የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የኢህአዴግን ስርአት በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላለቀሉን ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የ L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ እንደነበር መረጃው ያመለክታል።
ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ “ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ ያለምንም ወንጀል ለአምስት ወር ያህል ታስሮ እንደነበርና ከእስር እንደተለቀቀም በደህንነት አባሎች አማካኝነት በአይነ ቁራኛ ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ ፣ እንደገና ለ23 ቀናት በደብረዘይት እስር ቤት መታሰሩን፣ገልጿል፡፡ የአየር ሃይል ባልደረባው በዚህ መሃል ከእስር ቤት አምልጦ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላቀሉን” የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የአየር ሃይሉ ባልደረባ መኮብለሉን በተለመለከተ መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።
ግንባሩ በላከው ሌላ ዜና ደግሞ በሁመራ አካባቢ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ናችሁ በማለት ታስረው በነበሩ 10 ሰዎች ላይ ከ6 ዓመት እስከ 25 ዓመት እንደተፈረደባቸውና ወደ መቀሌና ሽሬ እስር ቤት እንደተወሰዱ ገልጿል።
አርበኞች ግንባር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ወታደራዊ ጥቃቶችን በመፈጸም ላይ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment