Monday, February 20, 2017

በህወሓት የበላይነት ስር የሚገኘው የኣገር መከላከያ ሠራዊት ከ25 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ

(በአርበኞች ግንቦት 7 ጥናትና ምርምር ቡድን የተዘጀ)

ታህሳስ 2009 ዓ.ም.

የመከላለያ አዛዞች የብሄር ስብጥር ጥናት ውጤት ታህሳስ 2009 (PDF)

መግቢያ

የዛሬ ሰባት አመት (እ.ኤአ. 2009) ያኔ “ግንቦት 7- የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ” ይባል የነበረውና አሁን አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ውስጥ የተጠቃለለው ድርጅት በዘር የተደራጀዉን የወያኔ መከላከያ ተቋም አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ብሎም ለዓለም ማኅበረሰብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ያ ጥናታዊ ሪፓርት ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብም ቀርቶ አገዛዙን ትዝብት ላይ በመጣሉ “የመካከያ ሠራዊታችንን ብሄራዊ ተዋጽዖ እናመጣጠንን ነው” የሚል ፕሮፖጋንዳ የወያኔ ኣገዛዝ መንዛት ተጀመረ።

በዝቅተኛና በተራ ውትድርና ደረጃ መመጣጠን መኖሩ ድሮም ጥያቄ ተነስቶበት አያውቅም። ድሮም አሁንም ጥያቄው ያለው በሠራዊቱ አመራር ላይ ያሉት እነማን ናቸው የሚለው ላይ ነው። በዚህ ረገድ በእርግጥ እንደሚባለው ለውጥ አለን? ይህ ጽሁፍ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የተደረገ ጥናት ውጤት ነው።

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው የአገዛዙ ሠራዊት አመራሮች የብሄር ተዋጽዖ በተመለከተ ዛሬ ሰባት ዓመት ከነበረው እጅግም የተሻለ ነገር የለም። በህወሓት ስር የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላም 6% ብቻ የሆነውን የትግራይን ሕዝብን አንወክለዋለን በማለት በሚነግዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች የበላይ ኃላፊነት፣ እዝና ቁጥጥር ስር ወድቆ እናገኛለን። ይህ ጥናት እንደሚያሳየው የኣሮሞና የኣማራ ብሄሮችም ሆኑ ሌሎችሁ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በመከላከያ ሠራዊቱ የኃላፊነትና የእዝ ቦታዎች ላይ እጅግ ዝቅተኛ ወይንም ከነኣካቴው ምንም እይነት የኃላፊነት ድርሻ የላቸውም። ይህ ያገጠጠ ኢ-ፍትሃዊነት ኣንድምታው ህሊና ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ምን ማለት መሆኑ ግልጽ ነው ብለን እንገምታለን። ዛሬም እንደትናቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ ለፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐት ብቸኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችለዉ በቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነጮች ፈጥረውት የነበረው ዘረኛ (Apartheid) ስርዐት ብቻ ነዉ።

በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ በተለይ በቁጥሩ ከፍተኛ ብልጫ ያለዉና ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነዉ ሠራዊት እጅግ ያኮረፈ፤ የተቆጣና ያመረረ ሠራዊት ከመሆኑ የተነሳ እራሱን የሚመለከተዉ እንደ አገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆን አንደ ህወሓት የቤት ዉስጥ አገልጋይ ባሪያ ነዉ። ይህ የህወሓት ዘረኞች በሠራዊቱ ላይ የፈጠሩት የመገዛትና የበታችነት ስሜት በየቀኑ ከፍተኛ ቁጣና የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ የሚገጥመዉ ቢሆንም ህወሓት በዘረጋዉ ከፍተኛ የአፈና መረብ የተነሳ የሕዝብ መነጋገሪያ አርዕስት መሆን አልቻለም። የህወሓት መሪዎችም ቢሆኑ ይህንን ቁጣና ተቃዉሞ በሚገባ ስለሚያዉቁ “ግምገማ” እያሉ በሚያዘጋጇቸዉ መድረኮች ላይ እንደነዚህ አይነቶቹን የህወሓትን የበላይነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማስተናገድ ቀርቶ ጥያቄዎቹ እንዲነሱም አይፈቅዱም። አንዳንዴ ደፍረዉ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሱ ግለሰቦች ሽብርተኛ፤ የደርግ ስርዐት ናፋቂዎች፤ ጠባብ ብሄረተኞች ወይም የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች የሚል ተቀጥላ ስም ይሰጣቸዋል። ዛሬ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዉ በተለያዩ የወያኔ እስር ቤቶች ዉስጥ የሚሰቃዩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የበቁት በመከላከያ ተቋሞች ዉስጥ ሠራዊቱን በዬትኛዉም እርከን የሚመሩ መኮንኖች አመዳደብ ወታደራዊ አመራር ችሎታን፤ ልምድንና የብሄር ስብጥርን ያካተተ መሆን አለበት ብለዉ ደፍረዉ በመናገራቸዉ ነዉ።


