Monday, March 31, 2014

በሀረር ከተማ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ድበደባ እየተካሄደባቸው ነው

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስር ቤት ምንጮች እንደገለጹት በሀረር ከደረሰው ተደጋጋሚ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተቃውሞቸውን አሰምተዋል በሚል የታሰሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፌደራል ደህንነት መርማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ እየተካሄደባቸው ነው:፡
ፖሊስ ጋራጅ ውስጥ የታሰሩት ወጣቶች ከምግብ ተከልክለው ከዘመድ እንዳይገናኙ ተደርገው ” እመኑ” በሚል ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው። ታከሉ ሙላቱ፣ ታገሰ ሙላቱና አዳነ የሚባሉ የጫማ ንግድ ድርጅት ባለቤቶች ከፍተኛ ድበደባ ተፈጽሞባቸው ራሳቸውን ስተው እንደነበር የእስር ቤት ምንጮች ገልጸዋል። በተለይ ታከለ ሙላቱ የተባለው ነጋዴ  ወደ ጀጉላ ሆስፒታል ቢወሰድም፣ ከሆስፒታል በሁዋላ የት እንደተወሰደ አልታወቅም።
በጥይት ተደብድበው የሞቱ ሰዎች መኖራቸውንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ተወከል የሚባል ወጣት ደረቱ አካባቢ በጥይት ተመትቶ በህክምና ላይ ነው።
ገንዘብ አላቸው የሚባሉ ነጋዴዎችን ደግሞ ” ተጠርጣሪዎች ናችሁ” በሚል እየታሰሩ ፣ ፖሊሶች ጉቦ እየተቀበሉ እየለቀቁዋቸው መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
መስተዳድሩ በቅርቡ በሃረር የደረሰውን  የእሳት አደጋ መነሻ በተመለከተ የተለያዩና የተምታቱ መግለጫዎችን እየሰጠ ነው።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የአንድነት ፓርቲን የሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከንቲባ ጽህፈት ቤቱ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎች ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ ለፓርቲው በጻፉት ደብዳቤ ” የአዲስ አበባ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነስርአት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ  የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ” አልተቀበንነውም ብለዋል።
የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት እንደገለጹት ፓርቲው የመስተዳድሩን ደብዳቤ አልተቀበለውም። መስተዳደሩ በ12 ሰአታት ውስጥ መልስ መስጠት ቢኖርበትም ይህን አለማድረጉን፣ መስተዳድሩ አማራጭ መስመር አቅርቡ ባለማለቱም ፓርቲው ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት እንደሚቀጥል ገልጸዋል

Sunday, March 30, 2014

የጥላቻው እሳት ቆስቋሹን ያቃጥለው

የጥላቻው እሳት ቆስቋሹን ያቃጥለው
March 30, 2014
ዳኛቸው ቢያድግልኝ

የትግል መሰረቱን ጎጥ ላይ ያደረገ፣ የእድገት ልኩን ዘረፋ ላይ ያዋለና የእውቀት ጥጉን ውሸት ላይ የመሰረተ እንዴትም ሆኖ የነጻነት ታጋይ አይሆንም። ይልቁንም በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተንፈራጥጦ እንዲኖር የክፋት መርዙን ይረጫል እንጂ። ምንም በሁኔታዎች አስገዳጅነት ቢተጣጠፍ እንኳ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የማድረግ አቅም ስለሌለው ሕብረት ያስፈራዋል፣ ነጻነት ያጥወለውለዋል፣ አንድነትም ያስበረግገዋል። ኢትዮጵያ ለወያኔ ትርፍ እስካስገኘች ድረስ እንደምትታለብ ላም ነች። ከዚያ በላይ ወያኔዎች ሀገራዊ ራዕይ የሚባል ነገር የላቸውም።

እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ያለብንን ፈተና በጎጥ መነጽር አይተን በጥላቻ ክርክር ተጯጩኸን በግል ስምና ዝና ጦዘን ልንወጣው ፈጽሞ አይቻለንም። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እለት በእለት የምንመለከተው ሁነት እያሳየን ያለው ተፋቅረንና  ተደጋገፈን መኖር የሚገባን ወገኖች ተናንቀን ስንነካከስ ነው። ጃስ እያሉ የሚያናክሱን ደግሞ እንግሊዝ በቀበረው የእርስ በእርስ መተላለቂያ ፈንጂ፣ ጣልያን በቀመመው የጎሳ ክልል መርዝና በየሃገሩ እሳት ጭረው በሚወጡት ለጥቅማቸው ሲሉ ምንም ከማድረግ በማይመለሱ ሀያላን እገዛ እየተጠቀሙ ወደ ጥፋት የሚነዱን ደናቁርቶች ናቸው። ሰሞኑን በወያኔዎችና ለወያኔ የጥላቻና ፕሮፖጋንዳ ሰለባ በሆኑ ቡድኖች ወገኖቻችንን በዘር ለማናከስ እንደ አበደ ውሻ የሚክለፈለፉ በዝተዋል። የሰከነ የአንድነት ድምጽ እንዳይደመጥ ወያኔ ከፍተኛ አፈና በሚያደርግባት ኢትዮጵያ ጎልቶ የሚደመጠው የደንቆሮ ጩኸት ነውና አማራጭ ድምጽ እንዲደመጥ ካላደርግን ህዝባችን ሊወናበድ ይችላል።

በከሃዲና ስግብግብ የአፍሪካ መሪ ተብዬዎች ውክልና የሀገርና አህጉር ሀብትና ቅርስ በንግድ ሽፋን ዘረፋ ላይ ለተሰማሩ ሀገር በቀልና የወጪ ከበርቴዎች እየተቸረ ነው። በዘመናዊ ትምህርት ስም የሀገር ፍቅርንና ለህዝብ የመቆም አስፈላጊነት ችላ እንድንል የተበረታታን ተልፈሰፈስንና የማንነት መሰረታችን ተናግቶብን ብዙ ዘመነኞች እኛንና ህዝባችንን ለብልቦ የሚፈጀንን የጥፋት እሳት እንደ ደመራ እያጨበጨብን ከበን እያየነው እንገኛለን።  ኢትዮጵያ በታሪክዋ አይታ የማታውቀው በሌላውም አለም ያልተለመደ አይነት አሳፋሪ የሀገር ጠላት የሆነ የዱርዬ ስብስብ መንግስት ነኝ እያለ አገሪቱን ለእቁብ ወይንም ለቤት ኪራይ ገንዘብ እንዳጠረው ነጋዴ ሃገራችንን በርካሽ ዋጋ እየቸበቸበ ይገኛል።

በሀገር ልማት ስም ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው የብድር መአት በኛ ዘመን ቀርቶ በልጅ ልጆቻችን ጊዜም ተከፍሎ አያልቅም። የተበደሩት ገንዘብ ግን ግማሹ ወደ መጣበት ሀገር ተመልሶ በሌቦቹ ባለስልጣናት ስም በተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች ገቢ ተደርጎ የጨረቃ ሚሊየነሮችን መፍጠሪያ ሆኗል። ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መሰረትዋና አብዛኛው ህዝቡዋ የሚተዳደርበት ሁኖ ሳለ የእርሻ መሬቶች ለውጪ መንግስታትና ግለሰቦች እየተቸበቸቡ ነው። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ዛሬ መሬት አልባ ነገ ደግሞ አገር አልባ  ያደርጋቸዋል።

የዛሬዎቹ መሪ ተብዬዎች መሬትን መያዝ ሀገርን መቆጣጠር ነው ብለውም ነው መሬት የመንግስት ነው የሚሉት። አዎን ዛሬ መሬት የትግራይ ማፊያዎች ሀብት ነው። ያሻቸውን ለማድረግ የያዙት ታንክና ላውንቸር መብት አጎናጽፎአቸዋል። የተቀረው ኢትዮጵያዊ መሬትም መብትም የለውም! ሌላ ቀርቶ ነገና ከነገወዲያ ጤፍ፣ ስንዴና ገብስም የትላልቅ ‘ምርጥ ዘር’ አምራቾች ሸቀጥ እንጂ ለዘመናት መሬቱንና የሰብሉን ዘር ሲንከባከብ የኖረው ገበሬው ሀብት አይሆኑም። ገበሬው የዘርና ማዳበርያ ዋጋ መክፈል እያቃተው መሬቱን ጥሎ ለማኝና ስደተኛ እንዲሆን እያደረጉት ነው። ይህን አደገኛ አኪያሄድ አሁን ካልገደብነው ኢትዮጵያ የምትባል አገር መኖሩዋ አጠራጣሪ ይሆናል። ይህም ባይሆን እንኩዋን ህዝባችን በገዛ ሀገሩ ለጥቂት የውጭና የውስጥ ዘራፊ ባለሃብቶች ጪሰኛ ይሆናል። ወያኔዎች ያለመታከት ለዚህ መከራ እያሰናዱን ነው እኛም ዛሬ ለነሱ ደባ ተመቻችተንላቸው ለዘመናት በጎሳ በቁዋንቁዋም ይሁን በሀይማኖት ሳንለያይ አብረን መኖራችንን ችላ በማለት በጎጥ አንሰን  በመንደርም እየተከፋፈልን  አገርም ማንነትም ለሚያሳጡን አረመኔዎች በራችንን በርግደን እንዲያምሱን ልንፈቅድ አይገባም።

ዛሬ በራሱና በወገኖቹ ላይ በሚደርሰው ሰቆቃ በማዘን “ራሴን ጠላሁ” “በኢትዮጵያዊነቴ አፈርኩ” የሚለው የተቆጣ ሕዝብ ብዙ ነው። ይህን ቁጣውንና ዱላውን ለሰቆቃው ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይ እንዳያሳርፍ እነ ስብሃትና በረከት ስምኦን ጸቡን በአማራና ኦሮሞ፣ በክርስትያንና ሙስሊም ወ.ዘ.ተ. መካከል ለማስቀረትና ለኛው የእልቂት ድግስ መደገስ ከጀመሩ ብዙ ቆዩ። ያለመንግስትና ያለፖሊስ ተከባብሮ የመኖር ድንቅ ባህልን ያዳበረውን ሕዝብ ዛሬ አናቁረውት ሌብነት ቅጥፈትና ዘረፋ የብልጥ መንገድ እንደሆነ እየሰበኩ ወደ ንቅዘት የሚመሩት እነዚሁ የወያኔ ወሮበሎች ናቸው። የማይሞላ ከርስና ባዶ ጭንቅላት ያላቸው የየብሄረሰቡ ተወካይ ተብዬዎች ደግሞ አንደ ተወጠረ ከበሮ አለቆቻቸው ትንሽ ኮርኮም ወይም ኮርኮር  ሲያደርጉዋቸው ይጮሀሉ። በጎሳና ሀይማኖት ህዝባችን አይነጣጠልም  ያልነው እውነት እንዲሆን እርስ በራሳችን እንዳንፋጅ ሁላችንም የወያኔን የጥላቻ ቅስቀሳ ልማክሰም የድርሻችንን የምናደርግበት  ጊዜ ዛሬ ነው። ይሄ አያገባኝም ወይም አይደርስብኝም ማለት ከሌሎች ተሞክሮ አለመማር  ይሆናል።

ሩዋንዳውያን አንድ ሚሊየን ያህል ወገኖቻቸው በግፍ ከተፈጁ በሁዋላ በህልማችንም በእውናችንም ጉዋደኛ ለጉዋደኛ ጎረቤት ለጎረቤት እየተራረድን እንዲህ ያለ ክፋት እኛው በኛው ላይ እንፈጸማለን ብለን አናስብም ነበር ሲሉ መስማት የተለመደ ነው። ከበርካታ አመታት በሁዋላ በሕዝብዋ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አሁንም ድረስ ድባቡ አልጠፋም። አሁንም ድረስ እያስታወሱ የሚያለቅሱ አሉ። በዚሁ ግፍ ምክንያት በርካቶች አይምሮአቸውንም ስተዋል። በቁንጅናዋ ተማርኮ በጸባይዋ ተመስጦ አፍቅሮ ያገባትን ሚስቱንና የልጆቹን እናት የጥላቻ ቅስቀሳ ሰለባ በመሆን በቆንጨራ ጨፍጭፎ እንዲገድል የተደረገ ሰው በህይወት ቢኖርም ሰው መሆን አይችልም። ሺህ ይቅርታ ሺህ ሱባዔ ሺህ ቅጣት ያንን ጤና መልሶ ሊሰጠው አይችልም። የጥላቻውን መርዝ መጀመሪያ የረጩትና እሳቱን ያራገቡት ግን ለመግዛት እንዲመቻቸው አንዱን ከሌላው አሳንሰው እርስበርስ እንዲጠላላ በማድረግ የኖሩት ቅኝ ገዢዎቹ ናቸው። ከነጻነት  በሁዋላም ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ በጥላቻ እንዲነሳሳና ያ ሁሉ እልቂት እንዲፈጸም እጃቸው አለበት የሚባሉት መስቀል ይዘው ክርስትና ሰባኪ ነን የሚሉ ነጮች መሆናቸው ይነገራል።

ኤርትራ “በነጻ አውጪዎቹ” ስትያዝ ለብዙ አመታት እዚያው ኑሮ መስርተው ሃብት አፍርተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን “አያት ቅድም አያቶቻችሁ ከዚህ አይደሉም” እየተባሉ በጎሳ ጥላቻ ቤተሰባቸው እንዲፈርስ ተደርጎ ባዶ እጃቸውን በባዶ እግር እንዲባረሩ ወደባህርም እንዲገፉ የተደርጉትን ልናስብ ይገባል። ከመሀል አገርም ከሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ጋር ተጋብተው ይኖሩ የነበሩ ኤርትራውያን እራሱ ኤርትራው በሆነው በመለሰ ዜናዊ “የአይናቸው ቀለም ካላማረን እናባርራልን” የሚል የ እብሪት ፖለቲካ ቤተሰባቸውንና ንብረታቸውን በትነው ከሀገር እንዲወጡ እንደተደርጉ  ልናስታውስ ይገባል። ዛሬም ከየቦታው የሚፈናቀሉት ወገኖቻችንን  ቁጣ ልናስብና ይህ ቁጣም ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ማሰቡ ከሚጠብቀን አደጋ እንድንጠነቀቅ ያመቻቻል።

አማራው ከኦሮሞው ቢጣላ ገላጋይ ሆነን እንቆማለን የሚሉት የትግራይ ተገንጣይ ቡድን አባላትና ደላሎቻቸው ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ ደፋ ቀና የሚሉት እሳቱ ቢነሳ እነርሱ የሚተርፉ መስሏቸው ነው። የተገፋው የተጨቆነውና በደል በቃኝ የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቱን ለይቶ አውቆ የጥላቻ እሳት እየቆሰቆሱ ያሉትን በተባበረ ክንድ ሊደቁሳቸው እንደሚችል የተገነዘቡ አይመስልም። ለዚህም ነው ሕዝቡ ቁጣውን ወደነዚህ አረመኔዎች ሊያዞርና ሴራቸውን ሊያከሽፍ የሚገባው ዛሬ ነው ጊዜው እየረፈደም ነው የሚል ጥሪ ከየአቅጣጫው የሚስተጋባው። በርካቶች ወደ ጥላቻ ወጥመዳቸው እንዳይገቡ እነዚህን ክፉዎች መንጥሮ ማውጣት ለነገ የማይባል አስቸኩዋይ የህልውና ጥያቄ ነው። መሰረታዊው ልዩነት ሀገር በሚዘርፉ፣ በሚያፈርሱና እልቂት በሚደግሱት ወያኔዎችና በተቀሩት ኢትዮጵያውያን መካከል እንጂ በተለያዩ ብሄረሰቦችና ሃይማኖት ተከታዮች መሀከል አይደለም።

በምዕራቡ ሀገራት በሚሰበክው የመድብለ ፓርቲዎች አስፈላጊነት ምክንያት ኬንያ በርካታ ፓርቲዎች ማቋቋም ባሰበችበት ወቅት ፖለቲከኞቹ መራጮቻቸውን ፍለጋ በየጎጡ መሄዳቸው ያስከተለው ከባድ ቀውስ ዛሬ የሚታወስ ነው። አሜሪካ መድብለ ፓርቲ ብላ አስጨንቃ ከያዘችን ብለው እነዚያው የቀድሞ ፖለቲከኞች ወደየዘመዶቻቸው ሲሄዱ ይህ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ያገናዘበ አገናዝቦም መፍትሄ የሰጠ አልነበረም። ብዙ ፓርቲዎችም ተፈጠሩ ግን የጎጥ ፓርቲዎች ሆኑ። ይህን በመከተልም አሰቃቂ የሆነ አደጋ ሰላማዊ ተብላ በምትታወቀው አገር ተከሰተ። የአንድ ሀገር ልጆች መሆናቸውን ከመቅጽበት ዘንገተው ኩኩዩ ሉዎ እየተባባሉ በገጀራና በቀስት እርስበርስ ይገዳደሉ ጀመር። ኬንያውያንም እኛ ሰላም ወዳዶችና የጎሳ ፖለቲካ ወደ ጽንፍ የማይወስደን ነን  የሚል ጽኑ እምነት የነበራችው ቢሆኑም የጥላቻው ቅስቀሳ ለጊዜያው የፖለቲካ ጥቅም ከተለኮሰ በሁዋላ በሀገራችን እናያለን ብለው ያልገመቱት የጥላቻ ግድያ ሲፈጸም ለመመልከትና ተሳታፊም ለመሆን ተገደዱ። ። የረገፉት ረገፉ የተፈናቀሉትና ከሞት የተረፉት ግን ዳግም የሰላም እንቅልፍ አይኖራቸውም። ኬንያ የበርካታ የውጭ መንገስታትና ድርጅቶች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያገኙባት ሀገር በምሆኑዋ ዓለም ትኩረት ሰጥቶት እንደ ኮፊ አናን ያሉ መፍትሄ አፈላላጊዎች ሁሉ ተረባርበው እሳቱን ለጊዜውም ቢሆን አበረዱት።

የኛዋ ኢትዮጵያ ግን እኛው ካላዳንናት   በእሳቱ ላይ ነዳጅ የሚጨምር እንጂ እሳት የሚያበርድላት ብዙ እንደማይኖር ልብ ልንል ይገባል። ወራሪን በማሸነፍ የሚገኝ ነፃነት የሚያስከፍለውን መስዋትነት በኩራት ልንሸከም የሚገባን እኛው ኢትዮጵያውያን ነን። አዋሳኝ አገሮችም በአብዛኛው ለኛ መዳከምና መበታተን ተግተው የሚሰሩ ናቸው። የጎጠኞችና የባንዳዎች ብቸኛ ሕልም ደግሞ ምንም ያክል ትሁን ስልጣንና ሀብት ማጋበስ ብቻ ነው። በጎጥ የጀመረ ፀብ በእንጭጩ ካለተቀጨ መንደርና ቤተሰብ ድረስ ይዘልቃል። የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ሚሊየኖችን አስፈጅቶ ስልጣኑና ሀብቱ ግን የተገደበው በጥቂት ቤተሰብና መንደር ላይ መሆኑ ሩቅ የማይወስድ ምሳሌ ነው። የትግራይ ሕዝብ በጥቅሉ ከሌላው በተለየ ደስተኛ እንዳልሆነ ማየት ትምህርት ነው። በመከባበርና በመተሳሰብ ለልጆቻችን ለልጅ ልጆቻችን ህልውናና ነፃነት ስንል የአቅማችንን እንስራ ኢትዮጵያንም እናድናት።

በጎጠኞች መርዘኛ ሴራ ኢትዮጵያዊነት አይረታም!

