(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት ተላላኪ ሆኖ በርካታ በደሎችን በህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ ታወቀ፡፡
ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች የተገደለው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አባል የነበረና በድርጅቱም ግዳጅ በመላክ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ አብሮት ሲሄድ የነበረውን የትግል ጓዱንና ድርጅቱን በመካድ የጠላት ተባባሪ በመሆን በታጠቀው የድርጅቱ መሳሪያ ጓዱን በመግደል ለወያኔ ስርዓት እጁን በመስጠት ተቀላቅሏል፡፡ ከአገዛዙ ተቀላቅሎ በመኖር ላይ እያለም ከአንድ የስርዓቱ አገልጋይ ጓደኛው ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን ይደግፋሉ እንዲሁም በገዢው ቡድን ላይ ህዝብን ያሳምፃሉ ብለው የሚፈርጇቸውን ሰዎች እንዲሰልሉ በአገዛዙ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም ከእለታ አንድ ቀን ሰው በመግደል ታስረው የቆዩ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያትም ብዙም ሳይቆዩ ከእስራት ተፈተዋል፡፡ ይኸው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ ከእስራት ከተለቀቀ በኋላም ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሆን በአሳቻ ሰዓትና በማታ ንፁሃን ዜጎችን በማደን ሲያሳስርና ሲያስደበድብ በተጨማሪም ሲያስገድል መቆየቱን የአካባቢው ህዝብ የአይን ምስክሮች ናቸው ፡፡
በመሆኑም ይህን የህዝብ ሰቆቃ ሰምቶ መታገስ ህሊናቸው ያልፈቀደላቸው በአርበኞች ግንት 7 ስር በሃገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የውስጥ አርበኞች በዚሁ ደረጄ መከታው በተባለው ግለሰብ ህዝብ የሚደርስበትን በደልና ይኸው ግለሰብ ለወያኔ መላላክን ምርጫው ያደረገ በንፁሃን ዜጋ ሞት የሚደሰት መሆኑን በመመልከታቸው የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ተከታትለው ሊገድሉት ችለዋል ፡፡
አሁንም በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ከህዝብ ጎን መቆም ሲገባቸው ለጥቅም ያደሩ ግለሰቦች መለስ ብለው መሳሳታቸውን አምነው ከህዝብ ጎን ካልተሰለፉና የህዝቡን ትግል ካልደገፉ ወይም ከቀደመው እኩይ ተግባራቸው ተቆጥበው ማሳሰራቸውንና ማስደብደባቸውን እስካላቆሙ ድረስ በሰላም መኖር እንደማይችሉና የእነርሱም እጣ ፈንታ እንደ ደረጄ መከታው እንደሚሆን የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ከሃገር ቤት ባደረሱን መረጃ አስታውቀዋል ፡፡
Monday, February 20, 2017
በህወሓት የበላይነት ስር የሚገኘው የኣገር መከላከያ ሠራዊት ከ25 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ
(በአርበኞች ግንቦት 7 ጥናትና ምርምር ቡድን የተዘጀ)
ታህሳስ 2009 ዓ.ም.
