Sunday, July 26, 2015

ህወሓት ለሽብር ጥቃት ተዘጋጅቷል፤ እንጠንቀቅ

ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል። እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ህወሓት ስልጣን ከመያዙ በፊትም በኋላም ሲያደርገው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ህወሓት እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብዓዊና ዘግናኝ ተግባር ለመፈፀም የሚያስችሉ እኩይ ስለልቦና እና ልምድ አለው።

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በቅርቡ የጀመረው የነፃነት ትግል የፈጠረበት መደናገጥ ለመሸፈንና ንቅናቄውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ለማስወገዝ ያግዘኛል ብሎ ያመነበት ይህን ዘግናኝ ሴራ ከሳምንት በፊት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁቱን አጠናቆ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የነፃ ሚዲያ አባላት ደርሰውበት ለሕዝብ ይፋ በማድረጋቸው እንዲዘገይ ተደርጎ ነበር። አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ ሴራው ከበፊቱ በባሰ እና ይበልጥ አውዳሚ በሆነ መጠን ተግባራዊ ለማድረግ የህወሓት “ስውር” መንግሥት ወስኗል። በዚህም ምክንያት ይህ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ እንዲገነዘብ የምንፈልገው ሀቅ የሚከተለው ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በደረሰው መረጃ መሠረት ህወሓት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ወስኗል። የእቅዱ ዓላማ ዘግናኝ እርምጃ በንፁሃን ዜጎችና ሕፃናት ላይ በማድረስ “የሽብር ጥቃቶች ሰለባ” ነኝ በማለት የኢትዮጵያ እና የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ አዘኔታ ማግኘት ነው። የዩ. ኤስ. አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን የሚጎበኙ መሆኑ ደግሞ ይህንን እቅድ ተግባራዊ የማድረግ ጉጉቱ እንዲጨምር አድርጓል። ስለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ በህወሓት የሽብር አደጋ ውስጥ ነች። የቦሌ ዓለም ዓቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ እና ወደዚያ የሚያደርሰው መንገድ፣ የአፍሪቃ ኅብረት ጽ/ቤት እና የአሜሪካ ኤምባሲ ህወሓት በሽብር ጥቃት ዒላማነት ከመዘገባቸው ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው።

አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚቃጡ የሽብር ጥቃቶችን መቃወም ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተባብሮ ያመክናል። ይህ በህወሓት የተደገሰልንን የሽብር ጥቃት ማምከን ይኖርብናል። እኩይ እቅድን አስቀድሞ አውቆ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አንድ ዓይነተኛ የሽብር መከላከያ ዘዴ ነው። በዚህ ረገድ በአገዛዙ ውስጥ ያላችሁ የሕዝብ ወገኖች ባለውለታዎች ናችሁ።

የእያንዳንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕይወት መለኪያ በሌለው መጠን ውድና ክቡር ነው። በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ዜጋ የህወሓትን እኩይ ሴራ ተገንዝቦ ራሱን፣ ቤተሰቡንና አካባቢውን ከጥቃት እንዲጠብቅ አርበኞች ግንቦት 7 በጥብቅ ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Thursday, July 23, 2015

ህወሓት በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ተኩኖ ህወሓትን ማዳከም አርበኝነት ነው!

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ለኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አባላት የሚከተለው መልዕክት ማስተላለፍ ይሻል።

ህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው የሚያፈናቅሉ፣ መኖሪያ ቤቱን የሚያስፈርሱ መሆናቸው እናንተም እየተሳተፋችሁበት ያለ ሥራ ነውና የምታውቁት ነው። “አጋር ድርጅቶች” የሚል ስያሜ የተሰጣችው አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ እና ኢሶዴፓ “አጋር” ሳይሆን የህወሓት ጀሌዎች መሆናቸው እናንተም እኛም የምናውቀው ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ የተባሉ አድርባይ ድርጅቶች ባይኖሩ ኖሮ ህወሓት ለ24 ዓመታት ኢትዮጵያዊያን እየገደለና እያሰረ፤ እየዘረፈ በውሸት ምርጫና በውሸት ዲሞክራሲ ስም ፍጹም የሆነ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ አምባገነናዊ ሥርዓት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሰፍን ባልቻለም ነበር። ህወሓት በኢትዮጵያዊያን አናት ላይ እንዲፈነጭ እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ድርጅቶች አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው።