ኢትዮጵያ በነፃነትዋ ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!

የወያኔን ከፋፋይ አገዛዝ እናምክን

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ሊከበርላቸውና ሊያሳድጋቸው የሚገቡ የተለያዩ የባህልና የታሪክ ቅርሶች ያሏቸውን ያህል በብዙ መንገድ የሚያይዝ የጋራ ታሪክ ቅርስና ዝምድና አላቸው። ልዩነቶቹ ራሳቸው ተጠቃቃሚ ለሆነ የእርስበርስ ግንኙነታቸው ጠቃሚ እንጂ ከአንድ ሀገር ማህበረሰብነታቸውና ከጋራ ህልማቸው ጋር የሚጋጩ የጠብና የግጭት መንስኤዎች አይደሉም። ከጠብና ግጭት ማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ተጠቃሚ አይደለም። ከጠብና ግጭት ጥቅም ይገኛል ብለው የሚያስቡ “ግርግር ለሌባ ይመቻል” የሚለውን የወሮ በላ ፍልስፍና የሚከተሉ የቀን ጅቦች እንጂ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አይደሉም። በወያኔ የግዛት ዘመን የደረሱትን ግጭቶች መፈናቅሎችና የተፈጠሩትን የእርስበርስ ጥርጣሬዎችን ልብ ብሎ ለተመለከተ ሁሉም በአገዛዙ እና በሎሌ የበታች ሹማምንቱ የተፈጠሩ እንጂ አንድም ጊዜ እንኳን ከህዝብ የመነጩ አይደሉም።

የወያኔ ጉጅሌ በአገዛዝ ዘመኑ ሁሉ ብሄር ብሄረሰቦችን ከሚያይዟቸው የጋራ ማህበራዊ ቅርሶችና ህልሞች ይልቅ ካለመታከት ልዩነቶቻችን ላይ ያተኮረ ፖለቲካ እያካሄደ እንዳለ ግልጽ ነው። ከዚህ አልፎም አዳዲስ የእርስበርስ ግጭቶችን እና ጠቦች እንዲፈጠሩ ተግቶ የሚሰራ ከፋፋይ ቡድን ነው። እርስበርሱ መጠራጠርና መፈራራት እንዲሰፍን ልዩ ልዩ ስልቶችን ይቀይሳል። ከአንዱ ብሄረሰብ ተንኳሽ አዘጋጅቶ ሌላው ብሄረሰብ ላይ አደጋ እንዲደርስ ከዚያም ተጠቃሁ የሚለው አጸፋ እንዲመልስ ያደርጋል። የአንዱን ብሄረሰብ መንደርና ንeበረት በእሳት ለኩሶ በሌላው ብሄረሰብ እንዲመካኝ ያድርጋል። አንዱ በአንዱ ላይ እንዲያማርር ከንፈሩን እንዲነክስ ማድረግ ለወያኔ ጉጅሌዎችና ለሎሌዎቻቸው እንደፖለቲካ ጥበብ ከታየ ሁለት አስርት አመታት አልፈዋል። በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች የተቀሰቀሱ የርስበርስ ጥርጣሬዎችና ግጭቶችን ያሸተተ ሁሉ ወያኔ፣ ወያኔ እንደሚገሙ ያረጋገጠው ጉዳይ ነው።

ወያኔዎች የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ከፋፍለውና ከቻሉም አጋጭተው ካልሆነ በስተቀር የዝርፊየ ኢኮኖሚያቸውን መቀጠል እንደማይችሉ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የጋራ ጥቅማቸውንና ህልማቸውን ይዘው የተነሱ እለት ወያኔ ያከተመለት መሆኑን ያውቃል። ለዚህም ነው በየክልሉ እና ዞኑ በፍጹም ከሆዳቸውና ጥቅማቸው በላይ ማሰብ የማይችሉ ግለሰቦችን ከየብሄረሰቡ እየመረጠ የሚሾምልን። ወያኔ ነጻ የህዝብ ምርጫ የሚፈራው ለዚህ ማረጋገጫ ነው፡፡

የወያኔ ጉጅሌዎች ከጊዚያዊ ጥቅም በዘለለ ማሰብ ስለተሳናቸው እንጂ ይህ አካሄዳቸው ለራሳቸውም ለዘለቄታው የማይጠቅም መሆኑን ዘንግተውታል። በልዩነታችን ላይ መጫወት ማለት በእሳት እንደ መጫወት የማይመስላቸው ለዚህም ነው። ይህ የተጀመረው እሳት ራሳቸውንም አይምርም።

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መላው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች የጋራ ግብና የተሻለው የነገ ነጻነት ተስፋቸው የሚረጋገጠው በጋራና እጅ ለእጅ ተያይዘው በሚያደርጉት ትግል ብቻ ነው ብሎ ያምናል። ለዚህ የወያኔ መሰሪ የከፋፍለህና አጋጭተህ ግዛ ተንኮል ራሳችንን እንዳናመቻች የገዛ መከራችንን ማራዘሚያ እድል ለዘራፊ ገዥዎቻችን እንዳንሰጥና ለጋራ ህልማችን እንድንቆም ጥሪውን ያቀርባል።

የወያኔ ጉጅሌ ሆን ብሎ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እንዲጋጩ፣ እርስበርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩና እንዲፈራሩ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ድርጊቱ በእሳት መጫወት መሆኑን አውቆ ከዚህ እኩይ ተግባር እንዲታቀብ ግንቦት 7 እያሳሰበ በማንኛውም ሁኔታ በማህበረሰቦች መካከል ለሚደርስ ግጭትና ጉዳት ሙሉ ሀላፊነቱ የወያኔና የወያኔ ብቻ መሆኑን አጥብቆ ያስገነዝባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!



Wednesday, March 26, 2014

ሃያ ሦስት የስቃይ፤ የሰቆቃና የእልቂትና ዓመታት

የኢትዮጵያ ህዝብ በፋሽስቱ ህወሓት ብልሹ አስተዳደርና አምባገነናዊ አገዛዝ ስር ወድቆ በኑሮ ውድነትና በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ፣ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱ ተነጥቆ ለአፈናና ለእስራት እየተዳረገ፣ ሉዓላዊ ክብሩ ተደፍሮ ለም መሬቱንና አንጡራ ሃብቱን እየተሸነሸነና እየተቦረቦረ ለባዕድ እየተሸጠ፣ በገዛ ሀገሩ ተፈናቃይና የውጭ እጅ ተመልካች ሆኖ ለስደትና ለእንግልት እየተዳረገ እነሆ ዛሬ ከ23 ዓመት በላይ የሰቆቃ፣ የእልቂትና የመከራ ዓመታት ተቆጠሩ።

ለአለፉት 23 ዓመታት የደፈረሰው ፖለቲካችን ወደ ጭቃነት እየተቀየረ ስለመሆኑም ምንም ምስክር አያሻውም።ፋሽስቱ ወያኔ ከሀገር ሉዓላዊነት እስከ ታሪካችን፣ ከባንዲራችን እስከ እንደ ሕዝብና እንደ ሀገር ያለን ደረጃ መቀመቅ አውርዶታል። አንዳንዶቻችን እንደዚህ ዘመን ትውልድ አባልነታችን ያለፈውን መለወጥ፣ ዛሬን የሰውነት ደረጀችን በጠበቀ ሁኔታ መኖርና ነገንም ላልተወለዱ ልጆቻችን መልክ አስይዞ ለማውረስ ከቁጥጥራችን እየወጣ መሆኑን በግልጽ እንመለከታለን። በሌላ ወገን ወያኔዎቹ የአለፉት 23 ዓመታት የአንድ ጀምበር ያህል አጥረውባቸው፤ ተጨማሪ 40 አመታትን ለመግዛት በማለም ሲንፈራገጡና በቀቢጸ ተስፋ ህዝብን ለማማለል ሲሞክሩ እያየንና እየሰማን ነው። ስንራብ መጥገባችንን ይነግሩናል። ስንታረዝ ደራርበን መጎናፀፋችን ይታያቸዋል። ሀገራችን ከአለም ሀገሮች ተርታ በሁሉም መስኮች ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ በማይታመን ፍጥነት እየወጣች ወደ ግርጌ ስትወረወር፤ ወንበዴዎቹ ወያኔወች ግን ሀገራችን ተሞሸረች አማራች ይሉናል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲረግጡት የሚደቅን ቅጠል ያህል በመቁጠር ከህግና ከአመክንዮ ውጭ በማን አለብኝነት ሕዝባችንን በንግድ ድርጅቶቻቸው እየገፈፉ እርቃኑን አስቀርተውታል።

ጉጅሌው ወያኔ ሥልጣን ሲይዝ፣ ከፎከረባቸው አንዱ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሶስቴ የሚበላበትን ሁኔት ፈጥሮ ከረሀብ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚገላገልበትን ባዶ ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር። ነገር ግን ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሶስቴ አበሳውን እየበላ ይገኛል። ምግብማ ከየት ተገኝቶ! ረሀቡ፣ ጠኔው ከዛሬ ሀያ ዓመት ሁኔታ በሶስት ዕጥፍ ጨምሮ፣ ዛሬ እስከ 25 ሚሊዮን ሕዝብ ጦሙን የሚያድርባት አገር ስለሆነች በየጊዜው የተባበሩት መንግስታትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከሚያወጡት መግለጫ መረዳት ይቻላል። ዛሬማ፣ ነጻ ገበያ ብሎ የፎከረብን ነጻነት ተረስቶ የዘይትና የስኳር ዋጋ እስከመቆጣጠር ገብቷል። ከመብራት፣ ውሃና ኔትዎርክም ብሶ ህዝብ በእጦት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ይገኛል። በቅርቡም በመላ ሃገሪቱ መብራት፣ ውሃና ኔትዎርክ እጦትን አስመልክቶ ሰልፍ ሊወጣ ቅድመ ዝግጅቶች እየተገባደዱ እንደሆነም እየተሰማ ነው። ከዚህ በላይ የጨለማ ጊዜ የለም።

የወያኔ አገዛዝ ለአለፉት 23 ዓመታት የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ በመስጠትም በተደጋጋሚ ብሄራዊ ክህደት ሲፈጽም የቆየ ቡድን ነው። ይህንን ብሄራዊ ክህደት ሲፈጽም ካለማወቅ፤ ከችኮላ ወይም በደመነፍስ ከመጓዝ የተሠራ ስህተት አይደለም። ከአጠቃላይ የፓለቲካ ስትራተጂውና ግብ ጋር የተያያዘ አካሄድ ስለመሆኑ መስካሪ አያሻም። ፋሽስቱ ህወሓት በህዝብ የተተፋ ቡድን በመሆኑ የሀገሪቱን ፓለቲካና ኤኮኖሚ ለመቆጣጠር የውጭ ኃይሎችን የገንዘብ፤ የወታደራዊና የዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ስለሚሻ ነው የሀገሪቷን ብሄራዊ ጥቅሞች መረን በለቀቀና ድፍረት በተሞላበት መልክ ለውጭ ኃይሎች በየጊዜው አሳልፎ የሚሰጠው።ለዚህም ነው የምግብ እጥረት ያለባት የሀገራችንን ሰፋፊ ድንግል መሬቶቿን ለሀገሪቷ ዜጎች ከልክሎና አፈናቅሎ ለመካከለኛው ምሥራቅና ለእስያ ሀገሮች ልማታዊ ድርጅቶች በነፃ በሚባል ደረጃ እስከ 99 ዓመት በሚደርስ ውል ፈርሞ እየሸጠ የሚገኘው። ሰፊ ለም የድንበር መሬታችንንም ቆርሶ ለባዕዳን በመሸጥ ላይም ለመሆኑ ከሰሞኑ ለሱዳን ተላልፎ የተሰጠው መሬት ማስረጃ ነው።

በርግጥ የተደራረበ ጭቆናና መከራ ያንገሸገሸውና በልቡ የሸፈተው ህዝብ የጥቂት አምባገነኖችና ሰው በላ መሪዎች የባርነት ቀንበር ተሸክሞ ዘላለም መኖር እንደማይችል ግልፅ እየሆነ መጥቷል። በመሆኑም እንደ እሳተ ጎመራ ውስጡ ውስጡን እየተብላላ ቆይቶ ዛሬ ሊፈነዳ የተቀራበውን የህዝብ ዓመፅ መለብለብ የማይቀርላቸው መሆኑን በውል የተረዳው የጉጅሌው ወያኔ ቡድን ከመቼውም በላይ በፍርሃትና በጭንቀት ተውጠው እንዳበደ ውሻ መቅበዝበዝ፣ መወራጨት፣ መናከስና መተራመስ እንደ ጀመሩ በጋሃድ እየታየ ነው። ባለፈው ሳምንት በሰማያዊ ፖርቲ ሴት አመራርና አባላት መሪነት የታየውን አመጽ ተከትሎ ፋሽስቱ ወያኔ የወሰደው እርምጃ ለዚህ በቂ ማሳያ ነው። ሌላው የአዋጅ ጋጋታ፣ የዉሸት እምብልታ፣ ዜጎችን ያላንዳች ምክንያት ማስፈራራት፣ እስር ቤት ማጎር፣ ማሳደድ፣ መግረፍና ማፍን የመሳሰሉ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎች በግልፅ የሚያሳዩን የስርዓቱን መፈረካከስና የውድቀቱን ዋዜማ መቃረቡን ነው።

ስለዚህ ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን በሞት ጣር ላይ ሆኖ እያቃሰተ የሚገኘውን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር መፍትሄው በእጃችን ነው ይላል። ግንቦት 7 መፍትሔው ስለጨቀየው ፖለቲካ እያወሩ ፈጣሪ ባመጣው ይመልሰው ማለት አይደለም ብሎ በፅኑ ያምናል። መፍትሔው እርስ በእርሳችን ስንወጋገዝ መኖርም ሳይሆን ልዩነቶቻችን በማጥበብ፤ ጠብታዎች ባህር እዲሆኑ ማድረግ ነው። መፍትሔው እጅን አጣምሮ ጥቂቶች ታምር እንዲሰሩ መጠበቅም አይደለም። መፍትሔው ከያንዳንዳችን የሚጠበቀውን ሌላውን ሳንጠበቅ መወጣት እንጂ። ስለዚህ አምባገነኖችን መካብ ዙፋናቸውን አግዝፎ በመመልከት ከትግል መሸሽ የችግሩ መፍትሔ በጭራሽ ስለማይሆን ኑ! ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገዛዙን ከህዝብ ጫንቃ ለማውረድና ሃገርን ለማዳን እያደረገ ያለውን ትግል ይቀላቀሉ በማለት ሃገራዊ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።



Ethiopia: Telecom Surveillance Chills Rights

(Berlin) – The Ethiopian government is using foreign technology to bolster its widespread telecom surveillance of opposition activists and journalists both in Ethiopia and abroad.

The 100-page report, “‘They Know Everything We Do’: Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia,” details the technologies the Ethiopian government has acquired from several countries and uses to facilitate surveillance of perceived political opponents inside the country and among the diaspora. The government’s surveillance practices violate the rights to freedom of expression, association, and access to information. The government’s monopoly over all mobile and Internet services through its sole, state-owned telecom operator, Ethio Telecom, facilitates abuse of surveillance powers.

“The Ethiopian government is using control of its telecom system as a tool to silence dissenting voices,” said Arvind Ganesan, business and human rights director at Human Rights Watch. “The foreign firms that are providing products and services that facilitate Ethiopia’s illegal surveillance are risking complicity in rights abuses.”

The report draws on more than 100 interviews with victims of abuses and former intelligence officials in Ethiopia and 10 other countries between September 2012 and February 2014. Because of the government’s complete control over the telecom system, Ethiopian security officials have virtually unlimited access to the call records of all telephone users in Ethiopia. They regularly and easily record phone calls without any legal process or oversight.

Recorded phone calls with family members and friends – particularly those with foreign phone numbers – are often played during abusive interrogations in which people who have been arbitrarily detained are accused of belonging to banned organizations. Mobile networks have been shut down during peaceful protests and protesters’ locations have been identified using information from their mobile phones.

A former opposition party member told Human Rights Watch: “One day they arrested me and they showed me everything. They showed me a list of all my phone calls and they played a conversation I had with my brother. They arrested me because we talked about politics on the phone. It was the first phone I ever owned, and I thought I could finally talk freely.”

The government has curtailed access to information by blocking websites that offer any independent or critical analysis of political events in Ethiopia. In-country testing that Human Rights Watch and Citizen Lab, a University of Toronto research center focusing on internet security and rights, carried out in 2013 showed that Ethiopia continues to block websites of opposition groups, media sites, and bloggers. In a country where there is little in the way of an independent media, access to such information is critical.

Ethiopian authorities using mobile surveillance have frequently targeted the ethnic Oromo population. Taped phone calls have been used to compel people in custody to confess to being part of banned groups, such as the Oromo Liberation Front, which seeks greater autonomy for the Oromo people, or to provide information about members of these groups. Intercepted emails and phone calls have been submitted as evidence in trials under the country’s flawed anti-terrorism law, without indication that judicial warrants were obtained.

The authorities have also detained and interrogated people who received calls from phone numbers outside of Ethiopia that may not be in Ethio Telecom databases. As a result, many Ethiopians, particularly in rural areas, are afraid to call or receive phone calls from abroad, a particular problem for a country that has many nationals working in foreign countries.

Most of the technologies used to monitor telecom activity in Ethiopia have been provided by the Chinese telecom giant ZTE, which has been in the country since at least 2000 and was its exclusive supplier of telecom equipment from 2006 to 2009. ZTE is a major player in the African and global telecom industry, and continues to have a key role in the development of Ethiopia’s fledgling telecom network. ZTE has not responded to Human Rights Watch inquiries about whether it is taking steps to address and prevent human rights abuses linked to unlawful mobile surveillance in Ethiopia.

