Wednesday, April 30, 2014

የኢህአዴግ መንግስት በሚቃወሙትና በሚተቹት ላይ እየወሰደ ያለውን አፈና እና እስር የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን!!!

April 29, 2014

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ፓርቲያችን አንድነት አበክሮ በተደጋጋሚ እንደገለፀው ኢህአዴግ ያነበረው አምባገን እና ክፉ ስርዓት ዜጎች በተለያየ ጊዜ የሚያነሱትን የሰብዓዊ መብት፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ የሚቀለብሰው ወታደራዊ አቅሙን በመጠቀም ነው፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ አካሄዱም ስርዓቱን ይቀናቀናሉ የሚላቸውን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎችና በግለሰብ ደረጃ ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎችን የተለያየ ስም እየሰጠ ወደ እስር ቤት አውርዷል፡፡ እያወረደም ይገኛል፡፡ በርካታ ዜጎች የአስከፊው ስርዓት ሰለባ ሆነዋል፣ እየሆኑም ነው፡፡ ሀገራችን በመነጋገርና በመደማመጥ ችግራችንን የምንፈታባት እንዳትሆን ሆን ተብሎ ለዘላለም መንገስ በሚፈልጉ ባለጊዜዎች የፊጥኝ ታስራ፤ ዜጎቿ እንደቀደመው ስርኣት ሁሉ በእስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡

እንደዜጋም በታላቋ ሀገራችን በሰቆቃ እንድንኖር ተፈርዶብናል፡፡ ኢህአዴግ ዛሬም ከመንገድ አፍሶ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ማሰቃየቱንና ማንከራተቱን ገፍቶበታል፡፡ ከጊዜና ሁኔታዎች እንደመማር ዛሬም ለስርዓቱ አደጋ ናቸው የተባሉ ወጣቶች ሰበብ እየተፈጠረ ወደ ማሰቃያ ስፍራ እየተጋዙ ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ አፈ-ቀላጤ በሆኑ ሚዲያዎች የታሰሩት ክስና ወደፊት የሚታሰሩት እነማን እንደሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ወጣት አመራሮቻችንና አባላትን የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራም ነው-ስራ ከሆነ፡፡

የኢህአዴግ መንግስት ሰሞኑንም በግል ተነሳሽነታቸው ለሀገራቸው አስተዋፅኦ ለማድረግ ወስነው በብዕራቸው የሰብኣዊ መብት እንዲከበርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲረጋገጥ በሚወተውቱ የነበሩ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደው የእስር ርምጃ የሚያመለክተው በቀጣዩ አመት የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ የተወሰደ የማሸማቀቅና የወጣቶችን ጥያቄ ለመቀልበስ የሚፈልገው የአምባገነኑ ስርዓት ተግባር ነው፡፡

ፓርቲያችን ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁትን ወጣት ጋዜጠኞች ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚሸረሽር እንደሆነ እናምናለን፡፡ አፈናው ግን ሌሎችን በሺዎች የሚቆጠሩ ብሎገሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንደሚፈጥር አንጠራጠርም፡፡

የኢህአዴግ መንግስት የከፈተው የእስር ርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆምና የታሰሩትም ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲጣራ፤ መንግስት ያሰረበትን ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡ ፓርቲያችን ዘላቂው መፍትሄ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል አፋፍሞ መቀጠልና በሰላማዊ ትግል አምባገነኑን ስርኣት ማስወገድ ብቻ እንደሆነ ያምናል፡፡

ድል የህዝብ ነው!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

ሚያዚያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም

አዲስ አበባ

በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የእስር እርምጃ እንዳሣሰበው ሲ.ፒ.ጄ ገለጸ።

