Tuesday, March 31, 2015

በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ (ዞን9)

March 31, 2015

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የማስረጃ መስማት ውሎ ዛሬ ምስክሮችን በማስማት ተጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያላቸውን 17 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን 15ቱ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ ችሎት አንዲሆን የጠየቀ ሲሆን ምስክሮቼ እና የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ችሎቱ በዝግ ሊሆን ይገባል የሚለውን አቤቱታውን ጠበቆች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውታል፡፡

ምስክሮቹ የጭብጥ ምስክሮች ሳይሆኑ ፍተሻን የታዘቡ የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እና ስማቸውም በግልጽ ተከሳሾች ጋር ስለደረሰ ምንም አይነት የደህንነተ ስጋት የለባቸውም ከሚለው የጠበቆች ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዳዬ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን ረፍት ወስዷል፡፡ በዚህም መሰረት የአቃቤህግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ ሆኖ መስክሮች ምስክርነታቸውን እነዲያሰሙ ታዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቃቤ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮች አነማን ላይ አንደሚመሰክሩ እና ምን አንደሚመሰክሩ በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም በጠበቆቹ ስለተነሱት ነጥቦች የአቃቤ ህግን ምላሽ ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግም በዛሬው ዕለት የቀረቡት ምስክሮች በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ5ኛ፣ በ6ኛ፣ በ7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ( በስድስቱ የዞን9 ጦማርያን ላይ እና በጋዜጠኛ አስማማው ላይ ) ላይ እንደሚመሰክሩ ገልጾ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በብርበራ ያገኛቸው ማስረጃዎች ከተከሳሾች የተገኙ ስለመሆናቸው ያስረዱልኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በምላሹም መሰረት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ምስክርነታቸው ሲሰጡ በነበረበት ወቅት የተከሳሾችን ስም አለማወቅ አንዲሁም የተከሳሾችን መልክ አለመለየት የመሳሰሉት ጉዳዬች የተስተዋሉ ሲሆን ምስክርነታቸውን የሰጡት ሰዎች ስም ዝርዝር እና የምስክርነታቸው ጭብጥ በአጭሩ አንደሚከተለው ነው ፡፡

1. ሙሉጌታ መዝገቡ ለማ – ናዝሬት ነዋሪ ነኝ መአከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፓሊስ ታዛቢ ምስክር አንድሆን ጠይቆኝ በዚያ መሰረት ምስክር ሆኜ ተገኝቻለሁ፡፡ ከአቤል ከኮምፒውተሩ ላይ ጽሁፍ ሲወጣ እና ሲፈርም አይቼ እኔም ፈርሜያለሁ ፡፡ የጽሁፉን ይዘት አላነበብኩም አንዳንድ ቦታ አፍሪካ ሪቪው ኬንያ የሚል ቃል አይቻለሁ የሚል ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡

2. በለጡ አበበ ዮሴፍ ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 32 ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የካ ምድብ ሰራተኛ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በማን ላይ ለመመስከር እንደመጡ ሲጠየቁ በስም እንደማያስታውሱት ገልጸው በአካል ግን ለይተው አሳይተዋል፡፡ መስካሪዋ በ6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት ላይ የሚመሰክሩ ሲሆን በተለየ ስም ሲጠሩት ተስተውለዋል “የሽብርተኝነት ጉዳይ የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡ ወደ 70 ገጽ አማርኛና 10 ገጽ እንግሊዝኛ ጽሁፍ ተገኝቷል፡፡ ያየሁትን አይቼ ፈርሜያለሁ፡፡” ካሉ በኋላ ተከሳሹስ ፈርሟል ተብለው ሲጠየቁ መጀመሪያ አላስታውስም ቢሉም እንደገና ሲጠየቁ ግን አዎ ፈርሟል ብለዋል፡፡

3. እታፈራሁ ጌታቸው ወልዴ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው 36 ነው፡፡ በመንግስት ት/ቤት በአስተዳደር ሰራተኛነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ሲጠየቁ ፍቃዱ እና…..(ስሙ ጠፍቶባቸው ቆይተው) እ…አጥናፉ ብለዋል፡፡ በአካል ደግሞ በፍቃዱን አሳዩ ሲባሉ አጥናፍን አሳይተዋል፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ማእከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄደው ጽሁፎች ሲታተሙ ማየታቸውንና በፍቃዱ በፍቃደኛነት ሲፈርም ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለጽሁፎቹ ሲጠየቁ “የአማርኛ ጽሑፎች ናቸው፡፡ 60 ገጽ የሚሆን ‹ወያኔ ይውደም› ምናምን የሚል ጽሑፍ አይቻለሁ፡፡ እንግሊዝኛም አለው 10 ገጽ ይሆናል፡፡ በምስል ከውጭ ሰው ጋር ሆነው የሚነጋገሩትም አይቻለሁ፡፡ ይዘቱ ግን ግር ይለኛል፡፡” ብለዋል፡፡ አጥናፍን አስመልክቶ ደግሞ ‹‹የእሱንም በዚያው መልኩ ነው ያየነው፡፡ ዕለቱም ግንቦት 16/2006 ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ የነበሩትን ጽሁፎች እዚያ ለነበሩት ሲያሳይ ነበር፡፡ ጽሑፎችን አይቻቸዋለሁ….‹የጨለማው ቀን….የጨለማው ንጉስ› የሚል አይቻለሁ፡፡ ‹ኢትዮጵያ አንድ ናት› የሚልም አይቻለሁ፡፡ ወደ 30 ገጽ ይሆናል፡፡ ሁሉም ፕሪንት ተደርጎ ሁላችንም ፈርመንበታል፡፡››ብለዋል

ሶስቱ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ጠበቆች በሂደቱ ላይ አስተያየት አለን በማለት፣ ዶክመንቶቹ ፕብሊክ ዶክመንት ናቸው በአደባባይ የተጻፉ ጽሁፎቻቸው እና በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ስለሆኑ ዶክመንቶቹን ክደን አልተከራከርንም የእኛ ክርክር ዶክመንቶቹ ለወንጀል ስራ የሚበቁ አይደሉም ነውና በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ምስክር መስማቱ ያብቃልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡አቃቤ ህግ በበኩሉ ሁሉም ምስክሮች አንዲሰሙልኝ እፈልጋለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያስረዱልኛል ካለ ይቀጥል በማለቱ ምስክሮቹ ቀጥለዋል፡፡ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጠይቁ ተከታዬቹ ምስክሮች መሰማታቸው ቀጥሏል፡፡

4. አራተኛው ምስክር አፈወርቅ ካሳ ይባላሉ፡፡ የግል ሰራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸው 46 ነው፡፡‹‹ቀኑ ሚያዝያ 18/2006 ነው፡፡ የተከሳሹ አስማማው ቤት ጠዋት 3፡00 አካባቢ ሲፈተሸ ታዛቢ ነበርኩ፡፡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፓስፖርት…ብዙ ወረቀቶች ላይ ‹‹አዎ የእኔ ናቸው›› እያለ ሲፈርም አይቻለሁ፡፡ እኔም ፈርሜያለሁ፡፡ ቤተሰቦቹም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ አብዛኛው ያየሁት የግል መጽሄቶችን ነው፡፡ ማህተምም አይቻለሁ፡፡ ደሞ ቢሮው ሄደን ላፕቶፕ፣ ፍላሽ፣ ሲዲ፣ መጽሔቶች አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ የሚፈልገውን እየለየ ፈርመናል፡፡ ወደቢሮው የሄድነው በመኪና ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ አድራሻችንን ይዘው ስለነበር ሰኔ 4….አይ 14/2006 ነው መሰለኝ ከማዕከላዊ ተጠርተን ላፕቶፕ ላይ የነበረውን ስዕሎችና የእንግሊዝኛ ንግግሮች ሲወጡ አይቻለሁ፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡›› ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

5. አምስተኛ ምስክር አጌና አንከና ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 48 ሲሆን ነዋሪነታቸው አ.አ ነው፡፡ የሚመሰክሩት ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ላይ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቸው፣ ‹‹ሰኔ 17/2006 ለግል ጉዳይ ማዕከላዊ ነበርኩ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ፖሊስ ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ላፕቶፑ ላይ አማርኛ ጽሑፎች አይቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹ የተከሳሹ ስለመሆናቸው አምኖ ሲፈርምባቸው ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ ይዘቱን ግን አላነበብኩትም፤ አልተረዳሁትም፡፡ የገጹን ብዛትም አላስታውስም፡፡›› የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

6. ስድስተኛ ምስክር ገብረጨርቆስ ገብረመስቀል ይባላሉ፡፡ የ50 ዓመት የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ምስክሩ በአስማማው ላይ ለመመስከር እንደመጡ ቢናገሩም በአካል ግን ለይተው አላወቁትም፡፡ እንዲያውም አስማማውን አሳዩ ሲባሉ አቤልን አሳይተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሎ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡት የተከሳሾች ጠበቆች አቃቤ ሀግ ያቀረባቸው ምስክሮች ወረቀት ሲፈረም አየን ከማለት ውጪ ምንም አይነት ለሂደቱ ቁም ነገር ያለው ምስክርነት የሚሰጡ አይደሉም ፡፡ ተከሳሾች ተገኘባቸው የተባለው ጽሁፍ የአደባባይ ዶክመንት ከመሆኑም በላይ አልተገኘብንም ብለን ክደን አልተከራከርንም በይዘቱ ላይ ክርክር ስላልተደረገ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብም ብዙ አልጨነቅንም ብለዋል፡፡አቃቤ ሀግ የወንጀሉን የመጀመሪያ ደረጃ ጭብጥ የሚያሳዬ ምስክሮችን ያቅርብ አይቅርብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱ ነገ ይቀጥላል፡፡

በተቃራኒው ምሳቸውን ችሎት ውስጥ የተመገቡት ሁሉም እስረኞች በጠንካራ መንፈስ ሆነው ሲጨዋወቱ እና ሲነጋገሩ ተስተውለዋል፡፡ የችሎቱ ተሳታፌዎች በምስክሮች መደናበር እየሳቁ ነበረ ሲሆን የዞን9 ወዳጆች አጋሮች ቤተሰብና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡

የዞን 9 ማስታወሻ

የዛሬውን አስቂኝ የፍርድ ቤት ውሎ ባልተካደ ነገር ላይ ወርቃማውን የተከሳሾች ሰአትም ሆነ የፍርድ ቤቱን የስራ ሰአት ማባከኑ የሚገርም ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ችሎቱ በግልጽ አንዲካሄድ መፍቀዱን በበጉ መልኩ ተመልክተነዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምስክሮቹ ደህንነት ሳይሆን የራሱን መዋረድ ለመቀነስ ሲል ችሎቱን በዝግ ለማድረግ መሞከሩ ተከትሎ የመጣውም የምስክሮች መወዛገብ ግልጽ የሚያደርገው ነው ፡፡ የዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ በተለያየ ቦታ የጻፏቸው የራሳቸው እና የሎሎች የአደባባይ ምሁራን ጽሁፎች በመሆናቸው ጽሁፉ የእኛ መሆኑ ምስክር አያሻውም ፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልነው ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የታሰሩት ወጣቶች ክስ የጸፉት ጽሁፍ ይዘት ላይ ነው፡፡ የታሰሩ ወዳጆቻችንን ለመፍታት አሁንም አልረፈደም ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለሚያሳዬ የዞን9 ወዳጆች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ህገ-መንግስታዊ መብት ይከበር ፡፡