Several European companies have also provided advanced surveillance technology to Ethiopia, which have been used to target members of the diaspora. Ethiopia appears to have acquired and used United Kingdom and Germany-based Gamma International’s FinFisher and Italy-based Hacking Team’s Remote Control System. These tools give security and intelligence agencies access to files, information, and activity on the infected target’s computer. They can log keystrokes and passwords and turn on a device’s webcam and microphone, effectively turning a computer into a listening device. Ethiopians living in the UK, United States, Norway, and Switzerland are among those known to have been infected with this software, and cases have been brought in the US and UK alleging illegal wiretapping. One Skype conversation gleaned from the computers of infected Ethiopians has appeared on pro-government websites.

Gamma has not responded to Human Rights Watch inquiries as to whether it has any meaningful process in place to restrict the use or sale of these products to governments with poor human rights records. While Hacking Team applies certain precautions to limit abuse of its products, it has not confirmed whether and how those precautions applied to sales to the Ethiopian government.

“Ethiopia’s use of foreign technologies to target opposition members abroad is a deeply troubling example of this unregulated global trade, creating serious risks of abuse,” Ganesan said. “The makers of these tools should take immediate steps to address their misuse; including investigating the use of these tools to target the Ethiopian diaspora and addressing the human rights impact of their Ethiopia operations.”

Such powerful spyware remains virtually unregulated at the global level and there are insufficient national controls or limits on their export, Human Rights Watch said. In 2013, rights groups filed a complaint at the Organization for Economic Co-operation and Development alleging such technologies had been deployed to target activists in Bahrain, and Citizen Lab has found evidence of use of these tools in over 25 countries.

The internationally protected rights to privacy, and freedom of expression, information, and association are enshrined in the Ethiopian constitution. However, Ethiopia either lacks or ignores judicial and legislative mechanisms to protect people from unlawful government surveillance. This danger is made worse by the widespread use of torture and other ill-treatment against political detainees in Ethiopian detention centers.

The extent of Ethiopia’s use of surveillance technologies may be limited by capacity issues and a lack of trust among key government ministries, Human Rights Watch said. But as capacity increases, Ethiopians may increasingly see far more pervasive unlawful use of mobile and email surveillance.

The government’s actual control is exacerbated by the perception among many Ethiopians that government surveillance is omnipresent, resulting in considerable self-censorship, with Ethiopians refraining from openly communicating on a variety of topics across telecom networks. Self-censorship is especially common in rural Ethiopia, where mobile phone coverage and access to the Internet is very limited. The main mode of government control is through extensive networks of informants and a grassroots system of surveillance. This rural legacy means that many rural Ethiopians view mobile phones and other telecommunications technologies as just another tool to monitor them, Human Rights Watch found.

“As Ethiopia’s telecom system grows, there is an increasing need to ensure that proper legal protections are followed and that security officials don’t have unfettered access to people’s private communications,” Ganesan said. “Adoption of Internet and mobile technologies should support democracy, facilitating the spread of ideas and opinions and access to information, rather than being used to stifle people’s rights.”

Monday, March 24, 2014

Hiber Radio: “ቦሌ ኤርፖርት ፓስትፖርቴን የሰጠሁት ሰራተኛ አለቃዬን ላነጋግር ብሎ ገብቶ የፓስፖርቴን አንድ ገጽ ቀዶ በመጣል አንድ ገጽ ጎሎታል አለኝ፤ ቀረሁ” – ኢንጂነር ይልቃል

<<...አሜሪካ ለመምጣት ቦሌ ፓስፖርቴን የሰጠሁት የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ቆይ አለቃዬን አነጋግሬ ልምጣ ብሎ ወደ ሌላ ቢሮ ገብቶ ተመልሼ ሲመጣ ፓስፖርትህ አንድ ገጽ ጎሎታል አለኝ። አንድ ገጽ ቀዶለት ነበር የመጣው። ድርጊቱ ከአገር እንዳልወጣ የተደረገ ነው ..አገሪቱም እነሱም ምን ያህል የወረደ ደረጃ ላይ እንዳሉ የሚያሳይ አሳፋሪም አስቂኝም ድራማ ነበር.. .>>

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወደ አሜሪካ እንዳይመጡ ስለታገዱበት ሁኔታ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ

ውሃ፣ መብራት፣ ኔትዎርክ የለም ፤ ኑሮ ከበደን” ሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮ

“ውሃ የለም፤ መብራት፤ ኔትዎርክ የለም፤ መብት የለም፤ ፍትህ የለም፤ ኑሮ ከበደን” እያሉ ስለኑሮዓቸው የተሰማቸውን በሀቅ የተናገሩ ልጃገረዶች በጋጠወጥ የህወሓት ካድሬዎችና ታጣቂዎች እጅ መከራና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በእነዚህ ለጋ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በዝምታ ያልፋል ተብሎ አይታመንም።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮን ጨምሮ በወያኔና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሥር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን በየዕለቱ ያለማቋረጥ ከሚዘገቡት የልማትና የዕድገት ዘገባዎች ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዘው በአገራችን ውስጥ እየተሠሩ ስላሉ ትላልቅ የሃይድሮ ኤለክትሪክ ማመንጫ ግንባታዎች፤ በየከተማው ስለተዘረጉ የውሃ መስመሮች፤ የስልክ አገልግሎት ለማዳረስ ስለተወሰዱ እርምጃዎች፤ ስለ ረጃጅም የባቡር መስመሮች ግንባታ እና ስለ አገር አቋራጭ የመንገድ ሥራዎች የሚቀርቡ የተጋነኑ ዘገባዎች ናቸው።

እነዚህ የልማት አውታሮች ግንባታ በአብዛኛው የሚካሄዱት ከምዕራባዊያን መንግሥታት በሚሰጡ የገንዘብ እርዳታና ዕዳው ለልጅ ልጆቻችን በሚተርፍ አለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ድርጅቶች ወለድ እያስከፈሉ በሚሰጡት የረጅም ጊዜ ክፍያ ብድር እንደሆነ ግልጽ ነው።

ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 23 አመታት በድህነት ቅነሳና የልማት ማስፋፊያ ስም ከአለም አቀፍ ኅብረተሰብ የተቀበለው የገንዘብ መጠን ሲሰላ ኢትዮጵያ አገራችን እንደ አገር ከተመሰረተችበት ዘመን ጀምሮ በብድርም ሆነ በእርዳታ ስም ይህንን ያህል መጠን ገንዘብ አግኝታ እንደማታውቅ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ ። በዚህም መሠረት ገንዘቡ በአግባብ ሥራ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አገራችን የትና የት በደርሰች ነበር እያሉ የሚቆጩ የአገሪቱ ልሂቃንና ቅን አሳቢ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም ።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት ከ3 አመት ገደማ በፊት ይፋ ባደረገው አንድ መረጃ ወያኔ ሥልጣን በተቆጣጠረባቸው የመጀመሪያዎቹ 9 አመታት ብቻ ከ11.5 (አሥራ አንድ ነጥብ አምስት ) ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በህገወጥ መንገድ ከአገር አሽሽቶ በምዕራባዊያን አገሮች ባንኮች ደብቆአል ። ይህ ከደሃው ጉሮሮ ተቀምቶ በባለሥልጣናቱ የተዘረፈና በህገወጥ መንገድ ከአገር የሸሸው 11.5 ቢሊዮን ዶላር በትክክል ልማት ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ወያኔዎች “ባለ ራዕዩ መሪያቸን” በሚሉት ዘረኛው መለስ ዜናዊ ሥም ለመሰየም ደፋ ቀና የሚሉትን ጅምር “የህዳሴ ግድብ” አይነቱን ሁለት ግዙፍ ግድቦችን በመገንባት የአገሪቷን ገጽታ አበላሽቶ የኖረውን ረሃብ ከምንጩ ማጥፋት ይቻል ነበር።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአገሪቱ የሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፤ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ “ውሃ የለም፣ መብራት የለም፣ ኔትዎርክ የለም። የሚላስ የሚቀመስ ነገር ማግኘት ተስኖናል፤ ኑሮ ከአቅማችን በላይ ሆኖአል። ትዳር መስርተንና ልጆች ወልደን እያሳደግንበት ካለው የደሃ ጎጆዎቻችን በቀበሌ ካድሬዎች ትዕዛዝ ቤቶቻችን በዶዘር ላያችን ላይ እንዲፈርስ ተደርጎ ሜዳ ላይ ተበትነናል። ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ጊዜ ጀምሮ እንገለገልበት ከነበረው የእርሻ ማሳችንና የግጦሽ መሬታችን ተነቅለን ዓይኖቻችን እያዩ ከህንድ፣ ከቻይናና ከአረብ አገር የመጡ ከበርቴዎች መሬታችንን ተቀራምተውታል። አቤት የምንልበት አጣን። ኑሮ መሮናል!!!” የሚሉ እሮሮዎች የወያኔ አፈና የፈጠረውን የፍርሃት ዝምታን ሰብሮ ከአጥናፍ አጥናፍ እየተሰማ ነው።

ይህንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየከረረ የመጣውን የሕዝብ እሮሮ ለማዳመጥ ጆሮ ያልፈጠረበት የዘረኛው ህወሓት አገዛዝ ግን “ነጋ ጠባ የሚደሰኮረው ልማት ምድር ላይ ጠብ አላለልንም፤ መሠረታዊ ችግሮቻችን ከመፍታት ይልቅ እያባባሰ ያለው ምን የሚሉት ልማት ነው?” ብሎ የጠየቀውን ሁሉ “ፀረ-ልማት፣ ፀረ-ሰላም፣ ሽብርተኞ” የሚል ስም እየለጠፈበት ማሰር ማዋከብና ማሳደድ የዘወትር ተግባሩ አድርጎታል።

በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ አለም አቀፍ የሴቶች በዓል ሲከበር ይኸው የሕዝብን ብሶት ባስተጋቡት ወጣት እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ የዚህ የወያኔ አፈና እርምጃ ማሳያ ነው። “ብሶት የፈጠረኝ ነኝ” የሚለው ህወሓት፤ ብሶት እሱን ብቻ ፈጥሮ የመከነ ይመስለዋል።

ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ እያካሄድኩ ነው በሚላቸው ትላልቅና ትናንሽ ግንባታዎች መጠነ ሰፊ ብዝበዛና ዘረፋ እያካሄደ መሆኑን የሚያጋልጡ በቂ መረጃዎች አሉት። የወያኔ ልማትና እድገት ማሳያ ተደርጎ ከሚጠቀሱ የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ግንባታ አንስቶ በመላው አገሪቱ ለሚሠሩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በሙሉ የሚያስፈልጉ የግንባታ ዕቃዎች ስምንቶ፤ አሸዋና ብረታ ብረት የመሳሰሉትን የሚያቀርቡት በባለሥልጣናቱ ንብረትነት የሚታወቁና በቤተሰቦቻቸው ወይም የቅርብ ዘመዶቻቸው ስም የሚተዳደሩ የግል ድርጅቶች ናቸው። የግንባታዎቹን ሥራ ደግሞ የሚያካሂዱት በወያኔ ንብረትነት የሚታወቁ የኢፈርት ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች ናቸው። በዚህ አይነት ኮንትራት ሰጪ፤ ኮንትራት ተቀባይና ዕቃ አቅራቢ በመሆን በሚበዘበዘውና በሚዘረፈው የሕዝብ ሃብት የወያኔ ሹማምንትና ግብረ አበሮቹ እስከ ልጅ ልጆቻቸው በልተው የማይጨርሱትን ሃብት አግበስብሰዋል።

ይህ አልበቃ ብሎአቸውም አይናቸው ያረፈባቸው ቁልፍ የከተማ ቦታዎች ላይ የሰፈረውን ደሃ ሕዝብ በማፈናቀልና ጎዳና ላይ በመበተን ረጃጅም ፎቆችን እየሰሩ በማከራየት ሥራ ላይ ተጠምደዋል። ከአመታት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በአነስተኛ ንግድ የተሰማሩ በርካታ ዜጎች የያዙትን ቦታ ለማስለቀቅ ሆን ተብሎ ንብረታቸው በእሳት እንዲወድም ተደርጎአል። በሕይወት ዘመናቸው ያፈሯት ሃብት በእሳት እንዲጋይባቸው የተደረጉ ዜጎች አቤት የሚሉበት ስላልነበራቸው ሥራ አጥና የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን ተገደዋል። ባለፈው ሁለት ሳምንት ተመሳሳይ እርምጃ ሀረር ከተማ ውስጥ በአነስተኛ ንግድ በተሰማሩት ወገኖቻችን ላይ ደርሶ እንባ ሲራጩ ተመልክተናል።

ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በልማት ስም በወገኖቻችን ላይ የሚፈጽመውን የማፈናቀል ዘመቻ ማስቆም የእያንዳንዳችን ግዴታ ነው ብሎ ያምናል። ሕዝባችን በጨለማ እየተሰቃዬ ከደጃችን የሚመረት የመብራት ኃይል ወደ ጎረቤት አገር እየተላከ ለማይጠረቃው የወያኔ ሃብት የማጋበስ ጥማት ማርኪያ መሆን ማስቆም የምንችለው እኛው ብቻ ነን። ወገኖቻችን በረሃብ አለንጋ እየረገፉና ነፍሰ አድን የምግብ እርዳታ ከፈረንጅ በምጽዋት እየተቸረን በምድራችን የሚመረት እህል ባህር አቋርጦ ለባለጸጋ አገሮች ገቢያ ሲውል አይተን እንዳላየን ማለፉን ማስቆም የኛ ተግባር ነው። ዕዳው ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ የብድር ገንዘብ በየአመቱ አገር ውስጥ በገፍ እየገባ እናቶችና ህፃናት በንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት መሰቃየታቸውን ማስቆም የምንችለው እኛው ነን። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት በቂ የትምህርት እድልና የጤና አገልግሎት የሚያገኙበት ገንዘብ በሙስናና በሌብነት በተጨማለቁ የአገዛዙ ሹመኞች መዘረፉን ማስቆም ያለብን እኛው ነን።

“ውሃ የለም መብራት የለም ኑሮ ከአቅማችን በላይ ሆኖ መኖር አቅቶናል” የሚለውን የወገን እሮሮ ያሰሙ ልጃገረዶችን ድምጽ መስማት ግዴታችን ነው። የእነዚህ ወጣቶች አርዓያነትን በመቀበል ዛሬውኑ የትግሉን ጎራ በመቀላቀል እብሪተኛውንና ዘረኛውን የወያኔ አገዛዝ ፍጻሜ በማፋጠን ነፃነታችንን እንድንጎናጽፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Wednesday, March 19, 2014

በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጉዳይ በድጋሜ ተቀጠረ

መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ ሩጫ ላይ ተቃውሞ አሰምታችሁዋል በሚል ከአስር በላይ ቀናትን በእስር ያሳለፉት የሰማያዊ ፓርቲ 7 ሴት እና 3 ወንድ አመራሮች መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓም ጉዳያቸው ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚታይና ለዛሬ መጋቢት 9 ውሳኔ እንደሚሰጣቸው በዳኛው ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፖሊስ ከዚህ ቀደም ምርመራውን በ5 ቀናት አጠናቆ ክስ እንዲመሰርት ቢታዘዘም ፣ ዛሬ የሚያዙ ተጨማሪ 20 ሰዎች አሉ በሚል ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።ጠበቃ አለሙ ጎቤቦ ግን የፖሊስን ጥያቄ አጥብቀው ተቃውመዋል።
ወጣቶቼ የፓርቲው የአመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ መብታቸው እየተጣሰ መሆኑን ገልጸዋል።

Tuesday, March 18, 2014

US state department 2013 Human Rights Reports: Ethiopia

EXECUTIVE SUMMARY  


Ethiopia is a federal republic. The ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF), a

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!!

የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ሺህ ጊዜ እንደሚሻል አካሉን ብቻ ሳይሆን ህሊናውንም ለትግራዩ ነፃ አውጪ ህወሓት ባርነት ላስገዛው “የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)” እያለ እራሱን ለሚጠራው ድርጅት መሪዎች ተናገረ።

ባርነት ክፉ ነው። በባርነት ላይ የጭንቅላት ባዶነት ሲታከልበት ደግሞ አለምነው መኮንንን የመሰሉ የብአዴን መሪዎችን ይፈጥራል። የብአዴን መሪዎች ለጌታቸው ህወሓት ያላቸውን ታማኝነት ለማሳየት ራሳቸውን ማዋረዳቸው ሳያንስ እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በጅምላ መስደባቸው ብአዴን እንደ ድርጅት የሚገኝበት የተዋረደ ደረጃ ያሳያል።

ህሊና ያለው ባርያ ዛሬ ነፃ ባይሆንም ወደፊት ነፃ የመውጣት ህልም አለው። ዛሬ በጉልበተኛ የባርያ አሳዳሪ ነፃነቱን ቢያጣም የህሊና ነፃነቱን ያላስደፈረ ባርያ ለነፃነት መታገሉ የማይቀር ነው። እንደ ብአዴን መሪዎች በታማኝ ባርያነቱ እየፈነጠዘ ያለ ባርያ ግን ነፃ ሰው የመሆን ህልሙንም ጭምር አጥቷል። እንዲህ ዓይነቱ ባርያ በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው። ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም።

የአማራ ሕዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በፋሽስት ጣልያን ወረራ ጊዜ ለጠላት ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። እነሱም ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖች ይሰሙ ነበር። በገዢዎቹ ለመወደድ የራሱን ሕዝብ የሚዘልፍ፣ የሚሰድብና የሚያዋርድ እንደ ብአዴን ያለ አዋራጅ ድርጅት በአማራ ምድር አልታየም።

ለዚህም ነው የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ የብአዴንና የወያኔን አፈናዎችን በጣጥሶ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ቁጣውን በባዶ እግሩ አደባባይ በመውጣት የገለፀው። እግር ባዶ መሆኑ ጭንቅላት ባዶ የመሆኑ ያህል የሚያሳፍር አይደለም። ድህነት ወንጀል አይደለም። ነፃ አዕምሮና የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ አስተዳደር ካለ ድህነትን ማሸነፍ ይቻላል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የየካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ምን ሕዝባዊ ተቃውሞ ላደራጁና በተቃውሞውም ለተካፈሉ ሁሉ ያለውን አክብሮት ይገልፃል። ሕዝብ ብሶቱን የሚገልጽበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ማደራጀትና መምራት መቻል ትልቅ ነገር ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የማደግ እድል አላቸው። ስለሆነም ግንቦት 7 ለባህርዳሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ አደራጆችና ተሳታፉዎች “እንኳን ደስ ያላችሁ” በማለት የትግል አጋርነቱን መግለጽ ይሻል።

ግንቦት 7፣ ብአዴንን ከአባላቱ ለይቶ ማየት ይሻል። ከዚህም በተጨማሪ የብአዴንን ከፍተኛ አመራር ከሌላው ለይቶ ይመለከታል። ብአዴን ነፍሳቸውን ሳይቀር ለወያኔ በሸጡ ሰዎች የሚመራ፤ ነፃ የመውጣት ተስፋ የሌለው ራሱ ባርያ የሆነ ድርጅት ነው። አባላቱ ግን ከዚህ የተለዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግንቦት 7 ያውቃል።

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህም በፊትም ደጋግሞ እንደገለጸው፤ በተለያዩ ጊዜያት ራሳቸውን ከወያኔ ባርነት ነፃ ለማውጣት በወሰዱት እርምጃ መስዋእትነት የከፈሉ የብአዴን አባላት መኖራቸውን ያውቃል። ግንቦት 7 ለእነዚህ ቆራጦች ትልቅ አክብሮት አለው። ዛሬም ህሊናቸውን ሙሉ በሙሉ ያልሸጡ የብአዴን አባላት አሉ ብሎ ያምናል። እነዚህ ወገኖቻችን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት የግል፣ የወገንና የአገር ግዴታ አለባቸው ብሎ ያምናል።

ስለሆነም ዛሬም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን ጥሪዓችንን እናድሳለን።

የብአዴን አባላት ሆይ!!! የገዛ ራሳችሁን፣ የአማራን ሕዝብ እና ኢትዮጵያን እያዋረደ ካለው ብአዴን ተላቀቁ፤ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ድርጅቱን ግደሉት። የብአዴን መኖር ለወያኔ ካልሆነ በስተቀር ለማንም አይበጅም። ነፃነት ካለ ድህነትን በሥራ ማሸነፍ ይቻላል። ሰው ባርያ ሆኖ በሀብት ቢንበሸበሽ ምን ይፈይድለታል?