የመከላለያ አዛዞች የብሄር ስብጥር ጥናት ውጤት ታህሳስ 2009 (PDF)
መግቢያ
የዛሬ ሰባት አመት (እ.ኤአ. 2009) ያኔ “ግንቦት 7- የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ” ይባል የነበረውና አሁን አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ውስጥ የተጠቃለለው ድርጅት በዘር የተደራጀዉን የወያኔ መከላከያ ተቋም አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ብሎም ለዓለም ማኅበረሰብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ያ ጥናታዊ ሪፓርት ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብም ቀርቶ አገዛዙን ትዝብት ላይ በመጣሉ “የመካከያ ሠራዊታችንን ብሄራዊ ተዋጽዖ እናመጣጠንን ነው” የሚል ፕሮፖጋንዳ የወያኔ ኣገዛዝ መንዛት ተጀመረ።
በዝቅተኛና በተራ ውትድርና ደረጃ መመጣጠን መኖሩ ድሮም ጥያቄ ተነስቶበት አያውቅም። ድሮም አሁንም ጥያቄው ያለው በሠራዊቱ አመራር ላይ ያሉት እነማን ናቸው የሚለው ላይ ነው። በዚህ ረገድ በእርግጥ እንደሚባለው ለውጥ አለን? ይህ ጽሁፍ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የተደረገ ጥናት ውጤት ነው።
የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው የአገዛዙ ሠራዊት አመራሮች የብሄር ተዋጽዖ በተመለከተ ዛሬ ሰባት ዓመት ከነበረው እጅግም የተሻለ ነገር የለም። በህወሓት ስር የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላም 6% ብቻ የሆነውን የትግራይን ሕዝብን አንወክለዋለን በማለት በሚነግዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች የበላይ ኃላፊነት፣ እዝና ቁጥጥር ስር ወድቆ እናገኛለን። ይህ ጥናት እንደሚያሳየው የኣሮሞና የኣማራ ብሄሮችም ሆኑ ሌሎችሁ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በመከላከያ ሠራዊቱ የኃላፊነትና የእዝ ቦታዎች ላይ እጅግ ዝቅተኛ ወይንም ከነኣካቴው ምንም እይነት የኃላፊነት ድርሻ የላቸውም። ይህ ያገጠጠ ኢ-ፍትሃዊነት ኣንድምታው ህሊና ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ምን ማለት መሆኑ ግልጽ ነው ብለን እንገምታለን። ዛሬም እንደትናቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ ለፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐት ብቸኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችለዉ በቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነጮች ፈጥረውት የነበረው ዘረኛ (Apartheid) ስርዐት ብቻ ነዉ።
በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ በተለይ በቁጥሩ ከፍተኛ ብልጫ ያለዉና ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነዉ ሠራዊት እጅግ ያኮረፈ፤ የተቆጣና ያመረረ ሠራዊት ከመሆኑ የተነሳ እራሱን የሚመለከተዉ እንደ አገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆን አንደ ህወሓት የቤት ዉስጥ አገልጋይ ባሪያ ነዉ። ይህ የህወሓት ዘረኞች በሠራዊቱ ላይ የፈጠሩት የመገዛትና የበታችነት ስሜት በየቀኑ ከፍተኛ ቁጣና የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ የሚገጥመዉ ቢሆንም ህወሓት በዘረጋዉ ከፍተኛ የአፈና መረብ የተነሳ የሕዝብ መነጋገሪያ አርዕስት መሆን አልቻለም። የህወሓት መሪዎችም ቢሆኑ ይህንን ቁጣና ተቃዉሞ በሚገባ ስለሚያዉቁ “ግምገማ” እያሉ በሚያዘጋጇቸዉ መድረኮች ላይ እንደነዚህ አይነቶቹን የህወሓትን የበላይነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማስተናገድ ቀርቶ ጥያቄዎቹ እንዲነሱም አይፈቅዱም። አንዳንዴ ደፍረዉ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሱ ግለሰቦች ሽብርተኛ፤ የደርግ ስርዐት ናፋቂዎች፤ ጠባብ ብሄረተኞች ወይም የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች የሚል ተቀጥላ ስም ይሰጣቸዋል። ዛሬ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዉ በተለያዩ የወያኔ እስር ቤቶች ዉስጥ የሚሰቃዩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የበቁት በመከላከያ ተቋሞች ዉስጥ ሠራዊቱን በዬትኛዉም እርከን የሚመሩ መኮንኖች አመዳደብ ወታደራዊ አመራር ችሎታን፤ ልምድንና የብሄር ስብጥርን ያካተተ መሆን አለበት ብለዉ ደፍረዉ በመናገራቸዉ ነዉ።

የአፈናውና ሰቆቃው መጠናከር ለነጻነታችን ከምናደርገው ትግል አይገታንም።
የመንግሥትን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ሃይል ተቆጣጥረው ያሉት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ላለፉት 25 አመታት በህዝባችን ላይ ተንሰራፍተው የዘረፉት የአገር ሃብት ፤ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በየባንኩ ያከማቹት ጥሬ ገንዘብና በዘመድ አዝማዶቻቸው ሥም እዚህና እዚያ የዘረጉዋቸው የንግድ ድርጅቶች ብዛት እንዲሁም ያለዕውቀታቸውና ልምዳቸው ለሩብ አመታት ሲሿሿሙበት የኖሩት ሹመትና ማዕረግ አሁንም ቢሆን በቃኝ ከሚሉበት ደረጃ እንዳላደረሳቸው ሥልጣንን በሰላማዊ መንገድ እንዲያስረክቡ የተቃውሞ ድምጻቸውን በሚያሰሙ ወገኖቻችን ላይ እየወሰዱት ካለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መረዳት ይቻላል።
በአንድ ወቅት አገሪቱ ውስጥ ሰፍኖ የኖረው አስተዳደራዊ በደል የፈጠረው ህዝባዊ ብሶት ብረት እንዲያነሱ እንዳደረጋቸው በኩራት በመደስኮር ገድላቸውን በታሪክ መዝገብ ላይ ለማስፈር ደፋ ቀና እያሉ ያሉ እነዚህ ሃይሎች፡ አስመርሮናል ብለው መሳሪያ ካነሱበት ሥርዓት የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ ፤ በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የአገር ሃብት ዘረፋ ተግባር ላይ በጅምላ ተሰማርተው ሃብት ሲያካብቱ ፤ በአገሪቱ ባህልና ወግ የገዘፈ ልዕልናና ክብር የነበረውን የህግ የበላይነት ባህል አጥፍተውና በራሳቸው ተጽፎ የጸደቀውን ህገ መንግሥት ተላልፈው በጠራራ ጸሃይ ብዙዎችን ጎዳና ላይ ሲጨፈጭፉ፤ ሲያስሩና ሲያንገላቱ ፤ ከአያት ቅድመ አያቱ ጀምሮ እትብቱ ከተቀበረበት ቀዬ ሺዎችን አፈናቅለው መሬቱን ሲቀራመቱና ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ለባዕዳን በርካሽ ዋጋ በመቸብቸብ ለጎዳና ተዳዳሪነት ሲዳርጉት ከማየት የበለጠ ወንጀልና ህሊናን የሚያቆስል ኢፍትሃዊነት በዚህች ምድር አይኖርም።
