Thursday, May 28, 2015

U.SETHIOPIA'S MAY 24 PARLIAMENTARY AND REGIONAL ELECTIONS

U.S. Department of State

Mobil



Press Statement
Marie Harf
Deputy Department Spokesperson, Office of the Spokesperson
Washington, DC
May 27, 2015

The United States commends the people of Ethiopia for their civic participation in generally peaceful parliamentary and regional elections on May 24. We acknowledge the National Electoral Board’s organizational efforts and the African Union’s role as the only international observer mission on the ground. We also note the importance of the nine televised party debates as progress in fostering open public discussion of the challenges facing the country. We encourage all candidates, political parties and their supporters to resolve any outstanding differences or concerns peacefully in accordance with Ethiopia’s constitution and laws.

The United States remains deeply concerned by continued restrictions on civil society, media, opposition parties, and independent voices and views. We regret that U.S. diplomats were denied accreditation as election observers and prohibited from formally observing Ethiopia’s electoral process. Apart from the election observation mission fielded by the African Union, there were no international observer missions on the ground in Ethiopia. We are also troubled that opposition party observers were reportedly prevented from observing the electoral process in some locations.

A free and vibrant media, space for civil society organizations to work on democracy and human rights concerns, opposition parties able to operate without impediment, and a diversity of international and domestic election observers are essential components for free and fair elections. The imprisonment and intimidation of journalists, restrictions on NGO activities, interference with peaceful opposition party activities, and government actions to restrict political space in the lead-up to election day are inconsistent with these democratic processes and norms.

The United States has a broad and strong partnership with Ethiopia and its people. We remain committed to working with the Ethiopian Government and its people to strengthen Ethiopia’s democratic institutions, improve press freedom, and promote a more open political environment consistent with Ethiopia’s international human rights obligations.




ፊታችንን ከምርጫ ፓለቲካ ወደ ሁለገብ ትግል እናዙር!የአርበኞች ግንቦት 7

ምርጫ 2007 ተጠናቆ ተወዳዳሪም አወዳዳሪም የሆነው ህወሓት ይፋ ውጤት እስኪገልጽ እየተጠበቀ ነው። ሁሉ በእጁ ነውና ባለሥልጣኖቹ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚስማማቸው እስከሚነግሩን ጥቂት ቀናት ይወስዱ ይሆናል። ከፈለጉ ሁሉን የፓርላማ ወንበሮች ሊወስዷቸው ይችላሉ፤ ካሻቸው ደግሞ ጥቂቱን ለተቃዋሚዎች ሊሰጡ ይችላሉ። ወሳኞቹ እነሱ ናቸው። በዚህ የፓርላማ ወንበሮች እደላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ አንዳችንም ሚና የለውም።

ምርጫ የሕዝብ የሥልጣን ባላቤትነት ማረጋገጫ ከሆኑ አቢይ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት አንዱ መሆኑ የታወቀ ነው። ሆኖም ግን ነፃ ተቋማት በሌሉበት፤ በአምባገነኖች አስፈፃሚነት የሚደረግ ምርጫ የመራጮች ነፃ ፍላጎት መግለጫ በመሆን ፋንታ የገዢዎች ሥልጣን ማረጋገጫ መሣሪያ ይሆናል፤ ከአገራችን እየሆነ ያለውም ይህ ነው።

የዘንድሮው ምርጫ 2007 ከዚህ በፊት ከነበሩ በባሰ ለአፈና የተጋለጠ የነበረ መሆኑ ከጅምሩ በግልጽ የታየ ጉዳይ ነበር። በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲዎች ላይ አገዛዙ የወሰደው የግፍ እርምጃ የዚሁ የምርጫ ዘረፋ ስትራቴጂ አካል ነበር። ከዚያ በተጨማሪም መራጮች እውነተኛ ፍላጎታቸውን በነፃነት መግለጽ እንይችሉ ዘርፈ ብዙ ጫናዎች ሲደረግባቸው ቆይቷል። የተወዳዳሪ ፓርቲዎች አባላት እንደተፎካካሪ ሳይሆን እንደጠላት ሲሳደዱ፣ ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡና ሲገደሉ ሰንብቷል። በምርጫው ሰሞንና በዕለቱ በተለይ ከተሞች በባዕድ ጦር የተወረሩ መስለው ነበር። ይህ ሁሉ ስነልቦናዊና አካላዊ ተጽዕኖ ታልፎ የተሰጠው ድምጽ ቆጣሪው ራሱ “ተወዳዳሪ ነኝ” ባዩ ህወሓት ነው።