ሚያዚያ ፳፩ (ሃያአንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለማቀፉ የጋሴጠኞች ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ)  ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን በ9 ጸሀፍያን ላይ የወሰደው የእስር እርምጃ፤ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ከተቃጡ የከፉ እርምጃዎች አንዱ ነው ብሏል።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን መግለጽን እንደወንጀል እየቆጠሩት ነው” በማለት ነው -የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪቃ ወኪል-ቶም ሩድስ-እርምጃውን የኮነኑት።
እሁድ ዕለት የመንግስት አቃቤ ህግ በ አዲስ ጉዳይ ዋና አዘጋጅ በ አስማማው ሀይለጊዮርጊስ፣ በፍሪላንስ ጋዜጠኞቹ በተስፋለም ወልደየስ እና በ ኤዶም ካሣዬ፣ እንዲሁም በጦማርያኑ በ አቤል ዋቤላ፣በ አጥናፍ ብርሀኔ፣በማህሌት ፋንታሁን፣ በዘላለም ክብረት እና በበፈቃዱ ሀይሉ ላይ  ከውጪ ድርጅቶች ጋር ይሠራሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀምም በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ይንቀሳቀሳሉ.. የሚል ክስ እንደመሰረተባቸው ሲፒጄ አውስቷል።
ተስፋለም፣አስማማውና ዘላለም ለፊታችን ሚያዚያ 28 ቀሪዎቹ ደግሞ ለሚያዚያ 29 እንደተቀጠሩ ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የደረሰውን መረጃ ዋቢ አድርጎ የጠቀሰው ሲፒጄ፤ በታሳሪዎቹ ላይ እስካሁን መደበኛ ክስ እንዳልተመሰረተ ጠቁሟል።
ሲፒጄ በመግለጫው-ፀሀፊዎቹ ዞን ዘጠኝ ተብሎ የሚጠራ የገለልተኛ አክቲቪስቶች ስብስብ አባል ሆነው የተለያዩ ዜናዎችንና ጽሑፎችን ይጽፉ እንደነበር  አመልክቷል።
“ዞን ሰጠኝ የተሰኘው ስያሜ ከቃሊቲ የተገኘ  መሆኑና  የጸሐፊዎቹ  መሪ ቃል፦”ስለሚያገባን እንጦምራለን” የሚል  መሆኑ በሲፒጄ መግለጫ ተመልክቷል።
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከደህንነቶች በሚደርስባቸው ወከባ ምክንያት ላለፉት ሰባት ወራት ዘግተውት የቆዩትን የፌስቡክ ገፃቸውን ዳግም በከፈቱ ማግስት መሆኑን እንደተረዳም የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ተቋሙ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ፦”የታሰሩት ጋዜጠኞች አይደሉም፤ እስሩ ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር የተገናኘ አይደለም። ከከባድ ወንጀል ጋር የተገናኘ ነው” ማለታቸውን ሲ.ፒ.ጄ ጠቁሟል።
“በጋዜጠኝነት ወይም ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ የቃጣነው በትር የለም። ሆኖም ማንም ቢሆን ሙያውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ለመፈፀም ሲሞክር በህግ ይጠየቃል” ሲሉም አክለዋል-አቶ ጌታቸው ረዳ።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደለየለት ፈላጪ ቆራጭ አገዛዝ  ማዘንበላቸውን እንዲገቱና በሀገሪቱ  ነፃ ሀሳቦች ይንሸራሸሩ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል-ሚስተር ቶም ሩድስ።
የታሰሩት 9ኙም ጸሀፊዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ድርጅቶችም የ ኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጦማርያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የወሰዱትን እርምጃ በማውገዝ ፤ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡት የ አሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ  እስረኞቹን እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
የተለያዩ ዓለማቀፍ የሚዲያ ተቋማትም ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በ9ኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደውን የማሰር እርምጃ ሽፋን ሰጥተውታል።
ከሚዲያ ተቋማቱ መካከል ኤ.ቢ.ሲ ኒውስ፣ ሲ ኤን.ኤን፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ሬውተርስ፣ እና አልጀዚራ ይገኙበታል።
እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በጉብኝታቸው ስለታሰሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አጠንክረው እንደተናገሩ  የኒውዮርክ ታይምሱ ታዋቂ አምደኛ  ኒኮላስ ክሪስቶች ለሰጣቸው አስተያዬት፤ “ በጣም  ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ዩናይትድስቴትስ  በመላው ዓለም ላይ የፕሬስ ነፃነትን በመደገፍና ከጥቃት በመከላከል ባላት ጠንካራ አቋም ትቆያለች” በማለት ምላሽ ሰጥተውታል።