ይህ ሁሉ ግፍና መከራ እየተፈራረቀበት ያለውን ህዝብ በትግላችን ውጤት ፍትህና ርትዕ አቀዳጅተንሃል፤ በብሄር ማንነትህና በምትናገረው ቋንቋ እንድትኮራ አድርገንሃል፤ ተገፍተህባት የኖርክባት አገር ባለቤት እንድትሆን አስችለንሃል ፤ዲሞክራሲን በአገራችን እውን በማድረግ በየ5 አመቱ በምትመርጠው መንግሥት የምትተዳደርበት ሥርዓት ዘርግተንልሃል ፤ ደሃውን ህዝብ ተጠቃሚ ያደረገ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በማውጣት በምድራችን ፈጣን የሆነ ልማትና ዕድገት አስገኝተንልሃል፤ በዚህም የተነሳ ከኖርክበት ረሃብና እርዛት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን በአጭር ግዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ልናሰልፍህ ነው ፤ ወዘተ እያሉ ሲያላግጡበትና ሲዘባበቱበት ማየት እጅግ የሚያሳምም ነው።
ላለፈው አንድ አመት አገሪቷ ውስጥ እጅግ ተጠናክሮ የቀጠለውና ወያኔ በፈረጠመ ክንዱ ለመጨፍለቅ ያለ የሌለ ሃይሉን ለመጠቀም ደፋ ቀና እያለ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት መሠረቱ ይህ ለሩብ አመታት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ተንሰራፍቶ የቆየውን ኢፍትሃዊነት፤ አፈናና ጭቆና ከህዝባችን ጫንቃ አሽቀንጥሮ ለመጣል የሚደረግ የነጻነት ትግል ነው። ይህንን ትግል ለማፈን ህወሃት ከአለም አቀፍ ለጋሽ አገሮች በተሰበሰበ ገንዘብ ከምዕራባዊያን ወዳጆቹ፤ ከራሺያና ከቻይና የፈለገውን ዘመናዊ የጦር መሣሪያ በግዢ ቢያግበሰብስ፤ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የተቀጠረ እልፍ አእላፍ የአጋዚ ወታደርና ልዩ ጦር በየመንደሩ ተሰማርቶ የታዘዘውን ያህል አፈና፤ ግዲያና እስራቱን ቢያጧጡፍ የሚቻል አይሆንም። በገዛ አገራችን እንደሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠርን ከሥራ ፤ ከመኖሪያ ቀያችንና ከትውልድ መንደራችን መፈናቀል ሰልችቶናል። ልጆቻችን በገዛ አገራቸው ተስፋ ቆርጠው እንጀራ ፍለጋ በረሃ ሲያቋርጡ በጨካኞች እጅ እየወደቁ በአክራሪዎች ሰይፍ እንደከብት መታረዳቸውን ማስቆም ከኛ ውጪ ለሌላ ለማንም የተሰጠ ሃላፊነት አይደለም። ከአሁን ቦኋላ የአገራችን የኢትዮጵያ ምድር የሚቆረቆሩላትን ልጆቿን እየቀበረች የጠላትን ህልም ለማሳካት ሊያጠፏት ሌት ተቀን የሚማስኑ ባንዳ ልጆቿን እሽሩሩ የምትልበት ዘመን ማብቃት ይኖርበታል።
አርበኞች ግንቦት 7 የህወሃት አገዛዝ ህዝባችንን በቋንቋና በዘር ከፋፍሎ እርስ በርሱ በማናከስ ለዘመናት የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ሲሰራው የነበረው የተንኮል ሴራ ሁሉ ከሽፎአል ብሎ ያምናል። የጎንደርና የባህርዳር ህዝብ ባሰማው ተቃውሞ በህወሃት አልሞ ተኳሾች ጥይት የሚሞተው ኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው ሲል በአርሲ፤ በቢሾፍቱ፤ በደምቢዶሎና በተለያየ የኦሮሚያ ክልል የሚኖረው ህዝብ አማራ ወገናችን ነው ከአሁን ቦኋላ እትለያዩንም፤ አንድ ነን ሲል ድምጹን ከፍ አድርጎ አሰምቷል። ይህ የወንድማማችነትና የአንድነት መንፈስ ህወሃትን ያሸብረዋል ብቻ ሳይሆን እንዳበደች ውሻ ያቁነጠንጠዋል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ የህወሃት ወታደራዊ መኮንኖች ሥልጣን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉበት የኮማንድ ፖስት የተቋቋመው ይህ የወንድማማችነትና የአንድነት መንፈስ ሊፈጥረው የሚችለውን ህብረት በጠመንጃ ሃይል ከወዲሁ ለመቅጨት ነው። በመላው አገሪቱ በተለይም በአማራ፤ በኦሮሚያና በኮንሶ በርካታ ሺዎችን ሰብስቦ በማጎር ፤ የታሠሩትን በጉልበት ወይም በጊዜያዊ ጥቅም በመደለል ቅስም መሥበር በስፋት የተያያዘውም የህብረትና የአንድነት ድምጽ ጎልቶ መሰማት ከጀመረ ወዲህ መሆኑ ግልጽ ነው። ከአንድ ወር የጅምላ እስር ቦኋላ ሰሞኑን የተለቀቁ 9 ሺህ ለውጥ ፈላጊዎችን “አይደገምም” የሚል ጽሁፍ የተጻፈበት ነጭ ካናቴራ ማልበስ በህወሃት ቤት ማሸማቀቅ ነው። ካለፈው ስህተቱ መማር ያልፈጠረበት ወያኔ በምርጫ 97 የንብ አርማ አልብሶ ለድጋፍ ሰልፍ መስቀል አደባባይ ያወጣው በሚሊዮን የሚቆጠር የአዲስ አበባ ህዝብ በማግሥቱ ካናቴራውን እንደለበሰ ለቅንጅት ሰልፍ ወጥቶ ጉድ እንዳደረገው ዘንግቶታል። ጮማና ውስኪ አዕምሮአቸውን ለሸፈናቸው ኋላ ቀር የህወሃት አመራሮች “አይደገምም” የሚል ካናቴራ በማልበስ ወደየቤታቸው ለሸኟቸው ታሳሪዎች ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ ያሳየው ድጋፍና ደማቅ አቀባበል ሚያዚያ 30,1997 ቀንን የደገመ ትዕይንት መሆኑን እንዲረዱ አያስችላቸውም።
ህወሃት ህዝባችን ለነጸነቱ የሚያካሂደውን ትግል ለመቀልበስ የፈለገውን ያህል ጉልበት ለመጠቀም ቢፍጨረጨር ፤ እስር ግድያና የማሳደድ ተግባሩን አጠናክሮ ቢቀጥል ከህዝባችን ልብ የበለጠ እየራቀ፤ የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚቀሰቅስ ወኔ ለምናካሄደው ትግል ይፈጥር እንደሆነ እንጂ ከጀመርነው የነጻነት ትግል ወደ ኋላ እንደማይገታን አርበኞች ግንቦት 7 በጽናት ያምናል። ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነበት አገር ባለቤት ለመሆን የጀመርነው ትግል የፈለገውን ዋጋ ቢያስከፍለንም በድል ይጠናቀቃል። ለዕለት ጉርሳቸው ሲሉ በውትድርና ተቀጥረው ለህወሃት የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ውድ ህይወታቸውን እየገበሩ ያሉ ምስኪን ወገኖቻችን እየተካሄደ ያለው ትግል ለነርሱም ነጻነት መሆኑን ተረድተው የያዙትን መሣሪያ የደሃውን ልጅ እየገደሉና እያስገደሉ የማይጠረቃ የሃብት ዘረፋ ጥማታቸውን ለመወጣት በሚያዘምቷቸው አለቆቻቸው ላይ እንዲያዞሩና ትግሉንም እንዲቀላቀሉ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Thursday, November 10, 2016
የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ሀገር ሠላማዊ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ሠዎችን ቤተሠቦች አስሯል ሲል የመብት ድርጅቱ ሒውማን ራይትስ ወች አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መንግስት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል። በተለያዩ የውጭ ሃገራት ወያኔን በከፍተኛ ደረጃ በመቃወም ወደ አደባባይ የሚወጡትን ኢትዮጵያውን ማሰርና ማፈን ቢያቅተው በኢትዮጵያ የሚኖሩትን ቤተሰቦቻቸውን ማሰር እንደጀመረ የሰብአዊ መብት ድርጅት (Human Rights Watch)በ 27 ጥቅምት 2009ዓም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በአውስትራሊያ ሜልቦርን በሰኔ 2008ዓም የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርና የዚህ ክልል ተወካይ ያካተተ ቡድን ወደ አውስትራሊያ ሊያደርገውን ያቀደውን የስራ ጉብኝት በመቃወም ኢትዮጵያውያን በሜልቦርን አደባባይ ለሰልፍ ወጥተው ነበር። በዚህ ከፍተኛ ተቋውሞ ምክንያት ይህ የስራ ጉብኝት ተስተጋጉላል። በዚህ ሰልፍ ላይ የተገኙ የወያኔ ቅጥረኞች ፎቶ በማንሳት ለወያኔ በማቀበል የእነዚህን ኢትዮጵያውያንን ቤተሰቦች ለእስር እንዲዳረጉ አድርገዋል።