ዞን9

Monday, March 30, 2015

“ከትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ በጎ ነገር ይመጣል ብሎ ማሰብ ከዕባብ ዕንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ ማመን ነው” – ሞረሽ ወገኔ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
አርብ መጋቢት ፲፰ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.           ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲፫
ሠሞኑን በትግሬ-ወያኔ፣ በግብፅ አረብ ሪፑብሊክ እና በሱዳን እስላማዊ አገዛዝ መካከል በአባይ ወንዝ የውኃ አጠቃቀም ላይ የሚያተኩር የጋራ የሥምምነት ሠነድ ተፈርሟል። የሥምምነቱ ሠነድ ለሕዝብ ይፋ የሆነው ማክሰኞ መጋቢት ፲፭ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. (Tuesday March 24, 2015)ነው። ሆኖም የሥምምነት ሠነዱ የወጣበት የካቲት ፳፮ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. (Thursday March 5, 2015) እንደሆነ በሠነዱ ራስጌ ላይ የሠፈረው ጽሑፍ ያመለክታል (ምንጭ፦ http://aigaforum.com/documents/Final-full-text-of-egypt-sudan-ethiopia-agreement-on-nile-use.pdf)። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የሦሥቱ አገዛዞች ገዢዎች እስካሁን ድረስ ዘግይተው ሠነዱን ለሕዝብ ይፋ ያደረጉበት ምክንያት ምናልባት ከሚገዟቸው አገሮች ሕዝብ ሊነሣባቸው የሚችለውን ተቃውሞ ለማለዘብ ታስቦ ይሆናል፣ ወይም ሌላ የተደበቀ አጀንዳ ይኖራቸዋል። ወጣም ወረደ ሠነዱ ለእያንዳንዱ አገር ሕዝብ፣ በተለይም ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የሚያመጣው በረከትም ሆነ የሚያወርደው መቅሠፍት ካለ ያንን በጥልቀት መመርመሩ እና ተገቢውን እርምጃ መውሰዱ የእያንዳንዱ ኃላፊነት የሚሠማው ዜጋ ግዴታ ነው።
Moreshየትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በአባይ ወንዝ የመብት ጥያቄ ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሉዓላዊነት አሣልፎ የሠጠው ገና ወደሥልጣን ከመጣ ሦሥት ዓመት ሣይሞላው ነው። በሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም.  (Thursday July 1, 1993) የያኔው የትግሬ-ወያኔ የሽግግር አገዛዝ ፕሬዘዳንት መለስ ዜናዊ ካይሮ ድረስ ሄዶ ከያኔው የግብፅ አምባገነን ገዢ ሆስኒ ሙባረክ ጋር አንድ ሠነድ ተፈራርሟል (ምንጭ፦ http://ocid.nacse.org/tfdd/tfdddocs/521ENG.pdf)። የዚያ ሥምምነት ዓላማ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ እና በገባር ወንዞቹ ላይ ያላትን ተፈጥሯዊ እና ሉዓላዊ መብት አሣልፎ የሚሠጥ መሆኑን በተለያዩ ባለሙያዎች እና ፖለቲከኞች የተተቸበት ጉዳይ ነው።
ሆኖም ከአራት ዓመታት በፊት ሟቹ የትግሬ-ወያኔዎች መሪ መለስ ዜናዊ በድንገት ተነስቶ «አባይን እንገድባለን» ሲል በኢትዮጵያውያን መካከል ያልተጠበቀ መከፋፈል ተፈጠረ፦ ከፊሉ «የዚህ ግድብ መገንባት ተገቢ ነው፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠቅማል፣ ወያኔንም በገንዘብ እና በማናቸውም መንገድ ልንደግፈው ይገባል» ብሎ ተነሣ። ከፊሉ ኢትዮጵያዊ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔ ለኢትዮጵያ የሚያስበው መልካም ነገርም ሆነ የሚያመጣው ጠቃሚ ነገር የለውም፤ እንዲያውም ለአሁኑ ብቻ ሣይሆን ለተከታዮቹም ኢትዮጵያውያን ትውልዶች የማይነቀል እና የተወሣሠበ የችግር ነቀርሣ ይተክላል» ብለው አምርረው ተቃወሙ። በዚህ መካከል ገለልተኛ ሆነው ከሁለቱም ወገን የሚወረወረውን የቃላት ጦርነት በትዝብት የሚከታተሉም አይጠፉም። ወጣም ወረደ መለስ ዜናዊ ያንን ያልተጠበቀ ቃሉን ከሠጠ ከዓመት በኋላ ቅዳሜ መጋቢት ፳፬ ቀን ፪ሺህ፫ ዓ.ም. (Saturday April 2, 2011) በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በ15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የግድቡን ሥራ አስጀመረ።
ሀገር ወዳድ እና ሃቀኛ ኢትዮጵያን አስቀድመው እንዳስጠነቀቁት፣ በግድቡ መገንባት ሥም የትግሬ-ወያኔ ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን አካበተበት፦ በመዋጮ ሥም በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ወደካዝናው አስገባ፣ በፖለቲካው ረገድ «ተቃዋሚ ነን» የሚሉትን ለመከፋፈል እና ለማዳከም ተጠቀመበት። ነገር ግን የግድቡ ሥራ በትክክል ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ሣይታወቅ ይኼው አራት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ቀርቶታል። የግድቡ ሥራ ከመጀመሪያውም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለታሪካዊ ጠላቶቿ አሣልፎ ለመስጠት መሆኑ አያጠራጥርም። ስለዚህ የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን አፈራርሶ፣ ዜጎቿን ከፋፍሎ፣ ግዛቷን ለውጭ ኃይሎች የመቸብቸብ የመጨረሻውን ግቡን ሣያሣካ እንደማያርፍ ማሰብ የማይችል ኢትዮጵያዊ ካለ የአዕምሮው ጤንነት የተቃወሰ ብቻ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ፣ የትግሬ-ወያኔዎች የተፈጥሮ ባሕሪያቸው የሆነውን የአገር ክህደት ድርጊታቸውን በመቀጠል፣ ባለፈው ሰኞ ዕለት መጋቢት ፲፮ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. (Monday March 23, 2015) የሠሞኑን የሥምምነት ሤራቸውን ሠነድ በድረ-ገፃቸው ላይ ይፋ አርገዋል (ምንጭ፦ (http://aigaforum.com/documents/Final-full-text-of-egypt-sudan-ethiopia-agreement-on-nile-use.pdf)። ስለሆነም «በዚህ የሤራ ሠነድ ካሉት አንቀፆች በተለይ የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን ኅልውና በእጅጉ የሚፈታተኑት የትኞቹ ናቸው?» ብሎ በጥንቃቄ መመርመሩ ተገቢ ነው። በተለይ፦
·               አንቀፅ 3፦ ፍትኃዊ የውኃ አጠቃቀም መርሆ (III. Principle of Equitable and Reasonable Utilization)
·               አንቀፅ 4፦ ሌላውን አካል ያለመጉዳት መርሆ (IV. Principle of Not to Cause Significant Harm)
·               አንቀፅ 5፦ የግድቡን ወኃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሙላት ስለሚያስፈልገው የትብብር ሥራ (V. Principle to Cooperate on the First Filling and Operation of the Dam)
በሚሉት አንቀፆች ላይ ኢትዮጵያውያን በጥልቀት ተወያይተው ብሔራዊ መግባባት እና የጋራ አቋም ላይ መድረስ ይገባቸዋል። እኒህ አንቀፆች እርስ በእርሣቸው በሚቃረኑ፣ በተድበሰበሱ እና የኢትዮጵያንም የወደፊት ኅልውና አደጋ ላይ በሚጥሉ አረፍተተገሮች የታጨቁ ናቸው። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በሠከነ መንፈስ፣ ሣንዘላለፍ፣ ነገሮችን በጥልቀት እየመረመርን ለችግሩ መውጫ መንገድ መፍትሔ የሚሆኑ ኃሣቦችን ማፍለቅ ይጠበቅብናል።
የዚህ የአዲሱ ሥምምነት ዓላማው በግልፅ፦ «እኛ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ማንም አዛዥ-ናዛዥ የሌለብን ገዢዎች ነን፣ ምን ታመጣላችሁ!» ለማለት ነው። ለነገሩ ከትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን መልካም ነገር ይመጣል ብሎ ማሰብ ከዕባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ የማመን ያህል ቂልነት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ተገቢውን የተግባር ምላሽ ልንሠጥ ይገባል። ይህንን ማድረግ ካልቻልን ግን የዚህ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከአገር አፍራሹ እና ሻጩ የትግሬ-ወያኔ ባልተለየ ከሃዲዎች በመሆናችን በታሪክ ከተጠያቂነት አናመልጥም።
ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

Thursday, March 26, 2015

ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!

አለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ሰንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልና መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውና አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።

ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባ ታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖችመናገር እንጂ መስማት የማ ችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝባ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለ ውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።

ለሚነሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና ህዝባዊ የመብት ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሾች እስር፤ አፈናና ግድያ ከሆነ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው። በእስር ፤በአፈናና በግድያ እንዲሁም በሰራዊት ሀይል ህዝብን በማሸማቀቅ በስልጣን መቆየት የሚቻል ቢሆን ደርግም ከቤተ-መንግስት ባልወጣ፤ ወያኔም ዛሬ ከቤተ-መንግስቱ ባልተንፈልለሰ ነበር። ይህ ደግሞ ሊያስተምር በተገባ ነበር።

እስከ ዛሬ የትኛውም አንባገነን ስርአት በሚተማመንበት የወታደራዊ ሀይል አማካይነት የመንኮታኮቻቸውን ሰአት በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት የቻለ እንደሌለ ሁሉ ወያኔም ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል ሲያርመሰምስ ውሎ ቢያድር ውድ ቀቱን በአንድ ሰኮንድ ማዘግየት እንደማይችል በተለይ እንቢ ለነፃነቴ፤ እንቢ ለሀገሬ… ብለን ለትግል የተነሳን ሀይሎች በመረ ዳት፤ ይበልጡኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀጣጠለ ያለውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይበልጥ እያሰፋን የጀመርነውን የነፃነት ጉዞ ከነፃነታችን አደባባይ ለማድረስ ሌት ተቀን የመስራት ሀላፊነታችናና መወጣት ይገባናል።

በጎንደር የሚታየውን የአልገዛም ባይነት ትንቅንቅ በሌሎች ክልሎችም በማቀጣጠል፤ በደብረወርቅ የታየውን የመምህራን የስራ ማቆም አድማ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት፤ እንደ ድምፃችን ይሰማ ሁሉ ተቃውሞን ወደ እንቢተኝነት በማሸጋ ገር …… ወዘተ የነፃነታችንን ቀን ለማቅረብ መከፈል የሚገባውን መክፈል ይገባናል።

በደርግ ል የተነሳው እንቢተኝነት እያየለ ሲመጣ ያሰለፈው ሰራዊት ወያኔን አጅቦ የደርግን ቀብር እንደቆፈረለት ሁሉ ዛሬም በወያኔ ላይ እየተቀጣጠለ የሚገኘው ህዝባዊ እንቢተኝነት እየጠነከረ በመጣ ቁጥር የደረደረው ሰራዊት የወያኔን ቀብር ቆፋሪ ከመሆኑ እንደማኢመለስ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን በመማር ነፃነታችንን ለማስከበር የጀመርነውን የእንቢተኝነት ትግል በ መ ላው የሀገራችን ክፍሎች በማስፋትና በማቀጣጠል አይቀሬውን የወ ኔ ቀብር ለማቅረብ በአንድነት የነፃነት ጉዞውን እንቀ ላቀል። የጀመርነው የነፃነት ጉዞ መቆሚያው የነፃነታችን አደባባይ መሆኑን በተግባር ከምናሳይበት ወቅት ላይ እንገኛለንና በአንድነት እንነሳ!!!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!

Tuesday, March 24, 2015

ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም!

ከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚል ዜና ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የህዳሴዉ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ባካሄዱት ጥናት መሠረት የህዳሴዉ ግድብ ፕሮጀክት ባጋጠመዉ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ መወሰኑን የሚያወሳ ዜና ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰሩ ምንም አይነት ስራዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከየትኛዉም አገር መንግስትና መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶችና ዉሎች ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም አርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ከሚመለከቱና በሚስጢር መጠበቅ አለባቸዉ ተብሎ ከሚታመኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዉጭ ሌላ ምንም ስራ ወይም አለም አቀፍ ስምምነትና ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ በድብቅ መደረግ የለበትም የሚል የጸና እምነት አለዉ። ሆኖም ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አገዛዝ ኢትዮጵያን ከቅኝ ገዢዎች በከፋ መልኩ የሚገዛ የጥቁር ፋሺስቶች አገዛዝ በመሆኑ የሚሰራቸዉ ስራዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈርማቸዉ ዉሎችና ስምምነቶች የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅም የሚጻረሩና የሚጋፉ ድብቅ ስምምነቶች ናቸዉ።

Monday, March 23, 2015

የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸምኩ የሚለው ቅዠት ነው ተባለ * “እንኳን የአየር ድብደባ ይቅርና ሞቅ ያለ ጭብጨባም አልተሰማም”

ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት በኤርትራ በማይ እዳጋ የሚገኘው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ላይ የአየር ጥቃት አደረስኩ ብሎ ከገለጸ በኋላ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ምንም አይነት ጥቃት እንደደረሰበት የገለጸው ነገር አልነበረም:: አስመራ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በማይ እደጋ እንኳን የአየር ድብደባ ይቅርና ሞቅ ያለ ጭብጨባም አልተሰማም::

በኤርትራ ይህን የወርቅ ማዕድን የሚያወጣው የካናዳው የማዕድን አውጪ ድርጅት ማምሻውን በድረገጹ  ባወጣው መግለጫ የአየር ጥቃት እንደደረሰበት አልገለጸም:: ድርጅቱ ማርች 13 ቀን 2015 ልክ በማንኛውም መስሪያ ቤት እንደሚደርስ አደጋ መጠነኛ መሰባበር የደረሰበት ቢሆንም ጥገና አድርጎ ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል:: ይህ ጉዳት የደረሰበት የሕወሓት መንግስት እንደሚለው በአየር ጥቃት እንደሆነ ካምፓኒው ያስቀመጠው ነገር የለም::

የሕወሃት መንግስት ለምን ይህ ዜናን ማሰማት ፈለገ? የሚለውን ዘ-ሐበሻ ወደ አስመራ ምንጮቿ ጋር ደውላ የነበረ ሲሆን ምንጮቹም “የሕወሓት መንግስት ይህን ዜና ማሰራጨት የፈለገው ከፍራቻ የተነሳ ነው:: በዚህ በሚሻዕ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በማንኛውም ድርጅት ውስጥ እንደሚፈጠር መጠነኛ የማሽኖች መሰባበር አደጋ መፈጠሩን የወያኔ ደህነንቶች መረጃ አላቸው:: የዚህ ድርጅት አካባቢ ደግሞ የኢትዮጵያ ነፃነት ታጋዮች የሚገኙበት ወታደራዊ ካምፖች አሉ:: አደጋው ከደረሰ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት እንደፈጸመ ማውራቱ ከገባበት ውጥረት የሕዝቡን አመለካከት ለመቀየር ነው” ብለዋል::
በተለይም በጎንደር አካባቢ በሕወሓት ወታደሮች እና በጎንደር ሕዝብ መካከል በተፈጠረው ውጥረት በዛሬው ዕለት 4 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎና ሰሞኑንም ሕዝቡ ጠመንጃ እየያዘ ጫካ እየገባ በመሆኑ ይህን ለማስቀየስ የሕወሓት መንግስት የቀየሰው የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው ሲሉ እነዚሁ ወታደራዊ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

Friday, March 20, 2015

ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።

በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።

አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት።በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው። በመረጥነው የትግል ስትራቴጂ መሠረት በሁለቱም ግንባሮች – ማለትም፣ በሕዝባዊ አመጽ እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት ግንባሮች ሥራዎች መሠራት አለባቸው። ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስትራቴጂዎች አኳያ መደራጀት ይኖርበታል። ሕዝባዊ የአርበኛ ሠራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሁሉ በኢትዮጵያከተሞችና ገጠሮች፤ በሥራና በመኖሪያ አካባቢዎች በምስጢር የተደራጁ ሕዝባዊ የአርበኛ ሲቪል ክበቦችም በብዛት መደራጀት ይኖርባቸዋል።

በዚህም ምክንያት አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከህወሓት ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲደራጅ ጥሪ ያቀርባል! እያንዳንዱ ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነውና ከሚመስለው ወዳጁ ጋር ይቧደን፤ ቡድኑንም በሥርዓትና በሚስጢር ያደራጅ።

ከእንግዲህ “ምን እንሥራ? ትግሉን እንዴት እንርዳ?” እያሉ ለሚጠይቁ ወገኖቻችን በሙሉ መልሳችን “ከቻላችሁ ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ” የሚል ነው። ድርጅት ኃይል ነው። መደራጀት በራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥርዓት ሲዋቀርና በሥነሥርዓት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ አደራጅና አስተባባሪ እንዲመጣለት ሳይጠብቅ በራስ አነሳሽነት እንዲደራጅ ይህ ጥሪ ተላልፏል።

በሥርዓት የተደራጀ ስብስብ ሲኖር የሚሠራ ሞልቷል። ይህንን መንገርም አያስፈልግም። የተደራጀ ስብስብ ራሱ ሥራዎችን አቅዶ መሥራትም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ለአብነት ተዘርዝረዋል።

የተደራጀ ስብስብ ጠላትና ወዳጁን ይለያል። የጠላቱን ጥንካሬና ድክመቱን ከራሱ ጥንካሬና ድክመት ጋር መዝኖ የወገን ኃይልን ጥንካሬ የሚያጎለብቱ፤ ድክመቶቹን የሚቀንሱ እርምጃዎችን በመውሰድ አቅሙን ይገነባል።
የተደራጀ ስብስብ የጠላትን እንቅስቃሴ እየሰለለ መረጃ ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ ያደርጋል።
የተደራጀ ስብስብ የተቀናጀ የሕዝባዊ እንቢተኝነት ተግባራትን ይፈጽማል። ለምሳሌ፣በሥርዓቱ የደረሰበትን ምሬት በወረቀት ገንዘብ፣ በአስፋልት፣ በታክሲዎችና በግድግዳዎች ላይ ይጽፋል፤ ገንዘቡን የኤፈርት ንብረት ከሆነው ውጋጋን ባንክ ያስወጣል፤ መዋጮዎችና ግብር ያጓትታል ከዚያም አልፎ አልከፍልም ይላል።
የተደራጀ ስብስብ በሥርዓቱ ላይ ለማመጽ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ሁኔታች ተሟልተው አመጽ ሲቀሰቅስ ደግሞ ትግሉ ግቡን ሳይመታ እንዳይበርድ ፀንቶ ይቆማል።
የተደራጀ ስብስብ ወዳጆቹን አስተባብሮ በጥንካሬው ላይ ተመርኩዞ በአካባቢው ባለ የህወሓት ኃይል ላይ ክንዱን ያነሳል።
በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባባሪና መመሪያ የሚጠብቅበት ጊዜ አልፏል። ህወሓት የዘረጋው የአፈና ሥርዓት የጠበቀ ትስስርና ቁጥጥር ያለው ድርጅት ማቆም እንዳይቻል አድርጓል። ስለሆነም ያለን አማራጭ በርካታ ያለዘወትር የበላይ አካል ትክክል ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ስብስቦችን በመላው የአገራችን ክፍሎች በአፋጣኝ ማደራጀት ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይቻላል።

ወቅቱ ህወሓትን ከጫንቃችን ላይ ለማውረድ የምንደራጅበት ነው። ድርጅት ኃይል ነው፤ አደራጅና አስተባባሪ ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ዛሬውን እንደራጅ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Wednesday, March 18, 2015

ልዩነታችን ጌጣችን፤ አንድነታችን ህልውናችን ነው

ኢትዮጵያ ስንል ብዙ የተለያዩ ዘውጎች፤ ብዙ የተለያዩ ቋነወቋዎችና ሀይማኖቶች በአንድነት ይዛና አስተሳስራ ብዙ ፈተ ናዎችን በማለፍ ለረጅም ዘመናት ህልውናዋን ጠብቃ የቆየች ሀገር መሆንዋ መታወቂያዋ ሀገር ማለት ነው። እንዳ ሳለ ፈችው ረጅም ዘመናት ሁሉ እንደየዘመኑ በህልውናዋ ላይ ይቃጣ የነበረውን ጥቃት እነዚያ በዘውጎች፤ በቋነወቋዎችና ሀይ ማኖቶች የተንቆጠቆጡት ልጆችዋ በአንድነት በመሰለፍ ብሎም ድል በመምታት ህልውናዋን አስጠብቀው መዝለቃቸው የነጻነት ሀገር የመሆን መለያዋ ምክንያቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው።

ይህ ልዩነታችንን ጌጡ አድርጎ ያስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነት በነፃነት የዘለቀ ህዝብ ከማድረግ አልፎ በአንድ ወቅት የስልጣኔ ምንጭና የአለማችን ሀያል ህዝብ ከመሆን ጫፍ አድርሶን እንደነበር አይዘነጋም። በዚያው ልክ ይህ በልዩነታችን ላይ የተገነባ አንድነታችን ሲላላ ህልውናችን ከገደል አፋፍ ላይ የደረሰበት ዘመንም በታሪካችን ውስጥ መታየቱ አልቀረም። “ዘመነ-መሳፍንት” በመባል የሚታወቀው ጥቁር የታሪካችን ክፍል አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ሌላው ዛሬ የምንገኝበት የወያኔ ዘረኛ ዘመን ነው። ትናንት በዘመነ መሳፍንት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር፤ ዛሬም በወያኔ ዘረኞች ዘመን ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ እንዲገኝ ተደርጓል። በአጭሩ ልዩነታችን ጌጣችን አንድነታችን ደግሞ የህልውናችን ማስጠበቂያ ዋነኛው ቁልፍ መሆኑን መገንዘብ ለማናም አያዳግትም።

ሌላው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በታሪካችን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በህልውናችው ላይ የከፋ አደጋ ያንዣበበት ወቅት ላይ መገኘታቸው ከማንም የተሰወረ አይደለም። ዘመነ መሳፍንት ትናንት ቋንቋ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለይ በእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ ህይወት ላይ አስከትሎት የነበረውን ችግርና በሀገሪቱም ከአዘቅት የከተተ ከመሆኑም በላይ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ውደ ቀድሞ ታላቅነቷ ለመመለስ ከባድ መሰናክል ተክሎ ማለፉን ከትናንት ታሪካችን መረዳት እየተቻለ ዛሬ በእኛ ዘመን ዳግም ከትናንቱ የከፋ ጥልቅ አዘቅት ውስጥእንድንፈቅ በዘረኞች እየተገፋን መሆኑንና ሊያስከትል የሚችለውንም ውጤት ለመረዳት የተለየ እውቀት አይፈልግም። ዛሬ ይህ ልዩነትን እያጎሉና ቂም በቀልን እየዘሩ መጓዛ የጥቂቶች ፍላጎት መሆኑ ባይካድም ከዚህ ቀደም ያስከተለውንና ዛሬም እየታየ ያለውን አደጋ ተገንዝቦ ከወዲሁ መከላከል የእያንዳዳችን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።

ጥቂቶች የህዝብ አሳቢ በመምሰል የሚረጩት የልዩነት መርዝ በሌሎች ሀገራት ላይ ያስከተለውን ፈተናም እንዲሁ ቆ ም ብሎ መፈተሽና ውጤቱንም መመዘን የፈሰሰ ውሀን አፋሽ ከመሆን ማዳኑን መጠራጠር የለብንም። የሶቭየት ህብረት መ ፍረስ፤ የዩጎዝላቪያ እርስ በርስ መባላት፤ የሶማልያ መቋጫ ያጣ ትርምስ ……. ወዘተ ንፁሀንን በገፍ የበላና ዜጎችን ለኢኮኖሚ ድ ቀት የዳረገ፤ በገፍ ስደትን ያስከተለ፤ የጦርነቶቹ መዘዝ ከልጅ ልጅ የማይታረቅ ቂም እያስቋጠረ መገኘቱ ሲታይ ዛሬ በእ ኛም ሀገር ጥቂት የመገንጠል አባዜ የተጠናወታቸው ይዘውን ሊጓዙ የሚፈልጉበትን መንገድ የት ሊያደርሰን እንደሚችል ከራ ሳችንም ያለፈ ታሪክ ሆነ በአለማችን ላይ የታዩ ክስተቶች ውጤት የሆነውን ትርምስና ሽብር በመመልከት ልንማርበትና ከወዲሁ አንድነታችንን በማጠናከር ለመከላከል መስራት ግድ ይለናል።

ከላይ እንደ ምሳሌ የተጠቀሱት ሀገራት በመበታተን ያተረፉተረ ሽብረ፤ ጦርነት፤ ስደትና ድህነት መሆኑ የታዘብነው የዘመናችን ክስተት ሲሆን ቀደም ሲል ለሁለት ተከፍላ የነበረችው ጀርመን ዳግም ከሁለትነት ወደ አንድነት መምጣቷዋ በሰጣት ሁለንተናዊ ጥንካሬ የዓለምችን ታላላቅና ሀብታም ሀገራት በኢኮኖሚ ውድቀት ሲመቱ ያለአንዳች ጭግር የፈተናውን ወቅት ያለፈች ሀገር ለመሆን መብቃትዋን ከአንድነት ሊገኝ የሚችለውን ሁለንተናዊ ጥንካሬ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። ሌላው ከሀ ገራችን ህልውናን የማስጠበቅ ፍልሚያ ታሪኮች ውስጥ ጎላ ብሎ የሚታየው የአድዋ ጦርነትና ድል የአንድነትን ዋጋ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ አኩሪ ታሪክ ነው። በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪበ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ የኢጣልያ ጦር በተመጣጣኝ የጦር መሳሪያና የሰለጠነ ሰራዊት ሳይሆ ን ቋንቋ፤ ዘውግና ሀይማኖት ሳይለያቸው ሁሉም በአንድነት ለሀገራቸው ህልውናና ለነፃነታቸው በአንድነት በመቆማቸው የተ ገኘ ድል መሆኑም መዘንጋት የለበትም።

ኢትዮጵያችን ደሀ ናት? አዎ ደሀ ናት። ህዝቧም ለዘመናት አንባገነን ስርአቶች እየተፈራረቁበት ህይወቱ የስቃይና የመከራ ሆኖ ቆይቷል? አዎ ቆይቷል። ሀገራችንን ከድህነትና ከዃላ ቀርነት፤ ህዝቧንም ከስቃይና ከመከራ ህይወት አውጥቶ የተሻለ ሀገር፤ ለመፍጠር ዛሬ የወያኔ ዘረኛ ቡድን የሚያራምደው የመንደር ፖለቲካ እውን መፈትሄ ነውን? ብለን ስንጠይቅ ያለፉት 23 የወያኔ የስልጣን ዘመናት እውነቱን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ህዝብ በጅምላ ስደት፤ ለቁጥር በሚታክት ሁኔታከመኖሪያ ቀዬ መፈናቀል፤ እስር ቤት በእስር ቤተረ መገንባት፤ እናትና ልጅ ተፈራርተው መመካከር ያልቻሉበት ዘመን፤ ድህነት ከሚባለው ደረጃ ተወርዶ ጭራሽ የሆቴል ትርፍራፊ በጉርሻ የሚሸጥበት ዘግናኝ ወቅት ላይ ለመገኘት ምክኒያት ከመሆኑም በላይ ሀገር አለኝ ብሎ መኩራት እንኳ ከማይቻልበት ህልውናችን ከከፋ አደጋ ላይ የሚገኝበት ወቅት ሆኖ እናገኘዋለን።

ዜጎችን ነቋንቋ በዘውግና በሀይማኖት ከፋፍሎ ለመግዛት የሚያራምደው በታኝ የጥፋት ፖለቲካ ሌላው ቢቀር ዛሬ በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ የማደር ሰዋዊ መብት እንኳ ማስከበር ከማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ ከእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም። በአንባገነኖች የተጫነበትን የአገዛዝ ቀንበር አስወግዶ የነፃነት አየር የሚተነፈስበት፤ ፍትህ የሰፈነበትና መብቶች የተከበሩበት ሀገር ለመፍጠር በተከፊለ የህዝብ ልጆች የህይወት ዋጋ ለስልጣን የበቃው ወያኔ በማር በተለወሰ መርዘኛ የዘር ፖለቲካው ሳቢያ የተገኘው ውጤት የእለት ጉርስን እስከማጣት የደረሰ ሆኗል ማለት ነው።

በአጭሩ ዛሬ ከ23 አመታት በዃላ እንደ ትናንቱ ሁሉ ይህን ርእሰ-ጉዳይ ማንሳታችን ያለ ምክንያት አይደለም። ይህ በለዩነታችን መካከል ለመገንባት ደፋ ቀና የሚባልለት የልዩነት አጥር እስካሁን የተፈለገውን ያህል ባይሳካም በጠንካራው አንድነታችን ላይ ያጠላው ጥላ ለምን አይነት አሰቃቂ ህይወት የዳረገን መሆኑና ጥያቄዎቻችን ለሆኑት ፍትህ፤ እኩልነትና ነፃነት ምላሽ ከማስገኘት ይልቅ ይባስ ለከፋ አፈናና አገዛዝ የዳረገን መሆኑን ተገንዝበን ቀኑ ሳይመሽ ከወዲሁ ለመፍትሄው በጋራ መስራትብቸኛ አማራጭ መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘበው ነው።

3000 ዘመን ያለ ፈተና የተቆጠረ የነፃነት ዘመን አይደለም። የገጠሙን ፈተናዎች በሙሉ በልዩነቶቻችን ላይ በተገነባው ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ተጠብቆ የተገኘ እንጂ…… ዛሬም ቢሆን ዜጎች ልዩነቶቻቸውን የጥንካሬያቸው መሰረት በማድረግ በአንድነት ነፃነታቸው የተረጋገጠበት፤ መብቶቻቸው የተከበሩበት፤ ፍትህ የሰፈነበት ሀገር ለመፍጠር የተጀመረውን ሁለገብ ትግል በማጀብ ከዳር ለማድረስ ለመነሳት ያለፉት 23 አመታት ከበቂ በላይ መሆኑን አጢነን በቃ የምንልበት ወቅት ላይ እንደምንገኝ ለማሳሰብ ነው።

ትናንትም ዛሬም ነገም ልዩነቶቻችን ጌጣችን አንድነታችን ህልውናችን መሆናቸውን ተረድተን ሳይመሽ ሁላችንንም በእኩልነት የማታስተናግድ የሁላችንን ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ!!!!!

ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!!!!

Saturday, March 14, 2015

Freedom House 2015 Report: Ethiopia’s Status NOT FREE

Freedom in the World : Ethiopia

Overview:

In 2014 the Ethiopian government continued to suppress free speech and associational rights, shattering hopes for meaningful reform under Prime Minister Hailemariam Desalegn. Government harassment and arrest of prominent opposition and media members continued, including the April arrest of nine journalists who were charged under Ethiopia’s controversial antiterrorism law. In April and May, massive protests in Oromia Regional State broke out following the announcement of the planned expansion of Addis Ababa into Oromia. At least 17 people died after the military fired on unarmed protesters.

Despite nascent signs of an opening with Eritrea, formal dialogues remain frozen between the two countries. The Ethiopian-Eritrean border remains highly militarized, though no major border clashes were reported in 2014.

Sporadic violence resumed in Ethiopia’s Ogaden region after talks failed in 2013 between the government and the Ogaden National Liberation Front (ONLF), a separatist group that has fought for independence since 1991. In January 2014, two ONLF negotiators dispatched to Nairobi for a third round of talks were abducted and allegedly turned over to Ethiopian authorities by Kenyan police. The kidnappings effectively ended the talks.

Ethiopia ranked 32 out of 52 countries surveyed in the Ibrahim Index of African Governance, below the continental average and among the bottom in East Africa. The country’s modest gains in the index are due to its improvement in human development indicators, but its ranking is held back by low scores in the “Participation and Human Rights” category.
Political Rights and Civil Liberties:

Thursday, March 12, 2015

በህወሓት ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎች ሁሉ ወደ እምቢተኝነት ይደጉ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን ይሰማ ኦርቶዶክሶች”፣ “ድምፃችን ይሰማ መምህራን”፣ “ድምፃችን ይሰማ ተማሪዎች”፣ … ወዘተ። በተለይ ሙስሊም ወገኖቻችን በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያሉ ሲወተውቱ ሦስት ተከታታይ ዓመታት አልፈዋል። ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በማለታቸው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
አቤቱታ የሚሰማ ጆሮ የሌለው አገዛዝ ሲገጥም ምን ይደረጋል? ለአቤቱታ አቅራቢው ያለው ምርጫ ከሁለት አንድ ነው። ወይ አቤቱታን እርግፍ አድርጎ ጥሎ በደልን ተቀብሎ “እህህ !” እያሉ መኖር፤ አሊያም “በቃኝ፣ እንቢ አልገዛም” ማለት፤ ሦስተኛ ምርጫ የለም።

አቤቱታ ሰሚ ሲያጣ እና ሕዝብ መሮት “እንቢኝ፣ አልገዛም” ሲል ነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ የሚባለው። ሕዝባዊ እምቢተኝነት ብዙ መልኮችና ቅርጾች ቢኖሩትም ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ሁለት ናቸው። አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የሚፈልገውን አለማድረግ እና/ወይም አገዛዙ ሕዝብ እንዲያደርግ የማይፈልገውን ማድረግ።

ለምሳሌ፣ አገዛዙ ሹማምንቱ እንዲከበሩ፣ ሕዝብ እንዲታዘዝላቸው ይፈልጋል፤ እንቢ ያለ ሕዝብ ግን የአገዛዙን ሹማምንት ይንቃል፣ በየደረሱት ያዋርዳቸዋል፣ “አልታዘዛችሁም” ይላቸዋል። ማንኛውም መንግስት የዳኝነት ሥርዓቱ እንዲከበርለት ይፈልጋል፤ በደል የመረረው ሕዝብ ግን የአምባገነኖች ችሎት ውሳኔ አይቀበልም፤ ዳኞችንም ዳኝነትንም አያከብርም። ሕዝብ የመንግሥትን ግብር በወቅቱ እንዲከፍል የማንኛውም መንግሥት ፍላጎት ነው። በመንግሥት ያመረረ ሕዝብ ግን ግብር አይከፍልም፤ መክፈል ግድ ከሆነበትም አዘግይቶ፣ አስለፍቶ ነው። የመረረው ሕዝብ ምሬቱን መፃፍ በሌለበት ቦታ ይጽፋል። በደል የበዛበት ሕዝብ “ዝም በል” ሲሉት ይናገራል፤ “ተናገር” ሲሉት ዝም ይላል።

አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝባዊ እምቢተኝተኝነት እርምጃዎች ጅምሮች እየታዩ ነው። በአማራ ክልል፣ ሕዝብ በሹማምንት ላይ የራሱን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። ሕዝብ ራሱ የፓሊስንም የፍርድ ቤትንም ሥራ ተክቶ እየሠራ ነው። ይህ መበረታታት ያለበት ትልቅ እርምጃ ነው። እንደዚሁም ሁሉ በተለይ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል።

በተጓዳኝ በርካታ አማራጭ ስልቶች ሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ፣ ተቀማጭ ገንዘብን ከህወሓት ባንኮች ማውጣት በቀላሉ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በውጋጋን ባንክ ተጀምሮ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ከዚያም ወደ ንግድ ባንክ ማሸጋገር ይቻላል።
በወገኖቻችን ላይ የግፍ ፍርድ የሚያስፈርዱ አቃቢያነ ህግ እና የግፍ ብይኖችን የሚሰጡ ዳኞች በቸልታ ሊታለፉ አይገባም። በእስር ቤቶችም በወገኖቻችን ላይ ሰቆቃ እየፈፀሙ ያሉ ጨካኞች ከሰላማዊ ሕዝብ ጋር ተደባልቀው ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነዚህ ሁሉ ሊወገዙ፣ ሊገለሉ፣ በየደረሱበት ሊዋረዱ ይገባል።

በአገዛዙ መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን በሥራቸው ላይ መለገም ተቀባይነት ያለው በጎ ተግባር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል። ከአምባገነን ሥርዓት ጋር መተባበር እኩይ ተግባር ሲሆን አምባገነን ሥርዓትን ከውስጥ መቦርቦር ደግሞ የሚበረታታ ሰናይ ሥራ ነው።

ለወያኔ አገዛዝ ግብር መክፈል የምናቆምበት ሰዓትም ተቃርቧል። በራሳችን ገንዘብ ገዳዮቻችን እንዲሰለጥኑብን መፍቀድ የለብንም። ስለሆነም “ግብር አንከፍልም”፤ “መዋጮዎቻችሁ አይመለከቱንም” የምንልበት ቀን ቀርቧል።
በፋይዳ የለሽ ምርጫ የሀገር ሀብት ሲመዘበር ማየት አንሻም። በአግባቡ ለማይቆጠር ድምፃችን አንድም ደቂቃ የምናባክንበት ምክንያት የለምና ሁላችንም የምርጫ ካርዶቻችንን ቀዳደን ቁርጭራጮቹን በየመንገዱ ልንበትናቸው ይገባል።
እነዚህን እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው የሕዝባዊ እምቢተኝነት የመጀመሪያ ደረጃዎች። እነዚህን እያደረግን በምስጢር መደራጀታችንን እንቀጥል። ከጥቂት በኋላ አምባገነኑን ሥርዓት የሚያንበረክክ ኃይል እንፈጥራለን። ጥቃት ቢደርስ የሚመክት ኃይል የተደራጀ በመሆኑም ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ተቀናጅተው እንዲሄዱ ይደረጋል።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሕዝባዊ እምቢተኝነትንና ሕዝባዊ አመጽን አቀናጅቶ ለመምራት የተዘጋጀ፤ ለዚህ የሚያበቃው ድርጅታዊ አቅም እየገነባ ያለ ድርጅት ነው። አርበኞች ግንቦት 7 “እንሰባሰብ በወያኔ ላይ የምናቀርባቸው ተቃውሞዎች በሙሉ ወደ እምቢተኝነት ከፍ እናድርጋቸው” ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Tuesday, March 10, 2015

Ethiopia: Amnesty International Report 2014/15

Federal Democratic Republic of Ethiopia
Head of state: Mulatu Teshome Wirtu
Head of government: Hailemariam Desalegn
 of expression continued to be subject to serious restrictions. The government was hostile to suggestions of dissent, and often made pre-emptive arrests to prevent dissent from manifesting. Independent media publications were subject to further attack. Peaceful protesters, journalists, and members of opposition political parties were arbitrarily arrested. The Charities and Societies Proclamation continued to obstruct the work of human rights organizations. Arbitrary detention and torture and other ill-treatment were widespread, often used as part of a system for silencing actual or suspected dissent.

Background

Economic growth continued apace, along with significant foreign investment including in the agriculture, construction and manufacturing sectors, large-scale development projects such as hydroelectric dam building and plantations, and widespread land-leasing, often to foreign companies.

The government used multiple channels and methods to enforce political control on the population, including politicizing access to job and education opportunities and development assistance, and high levels of physical and technological surveillance.

The politicization of the investigative branch of the police and of the judiciary meant that it was not possible to receive a fair hearing in politically motivated trials.

Federal and regional security services were responsible for violations throughout the country, including arbitrary arrests, the use of excessive force, torture and extrajudicial executions. They operated with near-total impunity.

Armed opposition groups remained in several parts of the country or in neighbouring countries, although in most cases with small numbers of fighters and low levels of activity.

Access to some parts of the Somali region continued to be severely restricted. There were continuing reports of serious violations of human rights, including arbitrary arrests and extrajudicial executions. There were also multiple allegations of the rape of women and girls by members of the security services.

Excessive use of force ‒ extrajudicial executions

In April and May, protests took place across Oromia region against a proposed “Integrated Master Plan” to expand the capital Addis Ababa into Oromia regional territory. The government said the plan would bring services to remote areas, but many Oromo people feared it would damage the interests of Oromo farmers and lead to large-scale displacement.

Security services, comprising federal police and military special forces, responded with excessive force, firing live ammunition at protesters in Ambo and Guder towns and Wallega and Madawalabu universities, resulting in the deaths of at least 30 people, including children. Hundreds of people were beaten by security service agents during and after the protests, including protesters, bystanders, and parents of protesters for failing to “control” their children, resulting in scores of injuries.

Thousands of people were arbitrarily arrested. Large numbers were detained without charge for several months, and some were held incommunicado. Hundreds were held in unofficial places of detention, including Senkele police training camp. Some detainees were transferred to Maikelawi federal police detention centre in Addis Ababa. Over 100 people continued to be detained in Kelem Wallega, Jimma and Ambo by security service agents after courts ordered their release on bail or unconditionally.

Many of those arrested were released after varying detention periods, between May and October, but others were denied bail, or remained in detention without charge. Others, including students and members of the Oromo Federalist Congress (OFC) opposition political party, were prosecuted and convicted in rapid trials on various charges relating to the protests.

Freedom of expression, arbitrary arrests and detentions

2014 saw another onslaught on freedom of expression and suggestions of dissent, including further targeting of the independent media and arrests of opposition political party members and peaceful protesters. Several attempts by opposition political parties to stage demonstrations were obstructed by the authorities. The Anti-Terrorism Proclamation continued to be used to silence dissidents. Opposition party members were increasingly targeted ahead of the 2015 general election.

In late April, six bloggers of the Zone 9 collective and three independent journalists associated with the group were arrested in Addis Ababa, two days after the group announced the resumption of activities, which had been suspended due to significant harassment. For nearly three months, all nine were held in the underground section of Maikelawi, denied access to family members and other visitors, and with severely restricted access to lawyers.

In July, they were charged with terrorism offences, along with another Zone 9 member charged in their absence. The charge sheet cited among their alleged crimes the use of “Security in a Box” – a selection of open-source software and materials created to assist human rights defenders, particularly those working in repressive environments.

Six of the group said they were forced to sign confessions. Three complained in remand hearings that they had been tortured, but the court did not investigate their complaints. The trial continued at the end of 2014.

Early in 2014, a “study” conducted by the national Press Agency and Ethiopian News Agency and published in the government-run Addis Zemen newspaper targeted seven independent publications, alleging that they had printed several articles which “promoted terrorism”, denied economic growth, belittled the legacy of former Prime Minister Meles Zenawi, and committed other “transgressions”. In August, the government announced that it was bringing charges against several of the publications, causing over 20 journalists to flee the country. In October, the owners of three of the publications were sentenced in their absence to over three years’ imprisonment each for allegedly inciting the public to overthrow the government and publishing unfounded rumours.

