Wednesday, November 6, 2013

በአዋሳ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ተወግቶ ተገድሎአል

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምሽቱ 7 አካባቢ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጀርባው አካባቢ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን ለማወቅ ተችሎአል። ግለሰቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛ ሳይሆን አይቀርም።
ግድያውን ማን እንደፈጸመውና ለምን እንደተፈጸመ የታወቀ ነገር የለም። የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን።

መከላከያ ኦዲት እንዳይደረግ የሚያስችል አዋጅ ተረቀቀ

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።
አዲሱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል ሲባል እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለጹ የማድረግ ስልጣን ተሰጥቶታል።
በአንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ሚኒስቴሩ ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ለአገር መከላከል ዓላማ የሚውሉ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በነጻ እንደሚያስገባ ተፈቅዶለታል። ዕቃዎቹን እንዲያስፈትሽ ወይም ሰነዶቹን እንዲያስመረምር እንደማይገደድም ተደንግጓል።
የመከላከያ ተቋማት በሠላም ጊዜ የሚኖራቸውን የማምረትና አገልግሎት የመስጠት አቅም ለገቢ ማስገኛ ተግባር እንዲውል በማድረግ የሚገኘውን ገቢ፣ ለመከላከያ ጠቀሜታ የማያስፈልጉ ንብረቶችን በማስወገድ የሚገኘው ገቢ፣ በተቆጣጣሪ ባለስልጣንነት ከሚመራቸው ድርጅቶች የሚገኘውን የትርፍ ድርሻ እና ከሠላም ማስከበር ስምሪቶች የሚገኘው ገቢ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ እንዲመረመር እንደሚያደርግ በረቂቅ አዋጁ መደንገጉን ጋዜጣው ዘግቧል።
የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ማጠናቀቂያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የ2004 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት መሰረት የመከላከያ ሚኒስቴር ባልተሟላ ሰነድ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ካደረጉ ዘጠኝ ያህል የመንግስት ተቋማት መካከል 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በማስመዝገብ የላቀ ድርሻ መያዙ ይፋ ከተደረገ በኋላ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ጨምሮ ሌሎች የመከላከያ ሹማምንት ሪፖርቱን ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ጋዜጣው አስታውሷል።
በህወሀት ታጋዮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሚኒስቴር ወጪውን በጄኔራል ኦዲተር እንዳይመረመር ለማስደረግ መቻሉ፣ በሚኒስቴሩ ውስጥ የሚታየውን ገደብ የለሽ የገንዘብ ዘረፋ እንደሚያባብሰው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ጸረ ሙስና ኮሚሽንም ደፍሮ መከላከያን እስካሁን ለመመርመር አልቻለም። አብዛኛዎቹ የህወሀት ጄኔራሎች በመከላከያ ስም ከቀረጽ ነጻ በሚያስገቡዋቸው እቃዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በሀብት ጣራ ላይ እንዲቀመጡ እንዳደረጋቸው ኢሳት መዘገቡ ይታወቃል።