ይህ ብቻም አይደለም። እናንተ አባል ሆናችሁ ድጋፍ ባታደርጉላቸው ኖሮ እነዚህ አድርባይ ድርጅቶች ባልኖሩም ነው። ስለሆነም ህወሓት በኢትዮጵያዊያን አናት ላይ እንዲፈነጭ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ ልጆቻችሁ እና የልጅ ልጆቻችሁ በሎሌነት እንዲያድጉ፤ ጥቂቶች በልጽገው ብዙሃኑ እንዲደኸዩ እናንተ በግል አስተዋጽዖ አድርጋችኋል።

ብዙዎቻችሁ እነዚህ አድርባይ ድርጅቶችን የተቀላቀላችሁት በኑሮ ግዴታ፣ በትዕዛዝ፣ በአማራጭ እጦት ሰበብ፣ የሰብዓዊ ተፈጥሮችን አካል በሆነው የመንፈስ ደካማነት ምክንያት እንደሆነ፤ ድርጅታችሁ በሕዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል እያያችሁ ህሊናችሁ እንደሚቆስል እናውቃለን። አንዳንዶቻችሁ ውስጣችሁ እያነባ እጆቻችሁ ኢፍትሀዊ ተግባር እንደሚፈጽሙ እናያለን። ኢህአዴግ እንደማፊያ ድርጅት መግባት እንጂ መውጣት የማይቻልበት ሆኖ እንዳገኛችሁት እናውቃለን። “ይህንን ድርጅት ከለቀቅኩ የሚጠብቀኝ እስር፣ አልያም ሥራ ማጣት ነው። ያኔ ምን ይውጠኛል? ትዳሬ፣ ልጆቼ፣ ወላጆቼ እንዴት ይሆናሉ?” የሚል ስጋት እንዳለባችሁ እንገነዘባለን። ህወሓትን በመርዳት ያቆማችሁት ሥርዓት እንኩዋንስ ለሌላው ለእናንተም ከፍርሃት ነፃ ሊያደርጋችሁ አለመቻሉን እናውቃለን። ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7፣ እናንተ ያላችሁበት አጣብቂኝ ቀላል እንዳልሆነ ይገነዘባል። በዚህም ምክንያት ይህንን ጥሪ ለእናንተ ያቀርባል።

ሀገራዊና ሕዝባዊ ስሜት ያላችሁ፤ ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ክብር የምትጨነቁ፣ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ሎሌነትን ሳይሆን ክብርን ማውረስ የምትፈልጉ የኢህአዴግ እና የአጋር ድርጅቶቹ አባላት ሆይ! አባል የሆናችሁባቸውን ድርጅቶች ሳትለቁ፤ ኢህአዴግም ሆነ አጋር ድርጅቶቹ ውስጥ እያላችሁ ለህሊናችሁ፣ ለልጆቻችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁና ለሀገራችሁ የምትሠሩበት መንገድ ተመቻችቶላችኋልና ተጠቀሙበት።

የአገራችን የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ እንደሚያስተምረን አርበኝነት ሁለት ዓይነት ነው። አንዱ በገሀድ፣ በግላጭ፣ በውጊያ ሜዳ የሚታይ አርበኝነት ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ፣ በጠላት ጉያ ውስጥ ተኩኖ፣ ጠላትን መስሎ የሚደረግ አርበኝነት ነው። ሁለተኛው ዓይነት አርበኝነት በተለምዶ “የውስጥ አርበኝነት” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በተግባርና በውጤት ከአደባባይ አርበኝነት በምንም የማይተናነስ የጀግንነት ሥራ ነው። የውስጥ አርበኛ፣ አርበኛ ነው። የውስጥ አርበኛ ገድሉ በታሪክ የሚወደስ፣ በአርዓያነቱ የሚጠቀስ የሀገሩ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

የኢህአዴግ አባላት ሆይ የውስጥ አርበኛ የመሆን እድላችሁን አታስመልጡ!

