Thursday, November 10, 2016

የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ሀገር ሠላማዊ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ሠዎችን ቤተሠቦች አስሯል ሲል የመብት ድርጅቱ ሒውማን ራይትስ ወች አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል። በተለያዩ የውጭ ሃገራት ወያኔን በከፍተኛ ደረጃ በመቃወም ወደ አደባባይ የሚወጡትን ኢትዮጵያውን ማሰርና ማፈን ቢያቅተው በኢትዮጵያ የሚኖሩትን ቤተሰቦቻቸውን ማሰር እንደጀመረ የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch)በ 27 ጥቅምት 2009ዓም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በአውስትራሊያ ሜልቦርን በሰኔ 2008ዓም የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርና የዚህ ክልል ተወካይ ያካተተ ቡድን ወደ አውስትራሊያ ሊያደርገውን ያቀደውን የስራ ጉብኝት በመቃወም ኢትዮጵያውያን በሜልቦርን አደባባይ ለሰልፍ ወጥተው ነበር። በዚህ ከፍተኛ ተቋውሞ ምክንያት ይህ የስራ ጉብኝት ተስተጋጉላል። በዚህ ሰልፍ ላይ የተገኙ የወያኔ ቅጥረኞች ፎቶ በማንሳት ለወያኔ በማቀበል የእነዚህን ኢትዮጵያውያንን ቤተሰቦች ለእስር እንዲዳረጉ አድርገዋል።

ቪኦኤ በዜናው ሽፋኑ የሰብአዊ የመብት ድርጅቱ  ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው  በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በአውስትራሊያ በሰኔ ወር ሠላማዊ ሠልፍ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊ በዕድሜ የገፉ ወላጅ እናት እንደሚገኙበትም ታውቋል።

የዚህ ግለሰብ ሶስት ወንድሞችም የደረሱበት መጥፋቱን የመብት ድርጅቱ ዘግቧል።

የ25 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሹክሪ ሻሃፌ ጉሌድ ተወልደው ያደጉት በሶማሊያ ክልል ሲሆን በአውስትራሊያ ለአለፉት ስድሥት ዓመታት ኖረዋል፤ በአለፈው ሰኔ ወር ሜልበርን አውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐሙድ ኡማር በቅፅል ስማቸው አብዲ ኢሌ ተብለው የሚታወቁት በጎበኙበት ወቅት ተቃውሞ መግለፃቸውን ይናገራሉ፡፡

የወያኔን አገዛዝና ወያኔን በመቃወም ከአውስትራሊያ በተጨማሪ በአውሮፓ በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ከፍተኝ ሰልፎች በማድረግ ድምጹን በነጻነት በኢትዮጵያ ውስጥ ማሰማት ላልቻለው ጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ አንደበት በመሆን ይገኛሉ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመረቀ

የኢትዮጵያን ህዝብ ከጭቆናና የስቃይ ህይወት ለማላቀቅ እና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ገርስሶ ለመጣል የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ለወራት ያክል በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ተጓዳኝ ትምህርቶች ዙሪያ ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ምልምል አርበኛ ታጋዮች እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል ፡፡

በዚህም የምረቃ ስነ-ስርዓት በዓል ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ግዳጅና ሃላፊነት ስለሚጠብቀን በምትመደቡበት ቦታ ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ሃገራዊና ድርጅታዊ ግዴታችሁን ለመወጣት በወታደራዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ሰራዊት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ለተቀደሰ አላማ መከፈል ያለበትን የህይወት መሰዋዕትነት ለመክፈልና የኢትዮጵያን ህዝብ ከባርነት ህይወትና ከጭቆና ለማላቀቅ በሚደረገው የትጥቅ ትግል የበኩላችሁን ድርሻ መወጣት ይጠበቅባችኋል በማለትና አጠቃላይ የስልጠናውን ሂደት የሚመለከት ሪፖርታቸውን አሰምተዋል፡፡

በዚህ የምረቃ በዓል ላይ ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእጅ በእጅ ውጊያን ጨምሮ የተለያዩ ትርኢቶችን በማሳየት ለበዓሉ ድምቀት ሰተውት የነበረ ሲሆን በተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የቀረቡ ስነ-ፅሁፎችና መነባንቦች እንዲሁም አዝናኝና ትምህርት ሰጪ ድራማዎችም ልዩ ትኩረት የሳቡ እንደነበርና በቦታው የተገኙትንም ተጋባዥ እንግዶች አስደምመውት ውለዋል፡፡

Friday, November 4, 2016

በህዝባችን የነጻነት ተጋድሎ እየኮራን ለመጨረሻው ድል ታጥቀን እንነሳ!

በኦሮምያ እና በአማራ የተለያዩ ከተሞች የሚካሄደው የነጻነት ትግል በእጅጉ አስደማሚ ነው። ባለፉት ሳምንታት በጎንደርና በባህርዳር ለስድስት ቀናት እንዲሁም በተለያዩ የሰሜን ጎንደርና የምዕራብ ጎጃም ከተሞች የተደረገው የስራ ማቆም አድማ በአገራችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያልታየ ወደር የለሽ ተግባር ነው። ህዝቡ የስራ ማቆም አድማ ያደረገው የሚበላውና የሚጠጣው ተርፎት እንዳልሆነ ይታወቃል። እንዲያውም በአገሪቱ የሰፈነው አስከፊ ድህነትና የኑሮ ውድነት እንኳንስ ስራ ተፈትቶ፣ 24 ሰአታት ቢሰራም የሚቋቋሙት እንዳልሆነ እናውቃለን። ነገር ግን ህዝቡ፣ ረሃቡንና ጥማቱን ለሳምንታት ችሎ የአድማውን ጥሪ ተግባራዊ አድርጓል። ይህ ምን ይነግረናል?  በቅድሚያ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳልነው ህዝቡ በዚህ ዘረኛና አፋኝ አገዛዝ መንገሽገሹን ያሳየበት ነው፤ “ልማቱ ተስፋፍቷል፣ ህዝቡም የደስታና የምቾች ኑሮ መኖር ጀምሯል” እያሉ በድህነቱና በብሶቱ ሲሳለቁበት ለቆዩት እውነተኛ ኑሮውን አሳይቷቸዋል። ይህንኑ ፕሮፓጋንዳ አምነው በመቀበል ወሬውን ሲያራግቡ ለነበሩ የአገር ውስጥና የውጭ የአገዛዙ ጠበቃዎች ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል ።
እንዲሁም አገዛዙን ለማስወገድ ህዝቡ ማንኛውንም አይነት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያሳየበት ነው። ረሃብና ጥማቱን ችሎ ከውስጡ የተጣበቀውን አለቅት ለማስወገድ መወሰኑን አሳይቷል። “ሩጥ ስንለው የሚሮጥ፣ ተቀመጥ ስንለው የሚቀመጥ ህዝብ ፈጥረናል” በማለት ሲሳለቁበት በነበረቡት ገዢዎች ላይ እየጠራ ተሳልቆባቸዋል። ከእንግዲህም እሱ በፈለገው እንጅ እነሱ በፈለጉት መንገድ እንደማይገዛላቸው ነግሯቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ አድማው ከፍተኛ የህይወት መስዋትነት ሳያስከፍል በሌሎችም አካባቢዎች ሊተገበር የሚችል መሆኑን አሳይቷል። ህዝብ ቆርጦ ከወሰነ ምንም ነገር ለማድረግ የማይሳነው መሆኑንም እንዲሁ መስክረናል። ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ህዝቡ ባደረገው ጠንካራ የስራ ማቆም አድማ የተሰማውን ኩራት ለመግለጽ ቃላት ያጥረዋል።
የህዝባቸውን ብሶት ብሶታቸው አድርገው፣ ህዝባቸውን በተሻለ ጎዳና ለመምራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ያላቸው መምህራንም የትግሉ መሪ መሆን በመጀመራቸው በእጅጉ ኮርተናል። የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ካድሬዎችን እያሳፈሩ የሸኙበት መንገድ አኩሪና በሁሉም ቦታ ሊተገበር የሚገባው ምርጥ የትግል ስልት ነው።  ምሁራን ለዲሞክራሲ፣ ፍትሃና ነጻነት የሚደረገውን ትግል በመምራት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳላቸው ድርጅታችን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ምሁራን ትግሉ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ  እንዲመራ እንደሚራ ብቻ ሳይሆን ከነጻነት በሁዋላ ለሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ስርዓት ዋስትና በመሆናቸው የጀመሩትን ትግል እስከመጨረሻው መርተው ዳር ያደርሱታል ብለን እናምናለን። በተለያዩ ምክንያቶች ትግሉን ያልተቀላቀላችሁ ምሁራን በፍጥነት ትግሉን ተቀላቅላችሁ ህዝባችሁን በመምራት አካባቢያችሁን ነጻ እንድታወጡ በድጋሜ ጥሪ እናቀርባለን።
ለህዝባዊ ጥሪው ፈጣን ምላሽ የሰጣችሁ ነጋዴዎች፣ የባጃጅና ታክሲ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች፣ ድርጅታችን እየከፈላችሁ ላለው ወደር የለሽ መስዋትነት ከፍተኛ አክብሮት አለው።  ግብር ባለመክፈል እንዲሁም የተለያዩ የትግል ስልቶችን እንደያካባቢያችሁ ሁኔታ በመጠቀም ትግላችሁን ከቀጠላችሁ፣ አገዛዙ እናንተን ለመግደል ለተሰለፉት ጥቂት የአገዛዙ ወታደሮች፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት የሚከፍለው ገንዘብ ስለማያገኝ  በመጨረሻ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል። አሁንም ትግሉን ዳር የማድረስ ታሪካዊ አደራ ተጥሎባችሁዋል እና ትግላችሁን ቀጥሎ እንላለን።
ከንቱ ለሆነ አላማ የህዝባችሁ መጨፍጨፍ እረፍት ነስቷችሁ የጠመንጃችሁን አፈሙዝ በአፋኙ አገዛዝ ላይ ያዞራችሁ ፣  መሳሪያችሁን አስረክባችሁ ከህዝባችሁ ጋር የተቀላቀላችሁ ወይም በውስጥ ሆናችሁ በተለያዩ መንገዶች ለምትታገሉ የስራዊቱ አባላትም እንዲሁ ከፍ ያለ አክብሮታችን ይድረሳችሁ።  ከህዝቡ ጎን ለመቆም ያልወሰናችሁ ዛሬውኑ ወስናችሁ ከነጻነት ትግሉ ጎን ተሰለፉ። ለህዝብ ያልሆነ አገዛዝ ለእናንተ ሊሆን አይችልም። እናንተ ምን አይነት ህይወት እንደምትገፉ እናውቃለንና ከዚህ የስቃይ ህይወት ለመውጣት ብቸኛው መንገድ የስቃዮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን የወያኔን አገዛዝ ማስወገድ በመሆኑ ጥሪያችንን እንደሰማችሁ የነጻነት ሃይሎችን ለመቀላቀል ወስኑ።
አርበኞች ግንቦት 7 እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም ባለው አቅም ሁሉ ህዝባዊ ትግሉን እየደገፈ ይገኛል። የመጨረሻው የነጻነት ደወል እሰከሚደወል ድረስም ትግሉን ከህዝቡ ጋር ሆኖ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ!!