የወያኔን መከላከያ ሠራዊት እየለቀቁም ሆነ ትግሉን አየተቀላቀሉ የመከላከያ ሠራዊት ኣባላት ቁጥር ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል። እነዚህ ወታደራዊ መሪዎች፤ የበታች መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረጎቸችና ተራ ወታደሮች ከጠላት እንከላከላን ብለዉ የማሉላትን እናት አገራቸዉን እየለቀቁ የሚወጡት በወያኔ ጦር ዉስጥ ስር የሰደደዉ ዘረኝነትና በዚህ ዘረኝነት ላይ የተመሰረተዉ አመራር የሚያደርስባቸዉ በደል አንገፍግፏቸዉ ነዉ። ዛሬም አንደትናቱ በየጎረቤቱ አገር ተሰድደዉ በችግር ላይ የሚገኙ ምርጥ የኢትዮጵያ የሚሊታሪ ሳይንስ አዋቂዎች ሁሉም በአንድ ድምፅ የሚናገሩት ሠራዊቱ ዉስጥ ይድርስባቸዉ የነበረዉ ንቀትና ዉርደት የሰዉ ልጅ መሸከም ከሚችለዉ በላይ መሆኑን ነዉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ በገነባዉ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ የዕዝ፤ የክፍለጦርና የመምሪያዎች አዛዥ ለመሆን ዋነኛዉ መለኪያ የህወሓት አባል መሆን ነዉ እንጂ ችሎታ፤ ልምድ፤ ብቃትና የወታደራዊ ሳይንስ ክህሎት አይደለም። ችሎታ፤ ልምድና ብቃት መመዘኛ ሆነዉ የሚቀርቡት በመጀመሪያ ለሹመት የታጨዉ መኮንን ህወሓትነት ከተረጋገጠ በኋላ ብቻ ነዉ። በህግ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የፓለቲካ ድርጅት አባላት አይሆኑም፤ በተግባር ግን ለሹመት የሚያሳጨው የፓርቲ አባልነት ነው።

አንደሚታወቀው የህወሓት የስልጣን ሞኖፖሊ በወታደራዊ ደህንነት ተቋሞች ላይ ብቻ ተወስኖ አያበቃም። አብዛኛዉን የአገሪቱ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ተቋሞችም ወይ ከላይ አለዚያም ከታች ሆነዉ ይቆጣጠራሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለይስሙላ የተቀመጠና ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የመጡ ሰዎች የሚገኝበት መንግስት አለ፤ በዚህ መንግስት ዉስጥ ደግሞ አገሪቱን ወዳሰኘዉ አቅጣጫ በዘፈቀደ የሚዘዉረዉና ከትግርኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ሌሎች የማይገኙበት በመንግስት ዉስጥ ሌላ መንግስት አለ። የሚገርመዉ ዛሬ እነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፤ አባዱላ ገመዳና ደመቀ መኮንንን የመሳሰሉ ምስለኔዎች ስልጣን ላይ የተቀመጡ ነገር ግን ህወሓት ጌቶቻቸዉ ከሚነግሯቸዉ ዉጭ በራሳቸዉ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉ አሻንጉሊቶች መሆናቸዉን እነሱ አራሳቸዉም የተገነዘቡት ይመስላል።

በዚህ በወቅታዊ መርጃዎች ላይ በመመስረት በኣርበኞች ግንቦት 7 የወታደራዊ ጥናት ቡድን ተሻሽሎና ታድሶ በኣዳዲስ መረጃዎች በተጠናቀረው ጥናት ቀጥሎ የሚቀርበዉ ሠንጠረዥ የተለያዪ የመከላከያ ተቋም የኃላፊነትና የእዝና ቁጥጥር ቦታዎችን፤ በእነዚህም ቦታዎችን እነ ማን እንደተቀመጡና የተወለዱበት ብሄረሰብ ያሳያል።

በዚህ ሠንጠረዥ ያልተመለከተ ሌላ አቢይ ጉዳይም አለ። ይህም በእስር ላይ ከሚገኙ የሠራዊቱ መኮንኖች ውስጥ እጅግ የበዙት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የመሆናቸው ሀቅ ነው። በጄኔራል ተፈራ ማሞና ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጋር በተያያዘ እነሱን ጭምሮ በርካታ ባለከፍተኛ ማዕረግ የአማራ ተወላጆች ታስረዋል፤ ከዚህ በቁጥር የበዙት ከሠራዊቱ ተባረዋል። ከጄኔራል ከማል ገልቹና ጄኔራል ኃይሉ ጎንፋ ጋር ተያይዞ እንደነዚ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ተወላጅ መኮንኖች ታስረዋል፣ ተባረዋል። አገዛዙ ውስጥ ችግር በደረሰ ቁጥር የችግር መወጫ የሚሆኑን የአማራ፣ የኦሮሚያና የሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ተወላጅ የሆኑ መኮንኖች ናቸው።

1. የመከላከያ የበላይ ኃላፊነቶችና እዞች የብሄር ስብጥር


  ትግሬ አማራ ኦሮሞ ኣገው የደቡብ ሕዝቦች ኣፋር ጋምቤላ ቤኒ ሻንጉል ሶማሊ ሀረሪ ድምር
የመከላከያ የበላይ ኃላፊዎችና ኣዛዦች 34 4 5 3 3 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 49
የእዝ ኣዛዦችና ምክትል የእዝ ኣዛዦች 9 1 5 ምንም 1 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 16
ሌሎች  የኣዝ ከፍተኛ ኃላፊዎች 21 2 2 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 25
የትምህርትና የስልጠና ኃላፊዎች 23 3 4 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 30
የክፍለ ጦር ዋና እዛዦች 12 5 1 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 18
የክፍለ ጦር ከፍተኛ ኃላፊዎች 19 8 7 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 34
የአየር ኃይል ከፍተኛ ኃላፊዎች 29 9 4 ምንም 3 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 45
ጠቅላላ ድምር 147 32 28 3 7 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም 217
ጠቅላላ በመቶኛ (%) 68 15 13 1.3 3 ምንም ምንም ምንም ምንም ምንም