ዛሬ በምንገኝበት ሁኔታ የውስጥ አርበኝነት ማለት ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ ወይም ኢሶዴፓ ውስጥ ሆኖ ህወሓትን ማዳከም ማለት ነው። በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ ቀንደኛ የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚዎች እንዳሉ ይታወቃል። የውስጥ አርበኞች ተግባር እነዚህ ከህወሓት በላይ ህወሓት ሆነው እናንተ በወገናችሁ ላይ በደል እንትድፈጽሙ የሚያደርጓችሁ፤ ለህወሓት ባርነት መገዛትን መታደል እንደሆነ አድርገው የሚሰብኩ ቀንደኛ ባንዳዎችን መቆጣጠር ነው። የውስጥ አርበኛ ማለት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ ሆኖ ሥርዓቱ የሚያዳክሙ ተግባራትን የሚሠራ ጀግና ማለት ነው። የውስጥ አርበኛ ማለት በሕዝብ ላይ በደል የሚሠራን ሥርዓት በአሻጥር የሚያሽመደምድ ብልህ ዜጋ ማለት ነው። የውስጥ አርበኛ ማለት አለቆቹን እየሰለለ፣ ራሱ የተሳተፈበትም ቢሆን የሥርዓቱን እቅዶች ለታጋዮች አሳልፎ የሚሰጥ ባለውለታ ማለት ነው። የኢህአዴግና “የአጋር” ድርጅቶች አባላት በውስጥ አርበኝነት በመሳተፍ ለህሊናችሁ፣ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ውለታ መሥራት ትችላላችሁ።

የህወሓትን ዓላማ የማይደግፉ የህወሓት አባላት እንዳሉም እናውቃለን። ለእነሱም ህወሓት ውስጥ ሆኖ ህወሓትን ማዳከም ትልቅ የውስጥ አርበኝነት እንደሆነ ማስገንዘብ እንወዳለን። የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጉዳይ ከዘር በላይ መሆኑ የሚረዱ፤ እነሱ ለራሳቸው እንዲሆን የሚፈልጉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም የሚመኙት መሆኑን የተረዱ የህወሓት አባላት የኢፍትሃዊነት ምንጭ የሆነው ድርጅታቸውን በማዳከም ላይ የመልካም ዜግነት አክሊል መቀዳጀት ይችላሉ።

በህወሓትና ህወሓት የፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ የምትገኙ ወገኖቻችን ፈልጋችሁ አግኙን፤ ደህንነታችሁ በተጠበቀ መጠን በዘረኛ ድርጅት ውስጥ ሆናችሁ ዘረኝነትን፤ በፋሽስት ድርጅት ውስጥ ሆናችሁ ፋሺዝምን መዋጋትና ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ መኖር ትችላላችሁ። ይህን ስትሰሩ እኛ ከናንተ ጋር ነን። ይህንን ስትሠሩ እኛና እናንተ ለጋራ ዓላማ የምንሰራ ጓዶች እንጂ ጠላቶች አንሆንም። ሥርዓቱን በማዳከም ረገድ የምትወስዱት ተጨባጭ እርምጃዎችን ማየት እንፈልጋለን። እኛን ማግኘት ከባድ አይደለም፤ ፈልጋችሁ አግኙን። ተባብረን አገራችን ከህወሓት ፋሽስታዊ ዘረኛ አገዛዝ ነፃ እናውጣ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Tuesday, July 21, 2015

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ

ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.

ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።

ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።

አርበኞች ግንቦት 7 አመራሩን ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን እና ትግሉ በሚጠይቀው ቦታ እንዲገኙ የሚያደርግ መሆኑ ሲገልጽ ቆይቷል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ የአመራሩ በትግሉ ሜዳ ውስጥ መገኘት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ሊቀመንበሩን ጨምሮ አመራሩን ወደ ትግሉ ሜዳ አንቀሳቅሷል። በዚህም መሠረት የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳ ወርዷል።

ትግሉ መሯል። ወሳኝ የሆነ ትግል ውስጥ ገብተናል። የትግሉ መሪዎች የሕይወት መስዋዕትነት እሚከፈልበት ቦታ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት የንቅናቄው አመራር በተሟላ ሁኔታ በትግሉ ሜዳ ውስጥ እንዲገኝ ማድረግ ተችሏል። ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ዘረኛው የህወሓት አገዛዝን ከጫንቃችን ለማስወገድ ቆርጠን እንድንነሳ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

ኢትዮጵያን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ የሚያወጣው አርበኞች ግንቦት 7 ብቻ አይደለም። ስለሆነም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደረገው ትብብር ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው ሥራዎች አንዱ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ለድል እንዲበቃ ይታገላል። ኢትዮጵያዊያንም በያሉበትም በተመሳሳይ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሱ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

እነሆ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአካል ትግል ሜዳ ውስጥ ይገኛል። የሚችል ሁሉ እንዲከተል፤ መከተል የማይችል በያለበት ሁኖ ሁለገብ ትግሉን እንዲያጧጥፍ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

Saturday, July 18, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት መፈጸም ከጀመረ ወዲህ የወልቃይት ሕዝብ በስርዓቱ አንገዛም ብሎ በአንድነት መነሳቱ ተዘገበ

አርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንደዘገበው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ስርዓት ክልል 1 እና ክልል ሦስት ብሎ የከፈለው የወልቃይት ህዝብ በስርዓቱ አንገዛም ብሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡
የወልቃይት ህዝብ “ክልል 1 እና ክልል 3 የሚባል አናውቅም እኛ የጎንደር በጌ ምድር ተወላጆች ኢትዮጵያዊያን ነን” ሲል በአንድነት “ሆ” ብሎ በመነሳት ከእንግዲህ ወዲህ ህወሓት በዘረጋው የፌደራሊዝም ጭምብል ያጠለቀ የጎሳ አስተዳደር እንደማይመራ እንደ ብረት የጠነከረ አቋሙን በመግለፅ ላይ ነው፡፡
የወልቃይት ህዝብ እስካሁንም ድረስ እትብቱ የተቀበረበት መሬቱ ከሁለት ተሰንጥቆ ከፊሉ ክልል 1 ከፊሉ ደግሞ ክልል 3 ተብሎ በህወሓት ዘረኛ ቡድን መቆረሱንና አንድነቱን ሸርሽሮ ለማዳከም የተቀነባበረውን ስውር ደባ እጆቹን በማጣጠፍ ቆሞ አልተመለከተም ነበር፡፡
ከ1992 ዓ.ም አንስቶ እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ከፍተኛ መሰዋዕትነት ሲከፍል ኖሯል፡፡ ዘረኛው የህወሓት ቡድን የወለቃይትን የአንድነትና የነፃነት ጥያቄ ያነሱትን ልጆቹን በየጊዜው በመረሸን ህዝቡንም በጅምላ መጨፍጨፍና ዘር በማጥፋት ጥያቄውን በኃይል አዳፍኖት ሊቀር ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡
ነገር ግን ዛሬ ህወሓት በወልቃይት መሬት ላይ ያዳፈነው ረመጥ ውስጥ ለውስጥ ሲቀጣጠል ቆይቶ ሳያስብው ግር ብሎ ነዶ ራሱን እየለበለበው ነው፡፡
በህወሓት የዘር አገዛዝ በእጅጉ የተማረረው የግፍና በደል ገፈትን ሲጎነጭ የኖረው የወልቃይት ህዝብ የህቡና ይፋዊ አስተባባሪ ኮሚቴዎቹን በመምረጥ በሚገባ ተደራጅቶ ህወሓትን በማንኛውም መስክ ሊፋለመው በአንድነት ተነስቷል፡፡
በመሆኑም ከአዲ ረመፅ 3፣ ከጠገዴ 3 እና ከቃፍታ 1 በድምሩ 7 ይፋዊ ኮሚቴዎችን መርጦ “ክልል 1 እና ክልል 3 አላውቅም፤ እኔ የጎንደር በጌምድር ኢትዮጵያዊ ነኝ” በማለት ከእንግዲህ ወዲህ የህወሓትን የጎሳ አስተዳደር ፈፅሞ የማይቀበለው መሆኑን እንዲያስታውቁለት ወደ አዲስ አበባ ልኳል፡፡

