Thursday, June 16, 2016

ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ ና የገቢማስባስቢያ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ !

በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ቅዳሜ ጅን 4 /2016 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የአርበኞች ግንቦት7ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ እና የገቢማሰባስቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ::
በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው በብዙ መቶወች የሚጠጉ የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊወች ለድርጅቱና ለመሪያችው አጋነታቸውን ለማሳየት ከኦስሎ እና ከመላው ኖርዌይ እዲሁም ከተለያዩ አገራት ተገኝተዋል በተለይም ክስቶኮልም የመጡ የድርጅቱ አባሎች ና ደጋፊወች ለዝግጅቱ ታላርትልቅ ድምቀት ስተውታል !!
የእለቱ የክብር እንግዳ
13332845_701472519992488_1110527214712924905_n13319992_620735551427292_8106480010588466899_n
• የአርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀምበር አርበኛ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ
• ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው ከቪዥን ኢትዮጵያ
• ዶ/ር ሙሉአለም አዳም በኖርወዌይ አርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር
• ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ
የእለቱ እንግዶች በተገኙበትሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 16:15ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 00:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ የለቱን ፕሮግራም በማስተዋወቅ ለዝግጁት ታዳሚውች እንኮን ደህና መጣችሁ በማለት ለዝግጅቱ መሳካት ክተለያየ ቦታ እርቀት ሳይገድባቸው ረጅም መንገድ ተጉዘው ለተገኙ እንግዶቻችን በድርጅታቸው ስምና ታላቅ ምስጋ ና አክብሮት ክአቀረቡ ቡሀላ የለቱ ፕሮገራም የመክፈቻ ንግግር በማድረገ አስጀምረዋል አያይዘውም በኢትዮጵያ ውስጥ በመላ የሀገራችን ህዝቦች በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ እንዲሁም አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ ፕሮግራሙን እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኃላ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከተለያዩ ሐገሮች ለመጡት አባላት እና ደጋፊዎች ያላቸውን አክብሮት እና ምስጋና አቅርበዋል። በእለቱ ለተገኙት የክብር እንግዶችም እጅግ ጠቃሚ እና ትምሕርት አዘል ንግሮችን አድርገው እንዳለቀ ዶ/ር ሙሉ አለም አዳም ፕሮግራሙን መሪ መድረኩ አስጀምረውታል።
በዝግጅቱም ላይ በእንግድነት ከተጋበዙት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ከኤርትራ በረሃ፣ ፕሮፈሰር ጌታቸው በጋሻው በተጨማሪም የኢሳት ጋዜጠኞች ገሊላ መኮንን አምስተርዳም እና መታሰቢያ ቀፀላ ለንደን እንግድነት ተገኝተዋል። በዚህም ዝግጅት ፕሮፈሰር ጌታቸው ስለ ኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ ትንተና በሰፊው ገልፀዋል።