በእንዲህ ዓይነት ምርጫ መሳተፍ ትርፉ “በሕዝብ ድምጽ ተመረጥኩ የማለትን እድል ለአምባገኑ ህወሓት መስጠት ነው”፤ “ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብም የተምታታ መልዕክት ማስተላለፍ ነው”፤ ”ለህወሓት ተጨማሪ ገንዘብ ማግኛና የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራ ማራዘሚያ ነው“ በሚል በዚህ ምርጫ ላይ ማዕቀብ እንዲደረግ አርበኞች ግንቦት 7 ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል። በርካታ ወገኖቻችን የምርጫ ካርድ ቢያወጡም የደረሰባቸውን ጫና ተቋቁመው በምርጫው ባለመሳተፍ ላሳዩት ጽናት አርበኞች ግንቦት 7 አድናቆቱን ይገልፃል።

ህወሓት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የምርጫ ጉዳይ እና የምርጫ ፓለቲካ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳን ተጨማሪ ማስረጃ ለሚፈልጉ ግንቦት 16 ቀን 2007 መጥቶላቸዋል። አሁን ከፊታችን የተደቀነው ጥያቄ የሚከተለው ነው – አገራችን ከህወሓት አፈና ነፃ ለማውጣት ያለን አማራጭ መንገድ ምንድነው?

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህወሓት ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ የሚወርደው ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽን ባቀናጀ ሁሉገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት ለሁለቱም የትግል ዘርፎች ተስማሚ የሆኑ አደረጃጀቶችን አዘጋጅቷል።

ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ታጋዩ ከመኖርያ ወይም ከሥራ ቦታው ሳይለቅ በህቡዕ የሚከናወን ትግል ነው። ሕዝባዊ አመጽ ደግሞ ከመኖሪያና ሥራ ቦታ ለቆ መንቀሳቀስን ይጠይቃል። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች የህወሓትን ህጎች በመቃወም የሚደረጉ ናቸው። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች ድርጅት፣ ዲሲሊንና ጽናትን ይጠይቃሉ። ለድላችን ሁለቱም የትግል ዘርፎች እኩል ዋጋ አላቸው። እናም ከዛሬ ጀምሮ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባለውና አቅሙ በሚመቸው የትግል ዘርፍ ይሳተፍ። ሕዝባዊ ኃይልን መቀላቀል የቻለ ይቀላቀል፤ ያልቻለው በያለበት ተደራጅቶ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ይታገል።

በየመኖሪያ ሠፈሩና በሥራ ቦታዎች የሚቋቋሙ የአርበኞች ግንቦት 7 ማኅበራት በርካታ ሥራዎች አሏቸው። ከሁሉ አስቀድሞ ድርጅትን ማጠናከር የሁላችንም ድርሻ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፤ እናም ትኩረታችን እዚያ ላይ እናድርግ። እያንዳንዳችን ከሚመስሉንና ከምናምናቸው ጋር ተነጋግረን እንደራጅ፤ ወያኔ የሸረሸረብንን በራስ መተማመን እና የእርስ በርስ መተማመንን መልሰን እንገንባ። ውስጥ ውስጡን ጠንካራ አገራዊ ኅብረት እንፍጠር፤ የዕለት ተዕለት ተግባሮቻችን ደግሞ አካባቢያዊ ይሁኑ። ድርጅታችንን እያጠናከርን ወያኔን ከሁሉም አቅጣጫ እንሸርሽረው እንገዝግዘው። በዚህ መንገድ በሚደረግ ሕዝባዊ ትግል የሚገኝ ድል ፈጣን ከመሆኑን በላይ የድሉ ሕዝባዊነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ይሆናል።

ስለሆነም እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ታጥቆ እንዲነሳ፤ ወደ ተግባራዊ ትግል ፊቱን እንዲያዞር አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

Thursday, May 21, 2015

በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የተመሰረተው ክስ ተሰማ * ‘ኤርትራን ተሻግራችሁ ግንቦት 7ን ልትቀላቀሉ ነበር’ ተብለው ተከሰዋል

•‹‹በይልቃል ጌትነት እና በዮናታን ተስፋዬ ላይ መስክር እያሉ ያሰቃዩኛል›› ብርሃኑ ተ/ያሬድ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የፌደራል አቃቤ ህግ በቀን ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ የመሰረተው ክስ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ዛሬ ግንቦት 12/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በንባብ ተሰምቷል፡፡
በብርሃኑ ተ/ያሬድ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ ላይ አራት ሰዎች የተካተቱ ሲሆን፣ እነዚህም 1ኛ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ 2ኛ እየሩሳሌም ተስፋው፣ 3ኛ ፍቅረማርያም አስማማው እና 4ኛ ደሴ ካህሳይ ናቸው፡፡ የሽብር ክስ የቀረበባቸው እነዚህ ተከሳሾች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ (አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና የጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 7(1)ን በመተላለፍ ወንጀል እንደተከሰሱ የክስ ቻርጁ ያመለክታል፡፡
በክሱ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ኤርትራ ውስጥ መቀመጫውን ባደረገውና በሽብርተኝነት በተፈረጀው ግንቦት ሰባት ስር አባል ሆነው የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ወስነው ከድርጅቱ ጋር ለመቀላቀል የኢትዮጵያንና የኤርትራን ድንበር አቋርጠው ሊሻገሩ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ በመሆናቸው በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በአባልነት መሳተፍ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
ተከሳሾቹ ክሱን ካዳመጡ በኋላ ጠበቃ ማቆምን በተመለከተ ከፍርድ ቤቱ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሁሉም ተከሳሾች፣ ‹‹ከተያዝን ጊዜ ጀምሮ በደል እየደረሰብን ነው፤ ይህ የብቀላ ስራ ነው ብለን ስለምናምን እና በዚህ ሁኔታ ተከራክረን ፍትህ እናገኛለን ብለን ስለማናምን የግልም ሆነ የመንግስት ጠበቃ አንፈልግም›› ብለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጠበቃ አለማቆም መብታቸው እንደሆነ በማውሳት ሀሳባቸውን የሚቀይሩ ከሆነ ጥያቄያቸውን ለመቀበል ዝግጁ ነው ሲል ገልጾዋል፡፡
በሌላ በኩል አንደኛ ተከሳሽ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለፍርድ ቤቱ ባሰማው አቤቱታ እንደገለጸው አሁን በሚገኝበት ቂሊንጦ ማቆያ ውስጥ በደል እየደረሰበት ይገኛል፡፡ ‹‹የተከሰስኩበት ወንጀል በክሱ ላይ የተመለከተው ሆኖ እያለ በግድ ቀድሞ እሰራበት በነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ጓደኞቼ ላይ በተለይም በፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እና በህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የግንቦት ሰባት አባል እንደሆኑ ተደርጎ መስክር እየተባልኩ ስቃይ እየደረሰብኝ ነው›› በማለት አቤቱታውን ያሰማው አቶ ብርሃኑ፣ በተጨማሪም ማንነትን መሰረት ያደረገ ስድብ እንደሚሰደብ፣ ጨለማ ቤት እንደሚታሰር እንዲሁም የተጠየቀውን ካልፈጸመ ወደማዕከላዊ ሊመልሱት እንደሚችሉ እንደሚዝቱበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ አቶ ብርሃኑ አለኝ ያለውን አቤቱታ በጽሑፍ እንዲያቀርብ በማሳሰብ፣ አቤቱታውን አይቶ የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጥ እንደሚያደርግ ገልጾዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች በክሱ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመቀበል ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41499#sthash.DMRe4EEf.dpuf