Wednesday, July 15, 2015

ሰማያዊ ከምርጫ ማግስት እየተወሰደ ያለው እስርና ግድያ እንዲቆም ጠየቀ

ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 7/2007 ዓ.ም ‹‹የወለደውን የረሳ ብሶት የወለደው ስርዓት! የዘመቻ እስርና ግድያ ተጠናክሮ ቀጥሏል!›› በሚል በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እዳመለከተው፣ ምርጫው ከተጠናቀቀበት ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ማግስት በምርጫው በንቃት ይሳተፉ የነበሩና በአስተሳሰባቸው በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዜጎች በማንአለብኝነት መደብደብ፣ ከሰራ ማፈናቀል፣ ማሰር፣ ማሸማቀቅና መግደል የአገዛዙ ዋና መገለጫ ሆኗል፡፡
ሰማያዊ በመግለጫው ‹‹በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የሰማዊ፣ የመኢአድ፣ የቀድሞው አንድነት፣ የመድረክና የሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በተለዬ ኢላማ ተጠምደው እየተሳደዱ፣ እየተደበደቡና በጅምላ እየታሰሩ አለፍ ሲልም በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ ይገኛሉ›› ሲል ገልጾአል፡፡
አሁን በገዥው አካል እየተወሰደ ያለው ድርጊት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እናመጣለን የሚለውን አስተሳሰባቸውን የሚያጨልምና የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞችን አንገት የሚያስደፋ ይዋል ይደር እንጅ መዘዙም ለማንም ወገን በተለይም ለገዥው መደብ የማይጠቅም መሆኑንም ፓርቲው በመግለጫው አስገንዝቧል፡፡
‹‹የአፈናው ስርዓት ብዙ ዓይነት አስተሳሰብና ልዩነት ባለባት ኢትዮጵያ ምርጫን መቶ በመቶ አሸንፌአለሁ ቢልም ሃቁ ግን የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግብዓተ መሬት እየተቃረበ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ገዥው ቡድንም የማይክደው መሆኑን በምርጫው ማግስት ጀምሮ የተዘፈቀበት ህዝብን እንደጦር የመፍራት አባዜው ገሃድ አድርጎታል›› በሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው አካል ከሚፈፅማቸው ህገ ወጥና የማን አለብኝነት ተግባሩ እንዲቆጠብ፣ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ደጋግሞ መጠየቁን አስታውሶ፣ አሁንም ይህ አይነቱ ህገ-ወጥና የማንአለብኝነት ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንደተናገሩት አሁን ያለው ትግል ‹‹ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ የነጻነት ትግል›› ነው፡፡
በመጨረሻም ፓርቲው ሕዝብ የስልጣን ባለቤትነቱን እንዲያረጋግጥ በሚያደርገው ትግል ሁሉ ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪውን አቅርቧል፡:

አርበኞች ግንቦት 7 በሁመራ በተደረገ ውጊያ ከሕወሓት መንግስት 40 ወታደሮችን ገደልኩ; ከራሴ 10 ተሰዉብኝ አለ

(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በበተነው መረጃ መሠረት ዛሬ በሰሜን ጎንደር ሁመራ አካባቢ በተደረገ ውጊያ ከ40 በላይ የስርዓቱን ቅጥረኞች ገደልኩ አለ:: ግንባሩ በበተነው መረጃ ከራሱ ወደ 10 የሚጠጉ ሰራዊቶች መሰዋታቸውን ገለጸ:: ዛሬ በሕወሓት አስተዳደር በኩል ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም አርበኞች ግንቦት 7 ባወጣው መግለጫ ግን በርካታ የስርዓቱ ወታደሮች አገዛዙን እየከዱ ግንባሩን ከመቀላቀላቸውም በርካቶች ጠመንጃቸውን እየጣሉ ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ መሆኑን አስታውቋል:: አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን በኩል የጀመርኩትን ውጊያ የማቆመው ድል እስከማደርግ ድረስ ነው ሲል ዘግቧል:: 

