Saturday, November 30, 2013

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በውጭ ስርአቱ ጥሩ ነው ይበሉ እንጅ በግል ሳናግራቸው ለውጥ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል ሲሉ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ተናገሩ

ህዳር ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያን የ1997 ምርጫ የታዘቡት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ይህን የተናገሩት አዲስ ስታንዳርድ ለተባለ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ነው።
በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮፓ፣ አፍሪካና ካረቢያን አገሮች የፓርላማ ጉባኤ ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና የአምባገነን ምንጭ የሆነው መለስ ዜናዊ ቢሞትም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ አለመምጣቱን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ተለውጣለች በማለት በአደባባይ የሚናገሩት ባለስልጣናት በግል ሳነጋግራቸው በኢትዮጵያ ፈጣን ለውጥ መደረግ አለበት ብለው ይላሉ ያሉት ወ/ሮ አና፣ አቶ ሀይለማርያም  ከሙስና ጋር በተያያዘ አንዳንድ መጠነኛ እርምጃዎችን ቢወስዱም፣ የትግራይ ተወላጅ ባለመሆናቸው ስልጣናቸውን ለማቆየት እየተቸገሩ መሆኑን ገልጸዋል። ቀደም ብለው እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ለመጎብኘት በጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ትእዛዝ ወደ ቃሊቲ የተጓዙት የአውሮፓ ህብረት ልኡካን፣ በእስር ቤቱ ሀላፊዎች መከልከላቸው በአገሪቱ ውስጥ ያለውን እውነታ የሚያሳይ ነው ያሉት ወ/ሮ አና በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ እንዳለ እንደሚያውቁም ተናግረዋል።
የመለስ ዜናዊ መንግስት ስልጣኑን ለማቆየት ሲል ሙስሊምና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ጥረት ሲያደርግ እንደነበርም የፓርላማ አባሉዋ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ወጣቶች አፍኖ መያዝ አይቻልም ያሉት ወ/ሮ አና የፖለቲካ ሜዳውን ለዲሞክራሲ መክፈት ኢትዮጵያን ከውድቀት እንደሚታደጋት ገልጸዋል።

ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በተያያዘ በሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ማንዣበቡን ኢትዮጵያውያን ተናገሩ

ህዳር ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ምድር ተጠራርገው እንዲወጡ እየቀሰቀሰ ነው። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አደጋ ሊፈጠር ይችላል ብሏል  አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ጋዜጠኛ።
በዛሬው እለት በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተነው የኤስ ኤም ኤስ መልዕክት  ህጋዊ ለተባሉትም ሆነ ህገወጥ ለሚባሉት ኢትዮጵያውያን የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ይላሉ እኝህ ጋዜጠኛ።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢ/ር ይልቃል በጀርመን- በስዊዘርላንድ – በሆላንድ – በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ያደርጋሉ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል። ትላንት ኖቨምበር 29 ጀርመን ፍራንክፈርት የገቡት ኢ/ር ይልቃል በመጪዎቹ ቀናት በአውሮፓ ከተሞች ተከታታይ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስተባባሪ ኮሚቴው በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ አስታውቋል።

ለጊዜው በደረሰን የስራ ሰሌዳ መሰረት :-

- ቅዳሜ ኖቬምበር 30 በጀርመን ኑረንበርግ ከኢትዮጵያኖች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
- ሰኞ ዲሴምበር 2 በፍራንክፈርት የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።
- ዲሴምበር 5 ጄኔቭ ስዊዘርላንድ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ይሳተፋሉ።
- ቅዳሜ ዲሴምበር 7 በሆላንድ ህዝባዊ ውይይት ያደርጋሉ።

ከአውሮፓ ቆይታቸው በኋላ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ በመጓዝ በዲሴምበር 30 አርሊንግተን በተዘጋጀው ስብሰባ ከፕ/ር አል ማርያም ጋር ንግግር ያደርጋሉ።

Nov 30: Nuremberg : Public meeting and fundraising
Dec 02: Frankfurt: Appearance at a rally; Meet with invited guests for dinner
Dec 05: Geneva: appearance at a rally
Dec 07: Amsterdam: Public meeting

Washington DC Public Meeting with Semayawi Party Chairman Eng. Yilkal Getnet – Sunday Dec 15, 2013 – Sheraton Arlington Hotel.


የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።

ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።

እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።

እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።

በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።

የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።

ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።

ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።

እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።

ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Thursday, November 28, 2013

የአና ጐሜዝ ውይይቶች ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር

አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን አደረግኩ አሉ


ከዘጠኝ ዓመት በፊት በተካሄደው የግንቦት 1997ቱ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጐሜዝ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ፡፡

ዛሬ በሚጠናቀቀው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ የመጡት አና ጐሜዝ፣ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የጋራ ስብሰባው ላይ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የመጡት የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባልና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት አና ጐሜዝ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ምንም ዓይነት የቪዛ ችግር እንዳልገጠማቸው ገልጸው ይህም አዲስ ዓይነት የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ በኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ አተያይ አለ ያሉት አና ጐሜዝ፣ አጠቃላይ የፖለቲካው ምህዳር ግን ከ1997ቱ ምርጫ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የባሰ ነው የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ «ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ተስፋ ይታይበት የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ምህዳር በምርጫው ምክንያት በተፈጠረው ቀውስ ከምርጫው በፊት ወደነበረበት አስከፊ ሁኔታ ተመልሷል፤» በማለት መንግሥትን ተችተዋል፡፡