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
ባሳለፍነው እሁድ ኦክቶበር 30 2016 ምስረታውን በመሪዎቹ የፊርማ ስነ-ስርአት ይፋ ያደረገውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ኖቨንበር 4 2016 በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ናሽናል ፕሬስ ክለብ በንቅናቄው አላማና ራእይ ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ንቅናቄው ባዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ፡ዶ/ር ዲማ ነገዎ፡ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ፡ አቶ ሙሉነህ እዩዔልና አቶ በቀለ ወያ እንደሚገኙና ማብራርያ እንደሚሰጡ ሲታወቅ በታዛቢነትም አቶ ሀ/ገብርኤል አያሌው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በተጨማሪ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ የሆነችው ጋዜጠኛና አክትቪስት እሪዮት አለሙ እንደምትገኝ ሲታወቅ ይህ በናሽናል ፕሬስ ክለብ የሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ አርብ ኖቨንበር 4 ከቀኑ 12፡15pm እስከ 2፡30pm ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሀገር ሉአላዊነት ማስከበር፡ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ማረጋገጥና እድገትና ብልፅግናን በማምጣት የፌደራል ስርአት መገንባት በሚሉ ሶስት ዋና ዋና አላማዎች የያዘውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ በወያኔ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ግድያ፤ እሰርና ወከባ አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን የታወጀውም ህገ-ወጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለወራት ሀገሪቱን ሲንጥ የቆየውን ህዝባዊ እንቢተኝነት በሀይል ለመጨፍለቅ ታስቦ የታወጀ መሆኑንና ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ላይ ዘላቂ መረጋጋትን ሊያመጣ እንደማይችል አስታውቆ  ለአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት በሀገራችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ለዚህ የወያኔ የሽብር አገዛዝ  ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ  ከንቅናቄው ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማድረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Saturday, September 3, 2016

Once a Bucknell Professor, Now the Commander of an Ethiopian Rebel Army Why Berhanu Nega traded a tenured position for the chance to lead a revolutionary force against an oppressive regime. BY JOSHUA HAMMERAUG. 31, 2016

Berhanu Nega was once one of Bucknell University’s most popular professors. An Ethiopian exile with a Ph.D. from the New School for Social Research in Manhattan, he taught one of the economics department’s most sought-after electives, African Economic Development. When he wasn’t leading seminars or puttering around his comfortable home in a wooded neighborhood five minutes from the Bucknell campus in rural Lewisburg, Pa., Nega traveled abroad for academic conferences and lectured on human rights at the European Parliament in Brussels. “He was very much concerned with the relationship between democracy and development,” says John Rickard, an English professor who became one of his close friends. “He argued that you cannot have viable economic development without democratization, and vice versa.” A gregarious and active figure on campus, he rooted for the Philadelphia Eagles and the Cleveland Cavaliers, campaigned door-to-door for Barack Obama in 2008 and was known as one of the best squash players on the Bucknell faculty. He and his wife, an Ethiopian-born optometrist, raised two sons and sent them to top-ranked colleges, the University of Pennsylvania and Carnegie Mellon. On weekends he sometimes hosted dinners for other Bucknell professors and their families, regaling them with stories about Abyssinian culture and history over Ethiopian food he would prepare himself; he imported the spices from Addis Ababa and made the injera, a spongy sourdough bread made of teff flour, by hand.

Once a Bucknell Professor, Now the Commander of an Ethiopian Rebel Army Why Berhanu Nega traded a tenured position for the chance to lead a revolutionary force against an oppressive regime. BY JOSHUA HAMMERAUG. 31, 2016

Berhanu Nega was once one of Bucknell University’s most popular professors. An Ethiopian exile with a Ph.D. from the New School for Social Research in Manhattan, he taught one of the economics department’s most sought-after electives, African Economic Development. When he wasn’t leading seminars or puttering around his comfortable home in a wooded neighborhood five minutes from the Bucknell campus in rural Lewisburg, Pa., Nega traveled abroad for academic conferences and lectured on human rights at the European Parliament in Brussels. “He was very much concerned with the relationship between democracy and development,” says John Rickard, an English professor who became one of his close friends. “He argued that you cannot have viable economic development without democratization, and vice versa.” A gregarious and active figure on campus, he rooted for the Philadelphia Eagles and the Cleveland Cavaliers, campaigned door-to-door for Barack Obama in 2008 and was known as one of the best squash players on the Bucknell faculty. He and his wife, an Ethiopian-born optometrist, raised two sons and sent them to top-ranked colleges, the University of Pennsylvania and Carnegie Mellon. On weekends he sometimes hosted dinners for other Bucknell professors and their families, regaling them with stories about Abyssinian culture and history over Ethiopian food he would prepare himself; he imported the spices from Addis Ababa and made the injera, a spongy sourdough bread made of teff flour, by hand.

Once a Bucknell Professor, Now the Commander of an Ethiopian Rebel Army Why Berhanu Nega traded a tenured position for the chance to lead a revolutionary force against an oppressive regime. BY JOSHUA HAMMERAUG. 31, 2016

Berhanu Nega was once one of Bucknell University’s most popular professors. An Ethiopian exile with a Ph.D. from the New School for Social Research in Manhattan, he taught one of the economics department’s most sought-after electives, African Economic Development. When he wasn’t leading seminars or puttering around his comfortable home in a wooded neighborhood five minutes from the Bucknell campus in rural Lewisburg, Pa., Nega traveled abroad for academic conferences and lectured on human rights at the European Parliament in Brussels. “He was very much concerned with the relationship between democracy and development,” says John Rickard, an English professor who became one of his close friends. “He argued that you cannot have viable economic development without democratization, and vice versa.” A gregarious and active figure on campus, he rooted for the Philadelphia Eagles and the Cleveland Cavaliers, campaigned door-to-door for Barack Obama in 2008 and was known as one of the best squash players on the Bucknell faculty. He and his wife, an Ethiopian-born optometrist, raised two sons and sent them to top-ranked colleges, the University of Pennsylvania and Carnegie Mellon. On weekends he sometimes hosted dinners for other Bucknell professors and their families, regaling them with stories about Abyssinian culture and history over Ethiopian food he would prepare himself; he imported the spices from Addis Ababa and made the injera, a spongy sourdough bread made of teff flour, by hand.

Once a Bucknell Professor, Now the Commander of an Ethiopian Rebel Army Why Berhanu Nega traded a tenured position for the chance to lead a revolutionary force against an oppressive regime. BY JOSHUA HAMMERAUG. 31, 2016

Berhanu Nega was once one of Bucknell University’s most popular professors. An Ethiopian exile with a Ph.D. from the New School for Social Research in Manhattan, he taught one of the economics department’s most sought-after electives, African Economic Development. When he wasn’t leading seminars or puttering around his comfortable home in a wooded neighborhood five minutes from the Bucknell campus in rural Lewisburg, Pa., Nega traveled abroad for academic conferences and lectured on human rights at the European Parliament in Brussels. “He was very much concerned with the relationship between democracy and development,” says John Rickard, an English professor who became one of his close friends. “He argued that you cannot have viable economic development without democratization, and vice versa.” A gregarious and active figure on campus, he rooted for the Philadelphia Eagles and the Cleveland Cavaliers, campaigned door-to-door for Barack Obama in 2008 and was known as one of the best squash players on the Bucknell faculty. He and his wife, an Ethiopian-born optometrist, raised two sons and sent them to top-ranked colleges, the University of Pennsylvania and Carnegie Mellon. On weekends he sometimes hosted dinners for other Bucknell professors and their families, regaling them with stories about Abyssinian culture and history over Ethiopian food he would prepare himself; he imported the spices from Addis Ababa and made the injera, a spongy sourdough bread made of teff flour, by hand.

Thursday, June 16, 2016

ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ ና የገቢማስባስቢያ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ !

በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ቅዳሜ ጅን 4 /2016 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የአርበኞች ግንቦት7ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ እና የገቢማሰባስቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ::
በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው በብዙ መቶወች የሚጠጉ የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊወች ለድርጅቱና ለመሪያችው አጋነታቸውን ለማሳየት ከኦስሎ እና ከመላው ኖርዌይ እዲሁም ከተለያዩ አገራት ተገኝተዋል በተለይም ክስቶኮልም የመጡ የድርጅቱ አባሎች ና ደጋፊወች ለዝግጅቱ ታላርትልቅ ድምቀት ስተውታል !!
የእለቱ የክብር እንግዳ
13332845_701472519992488_1110527214712924905_n13319992_620735551427292_8106480010588466899_n
• የአርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀምበር አርበኛ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ
• ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው ከቪዥን ኢትዮጵያ
• ዶ/ር ሙሉአለም አዳም በኖርወዌይ አርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር
• ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ
የእለቱ እንግዶች በተገኙበትሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 16:15ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 00:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ የለቱን ፕሮግራም በማስተዋወቅ ለዝግጁት ታዳሚውች እንኮን ደህና መጣችሁ በማለት ለዝግጅቱ መሳካት ክተለያየ ቦታ እርቀት ሳይገድባቸው ረጅም መንገድ ተጉዘው ለተገኙ እንግዶቻችን በድርጅታቸው ስምና ታላቅ ምስጋ ና አክብሮት ክአቀረቡ ቡሀላ የለቱ ፕሮገራም የመክፈቻ ንግግር በማድረገ አስጀምረዋል አያይዘውም በኢትዮጵያ ውስጥ በመላ የሀገራችን ህዝቦች በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ እንዲሁም አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ ፕሮግራሙን እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኃላ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከተለያዩ ሐገሮች ለመጡት አባላት እና ደጋፊዎች ያላቸውን አክብሮት እና ምስጋና አቅርበዋል። በእለቱ ለተገኙት የክብር እንግዶችም እጅግ ጠቃሚ እና ትምሕርት አዘል ንግሮችን አድርገው እንዳለቀ ዶ/ር ሙሉ አለም አዳም ፕሮግራሙን መሪ መድረኩ አስጀምረውታል።
በዝግጅቱም ላይ በእንግድነት ከተጋበዙት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ከኤርትራ በረሃ፣ ፕሮፈሰር ጌታቸው በጋሻው በተጨማሪም የኢሳት ጋዜጠኞች ገሊላ መኮንን አምስተርዳም እና መታሰቢያ ቀፀላ ለንደን እንግድነት ተገኝተዋል። በዚህም ዝግጅት ፕሮፈሰር ጌታቸው ስለ ኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ ትንተና በሰፊው ገልፀዋል።
ፕሮግራሙን በሰፊው ሲጠበቅ የነበረው የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ንግግር በመቀጠል በአገሩቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ትግል ሰፊ እና ጥልቅ ማብራሪያ አቅርበው በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኞች አስከፊው ስደትና መከራ በወያኔ መንግስት በመሸሽ እያደረሰባቸው ባለው ስቃይ ለዚ አስከፊ ስደት የዳረጉን የወያኔን የግፍ አገዛዝ ጫፍ መድረሱንም ጭምር ያሳየ ምልክት ነው በድርጊታቸውም በቃ ልንላቸው ይገባል ትግሉን መደገፍ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።
በቀጣዮም ፕሮግራም ታዳሚው ያልተጠበቀው ለተሳታፊውም በዓነቱ እንግዳ የሆነ ነገር በመከሰቱ ህዝቡን ያስደሰተ ክስተት ተከሰተ። በዝግጅቱም ላይ ከተሳታፊዎች ፊታቸውን በከፊል በመሸፈን ዝግጅቱን ሲከታትርሉ የነበሩት ግለሰብ ማንነታቸው በመድረክ ላይ በመወጣት ተሳታፊ ያስደመመ ያስደተና የአንድነት መንፈስን የበለጠ ያጠናከረ ክስተት በአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ ያልተጠበቁ እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል ። ወ/ሮ ብዙነሽ ጽጌ ግጥም በማቅረብ ተሳታፊው በእንባ ፥ በቁጭት ስሜት ያንገበበ መልዕክት ያለው ግጥም አስተልፈዋል። የተወሰን ደቂቃ የምሳና ሻይ እረፍት በማድረግ በቀጥታ ወደ ልዩ ታሪካዊ የጨረታ ዝግጅት ነበር የታለፈው በጨረታውና የገቢ ማሰባሰቢያ የቀረበው ፎቶ የታጋይ አርበኛ ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ፣ አርበኛ ታጋይ መዓዛ ፅጌ እና አንዳርጋቸው ፅጌ በ አንድ ላይ ያጠቃለለ ነበር። ለጨረታው ቀርቦ የነበረው ከፍተኛ ዋጋ በ ወ/ሮ ብዙ አየሁ ፅጌ አሸንፈዋል። በጨረታውም ያሸነፉትን የሶስቱ ታጋይ አርበኞች ፎቶ መልሰው ለአዘጋጁ አስረክበዋል አዘጋጁም ከረጅም ርቀት ተጉዘው ከስዊድን አገር ለመጡ አገር ወዳድ አርበኞች አስረክበዋል። በፕሮግራሙ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያዊነት ነግሶ የታየበት ነበር ። በቀሪ ልዩ ዕጣ የወጣላቸው በልዮ ስሙ ኦታ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የትግሉ አጋር በዕጣው የወጣላቸውን የኮምፒተር ዕጣ ለ አርበኞች ግንቦት 7 አባልት እና ደጋፊ ለትግሉ ይጠቅማል በማለት በስጦታ መልክ ለግሰዋል። ሌላም ሌላም ስጦታዎች የተካተቱበት እና ለትግል ሜዳ ለተሰማሩት አጋር ጋዶች የሚሆን በ አንድ ግለሰብ 1000 ቲሸርት በስጦታ ተለግሰዋል። በማጠቃለያውም በ ኖርዌዳን ክሮነር 800,162 /ስምንት መቶ ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሳንትም/ ተሰብስቦዋል ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀ ሁኔታ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የተሰማውን ትልቅ አድናቆት በምስጋና ሲገልጽ በተለይ ከስዊድን እንዲሁም ከሰሜንና ከተለያየ የአውሮፓ ክፍል የመጣችሁ፣ ከበርገን፣ ከትሮንድሃየም፣ ከክርስትያንሳንድ፣ ስታቫንገር እንዲሁም ከተለያየ የኖርዌይ ቦታ የመጣችሁ፣ በማያያዝም የከረንት አፌር ፓል ቶክ ሩም እንዲሁም ኢካዴፍ ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና ስናቀርብ በማያያዝ የፍጻሜ የትግሉ ለሚጠይቀው መስዋእትነት ከአፍ ባለፈ በተግባር ስላሳያችሁት አጋርነት የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፣ በተለይ የዘረኛው የጥጵልፍ አቃጣሪ ቡችሎች ፕሮጋራማችንን ለማስተጓጎን ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ከነሱ ውስጥ በመሆን እንቅስቃሴያቸውም ስታቀብሉን ለነበር የውስጥ አርበኞች ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና እናቀርባለን፣
በስተመጨረሻ ከአገር ቤት በመደወል የገንዘብ ድጋፍ ላደረጋችሁንም ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!! – መግለጫ

በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።

የህወሃት ዘረኝነት በፈጠረው ኢፍትሃዊነትና አፈና የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞውን እያጠናከረ ባለበት በዚህን ሰዓት በሙስና የተጨማለቁ የህወሃት የጦር ጀነራሎችና በሲቪል ማዕረግ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሃይሎች ለምን ይህንን ጦርነት መጫር እንደፈለጉ ግልጽ ነው። በኦሮሚያ የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማፈን ከ400 በላይ ሕዝብ መጨፍጨፉና በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት መታጎራቸው የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም እንደ አንድ መሣሪያ ሆኖ ላለፉት 25 አመታት ሲያገለግል በኖረው ኦህዲድ ውስጥ እንኳን ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ ካድሬ ያሉትን አስኮርፎአል። የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ ሌላኛው የህወሃት አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥ የማያባራ ክፍፍል ፈጥሮአል። የነጻነት ታጋዮች በቅርቡ አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ የፈጸሙት የጀግንነት ገድል የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያንቃቃና ለትግል የሚያነሳሳ አርአያነት እንደፈጠረ የህወሃት አገዛዝ ተረድቶአል። በቤኔሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአፋርና በሱማሌ ከመሬት ንጥቂያ ጋር በተያያዘ ወንጀል ህወሃት ከህዝቡ ጋር አይጥና ድመት ድብብቆሽ ውስጥ ከገባ አመታትን አስቆጥሮአል። በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ቀድሞውኑም የድጋፍ መሠረት እንደሌለው ማወቁ ብቻ ሳይሆን ይኩራራበት የነበረው የትግራይ ምሽግነትም ከእጁ ሙሉ በሙሉ እያፈተለከ መምጣቱን ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት ፊቱን ወደሰሜን በማዞር የሕዝቡን ትኩረት አስታለሁ ብሎ ወያኔ አምኖአል። አባይ ጸሃይዬና ሳሞራ ዩኑስ መቀሌ ላይ በቅርቡ ባደረጉት የህወሃት ስብሰባ ላይ “ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ አይኖርም፤ ኢህአደግ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም” ማለታቸው ኤርትራን በመውረር በተለይም የትግራይን ህዝብ ድጋፍ መልሶ ያስገኛል የሚል እምነት በአገዛዙ መሪዎች ውስጥ መፈጠሩን ያመለክታል።

ሌላው ህወሃትን ወደ ጦር አጫሪነት እየነዳው ያለው እብደት መለስ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ ድርጅቱ ውስጥ የነገሰው የእርስ በርስ የሥልጣን ሹኩቻ የፈጠረው ውጥረት እንደሆነ መገመት አያዳግትም። አንዱን ውጥረት ለማርገብ ሌላ የውጥረት ግንባር በመክፈት ለሚታወቀው ህወሃት ይህ የተለመደ ስትራቴጂ ነው።

አርበኞች ግንቦት7 ህወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትኩረት ለመቀየር የሚያደርገው ማንኛውም አይነት ጥረት እንዳይሳካለትና የጀመረው ይህ የትኩረት ማስቀየሻ ስትራቴጂ የህወሃትን ውድቀት አፍጣኝ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ካሁን ቀደም ለአገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የሚሰጠው ፋይዳ ሳይመከርበትና ሕዝባዊ ስምምነት ሳይኖር ከአሥራ አንድ አመት በፊት ሱማሌ ውስጥ ዘፍ ተብሎ የተገባበት ጦርነት በየቀኑ የስንት ወንድሞቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ እያየነው ነው። ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ሰሞኑ በሽብርተኛው አልሸባብ ሲጨፈጨፉ የወያኔ መሪዎች አንዲትም ወፍ የሞተቺባቸው ያህል እንኳ አልተሰማቸውም ። ይህንን ሁሉም ያገራችን ህዝብ ያውቃል። እስከዛሬ በሰላም አስከባሪነት ስም ወደ ሰው አገር እየተላኩ ደመ ከልብ እየሆኑ ያሉ ወገኖቻችን ህይወት እያንገበገበን ባለበት በዚህን ሰዓት ለወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ እንደ አገር የምንዋጋው ሌላ ጦርነት እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። በ1998ቱ የባድሜ ጦርነት ወቅት ህዝባችን የከፈለው ዋጋና ከባድሜ ጦርነት መልስ ጉልበቱን አጠናክሮ ለመውጣት ዕድል ያገኘው የህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ እስከዛሬ እየፈጸመው ያለው አፈናና ጭፍጨፋ ተረስቶ ሌላ ዕድል ለመስጠት ዳግም መሳሪያ የምንሆንበት ምክንያት የለም።

አርበኞች ግንቦት 7 ከአሁን ቦኋላ ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘምና የተዘፈቀበትን የሃብት ዘረፋ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያደርገውን የሞት ሽረት ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም አይነት ሁኔታ ማስተናገድ የለበትም ብሎ ያምናል። በዚህም ምክንያት በመላው አገራችን የተጀመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ከግቡ እንዲደርስ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ትግሉን ለማጠናከር እንዲረባረብ አርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል ። በመካሄድ ላይ ያለውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ወያኔ የሚያደርገውን የጦርነት እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የነጻነት ቀናችንን እንድናፋጥን ሁላችንም እንነሳ ።

አርበኞች ግንቦት 7 ወያኔ በሰሜን በኩል የጀመረውን ትንኮሳ እየተከታተለ ለህዝባችን ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

አርበኞች ግንቦት 7

Friday, May 20, 2016

Ehiopia : U.S. Department of State Human Rights Practices Report for 2015

This summary is not available. Please click here to view the post.

በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ፤ ሞትና ስደት ለማስቆም ሁላችንም ጠንክረን እንታገል

የአርበኞ ግንቦት 7 ሳምንታዊ ርዕስ አንቀጽ
አፕሪል 22 2016

ህወሃት ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በህዝባችንና በአገራችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል ቁጥር ስፍር የለውም። እስከ አምናና ካቻምና የሆነውን እንኳ ትተን በዚህ በያዝነው አመት ብቻ በወገኖቻችንና በአገራችን ላይ ከተፈጸሙት ወንጀሎች ጥቂቶቹን ብናስታውስ የሚከተሉትን እናገኛለን ፤

1.    በጎንደር በኩል አገራችንን ከሱዳን ጋር የሚያዋሰነውን ለምና ድንግል  መሬት ቆርሶ  ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ማራመጃ ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተፈጸመውን ስውር ስምምነት የተቃወሙ በርካታ ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ ስቃይና እንግልት ተፈጽሞአል።

2.    ለዘማናት ተዋህዶ የኖረውን የቅማንትና የአማራ ህዝብ በማንነት ጥያቄ ለመከፋፈልና ለማጋጨት በተደረገው ደባ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ህይወት እንዲቀጠፍ ተደርጎአል።

3.    የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን የማንነት ጥያቄ ለማዳፈን ሲባል ለዓመታት ወደ ክልሉ ተሰዶ በሠላም ሠርቶ የሚኖረውን የትግራይ ተወላጅ በማስታጠቅና  በማነሳሳት በሁለቱ መሃል ጥላቻና ቂም እንዲረገዝ ተደርጎአል።

4.    በደቡብ የአገራችን ግዛት የማንነት ጥያቄ ያነሱና ወያኔ ለሚያካሂደው የስኳር ምርት ከመሬታቸው አንፈናቀልም ባሉ የኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎች ላይ ግዲያና እስር ተፈጽሞአል። በባሪያ ፈንግል ዘመን ይካሄድ በነበረ አዋራጅ ሁኔታ ዜጎች ራቁታቸውን እጅና አንገታቸውን በገመድ ታስረው በወታደር መኪና ሲጓጓዙ ታይቶአል።

5.    በአርባምንጭ ፤ በቴፕና ማጂ በአገዛዙ ዘረፋና ሙስና የተማረሩና ተቃውሞ ያነሱ ዜጎች ሽብርተኛ ተብለው ተደብድበዋል፤ ተገድለዋል፤ ታስረዋል፤ ከሥራቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ተጥለዋል።

6.    በብዙ ድካምና ጥረት ያገኙትን ገንዘብ አጠራቅመው ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው መጠለያ ቤት በአነስተኛ ቦታ ላይ የገነቡ በርካታ ዜጎች የሠሩት ቤት ለከተማ ውቤት አይመጥንም ተብሎ በላያቸው ላይ በቡልዶዘር እንዲፈርስ ተደርጎ ለበረንዳ አዳሪነት ተዳርገዋል።

7.    በአፋርና በሱማሌ ክልሎችም እንዲሁ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ወንጀል ከመሬታችን አንፈናቀልም ያሉ ዜጎች ታስረዋል ፤ ተገድለዋል ፤ ለስደት ተዳርገዋል።

8.    ሃሳባቸውን በነጻነት ለመግለጽ የሞከሩ፤ የአገዛዙን ዘረኛ አካሄድና ዘረፋ የተቃወሙ በርካታ ዜጎች በተቀነባበረ የሽብርተኝነት ወንጀል እየተከሰሱ ዝብጥያ ወርደዋል፤ እስር ቤት ውስጥ እያሉም በጨካኞችና አረመኔዎች አሰቃቂ ድብደባና ማሰቃያ እርምጃ ተፈጽሞባቸዋል።

9.    ለወያኔ ባለሥልጣናት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ የሆነውን የመሬት ዘረፋ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሥም ለማካሄድ የተደረገውን እንቅስቃሴ ተቃውመው አደባባይ በወጡ የኦሮሚያ አካባቢ ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ጭፍጨፋ በአጋዚ ጦር እንዲካሄድ ተደርጎአል።በዚህም የተነሳ ከ400 በላይ ዜጎች ህይወት ተቀጥፎአል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከትምህር ገበታቸው ታድነው እስር ቤት ተወርውረዋል፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል።

10.    ህዝባችን ከፍተኛ የረሃብ አደጋ አንዣቦበት አለም አቀፍ ለጋሾች ህይወት ለማዳን በሚራወጡበት ወቅት  ለባለሥልጣናቱ መኖሪያ ዘመናዊ ቪላ ለመገንባት ከመንግሥት ካዜና በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ እንዲሆን ተደርጎአል።

11.    የወያኔ መሪዎች ከደሃው ህዝብ ጉሮሮ እየዘረፉ ወደ ውጪ ከሚያሸሹት በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ውስጥ አምስት ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ በአንድ የወያኔ አባል በሻንጣ ተይዞ እንግሊዝ አገር ለማስገባት ሲሞከር ተይዞአል።