ጦርነቱ ያስፈራው የሕወሓት አስተዳደር በጎንደር አፈናውን ተያይዞታል

(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜኑ የኢትዮጵያ ግዛት በሕወሓት አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የሕወሓት መንግስት ደህንነቶች በጎንደር የለውጥ አረአያና አንቀሳቃሽ ይሆናሉ ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች እያፈኑ ወዳልታወቀ ስፍራ እየወሰዱ እንደሚገኙ ለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች ጠቆሙ:: በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍራቻ ውስጥ የሚገኘው የሕወሓት አስተዳደር በተለይም በጎንደር ከተማ እንዲህ ያለውን የአፈና እርምጃ መውሰድ የጀመረው “አማራው ልቡ ከኛ ከራቀ ቆይቷል; አሁንም ግንቦት 7 እና አርበኞች ግምባርን ደብቆ ያስወርረናል” በሚል ፍራቻ እንደሆነ የደረሰን መረጃ አመልክቷል:: የዘ-ሐበሻ የጎንደር ዘጋቢዎች እንደሚሉት የሕወሓት አስተዳደር በአማራው ላይ ያለው እምነት ከመሟጠጡ የተነሳ አማራውን እስከመናቅና እስከማሸማቀቅ ደርሷል:: በአሁኑ ወቅት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ እነዚህ የጎንደር ነዋሪዎች እየታፈኑ የት እንደደረሱ አለመታወቅ በከተማው መነጋገሪያ ሆኗል::

Saturday, July 4, 2015

በህወሓት አገዛዝ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ደህንነት የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጫና ይቀጥል!

ከሣምንት በፊት የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የሚመለከት አንድ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫው፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ለአንድ ዓመት ሙሉ መሠረታዊ የሆኑ የታሳሪዎች መብት እንኳን ተነፍጎት ባልታወቀ እስር ቤት የሚገኝ መሆኑ እና በእንግሊዝ ባለሥልጣናትና በቤተሰቦቻቸው እንዲጠየቅ፣ ቋሚ የቆንስላና የህግ ምክር እንዲያገኝ በተደጋጋሚ የቀረበው ጥያቄ በወያኔ አገዛዝ ውድቅ መደረጉ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚያሻክር መሆኑ ከወትሮው ጠንከር ባሉ ቃላት ገልጿል። አዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታኒያ አምባሳደርም እንደዚሁ ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ለስላሳነት ወጣ ያለ ያለ መግለጫ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚታተመው ሪፓርተር ጋዜጣ ሰጥቷል። እነዚህ የሰሞኑ የእንግሊዝ መንግሥት መግለጫዎች በቀና የሚታዩ ቢሆንም የብሪታኒያ መንግሥት ማድረግ ይገባው ከነበረው እና ማድረግ ከሚችለው አንፃር ሲታይ ብዙ ይቀረዋል። የአውሮፓ ኅብረት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በተደጋጋሚ አንስቷል። የተባበሩት መንግሥታትም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዝ ጉዳይ ምርመራ እንዲደረግበት እንቅስቃሴ ጀምሯል። ከላይ የተዘረዘሩት ኩነቶች፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለሟቋረጥ የሚያደርጉት ውትወታ ውጤት እያመጣ መሆኑ ያሳያል። ይህ ጥረት ለወደፊቱም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አስልጥኖ አሰማርቷችኋል” ተብለው እንደተለመደው በሀሰት የተከሰሱ ወገኖቻችን “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ መከላከያ ምስክር እንዲሆኑን ይታዘዝልን“ ብለው ሲጠይቁ ዳኛ ተብየው “የት እንደሚገኙ የማይታወቁ ሰውን በመከላከያ ምስክርነት ማቅረብ ይከብዳል” ብሎ ሲናገር ተደምጧል። አቶ አንዳርጋቸው ለምስክርነት ይቅረብ አይቅረብ ብይን ሊሰጥበት ቀጠሮ ተይዟል።