መንግስት አገሪቱ በሽብር ጥቃት ኢላማ ውስጥ ገብታለች አለ

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሽብር ግብረሀይል  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላላፈው መልእክት አልሸባብና በኤርትራ የሚደገፉ ሀይሎች በመላው አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ብሎአል። ዜጎች እራሳቸውን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጿል።
ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፍተሻዎች ሲደረጉ የሰነበቱ ሲሆን፣ የትናንቱ ማስጠንቀቂያም ይህን ተከትሎ የተሰጠ ነው። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር ሀይሎች ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጅተዋል ቢልም እነዚህን ሀይሎች ከመዘርዝር ተቆጥቧል። መንግስት በኤርትራ የሚደፉ ሀይሎች ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው አላሳወቀም። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ አሸባሪዎች በማለት የፈረጃቸው ድርጅቶች  ግንቦት7፣ ኦነግና ኦብነግ  ናቸው። መግለጫውን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ኬላዎች ላይ ፍተሻ በመካሄድ ላይ ነው። መንግስት የሽብር ጥቃት አደጋ ተደቅኖብኛል ቢልም ከኢትዮጵያውያን በኩል የሚቀርበው ምላሽ ተቃራኒውን እየሆነ ነው። በማህበራዊ ድረገጾች የሚወጡ እንዲሁም ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች ፣ ” መንግስት ራሱ ፈርቶ ህዝቡን እያስፈራራ መሆኑን” የሚያመለክቱ ናቸው። ብዙ አስተያየት ሰጪዎች የመንግስትን ማስጠንቀቂያ አይቀበሉትም። አንዳንዶች ዜጎች ራሳቸውን ከመንግስት የተቀነባባረ የሽብር ጥቃት መጠበቅ እንዳለባቸው ይመክራሉ።የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ትናንት ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት የ2006 ዋነኛ አጀንዳው ኢትዮጵያን ከሽብር ጥቃት መከላከል መሆኑን አሳውቋል።

የእንግሊዝ ባንክና የሶማሊያ የገንዘብ መለወጫ

ዉጭ የሚኖሩ የሶማሊያ ተወላጆች ወደሀገራቸዉ ከፍተኛዉን የዉጭ ምንዛሪ እንደሚልኩ ይነገርላቸዋል። ሰሞኑን ግን ታዋቂዉ የብሪታንያ ባንክ ባርክሌ ከሶማሊያ ጋ መስራት አልፈልግም በማለቱ የሶማሊያዉያን ገንዘብ መለዋወጫ ባንኮች ችግር ገጥሟቸዋል።

ባንኩ ይህን የወሰነዉ በባንኩ የሚላከዉ ገንዘብ ለአሸባሪዎች መጠቀሚያ ይዉላል ከሚል ጥርጣሬ እንደሆነ ተገልጿል። ዘገባዎች እንደሚሉት ሶማሊያ ከአሜሪካ የሚሰጣትን የርዳታ ገንዘብ መጠን ያህል ገቢ በቀሪዉ ዓለም ከተበተኑት ከገዛ ዜጎቿ ታገኛለች። የተጠናከረ የመንግስት መዋቅርና የባንክ ስርዓት በሌለበት ይህን ያህል ገቢ የምታገኘዉ ጦርነት እና ግጭት ያመሳቀላት ሀገር የባርክሌ ባንክ ዉሳኔ ሊጎዳት እንደሚችል ነዉ የሚገመተዉ። ሕጋዊዉ የገንዘብ ማሸጋገሪያ መንገድ መስተጓጎል ለሕገወጥ የገንዘብ ዝዉዉር መንገድ ይከፍታል የሚሉ ወገኖች አሉ። ሆኖም ባንኩ ትናንት አዲስ ሃሳብ ብልጭ አድርጓል። ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ

የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ፤

November 6, 2013
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስናን አስመልክቶ ይሀ ለሰባተኛ ጊዜ ያቀረብኩት ትችት በማዕድኑ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በሙስና ላይ ያቀረብኳቸውን ሌሎችን ትችቶች “Al Mariam’s Commentaries” የሚለውን ድረ ገጽ በማየት ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ መዋቅራዊ ባህሪ እየያዘ በመጣው ዘርፈ ብዙ ሙስና ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ነቅቶ እንዲጠብቅ ለማስቻል በጉዳዩ ላይ አሁንም ትችቶቼን ቀጣይነት ባለው መልኩ አቀርባለሁ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ገዥው አስተዳደር የሕዝብ ትኩረትንና አድናቆትን ለማግኘት ሲል ጥቂት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣኖችና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ንክኪ አላቸው ባላቸው ጥቂት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ የሙስና ክስ በመመስረት የጸረ ሙስና ትግሉን በይፋ እንድታይለት ሰብስቦ በእስር ቤት አጉሮአቸዋል፡፡ እነዚህ በሙስና ተጠርጥረው በይስሙላው ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ቀርቦ እየተሰራ ያለው ድራማ ዓለም አቀፍ አበዳሪዎችና ለጋሽ ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት ግልጽነትና ተጣያቂነት ያለው ስርዓትን እንዲያሰፍን እያደረጉት ባለው ተጽዕኖ ምክንያት ለታይታ ያህል መንግስት የሚተገብረው የፖለቲካ ትወና ነው፡፡ ለአገር ውስጥ ህዝብ ፍጆታ ተብሎ ገዥው አስተዳደር እየተውነ ያለው ይህ የሙስና ድራማ ጥልቅና ስር ሰድዶ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተዋናይነት ተንሰራፍቶ ያለውን ከፍተኛ የህግ ልዕልና ሂደትን የሚጠይቀውን ያገጠጠና ያፈጠጠ ሙስና አሳንሶ በማቅረብ፤ የማታለል ዘዴ በመጠቀም እርባና የለሽና የጮሌነት ጭንብል በማጥለቅ ዋነኞቹን የሙስና ተዋናዮች ለመደበቅ የተዘየደ ተውኔት ነው፡፡