12.    በቅርቡም በቻይና አየር ማረፊያ በተመሳሳይ መንገድ የተገኘ ብዙ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለሥርዓቱ ቅርበት እንዳለው በተገለጸ ሰው እጅ ተገኝቶ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ቦኋላ በባለሥልጣናቱ ጣልቃገብነት መለቀቁ ተዘግቦአል።

ይህ ሁሉ ሰቆቃና ግዲያ መንግሥት ነኝ በሚለው የህወሃት አገዛዝ በወገኖቻችንና በአገራችን ላይ መፈጸሙ አንሶ ድንበር አቋርጠው ገቡ የተባሉ ታጣቂ ሃይሎች ከሰሞኑ በጋምቤላ ክልል ከ230 በላይ ወገኖቻችንን ገድለው ከ150 በላይ ህጻናትን ከእናቶቻቸው ጉያ ነጥቀው ተሰውሮአል። በጣም የሚያሳዝነውና አገራችን ያለቺበትን የውድቀት ደረጃ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው ደግሞ በሁለት ቀናት ዕድሜ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ በወገኖቻችን ላይ ፈጽሞ ወደመጣበት የተመለሰ የውጭ ታጣቂ ሃይል ማንነት እስከዛሬ አልታወቀም መባሉ ነው ።

ሌላው አሳዛኝ ክስተት  በአገራቸው ተስፋ የቆረጡና ኑሮ የምድር ስኦል ሆኖባቸው በስደት የተለያዩ አፍሪካ አገሮች ውስጥ በመንከራተት ላይ ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል በጀልባ ወደ አውሮጳ ለማምለጥ ሲጓዙ ከ200 በላይ የሚሆኑት ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ሰጥመው የአሳ እራት ሆነዋል።  በታንዛኒያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ የተያዙ በርካታ ወጣቶች ለረጅም ወራት በታንዛኒያ እስር ቤት ውስጥ ሲማቅቁ ቆይተው ከተለቀቁ ቦኋላ የታንዛኒያ መንግሥት አገልግሎቱን እንደጨረሰ ዕቃ ኬንያ ጠረፍ ላይ ወስዶ አራግፎአቸዋል። በእርምጃው ደስተኛ ያልሆነው የኬንያ ፖሊስም ወጣቶቹን አፍኖ ወደ መጡበት ታንዛኒያ ምድር በመመለስ አውላላ ሜዳ ላይ አራግፎአቸው ተመልሶአል። አዛኝና ተቆርቋሪ መንግሥት የሌላቸው እነዚህ ወጣቶች በማያውቁት አገር ለጅብ እራት አሳልፈው ተሰጥተዋል ። ይህ ሁሉ መከራና ስቃይ በወገኖቻችን ላይ ሲፈራረቅ ህዝባችንን ለዚህ ሰቆቃ የዳረጉት ወያኔና ግብረአበሮቹ  ከህዝብ በዘረፉት ገንዘብ ፎቅ ላይ ፎቅ በመገንባት በዶላር እያከራዩ  ሃብት ላይ ሃብት ያከማቻሉ። ልጆቻቸውንና የቅርብ ዘመዶቻቸውን በዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ከአገር እየሸኙ ውድና ምርጥ በተባሉ ትምህርት ቤቶች ያስተምራሉ ።

አርበኞች ግንቦት 7 በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ ፤ ግዲያ ፤ እስርና ስደት መቆም የሚችለው የአፈናው ፤ የግዲያው እና የስደቱ ምንጭ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ከህዝባችን ጫንቃ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ መወገድ ሲችል ብቻ ነው ብሎ ያምናል።  ለአገሩና ለወገኑ የሚቆረቆር ማንኛውም ዜጋ የዚህን ዘረኛና ከፋፋይ አገዛዝ የሥልጣን ዕድሜ ለማሳጠር የተጀመረውን ሁለገብ ትግል አቅሙ በፈቀደ መንገድ ሁሉ እንዲያግዝና ትግሉን እንዲቀላቀል አርበኞች ግንቦት 7 ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ጠንክረን በመታገል በአገራችንንና በወገኖቻን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ፤ ግዲያና ስደት ማስቆም እንችላለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

በጋሚቤላ ወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ጭፍጨፋ ተጠያቂው ወያኔ ነው!!! – የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

ባለፈው ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በመግባት በላሬና ጃካዋ ወረዳዎች በሚኖሩ የኑዌር ወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ማካሄዳቸውን በአገዛዙ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሚዲያዎች ጭምር ዘግበዋል።

ህወሃት ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ በጋምቤላ ክልል ነዋሪ በሆኑ ወገኖቻችን ላይ እንዲህ አይነት የጅምላ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በ1996 የህወሃት ልዩ ጦር የተሳተፈበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በአኝዋክ ተወላጆች ላይ ተካሂዶ ከ400 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ተቀጥፎአል። በወቅቱ የፈደራል ጉዳዮች ሃላፊ የነበረው አባ ጸሃይና ሌሎች ቱባ ቱባ የመከላኪያና የደህንነት ባለሥልጣናት እጃቸው እንደነበረበት ቢታወቅም እስከዛሬ ድረስ አንዳቸውም ለፍርድ አልቀረቡም። ከ1996ቱ ጭፍጨፋ በተጨማሪም በክልሉ የሚካሄደውን የመሬት ቅሚያ የተቃወሙ፤ ከአያት ቅድሜ አያቶቻችው የወረሱትንና እትብታቸው ከተቀበረበት በሃይል አንፈናቀልም ያሉ በርካቶች ተገድለዋል፤ ተደብድበዋል፤ ለእስርና ለስደት ተዳርገዋል። ከእስርና ከስደት ያመለጡ በርካቶችም በገዛ መሬታቸው ለአዳዲሶቹ ባለሃብቶች ጭሰኛ ሆነዋል አለያም ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳረገዋል። ይህ ሁሉ ግፍና መከራ አልበቃ ብሎ ከሰሞኑ ደግሞ “ማንነታቸው ያልታወቁ” የተባሉ ታጣቂዎች ከጎሬቤት ደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻግረው ከ208 በላይ የኑዌር ተወላጅ ወገኖቻችንን ጨፍጭፈው ወደመጡበት ተመልሰዋል። ከተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ከሃምሳ በላይ የሆኑት ህጻናት ሲሆኑ ሴቶችና አቅመ ደካማ የሆኑ ሽማግለዎች ቁጥርም ቀላል አይደለም።

ለመሆኑ ወያኔ “ማንነታቸው ያልታወቀ” የሚላቸው እነዚህ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው 40 እና 50 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገብተው ምንም መሣሪያ ባልታጠቁ ወገኖቻችን ላይ እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ የአገር ዳር ድንበር ለመጠበቅ የተቀጠረው መከላኪያ ሠራዊት አንዳችም የአጸፋ እርምጃ እንዳይወስድ ካምፕ ውስት ተዘግቶ እንዲቀመጠ የተደረገው ለምንድነው?የጥቃት ፈጻሚዎቹ ማንነትና የመጡበት ቦታ እንኳ በትክክል እንዳይታወቅና ተድበስብሶ እንድቀርስ የተፈለገው በምን ምክንያት ነው? የአገር ዳር ድንበርና የዜጎችን ደህንነት በአስተማማኝ የሚጠብቅ በሌለበት የአካባቢው ህዝብ ከጥንት ጀምሮ እራሱንና ንብረቱን የሚከላከልበት ነፍሰ ወከፍ መሣሪያ እንዲፈታ ማድረግ ለምን አስፈለገ? የሚሉ ጥያቄዎች ከጭፍጨፋው በስተጀርባ የወያኔ እጅ እንዳለበት ማሳያ ናቸው። ወያኔ የአገዛዝ ዕድሜውን ለማራዘም አንዱን ብሄር ከሌላው በማጋጨት በመካከላቸው መተማመን እንዳይኖር ፍርሃትና ጥርጣሬ እንዲነግስ ሲያደርግ የኖረ ቡድን ነው። ከዚህም የተነሳ “ድንበር ተሻግሮ ጥቃት ፈጸመ የተባለው ታጣቂ ” ጋምቤላ ውስጥ የሚካሄደውን የመሬት ቅርመታ የሚቃወሙትን ለማዳከም ሆን ተብሎ የጋምቤላንና የጎሬቤት ሱዳን ዜጎችን ለማጋጨት ከሚጠነስሰው ተንኮል ውጭ ሊሆን አይችልም። በክልሉ የሰፈረው የአገሪቱ መከላኪያ ሠራዊት ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ ከ208 በላይ ዜጎችን የጨፈጨፉ ታጣቂዎች ከመቶ በላይ ንጹሃን ዜጎችን አግተው በሰላም ወደ መጡበት መመለስ መቻላቸው ለዚህ ዋቢ ምስክር ነው።

አርበኞች ግንቦት 7 ምንም አይነት መንግሥታዊ ከለላና ጥበቃ በሌለው የኑዌርና የአኝዋክ ህዝባችን ላይ የተፈጸመውን ይህንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ አጥብቆ ያወግዛል። የመንግሥትን ሥልጣን ለሃብት ዘረፋ ብቻ እየተጠቀመ ዜጎች ለእንዲህ አይነት ዕልቂት እንዲጋለጡ የአደረገው የወያኔ አገዛዝ በጋምቤላ ለደረሰው ለዚህ እልቂት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ እንደሆነም ለመላው የአገራችን ህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስታወቅ ይወዳል።

ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 በዜጎቻችን ላይ ለደረሰው ለዚህ የጭፍጨፋ ወንጀል ተጠያቂ የሆኑ የወያኔ መሪዎች ህግ ፊት እንዲቀርቡ የጀመረውን ሁለገብ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል። ፍትህ እኩልነትና ነጻነት በአገራችን እንዲሰፍን የሚታገሉ የዲሞክራሲ ሃይሎች ሁሉ በህዝባችን ላይ የሚፈጸመውን ጭፍጨፋና ሰቆቃ ለማስቆም በተናጠል ከሚያካሂዱት ትግል ወደ ትብብርና የጋራ ግንባር እንዲመጡ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚገፋበት ይገልጻል። ለዚህ ጥረት መሳካትም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ቀናና ያላሰለሰ ትብብር እንዲያሳዩ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Friday, April 15, 2016

ትግሉ ሰፊ የምሁራን ተሳትፎ ይሻል!

ኢትዮጵያ በበብዛትም ይሁን በጥራት በውጭው አለምም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ምሁራን ያፈራች ሀገር ነች። በጅጉ የሚያሳዝነው ግን በሀገሪቱና በሕዝቧ ችግር ላይ ሀሳብ ሲሰጡ ፣ ባደባባይ ሲከራከሩና ሲታገሉ የሚታዩት በጅጉ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ ነው ተከታታይ መንግስታት በምሁራን ላይ ያደረሱት ጥቃትና ማግለል ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ብዙዎች መከራን ከህዝብ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ አጎንብሶ ማሳለፈን የመረጡበት ሁኔታ አለ። ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑም ለግል ጥቅማቸው ቅድሚያ በመስጠት ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር በመተባበር የሚሰሩ መኖራቸውም አይካደም። አብዛኛው ምሁራን በተለይም በብዙ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸው ጭምር ሀገሪቱን ከገባችበት ማጥ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ እየተሳተፉ አይደለም። ይህ ዛሬ ባለው ችግርም ይሁን በታሪክ ፊት አሳዛኝ ነው።

ሀገራችን ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። የተማሩ ልጆቿ መላ እንዲመቱ በመጠየቅ ላይ ትገኛለች። ይልቁንም በሀገራችን ያለው ችግርና ሀገሪቱ እየሄደች ያለችበት መንገድና አቅጣጫ በተለይ ምሁራንን እንቅልፍ ሊነሰ ይገባል። ዕውነታው ከዚህም አልፎ የሀገሪቱን አሳዛኝና አደገኛ ሁኔታ ለመቀየር በሚደረገው ትግል ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ግድ ይላል። የመንግስት ግፍና ሰቆቃ በበዛበትና የሀገራችን ሕልውና አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ሰዓት ምሁራን ላለመሳተፍ ምክንያት ማቅረብ የማይችሉበት ወቅት ላይ ደርሰናል። እንደማንኛውም ሀገር ምሁራን የኢትዮጵያ ምሁራን በሀገራችን ውስጥ ሰላምና ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና ፍትሕ የሰፈነበት ስርዓት እንዲመሰረት ሊሸሹት የማይገባ ትልቅ ሚና አላቸው።

ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች መንግስት በልማትና በልማት እያመካኘ የሚያካሂደውን ሰፊ ዝርፊያ እንዲሁም ወያኔ ሩብ ምዕተ አመት ሙሉ በብሄረሰብ እኩልነት ስም እየማለ የሚያደርሰውን ያንድ ብሄረሰብ ጉጅሌ የበላይነት ማስፋፋት እምርረው በመታገል ላይ ናቸው። መስዋዕትነቱን እየከፈሉ የሚታገሉትና የሚወድቁ የሚነሱት ወጣቶችና ምስኪን ገበሬዎች ናቸው። እነዚህ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ሳይቀር ሲገብሩ በየቀኑ እየሰማንና እያየን ነው። ይህንን የህዝብ ጥያቄና ትግል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምሁር ተመልካች ሆኖ ሊቀመጥ አይገባም። ትግሉን ከመምራት ጀምሮ እስከ ተራ ታጋይነት ባሉት ረድፎች ሁሉ ምሁራን ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል። ሰለትግሉ እቅጣጫም ሆነ ስለሀገሪቱ መጻዔ ዕድል ሃሳብ ማመንጨትና ማሰራጨት ይኖርበታል። ሀገራችን የደለቡ ችግሮቿን ተቋቁማ ፍትሕ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር የሚያደርጋትን የምህንድስና ስራ አስቀድሞ ማሰብና ማመቻቸት ይኖርበታል። ርግጥ ነው ይህን መሰል ተሳትፎ የሚያደርጉ ምሁራን አሁንም አሉ። ቁጥራቸው ግን ሊሆን ከሚገባው ጋር ሲወዳደር በጅጉ አነስተኛ ነው።

ምሁርነት ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ መቀዳጀት ብቻ እንዳልሆነ የታወቀ ነገር ነው። ምሁርነት ምሉዕ የሚሆነው መላውን የተፈጥሮ ከባቢ ከህዝብ ማህበራዊ ሕይወት ጋር አጣምሮ የሚያስብ አዕምሮን በዕውነት ላይ ለተመሰረተ ሀሳብና ዕውቀት ክብር መስጠትን ለተግባራዊነቱ መሟገትን የጨመረ ሲሆን ነው ። በመሆኑም ሁሌ እንደሚባለው ምሁርነት የጋን መብራትነት አይደለም። ምሁርነት በጨለማ ውስጥ ችቦ ሆኖ ብርሃን መፈንጠቅን ይመለከታል። ምስዋዕትነትንም ይጠይቃል።

ያለንበት ወቅት ለኢትዮጵያ ምሁራን ከፍተኛ ፈተናም ዕድልም ይዞ ቀርቧል። ይህ ልሽሽህ ቢሉት የማይሸሽ ፈተና ከመሆኑ ባልተናነሰ በታሪካችን እንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የጎላ አሻራን ለማኖርም ትልቅ የታሪክ ዕድል ነው። ይህ ፈተና ከፍተኛ ያርበኝነት ስሜትንና ሀላፊነት መውሰድን ይጠይቃል። አገር በተወሳሰበ ችግር ምክንያት ወደ አረንቋ እየገባች ምንም ሳይሰሩ መቀመጥ ወይም ዝም ብሎ ከመመልከት የበለጠ ለምሁር ሂሊና የሚከብድ ነገር ሊኖር አይችልም:: በጣም ላስተዋለ ሰው እንዲህ አይነት ዝምታ ሐጢያትም ነው። በእንዲህ አይነት ፈታኝ ወቅት የኢትዮጵያ ምሁራን ሀገሪቱን ወደተሻለ አቅጣጫ እንድትሔድ ላለመታጋል ምንም ምክንያት ማቅረብ አይችሉም። ሀሳብ የሚሰራጭባቸው የሀሳብ ክርክር የሚካሔድባቸው መድረኮች ፣ አደባባዮች ፣ የመገናኛ መሳሪያ አይነቶች የፖለቲካና የሲቪክ ማህበሮች ባገር ውስጥም በውጭም ያሉት መሳተፊያ ናቸው።

ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ምሁራን በሰፊውና እንደየፍላጎቶቻቸውና ችሎታቸው ሊሳተፉ የሚችሉባቸው በርካታ የትግል መስኮች አሉት። የሀገሪቱን ውስብስብ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የጥናት ውጤቶች ፣ ሀሳቦች ፣ ምክሮችም ሆነ ቀጥተኛ የምሁራን ተሳትፎ ለማስተናገድ አመቺ ሁኔታ ያለበት ድርጅት ነን። ወደፊትም የምሁራን ተሳትፎ እንዲጎለብት ሁኔታዎችን ይበልጥ ለማመቻቸት እንሰራለን። ዽርጅታችን የሀገራችን ችግር የሚወገደውና ዲሞክራሲና የዜጎች እኩልነት የሚረጋገጠው በበሰለና ከተራ ዜጋ እስከ ብስል ምሁራን በሚያከሂዱት ክርክርና የበሰለ ሃሳብ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ያምናል። አሁን ያለው የሀገራችን ምሁራን ተሳትፎ ደረጃ ሁላችንም ከምንጠብቀው በታች በጅጉ ያነሰ መሆኑ ሁላችንንም ከማሳዘን አልፎ የሚያስቆጭና የሚያንገበግብ ሆኖአል:: አገርና ህዝብ ድረሱልኝ እያለ በሚጣራበት በዚህ የታሪክ አጋጣሚ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ ማለፍ ይቻል ይሆናል። ይዋል ይደር እንጂ ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የደረሰበትን አፈናና ጭቆና እምቢኝ ብሎ ነጻነቱን ሲቀዳጅ ግን ከታሪክ ፍርድና ከህዝብ ትዝብት ማምለጥ አይቻለም።

አርበኞች ግንቦት 7 በአገር ውስጥም ሆነ በተለያየ ምክንያት በአለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ምሁር ለወገን ደራሽነቱንና አለኝታነቱን አሁኑኑ ይወጣ ዘንድ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Thursday, March 31, 2016

ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ተጠናክሮ ይቀጥል!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝባዊ እምቢተኝነት አድማሱን እያሰፋ በመሄድ ላይ ነው። የአዲስ አበባ የታክሲ አሽከርካሪዎች ያደረጉት አድማ፣ ወደ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ አለምበር፣ ነቀምት፣ ወለጋ፣ ወሊሶና ሌሎችም አካባቢዎች ተዛምቷል። በተለይ በአዲስ አበባ በሙስና የተጨማለቁት የወያኔ ሹማምንት ፣ የሚይዙትና የሚጨብጡት አጥተው ሲባዝኑ ተመልክተናል። ከዚህ ቀደም ይታይ የነበረው ድንፋታ ሁሉ ተንኖ፣ “ብቻ ስራ ጀምሩልን እንጅ እኛ ጥያቄውን በአፋጣኝ እንመልሳለን” በማለት ሾፈሮችን ሲማጸኑ አይተናል ።አድማው የወያኔን ትእቢት ያስተነፈሰ፣ የውስጡን ቀፎነት ገሃድ ያወጣና፣ እንደ ፊኛ ተነፍቶና ግዙፍ መስሎ የሚታየውን ሃይል በትንሽ ሃይል ማስተንፈስ እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ ክስተት ነው። የአለም በር አሽከርካሪዎች ደግሞ ” የምታደርጉትን አድርጉ እንጅ፣ በእኛ ላይ ቅጣት ልትጥሉ አትችሉም” በማለት ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ከመገናኛ ብዙሃን ሰምተናል። እንዲህ አይነት ህዝባዊ እምቢተኝነቶች፣ የነጻነት ታጋዮችን የትግል ወኔ የሚያነሳሱ ብቻ ሳይሆን፣ ወያኔ የማይቀረውን ሞት ሲሞት፣ በመቃብሩ ላይ አስተማማኝ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከፍተኛ እገዛ የሚያደርጉ ናቸው። ወያኔ ተለጣፊ የሲቪክና የሙያ ማህበራትን በራሱ አምሳል ፈጥሮ፣ በአባሎቻቸው የተመረጡት ማህበራት እንዲኮላሹ በማደረግ ለአመታት የመብት ትግሎች እንዲቀዛቀዙ ቢያደርግም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በእነዚህ ማህበራት ተስፋ የቆረጡ ሰራተኞች ፣ የይስሙላ ማህበራቱን ወደ ጎን በመተውና ራሳቸውን ከወያኔ እይታ ውጭ በማደራጀት ያካሄዱት ትግል፣ በአርያነቱ የሚዘከርና በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ ነው። ከሰሞኑ የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል የተገኘው ትልቁ ትምህርትም ይህ ነው፤ ዜጎች ለመብታቸው ለመታገል እስከቆረጡ ድረስ፣ የወያኔን አንድ ለአምስት የጥርነፋ ስልት በዘዴ በማለፍ ራሳቸውን በራሳቸው አደራጅተው መብታቸውን ለማስከበር የሚያግዳቸው ሃይል አይኖርም። በኦሮምያ የሚካሄደው ህዝባዊ እምቢተኝነትም ሆነ የታክሲ አሽከርካሪዎች አመጽ፣ ዜጎች ለመብታቸው ለመታገል ሲቆርጡ የሚፈጥሩት አቅም፣ ከወያኔ የጥርነፋ አቅም በላይ መሆኑን ያሳዬና ሌሎቻችችንም ትልቅ ትምህርት የምንወስደበት ነው።

የአለማችን የነጻነት ትግሎች ታሪክ እንደሚነግረን በጭቆናና አፈና ቀንበር ውስጥ የሚገኙ ህዝቦች ትክክለኛ አላማና ራእይ አንግበው አንድ ጊዜ ቆርጠው ትግል ከጀመሩ፣ ትግላቸው እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ይሄዳል እንጅ፣ በገዢዎች የአፈና መሳሪያዎች አይቆምም። ከአራት አመታት በፊት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የለኮሱት የድምጻችን ይሰማ ትግል፣ ከ 2 ዓመታት በፊት በደቡብ የአገራችን ክፍል ለነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ እርሾ ሆኖ አገልግሏል፤ የደቡቡ ህዝብ ትግል ደግሞ ኦሮምያን ከጫፍ ጫፋ ላዳረሰው ህዝባዊ ትግል መነሻ ሆኖ አግልግሏል፤ በኦሮምያ የቀጠለው ትግልም እንዲሁ በአማራ ክልል ለሚታዩት ተቃውሞች እና በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ለታዩት የታክሲ ሾፈሮች አድማ መነሻ ሆኗል። እነዚህ ተቃውሞች እስካሁን ተቃውሞውን ባልተቀላቀሉ ሌሎች ማህበረሰቦችም ዘንድ ተመሳሳይ መነቃቃት እንደሚፈጥሩና እኔም ለመብቴ መከበር መነሳት ይኖርብኛል የሚል እልህና ቁጭት እንደሚፈጥር አይጠረጠርም:: በዚህም ምክንያት መምህራን፣ የተለያዩ የፋብሪካ ሰራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ የተለያዩ የሙያ ማህበራት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ጡረተኞች፣ ፖሊሶች፣ የቀድሞ ወታደሮች፣ አርሶ አደሮች ወዘተ መብታቸውን ለማስከበር በአንድነት ወይም በየግላቸው እንደሚነሱ ይጠበቃል:: ህዝባዊ ትግል እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጣይ ነውና። ህዝባዊ አመጽ የሚቆመው ፣ በጥይት ወይም በዱላ ሳይሆን፣ ለአመጽ ምክንያት የሆነውን ጥያቄ በመመለስ ብቻ በመሆኑ፣ በአሁኑ ሰአት በአገራችን ዋነኛው የአመጽ መንስኤ የሆነው የመብት ጥያቄ ፣ ትክክለኛውን ምላሽ እስካላገኘ ድረስ ሊቆም አይችልም።