The OFC opposition party reported that between 350 and 500 of its members were arrested between May and July, including party leadership. The arrests started in the context of the “Master Plan” protests, but continued for several months. Many of those arrested were detained arbitrarily and incommunicado. OFC members were among over 200 people arrested in Oromia in mid-September, and further party members were arrested in October.

On 8 July, Habtamu Ayalew and Daniel Shebeshi, of the Unity for Democracy and Justice (UDJ) Party, and Yeshewas Asefa of the Semayawi Party were arrested in Addis Ababa. Abraha Desta of the Arena Tigray Party, and a lecturer at Mekele University, was arrested in Tigray, and was transferred to Addis Ababa. They were detained in Maikelawi and initially denied access to lawyers and family. In late October, they were charged under the Anti-Terrorism Proclamation. Yeshewas Asefa complained in court that he had been tortured in detention.

The Semayawi Party reported numerous arrests of its members, including seven women arrested in March during a run to mark International Women’s Day in Addis Ababa, along with three men, also members of the party. They had been chanting slogans including “We need freedom! Free political prisoners!” They were released without charge after 10 days. In late April, 20 members of the party were arrested while promoting a demonstration in Addis Ababa. They were released after 11 days.

In early September, Befekadu Abebe and Getahun Beyene, party officials in Arba Minch city, were arrested along with three party members. Befekadu Abebe and Getahun Beyene were transferred to Maikelawi detention centre in Addis Ababa. In the initial stages of detention, they were reportedly denied access to lawyers and family members. In late October, party member Agbaw Setegn, was arrested in Gondar, and was also transferred to Maikelawi, and held incommunicado without access to lawyers or family.

On 27 October, editor Temesgen Desalegn was sentenced to three years’ imprisonment for “defamation” and “inciting the public through false rumours”, in the now-defunct publication Feteh, after a trial that had lasted more than two years. The publisher of Feteh was also convicted in their absence.

People were detained arbitrarily without charge for long periods in the initial stages, or throughout the duration, of their detention including numerous people arrested for peaceful opposition to the government or their imputed political opinion. Arbitrary detention took place in official and unofficial detention centres, including Maikelawi. Many detainees were held incommunicado, and many were denied access to lawyers and family members.

Numerous prisoners of conscience, imprisoned in previous years based solely on their peaceful exercise of their freedom of expression and opinion, including journalists and opposition political party members, remained in detention. These included some convicted in unfair trials, some whose trials continued, and some who continued to be detained without charge.

Access to detention centres for monitoring and documenting the treatment of detainees continued to be severely restricted.

Torture and other ill-treatment

Torture took place in local police stations, Maikelawi federal police station, federal and regional prisons and military camps.

Torture methods reported included: beating with sticks, rubber batons, gun butts and other objects; burning; tying in stress positions; electric shocks; and forced prolonged physical exercise. Some detention conditions amounted to torture, including detaining people underground without light, shackled and in prolonged solitary confinement.

Torture typically took place in the early stages of detention, in conjunction with the interrogation of the detainee. Torture was used to force detainees to confess, to sign incriminating evidence and to incriminate others. Those subjected to torture included prisoners of conscience, who were arrested for their perceived or actual expression of dissent.

Defendants in several trials complained in court that they were tortured or otherwise ill-treated in detention. The courts failed to order investigations into the complaints.

In several cases, prisoners of conscience were denied access to adequate medical care.

Oromia region

Ethnic Oromos continued to suffer many violations of human rights in efforts to suppress potential dissent in the region.

Large numbers of Oromo people continued to be arrested or remained in detention after arrests in previous years, based on their peaceful expression of dissent, or in numerous cases, based only on their suspected opposition to the government. Arrests were arbitrary, often made pre-emptively and without evidence of a crime. Many were detained without charge or trial, and large numbers were detained in unofficial places of detention, particularly in military camps throughout the region. There was no accountability for enforced disappearances or extrajudicial executions during 2014 or in previous years.

In the aftermath of the “Master Plan” protests, increased levels of arrests of actual or suspected dissenters continued. Large numbers of arrests were reported, including several hundred in early October in Hurumu and Yayu Woredas districts in Illubabor province, of high-school students, farmers and other residents.

There were further reports of arrests of students asking about the fate of their classmates arrested during the “Master Plan” protests, demanding their release and justice for those killed, including 27 reported to have been arrested in Wallega University in late November.

Refugees and asylum-seekers

Forcible returns

Ethiopian government agents were active in many countries, some of which cooperated with the Ethiopian authorities in forcibly returning people wanted by the government.

In January, two representatives of the rebel Ogaden National Liberation Front were abducted and forcibly returned to Ethiopia from Nairobi, Kenya. They were in Nairobi to participate in further peace talks between the group and the government.

On 23 June, UK national Andargachew Tsige, Secretary General of the outlawed Ginbot 7 movement, was rendered from Yemen to Ethiopia. On 8 July, a broadcast was aired on state-run ETV showing Tsige looking haggard and exhausted. By the end of the year, he was still detained incommunicado at an undisclosed location, with no access to lawyers or family. The UK government continued to be denied consular access, except for two meetings with the Ambassador, to one of which Andargachew Tsige was brought hooded, and they were not permitted to talk privately.

In March, former Gambella regional governor Okello Akway, who has Norwegian citizenship, was forcibly returned to Ethiopia from South Sudan. In June, he was charged with terrorism offences along with several other people, in connection with Gambella opposition movements in exile.

Source: https://www.amnesty.org

Monday, March 9, 2015

የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔ – ወያኔ ብቻ ነዉ!

ባለፈዉ ሳምንት አይጋፎረም የሚባለዉና የወያኔን ቱልቱላ በዉጭ አገሮች የሚያናፍሰዉ ድረገጽ ከነብስ አባቱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአደራ የተሰጠዉን አንድ የመላምት ድርሰት የፊት ለፊት ገጹ ላይ ለጥፎት የህዝብን ስሜት የኮረኮረ እየመሰለዉ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ ከሁለት ሺ አመታት በኋላ ይሁዳዊ ክህደት ሲክድ እጅ ከፍንጅ ተይዟል። የሚገርመዉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆኖ ሳለ ያንን የመሰለ የክህደት መንፈስ ልቡ ዉስጥ ያስቀመጠለት ሰይጣን እንደሆነ ሁሉ አዲስ ዘመንና አይጋ ላይ የወጣዉን ጽሁፍ የጻፈዉ ግለሰብም የወያኔ ጌቶቹን ምክር ተቀብሎ አሜን አለ እንጂ የዚህ የዉሸት ድርሰት ጠንሳሾች በሰይጣን የሚመሰሉት የወያኔ መሪዎች ናቸዉ። የጽሁፉ ደራሲ ነኝ ግለሰብ የወያኔን ትዕዛዝ ከመቀበል ዉጭ ያደረገዉ ነገር ቢኖር ስሙ ከፅሁፉ አርዕስት ስር እንዲቀመጥ መፍቀዱ ብቻ ነዉ – ለዚያዉም የብዕር ስም!

አገሮች፤ ድርጅቶች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፕሮፓጋንዳ ጦርነት ዉስጥ ሲገቡ በዉሸት ዉስጥ እዉነት ወይም በእዉነት ዉስጥ ዉሸት እየሸነቆሩ ነዉ የፕሮፓጋንዳቸዉ ኢላማ የሆነዉን የህብረተሰብ ክፍል ቀልብ ለመግዛት የሚፍጨረጨሩት እንጂ ዉሸትን በዉሸት ለዉሰዉ ቢያቀርቡማ ህዝብ እንኳን ሊያምናቸዉ ደግሞ ሊሰማቸዉም ፈቃደኛ አይሆንም። ይህ ከሰሞኑ አይጋፎርምና አዲስ ዘመን ላይ የወጣዉ ጽሁፍ ግን ምንም አይነት የፕሮፓጋንዳ ህግ አይከተልም፤ ምክንያቱም ጽሁፉ የተጻፈዉ ህግ የሚባል ነገር በሌለባትና ወያኔና ግብረ አበሮቹ እራሳቸዉ ህግ በሆኑበት አገር ዉስጥ ነዉ። ጽሁፉ ሲጀምር በዉሽት ይጀምርና መሀል ላይ ዉሸቱን በዉሸት አጠናክሮ በዉሸት ይደመደማል። እንደዚህ አይነት የዉሽት ክምር የሚመጣዉ ደግሞ ከሌላ ከየትም ሳይሆን በዉሸት ተወልደዉ፤ በዉሸት አድገዉ በዉሸት ከሸበቱት የወያኔ መሪዎች ብቻ ነዉ። ዉድ አድማጮቻችን የዚህ ጽሁፍ አላማ ለሻዕቢያ ጥብቅና መቆም አይደለም፤ ሻዕቢያ ከኛ በላይ ለራሱ ጥብቅና መቆም ይችላል። የዚህ ጽሁፍ ብቸኛ አላማ የኢትዮጵያ ህዝብ ገንበዙን፤ ሀብቱንና ጉልበቱን አስተባብሮ መዋጋት የሚገባዉ ቀንደኛ ጠላቱ ወያኔ መሆኑን መናገር ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ትናንት ሲከናዉን የምናዉቀዉንና አይናችን ፊት ተፈጽሞ ከ “ሀ” ወደ “ፐ” የተጻፈዉን ታሪክ ዛሬ ወያኔና ቡችሎቹ ከ “ፐ” ወደ “ሀ” ሲያነብቡትና የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳሳት ሲሞክሩ ዝም ብለን አንመለከትምና ይህንን የዉሸት ክምር ከመሰረቱ መናድ እንፈልጋለን።

ይህንን በዉሸት የተጀቦደ የወያኔ ቡትቶ እንዳለ ማቅረቡ የአድማጭን ጆሮ ማደንቆር ስለሚሆን አንሞክረዉም። ሆኖም ወያኔ በተከበበና አንድ እርምጃ ወደማይቀረዉ ዉድቀቱ በቀረበ ቁጥር የሚመዝዛቸዉን አገር የሚገዘግዙ መጋዞች የኢትዮጳያ ህዝብ ከአሁኑ አዉቆ እንዲጠነቀቅ ስለምንፈልግ የፅሁፉን ጎላ ጎላ ያሉ የዉሸት ምሶሶዎች እንዳሉ ለማቅረብ እንገደዳለን።

Saturday, March 7, 2015

ሕወሓትን ለማስወገድ ሁላችንም እንረባረብ!!

በዳዊት ዮሃንስ

የዘመናት ሥልጣኔ ባለቤትና የአፍሪካ የነፃነት ፋና ወጊ የነበረችው አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ በህወሓት መዳፍ ሥር ወድቃ ሕዝቦቿ የመከራና የሰቆቃን እንጀራን በሚጋግሩበት በአሁኑ ወቅት ጥቂት የአገዛዙ ሹማምንት “ጊዜ የሰጠው ቅል …” እንዲሉ በጥጋብና በትዕቢት ተወጥረው አሸሸ ገዳሜ ይላሉ፡፡ ነገን በተስፋ መሰነቅ ያቃታቸው አያሌ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ግን አገር እያላቸው አገር አልባ ሆነው አለምን ባነጋገረ ሁኔታ ራሳቸውን ለብርቱ ስቃይና ለሞት አሳልፈው እየሰጡ በየማዕዘናቱ እየተሰደዱ በከፋ ሰቆቃ ውስጥ እያለፉ እነሆ 24 የመከራ አመታት ነጎዱ። ስደቱ ከዕለት እለት እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ በእርግጥም ይህች አገር የማን ናት? ያሰኛል፡፡ 

የዳቦ ቅርጫት እየተባለች ስትሞካሽ የኖረችው ኢትዮጵያ የሚላስ የሚቀመስ ጠፋቶ ሕዝቦቿ አንጀታቸው እየተጣበቀ አደባባይ ወጥተው ብሶታቸውን እንዳያስተጋቡ አንደበታቸው እየታፈነ፣ የሕወሓት ሹመኞች እንደልባቸው በሚቦርቁበት አሻንጉሊት ፓርላማ ሕዝብን የሚያሸማቅቁና ዜጎችን እግር ተወርች የሚጠፍሩ ሕጎች እየተፈበረኩ ሲተገበሩ፣ ሕዝቡ ከድህነት ጋር ታግሎ ያፈራውን አንጡራ ሃብቱን በጠረራ ፀሐይ ሲቀማና ሲዘረፍ የአገዛዙ ሹማምንትና ሆድ አደር ባለሃብቶች ለቀጣይ ሦስትና አራት ትውልድ የሚተርፍን የአገር ሀብት በየአቅጣጫው እየዘረፉና እየተቀራመቱ አገሪቱን በድቅድቁ አጨልመዋታል። 

ታሪክ እንደሚዘክረው ቀደምት አባቶቻችን ጣሊያን አገራችንን ሊነጥቅና በባርነት ሊገዛን በዘመናዊ ጦር ሲወረን አገር የለንም ብለው አልተሰደዱም፡፡ የሕይወት መስዋዕትነትን ከፍለውና የጠላትን ጦር ድባቅ በመምታት አንበርክከው ኢትዮጵያን የራሳቸው አደርገው ለኛ አስረክበውን አልፈዋል፡፡ ዛሬ ግን በመካከላችን የወጡ ዘረቢስ ፋሽስቶች አገር እንደሌላው ባይተዋር ወይም አንደ ፀጉረ ልውጥ ቆጠረውን ሲሳለቁብንና ሲያጎሳቁሉን ዝም ብለን የመመልከታችን ነገር ሁሌም ለእኔ እንቅልሽ ነው። ወገን ምንድን ነው ዝምታው! ከአባቶቻችን የወረስነው እኮ ባርነትን አይደለም ይልቁኑ ጀግንነትን አልገዛም ባይነትን እንጂ። ስለዚህ ዛሬ ዘረ ቢስ የሕወሓት ፋሽስቶቹን እምቢኝ አሻፈረኝ ብለን በፅናት ልንታገላቸው መነሳት በሁላችንም ጫንቃ ላይ የወደቀ ግዴታ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ 