Thursday, July 2, 2015

Ethiopia: Respect court rulings and release opposition members

Ethiopian authorities must stop harassing two men and two women linked to the opposition Semayawi (Blue) Party, and immediately release them from detention, Amnesty International said as
they were expected to face fresh charges in court today in the capital Addis Ababa.

“On five separate occasions over the course of the last 10 days, three different courts have ordered the police to release these four people,” said Michelle Kagari, Deputy Regional Director for East Africa, the Horn and Great Lakes. “Their continued detention is blatantly unlawful and in clear violation of their rights to liberty and a fair trial.”

Woyneshet Molla, Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye and Betelehem Akalework were arrested in April this year and charged with inciting violence during a rally in the capital. They remained in custody awaiting trial. The four were convicted at the Federal First Instance Criminal Court at Kirkos on 22 June 2015 and sentenced to two months in prison. The judge however ordered their immediate release on the basis that they had already served their time, but the police ignored court orders and returned them to Kality and Kilinto prisons.

They were released the following morning, but police and security officials immediately re-arrested the four without a warrant and brought them to Kasanchiz 6th police station. On 25 June, they were presented on the same charges before the same judge that had ordered their release. He dismissed the case and again ordered their immediate release but the police did not comply and instead unsuccessfully sought to have another judge in the same court accept the case.




The following day the police brought the four before a new judge at Keraa Federal First Instance Court, on new charges of threatening witnesses to their original case. In a hearing on 30 June the court accepted the case, but ordered that the accused be released on bail pending the case’s resumption today. Again, the police disregarded court orders and the four remain in custody.

Separately, the Federal High Court Lideta Branch on 29 June accepted to hear the public prosecutor’s appeal against the original verdict, but refused their request to keep the four in custody. The appeal has been adjourned until 3 July.

“This charade must come to a halt. These four men and women have already served their jail term. This blatant disregard for judicial orders, and attempts to press fresh charges amounts to persecution, and takes harassment and intimidation to new heights,”

Said Michelle Kagari, Deputy Regional Director, Amnesty International.
“By keeping Woyneshet Molla, Ermias Tsegaye, Daniel Tesfaye and Betelehem Akalework in detention, the Ethiopian authorities are undermining the credibility and authority of the court process and eroding the rule of law. They must stop harassing opposition members and ensure that the right to a fair trial is upheld.”

Background

Scores of demonstrators including opposition party members and officials were arrested and charged with inciting violence at a rally in Addis Ababa on 22 April. The rally had been organized as part of three days of mourning for 26 Ethiopians killed by the armed group calling itself Islamic State in Libya. Amnesty International issued a public statement calling for restraint from the police while managing demonstrations and adherence to regional and international laws and standards.

Members of the Blue Party were amongst those opposition party members arrested. Some of the party officials – Blen Mesfin, Tewachew Damtew, Matias Mekuriya, Sintayehu Chekol, Tewodros Assfaw and Meron Alemayehu – who were arrested in Addis Ababa in the days following the 22 April rally remain behind bars. Nigist Wondefraw and Wondemagegen Assefaw, also members of the Blue Party, were arrested in Addis Ababa on 27 May and 3 June respectively and accused of inciting violence at the rally. Wondemagegen was released after four days in custody but Nigist is still being held.

Amnesty International has learnt that several other demonstrators including Blue Party members arrested during the election campaigning period are still detained and are undergoing trial. Natnael Yalemzewud was sentenced to three years in prison charged with inciting violence at the 22 April rally and for insulting the Prime Minister while he was delivering a speech to the public during the mourning ceremony at Mesqel Square. Four other individuals who are not party members were sentenced on 2 June 2015 to five months in jail under the same charge as well as the additional charge of singing anti-government songs during the rally.