ቪኦኤ በዜናው ሽፋኑ የሰብአዊ የመብት ድርጅቱ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በአውስትራሊያ በሰኔ ወር ሠላማዊ ሠልፍ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊ በዕድሜ የገፉ ወላጅ እናት እንደሚገኙበትም ታውቋል።
የዚህ ግለሰብ ሶስት ወንድሞችም የደረሱበት መጥፋቱን የመብት ድርጅቱ ዘግቧል።
የ25 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሹክሪ ሻሃፌ ጉሌድ ተወልደው ያደጉት በሶማሊያ ክልል ሲሆን በአውስትራሊያ ለአለፉት ስድሥት ዓመታት ኖረዋል፤ በአለፈው ሰኔ ወር ሜልበርን አውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐሙድ ኡማር በቅፅል ስማቸው አብዲ ኢሌ ተብለው የሚታወቁት በጎበኙበት ወቅት ተቃውሞ መግለፃቸውን ይናገራሉ፡፡
የወያኔን አገዛዝና ወያኔን በመቃወም ከአውስትራሊያ በተጨማሪ በአውሮፓ በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ከፍተኝ ሰልፎች በማድረግ ድምጹን በነጻነት በኢትዮጵያ ውስጥ ማሰማት ላልቻለው ጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ አንደበት በመሆን ይገኛሉ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመረቀ
የኢትዮጵያን ህዝብ ከጭቆናና የስቃይ ህይወት ለማላቀቅ እና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ገርስሶ ለመጣል የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ለወራት ያክል በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ተጓዳኝ ትምህርቶች ዙሪያ ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ምልምል አርበኛ ታጋዮች እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል ፡፡
በዚህም የምረቃ ስነ-ስርዓት በዓል ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ግዳጅና ሃላፊነት ስለሚጠብቀን በምትመደቡበት ቦታ ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ሃገራዊና ድርጅታዊ ግዴታችሁን ለመወጣት በወታደራዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ሰራዊት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ለተቀደሰ አላማ መከፈል ያለበትን የህይወት መሰዋዕትነት ለመክፈልና የኢትዮጵያን ህዝብ ከባርነት ህይወትና ከጭቆና ለማላቀቅ በሚደረገው የትጥቅ ትግል የበኩላችሁን ድርሻ መወጣት ይጠበቅባችኋል በማለትና አጠቃላይ የስልጠናውን ሂደት የሚመለከት ሪፖርታቸውን አሰምተዋል፡፡
በዚህ የምረቃ በዓል ላይ ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእጅ በእጅ ውጊያን ጨምሮ የተለያዩ ትርኢቶችን በማሳየት ለበዓሉ ድምቀት ሰተውት የነበረ ሲሆን በተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የቀረቡ ስነ-ፅሁፎችና መነባንቦች እንዲሁም አዝናኝና ትምህርት ሰጪ ድራማዎችም ልዩ ትኩረት የሳቡ እንደነበርና በቦታው የተገኙትንም ተጋባዥ እንግዶች አስደምመውት ውለዋል፡፡

Friday, November 4, 2016
በህዝባችን የነጻነት ተጋድሎ እየኮራን ለመጨረሻው ድል ታጥቀን እንነሳ!