2. አጠቃላይ የመከላከያ የበላይ ኃላፊነቶችና እዞች የብሄር ስብጥር

3. ሰባቱ ዋና ዋና የመከላከያ የበላይ ኃላፊነቶችና እዞች የብሄር ስብጥር



የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና የበላይ ኃላፊዎች



ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ጄነራል ሳሞራ የኑስ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ትግሬ
2. ሌ/ጄነራል አደም መሃመድ (ኤፍሬም) የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አማራ
3. ሌ/ጄነራል ሰዓረ መኮንን የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ አዛዥ ትግሬ
4. ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል የህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ አዛዥ ትግሬ
5. ሌ/ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የሰላም ማስከበር ማስተባበሪያ ማእከል ኃላፊ ኦሮሞ
6. ሜ/ጄነራል ገብሬ አድሃና (ዲላ) የመረጃ ዋና መምሪያ አዛዥ ትግሬ
7 ሜ/ጄነራል ኢብራሂም አብዱልጀሊድ የሎጂስቲክ ዋና መምሪያ አዛዥ ትግሬ
8. ሜ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሴክተር ኃላፊ ትግሬ
9. ሜ/ጄነራል ተ/ብርሃን ወ/አረጋይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ዋና ዳይሬክተር ትግሬ
10. ሜ/ጄነራል ብርሃኔ ነጋሽ የመከላከያ ምኒስትር ዴኤታ ትግሬ
11. ሜ/ጄነራል ማሞ ግርማይ የብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ዋና አዛዥ አገው
12. ሜ/ጄነራል ሃሰን ኢብራሂም በደቡብ ሱዳን አቢዬ የሰላም ማስከበር ኃይል ዋና አዛዥ አማራ
13. ሜ/ጄነራል መሃሪ ዘውዴ የሰው ኃይል አመራር ዋና መምሪያ አዛዥ ትግሬ
14. ሜ/ጄነራል መሃመድ ኢሻ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የበላይ አዛዥ ትግሬ
15. ሜ/ጄነራል ደስታ አብቹ የውጭ ግንኙነት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ኦሮሞ
16. ሜ/ጄነራል ገ/ሚካኤል በየነ የጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና አዛዥ ትግሬ
17 ሜ/ጄነራል ተስፋዬ ግደይ የጤና ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
18 ሜ/ጄነራል ገ/አድሃነ ወለዝሁ ትግሬ
19 ብ/ጄነራል አታክልቲ ወ/ጊዮርጊስ የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋናመምሪያ ም/ል አዛዥ ትግሬ
20 ብ/ጄነራል ሙሉ ግርማይ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ አዛዥ ትግሬ
21 ብ/ጄነራል ህንጻ ወ/ጊዮርጊስ ትግሬ
22 ብ/ጄነራል ገ/መድህን ፍቃዱ የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ትግሬ
23. ብ/ጄነራል ሙላት ጀልዱ የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥ ለአስተዳደርና ፋይናንስ ኦሮሞ
24 ብ/ጄነራል ሃብታሙ ጥላሁን አለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ስልጠና ማዕከል ዋና አዛዥ ሃዲያ
25. ብ/ጄነራል አስካለ ብርሃነ የመከላከያ የፍትህ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
26 ብ/ጄነራል ተስፋዬ ወ/ማሪያም የመከላከያ ኢንስፔክሽን መምሪያ ም/ል አዛዥ ትግሬ
27. ብ/ጄነራል ገ/ኪዳን ገ/ማርያም የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚንኬሽን ዋና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
28 ብ/ጄነራል ታረቀኝ ካሳሁን የመገናኛ መምሪያ ዋና አዛዥ አገው
29 ብ/ጄነራል ያይኔ ስዩም የመከላከያ ፋውንዴሽን ኃላፊ ትግሬ
30 ብ/ጄነራል ጠና ጥሩንቄ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ም/ል ዳይሬክተር ሲዳማ
31. ብ/ጄነራል እንዳልካቸው ገ/ኪዳን የመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች አስተባባሪ ኦሮሞ
32 ብ/ጄነራል መሰለ መሰረት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ መምሪያ የኃይል ዝግጅት ኃላፊ አገው
33 ብ/ጄነራል ዘውዲ ኪሮስ በደቡብ ሱዳን አቢዬ የሰላም ማስከበር ኃይል ም/ል አዛዥ ትግሬ
34. ብ/ጄነራል ንጉሴ ለማ ሰላም ማስከበር ኦሮሞ
35. ብ/ጄነራል በላይ ስዩም በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር የዲፍራ ሴክተር ላይዘን ኦፊሰር አማራ
36. ብ/ጄነራል አዲሱ ገ/እየሱስ የመከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
37. ኮ/ል ታምራት አንዳርጌ አለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ስልጠና የቡድን ስልጠናዎች ዲቪዥን ኃላፊ አማራ
38. ኮ/ል ነጋሽ ህሉፍ አለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
39. ኮ/ል ታዜር ገ/እግዚአብሄር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ም/ል ዳይሬክተርና የጂኦስፓሻል ደህንነት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
40. ኮ/ል የኑስ ሙሉ በመከላከያ የውጪ ግንኙነትና ትብብርና ድጋፍ ቡድን መሪ ትግሬ
41. ኮ/ል ፍጹም ገ/ እግዚአብሄር መከላከያ ፋይናንስ ዳይሮክቶሬትር ዳይሬክተር ትግሬ
42. ኮ/ል አለሙ ተካ የመከላከያ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት አዛዥ ትግሬ
43. ኮ/ል ምኡዝ አብረሃ የመከላከያ በጀትና ፕሮግራም ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
44. ኮ/ል ነጋሲ ትኩ የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ፣ የግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
45. ኮ/ል ክብሮም ገ/ እግዚአብሄር የመከላከያ የኪነ ጥበባት ስራዎች ኃላፊ ትግሬ
46. ኮ/ል ጸጋዬ ግርማይ የመከላከያ ሚዲያ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
47. ኮ/ል በርሄ አረጋይ የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግንኙነትና ስርዓት ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
48. ኮ/ል ታደሰ ላምባሞ የአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥ ለሎጀስቲክ ደቡብ
49 ኮ/ል ሃጎስ አስመላሽ የመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬት ትግሬ


የእዝ ዋናና ምክትል አዛዦች



ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ሌ/ ጄነራል አብረሃ ወ/ማሪያም (ኳርተር) የደቡብ ምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ትግሬ
2. ሌ/ ጄነራል ገብራት አየለ የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ትግሬ
3. ሜ/ ጄነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊስ የማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ትግሬ
4. ሜ/ ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ የምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ትግሬ
5. ሜ/ ጄነራል ጌታቸው ጉዲና የደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊ ኦሮሞ
6. ሜ/ ጄነራል ማዕሾ በየነ የሰሜን እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ትግሬ
7. ሜ/ ጄነራል አጫሉ ሸለመ የሰሜን እዝ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ኦሮሞ
8. ሜ/ ጄነራል ድሪባ መኮንን የምዕራብ እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ኦሮሞ
9. ብ/ ጄነራል የማነ ሙሉ የደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
10. ብ/ ጄነራል ኃይለስላሴ ግርማይ የደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት አመራር ኃላፊ ትግሬ
11. ብ/ ጄነራል አብረሃ አረጋይ የሰሜን እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
12. ብ/ ጄነራል አስራት ዴኔሮ የማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ከፊቾ
13. ብ/ ጄነራል አብረሃ ተስፋዬ የማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ትግሬ
14. ብ/ጄነራል ከፍያለው አምዴ የማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ ኦሮሞ
15. ብ/ ጄነራል መሃመድ ተሰማ የምዕራብ እዝ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ አማራ
16. ብ/ ጄነራል አብዱራማን እስማኤል የምዕራብ እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ኦሮሞ