አርበኞች ግንቦት7 ህዝባዊ እምቢተኝነትን እንደ አንድ የትግል ስልት አድርጎ ሲያውጅ፣ የወያኔን አፋኝ ስርዓት በውጭም በውስጥም ለመከፋፋልና ለማዳከም ይጠቅማል ከሚል ስልት ብቻ ሳይሆን፣ የህዝባዊ እምቢተኝነት መጠናከርና ይህን ትግል የሚያካሂዱት የሲቪክም ሆነ የሙያ ማህበራትን ማጠናከር ፣ ከወያኔ ፍጻሜ በሁዋላ፣ በአገራችን ለሚጀመረው የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ከልብ በማመንም ጭምር ነው። ወያኔ ገና ወደ ስልጣን ሲመጣ፣ የሰራተኛ ፣ የመምህራን ፣ የጋዜጠኞች ወዘተ ማህበራትን ዳግም እንዳያንሰራሩ አድሮጎ የመታቸው፣ የማህበራቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንደልብ የሚዘርፍበትን ስልጣን እንደሚያሳጣው ስለሚያውቅ ነው፣ ለነገሩ ከመጀመሪየውም ለዝርፊያና ለቅሚያ የመጣ ሽፍታ፣ በአገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲፈጠር ፍላጎት ሊኖረው ይችላል ብሎ ማሰብም የዋህነት ነበር። አስገራሚው ነገር ደግሞ ይህ የሽፍታ ስብስብ፣ ከ25 አመታት ዝርፊያ በሁዋላ፣ በቃኝ ብሎ ከዘረፋ ተግባሩ ለመታቀብ አለመቻሉና የዘረፈውን ህብት እንኳን ተመቻቸቶ ለመብላት የሚያስችለውን ስርዓት ለመገንባት አለመቻሉ ነው። ስብስቡ ላለፉት 25 ዓመታት ዘርን ከዘር እያጋጨ፣ እየገደለና እያሰረ፣ ያለከልካይ እንዲዘርፍ በነበረው ከፍተኛ ፍላጎት የህዝባችን ነጻነትም በዛው ልክ እየተደፈጠጠ መጥቷል፣ ዛሬ እስከናካቴው ሰብሰብ ብሎ የግል ጉዳይን መጫወትም እንደሰላማዊ ሰልፍ እየተቆጠረ፣ የሚያስከስስበትና የሚያስደበድብት ደረጃ ተደርሷል ። የሙያና የሲቪክ ማህበራት እንዲኮላሹ መደረጋቸው፣ ወያኔ እንደልቡ እንዲዘርፍ ብቻ ሳይሆን፣ ለነጻነቱ የሚታገል፣ ወኔና የአገር ፍቅር ስሜት ያለው ትውልድ እንዳይፈጠር አድርጓል። ነገር ብዙ ጥፋቶች ከደረሰም በሁዋላም ቢሆን፣ ህዝባችን ቀስ በቀስ የወያኔን ማንነት ይበልጥ እያወቀ ሲመጣ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደምናየው ፣ ህዝባዊ ተቃውሞችና አልገዛም ባይነቱን እያሳደገ መጥቷል። ለዚህ ውጤት መገኘት ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፤ ህዝባችን ለመረጃዎች ቅርብ እየሆነ በሄደ ቁጥር የመብት ትግሎችም በዚያው ልክ እየተጠናከሩ የሚሄዱ በመሆኑ፣ መጪዎች አመታት የኢትዮጵያውያንን የነጻነት ትግል የሚያስተናግዱ ብቻ ሳይሆን የአገራችን መጻኢ እድል የሚወሰንባቸው ወሳኝ አመታት በመሆናቸው ሁላችንም ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት እየተከታተልን የራሳችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለብን።

አርበኞች ግንቦት7 በሃይል ትግሉም በህዝባዊ እምቢተኝነቱም በኩል ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ሌት ተቀን አቅም የፈቀደለትን ሁሉ እያደረገ ይገኛል። የንቅናቄያችን ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንዳደረጉት ሁለቱም የትግል ስልቶች ተቀናጅተው የወያኔን ግብአተ መሬት እንዲያፋጥኑ ድርጅታችን ሁኔታዎች አመቺ ናቸው ብሎ በሚያምንበት ጊዜ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ እርግጠኛ ነው። ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት በአገራችን እንዲሰፍን የሚሻ ማንኛውም ዜጋ በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ንቅናቄያችን የቆመለትን አላማ ለማሳካት በያለበት ሆኖ ትግሉን እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን መላልሰን እናቀርባለን:: በሥራ ዋስትና ሰበብ ከወያኔ አለቆቻቸው የሚሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው በገዛ ወገኖቻቸው ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ በማካሄድ ላይ የሚገኙ የመከላከያ ፤ የፖሊስና የደህንነት ሃይሎችም ቆም ብለው በማሰብ ከህዝባቸው ጋር እንዲወግኑ አርበኞች ግንቦት 7 ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
አርበኞች ግንቦት7

Monday, February 1, 2016

የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !

ኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ ቁጭቱን በቻለው መንገድ ሁሉ ሊገልጸው ሞክሯል። ነገር ግን እስካሁኗ ሰአት ድረስ መገደሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ፣ መዋረዱ አለቆመም። አገዛዙ ለአንድ ቀን በስልጣን ላይ ውሎ እስካደረ ድረስ ይኸው ግፍ ይቀጥላል።

የወልቃይት ህዝብ እኛ እንደፈለግን እንጅ አንተ እንደፈለክ አትኖርም ተብሎ ተፈርዶበት ያለፉትን 25 ዓመታት በስቃይ አሳልፏል። አሁንም እንደገና ” እኛ እናውቅልሃለን እየተባለ” መከራውን እየበላ ነው። በአካባቢው ያንዣበበው የሞት ደመና እጅግ አደገኛ ነው። እየተረጨ ያለው መርዝ ካልቆመ፣ አካባቢው በአጭር ጊዜ የግጭት አውድማ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ዘራፊው የህወሃት ቡድን ግጭትን ከማባበስ በተረፈ ችግሩን የማስቆም ፍላጎት አላሳዬም።

በዚሁ አካባቢ የአንድ አገር ሎጆችን ቅማንትና አማራ እያሉ እርስ በርስ ለመከፋፈልና ለማጋጨት ወያኔ እየዘራው ያለው ይጥፋት ዘር እስካሁን ከደረሰው እልቂት በላይ ሌላ እልቂት ይዞ እየመጣ ነው። የአገር ሰላምና ጸጥታ እናስከብራለን ብለው መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች በሁለቱም ወገን ግጭት ለመቀስቀስ ሲዶልቱ፣ ሲያቅራሩና ሲሸልሉ ውለው እያደሩ ነው። ከዚህ ሁሉ የእልቂት ጀርባ ያሉት ዜጎችን ካላጋጩ ውለው ማደር የማይችሉት የወያኔ መሪዎችና ግብረአበሮቹ ናቸው።

የደቡብ ህዝብም ልጆቹን በሞት እየተነጠቀ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቹም በየእስር ቤቱ ታጉረዋል፡፡ ዛሬ ወደ ኮንሶ፣ አርባምንጭ፣ ቁጫ፣ ሃመር ወዘተ ብንሄድ የምንሰማው ዋይታና ለቅሶ ነው።

የሶማሌው ወገናችን በልዩ ሃይል አባላት የዘረ ፍጅት እየተፈጸመበት ነው፤ አፋሩ ፣ ጋምቤላውና ቤንሻንጉሉ ከቀየው እየተፈናቀለ፣ መሬቱን እየተነጠቀ ለሞትና ለዘላለማዊ ድህነት ተዳርጓል።

ይሄ ሁሉ መከራና ግፍ ሳያንስ ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝባችን በረሃብ እየተጠቃ መሆኑ በሰፊው እየተነገረ ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በተፈጥሮ በሚሳበብ የአየር መዛባት ችግር ምክንያት ባለፈው የምርት ዘመን የተዘራው ሰብል እንዳለ ወድሞአል:: በዚህም የተነሳ በህዝባችን ላይ ያንዣበበው የረሃብ አደጋ እስከዛሬ ካየነው ሁሉ የከፋ እንደሚሆን አለማቀፍ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው። ላለፉት 10 አመታት በእጥፍ አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ እያለ ህዝብ ሲያደነቁርና የለጋሽ አገሮችን ቀልብ ለመሳብ ሲባዝን የኖረው ወያኔ ግን በፈጠራ ታሪክ የገነባው ገጽታ እንዳይበላሽበት ረሀቡን ለመደበቅና የጉዳት መጠኑን ለማሳነስ ብዙ ርቀት ተጉዟል። ያም ሆኖ የችግሩ ግዝፈት እያየለ ሲመጣና ተጎጂዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ወደየ አጎራባች ከተሞች መሸሽ ሲጀምሩ ሳይወድ በግድ ለማመን ተገዷል። ። በሰሜን ወሎ፣ በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በደቡብና በኦሮምያ በድርቁ ምክንያት በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ የሚገኙ እናቶችና ህጻናት ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም፣ ወያኔ ግን እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ እዚህም ላይ የቁጥር ጨዋታ በመያዙ አሁንም ተገቢው እርዳታ ለህዝባችን በጊዜ እንዳይደርስ እየተከላከለ ለህዝብ መከራ ደንትቢስነቱንና ጨካኝነቱን እያሳየ ይገኛል።

ወያኔ በህዝባችን ላይ የደገሰው የሞት ድግስ በዚህ ብቻ አያበቃም። የኑሮ ውድነቱ ጣሪያ በመንካቱ ህዝቡ እያንዳንዷን ቀን የሚያሳልፈው በጣርና በጭንቅ ነው፤ ከጥቂት የወያኔ ባለስልጣናትና ሸሪኮቻቸው ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ኑሮው ሲኦል ሆኖበታል። ችግሩና መከራው እየከፋ ሲሄድ እንጅ እየቀነሰ ሲሄድ አይታይም። በሚብለጨለጩና የህዝቡን መሰረታዊ የፍጆታ ችግር በማይቀርፉ ስራዎች ላይ በማትኮር ህዝብን በልማት ስም ለመሸንገል ሙከራ ቢደረግም፣ አልተሳካም። ከኑሮ ውድነት በተጨማሪ ስራ አጥነቱ፣ አፈናው ፣ ስደቱ እስርና እንግልቱ፤ ሙስናው፣ የፍትህ እጦቱ ወዘተ የአገራችን ህዝብ ኑሮውን በጉስቁል እንዲገፋ አድርጎታል።

አርበኞች ግንቦት 7 አገራችንና ህዝባችን ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ መውጣት የሚችለው አገዛዙ የዘረጋው የተበላሸ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲዎች ሲለወጡና ከህዝብ፡በህዝብ ለህዝብ የሚቆም የመንግሥት ሥርዓት በአገራችን እውን መሆን ሲችል ብቻ ነው ብሎ ያምናል:: የወያኔ የሥልጣን ዕድሜ በተራዘመ ቁጥር በህዝባችን ላይ የሚደርሰው በደልና ሰቆቃም እንዲሁ እየተራዘመ ይሄዳል:: ህዝባችን ከሚደርስበት ለቅሶና መከራ እንዲገላገል ሁላችንም በያለንበት አምርረን እንታገል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
አርበኞች ግንቦት7

Thursday, January 28, 2016

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው

የወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላዩ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በእጅጉ ማሳስብ ጀምረዋል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

አሜሪካንን ጨምሮ የወያኔ ለጋሽ ሀገራት የሆኑት ምዕራባውያን ሰሞኑን በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የከፈተውን የዕብሪት ጭፍጨፋ፣ እስራትና አፈና አስመልክቶ ችግሩን በውይይትና በስልጡን መንገድ ይፈታ ዘንድ የሚያሳስቡ ግልጽና ባንጻራዊ ደረጃ ሲታዩ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል። የደረሰውም ጥፋት ተመርምሮ ጥፋተኛ ወገን እንዲጠየቅ የሚጠይቁና ችግሩም በሰላምና በውይይት እንዲፈታ እየጎተጎቱ ይገኛሉ። ባለፉት በርካታ ዐመታት ምዕብራባውያኑ የወያኔ ጉጅሌ ይህንን አቅጣጫ እንዲከተል ተጽዕኖ የመፍጠር አቅማቸውን ተጠቅመው ያደረጉት በቂ ግፊት እንደሌለ ይታወቃል። የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገሮች ዘግይተውም ቢሆን ሀገራችን ውስጥ የተካሄደውንና እየተካሔደ ያለውን ጭፍጨፋ ማውገዛቸውና ወደፊትም በዝርዝር ተመርምሮ ተጠያቂው እንዲታወቅ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደ በጎ ጅምር እንመለከተዋለን።