ለዚህም እንደ መከራከሪያ የሚያነሱት ከምርጫው በኋላ የወጡትን ሕጐች በምሳሌነት በማቅረብ ነው፡፡ «ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት መታሰራቸው፣ የሲቪክ ማኅበራት መፈናፈኛ ማጣታቸው፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና የመሳሰሉት ነገሮች በአሉታዊነት የሚነሱ ናቸው፤» በማለት ተናግረዋል፡፡

«ከሁሉም በተለየ ሁኔታ ግን መንግሥት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን ያለአግባብ በመጠቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማድረግ እያዋለው ነው፤» በማለት አና ጐሜዝ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩ ሲሆን፣ በዚህም ጉዳይ ላይ ከአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር እንደተወያዩ አብራርተዋል፡፡

ምንም እንኳን የውይይቱን ዐበይት ነጥቦች በዝርዝር ከመግለጽ ቢቆጠቡም ውይይቱ ግን ገንቢ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ውይይቱ በዋነኛነት የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት፣ የፖለቲካ እስረኞችን ማስፈታት፣ ለሲቪክ ማኅበረሰቡ የምርጫ ሜዳውን ማስፋት፣ እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማጠናከር የሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ በዝርዝር የተወያዩ መሆኑን ከመግለጽ ውጪ፣ አና ጐሜዝ ከመንግሥት ወገን ያገኙትን ምላሽ ምን እንደሆነ ከማብራራት ተቆጥበዋል፡፡

የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስተዳደር የተሻለ ሊሆን እንደሚችል የገለጹት አና ጐሜዝ፣ በተለይ ሙስናን በተመለከተ የተጀመረው እንቅስቃሴ ሊበረታታ እንደሚገባው አስታውቀዋል፡፡

የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራ ስብሰባው ጥያቄ መቅረቡን ያመለከቱት አና ጐሜዝ፣ የመንግሥትን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነም አክለው አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን በተመለከተ ምንም ዓይነት ግለሰባዊ ችግር እንደሌለባቸው የገለጹት አና ጐሜዝ፣ ሥራዬን ግን በአግባቡ የመወጣት ግዴታ አለብኝ ብለዋል፡፡

የጋራ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሲሆኑ፣ በአባል አገሮች ሕገ መንግሥታት ላይ የሥልጣን ክፍፍል እንዲሰፍንና የፖለቲካ ምህዳሩ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሰፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰቡን ለመደገፍ፣ ፍትሕና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል፣ ሙስናን ለመዋጋት እንዲሁም የሥነ ዜጋ ትምህርትን ለማስፋፋትና ለማጐልበት ተቋማዊ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በእነዚህ ዙሪያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በጥምረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ግንኙነቱ ግን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ሳያሳስቡ አላለፉም፡፡

የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ስብሰባ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

ሁከት ፈጠሩ” የተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጉዳይ ፍ/ቤት ቀረበ

(አራያ ጌታቸው) ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2006 ዓ.ም ከላይ ባለው የክስ መጥሪያ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እና የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ስሜነህ ጸሀይ አዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበው፤ አቃቤ ህግ ወንጀሉን ከዘረዘሩ በኋላ ፍርድ ቤቱም ጥፋተኝነታቸውን ያምኑ ወይም ይቃወሙ እንደሆነ ጠይቆ ተከሳሾቹም ምንም አይነት ጥፋት እንዳለጠፉ ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለህዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ አሰናብቷቸዋል፡፡
የክሱን ዝርዝር እንዲያነቡት ከዚህ ዜና ጋር አቅርበነዋል።


የክሱ አቤቱታ

Wednesday, November 27, 2013

የአንዷለም አራጌ “ያልተሔደበትን መንገድ” መጽሃፍን የቃኘ መድረክ

(በዘሪሁን ሙሉጌታ) ባለፈው እሁድ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ አንድ የመፅሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ተካሂዶ ነበር። መፅሐፉ “ያልተሄደበት መንገድ” በሚል ርዕስ በቅርቡ ለሕትመት የበቃ መፅሐፍ ነው። መፅሐፉን ያሳተመው በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ የዕድሜ ልክ ፍርደኛ በሆነው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበረው አንዱአለም አራጌ ነው።

መፅሐፉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሁሉ አቀፍ ህፀፅ የሚዳስስ ታሪክ-ቀመስ የፖለቲካ መፅሐፍ ነው። ከመድረኩ ሲገለፅ እንደሰማነው 10ሺህ ቅጂ ታትሟል። በዕለቱ መፅሐፉን ቀደም ብለው አንብበው አስተያየት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ሁለት ሰዎች ነበሩ።
አንደኛው የቀድሞው የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አስራት አብርሃም ሲሆኑ፤ ሁለተኛው ደግሞ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነበር። ሁለቱም አስተያየት ሰጪዎች የመፅሐፉን አንኳር ጉዳይ ነቅሰው በማውጣት የየራሳቸውን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዕለቱ የሁለቱም አስተያየት ሰጪዎችን ትኩረት የሳቡት በዋናነት ሦስት ወይም አራት ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው። የመጀመሪያው ጠቅለል ባለ ዕይታ የሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ሲሆን፤ ይህንኑ ደካማ የፖለቲካ ባህልን ተከትለው የሚታዩ ጎጂ ልማዳዊ የፖለቲካ አስተሳሰቦችን ነው። በተለይም የጉልበት ፖለቲካ ባህል፣ የትግራይ ሕዝብና ህወሓትን አለመለያየት፣ የሰላማዊ ትግል የአተገባበር ችግርና የብሔራዊ መግባባት አስፈላጊነት ዙሪያ ላይ ያጠነጠኑ ነበሩ። በአቶ አስራት አብርሃም እምነት መፅሐፉ የተፃፈው ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ ህሊና በመሆኑ በሚዛናዊ አስተሳሰቦች የታጀበ መሆኑን አስምረውበታል። በአብዛኛዎቹ የመፅሐፉ ገዢ ሃሳቦች እንደሚስማሙበት ገልፀዋል።

የሀገሪቱ ምስቅልቅል የፖለቲካ ጉዞ መነሻ የሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል አለመዳበር መሆኑን፤ በተለይም ከሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ባህልን ለማስረፅ የኦሮሞ ብሔር ባህላዊ አስተዳደር ዘይቤ የሆነውን የገዳ ስርዓት በሀገሪቱ ውስጥ ቢኖርም እንደ ሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል አለመወሰዱ፤ በአንፃሩ የሰሜኑ የጉልበት ፖለቲካ፣ በሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ሚዛን ደፍቶ መታየቱ ለሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል አለመዳበር በማሳያነት ቀርቧል።

የኦሮሞ የገዳ ስርዓት ከስልጣን ሽግግር አንፃር ዴሞክራሲያዊ መልኮች ቢኖሩትም የሴቶችን ተሳትፎ ላይ ካለው ውስንነት አንፃር ጠቃሚ የሥልጣን ሽግግር ባህል ተደርጎ በአንዱአለም መፅሐፍ መገለፁ አግባብ መሆኑን አቶ አስራት አስምረውበታል።




የሰሜን የጉልበት ፖለቲካ እንደ ሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ተደርጎ የተወሰደበትን አግባብ ሲያሳዩም ከመፅሐፉ አንድ ምሳሌ ጠቅሰዋል። ነገሩ የሆነው በ1983 ኢህአዴግ የደርግን ሥርዓት ጥሎ ስልጣን ከያዘ በኋላ ወሎ ውስጥ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሕዝቡን ይሰበስቡና “አሁን ነፃ ወጥታችኋል። ደርግም የለም። እስቲ የመሰላችሁን ተናገሩ። አሁን ዴሞክራሲ አለ” ይላሉ። ይሄንን የሰሙ አያ ሙሄ የሚባሉ ሰው እጅ አውጥተው “ለምሳሌ እናንተ [ካድሬዎቹን] ልክ ልካችሁን ብንነግራችሁ ምንም አትሉኝም?” ይሏቸዋል። “ይናገሩ ችግር የለውም” ተባሉ። በዚህ ወቅት አያ ሙሄ “እናንተ ሀገር አስገንጣይ…. ናችሁ” ብለው ቁጭ አሉ። በአያ ሙሄ ንግግር የተበረታቱት አቶ ይመር የሚባሉ ሌላ ሰው፤ “አያ ሙሄ እንዳለው” ብለው ወደ እሳቸው ዞረው ሲያዩ፤ አያ ሙሄ በቦታቸው አልነበሩም። አቶ ይመርም ለመናገር ከተነሱ አይቀር “ዴሞክራሲ አያ ሙሄ እንዳለው ዴሞክራሲ ነው” ብለው ተቀመጡ። ይህ ምሳሌ የሰሜን የጉልበት ፖለቲካና የኢህአዴግ ዴሞክራሲ የይስሙላ ዴሞክራሲ መሆኑ አመላካች እንደሆነም ገልፀዋል። ኢህአዴግ በንድፈ-ሃሳብ ከደርግ ቢለይም በተግባር ግን ብዙ የሚያመሳስለው መገለጫዎች እንዳሉት ነው የገለፁት።
ለጉልበት ፖለቲካ ባህል መዳበር ሀገሪቱ የክርስትና ሃይማኖትን ተቀብላ ተግባራዊ ያደረገችበት ሁኔታ እንደሆነም በመፅሐፉ ውስጥ ትሁት በሆነ አቀራረብ መጠቀሱን ያደነቁት አቶ አስራት፤ በሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ውስጥ “ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ” የሚለው ብሂል የገዢዎችን የተጠያቂነት የፖለቲካ ስርዓት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር እንደሆነም ገልፀዋል።

በገጠሪቱ ኢትዮጵያም፤ “ኢህአዴግን ያመጣው እግዚአብሔር ነው” የሚል ኀሳብ መኖሩን ያስታወሱት አቶ አስራት፤ ይህን አመለካከት ተከትሎም “እግዜር ያመጣውን እግዜር ያውርደው” የሚል አረዳድ መኖሩን አስረድተዋል። እንደዚህ ብሎ በሚያስብ ማህበረሰብ ውስጥ ለዴሞክራሲ የሚደረግ ትግልም በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለዋል። እግዜር መቼ እንደሚያወርደው አይታወቅም። “ምክንያቱም አንዳንድ የቤተ-ክህነት ሰዎች እንደሚሉት ለእግዜር አንድ ሺህ ዓመትም አንድ ቀን ሊሆን ስለሚችል እግዜር እስኪያወርደው መጠበቅ አይገባም” ብለዋል። ፖለቲካ የምድራዊ ጉዳይ በመሆኑ ሰማያዊ ገፅታን ማላበሱ ተገቢ አለመሆኑንም አስምረውበታል።

የሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል የጉልበት በመሆኑም በመፅሐፉ ውስጥ ሦስት አይነት የፖለቲካ አማራጮች ብቻ መኖራቸውን አቶ አስራት ገልፀዋል። እነሱም አርፎ መቀመጥ፣ መሰደድ ወይም መታሰር መሆናቸውንም ጠቅሰዋል። በዚህ ወቅት መታሰር ደግሞ ጀግንነት መሆኑን በማውሳት “የጀግና ቤቱ እስር ቤት ነው” የሚለውን የአቶ አንዱአለምን ኀሳብ ይበልጥ አጠናክረውታል።

ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ የተለያዩ መሆናቸው በመፅሐፉም መጠቀሱን እንዲሁም እሳቸውም እንደሚያምኑበት ገልፀዋል። “የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ቢሆኑ፤ እኔም ዛሬ በዚህ መድረክ ላይ ባልተገኘሁ” ያሉት አቶ አስራት “የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንዲሉ ሕወሓትንና የትግራይን ሕዝብ ደባልቆ መመልከት ተገቢ አይደለም ብለዋል። አንድ ሥርዓትና ሕዝብ አንድ የሚሆኑበት አጋጣሚ እንደሌለ በመግለፅ በዚህ በኩል ያለው መደናገር ሊስተካከል እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሌላው በመፅሐፉ የተገለፀው የሀገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባህሪና መገለጫ ነው። በሀገሪቱ ሦስት አይነት አደናጋሪ የፓርቲ አይነቶች መኖራቸውም እነሱም በኢህአዴግ የሚመሰረቱና ለኢህአዴግ ዓላማ የቆሙ፣ በንፁህ ህሊና ተቋቁመው እየበረቱ ሲሄዱ ኢህአዴግ ሰርጎ ገብ አስገብቶ ፓርቲዎቹ እንዲከፋፈሉ የሚደረጉና እንዲሁም ሕዝብን መቀስቀስና ማደራጀት ያልቻሉ የሌሎችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተፅዕኖ መቋቋም ያልቻሉ፣ እንዲሁም ኢህአዴግ ከሚሰነዝርባቸው ዱላ የተነሳ ለኢህአዴግ የሚያገለግሉ ፓርቲዎች መኖራቸውን መጠቀሱ ተገቢነት ያለው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዲያስፖራ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በመፅሐፉ ላይ በእውቀትና ድፍረት ላይ የተመሠረተ ኀሳብና ትችት መቅረቡን ያወሱት አቶ አስራት በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በገንዘብ የሚረዱ በመሆኑ የእነሱን ደካማ ጎን መግለፅ አስቸጋሪ ነው፤ እነሱም ቶሎ የሚገነፍሉ ናቸው ብለዋል። አንዱአለም ግን በህሊናው በመመራት እነሱን መተቸቱ ተገቢ እንደሆነም ገልፀዋል። በዳያስፖራ ዴሞክራሲ ያለገደብ ቢኖርም አጠቃቀሙን ካላወቅንበት በኋላ ለእኛም አስቸጋሪ እንደሆነም አስገንዝበዋል። በዲያስፖራ በዘር፣ በሃይማኖትና በጎጥ ያለው መከፋፈል አስፈሪ ከመሆን አልፎ ተስፋም የሚጣልበት ከመሆን እየራቀ ነው ብለዋል።

ብሔራዊ መግባባት አስፈላጊነት በተመለከተም በመፅሐፉ መገለፁ ተገቢ እንደሆነ ያስረዱት አቶ አስራት የሀገሪቱ ፖለቲካ የጉልበት ፖለቲካ ባህል መሆኑን ተከትሎ ደም መፋሰስ በመፈፀሙ ብሔራዊ የመግባባት ጥያቄ መነሳቱ ተገቢ መሆኑን አውስተዋል። በዚህ ረገድ አንዱአለም ይሄንን የእርቅ ጥያቄ ማንሳቱ በአዎንታዊ ጎኑ የሚታይ እንደሆነና እንደዚህ አይነቱ አመለካከት በእነማንዴላና በእነ ማሕተመ ጋንዲ ይቀነቀን የነበረ አጀንዳ እንደነበረም አስረድተዋል።