ከፍተኛ የእዝ አዛዦችና ኃላፊዎች



ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ብ/ጄነራል ሙላለም አድማሱ የሰሜን እዝ ስልጠና ኃላፊ ትግሬ
2. ኮ/ል ላዕከ አረጋዊ የሰሜን እዝ ጤና ዳይሮክትሬት ዳይሬክተር ትግሬ
3. ኮ/ል ተስፋዬ ብርሃነ የሰሜን እዝ መሃንዲስ አዛዥ ትግሬ
4. ኮ/ል ገ/ዮሃንስ ተክሌ የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ጸ/ቤት ኃላፊ ትግሬ
5. ኮ/ል አስገደ ገ/መስቀል የሰሜን እዝ የመድሃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ኃላፊ ትግሬ
6. ኮ/ል ኪሮስ ወልደስላሴ የሰሜን እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ትግሬ
7. ኮ/ል ታደለ ገ/ህይወት የሰሜን እዝ ህብረት ዘመቻ ኃላፊ ትግሬ
8. ኮ/ል መሃሪ አሰፋ የሰሜን እዝ የሰው ሃብት አመራር መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
9. ኮ/ል ገ/ሚካኤል ኪዳነማሪያም የማዕከላዊ እዝ የህብረት ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
10. ኮ/ል አሊጋዝ ገብሬ የማዕከላዊ እዝ የኢንዶክትኒኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ትግሬ
11. ኮ/ል አደም ሰይድ የማዕከላዊ እዝ የህግ ጉዳይ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አማራ
12. ኮ/ል ተመቸው ተስፋዬ የማዕከላዊ እዝ የጤና ዳይሮክቶሬትዳይሬክተር አማራ
13. ኮ/ል ሃጎስ ሃይሉ የማዕከላዊ እዝ የትምህርት ክትትል ኃላፊ ትግሬ
14. ኮ/ል ጥያር በቀለ የማዕከላዊ እዝ የስነ ምግባር ኃላፊ ትግሬ
15. ኮ/ል ዮሃንስ ገ/ሊባኖስ የምዕራብ እዝ ኢንስፔክሽን ኃላፊ ትግሬ
16. ኮ/ል ተክላይ ገ/ጻድቃን የምዕራብ እዝ ሲግናል ሬጂመንት አዛዥ ትግሬ
17. ኮ/ል ገ/ኪዳን ቸኮል የምዕራብ እዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
18. ኮ/ል በርሄ ኪዳነ የምዕራብ እዝ የስልጠና ኃላፊ ትግሬ
19. ኮ/ል ቀለህ ገብረስላሴ የደቡብ ምስራቅ እዝ የትራንስፖርት ኃላፊ ትግሬ
20. ኮ/ል ገ/ሜካኤል ገብራት የደቡብ ምስራቅ እዝ የህግ ጉዳይ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር ትግሬ
21. ኮ/ል ጥላሁን ወርዶፋ የደቡብ ምስራቅ እዝ የስነ ምግባር ክትትል ኃላፊ ኦሮሞ
22. ኮ/ል አብዱሰላም ኢብራሂም የደቡብ ምስራቅ እዝ የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
23. ኮ/ል ተክላይ ገ/እግዚአብሄር የደቡብ ምስራቅ እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
24. ኮ/ል ኢሰታ ኢጄታ የደቡብ ምስራቅ እዝ የአቅርቦትና ስርጭት ክፍል ኃላፊ ኦሮሞ
25. ኮ/ል ስዩም ተፈራ የደቡብ ምስራቅ እዝ ጤና ማበልጸግና በሽታ መከላከል ኃላፊ ትግሬ


የክፍለ ጦር ዋና አዛዦች



ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ብ/ ጄነራል ይብራህ ዘሪሁን የ20ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
2. ብ/ ጄነራል ዋኘው አማራ የ21ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አማራ
3. ብ/ ጄነራል አዳምረህ መንግስቴ የ11ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አማራ
4. ብ/ ጄነራል ጋይም ሺሻይ የ7ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
5. ብ/ ጄነራል አልታወቀም የ23ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ
6. ብ/ ጄነራል ሹማ አብደታ የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ኦሮሞ
7. ብ/ ጄነራል ከድር አራርሳ የ13ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አማራ
8. ብ/ ጄነራል ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሄር የ32ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
9. ብ/ ጄነራል አሰፋ ቸኮል የ25ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አማራ
10. ብ/ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን የ12ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አማራ
11. ብ/ጄነራል ሰመረ ገ/እግዚአብሄር የተዋጊ መሃንዲስ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
12. ኮ/ል ነጋሲ ተስፋዬ የ4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
13. ኮ/ል ገ/ጊዮርጊስ መኮንን የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
14. ኮ/ል ወ/ጊዮርጊስ ተክላይ የ22ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
15. ኮ/ል ዘነበ ክፍሌ የ31ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
16. ኮ/ል ተክላይ ገ/ጊዮርጊስ የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
17. ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ዘሚካኤል የ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
18. ኮ/ል ሃጎስ ደስታ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ
19. ኮ/ል ይርዳው ገ/መድህን የ2ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ትግሬ


ከፍተኛ የክፍለ ጦር ኃላፊዎች

ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ብ/ጄነራል ሲሳይ ውብለኔ የ24ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ አማራ
2. ኮ/ል ገ/ስላሴ በላይ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊ ትግሬ
3. ኮ/ል ገ/ጻዲቅ አስረሳሀኝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ ትግሬ
4. ኮ/ል ሰመረ ተክሉ የ20ኛ ክ/ጦር ም/ አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊ ትግሬ
5. ኮ/ል ዘነበ ለማ የ20ኛ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አማራ
6. ኮ/ል ዋቆ አህመድ የ20ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ ኦሮሞ
7. ኮ/ል አብዱራሂም እንዲሪስ የ20ኛ ክ/ጦር የሰው ሃብት ቡድን መሪ ኦሮሞ
8. ኮ/ል መብራቱ ሃይለ የ21ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ትግሬ
9. ኮ/ል ሻምበል ፈረደ 21ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ አማራ
10. ኮ/ል ህንጻ ገ/እግዚአብሄር የ21ኛ ክ/ጦር የስልጠና ኃላፊ ትግሬ
11. ኮ/ል ካልዩ ሃብቴ የ22ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ ትግሬ
12. ኮ/ል አሰፋ ይርጋ የ31ኛ አደዋ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ አማራ
13. ኮ/ል ንጉሴ ወልዱ የ33ኛ ክ/ጦር የሎጀስቲክ አቅርቦትና ስርጭት ኃላፊ ትግሬ
14. ኮ/ል ፍቃዱ ጸጋዬ የ33ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና ለአስተዳረንና ፋይናንስ ኦሮሞ
15. ኮ/ል ምሳሁ ገብረተክሌ የ12ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
16. ኮ/ል ገ/ሚካኤል ግርማይ የ12ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ትግሬ
17. ኮ/ል ተሾመ ሽፈራው የ12ኛ ክ/ጦር ህብረት ዘመቻ ኃላፊ አማራ
18. ኮ/ል ተክለብርሃን አለማየሁ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
19. ኮ/ል በላቸው ገዳ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊ ኦሮሞ
20. ኮ/ል መሃመድ ጀመላዲን የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የስራ መሃንዲስ ኃላፊ ኦሮሞ
21. ኮ/ል ዘውዱ ጎሹ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ትግሬ
22. ኮ/ል ድጋፌ እጅጉ የ24ኛ ክ/ጦር የመሃንዲስ ኃላፊ አማራ
23. ኮ/ል ምሩጽ ወ/ሚካኤል የ24ኛ ክ/ጦር ኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ትግሬ
24. ኮ/ል ታደሰ በርሄ የ24ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
25. ኮ/ል ኑሩ ይዘይን ሁሴን የ13ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ኦሮሞ
26. ኮ/ል መኮንን ወልደስላሴ የ13ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
27. ኮ/ል ተስፋዬ ሃይለ የ13ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ ትግሬ
28. ኮ/ል መሃሪ በየነ የ32ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
29. ኮ/ል ገ/ሊባኖስ ገ/ጊዮርጊስ 25ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
30. ኮ/ል መኮንን በንቲ 8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ ኦሮሞ
31. ኮ/ል ክብረአብ ገብረዋህድ የ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ትግሬ
32. ኮ/ል ግርማ ክበበው የ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ አማራ
33. ኮ/ል ኪዱ ተክለ የ11ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
34. ኮ/ል ትእዛዙ ወንድሜነህ የ11ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊ አማራ


የትምህርትና ስልጠና ተቋማት አዛዦች

ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ሜ/ጄነራል ሃለፎም እጅጉ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ትግሬ
2. ሜ/ጄነራል ይመር መኮንን አሊ የህብረት ወታደራዊ ስታፍ ኮሌጅ አዛዥ አማራ
3. ብ/ጄነራል ኩመራ ነገሪ የሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ ኦሮሞ
4. ብ/ጄነራል ገ/እግዚአብሄር በየነ የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ትግሬ
5. ብ/ጄነራል ሙዘይ መኮንን አዋሽ 40 የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ዋና አዛዥ ትግሬ
6. ብ/ጄነራል መሸሻ ገ/ሚካኤል የመከላከያ የአዛዥነት መምሪያና የስታፍ መኮንኖች ኮሌጅ አዛዥ ትግሬ
7. ብ/ጄነራል ሰለሞን ኢተፋ አዋሽ 7 ጥምር ጦር አካዳሚ ዋና አዛዥ ኦሮሞ
8. ብ/ጄነራል ጀማል መሃመድ በሰሜን እዝ የብ/ ጄነራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ትግሬ
9. ኮ/ል ብርሃኑ በቀለ የመከላከያ የአዛዥነት መምሪያና የስታፍ መኮንኖች ኮሌጅ ም/ል አዛዥ ኦሮሞ
10. ኮ/ል ብርሃነ ተክሌ የሜ/ጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ትግሬ
11. ኮ/ል መንግስቱ ተክሉ የጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ትግሬ
12. ኮ/ል አደም ትኩ የተዋጊ መሃንዲስ ክ/ጦር ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ትግሬ
13. ኮ/ል ጎይቶም ፋሩስ ሜ/ጄነራል ሃየሎም አርያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ ትግሬ
14. ኮ/ል መረሳ በርሄ ሜ/ጄነራል ሃየሎም አርያ ወታደራዊ አካዳሚ የአጭር ኮርስ ስልጠና አዛዥ ትግሬ
15. ኮ/ል ገ/መድህን ተስፋዬ ሜ/ጄነራል ሃየሎም አርያ ወታደራዊ አካዳሚ ትግሬ
16. ኮ/ል ነጋሲ ጎይቶም አዋሽ 40 የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ም/ል አዛዥ ትግሬ
17. ኮ/ል በርሄ ኪዳኔ የምዕራብ እዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ትግሬ
18. ኮ/ል ንጉሴ ሃይሌ የምዕራብ እዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥና ለስልጠና ትግሬ
19. ኮ/ል ዮሃንስ ካህሳይ የብላቴ ልዩ ሃይሎች ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ትግሬ
20. ኮ/ል ደስታ ሃጎስ የልዩ ሃይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥ ትግሬ
21. ኮ/ል ተሾመ ይመር በሰሜን እዝ የብ/ ጄነራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛማዕከል ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ አማራ
22. ኮ/ል ከበደ ፍቃዱ በማዕከላዊ እዝ የፋና ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ትግሬ
23. ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ገ/ሰላማ በማዕከላዊ እዝ የፋና ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊ ትግሬ
24. ኮ/ል ዳኜ በላይ የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ አማራ
25. ኮ/ል ጌታሁን ካህሳዬ የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ትግሬ
26. ኮ/ል ግርማይ ገ/ጨርቆስ የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊ ትግሬ
27. ኮ/ል ሃይሌ ተስፋዬ በደቡብ ምስራቅ እዝ የ38ኛ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ትግሬ
28. ኮ/ል ሙሉጌታ ምንይሉ በደቡብ ምስራቅ እዝ የ38ኛ ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥ ኦሮሞ
29. ኮ/ል ሃጎስ ብርሃነ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አዛዥ ትግሬ
30. ኮ/ል ሃድጋይ አያሌው የመከላከያ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ትግሬ


