ከዚያው ነው፤ ሌኒን ጉሮሮን ግጥም አድርጎ በብረት ሰንሰለት አስሮ ነጻ ነህ ይላል! መገንጠል ትችላለህ! ይላል፤ ወያኔም ሲሉ ሰምቶ መገንጠል-መሳይ ሕግ-መሳይ አወጣ! ችግር ነው ጌትነት! ዱሮ ተረት ነበር፤ ዛሬ ግን በእውነት ሲቸግር እያየን ይመስለኛል፤ አንድ ሰው ራሱ ባፈራው ሀብትና በደረሰበት የጌትነት ደረጃ ችግር አይሰማውም፤ ሀብቱ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት እንደመጣ፣ ምን ያህል ልፋት እንዳስከተለ መገመት ይቻላል፤ በተዘረፈ ሀብት ጌትነት ሲመጣ ግን ችግርን አዝሎ ነው፤ አንድ ሰው አራት ሚልዮን ብር ወድቆ ቢያገኝ አራት መቶ ካሬ ሜትር መሬት ቢገዛበት አያስደንቅም፤ የገንዘብ አያያዝን ስለማያውቅና በስጋት ስለሚከሳ መሬቱ ላይ መቀመጥ አስተማማኝ መስሎ ይታየዋል፤ ከካስትሮ በፊት የነበረውን የኪዩባ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን የሚያውቅ በዛሬው ጊዜ በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነቱን ለመረዳት አያዳግትም፤ በኪዩባም ሆነ በኢትዮጵያ በተዘረፈ ሀብት ጌትነትን ያስፋፋው አሜሪካ ነው፤ ሕዝብ የሚደኸየውና የሚከብረው በጉልበትና በዝርፊያ ብቻ በሆነበት አገር ጊዜውን ጠብቆ ከሁለት አንዱን አርግዞ ይወልዳል፤ ወይ ዘራፊዎችን ሁሉ ዘርፎ ሙልጭ የሚያወጣቸው ጉልበተኛ ይመጣል፤ ወይ በሕጋዊ መንገድ ከዘራፊዎች እየገፈፈ ሀብትን ለሕዝብ የሚያደላድል ሕጋዊ ሥርዓት ይመሠረታል፤ ሁለቱንም በማስረገዝ ላይ ያሉት በግፍ ሀብታም የሚሆኑት ናቸው፡፡ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ምርጫ መሳይ አለ፤ ሕዝብ የሀብት ባለቤት እንደሆነ ለማስመሰል ግን ትንሽ ያስቸግራል፤ በኮንዶሚንየም ለማስመሰል ቢሞከርም አልሆነም፤ ለሎሌዎች ሹሞችም አልተዳረሰም! በምርጫ መሳዩ ማሸነፍ ቀላል ነው፤ እንዲያውም መቶ በመቶ ማሸነፍ ይቻላል፤ ችግሩ የሚመጣው ከዚያ በኋላ ነው፤ ደካሞች የፖሊቲካ ቡድኖችንና ደካማውን ሕዝብ ማሸነፍ እንደሚቻል ጉልበተኛው አስመስክሯል፤ ሌላው ቀርቶ ‹‹የኔ›› የሚላቸውን ቡድኖችም አፈር ላይ ሊያስተኛቸው ይችላል፤ እንዲያውም አፈሩ ምቹ ፍራሽ ነው ብለው በደስታ እንዲቀበሉ ሊያደርጋቸው ይችላል፤ አሁን የጉልበተኛው መድረክ እየጠበበ መጣ፤ ችግሩ የሚፈጠረው እዚህ የጠበበው መድረክ ውስጥ ባሉት ጉልበተኞችና ጉልበተኛ መሳዮች ነው፤ በአንድ በኩል በጉልበተኞች መሀከል፣ በሌላ በኩል በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፤ በሌላ በኩል በጉልበተኞችና በጉልበተኛ መሳዮች መሀከል፣ ይህ ትግል ዳካማዎች የፖሊቲካ ቡድኖችን እንደማሸነፍ ቀላል አይደለም፤ በአጥር ላይ እየተንጠለጠሉ የጣሉትን ለመልቀም እየተሻሙ ነው፤ በጉልበተኞቹ መሀከል ክፉ የሥልጣን ችጋር ገብቷል ማለት ነው፤ ጦር መማዘዝ ኪስን እንደሚያራቁት ያውቃሉ፤ ያለሥልጣን ኪስ ሙሉ እንደማይሆንም ያውቃሉ፤ ታዲያ ምን ይሻላል?