በመቀጠል በመፅሐፉ ላይ አስተያየት የሰጠው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነው። የተመስገን አስተያየቶች አቶ አስራት ከሰጡት አስተያየት ጋር ተቀራራቢነት ያላቸው ነበሩ። መፅሐፉ የተፃፈበት ሁኔታ አስቸጋሪና ውስብስብ በመሆኑ ደካማ ጎኑን ለማንሳት አስቸጋሪ እንደሆነም አመልክቷል። መፅሐፉ በብርድ ልብስ ተከልሎ የተፃፈ ከመሆኑ አንፃር የመፅሐፉን ደካማ ጎን ከማጉላት ይልቅ መፅሐፉ ተፅፎ ለንባብ መብቃቱን በአዎንታዊ ጎኑ መመልከቱ ተገቢ እንደሆነም አስምሮበታል።

መፅሐፉ ምስጢራዊ በሆነ መልኩ በመፃፉና በማረሚያ ቤቱም “መለስ ከልጅነት እስከ እውቀት” ከሚል መፅሐፍ በተለየ ሌሎች ማጣቀሻ መፅሐፎችን ማግኘት ስለማይቻል በማጣቀሻ መፅሐፎች ባይዳብር ላይገርም እንደሚችል ገልጿል።

በመፅሐፉ የሀገሪቱን የፖለቲካ ውጣ ውረድ የተገለፀ ቢሆንም ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ግን ብዙዎች ተስፋ አድርገው እንደነበር፤ ከእነዚህም መካከል አንዱአለምም አንዱ እንደነበር የጠቀሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ኢህአዴግ ጫካ በነበረበት ጊዜ የሚያቀርበው ፕሮፓጋንዳ ደርግን አባሮ አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት ለመግባት ሳይሆን፤ እየሱስ ክርስቶስን ማርኮ ገነትን ለመቆጣጠር ይመስል ስለነበር በወቅቱ በኢህአዴግ ላይ ተስፋ ማድረጉ ላይገርም ይችላል ብሏል። ነገር ግን ኢህአዴግ ከመጣ በኋላ ከገሃነብ ያልተሻለ ሀገር ነው ያለን ሲል ገልጿል።

በመፅሐፉ ከቤተ-እምነቶች ጋር ተያይዞ የተነሳው ኀሳብ ትኩረት የሚስብ መሆኑን የጠቀሰው ተመስገን የቤተ-እምነቶች ልዕልና ማጣትን ተከትሎ የአፋሸ አጎንባሽ ልማድ በመስፋፋቱ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለቄሳር መገዛት መጠቀሱ ተገቢ መሆኑን አስምሮበታል። ይህ ልማድ አሁን ላለው የሴራ ፖለቲካ መስፋፋት አስተዋፅኦ እንዳለውም አመልክቷል።

ህወሓትና የትግራይ ሕዝብን በአንድ ላይ ጨፍልቆ የመግለፅ አዝማሚያ ተገቢ አለመሆኑን የጠቀሰው ተመስገን፤ ኢህአዴግ አድዋ ላይ ማር አላዘነበም። አድዋ ላይ ህወሓትን የደገፈ ይጠቀማል። ጎንደር ላይ ብአዴንን የደገፈ ይጠቀማል። ወለጋም ላይ አባዱላንና ኦህዴድን የተወዳጀ ይጠቀማል እንጂ የአንድ ብሔር የበላይነት አይደለም ብሏል። ነገር ግን በዚህ አመለካከት “የሚጀነጅኑ” መኖራቸውን የጠቀሰው ተመስገን በተለይ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ህወሓትንና የትግራይን ሕዝብ የመቀላቀል ሁኔታ መኖሩንም አውስቷል።

“ነፍጠኛ አማራን አይወክልም ብለን፤ ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ይወክላል የሚል ፖለቲካ መኖር የለበትም” ሲል የገለፀው ተመስገን፤ ፓርቲዎችም ይህንኑ ግልፅ በማድረግ ጉልበተኛውን ስርዓት ከሕዝቡ መለየት አለባቸው ብሏል። ፓርቲዎቹ በ1967 ዓ.ም ህወሓት እንጂ የትግራይ ሕዝብ አልተመሰረተም ብለው አፅንኦት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ብሏል።

በትግራይ ሕዝብ ስም የተቋቋሙ ድርጅቶችም የስርዓቱን ተዋንያኖች ከመጥቀም ባለፈ የትግራይን ሕዝብ ተጠቃሚ አለማድረጋቸውንም ጋዜጠኛ ተመስገን ገልጿል።

የአደናጋሪ ፓርቲዎች ውልደትና ሚና ከእነመኢሶን ጊዜ ጀምሮ ያለ ችግር መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛ ተመስገን በታጠረ መንገድ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን በተመለከተም በመፅሐፉ የተጠቀሱ ጉዳዮች መካከል ውህደትን የመፍራትና ተያያዥ ችግሮችን መገለፁን አስረድቷል።

አንዱአለም የራሱን ፓርቲ አንድነት ጭምር መተቸቱ ተገቢ እንደነበረም አመልክቷል። በተቃዋሚ ፓርቲዎች ያደፈጠ ሽኩቻ መኖሩም ለፓርቲዎች መዳከም ጉልህ ሚና መጫወቱንም አስረድቷል።