በርግጥ አሁን ላይ የሕወሓትን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ ዜጋው ሁሉ እምቢኝ አልገዛም እያለ በሁሉም አቅጣጫ ሁሉንም የትግል አይነት ያልጀመረው ለመጀመር የጀመረው ለመቀጠል እየተሟሟቀ የሚገኝበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ይህ ደግሞ መልካም አጋጣሚ ነው። ስለዚህ ሁላችንም በተረባረበ ክንድ በአንድነት ሁሉንም ጸረ ሕወሓት ሃይላት የማበረታቻ ቃል ብቻ ከመስጠት በዘለለ አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ለመለገስ በያለንበት ዝግጁ መሆን ይገባናል። ዛሬ በሃገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች፣ የመብት ጠያቂዎች፣ የድምጻችን ይሰማ ሚሊዮን ሙስሊሞች ሌሎችም የበደሉ ግፍ ያረፋባቸው አያሌ ዜጎች በሙሉ እያስገመገሙት ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት፤ በሌላው ፈርጅ ደግሞ ነፍሰ በላውን የሕወሓት አገዛዝ በብረት ለመፋለም ቆርጠው ቤታቸውን በዱር በገደል ያደረጉ የነጻነት ታጋዮች በሙሉ በየፈርጃቸው በማበረታታትና በመደገፍ ለአገር አድኑ ህዝባዊ ትግል ጋሻ ሆነን መቀጠል ይኖርብናል።

በነገራችን ላይ የሕወሓት ነፍሰ ገዳይ ሹማምንት ፈጣሪን እየተገዳደሩ ኢትዮጵያን በእጃቸው በመጠፍጠፍ ሰርተው በገፀ በረከትነት የሰጡን ይመስል ነጋ ጠባ ለጆሮ የሚገለማ ዲስኩራቸውንና ውሸታቸውን እያንቧረቁ አደንቁረው ለመግዛት ሌት ተቀን የሚዶሉቱትን ሴራ በቃ በማለት ነቅተን ማክሸፍም የሁላችንም ግዴት መሆን ይገባዋል እላለሁ። ጆሮ ሰጥተን ልንሰማቸው ፈጽሞ አይገባም። ሕወሓቶች የሥልጣን ኮርቻው ላይ ጉብ ባሉ ማግስት በዘር በመገነጣጠል የከፋፈሉን፤ ከጐንደርና ከጋምቤላ ለም መሬቶችን ቆርሰው ለሱዳን በገፀ በረከትነት የሰጡ፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ድሃ ገበሬዎችን እያፈናቀሉ መሬቶቻቸውን በመንጠቅ ለውጭ አገር ቱጃሮች በማይረባ ገንዘብ የሸጡ፤ የአገር ሃብትን ጨምሮ በእርዳታና በብድር የተገኘ ገንዘብ ዘርፈውና አዘርፈው ከአገር ያስወጡ የጥፋት መልእክተኞች ናቸው።

ስለዚህ በመጨረሻ በድጋሚ አትኩሮት ሰጥቸ ማስተላልፈው የምፈልገው መልዕክት ቢኖር ሕወሓት ያፈረሳትን አገር፤ ሕወሓት የዘረፈውን የአገርና የሕዝብ ሐብት፤ ሕወሓት የበተነውን ሕዘብ ፤ ሕወሓት ያረከሳቸውን ቤተ እምነቶች፤ ሕወሓት ያነገሰውን ሕግ አልባነት ግድያ አፈና ሺብር ስደትና የግዞት ስርዓት ለማስወገድ መተኪያ የሌላትን ውድ ሕይወታቸውን በመገበር በዚህ ወቅት በየትኛውም የፍልሚያ ጎራ ተሰልፈው የሕወሓትን እብሪት ለማስተንፈስና ለኢትዮጵያዊያን ነፃነት፤ አንድነት፤ ለጋራ እድገት፤ ፍቅርና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ነፃነት ያለመስዋእትነት አይገኝምና የታሪክና የትውልድ አደራቸውን አንግበው ከሕዝባቸው ጎን ሆነው ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ ከሚገኙት ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ እንዲሁም ከሌሎች የአንድነት ሃይሎች ጎን በመሰለፍ የተጀመረውን እልህ አስጨራሽ የአገር አድን ትግል ከዳር ለማድረስ መረባረብ ያለብን ሰአት አሁን ስል አጥብቂየ ወገናዊ ጥሪየን አቀርባለሁ። ይንን የተቀደሰ አገርና ሕዝብን የማዳን ተግባር ለዲሰፖራው ወገን እግዚአብሔር ቅን ልቦና ስጥቶት በአንድነት የነፃነት ሃይሎችን እንዲቀላቀል ጥሪየን እያቀረብኩ ፈፃሚው እሱ ነውና ለሐያሉ ጌታም የነፃነታችንንና የትንሳኤያችንን ቀን እንዲያቀርብልን ልመናየን በማቅረብ ፅሁፌን እቋጫለሁ።

ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!



የአድዋ ድልን እያከበርን ለዛሬ ነፃነታች ቃል እንግባ!

መቶ አስራ ዘጠነኛውን የአድዋ ድል በዓል እየዘከርን እንገኛለን። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም ቀደምቶቻችን በርካታ የውስጥና የውጭ ችግሮች ነበሩባቸው። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም በመካከላቸው የሀሳብና የጥቅም ልዩነቶች ነበሩ። ያም ሆኖ ግን ቀደምቶቻችን በአገር ነፃነት ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ መግባባት ላይ መድረስ በመቻላቸው በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችና ድርጅት የተጠናከረውን የአውሮፓ ጦር በጥቁር የጦር አዛዦችና ተዋጊዎች መመከት ቻሉ። ከአድዋ በፊት አፍሪቃ በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ አውሮፓዊያን የተሸነፉባቸው ተናጠል አውደ ውጊያዎች ነበሩ፤ ጦርነትን ሲሸነፉ ግን አድዋ የመጀሪያው ነው። በዚህም ምክንያት ነው የአድዋ ድል የአፍሪቃውያን ከዚያም አልፎ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ድል ተደርጎ የሚወሰደው።

ዛሬ ግን እኛ ያኔ የነበሩት አያትና ቅድመ አያቶቻችን እደረሱበት የመግባባት ደረጃ ላይ መድረስ ባለመቻላችን አገር በቀሉን ቅኝ ገዢ – ህወሓትን – ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ ማውረድ አቅቶን አገራችንና ሕዝቧን ከባዕድ በባሰ ሁኔታ እያዋረደ በመግዛት ላይ ይገኛል።
ያኔ ለሀገሩ፣ ለነፃነቱና ለክብሩ ቀናዒ የሆነው ኢትዮጵያዊ ራሱን ወታደር አድርጎ በየጎበዝ አለቃው አዝማችነት በጠላት ላይ ዘምቶ ድልን ተቀዳጅቷል። ዛሬ ግን ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ የመከላከያ ሠራዊት አባል ለህወሓት አዛዦች ሎሌነት አድሮ የራሱን ወገን ይፈጃል። ያኔ በአገዛዙ ላይ ብሶት የነበረው እንኳን ሳይቀር ብሶቱን ችሎ ለሀገር ሉዓላውነትና ክብር ሲል ተዋድቋል። ዛሬ ግን ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ወገኖቻችን የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ከብሶቶቻቸው በላይ አሻግረው መመልከት ተስኗቸዋል።

ዛሬ 119ኛውን የአድዋ ድል በዓል አያቶቻችንን በማድነቅ ብቻ ልናሳልፈው አይገባም። የአያቶቻችንን ገድል ስናከብር ዛሬ የምንገኝበትን ሁኔታ መመዘን ይገባናል። ራሳችንን ከእነሱ ጋር በማስተያየት እንደምን ያለን ውለታ መላሽ ያልሆንን የልጅ ልጆች መሆናችንን መመዘን እና ራሳችንን መውቀስ ይገባናል። የሚሳዝነው ዛሬ ራሱን ከሚወቅሰው በላይ አያቶቹን የሚወቅስ መብዛቱ ነው። እነሱ ችግሮችን ተሻግረው የምንኮራበትን ድል አቀዳጅተውን አልፈዋል። እኛ ግን እነሱ ያቆዩልንን ድል እንኳን ማስጠበቅ አልቻልንም። ከአድዋ ድል አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ዓመታት በኋላ አገራችንን ለህወሓት የአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ማስረከባችን ሊያመንና ሊያንገበግበን ሲገባ ድሮ ሊደረጉ ሲችሉ አልተደረጉም በምንላቸው ነገሮች ላይ እየተከራከርን ግዜያችንን እናጠፋለን።

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ታላቁን የአድዋን ድል ለአጎናፀፉን ቀደምቶቻችን ያለንን ክብር መግለጽ ያለብን ዛሬ አገራችን ከህወሓት የአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በምንገባው ቃል ኪዳን ነው ብሎ ያምናል። አገራችንን በቅኝ ግዛትነት እያስገዛን የቀደምቶቻችንን ድል መዘከር ለእኛ ለልጆቻቸዉ የሚያሳፍር ተግባር ነው ብሎ ያምናል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አገር በቀል ቅኝ ገዥ በሆነው ሕወሓት እየተመራ የኢትዮጵያን ሕዝብ የማዳከሙን ተግባር በአስቸኳይ ማቆም ይኖርበታል ብሎ ያምናል። ስለሆነም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ልባችሁንም ክንዳችሁንም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አድርጉ። ቀደምት አባቶቻችን አድዋ ላይ ድል የነሱት ቅኝ ገዥ ዛሬ ቀለሙን ለውጦ “ህወሓት” ተሰኝቶ ያንተ አዛዥ ሆኗል። መሣሪያህን በህወሓት አዛዦችህ ላይ የምታዞርበት ወቅት አሁን ነው። ንቃ፤ ተነስ!

አገርን ለጠላት አስረክቦ በቀደምት ጀግኖች ታሪክ መኩራት አሳፋሪ ነው። አባቶቻችን በነፃነት ያቆዩልን አገር የህወሓት መፈንጫ ሆና ማየት የሚያሸማቅቅ ነው። የጀግኖች አያቶቻችን የልጅ ልጆች መሆናችንን የምናስመሰክረው አገራችንን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ ስናወጣና የዜጎቿ መብቶች የተከበሩባት ፍትህና እኩልነት የሰፈኑባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ስንመሠርት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ታላቅ ዓላማ ይነሳ ሲል አርበኖች ግንቦት 7 ጥሪ ያስተላልፋል።

አርበኞች ግንቦት 7: የአድዋ ድልን እያከበርን ዛሬ ነፃነታችንን ለማስከር ለመታገል ቃል እንግባ ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Wednesday, March 4, 2015

አሁንም ደግመን እንነግራችኋለን

ኢትዮጵያችን እግዚአብሔርንና ሰውን በማይፈሩ ጨካኞች እጅ ወድቃ የመከራ አገር ከሆነች ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። በህዝባችን ላይ የተመዘዘው የመከራ ሰይፍም ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። እንዲያውም በህዝባችን ላይ ሲዘንብ የቆየው የመከራ መንፈስ እንደገና ታድሶ ገና “ልክ እናስገባችኋለን” የሚል የጣዕረ ሞት ድምፅ ከህወሃት መንደር እየተሰማ ነው።

አባይ ፀሃይ የሚባለው ወላዋይና አደር ባይ ግለሰብ በህዝቡ ላይ ሲፈፅመው በኖረው ወንጀል ገና የረካ አይመስልም። ሌላ ግዲያ፤ ሌላ ስደት፤ ሌላ የላቀ መከራ ለኢትዮጵያዊያን ደግሶላቸዋል። አባይ ፀሃይ ለአዲስ አበባ ከተማ ልቀት እርሱ ብቻ አሳቢ፤ እርሱ ብቻ ተቆርቋሪ ሁኖ ራሱን ሹሟል።የአዲስ አበባም ሆነ በአካባቢው የሚኖረው ኗሪ ህዝብ ግን አባይ ፀሃይን የሚያውቁት በእኩይ ተግባሩ እንጂ በደግ ተግባሩ እንዳለሆነ እኛ ልናስታውሰው እንወዳለን። በዚህ ግለሰብ አማካሪነት የተጀመረው ኗሪውን ህዝብ የማፈናቀል፤ ቤተሰብን የመበተን፤ የህዝቡን አብሮነት የማፍረስ ተግባር ገና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል “ገና ልክ እናስገባችኋለን” በሚል መፈክር ሥር እንደሚቀጥል ታቅዷል። አዲስ አበባን በማስፋፋት ሰበብ ብዙ ገበሬዎች ከኖሩበት መንደር ያለምንም ካሳ ተፈናቅለው የሌላ ሎሌ እንዲሆኑ መደረጉ የሚረሳ አይደለም። ይሄን የአንድን ህዝብ ማንነት የማጥፋት ድርጊትን የተቃወሙ ብዙ ወጣቶች በሞት እና በእሥራት እንደተቀጡም አረሳነውም። ትላንት የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ፤ የፈሰሰው እንባ ሳይታበስ፤የተበተነው ሳይሰበሰብ፤ የተሰበረው ሳይጠገን እንደገና ለሌላ ዙር ጥፋት እየተዘጋጁ እንደሆነ ነግረውናል።