የሕወሓት አስተዳደር በጦር መኮንኖች ላይ ከግንቦት 7 ጋር ልባችሁ ኮብልሏል በሚል ክስ መሠረተ


Zehabesha News
ከግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል፤ አባላትን መልምለዋል፤ ለቡድኑ መረጃ አቀብለዋል፤ እንዲሁም ወደኤርትራ በመኮብለል የድርጅቱን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ተሰናድተው ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ በሚል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተባቸው ሰባት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ትናንት ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ።
በአዲስ አበባ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው “በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች 1ኛ መቶ አለቃ ማስረሻ ስጤ፣ 2ኛ መቶ አለቃ ብሩክ አጥናዬ፣ 3ኛ መቶ አለቃ ዳንኤል ግርማ፣ 4ኛ መቶ አለቃ ገዛኸኝ ደረሰ፣ 5ኛ ተስፋዬ እሸቴ፣ 6ኛ ሰይፉ ግርማ እና 7ኛ የሻምበል አድማው አዳሙ ናቸው። እንደክስ ዝርዝሩ ከሆነ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በቀጥታ እንዲሁም በመላ ሃሳባቸውና አድራጎታቸው በወንጀል ድርጊቱና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማን ይዘው ለማስፈፀም እና በመንግስት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር፤ ህብረተሰቡን ለማስፈራራት፤ የአገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተቋማት ለማናጋትና ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሰውና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ከተባለው የግንቦት ሰባት ድርጅት አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ለመሳተፍ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ” ይላል።
የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ትናንት በችሎት ለተገኙት ተጠርጣሪዎች ክሱ እንደደረሳቸው ተደርጎ በዝርዝር ሲነበብ፤ በተጠርጣሪዎቹ ላይ 10 ክሶች እንደቀረቡባቸው ለማወቅ ተችሏል። በተለይም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ተከሳሾች ላይ በቀረበው ክስ መሠረት ቀኑና ወሩ በትክክል ተለይቶ ባልታወቀበት በ2006 ዓ.ም ከሽብር ድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ከሆነው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ አማካኝነት በህቡዕ ተመልምለው አባላትን እንዲመለምሉም ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ይንቀሳቀስ ነበር ሲል ያትታል። በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው ከአፌዲሪ መከላከያ የአየር ኃይል ንብረት የሆኑ አንድ-አንድ ማካሮቭ ሽጉጥና 16 ጥይቶችን ይዘው በመውጣትና በመሸጥ፤ እያንዳንዱ አንዱን ማካሮቭ በ2ሺህ 500 ብር እንዲሁም እያንዳንዳቸው የያዙትን 16 ጥይቶች በ240 ብር ዋጋ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው በማዋል በፈፀሙት ወታደራዊ ትጥቅና መሣሪያዎችን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ተከሰዋል ባይነው፤ዐቃቤ ሕግ።
በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል፣ ለሽብር ድርጅቱ መረጃ በማቀበል እንዲሁም የሽብር ድርጅቱን ለመቀላቀል ወደኤርትራ ለመሄድ ሲሉ የተያዙ በመሆናቸው በፈፀሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በማናቸውም መልኩ መሳተፍ ወንጀል ተከሰዋል ሲል የክስ መዝገቡ ያትታል።
በዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ውስጥ በብቸኝነት 10ኛው ክስ የተመሰረተበት ሻንበል አድማው አዳሙ ፈፅሞታል የተባው ወንጀል ከኢፌዲሪ አየር ኃይል ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሆነ አንድ ማካሮቭ ሽጉጥ ከ8 ጥይቶች ጋር በ33 ሺህ 700 ብር መግዛቱ እንደሆነ የጠቀሰው የዐቃቤ ሕግ ክስ፤ በዚህም በፈፀመው በከባድ ሁኔታ የመሸሸግ ወንጀል ተከሷል ይላል።
ተከሳሾቹ ትናንት (ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም) ችሎት በቀረቡበት ወቅት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ሲሆን፤ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የጠቀስኳቸው የወንጀል አንቀፆች የዋስትና መብትን የሚያስከለክሉ ናቸው በሚል ለችሎቱ በማስረዳቱ ተቀባይነት አግኝቷል። በመሆኑም ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ታዟል። ነገር ግን በ7ኛ ተከሳሽ ጉዳይ ላይ ያለውን የዋስትና ጥያቄ መርምሮ ብይን ለመስጠትና ሁሉም ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን ሀሳብ ለማዳመጥ ለግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል ሲል ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል::

Tuesday, May 19, 2015

በትጥቅ ትግል ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ድርጅቶች የጥምረት ስምምነት ተፈራረሙ