በውጪ ሀገር ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አንዱአለም በመፅሐፉ በሁለት መክፈሉን ያወሳው ተመስገን፤ የመጀመሪያዎቹ ሞክረው፣ ሞክረው ያልተሳካላቸው ኦነግን ጨምሮ መኢሶን፣ ኢህአፓ ሲሆኑ፤ ሁለተኛዎቹ ስሪታቸው እዛው ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሆኑ ግንቦት ሰባትን የመሰሉ ናቸው ብሏል። በተለይ “ግንቦት ሰባትን” በተመለከተ አንዱአለም በመፅሐፉ ውስጥ መረር ያለ ነገር መግለፁ ዋጋ ያስከፈለው ጉዳይ በመሆኑ ነው ያለው ተመስገን፤ አንዱአለም “ኢህአዴግ ግንቦት ሰባት ያልዘራውን እንዲያጭድ አድርጎታል” የማለቱ ውጤት ትክክል መሆኑንና በርካቶችንም ለእስር እንዲዳረጉና ለሰላማዊ ትግሉ መዳከምም አስተዋፅኦ ማድረጉን አስረድቷል።

አንዱአለም የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ መሆኑ የሚደገፍ እንደሆነ የጠቀሰው ጋዜጠኛ ተመስገን የሥርዓት ለውጥ በጠመንጃ አፈሙዝ ከመጣ ለውጥ አይመጣም ብሏል። በሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታም በአፈሙዝ የመጣው ለውጥም የሥርዓቱን ቁንጮዎች ቱጃር ከማድረግ ባለፈ አስተማማኝ የዴሞክራሲ ስርዓት አለመገንባቱንም አስረድቷል። ይሁን እንጂ የሰላማዊ ትግሉን በአግባቡ በመጠቀም ላይ ችግር መኖሩንም አስረድቷል።

“ዛሬም አስፈቅደን ነው የተቃውሞ ሰልፍ የምናደርገው። ጋዳፊም ሆኑ ሙባረክ በፍቃድ ሰልፍ አይደለም ከስልጣን የተወገዱት። እኛን የሚያስቆጣ በቂ ምክንያት ስላለን የሥርዓት ለውጥ ለማድረግ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ሰልፍ መውጣት አለብን” ሲል ተመስገን ተናግሯል።

ጋዜጠኛ ተመስገን በዲያስፖራው በኩልም ኢትዮጵያውያን ከተሰደዱ በኋላ በሃይማኖትና በብሔር የሚከፋፈሉበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አንዱአለም በመፅሐፉም መገለፁ እሱም የሚጋራው ስጋት እንደሆነ ገልጿል።

ክፍፍሉ “የጎንደሬ ገብሬል፣ የትግራይ ማርያም” እስከመባል መድረሱ ዞሮ ዞሮ እየጠቀመ ያለው 22 ዓመት ስልጣን ላይ ለቆየውና ለሌላ 22 ዓመት እየተዘጋጀ ላለው ሥርዓት ነው ብሏል። ስለሆነም በመፅሐፉ ላይ ለዲያስፖራው የተላለፈው መልዕክት ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብሏል።

በመጨረሻም በመፅሐፉ ውስጥ ያልተሄደበት መንገድ ሲባል ሰላማዊ ትግል መሆኑን ነገር ግን ሰላማዊ ትግሉ በሚገባ ያልተተገበረ መሆኑን ለመግለፅ ነው ያለው ተመስገን፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ የተቀመጠው የብሔራዊ መግባባት የመውጫ መንገድ (exit strategy) ላይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተናግሯል።

ከኢትዮጵያ እሳት ወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ፤ከድጡ ወደ ማጡ (ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

ባለፉት አስርት ዓመታት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በአገራቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር በተለየ መልኩ ተንሰራፍቶ እየተፈጸመ ካለው ጭካኔና ርህራሄ የጎደለው አምባገነናዊ ስርዓት ለማምለጥ ሲሉ እግራቸው ወዳመራቸው አገር በመሰደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ “ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር” እንደዘገበው ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 በግምት 200,000 ኢትዮጵያውያት ሴቶች በውጭ አገር በአብዛኛውም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የውጭ የስራ ዕድል ለመፈለግ ተገደዋል፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያት ሰራተኞች አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው አምባገነናዊ የእሳት ነበልባል አመለጥኩ የሚል እምነት ነበራቸው፣ ሆኖም ግን ወደ ሳውዲ አረቢያው የእሳት እረመጥ ተወርውረው እራሳቸውን አገኙት፡፡

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።
ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል።  በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል።

Tuesday, November 26, 2013

ተዋርደን አንቀርም!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

November 26, 2013
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝ

ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::

እንዴት!በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡

መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡

አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

November 26, 2013
ከቅዱስ ዬሃንስ

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

November 26, 2013
የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/



የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።

በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል።

ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል ። በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል።

በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።

ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።

Monday, November 25, 2013

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው? (ተመስገን ደሳለኝ)

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው?
ተመስገን ደሳለኝ
November 25, 2013


የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡
ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊው ጀሀድ ያወጀው አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ባመጣው ዕዳ በድሃ ወንድም-እህቶቻችን ጀርባ ላይ ያረፈ ምህረት የለሽ ብትር እንጂ፡፡ …ይህ ግን ለምን ሆነ? ጥያቄ ነው፡፡

ርግጥ ነው፣ እንዲህ አይነቱ የእልቂት ነጋሪት መጎሰም ከጀመረ ዓመታት ነጉደዋል፤ መነሻ ሀገሩ ግን ሳውዲ አረቢያ ወይም ሊቢያ አይደለም፤ እዚሁ ኢትዮጵያችን ምድር ላይ እንጂ…

ዘ-ፍጥረት…
የየካቲቱ አብዮት ድንብዥታ (ሀንግኦቭር) ዛሬም ድረስ ዘመን ተጋሪዎቼን እያሳደደና እያሰደደ ይገኛል፡፡ ያኔ ያ ትውልድ ‹ኑ እንነሳ፣ ከተማውን እንውረር፤ አሮጌውንም ቅፅር በጩኸት አፍርሰን፣ አዲሱን እንፍጠር!› የሚል መለከት መንፋቱ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ባይሆንም ‹የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ጥቂቶች› እንዲል መፅሀፉ፣ እፍኝ ለማይሞሉ ‹ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖች› የተናጠል አሸናፊነት፣ የወል ተጠያቂ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለምን ቢሉ? ስለተከሰተው ታሪክ ይሆናል መልሱ፡፡ በርግጥም ‹ፓርቲ› የሚባል የ‹ጦስ ዶሮ› ባነበረው ልዩነት በጥይት ደብድበው ሲያበቁ፣ አፈር ፈጭቶ፣ ውሃ ተራጭቶ ባደገበት መንደር እንደ መናኛ በየመንገዱ አስጥቶ ማዋል፣ ለግብዓተ መሬቱ የጥይት ዋጋ ማስከፈል፣ ወላጆችን እርም መከልከል… ከዚህ የከፋ ምን ሊያመጣ ኖሯል? …ከተኛበት አልጋ
እያነቁ መስቀል፣ ከገሀነም በከፋው ቅጣት ‹ወፌ-ላላ› ገልብጦ ማሰቃየት፣ በአንድ ጉድጓድ ስልሳውን አነባብሮ መቅበር… ከዚህ ሌላ ምን ሊያስገኝ ኖሯል? …የሆነውም ይህ ነበር፡፡ እነሆም ያ ትውልድ የፀነሰው የተገነባውን መናድ፣ የተሰራውን ማፍረስ፣ በራስ ወገን ላይ መከራ ማዝነብን የሚመክረው የዘ-ፍጥረት መፅሀፍ ምዕራፍ እዚህ ጋ ነበረ የጀመረው፡፡

አዲስ ታሪክ አልተሰራም!

‹አዲስ ንጉስ እንጂ፣ ለውጥ መቼ መጣ!› እንዳለው ከያኒው፣ ታጋዮቹ በወታደሮቹ ቦታ ከተቀመጡ በኋላ የነበረው-እንደነበረው ነው የቀጠለው፤ ‹ባለሙያ› ገራፊዎች በአሸናፊዎቹ ከመተካታቸው በቀር፣ ማሰቃያ ጎሮኖቹ ዛሬም ወደ ሙዚየምነት አልተቀየሩም፣ መገረፊያው፣ መገልበጫው፣ መግደያው፣ መጋዣው… አሁንም የቀድሞውን ግልጋሎታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ ማን ያውቃል? ነገም በዚሁ ይቀጥሉ ይሆናል፤ ለአጎራባች መንደሮች መቀጣጫ በሚል የጭካኔ ፈሊጥ፣የአማፅያን ኮሽታ የተሰማበትን መንደር ሁሉ ዶግ አመድ ማድረግም፣ የጄነራሎቻችን የጦር ‹ጠበብ›ነት መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል፤ በሀውዜን፣ አርባ ጉጉ፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ጋምቤላ፣ አዋሳ፣ ኦጋዴን፣ ቀብሪ-ደሀር፣ ደገ-ሀቡር… የፈሰሰው የግፉአን ደም፣ የተከሰከሰው የንፁሀን አጥንት ታሪክ ነጋሪ ጥቁር ሀውልት መሆኑን ማን ይክዳል? ይህንን ሁሉ ምድራዊ ፍዳ፣ ዓለም እንደ ማንኛውም አሳዛኝ ዜና ሰማው እንጂ፣ ሰለባዎቹን ለመታደግ ያደረገው እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ
አልነበረም፤ በራስ መንግስት፣ በራስ ወገን መናቅ፣ ክብር መነፈግ፣ ለ‹ምርኮኛ ሕግ› ማደር… ክፋቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ የዛሬዎቹ አረቦቹም በወገኖቻችን ላይ የጭካኔ እጃቸውን እንዲያነሱ የልብ ልብ የሰጣቸው፣ ይኸው የእኛው የእርስ በእርስ አለመደጋገፍና አለመከባበር ነው፡፡ ትላንትና በጉራ ፈርዳና ቤንች ማጂ ዞን ጎሳ መመዘኛ ሆኖ ‹ውጡ የክልሉ ተወላጅ አይደላችሁም› በሚል በገዛ ወገኖቻቸው እንደጠላት ሀገር ሰው በጦር መሳሪያ ተከበው፣ ንብረታቸውን ሜዳ በትነው ስለተባረሩ ኢትዮጵውያኖች፣ የሰሙ አረቦች ‹ሳወዲያ አረቢያን ልቀቁና ውጡ› ብለው ይህ አይነቱን መዓት ቢያወርዱ ምን ይደንቃል? የባዕድ ሀገር ሰው የትንኝ ነፍስ ያህል እንኳ ሳይጨነቅ እንደዘበት ህይወታችንን ቢነጥቀን በእርሱ ላይ መፍረድ እንዴት ይቻለናል? አሳልፈው የሰጡን እነማን ሊሆኑ ነው?