የአየር ኃይል አዛዦችና ኃላፊዎች

ተ.ቁ ማዕረግ ስም የኃላፊነት ቦታ ብሄር
1. ሌ/ ጄነራል አደም መሃመድ (ኤፍሬም) የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አማራ
2. ሜ/ ጄነራል አቤል አየለ የአየር ኃይል ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ጎፋ
3. ብ/ ጄነራል ማዕሾ ሃጎስ የአየር ኃይል ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ ትግሬ
4. ብ/ ጄነራል አሰፋ ገብሩ የአየር ኃይል ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ትግሬ
5. ብ/ ጄነራል ይልማ መርዳሳ ምዕራብ አየር ምድብ ዋና አዛዥ ኦሮሞ
6. ኮ/ል ሃይሌ ለምለም ሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥ ትግሬ
7. ኮ/ል አበበ ተካ ምስራቅ የአየር ምድብ ዋና አዛዥ ትግሬ
8. ኮ/ል ሰለሞን ገ/ስላሴ ማዕከላዊ አየር ምድብ ዋና አዛዥ ትግሬ
9. ኮ/ል ሃይለስላሴ ጸጋይ ማዕከላዊ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
10. ኮ/ል አስናቀ ብርሃኑ ማዕከላዊ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ አማራ
11. ኮ/ል መኮንን ብስራት ማዕከላዊ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የዘመቻ ኃላፊ አማራ
12. ኮ/ል ንጉሴ አበራ ሰሜን አየር ምድብ አቪዬሽን ጥገና ኃላፊ አማራ
13. ኮ/ል ወርቃለማው አኔቶ ሰሜን አየር ምድብ ሴፍቲና ኢንስፔክሽን ኃላፊ ሃዲያ
14. ኮ/ል መንግስቱ ሃድጉ ሰሜን አየር ምድብ ኢንዶክትሪኒሽን ኃላፊ ትግሬ
15. ኮ/ል ይታያል ገላው የሰሜን አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የዘመቻ ኃላፊ አማራ
16. ኮ/ል አድነው እሸቱ የሰሜን አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊ ኦሮሞ
17. ኮ/ል ጸጋይ ካህሳይ የሰሜን አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
18. ኮ/ል ኪዱ ገ/ስላሴ ምዕራብ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
19. ኮ/ል ሙሉ ገብረ የምስራቅ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የዘመቻ ኃላፊ ትግሬ
20. ኮ/ል የአብዬ አብረሃ የምስራቅ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ትግሬ
21. ኮ/ል አለማየሁ ጌታቸው የአየር ኃይል ዘመቻ ስልጠናና ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ ኦሮሞ
22. ኮ/ል ሃጎስ ገ/እግዚአብሄር የአየር ኃይል የመረጃ መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
23. ኮ/ል ማሞ ወርቁ የአየር ኃይል ዘመቻ ስልጠና ኃላፊ አማራ
24. ኮ/ል አረጋዊ ባህረ የአየር ኃይል የዘመቻ እቅድ ኃላፊ ትግሬ
25. ኮ/ል ጌታቸው ካህሳይ የአየር ኃይል የአየር መከላከያ ማስተባበሪያ ኃላፊ ትግሬ
26. ኮ/ል ደሳለኝ አበበ የአየር ኃይል የውጊያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
27. ኮ/ል ብርሃኔ አበራ የአየር ኃይል ኢንዶክትሪኒሽን አስተዳደር ኃላፊ ትግሬ
28. ኮ/ል ሃይሉ ገብረየሱስ የአየር ኃይል የሲግናል ሬጅመንት አዛዥ ትግሬ
29. ኮ/ል ሃይሉ ደስታ የአየር ኃይል ተሸከርካሪ ጥገና መምሪያ ሀላፊ ትግሬ
30. ኮ/ል ረታ ተ/ማሪያም የአየር ኃይል አሙኒሽን ኃላፊ አማራ
31. ኮ/ል ወልደስላሴ ስባጋድስ የአየር ኃይል ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ ትግሬ
32. ኮ/ል ግርማይ ደሳለኝ የአየር ኃይል የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክተር ትግሬ
33. ኮ/ል ኢሳያስ ሞገስ የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብሮች መዝናኛ ክበብ ኃላፊ ትግሬ
34. ኮ/ል ሲሳይ ታደሰ የአየር ኃይል የሰው ኃብት አመራር መምሪያ ኃላፊ ትግሬ
35. ኮ/ል ነገራ ሌሊሳ የአየር ኃይል አቭዬሽን ጥገና መምሪያ ኃላፊ ኦሮሞ
36. ኮ/ል ታደሰ ይመር የአየር ኃይል ወታደራዊ ፅንሰሃሳብና ቴክኖሎጂ ጥናት ኃላፊ ትግሬ
37. ኮ/ል ሃጎስ ግደይ አየር ኃይል አዛዥ ፅ/ቤት ኃላፊ ትግሬ
38. ኮ/ል ጠቅለው ክብረት የአየር ኃይል ኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አማራ
39. ኮ/ል ካልአዩ ዘምቸል የአየር ኃይል የጤና ማበልፀጊያና በሽታ መከላከል ኃላፊ ትግሬ
40. ኮ/ል ዜናዊ ይብራህ የአየር ኃይል ህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ትግሬ
41. ኮ/ል ሙሉጌታ ወ/ሩፋኤል አየር ኃይል ቴክኒክ ኮሌጅ አዛዥ ትግሬ
42. ኮ/ል ካህሳይ በየነ የአየር ኃይል ሙዚቃ ሲኒማና ቲያትር አስተዳደር ኃላፊ ትግሬ
43. ኮ/ል ኢሳያስ አሰፋ የአየር ኃይል ጤና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አማራ
44. ኮ/ል ታደሰ ካህሳይ የአየር ኃይል በረራ ሴፍቲ ኃላፊ ትግሬ
45. ኮ/ል አበራ አጭቆ የአየር ኃይል ኦዲት ፅ/ቤት ማስተባበሪያ ኃላፊ ከምባታ

No comments:

Post a Comment