በኦሮምያ እና በአማራ የተለያዩ ከተሞች የሚካሄደው የነጻነት ትግል በእጅጉ አስደማሚ ነው። ባለፉት ሳምንታት በጎንደርና በባህርዳር ለስድስት ቀናት እንዲሁም በተለያዩ የሰሜን ጎንደርና የምዕራብ ጎጃም ከተሞች የተደረገው የስራ ማቆም አድማ በአገራችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያልታየ ወደር የለሽ ተግባር ነው። ህዝቡ የስራ ማቆም አድማ ያደረገው የሚበላውና የሚጠጣው ተርፎት እንዳልሆነ ይታወቃል። እንዲያውም በአገሪቱ የሰፈነው አስከፊ ድህነትና የኑሮ ውድነት እንኳንስ ስራ ተፈትቶ፣ 24 ሰአታት ቢሰራም የሚቋቋሙት እንዳልሆነ እናውቃለን። ነገር ግን ህዝቡ፣ ረሃቡንና ጥማቱን ለሳምንታት ችሎ የአድማውን ጥሪ ተግባራዊ አድርጓል። ይህ ምን ይነግረናል? በቅድሚያ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳልነው ህዝቡ በዚህ ዘረኛና አፋኝ አገዛዝ መንገሽገሹን ያሳየበት ነው፤ “ልማቱ ተስፋፍቷል፣ ህዝቡም የደስታና የምቾች ኑሮ መኖር ጀምሯል” እያሉ በድህነቱና በብሶቱ ሲሳለቁበት ለቆዩት እውነተኛ ኑሮውን አሳይቷቸዋል። ይህንኑ ፕሮፓጋንዳ አምነው በመቀበል ወሬውን ሲያራግቡ ለነበሩ የአገር ውስጥና የውጭ የአገዛዙ ጠበቃዎች ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል ።
እንዲሁም አገዛዙን ለማስወገድ ህዝቡ ማንኛውንም አይነት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያሳየበት ነው። ረሃብና ጥማቱን ችሎ ከውስጡ የተጣበቀውን አለቅት ለማስወገድ መወሰኑን አሳይቷል። “ሩጥ ስንለው የሚሮጥ፣ ተቀመጥ ስንለው የሚቀመጥ ህዝብ ፈጥረናል” በማለት ሲሳለቁበት በነበረቡት ገዢዎች ላይ እየጠራ ተሳልቆባቸዋል። ከእንግዲህም እሱ በፈለገው እንጅ እነሱ በፈለጉት መንገድ እንደማይገዛላቸው ነግሯቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ አድማው ከፍተኛ የህይወት መስዋትነት ሳያስከፍል በሌሎችም አካባቢዎች ሊተገበር የሚችል መሆኑን አሳይቷል። ህዝብ ቆርጦ ከወሰነ ምንም ነገር ለማድረግ የማይሳነው መሆኑንም እንዲሁ መስክረናል። ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ህዝቡ ባደረገው ጠንካራ የስራ ማቆም አድማ የተሰማውን ኩራት ለመግለጽ ቃላት ያጥረዋል።
የህዝባቸውን ብሶት ብሶታቸው አድርገው፣ ህዝባቸውን በተሻለ ጎዳና ለመምራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ያላቸው መምህራንም የትግሉ መሪ መሆን በመጀመራቸው በእጅጉ ኮርተናል። የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ካድሬዎችን እያሳፈሩ የሸኙበት መንገድ አኩሪና በሁሉም ቦታ ሊተገበር የሚገባው ምርጥ የትግል ስልት ነው። ምሁራን ለዲሞክራሲ፣ ፍትሃና ነጻነት የሚደረገውን ትግል በመምራት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳላቸው ድርጅታችን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ምሁራን ትግሉ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲመራ እንደሚራ ብቻ ሳይሆን ከነጻነት በሁዋላ ለሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ስርዓት ዋስትና በመሆናቸው የጀመሩትን ትግል እስከመጨረሻው መርተው ዳር ያደርሱታል ብለን እናምናለን። በተለያዩ ምክንያቶች ትግሉን ያልተቀላቀላችሁ ምሁራን በፍጥነት ትግሉን ተቀላቅላችሁ ህዝባችሁን በመምራት አካባቢያችሁን ነጻ እንድታወጡ በድጋሜ ጥሪ እናቀርባለን።
ለህዝባዊ ጥሪው ፈጣን ምላሽ የሰጣችሁ ነጋዴዎች፣ የባጃጅና ታክሲ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች፣ ድርጅታችን እየከፈላችሁ ላለው ወደር የለሽ መስዋትነት ከፍተኛ አክብሮት አለው። ግብር ባለመክፈል እንዲሁም የተለያዩ የትግል ስልቶችን እንደያካባቢያችሁ ሁኔታ በመጠቀም ትግላችሁን ከቀጠላችሁ፣ አገዛዙ እናንተን ለመግደል ለተሰለፉት ጥቂት የአገዛዙ ወታደሮች፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት የሚከፍለው ገንዘብ ስለማያገኝ በመጨረሻ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል። አሁንም ትግሉን ዳር የማድረስ ታሪካዊ አደራ ተጥሎባችሁዋል እና ትግላችሁን ቀጥሎ እንላለን።