የብአዴን አባላት ሆይ!!! ወደ ህሊችሁ ተመለሱ። ራሳችሁንም የበደላችሁትን ሕዝብ የመካስ እድል አድል አላችሁ ተጠቀሙበት። ይህንን ባታደርጉ ግን ለገዛ ራሳችሁ ፀፀት፤ ለልጆቻችሁ ሀፍረትን የምታወርሱ መሆኑን አትዘንጉ። ወያኔ መሸነፉ በጭራሽ የማይቀር መሆኑን እያወቃቸው በድህረ ጣልያን ወረራ ባንዶች ያገኙትን ምህረት እናገኛለን ብላችሁ አታስቡ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!



Monday, March 17, 2014

ብሄር ብሄረሰብ፤ የዘር ፓለቲካ

ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)
destawats@yahoo.com

እውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥፋ
ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ።
ተስፋ ገብረሥላሴ

ፊደል የቆጠርሁት በአገራችን የህትመት ፋናወጊ (እና አርበኛ) የሆኑት ተስፋ ገብረሥላሴ ያሳትሟት በነበረው የባለ ፲ ሣንቲም ፊደል ነበር። ከፊደሏ ሽፋን ላይ ታዲያ ‘ተስፋገብረሥላሴ ዘብሄረ ቡልጋ’ ይላል። መጠየቅ እወድ ነበርና መርጌታን ‘የንታ ብሄረ ቡልጋ ምን ማለት ነው?’ ብየ ጠየኳቸው። የንታም ልጄ ብሄር ማለት በግእዝ አገር ማለት ነው። ቡልጋ ደሞ ሽዋ ክፍላገር ውስጥ የሚገኝ አውራጃ ነው። የተስፋ ገብረሥላሴ አገር እዚያ ነው፤ አሉኝ።

ከዚያ አስኮላ ትምርት ገብቸ ፬ኛ ክፍል ህብረተሰብ መጽሀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ‘ብሄረሰቦችን’ የሚያሳይ ስዕል ተደርድሮ አየሁ። በተለይ ሲዳማን የዎከሉት ቆንጃጅት ሙገጫ ሲዎግጡ የሚያሳየው ስእል አይረሳኝም። ይሁን እንጅ ብሄረሰብ የሚለው ቃል አልገባኝም ነበርና አስተማሪየን ጠየኳት። እሷ ግን ጎሳ፣ ነገድ ቅብጥርሴ ብላ የባሰ ግራ አጋባችኝ። ደግነቱ ማታ ማታ የንታ ዘንድ ወንጌል እማር ነበርና ወንበር ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብዬ ሄጄ የንታን ‘ብሄረሰብ ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየኳችው። የንታም ብሄር ማለት አገር ነው፣ ሰብ ደሞ ሰው ማለት ነው። እንግዲህ ብሄረሰብ ያው የሰው አገር መሆኑ ነዋ አሉኝ። የበለጠ ግራ ተጋባሁ። ህብረተሰብ መጽሀፌ ውስጥ ያዬሁት የሚያማምሩ ቆንጃጅትን ምስል እንጅ ወንዝ ወይ ጋራና ሸንተረር አልነበረማ።Ethiopia and Eritrea map

ሁሉ ሆነና ደርግም በኢሕአዴግ ተተካ። አሁን ግራ ያጋባኝ የነበረው ‘ብሄረሰብ’ የሚለው ቃል ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ተብሎ ተራብቶ መጣ። የግዕዙን ቀጥተኛ ትርጉም ካየን እንግዲህ አገራት፣ የሰው አገራትና ህዝቦች እያልን መሆኑ ነው። ይሁንና ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ተብለው ይጠሩ የነበሩት የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች አሁን ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ ሆነው የተባዙት አንዳንዶቹ ብሄረሰቦች ወደ ብሄርነት ሌሎቹ ደግሞ ወደ ህዝብነት ተለውጠው ይሁን በሌላ ምክንያት በውል አይታዎቅም። በአንጻሩ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚል ቃል አይገኝም። ፖለቲከኞችም ‘የኢትዮጵያ ህዝቦች’ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ አትሰሙም። ይህ አጋጣሚ የሚመስለው ካለ እሱ የዋህ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት (ልክ በኢህአዴግ የመጀመሪያዎቹ ሰባት የስልጣን አመታት ኢትዮጵያ አገሬ የሚል ዘፈን እንደማዳመጥ ያለ) በትምክህተኝነት ሊያስከስስ የሚችል የፖለቲካ ፋውል መሆኑን እያንዳንዱ ካድሬ ስለሚረዳ ነው።

የኢትዮጵያ ሕገ፡መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ስልጣኑም ሆነ ምድሩ አንዲሁም በላዩና በውስጡ ያለው ሀብት ሁሉ ‘የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የጋራ ሀብት ነው ይላል። ይህ ደግሞ ከሌሎች ኣገሮች ሕገ፡መንግስታት ሁሉ ልዩ ያደርገዋል (ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚለው ሀረግ እንደ ዋሊያ ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚታወቀው)። ይህ ይገርመኝ ነበርና ከአስር ኣመታት በፊት ከህገ፡መንግስት ጋር በተገናኘ የመመረቂያ ጽሁፍ ሳዘጋጅ ለመሆኑ አነዚህ የኣገሪቱን የፖለቲካ ስልጣንና ሀብት ኣንድም ሳያስቀሩ ጠቅልለው የያዙ ፍጡራን በትክክል አነማን ናቸው? ኣንዳቸው ከሌላቸው የሚለዩት በምን ነው? በአገሪቱ ውስጥስ ስንት ብሄሮች፣ ስንት ብሄረሰቦችና ስንት ህዝቦች አሉ? ለምሳሌ የቀበሌ መታወቂያ ስትወስድ ብሄርህን ተጠይቀህ ጉራጌ ብለህ ከሞላህ በኋላ ማታ በኢቲቪ የጉራጌ ብሄረሰብ ስላስመዘገበው ልማት ትሰማለህ። ታዲያ ብሄርና ብሄረሰብ አንድም ሁለትም ናቸው? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን ይዠ መልስ ፍለጋ ሰነዶች ማገላበጥ ነበረብኝ። የህገ፡መንግስቱን ረቂቅ (ፕሪፓራቶሪ ዎርክስ) ሳይቀር አገላብጨ የሚረባ ነገር ላገኝ አልቻልሁም። ሕገ፡መንግስቱን በማርቀቅ የጎላ ድርሻ ነበራቸው የሚባሉትን ሰዎችም ጠይቄ ያገኘሁት ውጤት ኣልነበረም። በጣም ተገረምሁ። በአገራችን ላይ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሁሉን ሀብትና ስልጣን ‘የተቆጣጠሩት’ ግኡዛን ማንነት እንዴት አይታዎቅም? ይህ እኮ እጅግ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።

በተለይ ህዝቦች የሚለው ቃል ግራ አጋቢ ነው። በአለም ላይ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወይም እንድ አይነት ማንነት ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚኖሩባቸው አገራት ከአምስት አይበልጡም፤ ይህም ቢሆን በጣም የሚያከራክር ነው። ይሁን እንጅ የብራዚል ህዝቦች ወይንም የኬንያ ህዝቦች ቢባል እንግዳ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ህዝብ በትርጉሙ ያልተወሰነ ቁጥርና ማንነት ያላቸው ሰዎችን ያካተተ የጥቅል (የወል) ስም ስለሆነ ነው። ለዚህም ነው የአለም ህዝብ ቁጥር እንጅ የአለም ህዝቦች ቁጥር የማንለው። በርግጥ ፈረንጆቹም ከቅኝ በፊት ይኖሩ የነበሩ ቀደምት ጎሳዎችን (ትራይብስ) ለማመልከት ኢንዲጅነስ ህዝቦች ወይም አማዞን ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ይላሉ። ይህ ግን ቀደምት ጎሳዎችን (ነገዶችን)የሚተካ ተለዋጭ ቃል እንጂ ተደራቢ ስያሜ አይደለም። ስለሆነም ቀደምት ጎሳዎችና ኢንዲጅነስ ህዝቦች አይሉም። እንዲያውም ኢንዲጅነስ ህዝቦች የየአገራቸው (ሰፊ)ህዝብ አካል ናቸው። ለምሳሌ የካናዳ ህዝብ በአገሩ የሚኖሩ ኢንዲጅነስ ህዝቦችን ያጠቃልላል። በዚህ አግባብ ከመደበኛ ሰዋሰው ርባታ ተቃራኒ ቢመስልም በአንድ አገር ውስጥ ህዝብ የሚለው ቃል ህዝቦች ከሚለው ቃል ይሰፋል ማለት ነው። ከላይ በጠቀሁት ምሳሌ የካናዳ ህዝብ ካናዳዊያንን በሙሉ ሲያመለክት የካናዳ ኢንዲጅነስ ህዝቦች ግን የካናዳ ህዝብ አካል የሆኑ (ከአጠቃላዩ ህዝብ ፭ ፕርሰንት እንኳን የማይሞሉ) ግን ደግሞ የየራሳቸው የተለየ ማንነት ያላቸውን ነገዶችን ብቻ የሚያመለክት ነው። በሁሉም አገሮች የሚኖሩ የተለያዬ ቋንቋና ማንነት ያላቸው ሁሉ በአንድ ላይ የዚያ አገር ህዝብ ተብለው ነው የሚታዎቁት።

ወደ አገራችን ስንመጣ ግን ሁለት አደናጋሪ ነገሮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ህዝቦች የሚለው ቃል አግባብ በሌላው አለም እንደሚታወቀው ሁሉ ቀደምት ነዋሪወችን (ኢንዲጅነስ ትራይብስ) ለማመልከት ነው እንዳይባል ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ያልሆነው ማን እንደሆነና ማን ከማን እንደሚቀድም አይታወቅም። እንዲያውም ሁሉም ‘ብሄር ብሄረሰቦች’ ቀደምት ነዋሪወች ናቸው ማለት ይቻላል። ቢያንስ ይህ ላለመሆኑ ተቃራኒ ማስርጃ የለም (እንዲያውም እኮ እንደ ሳይንሱ ከሆነ የአለም ህዝብ ሁሉ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው)። ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አንዳንዶች እንደሚሉት አናሳ ቁጥርና አገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለማመልከት ነው እንዳንል እነሱው መልሰው ታዳጊ ብሄረሰቦች (አንዳንዴ አናሳ ብሄረሰቦች) ሲሏቸው እንሰማለን። ያ ከሆነ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦች በሚለው አገላለጽ ብንስማማ እንኳን ‘ህዝቦች’ የሚለው ቃል አላስፈላጊ ድግግሞሽ ከመሆንና ከማደናገር ኣልፎ የሚጨምረው ነገር የለም ማለት ነው። ሁለተኛውና በጣም የሚገርመው በአለም ላይ ባልተለመደ ሁኔታ በአገሪቱ የሚኖሩት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በአንድላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይሆኑም። ይህ የሆነው አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሕገ፡ መንግስታዊ ቃልኪዳን ገብተናል ያሉት ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ የሚጋሩት ማንነት ሳይኖራቸው ቀርቶ ይሁን በሌላ ምክንያት አይታወቅም። ለነገሩ የአንድ አገር ህዝብ አካል ለመሆን የዚያ አገር ዜጋ ከመሆን ሌላ ምን የተለየ የጋራ ማንነት ያስፈልጋል?

ግድየለም፤ ያ ሁሉ ፖለቲካ ነው ብለን እንለፈው። እኛስ ቢሆን ቃላትን (አንደኣብዛኛዉ ነገራችን) እንደልባችን የምንጠቀመው ለምን ይሆን? ኢትዮጵያ በዘር ተከፋፈለች፣ የዘር ፖለቲካ ያጠፋናል፣ የጦር ሰራዊቱ ከኣንድ ዘር በወጡ አዛዦች ቁጥጥር ስር ነው፣ አቶ እከሌ በተቋሙ ውስጥ የነገሰውን ዘረኝነት በመቃዎም ስልጣናቸውን ለቀቁ፣ ወዘተ…በየቀኑ የምንሰማው ሮሮ ነው። ለመሆኑ ዘር ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ዘር አለ? ለምሳሌ አማራ አንድ ዘር ትግሬ ደግሞ ሌላ ዘር ናቸው? ከሆነስ ከየት ነው የመጡት? እንደሚታወቀው ያን ያህል ሩቅ ከማይባል ጊዜ በፊት ግእዝ እንጂ ትግርኛም አማርኛም ኣልነበሩም። ታዲያ ያኔ ትግሬ ነበር? ኣማራስ? ሌላው ቀርቶ ሴሜቲክ፣ ኩሽቲክ የሚባለውስ ምናልባት ቋንቋን ከመግለጽ (ይህም አከራካሪ ይመስለኛል) የዘለለ ያለው አንድምታ ምንድን ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ችሎታየም አላማየም አይደለም፤ ነገር ግን በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ይመስሉኛል። እንዲያውም ስለማንነታችን ሳይንሳዊ ብንሆን ብዙ ችግራችን የሚቃለል ይመስለኛል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ እንጅ እናንተ ቦታ የላችሁም፤ መሬቱ በሙሉ የእነሱ በመሆኑ እናንተ የመሬት ባለቤት መሆን አትችሉም ሲለን ቢያንስ እነዚያ ‘ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች’ በትክክል እነማን እንደሆኑ እንዲነግረን እንጠይቃለን። በአንጻሩ ደግሞ እኛ የዘር ፖለቲካ ወዘተ…ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ መረዳትና ማስረዳት ያለብን ይመስለኛል።

በዚሁ ላብቃ።

ሰላም

ችግር ነው አስቀድሞ ማሰብ (ፐ/ር መስፋን ወ/ማርያም )

March 13, 2014
ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።


የግለሰብ ነጻነት ታፍኖ የጎሣ ነጻነት መታወጁ ፋይዳ እንዳላመጣ ታየ፤ የግለሰብን ነጻነት ለመደፍጠጥ ሲባል የጎሣዎች ነጻነትም አብሮ ተደፍጥጦ ነበር፤ ይህንን አስቀድሞ ለማየት ለምን ሳይቻል ቀረ? የሚል ጠያቂ ከመጣ መልሱ ቀላል ነው፤ በሚልዮኖች ብር እየወጣ መንገድ ሲሠራና አስፋልት ሲለብስ ቆይቶ ከጥቂት ወራት በኋላ የባቡር ሀዲድ ለመዘርጋት ተብሎ የተሠራውን አስፋልት የለበሰ መንገድ ማፍረስ እንዳስፈለገ አይተናል፤ የባቡሩ ጉዳይ ለምን አስቀድሞ አልታየም? የጎሣን ነጻነት ለማጉላት ሲባል የግለሰብን ነጻነት መደፍጠጡ ዞሮ ዞሮ የጎሣውንም ነጻነት አንደሚደፈጥጠው ያልታየበት የተለየ ምክንያት የለውም፤ አሰቀድሞ አለማየት የባሕርይ ነው፤ በተጠቀሱት ምሳሌዎች ሁለቱም ዋጋ ያስከፍላሉ፤ ልዩነቱ የአንዱ ዋጋ የሚከፈለው በፖሊቲካ ኪሳራ ሲሆን፣ ሌላው የሚከፈለው በኢኮኖሚ (በሀብት) ኪሳራ ነው፤ ሆኖም የፖሊቲካውም ሆነ የሀብቱ ኪሳራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሙሉ ያለምንም የጎሣ ልዩነት ሲጫንበትና ችጋር ሲያንዣብበት በሥልጣኑ ወንበር ላይና በዙሪያው የሚንሳፈፉት ፈጣሪዎቹ ናቸውና የችግሩ ሸክም ሲያልፍም አይነካቸው! እንኳን ለፖሊቲካና ለሀብት ኪሳራ ለሕይወት ኪሳራም ቢሆን የማይጠየቅ መሆኑን በምክር ቤት በሚባለው ውስጥ በድፍረት የተነገረበት አገዛዝ ነው።

የትግራይ ሕዝብ የአገዛዙ ጉልበትና የጥቅም ተካፋይ ነው እየተባለ እስቲያምመው ድረስ በሐሜት ተለበለበ፤ የሚናገርለት ቡድንና የሚናገርበት መድረክ ሳያገኝ ሃያ ሁለት ዓመታት ያህል ኢትዮጵያዊ ትእግስቱን አሳየ፤ ዛሬ አረና የሚባለው የትግራይ የፖሊቲካ ቡድን ወያኔ ለብቻው በትግራይ ሲቆጣጠረው የቆየውን የፖሊቲካ መድረክ ለመጋራት ፊት ለፊት በሰላማዊ የፖሊቲካ ትግል እየተጋፈጠው ነው፤ ይህ አዲስ ሁኔታ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ የፈጠረውንና ሊፈጥር የሚችለውን የፖሊቲካ እንቅስቃሴ እንኳን ሌሎች በሩቅ የሚከታተሉ ወያኔዎችም ገና አልገባቸውም፤ በፖሊቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው አገዛዙ ችግርን አስቀድሞ የማየት ብቃት እንዳላሳየ ከላይ በተጠቀሱት ምሳሌዎች አረጋግጠናል፤ ስለዚህም አገዛዙ በትግራይ የገጠመውን ሰላማዊ ፉክክር ለመቋቋም አዲስ ዘዴ አላገኘም፤ እስካሁን በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደተደረገው ሁሉ በትግራይም ተቀናቃኞቹን በእስርና በዱላ ለማገድ እየሞከረ ነው፤ ሌላ ዘዴ ገና አላገኘም፤ የሚፈልግም አይመስልም፤ በዱላ መጠቀም ሲለመድ አንጎል ይደነድናል፤ ወገንን ጠላት ያደርጋል፤ ወገን ጠላት ከሆነ ማን ወዳጅ ሊሆን ነው? ትልቁ አደጋ ይህ ነው።

መሠረታዊ ችግርም አለበት፤ በእውነተኛ የጎሣ ፖሊቲካ ውስጥ የማይታዩ ነገሮች እየተከሰቱ ነው፤ በአንድ ጎሣ ውስጥ ከባድ የሆነ የአስተሳሰብ ልዩነት፣ የሥልጣን ክፍፍልም ሆነ የሀብት ልዩነት ጎልቶ ሲወጣ የጎሣው ሥርዓት መክሸፉንና መምከኑን ያመለክታል፤ መስታወት ሆኖ የመሠልጠንና የመለወጥ ልዩነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው፤ መሠልጠን የማይለውጣቸውን ሰዎች መማር ይለውጣቸዋል፤ ከማትጊያ ጋር በሚሰጥ የቡድን መመሪያ የሚሠሩትን ሰዎች በግል ማንበብና ማሰብ ይለውጣቸዋል፤ ይህንን የማይቀርና ሊታገድ የማይችል የለውጥ አቅጣጫ ማየት የማይችሉ ለዛሬ እንጂ ለነገ የሚኖሩ አይደሉም፤ በትግራይ በመታየት ላይ ያለው የነጻ ሰዎችን፣ የነጻ ግለሰቦችን አስተሳሰብ የሚገልጽ አንቅስቃሴ ለትግራይ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፤ የመንጋ አስተሳሰብን ለመረዳት ፌስቡክን ማጥናት ነው፤ የወያኔ የካድሬ ሠራዊት በሻገተው አስተሳሰቡ (መለስ ዜናዊ በጸያፍ ቃላት ገልጾታል፤) እያየው በዚያው በለመደውና ባስለመዱት የዱላና የጉልበት ዘዴ ሊያመክነው እየጣረ ነው፤ ወጣቶቹ ግን እየተደረገ ያለውን በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ከተጫነባቸው የተስፋ ክምር ጋር እያስተያዩ ማን እንደጠገበና ማን እንደተራበ ያያሉ፤ ያመዛዝናሉ፤ አቅዋማቸውንም ያስተካክላሉ፤ የትግራይ ወጣቶች የፖሊቲካ ንቃትና ነጻ አስተሳሰብ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ የወያኔ ካድሬዎች አስበው ሊደርሱበት አይችሉም፤ የተለመደው አስቀድሞ አለማየት አወዳደቅን የሚጎዳ፣ የሚያስከፋና የሚያሳፍር ያደርገዋል!

የጭቆና ሠራዊት እንዲሆን የሚሠለጥነው የካድሬ ሠራዊት ጸረ-ማሰብ ነው፤ አስቦ ሳይሆን ለትእዛዝና ለሆዱ የሚገዛ ነው፤ ከላይ እስከታች በአንድ አስተሳሰብ ብቻ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ የአገር ጉዳዮችን ለሕዝባዊ ሙግት አይከፍትም፤ ስለዚህም ሀሳቡ አይናፈስም፤ ስለዚህም አስተሳሰቡ የጊዜ መጫወቻ ይሆናል፤ ይሻግታል፤ ጸረ-ማሰብ ሆኖ ከመሻገት መዳን አይቻልም፤ መለስ ዜናዊ ይህንን በደንብ ያውቅ ነበር! ዛሬ እነኮኸንና እነሺን (ኮኸን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ውስጥ የአፍሪካ ክፍል ኃላፊ የነበረ ሲሆን ሺን ደግሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ነበር፤) በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ የሚናገሩት በኤርትራና በሶማልያ ላይ የተነደፈው መመሪያ አልሠራምና እንደገና መፈተሽ አለበት እያሉ ነው፤ እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት የማንን መሠረታዊ ጥቅም ለማራመድ ነው? በጊዜው ጥያቄውን ለመመርመርና በትክክል ለመመለስ ካልተቻለ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ሲለዋወጥ የኢትዮጵያ አገዛዝ ይጨማደድና ብዙ ባዶ ቀፎዎችን ይዞ ይቀራል።

አሜሪካ የበለጠ ትናገር! (ከጸጋዬ ገ/መድህን አርአያ)

ነፃነቴን ካልሰጣችሁኝ ሞትን እመርጣለሁ
ፓትሪክ ሔንሪ Give me Liberty or Give me Death

ፍሬደሪክ ዳግላስ (1818- 1895) ከባርያ እናትና ከነጭ አባት የተወለደና ራሱም ቢሆን በቦልቲሞር (ሜሪላንድ) የቤት አሽከር ሆኖ የቆየ ሰው ነበር። አንድ ማለዳ ጁላይ 4 ቀን 1852 ን ተንተርሶ (አንተርሶ) በሮቼስተር ከተማ (ኒውዮርክ) ንግግር እንዲያደርግ ጥሪ ይደርሰዋል። ደብዳቤው ሲደርሰው እንደ እብድ ከራሱ ጋር መነጋገር ያዘ። መቸም አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ለማመን የሚከብድ አጋጣሚ ሲመጣብህ ናላህ ይበጠበጣል። ፍሬደሪክ ዳግላስም “በእርግጥ ይህ ደብዳቤ ለእኔ የተጻፈ ነው? የተቀባይ ስምና አድራሻ ስሕተት ተፈጽሞ ይሆን?” ሳይል አልቀረም። ዳግላስ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ጭንቅላቱን ሲበጠብጥ ቆይቶ ትንሽ አረፍ አለ። ሲነቃ ይኸ ዕድል እንዳያመልጠው ፈለገ። ይልቁንም የሚናገርበት ርዕስ መጣለት። “ በመሰረቱ እኔን ባርያውን በዚህ በዓል ላይ እንድገኝ- ለዚያውም ተናጋሪ መሆኔን ሳስበው ይህ ሁሉ ግብዝ- የግብዝም ግብዝ ነው አለ። ይበልጥ ደግሞ ለተሰብሳቢው ስለጁላይ 4 (ነፃነት በዓል) እንድናገር እኔን ባርያውን መጋበዛቸው ሌላው ግብዝና ነው ” አለ። ለማንኛውም ንግግሩን አዘጋጀ። በዚያ ወቅት በሮቼስተር ከተማ ያደረገው ንግግር እስከ ዛሬ ድረስ ከዓለም ታላላቅ ዲስኩሮች አንዱ ለመሆን በቅቶአል። “ጁላይ 4 ቀን ለመሆኑ ለባርያው ምኑነው? What to the Slave is the Fourth of July?

ዛሬ ከብረት በከበደ ክንድ ኢትዮጵያን እየገዙአት የሚገኙት ጌቶች- አዳዲስ መሳፍንት- አዳዲስ መኳንንት፣ አዳዲስ ዲታዎች…የንግስ በዓል ከሳምንታት በኋላ ይከበራል። (በዩጐዝላቩ ጂላስ The New Class, ወይም ከሮማውያን ዘመን አንስቶ Nouveau Riche ቀላል ድግስ አያውቁም። ስለዚህ ጉንበት 20 ቀን በታላቅና ታይቶ በማያውቅ ድምቀት ይከበር ዘንድ ዝግጅቱ እየተሟሟቀ ነው። አገር ያፈራው ትልልቁ የሐረር ሰንጋ፣ ወደል ወደል የሚያክለው የወለጋ ላታም በግ ወዘተ ተመርጦ ተመርጦ ይቀርባል። ሻምፓኙ፣ ውድ ውዱ አይሪሽ መጠጥ- ዊስኪ፣ ድራንቡዬ፣… የፈረንሳይ ኮኛኮች፣ ምርጥ ወይን ጠጆች..ያልፍላቸዋል። ምንም ማጋነን የለበትም። ጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ እንኳ ለድግስ ስንትናስንት ሚሊዮን ብር ሲያወጡ እንደነበረ ከጉያቸው የወጣው ጠንካራ ኢትዮጵያዊ…ገብረ መድኅን አርአያ ገልጦታል።

“ኑና ጉንበት 20ን አብረን እናክብር” ተብለው የተጠሩ ወይም እንጠራለን ብለው ቀኑን እንደወላድ እየቆጠሩ- የራቀባቸው ሰዎች የሉም አትሉም። እናንተም እንደኔ። ከውጭ የሚጋበዙ በርካታ ሰዎች ይኖራሉ። አዳራሾች-ሆቴሎች- በየደረጃው… ላይበቁ ነው። እሸሸ ገዳሜው፣ አስረሽ ምቺው ደግሞ የሚጠበቅ ነው። ስለገዢዎቻችን ሀብትና ንብረት ያልተባለ ነገር የለም። ይኸ ደግሞ የሞራሉን ቁልቁለት ምንኛ እንደ ተያያዙት ስም እየጠቀሰ መረጃ የሚሰጠንን ውስጥ አወቅ ኢየሩሳሌም አርአያን ማድነቅ እወድዳለሁ። በሽምግልናና ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ በሚገባቸው ዕድሜ የእኝኝ ብላ ባዝራዎች፣ አንድና ሁለት (በቀን) የማይበቃቸው የወንድ መለኮኖች አሉባቸው። ከዚህ ተራ ውስጥ ሁለት ሰዎችን ብቻ (በረከተ-መርገም ስምዖንና ስዬ አብርሃ) ነፃ ያወጣቸው ደግሞ ተስፋዬ ገብረ-አብ ነው። ስለሆነም ዳንኪራውና ስድ የሆነው በዓል የሚጠበቅ ነው። እኛም የኢትዮጵያ ጉስቁሎች የሌላ ሕዝብ በዓል በሥነ ሥርዓት መጠበቅ አለብን። የበዓሉን መንፈስ ማደፍረስ፣ ማደናቀፍና ማቃወስ በአሸባሪነትና በመሳሰለው አንቀጽ ያስቀጣል። አዎን ጉንበት 20 ቀን የድግሦች ድግሥ፣ አውራ በዓልና የድግሦችና የበዓሎች ሁሉ እናት ናት። ማን ያውቃል? ድሮ ጃንሆይ አጤ ኀይለ ሥላሴ ሐምሌ 16ን “የትዮጵያ የልደት ቀን” እንዳሉአት እነዚህ አዳዳሶቹ መሳፍንትም ጉንበት 20ን “እውነተኛው የኢትዮጵያ ናጽናት ቀን” ቢሉት አይደንቀኝም። ( ብቻ ማን ነበር- የአንዱ ሕይወት የሌላው መርዞ ነው- ያለው?)let America speak

በአገራችን የድግስ ነገር ሲነሳ ትንሽ የማስታውሳቸው ነገሮች አሉ። በአጤው ጊዜ ጃንሆይ የተወለዱበት (ሐምሌ16) እንዲሁም የነገሱበት (ጥቅምት 23) ይከበሩ ነበር። ለኢትዮጵያ ባሕልና ፖለቲካ እንግዶች የሆናችሁ ወጣቶች ምናልባት አታውቁት ይሆናል እንጂ በክብርም ቢሆን ቤተ መንግስት ስትጠሩ ግርግሩ ብዙ ስለሆነ ትንሽ ጨፈቃ ትቀምሳላችሁ። እንጀራው በእግር የተቦካ ነው ይባላል። ለማንኛውም “የንጉስ በረከት” አይናቅም ትባላላችሁ። (ይህንን የበለጠ ለማወቅ ፍቅር እስከ መቃብርን ያነብቡአል) ወደኋላ ጊዜ የሐምሌ 16 በዓል አከባበር ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተሰጥቶ ነበር።

የድግስ ነገር- በመንግስት ሰፈር- ብዙ ምልኪ አለበት። ስለ ጃንሆይ መንግስት አወዳደቅ ብዙ ቢባልም ለጊዜው አንዱን አነሳለሁ። አንዳንድ ሚኒስትሮች እጅግ ከቅብጠትም ባሻገር ስለሄዱ ክራር ይዘው ወደ መሸታ ቤት መሄድ አብዝተው ነበር። የዛሬዎቹ ከእነዚያ ጋር ባይወዳደሩም ትንሽ ትንሽ ሕዝብንና አኗኗሩን ወደ መርሳቱ ደርሰው ነበርና ሌላው ቀርቶ ከመሳፍንቱ አንዱ የነበሩት ጄኔራል ዐቢይ- “አውቀን እንታረም” የሚል መጽሐፍ ደርሰው ነበር። ጠንቃቃው ጄኔራል “አውቀን ካልታረምን ሌላው ቀርቶ ሬሳችን እንኳ የወደቀበት አይታወቅም” ብለው ነበር። አዎን አርማጌዶን በዓለም ፍጻሜ ላይ የሚከሰት ሳይሆን ያልታሰበ የእልቂት መውረድም አርማጌዶን ሊባል ይችላል። ያ ወቅት የሞራል ድቀት ሥጋና ደም ገዝቶ የሚታይበት፣ ሕዝብ ሲያልቅ አንዳንድ ሹማምንት መንደላቀቅ ያበዙበት ነበር። ደርግ ጃንሆይን ከሥልጣን ሲያወርድ “ሕዝብ በሺህ ቤት ሲረግፍ እነሱ በእሸሸ ገዳሜ ተጠምደው…” እያለና የቀለጠ ድግስ በቴሌቪዥን እያቀረበ ነበር። ድግስ….

ደርግ ራስዋ በራስዋ ያመጣችው ጣጣም አለ። ወደ ሥልጣን የመጣበትን ቀን ለማክበር ብልጭልጩንም ማናምኑንም ሰልፉንም…ሲያበዛ የእንግሊዝ ጋዜጠኞች በሁለት መቶ ሺህ ዶላር ውስኪ ሸጥን አሉና…የደርግ መሰላል ወደታች ብቻ የሚያወርድ ሆነ። ድግስ እየተኮነነ መጣ። ድግስ እየተጠቀሰበት ወረደ። ሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ በረሃብ አለቀ ብሎ ተሳለቀ ተባለ። በራሱ ጊዜ ዘጠኝ ሚሊዮን ሕዝብ ተርቦ ውስኪ ተራጩ ተብሎ ለወያኔ ፕሮፖጋንዳ ተመቸ። እዚህ ላይ ያነሳሁት የጉንበት 20 አከባበር ያንኑ እድል ይከተል ይሆናል- ይከተላልም- ቁልቁለቱን ጀምሮአል በሚል ነው። ድግሶች በሦስቱ መንግስታት- የሥልጣን መልቀቂያ ጊዜ ምልክቶች- ብልሽትሽቱ የወጣ መንግስት ማክተሚያ ወቅቶች ሆነው አይተናቸዋል። ( ሁሉም የእጁን ያገኛል- ብድሩን ወይም ብድራቱን ተከፈለ- በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም የሚባል አነጋገር ያለ ይመስለኛል። የእንግሊዝኛው ፈሊጥ ግን Poetic Justice ይለዋል) “ያርግላቸው!” አሜን ያድርግላቸው!!

ደርግ የተወነጀለበት 200ሺህ ዶላር ዛሬ አንድ ባለ ጊዜ ወያኔ ለልጁ ልደት ከሚደግሰው በታች ነው። በ1997ዓ.ም አባዱላ ገመዳ ለልጃቸው ዘኪያስ አባዱላ 24ኛ ልደት በዓል የ100ሺህ ዶላር ኮብራ ዘመናዊ መኪና በስጦታ መልክ አበርክተዋል። በ1994ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 14ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ተጋልጦ ነበር። መለስ ዜናዊ ከ10 ዓመት በኋላ “በቀን ሶስት ጊዜ ትበላላችሁ” ባሉበት ዓመት መሆኑ ነው። የመለስ ዜናዊ መንግሥት ለተራቡት ወገኖች ደንታ አልነበራቸውም። በድርጅታቸው የተፈጠረው ቀውስ ላይ በማተኮርና ለእርሳቸው የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ሲሉ “ተሃድሶ” ብለው ለሰየሙት ቱማታ 280ሚሊዮን ብር ባጀት መድበው ካድሬዎቻቸውንና ተከታዮቻቸውን በድግስና በውስኪ ያምነሸንሹ ነበር። በዛው ዓመት ልጃቸው ሠማሃል መለስ የልደት በዓልዋን በግዮን ሆቴል ዳስ ተጥሎ አክብራለች። ለኬክ ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር ነበር ወጪ የተደረገው። የመለስ ልጅ ልደትዋን በምታከብር እለት በግዮን ሆቴል ደጃፍ በርካታ በረሃብ የገረጡ ወገኖች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ወድቀው ነበር።

ስለ ድግስ ዝርዝር ለመጻፍ ፍላጐቱ የለኝም። ደግሼም አላውቅም። መንግስት ሲቀናጣ፣ እሸሸ ገዳሜው ልክ ሲያጣ፣ የሞራል ድጡ መጠነ ቢስ ሲሆን፣ ሰብአትካትን- ሰዶምና ገሞራን ወይም የጥፋት ውሃን ዘመን ሊያመለክተን ይችላል። ራስ ተፈሪዎች “ባቢሎን” ይሉታል። እንዲያውም በቀድሞው መንግስት በጠቅላይ ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ሥዩም ሐረጐት The Bureaucratic Empire, Serving Emperor Haile Selassie በሚለው መጽሐፋቸው ያነሱት አንድ ነጥብ ስለድግስና ስለመሳሰሉት ጉዳዮች ነበር። ኮረኮረኝ። ሥዩም ሐረጐት እንደጻፉት የቀ.ኀ.ሥላሴ ባለስልጣኖች የታሰሩት ጠጅ ለመጣል ምቹ ቅዝቃዜ በነበረው ሥፍራ ነበር። ከላይ የደርግ አባላት ስብሰባ ሲካሄድ፤ ሑካታ ሲፈጠር፣ ጭብጨባ ሲበዛ ወዘተ በእሥረኞቹ ላይ ይፈጠር የነበረውን የመንፈስ ጭንቀት ይነግሩናል። አሳሪዎች የእሥረኞች ሥቃይ ሊታያቸው ከቻለ በእርግጥ “ሰው” የመባል ሙሉ ባሕርይ አላቸው ለማለት ይቻላል። (የደርጉን ዘመን ግፍ ለማውራት የምደፍርበት ወኔ የለኝም። ራሳቸውን እየቀደሱ በሌሎች ግለሰቦች ላይ ከሚደነፋፉም ጋር ጠበል የምጠጣ አይደለሁም። አንድ ነገር ላይ ከተስማማችሁልኝ ደርግ በውሃ አጥምቆ ቢሆን ወያኔ ይኸውና በእሳት እያጠመቀ ይገኛል። የጥምቀቱ ተቀባይ ደግሞ መላው ወገኔ ነው።)