ለሀገራችንና ለህዝባችን እጣ ፋንታ የምንጨነቅና የህዝቡ ጥቃት ያንገፈገፈን የሀገሪቱ ልጆች የችግሩ የመፍትሔ መጀመሪያ ይህ በጉልበቱ ህዝባችን ላይ የተጫነ መንግስት ነኝ ባይ የግፈኞች ጥርቅም በሃይል በሚደረግ ትግል ጭምር መወገድ አለበት ወደሚለው ውሳኔ የደረስነው የሰላም በርና ጭላንጭል ሁሉ በመዘጋቱ እንደሆነ ስንገልጽ ቆይተናል ። ላለፉት ሁለት ወራት በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውና ከመቶ ሀምሳ በላይ ወገኖቻችን ያለቁበት ጭፍጨፋ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ተመሳሳይ ግድያ፣ እስራትና የተቀናቃኝን አድራሻ ደብዛ ማጥፋት እርምጃ የሚያሳየው ይህ ስርዓት የበለጠ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በፍጥነት መወገድ ያለበት መሆኑ ላይ ያለን አቋም ለሁሉም ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ነው። እንደ ወያኔ ያለ ከህዝብ የተጣላ የፖለቲካ ሀይል የፖለቲካ ጥቅምን የሚያየው ከራሱ ህልውናና ደህንነት አንጻር እንጂ ከህዝቡ ሰላም ብልጽግናና ነጻነት ወይም ከሀገሪቱ የረጅም ጊዜ እጣ ፋንታ አንጻር አይደለም። የወያኔን ገዥዎች የሚያስጨንቃቸው የህዝቡ ኑሮ ሳይሆን የራሳቸው የዝርፊያ ስርዓት ባግባቡ መጠበቅ አለመጠበቁ ነው። ለዚህ ነው ስርዓታቸውን ለመጠበቅ የነጻነት ጥያቄ ኮሽታ በሰሙ ቁጥር የሚባንኑት። ለዚህ ነው በሰላም መብቱን የጠየቃቸውን ሁሉ መደዳውንና በጭካኔ በጥይት የሚረፈርፉትና የተረፋቸውን እንደ እንስሳ ወህኒ በረት ውስጥ የሚያጉሩት።

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ ጸረ ህዛብና ጸረ አገር እርምጃ ሊቆም የሚችለው ላለፉት 25 አመታት ወያኔ በመካከላችን የገነባው የመከፋፈልና የልዩነት ግድግዳ ለመናድ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንዳችን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በሁላችንም ላይ እንደ ተፈጸመ ቆጥረን በጋራ ስንንቀሳቀስ ብቻ ነው ብሎ ያምናል:: ዛሬ በኦሮሚያ ወገኖቻ ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃና ግዲያ ትናንት በጋምቤላ ፤ በኦጋዴን ፤ በአፋር፤ በቤኔሻንጉል ፤ በደቡብና በአማራ ወገኖቻችን ላይ በፈረቃ ሲፈጸም የቆየና እየተፈጸመ ያለ መከራ መሆኑን የማይገነዘብ የለም:: በፈረቃ መገደል፤ በፈረቃ ወህኒ መወርወር ፤ በፈረቃ መፈናቀል፤ በፈረቃ ለስደት መዳረግ የሁላችንም ዕድል ፈንታ ሆኖአል:: ይህንን ስቃይና መከራ ማስቆም ለፍትህና ለነጻነት የቆመ ዜጋ ሁሉ ግዴታ ነው::

ወያኔ የሰላም በሮችን በሙሉ ጠርቅሞ ሲዘጋ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ዝምታን የመረጡ ምዕራባዊያን የህዝብ ብሶት ገንፍሎ አደባባይ ከወጣና ብዙዎች በአጋዚ ጦር ጨካኝ ግዲያ ህይወታቸውን ከገበሩ ቦኋላ ዘግይተውም ቢሆን መናገር መጀመራቸው መልካም ጅምር ነው:: ነገር ግን በእብሪት የተወጠሩ የወያኔ መሪዎች በባዕዳን አለቆቻቸው ቁጣ ከአቋማቸው ፍንክች ይላሉ ብሎ መጠበቅ መዘናጋት እንዳያስከትል መጠንቀቅ ተገቢ ነው::  ችግሮችን ተነጋግሮ መፍታት ትልቅ አቅምና ችሎታን የሚጠይቅ የዘመናችን ሥልጣኔ ውጤት ነው:: በጠመንጃ ተጸንሶ በጠመንጃ የተወለደው ወያኔ ለእንዲህ አይነት ዕድገትና ሥልጣኔ አልታደለም::

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔ ስርዓት ሊወገድ እንጂ ሊጠገን የማይችል የተበላሸ ስርዐት መሆኑን ይገነዘባል:: በመሆኑም በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጸመውን ወንጀል ለማስቆም የጀመረውን ሁለገብ ትግል የወያኔ አገዛዝ እስኪወገድና ሠላምና ዲሞክራሲ በአገራችን እስኪሰፍን ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ለወዳጅም ለጠላትም ያረጋግጣል ::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

Friday, January 22, 2016

European Union Parliament condemns the wide range of human rights violations by the TPLF regime in Ethiopia

In what is being described as the strongest resolution on Ethiopia thus far, the European Union Parliament passed a resolution that condemned the ever increasing human rights violations in Ethiopia by the minority TPLF regime. The Parliament also deplores the recent use of excessive force by security forces in Ethiopia against peaceful protesters in the Oromia region.

“Parliament strongly condemns the recent use of violence by the security forces and the increased number of cases of human rights violations in Ethiopia. It calls for a credible, transparent and independent investigation into the killings of at least 140 protesters and into other alleged human rights violations in connection with the protest movement after the May 2015 federal elections in the country,” according to the news release by the EU parliament.

“It also calls on the Ethiopian authorities to stop suppressing the free flow of information, to guarantee the rights of local civil society and media and to facilitate access throughout Ethiopia for independent journalists and human rights monitors. The EU, as the single largest donor, should ensure that EU development assistance is not contributing to human rights violations in Ethiopia,” the release said.

The resolution which was passed with a majority vote, with the exception of objections by the right wing members of the parliament, has covered a wide range of violations by the minority regime in Ethiopia against peaceful citizens who only demanded for the respect of their political, human, economic and religious rights.

Following is the full text of the resolution:

The European Parliament,

–  having regard to its previous resolutions on Ethiopia and in particular to its most recent plenary debate on the matter, of 20 May 2015,

–  having regard to the statements by the EEAS spokesperson on 23 December 2015 and on 27 May 2015,

–  having regard to the EU Council conclusions on the EU Horn of Africa Regional Action Plan 2015- 2020 on 26 October 2015,

–  having regard to the Universal Declaration of Human Rights of 1948,

–  having regard to the International Covenant on Civil and Political Rights of 1966, to which Ethiopia acceded on 11 June 1993,

–  having regard to the African Charter on Human and Peoples’ Rights of 1981, ratified by Ethiopia on 15 June 1998,

–  having regard to the second revision of the Cotonou Agreement,

–  having regard to the Constitution of the Federal Republic of Ethiopia adopted on 8 December 1994, and in particular the provisions of Chapter III on fundamental rights and freedoms, human rights and democratic rights,

–  having regard to Rule 123(2) of its Rules of Procedure,



Whereas Ethiopia is witnessing a wave of protests against the planned expansion of Addis Ababa’s municipal boundary,


Whereas protesters feel that this expansion will lead to displacement of farmers,


Whereas police and military forces have responded to the generally peaceful protests by killing and wounding many protesters; whereas the toll could be as high as 140 casualties and more than thousand injured people according to international human rights’ organisations,


Whereas senior Ethiopian government officials alleged the protests were connected to “foreign terrorist groups,” an apparent attempt to justify the deployment of the army and the use of lethal force to quell the protests,


Whereas terrorism related accusations are routinely used by Ethiopian authorities in order to repress opposition forces and independent journalists,


Whereas Ethiopian security forces have a record of using excessive force against peaceful protesters, including firing into the crowd,


Whereas since the protests began the government has arbitrarily arrested and detained several journalists and political opposition leaders, including the deputy chairman of the party Oromo Federalist Congress (OFC), Bekele Gerba, whose whereabouts are unknown today,


Whereas the Ethiopian government has started to show signs of flexibility on the question of the “Addis Ababa Masterplan” linking its implementation to reaching a consensus after in-depth and full discussions;


Whereas the Ethiopian political environment is characterized by the presence of an ultra-dominant ruling party, a large state control on the media, restricted campaign possibilities for the opposition, a year-long clamp down on independent media outlets which has recently extended to social media, oppression of peaceful protests, a restricted space for human rights’ defenders and civil society organisations and a lack of accountability of Ethiopian authorities,


Whereas the abduction in neighbouring Eritrea of political activist and British national Andargachew Tsege led to the recommendation by the Human Rights Council’s Working Group on Arbitrary Detention to the Government of Ethiopia to immediately release him,


Whereas the preferred government strategy for eliminating independent media is to file criminal charges against publishers, and to impose hefty fines and prison terms,


Whereas Ethiopia’s Civil Society Organisations (CSOs) and Charities law requires organisations engaged in advocacy to generate 90% of the funding for their activities from local sources leading to decrease of CSO action and to the disappearance of many organisations,


Whereas numerous individuals have been arrested and tortured for speaking to human rights organisations and the international media,


Whereas Ethiopia has adopted a national human rights action plan in 2013,


Whereas large scale development programmes and projects, such as the Gibe III dam, and wide-scale leasing of land to international investors are accompanied by resettlement programmes and the reduction of living space for local pastoralists,


Whereas in these contexts pastoralists are often relocated by force, imprisoned and killed by Ethiopian security forces;


Whereas foreign aid has widely finance such programmes and thereby indirectly contributed to human rights abused against local populations,


Whereas Article 40/5 of Ethiopia’s constitution guarantees Ethiopian pastoralists the right to free land for grazing and cultivation as well as the right not to be displaced from their own lands,


Whereas Ethiopia persecutes the Ogaden Oromo and other ethnic groups, targeting women and children; whereas rape and torture have been systematically used to spread fear, and the Ogaden region is effectively under government embargo.






Condemns the violent repression of peaceful protests and calls for the immediate release of peaceful protesters;


Urges the Ethiopian authorities to put in place an independent investigation of the events and to pursue perpetrators of violence and of human rights violations;


Urges the government to immediately invite the UN Special Rapporteur on the rights to freedom of association and peaceful assembly and other UN human rights experts to visit Ethiopia to report on the situation;


Urges the government to commit to genuine consultation with Oromo communities about the impact of the expansion of Addis Ababa’s municipal boundary, including potential displacement of communities and compensation for those affected;


Calls on the Ethiopian authorities to guarantee, as foreseen inter alia in the Ethiopian Constitution, a space for political debate and controversies without fear for repression;


Requests the Ethiopian authorities to stop using anti-terrorist legislation for repressing political opponents, dissidents, human rights defenders, other civil society actors and independent journalists;


Condemns the excessive restrictions placed on human rights work by the Charities and Societies Proclamation, denying human rights organisations access to essential funding, endowing the Charities and Societies Agency with excessive powers of interference in human rights organisations, further endangering victims of human rights violations by contravening principles of confidentiality;


Urges the Ethiopian authorities to allow access to prisons and all places of detention to independent monitors, and grant all detainees and prisoners access to their families and legal counsel, and provide any medical treatment they may require;


Urges the Ethiopian authorities to move any detainees currently held in unofficial places of detention to a recognised detention centre and charge all of them with a recognisable criminal offence, and try them in a timely manner in trials which meet international standards of fair trial, or immediately and unconditionally release them;


Urges them in particular to implement the Human Rights Council’s Working Group on Arbitrary Detention recommendation and to immediately release British national and political activist Andargachew Tsege, who is being held under an in absentia death sentence having been kidnapped and rendered to Ethiopia in 2014;


Calls on the government to stop suppressing the free flow of information, including by jamming media broadcasts and harassing media, and facilitate access throughout Ethiopia for independent journalists and human rights monitors;


Calls on Ethiopian authorities to remove restrictions on freedom of expression imposed on the Mass Media by the Access to Information Proclamation (2008) and the Anti-terrorism Proclamation (2009) that do not conform to rights of freedom of expression provided in international human rights law;


Welcomes the Ethiopian 2013 human rights action plan and calls for its swift and complete implementation;


Invites donors to include into their development programmes funds specifically dedicated to strengthening independent media outlets and journalists; welcomes in this context the EU approach consisting of providing assistance to local human rights and democracy groups through the Civil Society Fund;


Calls on the Ethiopian authorities to ensure that all resettlement programmes are voluntary, that affected people are consulted before moving them and to offer pastoralists alternatives to becoming sedentary;


Calls on the EU and other major donors to review programs and policies to ensure that development assistance is not contributing to human rights violations in Ethiopia, particularly programs linked to displacement of farmers and pastoralists, develop strategies to minimize any negative impact of displacement within EU funded development projects and to ensure protection and support to human rights defenders and inclusion of the Ethiopian civil society in the planning, implementation and evaluation of all development efforts;


Urges the Ethiopian authorities to stop its persecution of the Ogaden Oromo and other ethnic groups;


Instructs its President to forward this resolution to the Council and the Commission, the Vice-President of the Commission / High Representative of the Union for Foreign Affairs and Security Policy, the governments and parliaments of the Member States, the Government of Ethiopia, the institutions of the African Union, the United Nations Secretary-General, the United Nations General Assembly, the Co-Presidents of the ACP-EU Joint Parliamentary Assembly and the PAN-African Parliament (PAP).

