አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
አክሊሉ ታደሰ
ባሳለፍነው እሁድ ኦክቶበር 30 2016 ምስረታውን በመሪዎቹ የፊርማ ስነ-ስርአት ይፋ ያደረገውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ መሪዎች በመጪው አርብ ኖቨንበር 4 2016 በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ናሽናል ፕሬስ ክለብ በንቅናቄው አላማና ራእይ ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ንቅናቄው ባዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ፡ዶ/ር ዲማ ነገዎ፡ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ፡ አቶ ሙሉነህ እዩዔልና አቶ በቀለ ወያ እንደሚገኙና ማብራርያ እንደሚሰጡ ሲታወቅ በታዛቢነትም አቶ ሀ/ገብርኤል አያሌው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በተጨማሪ በሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማት ተሸላሚ የሆነችው ጋዜጠኛና አክትቪስት እሪዮት አለሙ እንደምትገኝ ሲታወቅ ይህ በናሽናል ፕሬስ ክለብ የሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ አርብ ኖቨንበር 4 ከቀኑ 12፡15pm እስከ 2፡30pm ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሀገር ሉአላዊነት ማስከበር፡ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ማረጋገጥና እድገትና ብልፅግናን በማምጣት የፌደራል ስርአት መገንባት በሚሉ ሶስት ዋና ዋና አላማዎች የያዘውና በአራት ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ በወያኔ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ግድያ፤ እሰርና ወከባ አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን የታወጀውም ህገ-ወጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለወራት ሀገሪቱን ሲንጥ የቆየውን ህዝባዊ እንቢተኝነት በሀይል ለመጨፍለቅ ታስቦ የታወጀ መሆኑንና ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ላይ ዘላቂ መረጋጋትን ሊያመጣ እንደማይችል አስታውቆ ለአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት በሀገራችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ለዚህ የወያኔ የሽብር አገዛዝ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ከንቅናቄው ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ማድረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment