Monday, April 13, 2015

መተማመን በጠፋበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል * ኮረኔል ጋይም እና ኮረኔል እሸቴ ከስልጣናቸው ዝቅ ተደረጉ

በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ስርዓት በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ላይ እምነት በማጣቱ ምክንያት እንዱን በማውረድ ሌላኛውን በመሾም ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ምንጮቹን ጠቅሶ ደህሚት ዘገበ:: ዜናው እንደወረደ እንደሚከተለው ተስተናግዷል::


ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በደረሰን መረጃ መሰረት ውስጣዊ አሰራሩ በስብሶ በሰራዊቱ አዛዦች እምነት አጥቶ የሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት በ31ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ እየሰራ የቆየውን ኮነሬል ጋይም የተባለውን አዛዥ በስርዓቱ ላይ እምነት የለውም በሚል ምክንያት ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ። በምትኩ ኮነሬል ዘነበ የተባለውን ከ23ኛ ክፍለጦር በማስመጣት ኮነሬል ጋይም ምክትል ሆኖ አዲሰራ መደረጉን የተገኘው መረጃ አስረድቷል::
የኢህአዴግ ገዢ ስርዓት የአመራር ለውጥ በማድረግ ካጋጠመው ስጋት የሚላቀቅ ስለመሰለው የ7ኛ ሜካናይዝድ አዛዥ የነበረውን ኮረኔል እሸቴ ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ የአመራር ለውጥ እየተደረገላት ባለችው የ31ኛ ክፍለጦር በሦስተኛ ደረጃ አዛዥ ሆኖ እንዲሰራ መመደቡን የገለፀው መረጃው እየተካሄደ ባለው ከሃላፊነት የማውረድና የመሾም ተግባር ያልተደሰቱት አዛዦች በስርዓቱ ላይ የከፋ ጉዳት ማድረስ እንደሚችሉ ከቦታው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል::

No comments:

Post a Comment