አባይ ፀሃይ “ልክ እናስገባችኋለን” ሲል የተማመነው ጠመንጃ ያነገተውን ኢትዮጵያዊ ወታደር እንጂ ህዝብን እንዳልሆነ እናውቃለን። ወታደር አገሩን መጠበቅ፤ ህዝቡንም ከጥፋት መታደግ፤ አጠቃላይ የአገሪቷን ህግም ማስከበር ዋናው ተልዕኮው ነበር። የአገራችን ወታደሮች ግን ዋናውን ተልእኳቸውን ትተው ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዳትቀጥል የሚያደርጉ ቡድኖችን እድሜያቸውን ለማራዘም እየሰሩ እንደሆነ እያየን ነው።በአገራችን ጠመንጃ የታጠቁ ኃይሎች መከላከያ ኃይል አባላት፤ የፖሊስ አባላት፤ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እና በአገራችን ታሪክ በነፍሰ ገዳይነቱ የሚታወቀው አግዓዚ የተባለው ክፍለ ጦር አባላት እና የአገር ውስጥ ደህንነት አባላት የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም ከልብ የመነጨ ፍላጎት አላቸው ብለን አናምንም። እነዚህ ኃይሎች የወጡበትን ጎጆ፤ ነገ ዞሮ መግቢያ የሚሆናቸውን ማህበረሰብ ወደውና ፈቅደው ያፈርሳሉ ብለን ለማሰብ ይቸግረናል።በሌላ በኩል ደግሞ ድርጊታቸው ብዙዎችን እያስከፋ እንደሆነም እናውቃለን።

አሁንም ደግመን ደጋግመን በኢትዮጵያችን ጠመንጃ ላነገቱ ኃይሎች መልዕክት መላካችንን አናቋርጥም። ጠመንጃውን ያነገቱ ኃይሎች ካነገቱት ጠመንጃ የተለዩ ናቸው። እነዚህ ኃይሎች ስሜት አሏቸው፤ ፍላጎት አሏቸው፤ ማሰብ የሚችል አዕምሮም እንዳሏቸውም የሚካድ አይደለም።የሚያዝንና የሚደሰት ስሜት፤ ለመኖር ፍላጎት፤ በጎውን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል አዕምሮ ያሏቸው ስለሆነ ፈፅሞ እስከ ሚመሽ ድረስ መልዕክታችንን ከመስደድ አናቆምም። መልዕክታችንም አጭርና ግልፅ ነው። በዚያች አገር ውስጥ ጠመንጃ የታጠቀው ኃይል ጋር ጠላትነት የለንም።በእኛ እምነት መከላከያ ኃይል፤ ፖሊስ እና የደህንነት ሠራተኞች ጠላቶቻችን አይደሉም። እኛ ጠላት የምንለው ጠመንጃ የታጠቀውን ድሃ እና ከርታታ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ይህን ኃይል በገዛ ወገኑ ላይ ሰይፉን እንዲመዝ እና የንፁሃንን ደም እንዲያፈስ የሚያደርገውን ኃይል ነው።የአገሪቷ መከላከያ ኃይል አሁን ባለበት ሁኔታ ለተሻለ ውጤት የሚያበቃው አማራጭ ስለሌለው ሂሊናው እየወቀሰውም ቢሆን የገዛ ወገኑን ደም እያፈሰሰ ለመቆየት የተገደደ ይመስላል። ይህን ማለታችን የድርጊቱን መፈፀም ትክክል ነው እያልን አይደለም። በማንኛውም መለኪያ የንፁህ ሰውን ደም ማፍሰስ ትክክል አይደለም። በሰማይ በእግዚአብሄር ፊት የሚያስጠይቅ፤ በምድር በሰው ዘንድም የሚያስወቅስ ክፉ ተግባር መሆኑን ሳንናገር አናልፍም።

እስከ ዛሬ የተሻለ መረጃ ስለሌለኝ፤ የተሻለ አማራጭ ስላጣሁ፤ የተሻለን መንገድ ለመፈለግ ሁኔታው ስላልፈቀደልኝ ከሂሊናየ ውጪ ሁኜ ለመኖር ተገድጄአለሁ የሚለው ምክንያት አሁን አብቅቷል። አሁን መረጃ አለ፤ ኢትዮጵያን እንደ አገር እንድትቀጥል ለማስቻል የተሻለ አማራጭም አሁን ተዘጋጅቷል። መረጃና አማራጭ መንገድ ካለ ደግሞ ከሂሊና ጋር ታርቆ እንደ ሰው ለመኖር ሁኔታው የተመቸ ሁኗል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል፤ የፖሊስ ሠራዊት አባላት፤የአገር ውስጥ የደህንነት ኃይሎች ሆይ ስሙን !

ህወሃቶች እናንተን ተገን አድርገው የገዛ ወገኖቻችሁን “ልክ እናስገባለን” ማለታቸውን ሰምታችኋል የሚል ግምት አለን። ልክ ማስገባት ማለት-ከሥራ ማባረር፤ከትውልድ ሥፍራ ማፈናቀል፤ እስር ቤት መጨመር፤ ለስደት መዳረግ እና መግደል ማለት ነው። የአባይ ፀሃይ ልክ ማስገባት ይሄን ይመስላል።ይሄን የምትፈፅሙት ደግሞ ጠመንጃ ያነገታችሁ ኃይሎች ትሆናላችሁ። ወገኖቻችሁ በህወሃቶች እጅ እንባቸውን በመዳፋቸው ሲያፍሱ ኑረዋል።በህወሃት አገዛዝ ሥር ያለች አገራችሁ ከውዳቂ አገራት ተርታ ገብታለች፤ ከዓለም አስር ፍፁም ድሃ አገሮች መካከል አንዷ ሁናለች።የአገራችሁ ወጣቶች ሞትን ፊት ለፊታቸው እያዩ ተሰደው የዓዞና የበርሃ ዕራት ሁነው ቀርተዋል። ከዚህ የተረፉትም የዓረብ መጫወቻ ሁነዋል። ይህ ሁሉ መከራ ህወሃት በተባለው ክፉ ዘረኛና ቂመኛ ቡድን ይፈፀማል። አሁን ይሄን በቃ ለማለት ግዜው ነው። ከእንግዲህ ወዲያ ታዝዤ ነው፤ ለእንጀራ ብየ ነው፤ ልጆቼን ላሳድግ ብየ ነው፤ አማራጭ አጥቼ ነው፤ የሚሉ ምክንያቶች ሚዛን የሚያነሱ ባለመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

አሁን አስተማማኝ አማራጭ አለ። የኢትዮጵያ ውረደት ያንገበገበን፤ የህዝባችን ጉስቁልና ያስቆጨን ወገኖች የአያቶቻችንን ጋሻና ጦር አንስተን ለግዳጅ ተዘጋጅተናል። ከመቸውም ግዜ በተሻለ ህዝባዊ መሠረት ላይ የቆመ ድርጅት መሥርተን ንቅናቄ ጀምረናል። ትግላችን ኢትዮጵያዊያን ከተዘፈቁበት ጭለማ ወደ ብርሃን የሚያሻግር ነው። ትግላችን ህወሃት የጫነውን የዘረኝነት ቀንበር የሚሰብር ነው። ትግላችን ህወሃት የዘረጋውን የዝርፊያ መረብ የሚበጣጥስ ነው። ትግላችን ህዝቡን በሙሉ የተጫኑ ጥቂት መንደርተኞች ሥፍራቸውን እንዲይዙ ማድረግ ነው።ትግላችን ጎጠኛ አስተሳሰብን አምክኖ ብሄራዊ ስሜትንና ውህደትን የሚፈጥር ነው። ትግላችን ዜጎች በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ውስጥ በማንኛውም ሥፍራ ያለ ፍርሃት የሚኖሩበትን ሁኔታ የሚፈጥር ነው። ትግላችን አብዛኛው ህዝብ በመረጠው መንግስት የሚተዳደርበት፤ ይህም መንግስት ህዝቡን ፈርቶና አክብሮ የሚሠራበት ሁኔታ የሚፈጥር ነው። ትግላችን የአገሪቷ መከላከያ ኃይል አገሩንና ህዝቡን የሚጠብቅ እንጂ የገዛ ወገኑን ደም በከንቱ የሚያፈስበት ሁኔታ እንዲያበቃ የሚያደርግ ነው።ጠመንጃውን ያንገትከው ኃይል የቀረበልህ አማራጭ መሥመር ይሄ ነው።

ደግመን እንነግርሃለን አሁን አማራጭ መንገድ አለህ። በገዛ ወገኖችህ ላይ ስይፍህን ለመምዘዝ እምቢ የማትል ከሆነና አሁንም በዚያው በጭለማ መንገድ መሄድን ከመርጥክ መጨረሻህ መልካም አይሆንም። እኛ እንድሆንን ተነስተናል። ከመንገዳችን የሚያቆመን ምዳራዊ ኃይል አይኖርም።የቃየል ልጆች ሲያጠፉን እንዲያው ዝም ብለን የምንጠፋ አይደለንም።ከእኛ ዘንድ እውነት አለ፤ ከእኛ ዘንድ የነፃነት ብርሃን አለ፤ ከእኛ ዘንድ የፍትህ ዘንግ አለ፤ከእኛ ዘንድ የእኩልነት ሚዛን አለ፤ ከእኛ ዘንድ እግዚአብሄር አለ።ይሄን ሁሉ ይዘን እናሸንፋለን እንጂ አንሸነፍም።የምናሸንፈው ለበቀል እንዳይደለ አሁንም እንነግራችኋለን። የምናሸንፈው በክፉው ላይ መልካሙን ዘር በመዝራት ነው።በጭቆና ላይ ነፃነትን፤ በአድልዎ ላይ ፍትህን፤ በህግ አልባነት ላይ የህግ የበላይነትን፤ በጎጠኛ አስተሳሰብ ላይ ብሄራዊ አስተሳሰብን ማስረፅ ስንችል ነው አሸንፈናል የምንለው። የጎሰኛነትን አጥር አፍርሰን የኢትዮጵያዊነት ስሜት ማስረፅ ስንችል ነው አሸንፈናል የምንለው። እኛ ስናሸነፍ የሚሆነው ይሄው ነው። ከእኛ ዘንድ የበቀል ስሜት የለም። ከእኛ ዘንድ ያለው ሁሉም ከህግ በታች ሁኖ ህግና ፍትህ እንዲነግሱ የሚያስችል ብርቱ ፍላጎት ነው።

ስለዚህ ጠመንጃ ያነገታችሁ ኃይሎች እኛ ከቆምንለት ቅዱስ ዓላማ ጋር እንድትተባበሩ እንጠራችኋለን።ኑና የጭለማ ኃይሎችን ምሽግ አፍርሰን የብርሃን ልጆችን አምባ አብረን እንሥራ። ኑና አብረን የወገኖቻችንን እምባ እናብስ። ኑና በግፍ ያለፍርድ የታሠሩትን እናስፈታ ።ኑና የጭቆናን ቀንበር አብረን እንስበር። ኑና አብረን አገራችንን ከፍ ከፍ እናድርጋት።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

Sunday, March 1, 2015

ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! – “ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ

ይህ ዘገባ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዘገባ ነው ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡” ይህ ለመሠረታዊ ልማት እንዲውል በዓለም ባንክ በኩል የሚሰጠውን ገንዘብ የሚደጉሙት ምዕራባውያን አገራት ሲሆኑ አንዷ ተጠቃሽ አገር እንግሊዝ ናት፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከምዕራባውያን በዓለም ባንክ በኩል የሚያገኘውን ገንዘብ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑ ለዓለም ባንክ ተደጋጋሚ መረጃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ሟቹ መለስ በቀጥታ በሰጡት ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ ኢህአዴግ በቦታው ያሰማራው የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው የሚኖሩትን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል እምቢ ያሉትን በግድ በማስነሳት፣ በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በማሰቃየት፣ ወዘተ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ባገኙ ዘገባዎች ሲነገር ቆይቷል፡፡ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ ልማት በማለት የሚሰጠው ገንዘብ ኢህአዴግ ወታደሮቹን የግፍ ሥራ ላይ በማሰማራት ደመወዝ የሚከፍልበት መሆኑን በመጥቀስ ወደ ኬኒያ የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ጎልጉል በወቅቱ የዘገበው ዜና ነበር፡፡ ““ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ዜና ለማንበት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሚስተር ኦ” በመባል የሚጠሩት አኙዋክ ተወላጅ ኢህአዴግ የዕርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣና ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳዋለው በመጥቀስ የእንግሊዝ መንግሥት ከግብር ከፋይ ዜጎቹ የሚያገኘውን ገንዘብ አምባገነንነት እየደገፈበት መሆኑን በተለይም የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ተጠያቂ ስለሆነ ከዚህ እንዲታቀብ ክስ መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡ የክሱ ሒደት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሚስተር ኦ በተደጋሚ እንደመሰከሩት ኢህአዴግ ነዋሪዎችን በግዳጅ ከቀያቸው በማፈናቀል የሚያካሂደው የግዳጅ ሰፈራና የመንደር ምሥረታ ሕገወጥ መሆኑ በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ እንደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ብዙዎች ለአካላዊ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፣ ሴቶች ክብረንጽህናቸው ተደፍሯል፣ አዛውንትና ህጻናት ለአሰቃቂ መከራ ተዳርገዋል፤ ይህንንም እርሳቸው እንዳዩ ሚስተር ኦ ይመሰክራሉ፡፡ የሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ወደ ውሳኔ ሊደርስ ባለበት ወቅት የልማት መ/ቤቱ ይህንን ዓይነት ውሳኔ መውሰዱ ከፍርድ ቤቱ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ፡፡ የልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ግን የመ/ቤታቸው ውሳኔ ከሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ መናገራቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መ/ቤቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ኢትዮጵያ “የዕድገት ስኬት” እያስመዘገበች በመምጣቷ የመሠረታዊ ልማት አገልግሎት የገንዘብ ዕርዳታ የማያስፈልጋት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ይህ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የተባለውና ለኢህአዴግ ንጹህ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚያስገኝ ገንዘብ እንደነጠፈበት መሰማቱን አስመልክቶ ጋዜጣው የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴን በጠየቃቸው ወቅት የመለሱት አልነጠፈብንም የሚል እንድምታ ያለው ነው፡፡ “እነርሱ ያሉት ዕርዳታውን አንሰጥም ወይም እናቆማለን ሳይሆን ዕርዳታ አሰጣጡ እንደገና ይዋቀራል ነው” በማለት ሬድዋን ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) ዕርዳታ ለመስጠት ከዓለምባንክ ጋር ስምምነት የነበረው የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት በ2015/2016 በፓውንድ 256ሚሊዮን ብቻ (5በመቶ) ዕርዳታ ለመስጠት መወሰኑን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊው ሬድዋን ሁሴን አላብራሩም፡፡ ኢህአዴግ ለዕርዳታ የሚሰጠውን ገንዘብ ዜጎችን ለማሰቃየት፣ ወታደር ለመቀለብ፣ ወዘተ እንደሚጠቀምበት በተደጋጋሚ ዘገባዎች እና ማስረጃዎች ሲወጡበት የከረመ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ተከትሎ የዓለም ባንክ በዕርዳታ አሠጣጡ ላይ አንዳች ውሳኔ እንዳያደርግ ብዙ ሲደክም ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት እንዲስተጓጎል በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዲጓተት ማድረጉን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይመሰክራሉ፡፡ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን ገና ከጅምሩ የሚያውቁትና ድርጅታቸው ለዓመታት ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑንም ይህንን የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት ውሳኔ የጋራ ንቅናቄያቸው ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ያገኘው ድል እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ “ገና ከጅምሩ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በመሆን ይህንን ሥራ በመደገፍ የተባበራችሁንን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ታላቅ ሥራ ተሰርቷል፤ እናመሰግናለን” ብለዋል “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ በተለይ ከጎልጉል ለቀረበላቸው አጭር ጥያቄ በሰጡት አስተያየት የጋራ ንቅናቄያቸው ደስታውን የገለጸው የልማት ገንዘብ በመቋረጡ ሳይሆን በልማት ስም የሚሰጠው ዕርዳታ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ በመዋሉና ለዚህም ደግሞ ከበቂ በላይ ማስረጃ ድርጅታቸው ያለው በመሆኑ ነው፡፡ “አገር ብትለማ የሁሉም ደስታ ነው” ያሉት ኦባንግ አገርን በማልማት ሽፋን ደጋፊና ተቆርቋሪ የሌላቸውን ንጹሃን መበደልና የመኖር መብታቸውን መንፈግ ግን በየትኛውም መልኩ እርሳቸውም ሆነ አኢጋን የሚቀበለው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ በቅርቡ አካሂዳለው ለሚለው ምርጫ እንደ ዕቁብ ዕጣ በማውጣትና በማስወጣት “አልደረሳችሁም” እያለ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን ከምርጫ እያስወገደ ባለበት፤ ሌሎችንም ሕጋዊ አይደላችሁም እያለ በተለጣፊ ድርጅት በማስበት ኅልውናቸውን እያሳጣ ባለበት ባሁኑ ወቅት በዜጎቹ ላይ የሚያካሂደውን መረን የለቀቀ የመብት ገፈፋ ለሥልጣን ያበቁትን ምዕራባውያንን ያስደሰተ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ከማለቱ በተጨማሪ በሚዲያ ላይ የተጫነው አፈና በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይፋ ከሆነ ወዲህ ማነቆው በኢህአዴግ ላይ እየከረረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ኢህአዴግን ለሥልጣን ከማብቃት አልፋ ነፍጥ አንጋቢዎቹን የህወሃት መሪዎች ጸጉርና ጺም ከርክማ፤ ልብስ አልብሳ፤ ቋንቋ አስተምራ፤ የከተማ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አሠልጥና፣ ቶሎ ባይገባቸውም ፕሮቶኮል አስተምራ፣ እስካሁንም ተንከባክባ እዚህ ድረስ ያቆየቻቸው እንግሊዝ እንዲህ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስታደርቅ “ቀጣዩስ ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ “ምዕራባውያን መግደልም ማንሳትም ያውቁበታል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እንደሚሉት ቀጣዩ የኢህአዴግ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ለህወሃት ሲቀጥል ለኢህአዴግ አስጊ ከመሆን ባሻገር በውጭ ምንዛሪ እጥረት በየጊዜው የሚፈጠረውን ግሽበት በዕርዳታ ገንዘብ የሚያስተካክለው ኢህአዴግ እንዲህ ያለው የገንዘብ ማዕቀብ ክፉኛ ያነጥፈዋል ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሙስናው መረን በለቀቀባት አገር ከሕዝብ እየተዘረፈ በተለያዩ አገራት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚከማቸውን ገንዘብ በሚካፈሉትም ላይ የድርሻ ቅነሳ የማስከተሉ ጉዳይ አብሮ የሚታይ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዚህ ዜና ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች እንደሚከተለው እንደገና አትመነዋል፡፡ ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል! ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም። ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል። የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል። አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡ በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) የጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል። በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። (የመግቢያው ፎቶ የተወሰደው: ዘጋርዲያን)

ምርጫ ለኢትዮጵያ ወታደርና ፓሊስ: – ለህወሓት ባርነት ወይስ ለኢትዮጵያ ነፃነት

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውትድርና ከፍተኛ ክብር አለው። ውትድርና ከሙያና ሥራ በላይ የነፃነትና የክብር መገለጫ፤ ሀገርን ከባዕድ ወረራ መከላከያ ጋሻ ነው ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ህግና ሥርዓት አክባሪ በመሆኑ ለፓሊስም ከፍተኛ አክብሮት አለው። የፓሊስ ሥራ ወንጀልን መከላከልና ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ማቅረብ መሆኑ በኢትዮጵያ ባህል የተከበረ ቦታና እውቅና አለው።

በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ግን ይህ እየተቀየረ ነው። የህወሓት አዛዦች እየመሩት ያለው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ሀገርን ከባዕድ ጠላት ከመከላከል ጋር ምንም ዝምድና በሌላቸው ሁለት አበይት ተግባራት ላይ ተጠምዷል። በህወሓት አዛዦች የሚመራው ሠራዊት ዋነኛ ተግባር ለሰብዓዊ መብቶቻቸው መከበር እና ለፍትህ መስፈን የሚታገሉ ዜጎችን ማጥቃት ሆኗል። የጦሩ ሁለተኛው አቢይ ተግባር ደግሞ ለአዛዦች የግል ጥቅም ማካበቻ ገቢዎችን በሚያስገኙ ሥራ ላይ መሠማራት ነው።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያዊያንን ማጥቂያ ሠራዊት መሆኑ ሲቪሉን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱንም አባላትን ጭምር ለህሊና ወቀሳ የዳረገ ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን ይህ በህሊና ወቀሳ ብቻ ሊታለፍ የማይችል ወንጀል ነው። ሠራዊቱ በህወሓት እየታዘዘ የሚዘምተው በገዛ ራሱ ልጆች፣ እህቶች፣ ወንድሞችና ወላጆች፤ በገዛ ራሱ ጥቅሞች እና በገዛ ራሱ ላይ መሆኑ መገንዘብ ይኖርበታል። በገዛ ራሱ ጥቅሞች ላይ የሚዘምት አንድም ህሊና የሌለው አሊያም ነፃነት የተነፈገው ሰው ብቻ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሠራዊቱ እየተራበና እየታረዘ አለቆቹ የታላላቅ ህንፃዎች ባለቤቶች፣ ባለፋብሪካዎች፣ የባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ባለአክሲኖች የሚሆኑበት ሥርዓት ከዳር ሆኖ የሚመለከት መሆኑ የሚገርም ነው። ሠራዊቱ ቤተሰቦቹን መመገብ አቅቶት እያለ የአዛዦቹ ልጆች ለሽርሽር ዓለምን ይዞራሉ። እንዴት ነው ሠራዊቱ እየደኸየና እየሞተ አዛዦቹ እየከበሩ የሚሄዱት? ይህ አዋራጅ ሁኔታ እንዲያበቃ መታገል የሠራዊቱ ግንባር ቀደም ኃላፊነት ነው። ሠራዊቱ ወይ ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል አለበት አለበዚያም እሱም እንደነሱ ሰው መሆኑን ማሳየት መቻል አለበት። በኢትዮጵያ ውስጥ የህወሓት አገዛዝ ወድቆ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጠቅማቸው የኅብረተብ ክፍሎች ግንባር ቀደሙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው። በዚህም ምክንያት የሠራዊቱ አባላት ለሥርዓቱ መውደቅ በግልጽም በስውርም መታገል የዜግነት ብቻ ሳይሆን አዕምሮ ያለው ሰው ሆነው በመፈጠራቸው የተቀበሉት ግዴታ ነው።

ፓሊስን በተመለከተም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍኖ ለመግዛት የቻለው በዋኛነት የፓሊስን ኃይል ለአፈናው ተግባር የሚጠቀም በመሆኑ ነው። የተቃውሞ ድምጾች በተሰሙ ቁጥር የኢትዮጵያ ፓሊስ በወገኖቹ ላይ የሚያወርደው ዱላ የሚዘገንን ሆኗል። ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት መግደልና ማቁሰል፤ አረጋዊያንን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን መግደል፣ ማቁሰል፣ መደብደብ በዚህ ተግባር የተሠማሩ ፓሊሶችን በቡድንም በግልም በህግ የሚያስጠይቅ ከባድ ወንጀል ነው። በህወሃት እየተመራ ያለው የኢትዮጵያ ፓሊስ ተግባራት ተበዳዮችን ብቻ ሳይሆን ራሱ ፓሊስንም ጭምር አንገት የሚያስደፋ ተግባር ነው። ለመሆኑ አንድ ተራ የኢትዮጵያ ፓሊስ ባልደረባ ከህወሓት አገዛዝ ምን ተጠቀመ? መልሱ “ምንም” የሚል ነው። ይልቁንስ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ፓሊስ የተናቀና የተዋረደ ሥራ ሆነ። በህወሓት አገዛዝ ፓሊስ እንደሰለጠነ አዳኝ ውሻ “ያዝ” ሲሉት የሚነክስ፣ የሚያደማ፣ የሚቦጭቅ ሆኗል። ይህ ለፓሊስ፣ ወንጀልም ውርደትም ነው። በህወሓት አገዛዝ መገርሰስ እና በምትኩ የህግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መስፈን ፓሊስ ከሁሉ በላይ ተጠቃሚ ነው፤ ሰብዓዊ ክብሩን ያረጋግጥለታልና።

ዛሬ በኢትዮጵያችን ውስጥ የታዘዙትን የሚፈጽሙ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ስላሉ ነው የህወሓት ሹማምንት ልባቸው ያበጠው። ለማስረጃ ያህል ሰሞኑን የህወሓቱ ሹም አባይ ፀሐዬ የአዲስ አበባ ዙሪያ ገበሬዎች በግዴታ መነሳታቸው የሚቃወሙትን ዜጎችን ሁሉ ”ልክ እናስገባቸዋለን” ብሎ በሸንጎ የዛተው የታዘዘውን የሚፈጽም የጦርና የፓሊስ ሠራዊት መኖሩን ተማምኖ ነው። እስከ መቼ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ሕዝብን ማስፈራሪያ መሣሪያ ይሆናል?

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ለራሳቸው እና ለወገናቸው የሚበጀው ሥርዓት የቱ እንደሆነ ያውቃሉ ብሎ ያምናል። በዚህም ምክንያት ስብዕናቸውን እያዋረደ እና እያደኸያቸው ያለውን የህወሓት አገዛዝን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን ይፋለሙታል ብሎ ያምናል። ይህ ውሳኔ ግን ሠራዊቱ በጅምላ ሳይሆን እያንዳንዱ የሠራዊቱ አባል በግሉ የሚወስደው ውሳኔ እንደሆነ አርበኞች ግንቦት 7 ይገነዘባል።

በዚህም መሠረት ተደጋጋሚ ጥሪ እየተደረገለት፤ ጥሪውንም እየሰማ ከህወሓት ጋር ወግኖ ሕዝብን መውጋት የቀጠለ የሠራዊቱ አባል ላደረሰው ጥፋት በግል መጠየቁ የማይቀር መሆኑ ሊገነዘብ ይገባል። በእያንዳንዳንዱ የጦርና ፓሊስ ሠራዊት ባልደረባ ፊት የቀረበው ምርጫ “ለህወሓት ባርነት ታድራለህ ወይስ ራስህንና ሀገርን ነፃ ታወጣለህ” የሚል ነው።

ራስህንና ሀገርህን ነፃ ለማውጣት የመረጥክ የሠራዊቱና የፓሊስ ባልደረባ አሁኑኑ ሕዝባዊ ትግሉን ተቀላቀል። እስከዛሬ የበደልከውን ሕዝብ ለመካስ ምቹ ሁኔታ አለህ። በግልጽ የነፃነት ኃይሎችን እንድትቀላቀል፤ አሊያም አለህበት ሆነህ በውስጥ አርበኝነት እንድትደራጅና ተግባራዊ ሥራ እንድትጀምር መንገዱ ተመቻችቶልሃል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!