በገዢው የኢህአዴግ መንግስት ላይ የትጥቅ ትግልን እያካሄዱ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወደ ጥምረት እና ውህደት የሚወስዳቸውን ውይይት መጀመራቸውን ባለፈዉ አርብ ይፋ አደረጉ ።
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፥ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ነቅናቄ፥ እና የአርበኞች ግንቦት ፯ ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ የጥምረት ብሎም የውህደት ዉይይቶችን መጀመራቸውን አስታወቁ ።
“ሀገርን እና ህዝብን ለማዳን የጋራ ግብ አድርጎ ለመስራት” በሚል መርህ የተዘጋጀውን ውይይት በማካሄድ ላይ መሆኑን ንቅናቄዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል ።
በቅርቡ በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኘው አርበኞች ግንባር፥ ከግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ጋር ውህደት ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አምስቱ ንቅናቄዎች በማካሄድ ላይ ያሉትን ውይይት አስመልክቶ ውጤቱን በቀጣይ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከድርጅቶቹ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ንቅናቄዎቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ከመቼውም ግዜ በላይ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና መከራ ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት ድርጅቶቹ፥ አንድነትን በማጠናከር ሀገርንና ህዝብን ነጻ ማውጣት የሚገባበት ወቅት አሁን ነው ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ አክለው አስታቀዋል።

Monday, May 18, 2015

ሃያአራት አመት ጊዜ ያለወጠው አዙሪት! ከአዙሪት ለመውጣት .. (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በሕወሓት የበላይነት የሚተዳደረው የኢሕአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ላለፉት ሃያአራት አመታት እጅግ ከፍተኛ ወንጀሎችን በሕዝብ
ላይ በመፈጸም ንጹሃንን በማሰር ሰርቶ አገር ሊለውጥ የሚችለውን ትውልድ በማሰደድ እምቢኝ ያሉትን በመግደል…በተከታታይ እና በተደጋጋሚ በሚፈጽማቸው አሰቃቂ ግፎች ስልጣን ላይ ለመቆየት በሚያደርገው ትንቅንቅ እጅግ ዘግናኝ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ ፈጽሟል እየፈጸመ ነው::ወንጀል መፈጸሙ ሳያንሳ የራሱን የደም እጆች በሌሎች ላይ ለማቀባባት በመሞከር ራሱን ነጻ ለማውጣት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ቢረጭም አልተሳካለትም:: እያንዳንዳችን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ቆም ብለን ልናስብበት የሚገባ እድሎችን በመተቀም ለዘላቂ መፍትሄ ራሳችንን በማዘጋጀት እንዲህ አይነቱን አምባገነን መንግስት ልናስወግድ ይገባል::እስከዛሬ በሰቀቀን እና በ እ ህ ህ ያሳለፍነው ዘመናችን ችግሩ ማነው ብለን ልናጤነው እና ችግሩን በዘላቂነት ልናስወግድ የዜግነት ግዴታችን ነው::የወያኔው ስርአት በፈጠረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ግድፈት ሕዝቦች በከፍተኛ ደረጃ በኑሮ ውድነት ከመሰቃየታቸውን አልፎ ጥቂት የባለስልጣናት እና የዘመዶቻቸው ቱጃርነት የብዙሃን ድህነት ሲንሰራፋ ሙስና የስር አቱ ዋና መገለጫ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው::የኢኮኖሚ ፖሊሲው ኑሮ ውድነትን ብቻ ሳይሆን ስራ አጥነትንም በሰፊው አንሰራፍቷል::የዚህ ስራ አጥነት የፈጠረው ችግር ትኩሱን የስራ ሃይል ወደ ሰው አገር ከመሰደዱም በላይ ከፍተኛ ብሄራዊ ውርደትን አስከትሏል:: በመላው ኢትዮጵያ መብራት፣ ውሃና ኔትወርክ የለም የለም ብቻ ሳይሆን ላለመኖሩ ሰበብ ከሚፈጥር ውጪ ችግሩን የሚፈታ መንግስት የለም::በመላው አገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ የመንግስት ሰራተኞች ተማሪዎች የግል ተቀጣሪዎች በትራንስፖርት ችግር እየተንገላቱ ነው:ለዚህም መፍትሄ የሚሆን ነገር የሚያመጣ መንግስት ስለሌለ ሕዝቡ ራሱን እያስተዳደረ መሆኑ እሙን ነው::በጉልበት የሕዝብን ስልጣት ይዞ አለቅም ያለ ፓርቲ የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠሩ ሕዝብ አቤት የሚልበት እና ችግሩን የሚፈታበት ቦታ በማጣቱ ቤቱ ተቀምጧል::በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ነጻ ሚዲያዎች በነጻነት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ግማሹ ለስደት ግማሹ ለእስር ግማሹ ለሞት ግማሹ ሰርቶ እንዳይበላ ተደርጎ በአምባገነኖች ተኮላሽቷል::ተቃውዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሁኑ የሲቭክ ማህበራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚፈለገው መልኩ በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም::ይህ ሁሉ የፈጠረው የስር አቱ ፖሊሲዎች በርካቶችን ለሞት እና እስር እንዲሁም በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን ለአደጋ በሚዳርግ መልኩ እየተሰደዱ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለቁጥር የሚታክቱ ምሬቶችና አቤቱታዎች ከየአቅጣጫው በየጊዜው ይሰማሉ፡፡ ያለው ስርአት በሃገር እና በሕዝብ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በፍጹም እንደማይፈታ የታወቀ ነው::ከመፍታት ይልቅ በሰበብ እና በሌሎች ላይ በመላከክ ስለተጠመድ የህዝብን አቤቱታ መስማት በፍጹም ፍቃደኛ ባለመሆኑ ባለፉት 24 አመታት ባለበት ዛቢያ እየዞረ ምንም ነገር ስላለወጠ ካለ አዙሪት ለመውጣት የወያኔን የሰከረ ፖለቲካዊ ስርአት በሰበብ እና በሌሎች ላይ የሚላከኩ ጉዳቸውን አሸክሞ ከኢትዮጵያ ማስወገድ ችላ ሊባል የማይገባ ወሳኝ ወቅት ላይ ስለሆንን አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ በሕዝባዊ አመጽ በአንድነት ስርአቱን ታግለን ልናስወግድ ግዴታ አለብን::