የአሜሪካ መንግሥት ባለፉት ቀናት የኢትዮጵያን ድንኳን ገለጥለጥ አድርጐ የአገሪቱን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ፣ የፖለቲካ እሥረኞች አያያዝ፣ በገጠር ያለውን ብሔረሰቦችን የመከፋፈል መንግስታዊ ጫናና ወንጀል አሳውቆናል። አሳውቆልናልም። በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሰማንያ ሺህ የፖለቲካ እሥረኞች አሉ። ከእነዚህም መካከል ስድሳ ከመቶው አእምሮ እስከ መሳት መድረሳቸውን በምስክርነት አቅርቦልናል። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ታላቅ ወንድም (የተጠጋኸው ትልቅ መንግሥት በፖለቲካው ቋንቋ ቢግ ብራዘር ይባላልና) ምናልባትም የእሥረኛውን ቁጥር ቀንሶት ይሆናል እንጂ በኢትዮጵያ እየኖረ ወያኔንና ትውልደ ወያኔ ያልሆነ ለመሆኑ ያልታሰረ – አለዚያም እሥራት የማያስጨንቀው ማነው? ብለው የሚጠይቁ የትየለሌ ናቸው። ያልታሰሩ የሚመስላቸው ሰዎች ደግሞ የጥርስ ችግር እያለው ሕመም ሳይሰማው በመጨረሻ ላይ አምስትና ስድስት ጥርሶቹ ሲረግፉለት ለቃቅሞ ወደ ሐኪም ቤት እንደሚሮጥ ሰው ናቸው።

እንደሁም ልጆቻቸው ወይም የአገር ወጣቶች በነቂስ እየታረዱ ኅዘኑ ከቤታቸው የማይገባ፣ የቤተሰብ አውራ በባለቤቱ ፊት ታስሮ ሚስት ስትነወር፣ ንብረቱ ሲድፋፋ፣ ጐታው ሲደፋ ልቅሶውና ዋይታው ከጆሮአቸው የማይደርስ ጐረቤት ወገናችን አለ። የድንጋይ ልብ የገባለት። አንዳንድ የማውቃቸው ሰዎች – ጐይትኦም ብቻ ሳይሆን- ደባልቄና አምበርብርም ጭምር – ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ሲመለሱ ተመሣሣይ ትዝታ ይዘው ይመጡላቸዋል። አዲስ አበባ ውስጥ የሚሠራው የእድገት ምልክት የሚገለጥ አይደለም። የአለቃ ደስታና የተሰማ ግጽው መዝገበ ቃላት በቂ ቃላት የላቸውም። “እንዲያውም በእንግሊዙ ንገረኝ” ትለዋለህ። አንተም አሿፊ እሱም አሹዋፊ ትባላላችሁ። ጓድ መንግሥቱ ኅይለማርያምን ብጠቅስ እንደማትቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በኢትዮጵያ ራዲዮ በሠራሁባቸው ዓመታት አንድ ቀን ስለ ራዲዮ አሠራር ስንገልጽላቸው ምርር ትክን ብለው “ ዘፈኑና ጭፈራው አልበዛም ወይ? ለመሆኑ ወገኖቻችን በጠላቶቻችን ሰይፍ እየተመቱ፣ አብዮታዊ ሠራዊታችን በግራም በቀኝም – በሰሜንም በምሥራቅም፣ በመሐል አገር ደግሞ በአምስተኛ ረድፈኞች ጓዶቻችን ሁሉ እተየረሸኑ..እያለቅን አይደለም ወይ? ኢትዮጵያ ራስዋ እንደ አንድ ልቅሶ ቤት መታየት የለባትም ወይ? እንዴት ነው በዚህ ሁሉ ልቅሶኛ ላይ እሸሸ ገዳሜ ዘፈን ለማሰማት ፈቃድ የምትፈልጉት? ፈቃድ የሚጠየቅበት አይደለም። እንደየስሜታችሁ ነው። ደስ ካላችሁ ዝፈኑ። አስዘፍኑ። አለዚያም ዳኝነቱ የእናንተ ነው” ብለው ነበር። አንዱ ሲደሰት ሌላው ያዝናል። ዓለም ጉራማይሌ!

ሕይወት ከዚህ መሠረታዊ አመለካከት ይጀምራል። ግን ከአለቃችን ንግግር ውስጥ ማንንም ሊነካ የሚገባው ለአገራቸው ባበረከቱት ቅንና ሕጋዊ አገልግሎት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ወደ ወህኒ ዓለም የተወረወሩትን ሰማንያ ሺህ ኢትዮጵያውያን በዓይነ ሕሊናችሁ ጐብኙልን። አሜሪካ የምትነግረን- የማናውቅወን አይመስለኝም። ራስዋን በምስክርነት አቅርባለች። ከተጠቀምንበት። ወይም ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ አንድ ሰሞን ይሉ እንደነበረው “በደርግ ጊዜ አሜሪካ በክምር ሳር ውስጥ የወደቀች መርፌ ይታያት ነበር። አሁን ግን በእልፍኝ ውስጥ የቆመው ዝሆን እንዳይታያቸው አንድ ዓይነት ግርዶሽ (ማዮፕያ) ተፈጥሮባቸዋል” አይደለም? ጉዳዩ የኢትዮጵያውን ጉዳይ ነው ተባብለናል። የኢትዮጵያን ዋና ዋና ትግሎች (ጦርነቶች) በቅጥረኛና ካልሆነም በአሜሪካ አማካይነት የምንዋጋቸው አይደሉም። ይልቁንም ዛሬ አሜሪካ የነገረችን ሁላችንም እሥረኝነት እንዲሰማን ይመስላል። ጐበዞቻችን በወህኒ እየማቀቁ ነው።

ስለ እስክንድር፣ ስለ በቀለ፣ ስለ አንዱዓለም፣ ስለ ርእዮት….ሰምተን ነበር? ከእነሱ ሌላ ሰማንያ ሺህ ማን ያውቃል 180ሺህ ሰዎች በወህኒ ዓለም ይማቅቃሉ። ሌሎች ያልታሰሩ ግን “በመተካካት መልክ” ሊገቡ ወረፋ እየጠበቁ ናቸው። አፍጥጦ የመጣብን- እስካሁንም ያልተመለሰው ከባድ ጥያቄ- ለመሆኑ እኛስ አልሞትንም ወይ? መቸም ወደፊት እንደምንተሳሰበው ከሞቱት አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አምሳ ሺህ ውስጥ አይደለንም ወይ? የመኖር ያለመኖር ማረጋገጫ (ምናልባት ሰርተፊኬት ወይም ሊቸንሳ) አግኝተናልን? ራስ ቢተወደድ መኮንን እንዳልካቸው “አልሞትሁም ብዬ አልዋሽም” ነበር ያሉት? ሙኩሼዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ቀዌሳ ደግሞ ልዑል ሐምሌት የሚያንበለብለውን ዘላለማዊ ስንኝ እንዲህ ብሎ በከፊል ወደ አማርኛ መልሶታል።

መኖር አለመኖር እዚህ ላይ ነው ምሥጢሩ
የዕድል ፈተና አለንጋ ሲወናጨፍ ወስፈንጥሩ

ይህ ዕድል ያልደረሰውና የፈተናውም አለንጋ ያልገረፈው አለ ወይ? ይለናል። ኦስካር ዋይልድ ይመስለኛል በሶሻሊዝም ሥር የሰው ነፍስ (The Soul of Man under Socialism) ድርሰቱ “መኖር እጅግ ብርቅ ከሆኑ ባሕርያት ዋነኛው ነው። ብዙ ሰዎች እንዲሁ አሉ። ግን አይኖሩም ” ያለው (To live is the rarest thing in the World. Most people exit, that is all ) ይለናል በአንክሮ። የእኔው የትግል አድባር (አያውቀኝም) ፕሮፌሰር ሐጐስ ገብረ ኢየሱስ እናቱን ለመጠየቅ ጓድ መንግሥቱ ሔሊኮፕተር አዘዙለትና ወደ አድዋ ሔዶ ነበር። ሲመለስ A Requiem of History በሚል ያቀረበውን መጣጥፍ አልረሳውም። በዚያው ሰፊ ጽሑፉ ውስጥ እንደ ፈርጥ ያየሁለት “እናቴ በእርግጥ በሕይወት አለች። እየኖረች ግን አይደለም። She was alive, but Not living.” ይላል።

በ1980ዎቹ ካነበብኋቸው መጻሕፍት መካከል በሔንሪ ኪየምባና በዴቪድ ማርቲን የተገለጡ አስደንጋጭ አጋጣሚዎች በአእምሮዬ ውስጥ የተከሉት ክፉ ትዝታ አለ። በኢዲአሚን ኡጋንዳ ጊዜ የተፈጸመ ነው። እንዲያውም የ“State of Blood” የሚለው ጸሐፊ የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር የነበረው ሔንሪ ኪየምባ ነው። ወደ ወጉ እንመለስና ኢዲአሚን በየቀኑ ሥፍር ቁጥር የሌለው ኡጋንዳዊ የሚገድልበትና የጭፍጨፋው ወፍጮ እንበለ እረፍት የሚሠራበት ሥፍራ ነበር። በዚህ “ሥራ” ላይ የተሰማሩት ባለሙያ ነፍሰ- ገዳዮች ትንሽ ፋታ ካገኙ ወደ ሰፈር መሸታ ቤት ይሄዱና ካቲካላና ቡቅር ከሚመስለው “ነፍስን ጭምር” ከሚያስረሳው መጠጥ ይጨልጣሉ። ግድያው እንደ ጫት ሐራራ ስለሆነባቸው በማይገድሉበት ሰዓት ሁሉ ሲያፋሽጉ ይውላሉ።

አንድ ቀን ያለወትሮው ግድያው በምሽት ሰዓት ሊጠናቀቅ ስላልቻለ ዋናው ገዳይ እስረኞቹን ይሰበስብና “ዛሬ ስለመሸ ሄዳችሁ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር እደሩና ነገ በጠዋት መጥታችሁ መቃብራችሁን ቆፍራችሁ ትገደላላችሁ። አሁን ሂዱ። መልካም ዕድል” ይላቸዋል። በማግስቱ እስረኞቹ ተሽቀዳድመው በመሰለፍ መቃብራቸውን ቆፍረው በተሰጣቸው ትልልቅ መዶሻ አንዱ ሌላውን ገደለ ይባላል። ተረት ወይም የፈጠራ ድርሳን አይደለም። ዴቪድ ማርቲን በኦብዘርቨር ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ያቀርብ የነበረውን ሐተታና ከላይ በርእሱ ያመለከትሁትን የሔንሪ ኪየምባ መጽሐፍ ያነብቡአል።

ገዥዎቻች፣ አንዱን ጠባብ፣ ሌላውን ነፍጠኛ በማለት የሰየፉት ወገን ቁጥር ይታወቃል? ከምዕራብ ወደ ደቡብ፣ ከደቡብ ወደ ምዕራብ እያንከራተቱ በየኪሎ ሜትሩ የረገፈው ወገናችን ቁጥር ይታወቃል? በአኅዝ የማይገለጠው መከራውና ሰቆቃው በምን ይተመን? እዚህስ ደረጃ አልደረስንም የሚያሰኝ ምን ምልክት አለ? አሁንም ለእርድ የተዘጋጀን ነን- ሁላችንም ባንሆን አብዛኞቻችን። ንጹሐን ዜጐችን ግደሉ ብንባል ዓይናችንን የማንጨፍን አለን። አሁንም ቢሆን እኛን በእኛ እየጨረሱንም እያጫረሱንም ነው። አይደለምን? የኢዲአሚኑ ሪፖርት ይዘገንናልን?

ያንን የምታውቁትን ለፍቶ ያስተማረኝ የኢትዮጵያ ገበሬ ሲባልለት የቆየውን “ናስቲለው”…አልፎ አልፎ ታስታውሱታላችሁ? ትዝ ሲላችሁ ዓይናችሁ እንባ ይቋጥር ይሆን? (ናስቲለው በሰሜን ኢትዮጵያ ገበሬ ማለት ነው።) አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ገበሬ በመንግስት መሰቃየት ያርዳን? አቦ! አቦ! እንደ ብዕርና ወረቀት ያስጠላኝ ነገር የለም። ካሣ ተሰማ ትዝ አለኝ። ድንቀኛው ጸሐፊ ጓደኛዬ ብርሃኑ ዘሪሁን ካሣ ተሰማን አንድ ቀን አነጋግሮት ነበር። ለመነን መጽሔት ነበር። ብርሃኑ ወርቅ የሆነውን የካሣን ፕሮፋይል ሲያቀርበው “ቧንቧ ሠራተኛው ካሣ” በማለት ነበር። ካሣ ክራር መደርደር የለመደው በስሜት ነው። ከተቃጠለ አንጀቱ የሚያወጣውን ትንፋሽ በዘፈን ለማብረድ ነው። ካሣ ይዘፍናል። ስሜቱ ወደ ጽርሐ-አርያል ይከንፋል። እሱም ራሱ እንደ ማኰብኰብ ሲለው ክራሩን ሰባብሮ ሲጃራ መግዣ ፍለጋ ይሄዳል።

ይኸ ሁኔታ ዛሬ ይገባኝ ጀምሮአል። ከክራሩ ባሻገር የሚሰማው ድምፅ ያለ ይመስለኛል። ከመላእክት ጋር ሲነጋገር ቆይቶስ ቢሆን? ከአድማስ ባሻገር ከታላላቆቹ ተራሮች ላይ ሆኖ ስለዚች አገር ዕድል- ስለሚደርስባት አደጋ፣ ስለ ትንንሽ ልጆችዋ መቀጨት፣ እንደ ዛሬ ስላለው የመከራ ሌሊት ያጫወቱት እንደሆነ ማን ያውቃል? እንዲያ ሆኖ ሆኖ ካሣ ወደ ቧንቧ ሥራው ይመለሳል። እሱም ዘመንን ቆጥሮ ወደ መሬቲቱ ተመለሰ። ወደ ማኅፀናዋ።

እኛንም ደካሞች ልጆችዋንም እነሱንም ባሊጊዜና ቅምጥል አዳዲስ መኳንንትና መሳፍንት የኢትዮጵያ መሬት እኩል ትበላናለች ወይ? ስለ ጄኔራል ደጐል ያነበብሁት አንድ ታሪክ አለ። ጄኔራል ደጐል ሽባ ሆና የተወለደች ልጅ ነበረቻቸው። ወላጆች እጅግ እያዘኑ ልጅቱ በመንፈስ እንድትጠነክር የማያደርጉት አልነበረም። የሚችሉትን ጥረት ሁሉ ካሙዋጠጡ በኋላ ልጅቱ ትሞታለች። እናት መሆን አይቀርምና ማዳም ደጐል ምርር ብለው ያለቅሳሉ። ያዝናሉ። እሳቸውን ማጽናናትም ከባድ ሆነ። በዚህ ጊዜ ጄኔራል ደጐል ባለቤታቸውን “እስካሁን ድረስ ምኞታችንና ጸሎታችን ሁሉ እግዚአብሔር ከሰው እኩል እንዲያደርጋት ነበር። ይኸውና በሕይወት ባይሆን በሞት ከሁሉ ጋር እኩል ሆናለችና ልቅሶሽን ተይ…” በማለት ባለቤታቸውን አጽናኑአቸው።

ኢትዮጵያውያን ሽባ ሆነን አልተፈጠርንም። ወይም አዳዲሶቹ ዲታዎች (ኖቮሪሽ) በአፋቸው ላይ የወርቅ ፍልቃቂ እየነከሱ ከማኅፀን አልወጡም። ሕዝብ የሚገዛው እንዲህ ነው ተብለው ጊንጥ የሚመስል አለንጋ የሰጣቸው አንዳች ኅይል የለም። ለምን ገዥና ተገዥ፣ ገራፊና ተገራፊ ሆነን ቀረን? አንመራመር። አስፈላጊ ወዳልሆነ እሽኰለሌም አንግባ። ይልቁን ከሞት በፊት ስላለው እኩልነት እናንሳ። በሞት ሕይወትን ስለማምጣት፣ በደምና በአጥንት ነፃነትንና እኩልነትን ስለመቀዳጀት።- ውይይይይ ለአፍ አይገድም። ትግሉን፣ መስዋዕትነቱን በወረቀት ላይ ጨረስነው አይደል? በሃያኛው ክፍለ ዘመን መነሻ የተጫነው የእኩልነት ትግል እነ W.E.B Du Bois የጀመሩት የጥቁር አሜሪካውያን ተጋድሎ ስትራተጂ የሚነደፍበትና ፕሮግራሙ በሥራ ላይ የሚውልበት ስልት የሚወጣበት ነበር። ታላቁ ዱብዋ ተፈጥሮ ለሰው ልጆች እኩል የሰጠችውን መብት ከሰው ልጆች መለመንን የመሰለ ውርደት እንደሌለ ይገልጣል። የመብትና የነፃነት ልመናን የመሰለ ወራዳ አቋም የለም። W.E.B Du Bois The Souls of Black Folk በሚል ድሮ ባሳተመው መጽሐፍ “ተነሥ! የምታጣው ሰንሰለትህን ነው” ወደሚለው የተራማጆች ፍልስፍና ያመራል። እንዲያውም ሎወልን በመጥቀስ-

Twixt old systems and the word
Truth forever on the scaffold
Wrong forever on the throne
yet that scaffold sways the future
And behind the dim Unknown
Standeth God within the shadow Keeping watch above His own
ይላል። እውነት ዘወትር በመሰቀያው ሥፍራ፣ ውሸትና የማይገባው ሁሉ ዘወትር በዙፋኑ (በአልጋው) ላይ የመገኘቱ ነገር- ያ የመሰቀያው ጣውላ የወደፊቱን ሁሉ እየነቀነቀ መገኘቱ፣ እነሆ በጭላንጭሉ መሐል ደግሞ እግዚአብሔር ከፍ ብሎ ቆሞ የራሱን ወገኖች የማበረታታቱ ጉዳይ ዘላለማዊ ነው።