ፕሮግራሙን በሰፊው ሲጠበቅ የነበረው የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ንግግር በመቀጠል በአገሩቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ትግል ሰፊ እና ጥልቅ ማብራሪያ አቅርበው በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኞች አስከፊው ስደትና መከራ በወያኔ መንግስት በመሸሽ እያደረሰባቸው ባለው ስቃይ ለዚ አስከፊ ስደት የዳረጉን የወያኔን የግፍ አገዛዝ ጫፍ መድረሱንም ጭምር ያሳየ ምልክት ነው በድርጊታቸውም በቃ ልንላቸው ይገባል ትግሉን መደገፍ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።
በቀጣዮም ፕሮግራም ታዳሚው ያልተጠበቀው ለተሳታፊውም በዓነቱ እንግዳ የሆነ ነገር በመከሰቱ ህዝቡን ያስደሰተ ክስተት ተከሰተ። በዝግጅቱም ላይ ከተሳታፊዎች ፊታቸውን በከፊል በመሸፈን ዝግጅቱን ሲከታትርሉ የነበሩት ግለሰብ ማንነታቸው በመድረክ ላይ በመወጣት ተሳታፊ ያስደመመ ያስደተና የአንድነት መንፈስን የበለጠ ያጠናከረ ክስተት በአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ ያልተጠበቁ እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል ። ወ/ሮ ብዙነሽ ጽጌ ግጥም በማቅረብ ተሳታፊው በእንባ ፥ በቁጭት ስሜት ያንገበበ መልዕክት ያለው ግጥም አስተልፈዋል። የተወሰን ደቂቃ የምሳና ሻይ እረፍት በማድረግ በቀጥታ ወደ ልዩ ታሪካዊ የጨረታ ዝግጅት ነበር የታለፈው በጨረታውና የገቢ ማሰባሰቢያ የቀረበው ፎቶ የታጋይ አርበኛ ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ፣ አርበኛ ታጋይ መዓዛ ፅጌ እና አንዳርጋቸው ፅጌ በ አንድ ላይ ያጠቃለለ ነበር። ለጨረታው ቀርቦ የነበረው ከፍተኛ ዋጋ በ ወ/ሮ ብዙ አየሁ ፅጌ አሸንፈዋል። በጨረታውም ያሸነፉትን የሶስቱ ታጋይ አርበኞች ፎቶ መልሰው ለአዘጋጁ አስረክበዋል አዘጋጁም ከረጅም ርቀት ተጉዘው ከስዊድን አገር ለመጡ አገር ወዳድ አርበኞች አስረክበዋል። በፕሮግራሙ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያዊነት ነግሶ የታየበት ነበር ። በቀሪ ልዩ ዕጣ የወጣላቸው በልዮ ስሙ ኦታ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የትግሉ አጋር በዕጣው የወጣላቸውን የኮምፒተር ዕጣ ለ አርበኞች ግንቦት 7 አባልት እና ደጋፊ ለትግሉ ይጠቅማል በማለት በስጦታ መልክ ለግሰዋል። ሌላም ሌላም ስጦታዎች የተካተቱበት እና ለትግል ሜዳ ለተሰማሩት አጋር ጋዶች የሚሆን በ አንድ ግለሰብ 1000 ቲሸርት በስጦታ ተለግሰዋል። በማጠቃለያውም በ ኖርዌዳን ክሮነር 800,162 /ስምንት መቶ ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሳንትም/ ተሰብስቦዋል ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀ ሁኔታ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የተሰማውን ትልቅ አድናቆት በምስጋና ሲገልጽ በተለይ ከስዊድን እንዲሁም ከሰሜንና ከተለያየ የአውሮፓ ክፍል የመጣችሁ፣ ከበርገን፣ ከትሮንድሃየም፣ ከክርስትያንሳንድ፣ ስታቫንገር እንዲሁም ከተለያየ የኖርዌይ ቦታ የመጣችሁ፣ በማያያዝም የከረንት አፌር ፓል ቶክ ሩም እንዲሁም ኢካዴፍ ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና ስናቀርብ በማያያዝ የፍጻሜ የትግሉ ለሚጠይቀው መስዋእትነት ከአፍ ባለፈ በተግባር ስላሳያችሁት አጋርነት የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፣ በተለይ የዘረኛው የጥጵልፍ አቃጣሪ ቡችሎች ፕሮጋራማችንን ለማስተጓጎን ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ከነሱ ውስጥ በመሆን እንቅስቃሴያቸውም ስታቀብሉን ለነበር የውስጥ አርበኞች ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና እናቀርባለን፣
በስተመጨረሻ ከአገር ቤት በመደወል የገንዘብ ድጋፍ ላደረጋችሁንም ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!! – መግለጫ

በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።

የህወሃት ዘረኝነት በፈጠረው ኢፍትሃዊነትና አፈና የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞውን እያጠናከረ ባለበት በዚህን ሰዓት በሙስና የተጨማለቁ የህወሃት የጦር ጀነራሎችና በሲቪል ማዕረግ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሃይሎች ለምን ይህንን ጦርነት መጫር እንደፈለጉ ግልጽ ነው። በኦሮሚያ የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማፈን ከ400 በላይ ሕዝብ መጨፍጨፉና በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት መታጎራቸው የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም እንደ አንድ መሣሪያ ሆኖ ላለፉት 25 አመታት ሲያገለግል በኖረው ኦህዲድ ውስጥ እንኳን ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ ካድሬ ያሉትን አስኮርፎአል። የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ ሌላኛው የህወሃት አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥ የማያባራ ክፍፍል ፈጥሮአል። የነጻነት ታጋዮች በቅርቡ አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ የፈጸሙት የጀግንነት ገድል የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያንቃቃና ለትግል የሚያነሳሳ አርአያነት እንደፈጠረ የህወሃት አገዛዝ ተረድቶአል። በቤኔሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአፋርና በሱማሌ ከመሬት ንጥቂያ ጋር በተያያዘ ወንጀል ህወሃት ከህዝቡ ጋር አይጥና ድመት ድብብቆሽ ውስጥ ከገባ አመታትን አስቆጥሮአል። በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ቀድሞውኑም የድጋፍ መሠረት እንደሌለው ማወቁ ብቻ ሳይሆን ይኩራራበት የነበረው የትግራይ ምሽግነትም ከእጁ ሙሉ በሙሉ እያፈተለከ መምጣቱን ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት ፊቱን ወደሰሜን በማዞር የሕዝቡን ትኩረት አስታለሁ ብሎ ወያኔ አምኖአል። አባይ ጸሃይዬና ሳሞራ ዩኑስ መቀሌ ላይ በቅርቡ ባደረጉት የህወሃት ስብሰባ ላይ “ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ አይኖርም፤ ኢህአደግ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም” ማለታቸው ኤርትራን በመውረር በተለይም የትግራይን ህዝብ ድጋፍ መልሶ ያስገኛል የሚል እምነት በአገዛዙ መሪዎች ውስጥ መፈጠሩን ያመለክታል።

ሌላው ህወሃትን ወደ ጦር አጫሪነት እየነዳው ያለው እብደት መለስ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ ድርጅቱ ውስጥ የነገሰው የእርስ በርስ የሥልጣን ሹኩቻ የፈጠረው ውጥረት እንደሆነ መገመት አያዳግትም። አንዱን ውጥረት ለማርገብ ሌላ የውጥረት ግንባር በመክፈት ለሚታወቀው ህወሃት ይህ የተለመደ ስትራቴጂ ነው።

አርበኞች ግንቦት7 ህወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትኩረት ለመቀየር የሚያደርገው ማንኛውም አይነት ጥረት እንዳይሳካለትና የጀመረው ይህ የትኩረት ማስቀየሻ ስትራቴጂ የህወሃትን ውድቀት አፍጣኝ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ካሁን ቀደም ለአገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የሚሰጠው ፋይዳ ሳይመከርበትና ሕዝባዊ ስምምነት ሳይኖር ከአሥራ አንድ አመት በፊት ሱማሌ ውስጥ ዘፍ ተብሎ የተገባበት ጦርነት በየቀኑ የስንት ወንድሞቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ እያየነው ነው። ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ሰሞኑ በሽብርተኛው አልሸባብ ሲጨፈጨፉ የወያኔ መሪዎች አንዲትም ወፍ የሞተቺባቸው ያህል እንኳ አልተሰማቸውም ። ይህንን ሁሉም ያገራችን ህዝብ ያውቃል። እስከዛሬ በሰላም አስከባሪነት ስም ወደ ሰው አገር እየተላኩ ደመ ከልብ እየሆኑ ያሉ ወገኖቻችን ህይወት እያንገበገበን ባለበት በዚህን ሰዓት ለወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ እንደ አገር የምንዋጋው ሌላ ጦርነት እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። በ1998ቱ የባድሜ ጦርነት ወቅት ህዝባችን የከፈለው ዋጋና ከባድሜ ጦርነት መልስ ጉልበቱን አጠናክሮ ለመውጣት ዕድል ያገኘው የህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ እስከዛሬ እየፈጸመው ያለው አፈናና ጭፍጨፋ ተረስቶ ሌላ ዕድል ለመስጠት ዳግም መሳሪያ የምንሆንበት ምክንያት የለም።

አርበኞች ግንቦት 7 ከአሁን ቦኋላ ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘምና የተዘፈቀበትን የሃብት ዘረፋ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያደርገውን የሞት ሽረት ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም አይነት ሁኔታ ማስተናገድ የለበትም ብሎ ያምናል። በዚህም ምክንያት በመላው አገራችን የተጀመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ከግቡ እንዲደርስ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ትግሉን ለማጠናከር እንዲረባረብ አርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል ። በመካሄድ ላይ ያለውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ወያኔ የሚያደርገውን የጦርነት እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የነጻነት ቀናችንን እንድናፋጥን ሁላችንም እንነሳ ።

አርበኞች ግንቦት 7 ወያኔ በሰሜን በኩል የጀመረውን ትንኮሳ እየተከታተለ ለህዝባችን ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

አርበኞች ግንቦት 7