እውነታው ሲታይ ግን በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ያለው ሙስና እንዲህ በቀላሉ በጥቂት ታማኝ ያልሆኑና ህገወጥ በሆኑ ባለስልጣናት ጓደኞችና ተባባሪዎቻቸው አማካይነት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በሚገቡ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ በሚደረግ የሙስና መሞዳሞድ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ሙስና መዋቅራዊ ሲሆን፤ በመላ አገሪቱ የፖለቲካ ሰውነት ላይ በስፋት ተሰራጭቶ የሚገኝ ነቀርሳ ነው፡፡ በመሆኑም የዓለም ባንከ ያዘጋጀውን ትልቅ ሪፖርት “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ የሚል ርዕስ መስጠቱ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ይልቁንም እንዲህ በሚል ሊነበብ ይገባዋል “በኢትዮጵያ በስፋት እየተሰራጨ ያለውን የሙስና ነቀርሳ መመርመር“::

Ethiopia on heightened alert for attacks by Somali militants


By Aaron Maasho
ADDIS ABABA | Tue Nov 5, 2013 7:07pm GMT
(Reuters) - Ethiopia has put its police and security forces on heightened alert after receiving strong evidence that Somalia's Islamist al Shabaab group is planning attacks in the country, officials said on Tuesday.
The move came three weeks after officials said two Somali suicide bombers accidentally blew themselves up while preparing to kill football fans during Ethiopia's World Cup qualifying match against Nigeria.
Al Shabaab has vowed to exact revenge on Ethiopia for sending troops to Somalia to fight the al Qaeda-linked militants, alongside African Union forces from Uganda, Burundi and Kenya.
"There is strong evidence that indicates Al Shabaab and terrorist groups backed by Eritrea are preparing to carry out attacks in Addis Ababa and other areas of the country soon," the National Intelligence and Security Service (NISS) and the federal police said in a joint statement.
Addis Ababa often accuses the government in neighbouring Eritrea of supporting rebels, which Asmara staunchly denies.
The statement, read on state television, said security forces were already on heightened alert and called on the public to inform police if they encountered "suspicious" activity.
Hotel staff and private landlords should verify the identity of visitors, the statement said.
It urged soldiers to remain vigilant at checkpoints along the country's borders.
In September, al Shabaab gunmen raided an upmarket shopping mall in Nairobi, killing at least 67 people in a four-day siege.
Ethiopia says it has thwarted several attacks over the past two years which it blamed on domestic rebel groups as well as Somali insurgents.
However, it has so far been spared the sorts of assaults seen in nearby countries - such as the Nairobi mall siege and an attack that killed 74 football fans in Uganda as they watched the 2010 World Cup final on television.

Tuesday, November 5, 2013

የአንዷለም አራጌ መጻህፍ ዛሬ በገበያ ላይ ዋለ ቅምሻ በዳናኤል ተፈራ

ወጣቱ የነፃነት ሰላማዊ ታጋይ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ዋለ የፃፈው ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› ገበያ ላይ ዋለ፡፡ አንዷለም አርአያ ክብር ነው፡፡ ምሳሌና አርአያ ብናደርገው የምንጠቀምበት ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በቅርበት ስለማውቀው ብቻ እራሴን እንደ ዕድለኛ እቆጥራለሁ፡፡ ማርቲን ሉተር ኪነግንና ማህተመ ጋንዲን አንስቶ አይጠግብም፡፡ ስለፍቅር ሲል ሁሉን አሳልፎ መስጠት የሚችል፤ ስለ ኢትዮጵያ የሚሰስተው የሌለው ውድ ወጣት ነው፡፡ ለአላማው በፅናት መቆምን ተክኖበታል፡፡ እነሆ አሁን ደግሞ ጨለማው ሳይበግረው ያልተሄደበት መንገድን ሊያሳየን በመፅሐፍ መጣ፡፡ የማይበገር ራዕይ ያላቸው ሰዎች እንደዚህ ናቸው፡፡ እድለኛ ካልሆኑ በስተቀር እንደዚህ መሆን ከባድ ነው፡፡

ለቅምሻ ያህልም ከመግቢያው እነሆ ብያለሁ፡-

‹‹….መታሰር ነገሮችን በጽሞና ለማየት እድል ይሰጣል፡፡ በስራ የተጠመደ ሰው ነገሮችን በአንክሮ ለማሰብ የሚፈልገውን ያህል ጊዜ አያገኝም፡፡ ድንገት የሚከሰቱ ነገሮች ማእበል ከአንዱ ጉዳ ወደ ሌላው ያላጋዋል፡፡ እኔ አሁን ከእንዲህ አይነት ሁኔታ ነፃ ነኝ፡፡ስለዚህ ፍፁም አስቸጋሪ በሚባል ሁነታም ቢሆን በግፍ ከተለየሁት የኢትጵያ ህዝብ ጋር በሃሳብ ለመገናኘት መሞከር እንደሚገባኝ ወደንኩ፡፡ ጥረቴ የሚገትመው ፈተና በጣም አስቸጋሪ እንደነበር ግልፅ ነበር፡፡ በመሆኑም የሃገራችን አንዳንድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ነገሮችን አንስቼ ለመወያየት በማሰብ ‹‹ከዚህ ወዴት እንሄዳለን? ትላንት ዛሬና ነገ›› የሚል ርእስ መዘገብኩ እንደሃገር ካለፈው ይልቅ ስለሚመታው አብዝትን ልንጨነቅ እንደሚገባን ባምንም ያለፈውና አሁን ያለንበት ደግሞ ወደሚመጣው ዘመን የምንደርስበት ሜዳ በመሆኑ መዳሰስ ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ያለሁባት ክፍል እጅግ ጠባብ ከመሆኗ የተነሳ ስድስት ሆነን እግርና ጭንቅላታችንን ገጥመን ከዳር እስከዳር ሞልተናታል፡፡ መኝታውም መቀመጫውም ፍራሽ ነው፡፡ እጅና እግር ሲጠጋጉ የጠረጴዛና ወንበር ሚና ይጫወታሉ፤ እጅም የመፃፍ ስራውን ይሰራል፡፡ ለመቀመጥ አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ ግን የጀርባ ህመም ማስከተሉ አልቀረም፡፡ በዚህ ሁኔታ ለመፃፍ ሌሊቱን መጠቀም ነበረብኝ፡፡ ለምን ቢሉ እኔ ምን እንደምሰራ እንዲከታተሉ የተመደቡ ወንደሞች በመኖራቸው እነርሱም በማዳከም እንቅልፍ ባለውለታዬ ነው፡፡ ከጎኔ ተኝተው እንቅልፋቸውን ሲያጣጥሙ እኔ ደግሞ በሃሳብ ፈረስ ጋልቤ የምወዳት ሃገሬን የእስር ቤት አጥር ሳይገድበኝ እዞራታለሁ፡፡ በሃሳብ ዶሴዎቿን ከመሳቢያ እያወጣሁ አገላብጣለሁ፤ የሚመስሉኝን ሃሳቦች እሰነዝራለሁ፤ እፅፋለሁ፡፡