Monday, April 28, 2014

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ዲስ ጉዳይ) ፖሊስ ለምርመራ 10 ቀናት ጠይቋል ባለፈው ሳምንት ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር
የዋሉት 3 ጋዜጠኞች እና 6 ብሎገሮች ዕሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን
ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በማዕከላዊ እስር ቤት የቆዩት ተጠርጣሪዎች ሰኞ ለፍርድ
እንደሚቀርቡ የተጠበቀ ቢሆንም ባልተለመደ ሁኔታ ዕሁድ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን የክሱም ሃሳብ በአጭሩ “ሀገሪቱን በሶሻል
ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሃሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና
ተስማምተው የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል” የሚል ነው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ተመሳሳይ
ክስ የቀረበባቸው
ቢሆንም በ3 የተለያዩ
መዝገቦች ተከፋፍለው
ነው ፍርድ ቤት
ቀረቡት፡፡ የአዲስጉዳይ
ጋዜጠኛ አስማማው
ኃይለጊዮርጊስ፣ የአምቦ
ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር
የሆነው ዘላለም ክብረት
እና የቀድሞው አዲስ ነገር
ጋዜጠኛና በአሁኑ ወቅት
በአዲስ ስታንዳርድ
መጽሔት ላይ የሚሰራው
ተስፋለም ወልደየስ
በመዝገብ ቁጥር
118722 የተጠቃለሉ ሲሆን፤ አጥናፉ ብርሃነ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና ኤዶም ካሣ በመዝገብ ቁጥር 118721 እንዲሁም በፍቃዱ
ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው።
በመዝገብ ቁጥር 118721 እና መዝገብ ቁጥር 118722 የተካተቱት ተጠርጣሪዎች ለሚያዝያ 29 ቀን 2006 ተቀጥረዋል።
ጉዳያቸው በመዝገብ ቁጥር 118720 የተካተተው ተጠርጣሪዎች ደግሞ ለሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓመተምህረት ተቀጥረዋል።

Sunday, April 27, 2014

የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ለማስፈራራት ሙከራ እያደረጉ ነው

ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው እሁድ በጃንሜዳ ለሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ቢሰጥም ፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር ፖሊሶች ህዝቡ በብዛት እንዳይገኝ ለማድረግ የማስፈራሪያ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ገልጿል።
ወጣት ብርሃኑ እንዳለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር በሰልፉ ላይ አንድም ነገር ቢከሰት እንዲሁም ከተሰጣችሁ ጊዜ አንድ ማይክሮ ሰከንድ ብታልፉ ሰልፉን እንበትናለን በማለት ለማስፈራራት ሞክረዋል።
ማስፈራሪያውን የሰጡት የፖሊስ አዛዡ በስም ይታወቁ እንዲሆን ጥያቄ የቀረበለት ወጣት ብርሃኑ፣ ኮሚሽነሩ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ በጠረጴዛው ላይ ባለማስቀመጡ ስሙን ለማወቅ እንዳልተቻለ፣ ነገር ግን ቢሮው ውስጥ አብረው የነበሩትን ኮሚሽነር እንደሚያውቃቸው ገልጿል
ቅስቀሳው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ና የህዝቡም ማበረታቻ ጥሩ መሆኑን  የገለጸው ወጣት ብርሃኑ ፣ ነገር ግን  በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 25 አባሎቻቸው ታስረው እስካሁን አለመፈታታቸውን ገልጿል።
ወጣት ብርሃኑ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ግብ ሳይሆን ወደ ቀጣዩ ትግል መሸጋገሪያ መሆኑን ገልጾ ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን ያሰማል ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በደረሰን ዜና ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትሉ አቶ ስለሺ ፈይሳ እና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በፖሊስ ተይዘው ወደ እስር ቤት ተጉዘዋል። ወደ እስር ቤት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ኢንጂነር ይልቃልን አነጋግረነው ነበር።

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ፣ የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡

April 26, 2014

ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7 ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ ናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ ማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡

ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Thursday, April 24, 2014

ሰበር ዜና፣ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ማሰሩን ቀጥሏል

April 24, 2014

በዳንኤል ሃረጋዊ

ፖሊስ ቀስቃሾቹን እያሰረ ነው ፖሊስ የእውቅናው ደብዳቤ አልደረሰኝም በሚል በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ቅስቀሳ ላይ የተሰማሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እያሰረ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ቀስቃሾቹ ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የሚያመለክተውን ወረቀት ለፖሊስ ቢያሳዩም ፖሊሶች የእውቅናው ደብዳቡ አልደረሰንም በሚል አስረዋቸዋል፡፡ ቀስቃሾቹ የያዙት የእውቅና ደብዳቤ ግልባጭ ለፖሊስ የተጻፈበት በመሆኑ ሰልፉ እውቅና አግኝቶ እያለ ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ እንደሆነ ምክትር ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ገልፀዋል፡፡

በላም በረት፣ ቦሌ ድልድይ፣ ኮተቤ፣ መገናኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ቅስቀሳቸውን በተሳካ መልኩ አጠናቀዋል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የተሰማሩት አባላት ቅስቀሳውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በሌላ በኩል በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬን ጨምሮ በሌሎች የከተማይቱ ክፍሎች ፖሊስ ከ20 በላይ አባላትን ማሰሩ ታውቋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ፖሊስ ቅስቀሳው ላይ ያልነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው፡፡ የታሰሩትን አባላትና ደጋፊዎች ሁኔታ ለማጣራት ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡

በዛሬው ቀን ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት

1. ብሌን መስፍን
2. አስናቀ በቀለ
3. መስፍን
4. ተስፋዬ አሻግሬ
5. እዮብ ማሞ
6. ኩራባቸው
7. ተዋቸው ዳምጤ

የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች

1. ፍቅረ ማሪያም አስማማው
2. እያስፔድ ተስፋዬ
3. ጋሻው መርሻ
4. ተስፋዬ መርኔ
5. ሀብታሜ ደመቀ
6. ዘሪሁን ተስፋዬ
7. ጌታነህ ባልቻ
8. ንግስት ወንዲፍራው
9. ሜሪን አለማየሁ ናቸው

የካ አካባቢ ታስረው የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ምግብ እንዳይገባላቸው ተከልክለዋል፡፡ በሌላ በኩል አህመድ መሃመድ፣ሀይለማሪያም፣ ሱራፌልና አምሃ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መገናኛ አካባቢ ተይዘው ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ተዘዋውረዋል፡፡ በአጠቃላይ የካ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት 14 መሆናቸው ታውቋል፡፡ በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙት አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ቃል እየሰጡ ሲሆን ሊያድሩ እንደሚችሉም ተነግሯቸዋል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቢሮ ተደውሎ የሰላማዊ ሰልፉን አስተባባሪዎች ጧት ሁለት ሰዓት ላይ ‹‹ኑ እና እንነጋገር!›› የሚል ጥሪ አድርጓል፡፡ ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ጌታነህ ባልቻ ታስሮ ይገኛል፡፡

Tuesday, April 22, 2014

የኢሳትየድጋፍኮሚቴበኖርዌይየባንክሒሳብቁጥርከፈተ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳትኖርዌይየድጋፍኮሚቴ፤በኦስሎናበተለያዩአካባቢዎችኢሳትን  ለማጠናከርናየአቅማቸውንለማበርከትለሚተጉየኢሳትደጋፊዎችናቤተሰቦች፤በያሉበትቀላልእናአመቺየሆነውንየአከፋፈልመንገድይጠቀሙዘንድበማሰብ፤በኖርዌይኦስሎበኢሳትስም  የባንክሒሳብቁጥርመክፈቱንበደስታገልጿል።
በተለያየምክንያትየባንክሒሳብቁጥራችንለመጠቀምሁኔታዎችየማያመቿችሁየኢሳትደጋፊዎችለዚሁበተዘጋጁየገነዘብመቀበያደረሰኞችበመጠቀምኢሳትንበመደገፍለድምፅአልባወገንዎድምፅ እንዲሆኑ ኮሚቴው አስታውቋል። የሂሳብ ቁጥሩን በድረገጻችን የምታገኙት መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን።
የባንክ ሒሳብ ቁጥር
DNB 1503 462 8537
Oslo Norway ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ ፦ 452 06 390 / 947 11 734  ይደውሉ ።
የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ በኖርዌይ