ልመለስ ወደ አሜሪካ ዓመታዊ የሰብአዊ መብት መግለጫ። ከላይ ያነሳሁአቸው የዱብዋ (አሜሪካኖች ዱባይስ ይላሉ ፈረንሳዮችን ለማብሸቅ) ወይም የፍሬደሪክ ዳግላስ ታሪኮች ለእነሱ ብዙ ይጥማቸው እንደሆነ አላውቅም። በተለይ ለሪፐብሊካኖቹ። እንደዚያም ሆኖ ይህ በእነሱ ድጋፍና ርዳታ ሞልቃቃ ሆኖ የተወለደውና የሚጨፍርብን ሥርዓት (መንግሥት) ፀረ ሕዝብ፤ ፀረ አገር፣ ፀረ እንጨት፣ ፀረ ሳር፣ ፀረ ሕዝብ፣ ለመሆኑ- እደግመዋለሁ- የእነሱ እማኝነት አለን። ጊዜው- የመለያያው- ደረሰና ነው ምሥጢሩን ሁሉ ያፈነዱት? ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። እዚያ ላይ ያለውን ነጥብ የምንመለስበት ይመስለኛል። ለአሁኑ ግን አሜሪካ በአንድ በኩል ልትረዳን የምትችላቸውን ጉዳዮች ባነሳ- ከአንባብያን ድጋፍ ካገኘሁ።

አንደኛ- እስካሁን ድረስ አሜሪካ እንዲህ ያለ በሰብአዊ መብት አከባበር ረገድ የተበላሸ አቋም፣ በፖለቲካና በአገር አንድነት ጥበቃው ረገድ አሳፋሪ ሪኮርድ፣ በሕዝብ ሰላም ጥበቃና የፍትሕ መስተንግዶ መላሸቅ ረገድ ያልሆነላቸውን መንግሥታት ወይ Evil ኤምፓየር- ወይ Rogue State አለዚያም አሸባሪ (Terrorist) ሲሉ ባጅተዋል። ወያኔ ምንድነው? በእኛ ምደባ Terrorist Regime ሊባል ይገባዋልና ስያሜው በዚሁ እንዲሆን እንጠይቃለን።

ሁለተኛ፥ ይኸ ሁሉ ከተወሳና የወያኔዎች መንግሥትም ከሕዝብ የብድርና የርጥባን ገንዘብ 20 ቢሊዮንዶላርስ ጠልፎ ወደግል ሂሳብ ያዋለ እንደመሆኑ- የዋና ዋና ሌቦችን የስም ዝርዝር እናቅርብና ወደየምዕራቡ መዲና ሲገቡ እንዲያዙና እንድንፋረዳቸው።- ገንዘባቸው እንዳይንቀሳቀስ እንዲደረግ- ከምዕራባውያን የሚሰጣቸው ማናቸውም ርዳታ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲቋረጥ- ኢኮኖሚው ራሱ የተጠለፈና ወደ ግል ኩባንያነት የተዛወረ ስለሆነ የትኛውም አገር ከወያኔዎች ጋር የንግድ ልውውጥ እንዳያደርግ ዘመቻችንን እንዲቀበለን ትብብር እንጠይቃለን።- ከናይን ኢለቨን ጋር በተያያዘ አሜሪካ እንዳይደርሱ እግድ የነበረባቸው አንዳንድ ዘራፊና አቀባባይ ሌቦች እንደገና ወደ አሜሪካ ብቅ እያሉ የለመዱትን የሞራል ድቀት ትርኢታቸውን እያሳዩ ናቸው። ከእነዚህ መካከል አንዱን አረብ ግለሰብ የኢትዮጵያ ትውልድ ሁሉ የሚፋረደው ስለሆነ ተይዞ እንዲመረመር እንጠይቃለን። ወርቃችን፣ ሌሎች የማዕድን ሀብቶቻችን ወዘተ በዚሁ ሰው እንደ ትንሽ ዕቃ በየቀኑ እየተጫነ እንደሚወሰድ እናውቃለን። እናስረዳለንም። …………

በ1980ዎቹ Republic of Fear በሚል ርእስ ስለ ሳዳም ሑሴን ጨለማ አገዛዝ የሚያወሳው መጽሐፍ በእጅጉ ያሸማቅቃል። ጸሐፊው ኬናን ሜኪያ ይባላል። የኢትዮጵያ የዛሬ ሁኔታ ደግሞ ሌላ ባሕርይ ያለበት ይመስለኛል። ስለ ዋናዎቹ አምባገነኖች ሲነሣ አብዛኛዎቹ ነጠላ ናቸው። በቺሊ ፒኖቼ- በሩማንያ ቻይቼስኮ፣ በኢራቅ ሳዳም ሑሴን፣ በሊቢያ ጋዳፊ…ናቸው። ለወርቅ ጥጃቸው የማይንበረከክ፣ ለምስላቸው የማይሰግድ ከሁለት ስፍራ ይከፈላል። ያማቸው፣ ስማቸውን ያጐደፈ…የሚሰቃይበት አዳዲስ መሣሪያ አስፈልፍለዋል። ዝርዝር የማሰቃያውን ስልትና ድርጅት ከማእከላዊ ምርመራ ሠራተኛነት አምልጠው የወጡ ሰዎችን ማነጋገር ይቻላል። ባይሆን አንድ ጥያቄ በአእምሮአችሁ የሚመላለስ ወገኖቼ አትታጡም። መለስ ከሞተ በኋላም ይኸ አገር በአምባገነን የሚመራ ነው ለማለት ይቻላል ወይ? በእኔ በኩል ከሰዎች ጋር ስወያይ “አምባገነኑ የማይታወቅ አምባገነን መንግሥት” A Dictatorship without a Dictator ግን አገዛዙ መንጋ ጨካኖች፣ ነፍሰ- ገዳዮችና በዝባዦች ቢኖሩትስ? የፈረንሳዩ ታላቅ ምሁር ዣን ፍራንስዋ ሬቨል Without Marx or Jesus በሚለው መጽሐፉ እንዲህ ያሉትን አምባገነኖች ባሕርይ Collective Mediocrity and Collective bestiality ይለዋል። ነገሩ እንዲህ ነው። መለስ ሲሞት የእሱ እጓለማውታ (Orphans) መፈላለግ ያዙ። ሰብሳቢ አጣን ብለው ወደ ትካዜው ዓለም ተሰደዱና መጠራራቱን አንድ መፍትሔ አደረጉት። ምንጣፉን ቶሎ ብለው የረገጡት እነ እንቶኔ ደግሞ አራት ኪሎን የተጫጫነውና አሁንም የሚገዛውን መንፈስ በፍጥነት በማናቸውም አስማት ለማስወጣት አልቻሉም። ትንሽ ፋታ ሳያስፈልጋቸው አልቀረም። ጥቂት ጊዜ ከገዙ በኋላ የፕሮፓጋንዳውም መሣሪያ ትንሽ ትንሽ ይደፍረዋል። “መለስኮ ሰው ነው” ማለት ይጀምራል። ሰው መሆኑን ዛሬ ነው ያወቁት አትበሉአቸው። እኛ መለስን ከመቃብር አውጥተን አንፋረደውም። እነሱ ራሳቸው ከሳሽም ፈራጅም ይሆናሉ። ጠብቁ ብቻ።

በደርግ ጊዜ ስለአባካኝነትና አሻጥር ትልቅ ጉባኤ ተዘርግቶ ነበር። በንቁዝ (ኮራፕት) ባለሥልጣኖችና በመሳሰሉት ላይ ጥብቅና ወሳኝ የሆነ ርምጃ ስለሚወሰድበት ሁኔታ ውይይት ሲካሄድ በየቦታው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ አሳብ ይቀርባል። በዚያ መድረክ ላይ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር የነበሩት ጄኔራል ታዬ ጥላሁን የተናገሩት ትዝ ይለኛል። በአጤ ምኒልክ ዘመን እቴጌ ጣይቱ “ለአገሬ ለየጁ ያለው አንድ አፈንጉሥ ብቻ ስለሆነ ሌላ እንዲጨመርለት እጠይቃለሁ” ሲሉ እቴጌይቱን በአደባባይ ተቃውመው የማያውቁት ንጉሠ ነገሥት “እንኳን ሌላ ተጨምሮበት አንዱም ቢሆን አልተቻለም” አሉ ይባላል።

በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ከመለስ ሞት በኋላ አንድ ታዋቂና በአደባባይ ስሙና ሹመቱ የተገለጠ አምባገነን ባይኖርም ሟቹ በመጠኑ ራቅ ያደረጋቸው ሰዎች አልጋው ላይ የተረባረቡ ይመስለኛል። አቦይ ስብሐት፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ዐባይ ወልዱ፣ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ወዘተ ወዘተ…በአንድ አገር የስለላው መረብ እንዳለ ወደ ፍጹማዊ ኅይል ሲለወጥ ደግሞ የዜጐች ሁሉ (መካከለኛ ደረጃ ያሉት ወያኔዎች ሳይቀሩ) መብት ወደ ኢምንትነት ይለወጣል። የሥነ መንግሥት ምሁራን በመንግሥት ውስጥ መንግሥት (ኤስቴት ዊዝን ኤ ስቴት) የሆነውን እንዲህ ያለውን ሥርዓት “መሪ” የሚባለውን ግለሰብ ጭምር ሽባ አድርጐ የሚቀፈድደው ያደርጉታል። በአሁኑ ሁኔታ ቀስ በቀስ የመለስ የቅርብ ሕዝብ አጫራሾች ዕጓለማውታ (ኦርፋንስ) ቢመስሉም ሌሎች በርካታ አምባገነኖች ጡንቻቸውን እያፈረጠሙ ናቸው። ወትሮ አንድ አምባገነን ያልቻለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የብዙ አምባገነኖች ተሸካሚ ሆኖዋል። ሁሉም ነፍሰ ገዳዮች! ነፍሰ ገዳይ የማይፈራስ ማነው?

ለጊዜው በመንጋ ተንኮለኞች- ነፍሰ ገዳዮችና የዝርፊያ ሠራዊት እየተገዛን እንገኛለን። ስለእነሱ ድግስ፣ ስለ እነሱ ጥቅም፣ እነሱ የትኛዋን ጋለሞታ እንደሚጐበኙ፣ የትኛዋን መለኮን ዛሬ እንደወሰዱ እንወያያለን። በጥቃቅን ጉዳዮች አእምሮአችንን አስጨንቀናል። ወጣጥረነዋል። ይልቁን በሌላው ዓለም እየተቀጠቀጠ ማረፊያ ያጣው መንግሥታዊ አሸባሪነት የሙጥኝ ብሎ የሚገኘው በኢትዮጵያ መሆኑን እንተባበር። ይህን የሽብር መንግሥት ሌላው ቀርቶ በብረት መሞከርን ካህናቱና መነኮሳቱም መደገፍ አለባቸው። ከቶውንም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በፋሺስቶች ጥይት ሊደበደቡ ጥቂት ሰከንዶች ሲቀራቸው “ልጆቼ ኢትዮጵያውያን ለፋሺስቶች እንዳትገዙ አውግዤአለሁ” ማለታቸው ይጠቀሳል። አዳዲስ ካሕናትና የዚህ ትውልድ ቀሳውስት ነገሩን ቸል እንኳ ቢሉ የአቡነ ጴጥሮስ ግዝትና ውግዘት አለብን። ቋሚ ነው- እስከማዕዜኑ።

ትግልና ታጋይ የሚጠይቁት አንድ ነገር ብቻ ነው። በደረትህ ውስጥ ጤነኛ ልብ፣ በጭንቅላትህ ውስጥ ጤናማ አእምሮ ካለህ ማናቸውም ችግር አይፈታህም። ጥይት አይመታህም። ድንፋታ ትርጉም አይሰጥህም። ቅጥፈትና ማስፈራራት ትጥቅህን አያስፈታህም። ልጆቼ ልላቸው የምችለው እነ እስክንድር፣ በቀለ፣ አንዱአለምና ርእዮት ይህን ወኔ በሰፊው የተቀዳጁ ናቸውና እንኮራባቸዋለን። እነሱ ወኅኒ ዓለም ሲገቡ የከዳናቸውና የቆሙለትን ዓላማ ጭምር የረሳንባቸው ከመሰላቸው ደግሞ አደራ በላነት ሊሰማን ይገባል።

ይህን ጽሑፍ የጀመርሁት በወያኔ የልደት በዓል ምክንያት ትንሽ የምለውን ለማቃመስ ነበር። ምናልባትም እንደ ፍሬደሪክ ዳግላስ ለእነዚህ ሰዎች “ጉንበት 20- ጉንበት ሃያ ትሉናላችሁ ጉንበት ሃያ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥቃይ ሁሉ እናት የሆነችው ስቃይ የመጣችበት ቀን። ጉንበት 20 የባርነትና ወደር የሌለው ውርደት መታሰቢያ ቀናችን ናት። ጉንበት 20 ለእሥራታችን መታሰቢያችን ናት።” ልንላቸው እንችላለን። ይኸ የደፋሮቹ ጋዜጠኞች – የጀግኖቹ የፖለቲካ መሪዎችና ገበሬዎች የተባበረ ድምጽ ነው። በሬሳችን ላይ የሚጨፍሩበት፣ በመቃብራችን ላይ የሚያሽካኩበት፣ ቤትና ንብረት አሳጥተው ለስደት ያበቁንና በዚህ ደስታ የሚሰክሩበት በዓላቸው- የእኛ የልቅሶ ዕለት፣ የእኛ የመከራ ቀን መታሰቢያ ነው።

በመጨረሻም እንደገና ለአሜሪካ በማቀርበው ጥያቄ ላይ ይህችን ነጥብ እደግማለሁ። ይህ መንግስት ኢቭል የምትሉት አይነት ነው? ወይስ አሸባሪ? የወያኔ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች ላይ የሚፈጽሙትን እልቂት፣ የወያኔ አማራዎች (እነበረከት አምሮች ከተባሉ) በኢትዮጵያውያን አማሮች ላይ የሚያካሄዱትን መጠነ ሰፊ ድምሰሳ፣ የወያኔ ሙስሊሞች በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እያደረሱ የሚገኙትን ወከባና ወደር የሌለው ጥቃት፣ ሟቹ የመለስ የሃይማኖት የይስሙላ ፓትርያርክና እንደ ሩሲያዊው ራስፑቲን የሚቆጠረው አባ ጳውሎስ በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ያካሄደውን ሥቃይ አሜሪካ ከእኛ በላይ እንደማያውቀው ለዴሞክራሲ፣ ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ስትል ርምጃ ለመውሰድ አቅዳለች? አጤ ኅይለሥላሴ በቀድሞው የመንግሥታት ማኅበር ጉባኤ ላይ ያደረጉትን ንግግር ለመጥቀስ እገደዳለሁ – “ታሪክና ትውልድ ፍርዳችሁን ይጠባበቃሉ!”
እነሆ ዛሬ በኢትዮጵያ የሰው ዘር ጠላት የሆነ ሥርዓት አለ። የሒትለርን ፀረ ሕዝብነት ለመረዳት የፖላንድ መወረር፣ የሃምሳ ሚሊዮን ሕዝብ ማለቅ፣ የስድስት ሚሊዮን አይሁድ መጨፍጨፍ መጠበቅ ይገባል? ታሪክ አላስተማራችሁምን? በአሜሪካ ላይ ስንት ክህደትና ቸልታ እንቁጠር? በፋሺስት ወረራ ዘመን ሩዝቬልትና ሴክሬተሪ ሐል ያሳዩን ክሕደትና ቸልታ አይረሳንም። አሜሪካ የበለጠ ትናገር! እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይጠብቃችሁ!!

ወያኔ በግንቦት 7 ስም ሠላማዊ ዜጎችን ማሰቃየቱን ባስቸኳይ ማቆም አለበት

ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ2003 ዓም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትዕዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት 7 ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርዐት የሚቃወሙ ግለሰቦችን፤ ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልጹ ዜጎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን “ግንቦት ሰባቶች” ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነጻነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን፤ ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት 7 አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሠረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል።

ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ሥልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ሥልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ሥርዓቱን ዕድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል:: ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈጸሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሠላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል:: በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ ፡በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈጸመው ጭፍጨፋና ከ2004 እስከ 2005 ዓም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የምስት የለም::

ሟቹ መለስ ዜናዊና በህይወት የሚገኙ ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ በጸረ ፋሽስት ዘመቻ ወቅት ባንዳ ከነበሩ አባቶቻቸዉና አያቶቻቸዉ የተወረሰ ፋሽስት ጣሊያን ለደረሰባት ሽንፈት በዘርና በሃይማኖት ተከፋፍለን እርስ በርሳችን እንድንጠፋፋ ተክላብን የሄደቺው ተንኮል አካል ነው ::

የዚህ የጥፋት አጀንዳ አስፈጻሚ የሆነው ወያኔ የጀመረውን አገር የማፍረስና ህዝብ የመከፋፈል አጀንዳ ለማሳካት በየክልሉ የተኮለኮሉ ምስሌኔዎች እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብና ክልል ላይ እየፈጸሙት ያለው በደልና ሰቆቃ አዲስ ምዕራፍ በያዘበት በአሁኑ ወቅት እራሳቸዏን ለባርነት አዋርደው ህዝባቸውን በማዋረድ ላይ የሚገኙት የብአዴኑ አለምነህ መኮንንን የመሳሰሉ ሆድ አደሮች ውርደት በቃን ዘረኝነት በቃን ብለው በተነሱ ዜጎች ላይ እየወሰዱ ያለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሆኖአል::

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ሞክራሲ ንቅናቄ ከሰሞኑ በደረሰው መረጃ ወያኔ ከአማራው ቀምቶ በትግራይ ክልል ባስገባቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ንጽሃን ዜጎች ለምን በወያኔ የግፍ አገዛዝ ትማረራላችሁ እየተባሉ በወያኔ ታማኝ ሚሊሻዎች

እስር እንግልትና ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አረጋግጦአል:: በዚህ በአዲስ መልክ በተጀመረዉ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ መሳሪያ ያነገቡ የህወሃት ሚሊሻዎች ከክልላቸዉ ዉጭ ወደ ተለያዩ የአማራ ከተማዎችና ወረዳዎች ሰርገዉ እየገቡ የእነሱን ቋንቋ የማይናገረዉን ሁሉ የግንቦት 7 ተላላኪዎች ናችሁ በሚል እያሰሩ በመደብደብ ላይ ናቸዉ።

ይህ በመሆኑ ዛሬ አትዮጵያን ከሱዳንና ትግራይን ከጎንደር ጋር በሚያዋስኑ የአማራ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ገበሬዎች እጃቸዉ እርፍ ከሚጨብጥበት ግዜ በወያኔ ሰንሰለት የሚታሽበት ግዜ ይበልጣል፤ የመንግስት ሰራተኛዉና የከተማ ነዋሪዉም ቢሆን አብዛኛዉን ግዜ የሚያጠፋዉ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር ግምገማ በመቀመጥ ሲሆን ተማሪዉና ወጣቱ ህብረተሰብ ደግሞ “መጡ አልመጡም” እያለ ሌሊቱን የሚያሳልፈዉ በየጫካዉ እየተሸሸገ ነዉ።

የዚህ አይነት አስከፊ ግፍና መከራ በአፋር ፡ በጋምቤላ በኦጋዴንና በኦሮሚያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ሲፈጸም ቆይቶአል:: ? ወያኔ እራሱ አርቅቆ ባጸደቀውና በሐምሌ ወር 1987 ዓም በስራ ላይ የዋለዉ የወያኔ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ በዘጠኝ የፌዴራል ክልሎች መከፈሏንና እያንዳንዱ ክልል እራሱን በእራሱ የማስተዳደር መብቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ህገ መንግስት መሠረት እያንዳንዱ ክልል የራሱ ቋንቋ፤ የአስተዳደር ማዕከልና እንዲሁም የክልሉን ሠላምና ጸጥታ የሚያስከብር የፖሊስ ኃይል ይኖረዋል ይላል። ታድያ ለምንድነዉ እያንዳንዱ ክልል የራሱ ፖሊስ ኃይል አያለዉ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ የህወሃት ታማኝ ሚሊሻዎች አማራ ክልል ዉስጥ እየገቡ አማራዉን የሚያሰቃዩት?