በዚህ ሁኔታ ሆኜ ወረቀትና ብእርን ማገናኘት ቀላል ባይሆንም ከሁሉ የሚያስቸግረው ግን ዋቢ መፅሃፍትን ሰብስቦ እያጣቀሱ በጥሩ ሁኔታ የተጠና መፅሃፍ ማዘጋጀት ነበር፡፡ መፅሃፍትን ማስገባት በጣም ከባድ ነው፡፡ ማስገባት ቢቻል እንኳን መፅሃፍቱን በሚገባ አመሳክሮና ጊዜ ወስዶ አንድ መፅሃፍ ማበርከት በጣም ከባድ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ሞልቷል፡፡ ነገርግን የሚፃፉ ፅሁፎች በየጊዜው በሚደረግ ፍተሻ ይወሰዳሉ፡፡ የዶ/ር ኪንግን መፅሃፍ ትርጉምን አጥቻለሁ፡፡ ሌላ ተመሳሳይ ችግር ደግሞ ማስተናገድ ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ከጊዜ ጋር የሚደረገው ግብግብም ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያዩ ምክንያቶች ዋቢ መፅሃፍትን ማመሳከር አለመቻሌን እንዳለመታደል እቆጥረዋለሁ፡፡ አንባቢም ይኸንን ውሱንነት እንዲረዳልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ በእርግጥ ያም ሆኖ እጄ ላይ ያሉ ውሱን መፃህፍትን ማገላበጥ ችለሁ፡፡

በመሆኑም ለመፃፍ እቅድ ማውጣት በንፅፅር ሲታይ ቀለል ቢልም በተለይ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሃሳብን አደራጅቶ ለመከራከር ብሎም ለመፃፍ መሞከር በጣም ከባድ ነበር፡፡ ፈጣሪ ፀጋውን አብዝቶልኝ ግን ለመፃፍ ሞክሬያለሁ፡፡ ለእኔ ትልቁ ቁምነገር በዚህ አይነት ሁኔታም ሆኜ ለሃገሬ ይበጃል የምለውን ነገር ሃሳቤን የመግለፅ ተጠቅሜ መፃፍ መቻሌ ነው፡፡እንደመሸበብ ክፉ ነገር ይኖር ይሆን?

በእኛ ሃገር የፖለቲካ ባህል ውስጥ ላደገ ሰው በግፍ ከሚስቱ፣ ከልጆቹና በዙርያው ካሉ ወዳጅ ዘመዶቹ ተለይቶ በወህኒ ቤት ሆኖ የጭቆናን ገፈት የሚጎነጭ ሰው ስሜታዊ እንደሚሆንና የመጠቃት ስሜትም ሊታይበት እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ከደረሰብኝ ነገር ሁሉ አንዳች ያልጠበኩት ነገር ባይኖርም አንዳንድ ጊዜ ስሜቴ መጎዳቱ አልቀረም፡፡ ስሜቴ በምፅፍበት ወቅትም ሚዛናዊ እንዳልሆን ይልቅስ ስሜቴን ብቻ እንደወረደ እንዳስተናግድ በተደጋጋሚ ቢፈትነኝም በተቻለኝ መጠን ፈተናውን ለማለፍ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ በግል በደል ወይንም ጥቅም ላይ ተመርኩዞ ከመፃፍ ይልቅ ለሁላችን የሚጠቅመውን በተለይም ከዛሬ ይልቅ ለነገ ይበጀናል የምለውን ሃሳብ ለማመላከት ሞክሬያለሁ፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሞት ለሁላችንም ማይቀር እዳ ነው፡፡ ከሞት በኋላም ግን ዛሬ ያላነሳነው አጀንዳና ያነገብነው እውነት በልጆቻችን ፊት መቅረቡ አይቀርም፡፡ ዛሬ የያዝነው ሃሳብ የጊዜን ፈተና አልፎ በትውልድ ፊት ሞገስ ቢያገኝ ፍሬም ቢያፈራ ትልቅ መታደል ነው፡፡ ስለዚህ በተቻለኝ መጠን ሚዛናዊ ለመሆን አቅሜ የፈቀደውን ጥረት አድርጌያለሁ፡፡