Monday, June 1, 2015
የወያኔ የመከላከያ ከፍተኛ በጀት
የወያኔ የመከላከያን ከፍተኛ በጀት ለትግራይ ክልል እንደ ተጨማሪ ልዩ በጀት አድርጎ ይጠቀማል፡፡ በሰራዊቱ ውስጥ ዘረኛ መድሎን ይፈጽማል፡፡ የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ህልሙንም አልረሳም፡፡
በአሁኑ ጊዜ 85% የሚሆነው የመከላከያ ሠራዊት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ሠፍሮ ይገኛል፣ ይህንንም አጋጣሚ
በመጠቀም ፦
ለሠራዊቱ ቀለብ አቅርቦት ያለ ጨራታ ከአዛዧች ጋር በመመሳጣር፣ የትግራይ ሰዎች ብቻ እንዲያቀርቡ ተደርጓል። አቅራቢ ከሆኑትም መሀል አቶ ጉዕሺ፣ ወ/ሮ ዘውዴ ፣ አቶ ስብሀት ፣ ወ/ሮ አዲስ፣ አቶ ገብረስላሴ፣ አቶ ሃጎስ በመባል የታወቁ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ለሰራዊቱ የሚያቀርቡትም አትክልት ፣ በርበሬ፣ የወጥ እህሎችና ሥጋ፣ ዱቄት ፣ ዘይት ወዘተ. መሆኑ ታውቋል። አቅራቢዎቹ የትግራይ ሰዎች አቅርቦቱም ከትግራይ ክልል እንዲገዛ ተደርጓል።
ሰራዊቱ በከፍተኛ ቁጥር ትግራይ ላይ በመስፈሩ ብቻ ምን ያህል የክልሉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደጠቀመ አንድ ምሳሌ እንስጥ፡፡ የወያኔ አንድ ወታደር በቀን 8 ዳቦ ይበላል፡፡ ይህም ማለት ወደ መቶ ሽህና ከእዛም በላይ የሚቆጠረው በትግራይ ውስጥ የሰፈረው ሰራዊት በአማካይ በትንሹ በቀን 800000 ዳቦ ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ በቀን ይህን ያህል ዳቦ የማቅረብ ስራ ብቻ ምን ያህል ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገው እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ወያኔ ሰራዊቱ በሆዱ እንዳይከፋበት ካለው ፍላጎት ለምግብ ከፍተኛ ወጪ ያደርጋል፡፡ ካዳቦ ውጭም በእዚሁ በትግራይ ክልል ውስጥ ሰራዊቱን መሰረት በማድረግ የሚመረተው የተለያየ የምግብ ውጤትና ሽያጭ በገንዝብ ሲለካ በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ይሆናል፡፡
ሌሎች ከቀለብ ውጭ በመደበኛ በጀት የሚገዙ አላቂና ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌትሪክ ማሽነሪዎች ፣ የጽህፈት ዕቃዎች፣ ማንኛውም የቢሮና የመኖሪያ ቤት መገልገያ ዕቃዎችና የስልጠና መገልገያ ዕቃዎች፣ በሙሉ ከትግራይ ክልል ብቻ እንዲገዙ በመመሪያ ታዟል። ሌላው ቀርቶ ጠቅላላ የመከላከያ ወታደራዊ አገልግሎትና ሌሎች ጨርቃ ጨርቆች በሙሉ፣ ያለ ጨረታ አድዋ ከሚገኘው ከአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ብቻ እንዲገዛ ተወስኖ፣ ተግባራዊ ከሆነ ብዙ አመታት አስቆጥሯል። ይህ ሰራዊት በአመት ሁለት ግዜ የደንብ ልብሱን እንዲቀይር ከወጣው መመሪያ ጋር ተደምሮ እነአልሜዳ ምን ያህል ገንዝብ ከመከላከያ ሚኒስቴር እንደሚዘርፉ ማየት ይቻላል፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)