ከንቱ ለሆነ አላማ የህዝባችሁ መጨፍጨፍ እረፍት ነስቷችሁ የጠመንጃችሁን አፈሙዝ በአፋኙ አገዛዝ ላይ ያዞራችሁ ፣ መሳሪያችሁን አስረክባችሁ ከህዝባችሁ ጋር የተቀላቀላችሁ ወይም በውስጥ ሆናችሁ በተለያዩ መንገዶች ለምትታገሉ የስራዊቱ አባላትም እንዲሁ ከፍ ያለ አክብሮታችን ይድረሳችሁ። ከህዝቡ ጎን ለመቆም ያልወሰናችሁ ዛሬውኑ ወስናችሁ ከነጻነት ትግሉ ጎን ተሰለፉ። ለህዝብ ያልሆነ አገዛዝ ለእናንተ ሊሆን አይችልም። እናንተ ምን አይነት ህይወት እንደምትገፉ እናውቃለንና ከዚህ የስቃይ ህይወት ለመውጣት ብቸኛው መንገድ የስቃዮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን የወያኔን አገዛዝ ማስወገድ በመሆኑ ጥሪያችንን እንደሰማችሁ የነጻነት ሃይሎችን ለመቀላቀል ወስኑ።
አርበኞች ግንቦት 7 እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም ባለው አቅም ሁሉ ህዝባዊ ትግሉን እየደገፈ ይገኛል። የመጨረሻው የነጻነት ደወል እሰከሚደወል ድረስም ትግሉን ከህዝቡ ጋር ሆኖ ይቀጥላል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ!!
አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
አክሊሉ ታደሰ
ባሳለፍነው እሁድ ኦክቶበር 30 2016 ምስረታውን በመሪዎቹ የፊርማ ስነ-ስርአት ይፋ ያደረገውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ኖቨንበር 4 2016 በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ናሽናል ፕሬስ ክለብ በንቅናቄው አላማና ራእይ ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ንቅናቄው ባዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ፡ዶ/ር ዲማ ነገዎ፡ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ፡ አቶ ሙሉነህ እዩዔልና አቶ በቀለ ወያ እንደሚገኙና ማብራርያ እንደሚሰጡ ሲታወቅ በታዛቢነትም አቶ ሀ/ገብርኤል አያሌው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በተጨማሪ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ የሆነችው ጋዜጠኛና አክትቪስት እሪዮት አለሙ እንደምትገኝ ሲታወቅ ይህ በናሽናል ፕሬስ ክለብ የሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ አርብ ኖቨንበር 4 ከቀኑ 12፡15pm እስከ 2፡30pm ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሀገር ሉአላዊነት ማስከበር፡ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ማረጋገጥና እድገትና ብልፅግናን በማምጣት የፌደራል ስርአት መገንባት በሚሉ ሶስት ዋና ዋና አላማዎች የያዘውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ በወያኔ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ግድያ፤ እሰርና ወከባ አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን የታወጀውም ህገ-ወጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለወራት ሀገሪቱን ሲንጥ የቆየውን ህዝባዊ እንቢተኝነት በሀይል ለመጨፍለቅ ታስቦ የታወጀ መሆኑንና ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ላይ ዘላቂ መረጋጋትን ሊያመጣ እንደማይችል አስታውቆ ለአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት በሀገራችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ለዚህ የወያኔ የሽብር አገዛዝ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ከንቅናቄው ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማድረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)