Tuesday, January 19, 2016

ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እንቢ ትበል!!!

ሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ ከ150 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በአማራ፣ በጋምቤላና በሶማሌ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ በሌሎችም ክልሎች ወገኖቻችን እየተገደሉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ታስረዋል። የህወሓት አገዛዝ ዜጎች መግደል፣ መደብደብና ማሰር መደበኛ ሥራው አድርጎታል።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየቀጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት እና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሁላችንም ተሳትፎ የሚሻ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትናንሽ የገጠር ከተሞችን ሳይቀር ያዳረሰ መሆኑ የበርካታ ሕዝብ ስሜትንና ጥቅምን የሚነካ አጀንዳ በፍጥነት እንደሚሰራጭና ሕዝብን እንደሚያደራጅ አመላካች ነው። ከዚህ ሕዝባዊ ትግል በርካታ ድሎች የተገኙ ቢሆኑም ሁለቱ መሠረታዊ በመሆናቸው አጽንዖት ሊሰጣቸው ይገባል።

አንደኛ

በአለፉት ሁለት ወራት በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት የኢትዮጵያን ማኅበረሰብ አቀራርቧል። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ሕዝብ ያልመከረበት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መቃወም ፍትሃዊ መሆኑ በሰላማዊም ሆነ በአመፅ መንገድ የህወሓትን አገዛዝ መታገል የመረጡ የዲሞክራሲ ኃይሎችን በሙሉ ያስማማ፤ በኦሮሞና በአማራ ማኅበረሰብ መካከል መልካም የሆነ መግባባትን የፈጠረ መሆኑ ትልቅ ድል ነው። ይህ ማለት ግን አፍራሽ ጽንፈኛ አስተያየቶች ከወዲህም ከወዲያም መወርወራቸው ቀረ ማለት አይደለም፤ ያም ሆኖ ግን በሕዝቡና በፓለቲካ ልሂቃኑ መካከል ያለው መናበብ ከቀድሞው በጣም በተሻለ ሁኔታ መገኘቱ ተስፋ ሰጪ ነው። ይህንን ድል ማስከንና አድማሱን ማስፋት ያስፈልጋል። በተለይም የነፃነት ትግሉ አካል የሆኑትን የትግራይ ወገኖቻችንን ማቀፍ እና ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል ያስፈልጋል። ወደ ህወሓት የሚወረወሩ ፍላፃዎች ወደ ትግራይ ሕዝብ የተወረወሩ መስለው እንዳይታዩ በንግግሮቻችንና ጽሁፎቻችን ሁሉ ግልጽ ማድረግ ይኖርብናል። ሶማሌን፣ አፋርን፣ ሲዳማን እና ሌሎችን ማኅበረሰቦችን በተመለከተ ተመሳሳይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ወሳኝ ወቅት በማኅበረሰቦች መካከል እየተፈጠረ ያለው መግባባትን የሚቀለብስ ወይም ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ አንዳችም ተግባር እንዳይፈፀም ነቅቶ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ይህ ትግል፣ እስካዛሬ አጥተነው የነበረው የኢትዮጵያውያንን ማኅበረሰብ መቀራረብን አምጥቶልናል፤ በሚገባ ከተጠቀምንበት ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያን የመገንባት አቅማችንን በከፍተኛ ሁኔታ ያጠነክርልናል። ስለሆነም፣ ከግራ እና ቀኝ በሚወረወሩ ዘረኛ አስተያየቶች እና ተግባራት ይህንን ስሜት ለማደፍረስ የሚጥሩትን በጋራ ልንታገላቸው ይገባል።

ሁለተኛ

ከእንግዲህ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም፤ አስፈፃሚም የለውም። ይህ አንድ ትልቅ ድል ነው፤ ሆኖም ህወሓት የአገዛዙ ወንበር ላይ እስካለ ድረስ ይህ ድል መሠረታዊ የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ አያመጣም። እስከ አሁን ከአንድ መቶ አምሳ በላይ ዜጎች ተገለውብናል፤ የሟቾች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረም ነው። ገዳዮች በመግደላቸው ሲሸለሙ እንጂ ሲጠየቁ አላየንም። በግልባጩ የሟች ቤተሰቦች የጥይት ወጪ ካልከፈላችሁ አስከሬን አንሰጥም እየተባሉ ነው።

ገዳይን እየሸለመ፤ ሟችን የሚቀጣ ኋላ-ቀር ፍርደ-ገምድል ሥርዓት ማብቃት ይኖርበታል። ስለሆነም የወቅቱ ጥያቄ መላዋን ኢትዮጵያ ከህወሓት አገዛዝ ነፃ ማውጣትን ዓላማው ያደረገ መሆን ይኖርበታል። “ኦሮሚያ አምባገነንነትን እንቢኝ ብላለች!” ከሚለው መሪ መፈክር “ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እንቢኝ ብላለች!” ወደሚለው መሪ መፈክር መሸጋገር ድላችንን ያቀርባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የወገኖቻችን ደም በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም፤ ገዳዮች በህግ ሊጠየቁና ሊቀጡ፣ ተበዳዮች ደግሞ ሊካሱ ይገባል ብሎ ያምናል። ሆኖም ህወሓት ስልጣን ላይ ሆኖ እያለ እነዚህ ነገሮች ሊፈፀሙ ይችላሉ ብሎ አያምንም። በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ኢትዮጵያ አምባገነንነትን አሻፈረኝ ብላለች፤ ይህም በሕዝባዊ እምቢተኝነት እና በሕዝባዊ አመፅ እየታየ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመፅ ሲደጋገፉ ባነሰ ኪሳራ አምባገነኑን አገዛዝ ከጫንቃችን ለማውረድ ያስችለናል ብሎ ያምናል። ስለሆነም ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እምቢ ትበል!

አንድነት ኃይል ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Tuesday, January 12, 2016

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ይመለከታል!

የንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት የትግል ጥሪ በ11ኛው ሰዓት ላይ እንደምንገኝ ገልጸዋል ። የ 11ኛው ሰዓት መልዕክት፣ አንደኛ፣ ወደ 12ኛው ሰዓት ወይም ወደ ፍጻሜው እየተቃረብን መሆኑን የሚነገረን ነው። የ11ኛው ሰዓት የትግል ጥሪ የአንድን የትግል ምዕራፍ ለመዝጋት እና አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሪው ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት ከአሁኑ ማሰብ መጀመር እንዳለብን የሚያነቃን ደወል ነው። 11ኛው ሰዓት ላይ ቆመን ከ12ኛው ሰዓት በሁዋላ ስለሚፈጠረው ነገር መጨነቅ ካልቻልንና በጊዜ ቤታችንን ካላሰናዳን ፣ ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ሊገጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶች በጊዜና ብቃት ባለው መልኩ ለመፍታት መቸገራችን አይቀርም ። አንድ በእድሜ የገፋ ሰው 11ኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ከህይወቱ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚኖረው ህይወት ማሰላሰሉ ተፈጥሯዊ ነው። የ11ኛው ሰዓት ጥሪም የአንድን አገዛዝ እርጅናና ፍጻሜ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ በቦታው የሚወለደውን አዲስ ስርዓት ምንነትም የሚያሳይ ነው።

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ ተደራሾች እነማን ናቸው? የጥሪው ተደራሾች በኢህአዴግ ዙሪያ የተሰባሰቡት እና እነዚህን ስብስቦች በማፍረስ አዲስ ስርዓት ለመገንባት የሚታገሉት የነጻነት ሃይሎች ሁሉ ናቸው። የ11ኛው ስዓት ጥሪ ለወያኔ ገዢዎች መገርጀፋቸውን የሚያረዳ የሞት ጥሪ ደወል ነው፤ ወደማትመለሱበት መቃብር ከመወርወራችሁ በፊት በቀራችሁ የአንድ ሰአት እድሜ አሟሟታችሁን አሳምሩ ብሎ የሚመክር ነው። በተለይ በጣት የሚቆጠሩ የሻገቱ ገዢዎችን ደግፋችሁ የቆማችሁ የመከላከያ፣የፖሊስና የደህነት አባላት አሰላለፋችሁን በጊዜ አስተካክሉ የሚል አርቆ ከማሰብ የመነጨ ምክር ነው ። የ11ኛው ሰዓት ጥሪ የሚመክር ብቻ ሳይሆን የሚያስጠነቅቅም ነው። ይህን የገረጀፈ አገዛዝ ደግፈው የቆሙ ሁሉ በጊዜ ከህዝብ ጋር እንዲታረቁ ይህ ካልሆነ ግን በመጨረሻው ሰዓት ከፍርድ እንደማያመልጡ የሚያስጠነቅቅ ነው። ካለፈው የሚመጣው ይበልጣል፤ ወያኔን ደግፋችሁ የቆማችሁ ሁሉ ያለፈ ጥፋታችሁን ለወደፊት በምትስሩት ስራ እንድትክሱ መልእክት ተላልፎላችሁዋል።

የ1ኛው ሰዓት ጥሪ የነጻነት ሃይሎች በአንድነት እንዲሰባሰቡና ትግሉን እንዲያቀጣጥሉም ያሳስባል። አገዛዙ 11ኛው ሰዓት ላይ ነው ማለት በራሱ ጊዜ ይወድቃል ማለት አይደለም። አገዛዙ ከደሃው በዘረፈው ገንዘብ ኪኒኖችን እየዋጠና ምርኩዞችን እየገዛ እድሜውን ሊያራዝም ይችላል። ከገፋነው በቀላሉ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ ዝም ካልነው ግን ድዱ ረግፎም በህይወት መቆየቱና ስቃያችን ማራዘሙ አይቀርም። እኛ በዘር፣ በጾታ፣ በትምህርት ወይም በሌሎች ጥቃቅን ነገሮች ሳንለያይ አንድ ሆነን ይህን የሻገተ አገዛዝ እንድናስወግድ ግልጽ ጥሪ ተላልፏል።

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ ያረጀውን ስርዓት ወደ መቃብሩ ከከተትነው በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት እንድናስብ የሚመክርም ነው። ዛሬ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንድንነጋገርና የነገውን ትልም እንድንተልም የሚጠይቅ ነው። አስቀድሞ በጋራ መተለሙ ነገ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ከመቀነሱም በላይ፣ የሻገተውን አገዛዝ በህብበረት ለመጣል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል። በጭሩ የ11ኛው ሰዓት ጥሪ ወያኔን ተባብሮ ለመቅበር ብቻ ሳይሆን፣ በመቃብሩ ላይ ስለሚተከለው አዲስ ችግኝ ለመነጋገር ጥሪ የሚያቀርብ ነው።

ሁላችንም የ11ኛውን ሰዓት ጥሪ ተቀብለን ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። ድሉ የሁላችንም ነው!

አርበኞች ግንቦት7!