Wednesday, May 13, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 አዳዲስ ታጋዮችን አስመረቀ


አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ውህደት አድርጎ አንድ ከሆነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ አርበኛ ታጋዮችን ማስመረቁ ተሰማ:: አርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮቹን በኤርትራ ያስመረቀው ያለፈው እሁድ ግንቦት 2 ነው:: ከኤርትራ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ኤርትራ በመግባት አርበኞች ግንቦት 7ን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ:: የምርቃቱን ፎቶዎች ይመልከቱ::

Monday, May 11, 2015

“ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም” – አርበኞች ግንቦት 7

የአርበኞች ግንቦት 7 በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ጽሁፍ
የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።

አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።

ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

Thursday, May 7, 2015

የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!

የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።

አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።

ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።

ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

Wednesday, May 6, 2015

አውነቱ ይውጣ! – መስፍን ወልደ ማርያም

ሴቶችን በወንዶች ፊት፣ ወንዶችን በሴቶች ፊት ልብስ እያስወለቁ የአካላቸውን ክፍሎች ሁሉ ለማየት የሚያስችል አንቅስቃሴ አንዲሠሩ ማስገደድ በሽተኞችን ያስደስታል፤ የምርመራ ዘዴ ግን አይደለም፤ ውርደት እንዲሰማቸው ከሆነ በወራዶች ሰዎች ፊት የምን መዋረድ አለ? ወራዶች እነሱ ደረጃ ላይ ከእነሱ ጋር ያስተካክላሉ አንጂ አያዋርዱም፤ በሌላ አነጋገር ወራዶች አያዋርዱም፤ ወራዶቹ ደንቆሮዎችም ሆነው ነው እንጂ ልብስ የሚያስወልቁ እነሱ ብቻ አይደሉም፤ ሀኪሞችም ልብስ አስወልቀው፣ አጋድመው በጣታቸውም ሆነ በመሣሪያ የፈለጉትን የአካል ክፍል አንደፈለጉ ያደርጉታል፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ከሚያደርጉት የሀኪሞቹ የሚለየው ሀኪሞቹ ሰዎችን ለማዳን ሲሉ ነው፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ግን የራሳቸውን ሱስ ለማርካት፣ የራሳቸውን ህመም ለማስታገስ ነው፤ ወራዶቹንና ደንቆሮዎቹን ከመለዮአቸው አራቁቻቸዋለሁ!

