የኢትዮጵያ መንግስት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል። በተለያዩ የውጭ ሃገራት ወያኔን በከፍተኛ ደረጃ በመቃወም ወደ አደባባይ የሚወጡትን ኢትዮጵያውን ማሰርና ማፈን ቢያቅተው በኢትዮጵያ የሚኖሩትን ቤተሰቦቻቸውን ማሰር እንደጀመረ የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch)በ 27 ጥቅምት 2009ዓም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በአውስትራሊያ ሜልቦርን በሰኔ 2008ዓም የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርና የዚህ ክልል ተወካይ ያካተተ ቡድን ወደ አውስትራሊያ ሊያደርገውን ያቀደውን የስራ ጉብኝት በመቃወም ኢትዮጵያውያን በሜልቦርን አደባባይ ለሰልፍ ወጥተው ነበር። በዚህ ከፍተኛ ተቋውሞ ምክንያት ይህ የስራ ጉብኝት ተስተጋጉላል። በዚህ ሰልፍ ላይ የተገኙ የወያኔ ቅጥረኞች ፎቶ በማንሳት ለወያኔ በማቀበል የእነዚህን ኢትዮጵያውያንን ቤተሰቦች ለእስር እንዲዳረጉ አድርገዋል።
ቪኦኤ በዜናው ሽፋኑ የሰብአዊ የመብት ድርጅቱ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በአውስትራሊያ በሰኔ ወር ሠላማዊ ሠልፍ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊ በዕድሜ የገፉ ወላጅ እናት እንደሚገኙበትም ታውቋል።
የዚህ ግለሰብ ሶስት ወንድሞችም የደረሱበት መጥፋቱን የመብት ድርጅቱ ዘግቧል።
የ25 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሹክሪ ሻሃፌ ጉሌድ ተወልደው ያደጉት በሶማሊያ ክልል ሲሆን በአውስትራሊያ ለአለፉት ስድሥት ዓመታት ኖረዋል፤ በአለፈው ሰኔ ወር ሜልበርን አውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐሙድ ኡማር በቅፅል ስማቸው አብዲ ኢሌ ተብለው የሚታወቁት በጎበኙበት ወቅት ተቃውሞ መግለፃቸውን ይናገራሉ፡፡
የወያኔን አገዛዝና ወያኔን በመቃወም ከአውስትራሊያ በተጨማሪ በአውሮፓ በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ከፍተኝ ሰልፎች በማድረግ ድምጹን በነጻነት በኢትዮጵያ ውስጥ ማሰማት ላልቻለው ጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ አንደበት በመሆን ይገኛሉ።
No comments:
Post a Comment