መልሱ ቀላል ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝባዊ አምቢተኝነቱ እያየለ በመጣና የነጻነት ኃይሎች ጡንቻ በፈረጠመ ቁጥር ወያኔ አንገቷ ላይ ቀጭል እንደታሰረባት በቅሎ ይደነብራል። የደነበረ ደግሞ መራገጡ አይቀርምና መሳሪያ ያነገቡ ኃይሎችን እንቅስቃሴ እገታለሁ በሚል ከንቱ ጥረት ደንባራዉ ወያኔ የፈሪ በትሩን በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች፤ ወጣቶችና ሠራተኞች ላይ ማሳረፍ ጀምሯል።

ወያኔ እንደ ግንቦት ሰባት የኮነነዉና የህዝብና የአገር ጠላት አድርጎ የሳለዉ ድርጅት የለም፤ የወያኔ የዜና ማሰራጫዎችም ይህንን የአገዛዙን አቋም በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰምተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ማን ለመብቱና ለነጻነቱ እንደቆመና ማን መብቱና ነጻነቱ ላይ እንደቆመበት ለይቶ የሚያዉቅ ህዝብ ነዉ። ስለዚህም ግንቦት ሰባት ወያኔዎች አላፊዉንና አግዳሚዉን “ግንቦት ሰባት” ነህ እያሉ ከሚያሰቃዩ፤ ህዝብንና ግንቦት ሰባትን ያስተሳሰረዉ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ነዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ቢመልሱ ለእነሱም፤ ለእኛም ለአገርም ይበጃል የሚል የጸና እምነት አለዉ። ወያኔ በኢህአዴግ ስም ያሰጠጋቸዉን ምሰለኔዎች ጨምሮ ከራሱ ዉጭ ሌላ ማንንም አያምንም፤ ስለዚህም ነዉ የአገሪቱን የመከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች በራሱ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያደረገዉ። ዛሬ በግልጽ እንደምንመለከተዉ ወያኔ በጉልበት ለያዘዉ ስልጣን ያሰገኛል ብሎ በሚጠረጥረዉ ቦታ ሁሉ የራሱን ልዩ ሚሊሺያ እየለላከ የኢትዮጵያን ህዝብ መኖሪያ ቤቱ ድረስ አየሄደ እያጠቃ ነዉ። ግንቦት ሰባት ወያኔና የፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐቱ የቆሙት በፍጹም ማንሰራራት የማይችሉበትት የመጨረሻ መቀበሪያ ጉድጓዳቸዉ ጫፍ ላይ ነዉ የሚል ጽኑ እምነት አለዉ። ሆኖም ጉድጓድ ጫፍ ላይ የቆመ ጠላት በራሱ ተወርዉሮ ጉድጓዱ ዉስጥ አይገባምና ይህንን የተዳከመ ጠላት እተፈራገጠ ጉዳት ከማብዛቱ በፊት ለመደምሰስ ክንዳችንን አጠናክረን በህብረት እንደ አንድ ሰዉ እንነሳ ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

በዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ዝክር፤ በእህቶቻችን ኮርተናል!!!

ለዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን መታሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የሩጫ ትዕይንት ላይ ወጣት ሴቶች ባሳዩት ልበ ሙሉነት ኮርተናል። የሩጫውን ትዕይንት አስታከው፣ በአብዛኛው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ የተነገረላቸው ወጣት ሴቶች ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለህሊና እስረኞች መፈታት እና ለሀገር አንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድረገው ጮኸዋል፤ ዘምረዋል። እነዚህ ወጣት ሴቶች በሥርዓቱ ምን ያህል እንደተማረሩ በቃላትም በአካል ንቅናቄም አሳይተዋል። ዘረኛውና ፋሽስቱ ወያኔ ግን “ለምን ተቃወማችሁኝ” ብሎ አስሯቸዋል፤ ከፊሎቹም የደረሱበት አይታወቅም። በእህቶቻችን ቆራጥነት ኮርተናል፤ በወያኔ የፈሪ ዱላ ደግሞ ተቆጥተናል። በ1997 እና 98 “የወላጆቻችን ድምጽ ይከበር” ያሉ ሕፃናትን የጨፈጨፈው ወያኔ በ2006 ወጣት ሴቶችን ከማሰቃየት ይመለሳል ብለን አናምንም። ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ የፈሪ ዱላው የማይቀር ነገር ነው።

የወንዶቹን ያህል የተዘገበ አይሁን እንጂ በክፉም በደጉም ሴቶች ያልተሳተፉበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም። የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብናይ በፋሽስት ወረራ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች በአርበኝነት ዘምተው አዋግተዋል፤ ተዋግተዋል። በተለያዩ ምክንያቶች መዝመት ያልቻሉት ደግሞ በውስጥ አርበኝነት ተሰልፈው የጠላት ምስጢሮች ለአርበኞች እንዲደርሱ በማድረግ ከፍተኛ ጀብዱዎችን ፈጽመዋል። ከፋሺስት ወረራ ወዲህ በነበሩ ዓመታት ውስጥም ለፍትህ እና ለነፃነት በተደረጉ ተጋድሎዎች ሴቶች ጉልህ ተሳትፎ ነበራቸው። በተማሪዎች ትግል ውስጥ ለምሳሌ፣ ወጣት ሴቶች በአመራር ደረጃ በመሳተፍ ትግሉን መርተዋል፤ የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር ከፍለዋል። ከዚያ ወዲህም በነበሩት ዓመታት በኢሕአፓ እና ሌሎችም ድርጅቶች አመራርና አባልነት ተሳትፈው ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ነበሩን። በቅርቡም በምርጫ 97 እንቅስቃሴም የሴቶች በተለይም የወጣት ሴቶች ተሳትፎ ምን ያህል ጉልህ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነውና እናስታውሳለን። ለምርጫ ድምጽ መከበር ወጣት ሽብሬ ደሣለኝን ጨምሮ በርካታ ሴቶች ሕይወታቸውን ሰውተዋል፤ ከዚያ የበለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዛሬም እንደ ርዕዮት ዓለሙ የመሳሰሉ ጀግኖች በወያኔ ወህኒ ቤቶች እየማቀቁ፤ በየእለቱ ሰቆቃ (ቶርቸር) እየተፈፀመባቸው መሆናቸው በሀዘንና በቁጭት እናስባቸዋለን።

በሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ አስፈላጊነት በመፈክር ደረጃ አንስተን የምንተወው ጉዳይ አይደለም። የሴቶች ተሳትፎ ያልታከለበት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ግቡም አይመታም፤ ቢመታም ዋጋ የለውም።

ከጥቂት ዓመታት በፊት የተካሄዱትን የሰሜን አፍሪቃና የመካከለኛው ምሥራቅ አብዮቶችን በአንክሮ የተከታተለ ማንኛውም ሰው ከሚገረምባቸው ነገሮች አንዱ ሴቶች ያሳዩት ቆራጥነት እና ያካሄዱት ብስለት የተሞላው ትግል ነው። በቱኒዚያ የወጣቶች እንቅስቃሴ ውስጥ ወጣት ሴቶች ከመጀመሪያው ጀምሮ የአመራር ቦታ በመያዝ ተሳትፈዋል። በግብጽም የወጣት ሴቶች እልህ ከወንዶቹ በልጦ ታይቷል። አሁን በዩክሬን ውስጥ የምናየው ሀቅም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው።

የሴቶች በሕዝባዊ አብዮቶች በስፋት መሳተፍ ከቁጥር ማብዛት እጅግ የላቀ መሠረታዊ ጠቀሜታዎች አሉት። ጥቂቶቹን እንደሚከተለው መዘርዘር ይቻላል።

ለሴቶች ያልተመቸ ሥርዓት ለማንም አይመችም። ለማኅበረሰብ በጠቅላላ የሚመች ሥርዓት መገንባት ማለት በቅድሚያ ለሴቶች የሚመች ሥርዓት መገንባት ማለት ነው። ይህ ሥርዓት ደግሞ እነሱ እራሳቸው እየተሳተፉበት፤ ከዚያም አልፎ እየመሩትም ነው መገንባት ያለበት።
ሴቶች ከወንዶች በላይ ታጋሾች ናቸው፤ ሲያመሩ ደግሞ በቀላሉ አይመለሱም ተብሎ ይታመናል። እናም የሴቶች በተቃውሞ ትግል ውስጥ በብዛት መሳተፍ ሥርዓቱ በሕዝቡ ምን ያህል እንደተጠላ ግልጽ አመላካች ነው።
የወጣት ሴቶች በድፍረት ለተቃውሞ አደባባይ መውጣት ወጣት ወንዶችን ያጀግናል። የወጣት ወንዶች መጀገን ደግሞ ወጣት ሴቶቹን ይበልጥ ያጀግናል። ወጣት ሴትና ወንዶች በእርስ በርስ አርዓያነት ይጀጋገናሉ። እናም ወጣት ሴቶች አምረው ተነሱ ማለት ሁሉም ወጣቶች ሁሉ አምረው ተነሱ ወደማለት ያመራል።
የእናቶች መቁረጥ አባቶችን ያነሳሳል፤ የእናትም የአባትም መነሳት ደግሞ መላው ቤተሰብ በሥርዓቱ ላይ እንዲነሳ ያደርገዋል። እናም እናቶች አመረሩ ማለት መላው ቤተሰብ አመረረ ማለት ይሆናል።
የሴቶች በትግል አመራር ቦታ ላይ መገኘት በተቃዋሚዎች መካከል ኅብረትን፣ መተሳሰብን ባጠቃላይም ቤተሰባዊ ስሜት ይፈጥራል።
ሴቶችና ወንዶች አብረው ሲቆሙ ነው የመተባበር ጥቅም በጉልህ የሚታየው!
የእህቶቻችን በድፍረት ድምፃችሁን ማሰማት ያለው ትርጉም ከድምፃችሁ ከፍታ እና ከቁጥራችሁ በላይ ነው። ዛሬ ጥቂት እንኳን ብትሆኑ ነገ ብዙዎቻችን አርዓያነታችሁን እንድንከተላችሁ ያደርገናል። እናም እህቶቻችን በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ባሳያችሁን ድፍረት ተበረታተናል። ኢትዮጵያ ብሩህ ራዕይ ያላት፤ ቆራጥነትን የተላበሱ ወጣቶች ያሏት መሆኑን አሳይታችናል። ይህ ትንሽ ጅምር የትልቅ ሕዝባዊ ማዕበል መንገድ አመላካች ነው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ዘረኛውንንና አምባነኑን ወያኔ ከጫንቃችን ለማውረድ በምናደርገው ትግል የእህቶችና የእናቶች ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ያውቃል፤ ስለሆነም ሴቶች ትግሉን በስፋት እንዲቀላቀሉ ጥሪ ያደርጋል። ሴቶችና ወንዶች፤ ወጣቶችና አረጋዊያን ሁላችንም የወያኔን ዘረኛ አገዛዝን እንዲያበቃ በጽናት እንታገል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Wednesday, March 5, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የስምሪት ሃላፊ ሾመ

የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 በመጥለፍ ጄኔቫ በማሳረፍ ጥገኝነት መጠየቁን ተከትሎ፣ ካፒቴን ዮሃንስ ሃይለማርያምን አዲስ የስምሪት ሃላፊ አድርጎ ሾሟል።
የቀድሞው ሃላፊ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን በምን ሁኔታ እንደለቀቁ ባይታወቅም፣ ስልጣናቸውን የለቀቁት በጠለፋው ማግስት መሆኑ ጉዳዩ ከሃይለመድህን አበራ ጠለፋ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም የሚሉ አስተያየቶች ይቀርባሉ።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ጠለፋው የአየር መንገዱን ስም በምንም መልኩ እንዳልጎዱት ተናግረዋል። የስዊስ አቃቢ ህጎች በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን ላይ የሚያደርጉትን የምርምራ ውጤት ይፋ ሳያደርጉ ፣ የአየር መንገዱ ስራአስኪያጅ በየትኛው ጥናት ላይ ተመስርተው “ጠለፋው ምንም አይነት ተጽኖ አላመጣም” ብለው እንደተናገሩ ግልጽ አላደረጉም።
አቶ ተወልደ ከጠለፋው ጋር የተያያዙ ችገሮችን በብቃት መፍታታቸውንም ተናግረዋል፣ ይሁን እንጅ የትኛውን ችግር እንደፈቱ አላብራሩም።
የረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ጠለፋ የመገናኛ ብዙሃንን እና የኢትዮጵያውያንን ስሜት እንደያዘ ነው። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአብራሪው ድጋፋቸውን በተቃውሞ ሰልፎች እየገለጹ ነው። በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሃይለመድህን እንዲፈታ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረዋል።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን ሳያስረክቡ እንዳስረከቡ ተደርጎ የተነጠቁት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ታይላንድ ባንኮክ ውስጥ በጥብቅ የህክምና ክትትል ወይም (ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት) ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል።
ግለሰቡ ያለመሳሪያ ድጋፍ በራሳቸው መተንፈስ እንደማይችሉ ፣ ሰዎችን እንደማያናግሩና በዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ እኩለቀን ላይ አንድ የሆስቲታሉ ሰራተኛ ለኢሳት ተናግረዋል።
አቶ አለማየሁ ከኦህዴድ የምክር ቤት አባላት ጋር በክልሉ ስለሚታየው ሙስናና የመልካም አስተዳደር መበላሸት ጭቅጭቅ የተሞላበት ስብሰባ ካደረጉ በሁዋላ ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ ራሳቸውን መሳታቸው ይታወቃል።
በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩት አዲሷ የኦህዴድ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ አስቴር ማሞ አቶ አለማየሁ ገርጂ በሚገኝ ሆስፒታል አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ ከተደረገ በሁዋላ ሆስፒታሉ ወደ ውች እንዲላኩ ማዘዙንና ማምሻውን ወደ ውጭ እንዲላኩ ተደርጓል። ባንኮክ ከደረሱበት እለት ጀምሮ አቶ አለማየሁ ራሳቸውን በመሳት ሰዎችን ለማነጋገር ሳይችሉ ቀርተዋል። ባለቤታቸው ከጎናቸው በመሆን እያስታመሙዋቸው መሆኑንም ኢሳት ለመረዳት ችሎአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረገው የኦሮሚያ ምክር ቤት ስብሰባ የአዲሱን የክልሉን ፕሬዚዳንት ሹመት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ ዜና ደግሞ በመልካም አስተዳደርና በሙስና ዙሪያ የኦሮምያ ክልል ሲቪል ሰርቪስ አባላት ባለፈው ቅዳሜ በአዳማ ከተማ ለስብሰባ ቢጠሩም አብዛኛው ሰራተኛ ሊገኝ ባለመቻሉ በድጋሜ እንዲጠራ ተወስኗል።
በስብሰባው ላይ የተገኙ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ” ዘወትር ከማውራት ውጭ ምንም የሚገኝ መፍትሄ የለም፣ የእረፍት ጊዜያችንንም በከንቱ ማባከን” የለብንም በማለት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
በስብሰባው ላይ ያልተገኙት ሰራተኞች በሚቀጥለው ስብሰባ ላይ የማይገኙ ከሆነ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሎአል።

በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኘው ብአዴን የአቶ አለምነው መኮንንን ንግግር ለማስተባበልና ምንጩን ለማወቅ እየተዋከበ ነው

የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ህዝብ ላይ ያዘነቡትን ጸያፍ ስድብ ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባው ብአዴን፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ በራሳቸው በአቶ አለምነው መኮንን እንዲሁም በብአዴን ሊቀመንበርና በምክትል ጠ/ሚንስትር ደመቀ መኮንን አማካኝነት መግለጫ ቢሰጠም፣ ህዝቡን ለማሳመን ባለመቻላቸው፣ በወቅቱ በስብሰባው ላይ የተገኙ ጋዜጠኞችና ሌሎች ተወያዮች ቀርበው አቶ አለምነው አልተናገሩም እያሉ እንዲያስተባብሉ እየተደረገ ነው።
ከአስተማማኝ የደህንነት ምንጮች በተገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ መረጃውን ለኢሳት ያቀበሉትን ሰዎች ለማወቅ በወቅቱ የነበሩትን ጋዜጠኞች፣ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎችና የደህንነት ሰራተኞች ስልክ በመጥለፍ ተጨማሪ ክትትል እያደረጉ ነው። ይሁን እንጅ መረጃው አስቀድሞ የደረሳቸው የደህንነት ሰዎች ማንኛውንም በስልክ የሚያደርጉትን ግንኙነት በማቆማቸው የተፈለገው ውጤት ሊገኝ ባለመቻሉ ተጨማሪ ራስ ምታት መፍጠሩ ታውቋል።
አቶ ደመቀ መኮንን ተቃዋሚዎች ልማቱን ለማደናቀፍ የፈጠሩት የኮምፒዩተር ቅንብር ነው ቢሉም የብአዴን አባላት ሳይቀሩ በሊቀመንበሩ ንግግር መበሳጨታቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። በሚቀጥለው አርብ በሚደረገው የአማራ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ጉዳዩ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
አንድነትና መኢአድ በባህርዳር ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍና ለተቃውሞ የወጣው ህዝብ ብዛት ያስደነገጣቸው የብአዴን አንዳንድ አመራሮችና አባላት፣ አቶ አለምነው በይፋ ህዝቡን ይቅርታ ይጠይቁና ይህ ምእራፍ ይዘጋ በማለት እየጠየቁ ሲሆን፣ ዋናዎቹ አመራሮች ግን ጉዳዩ የአንድ ሰሞን ጫጫታ ከመሆን አይዘልም በማለት የሌሎችን አስተያየቶች ሊቀበሉ ፈቃደኞች አልሆኑም።