ከነውር በቃላት ወደነውር በተግባር፣ ያውም በመሥሪያ ቤት! ዱሮ ዱሮ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር ፊት ለፊት የአንድ ኢጣልያዊ ቡና ቤት ነበር፤ እዚያ ውጭ ተቀምጠን ቡና ስንጠጣ አንዲት ውብ ሴት ወደጸጉር መሥሪያው ቤት ስትመጣ የሁላችንም ዓይኖች እየዘለሉ እስዋ ላይ ዐረፉ፤ ከሦስታችን አንዱ ስለሴትዮዋ የወሲብ ችሎታ በዝርዝር መናገር ሲጀምር ሁለታችን ተያየንና አፈርን፤ ጨዋታው የጣመለት መስሎት ሲቀጥል የሕግ ባለሙያ የሆነ ጓደኛዬ አቋረጠውና ‹‹ስማ! ይህን ጊዜ እናትህ በአንድ ቦታ ስታልፍ አንዱ እንዳንተ ያለ ስለስዋ ችሎታ ያወራ ይሆናል!›› አለው፤ ሊጠጣ ወደአፉ ያስጠጋውን ስኒ ቁጭ አደረገና ተነሥቶ ሄደ፡፡
ሥልጣን ተሰጥቷቸው ሴቶችን ልብስ እያስወለቁ ምርመራ ነው የሚሉ በእናቶቻቸውና በእኅቶቻቸው ላይ ሊደርስ እንደሚችል አይገነዘቡም ይሆናል፤ ደንቆሮ የሚያደርጋቸውም ይኸው ነው፤ የአንዱ እናት አንድ ቦታ ላይ ራቁትዋን ቆማ በሽተኞች ተሰብስበው ሲስቁባት፣ በሌላ ቦታ ደግሞ ጓደኛው የእሱን እናት ወይም እኅት ያንኑ እያደረገ ያስቅባት ይሆናል፤ አንተ በእኔ እናትና በእኔ አኅት አስቅባቸው፤ እኔ ደግሞ በአንተ እናትና በአንተ እኅት አስቅባቸዋለሁ፤ ይህንን እየሠራን ኑሮአችንን እናቃናለን፤ እቤታቸው ሲገቡና ከእናቶቻቸውና ከእኅቶቻቸው ጋር ሲቀመጡና ሲበሉ (?!) ሰው ይመስላሉ፤ እነዚያም ግፉ የተፈጸመባቸው እናቶችና እኅቶች ‹ነውራቸውን› ምሥጢር አድርገው ለሰው ስለማይናገሩ ግፈኞችና የግፍ ሰለባዎች አብረው ይበላሉ!
አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳንድ ሴቶች የደረሰባቸውን ተናገሩ፤ አሁን ያፍራሉ የተባሉት እውነቱን ራቁቱን አወጡትና ከእፍረት ነጻ ወጡ! እውነቱ ሲወጣ የሚያፍረው ማን ነው? ደካማዎቹና የግፍ ሰለባ የነበሩት በጭራሽ አያፍሩም፤ የሚያፍሩት ግፈኞቹ ናቸው፤ የሚያፍሩት የሕዝብን አደራ በማቆሸሻቸው፣ በሥልጣን በመባለጋቸው፣ የሕዝብንና የአገርን ክብር በማዋረዳቸው ያፍራሉ፤ ኅሊናቸው በየቀኑ ነፍሳቸውን አርባ ሲገርፋት እየሳሳች እንቅልፍ ትነሳቸዋለች፡፡
ለመሆኑ በአገሩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት — ሼሆች፣ ሽማግሌዎች በአገሩ የለንም?
መስፍን ወልደ ማርያም

Friday, May 1, 2015

ፖሊስ በ‹‹በሁከትና ብጥብጥ›› ተጠርጣሪዎች ላይ ሦስት መዝገብ አደራጅቻለሁ አለ •እነ ወይንሸት ለሁለተኛ ጊዜ 6 ቀን ተቀጥሮባቸዋል