ከዚህ በተጓዳኝ ሌላም የሃሳብ ውጣ ውረድ ለማስተናገድ ተገድጃለሁ፡፡ እንደሚታወቀው የሃገራችን ፖለቲካ በብዙ መልኩ ጠርዝ የያዘ ነው፡፡ ሚዛናዊ ለመሆን ስሞክር በኢህአዴግ በኩል‹‹ ክንዳችንን አቀመስነው፣ አስተነፈስነው›› የሚል ስሌት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ በመገመቴ ይኼን አይነት ስሜት በማይፈጥር መልኩ ለመፃፍ መታገል ነበረብኝ፡፡ ይኼን ሳደርግ ደግሞ እኔም ደግሞ በቃራኒው ከእምነቴ ውጪ የሆነ ነገር እንዳላራምድ መጠንቀቅ ከባድ ኃላፊነት ነበር፡፡ በሌላ ወገን አንባቢ የተሳሳተ ግምት እንዳያድርበትም እንዲሁ መጠንቀቅ ነበረብኝ፡፡ በተቀውሞው ጎራ ያለው ወገን ደግሞ ‹‹ተሸጠ፣ተለወጠ፣ ከኢህአዴግ ጋር ተሞዳሞደና እጅመንሻ የውዳሴ መፅሃፍ ፃፈ›› የሚል የተሳሳተ ሃሳብ ውስጥ እንዳይገባ ለመጠንቀቅ ሞክሬያለሁ፡፡በእነዚህ ሁለት ፅንፎች ውስጥ ለማለፍ ስሞክር ማስተላለፍ የፈለኩትን መሰረታዊ ሃሳብና ልከተል የፈለኩትን የሃሳብ መስመር ላለመልቀቅ ተፍጨርጭሬያለሁ፡፡ እንዲህ አይነት የሃሳብ ማእበል ሲኖር ምንም ያህል ቢደከምም የሚፈለገውን ያህል ሌላውን ቀርቶ እራስንም ለማስደሰት ይከብዳል፡፡ ኃላፊነት ከባድ ነው፡፡ ሁላችንም ከልዩነቶቻችን ይልቅ ወደአንድነታችንና በጎ ነገሮቻችንን እንደናይ የሚያስችል ፅሁፍ ለመፃፍ ሞክሬያለሁ፡፡ ስሜቴ አሸንፎኝ ልዩነቶቻችንን የሚያሰፋ ጎዳና ተከትዬ ከሆነ አንባቢ እኔ ያልሄድኩበትን መንገድ እንዲሄድበት እጋብዛለሁ፡፡ ምናልባት በለስ ቀንቶኝ አንድነታችንን የሚያጠናክርና እራሳችንን እንድናርም፤ ያለመቆጠብ ወደ ውስጣችን እንድናይ፣ ልዩነቶቻችንም በሰከነ መንገድ ለመፍታት እንድንችል ሃሳብ ሰንዝሬ ከሆነ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ከተዘጋጀ መፅሃፍ ክፍተት አይጠፋምና አንባቢ ክፍተቶችን ለመሙላት ይሞክር፡፡ ውይይቱንም በማስፋት የተሸለና የተሞረደ ሃሳብ እንዲወለድ ሃገራችንም ከምትገኝበት አዘእቅት ውስጥ እንድትወጣ የበኩሉን አስተዋፅዎ ያድርግ ቢለዋ ከቢለዋ ሲፋጭ ስለት ይወጣዋልና፡፡››

source abugida