•እነ ወይንሸት ለሁለተኛ ጊዜ 6 ቀን ተቀጥሮባቸዋል
•‹‹ወይንሸት ከአሁን በፊትም ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ስታሸብር ነበር›› ፖሊስ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስታችኋል፤ ተካፍላችኋልም›› በሚል ፖሊስ ባሰራቸው ሰዎች ላይ ሦስት የተለያዩ መዝገቦች ማደራጀቱን አስታውቋል፡፡

ዛሬ ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ሌሎች በዕለቱ የተያዙ ሰዎችን በተመለከተ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ እንደገለጸው፣ ፖሊስ የራሱን ቡድን በማዋቀር ተጠርጣሪዎችን በሦስት መዝገቦች ስር እንደየተሳትፏቸው አደራጅቻለሁ ብሏል፡፡ በዚህ መሰረት በሶስተኛው መዝገብ ላይ ያካተታቸውን በርካታ ታሳሪዎች አጣርቶ መልቀቁን የገለጸው ፖሊስ፣ በሁለተኛውና በአንደኛው መዝገብ ላይ ባሉት ተጠርጣሪዎች ግን ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጹዋል፡፡
አንደኛው መዝገብ ላይ በእነ ወይንሸት ሞላ መዝገብ 5 ሰዎች የተካተቱ ሲሆን አራቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፤ አንደኛዋ ተጠርጣሪ ደግሞ ፖሊስ የፓርቲው አባል እንደሆነች የሚገልጸው፣ እሷ ግን አባል አለመሆኗን የገለጸች መሆኗን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ስለሆነም በዚህ መዝገብ የተካተቱት ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ማስተዋል እና የፓርቲው አባል ያልሆነችው ቤተልሄም ይገኙበታል፡፡ ማስተዋል በዛሬው ዕለት ቀደም ብሎ የተሰጠው የቀጠሮ ቀን ስላልደረሰ ፍርድ ቤት አልቀረበም፡፡ ቤተልሄም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሳልሆን አባል ነሽ እየተባልኩ ምርመራ ይደረግብኛል፤ ሌሊት እየተጠራሁ እመኝ እየተባልኩ ነው›› ስትል ለፍርድ ቤቱ ገልጻለች፡፡

በሁለተኛው መዝገብ ላይ ደግሞ 15 ተጠርጣሪዎች ተካትተዋል፡፡ ፖሊስ በዚህ መዝገብ በተካተቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ክሱን ሲያሰማ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ተጠርጣሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ሲያደርጉ ‹ጠንካራ መሪ እንጂ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም›፣ ‹ወያኔ አሳረደን›፣ ‹ፍትህ የለም!››› በማለት ሁከት እንዲነሳ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡››
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በምርመራ ወቅት የገጠማቸውን አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ የሚደረግባቸው ምርመራ ከፓርቲው ጋር የተያያዘ እንጂ ከተጠረጠርንበት ጉዳይ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምርመራው ከጉዳዩ ጋር የሚገናኝ አይደለም፤ ሌሊት ሌሊት እየተጠራሁ ምርመራ ይደረግብኛል፡፡ የፓርቲ አባል መሆን ወንጀል እስኪመስለኝ በፓርቲ አባልነቴ ጫና ይደረግብኛል፡፡ በዚያ ላይ የጤና እከል ገጥሞኛል፤ ህክምና ያስፈልገኛል›› ስትል ለፍርድ ቤቱ ያስረዳችው ወይንሸት ሞላ፣ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት እንዲሰጣት ጠይቃለች፡፡
በሁለቱም መዝገብ የተካተቱት ሁሉም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ በመጀመሪያው መዝገብ ላይ ያሉት እነ ወይንሸት ላይ የምርመራ ስራውን እንዳልጨረሰ በመግለጽ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ በተለይ ወይንሸት ሞላ ላይ ፖሊስ፣ ‹‹ከአሁን በፊትም ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ተመሳስላ በመልበስ ስታሸብር ነበር›› በማለት ዋስትና እንዳይሰጥና የጠየቀው የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ በሁለተኛው መዝገብ ላሉት ደግሞ 7 ቀን ፖሊስ ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በሁለቱም መዝገብ ላይ በተመሳሳይ የ6 ቀን ጊዜ በመስጠት ለሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እስር አሁንም እንደቀጠለ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ በትናንትናው ዕለትም ሦስት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባላት (አንደኛው አሁን ላይ የሰማያዊ አባል) መታሰራቸው ይታወሳል፡፡