እመነኝ፣ በሳውዲ አረቢያ ጎዳናዎች የሰው ራስ ቅል እንደ በግ በመጥረቢያ ሲከሰከስ፣ እንደ ጦስ ዶሮ ተጋድሞ ሲታረድ፣ በቁሙ እሳት ሲለቀቅበት፣ ህፃናት የወታደር መለዮ በለበሱ አረመኔዎች ሲረገጡ… ልብህ እያለቀሰ፣ ፊትህ በእንባ እየታጠበ ያየኸው አይነት ጭካኔ ምንጩ ይህ ነው፤ ይህም ነው የኢትዮጵያን ሰው በአልባሌ ምክንያት መግደል፣ እያፏጩ ጉዞን የመቀጠል ያህል ያቀለለው፤ ለዚህም ነው በሙስሊሞች ቅድስቲቷ መዲና ላይ በድንጋጤ የጨው አምድ የሆነ አካለ-ቁመና፣ በሽብር ተውጣ አቅሏን የሳተች እህት፣ ስጋት ያናጠበው ወንድም ተመልክተህ በሀዘን የተቆራመድከው፤ ‹‹ወይኔ ወገኔ!›› ብለህ ደም እንባ የተራጨኸው፡፡ …እናስ! ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተመጣጣኝ ዋጋ መክፈል ያለበት ማን ነው? ንጉሥ አብደላና ዕኩይ ተከታዮቹ ብቻ? ወይስ እንዲህ የፊጥኝ አስሮ ለአረብ ሀገራት መቀለጃ የዳረገህ መንግስትህም ጭምር?

ከችጋርና ጭቆና ያልተፋታ ሕዝብ ዳቦና ነፃነት ፍለጋ እግሩ ወዳደረሰው ሀገር ተሰዶ መኖሩ በእኛ የተጀመረ አይደለም፤ እንዲያውም ስደተኞችን ካስተናገዱ ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዓለም ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀሰው የእኛዋ የአቢሲኒያ ምድር ኢትዮጵያ ነች፡፡ የሩቁን ትተን እስከ የኃ/ስላሴ ስርዓት ፍፃሜ ድረስ የነበረውን ተጨባጭ ሁነት ብንመለከት እንኳ፣ ‹አረብ ቤት› በሚል ተቀፅላ የሚታወቁት ብዙዎቹ ሱቆችና የንግድ መደብሮች፣ በስደት መጥተው እኩል እንደ ዜጋ ሀገራችን መኖር በቻሉ አረቦች የተያዙ ነበሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይህች ገናና ሀገር ለሌሎች ሀገራት ሕዝቦች የነፃነትና የክብር ተምሳሌትም ነበረች፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በፈሪሐ እግዚአብሔርነቷ፣ በፍትሐዊነቷና በርትዓዊነቷ ስሟ ተደጋግሞ የተወሳና የተመሰከረላት፣ የታላቅ ሕዝብ ታላቅ ሀገር ነበረች፡፡ ዛሬ በተፈጥሮ ማዕድን በልፅጋ የሀበሻ ስደተኞች መናኸሪያ ለመሆን በበቃችው ሳውዲ አረቢያ የተወለዱት ነብዩ መሀመድ የዛሬ 1400 ዓመታት ገደማ በስደት መጠለያነት የመረጧት፣ ሀገሪቷም ተከታዮቻቸውን እጇን ዘርግታ በመቀበል ከራሷ ዜጋ እኩል ተንከባክባ ያኖረቻቸው ስልጡን ሀገር ነበረች፡፡ ማን ነበረ ‹ወርቅ ላበደረ…› ያለው? እነሆም ዘመኑ ተቀያየረና ‹‹የኋላኞቹ ፊተኞች፣ የፊተኞቹ ኋለኞች›› ይሆኑ ዘንድ ግድ በማለቱ ዛሬ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራ ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እየተጎነፀፉ ሲመጡ፣ እኛ የኋሊት ተንሸራተን ቁልቁል ለመውረድ በቃን፡፡

ምንም እንኳ እነዛ ሁሉ መልካም መገለጫዎቻችን ዛሬም ድረስ ባናጣቸውም፣ በብሔር ክፍፍልና በእርስ በእርስ ሹኩቻ የተነሳ ግን በደህነት ማጥ ውስጥ ተዘፍቀን፣ እኛም በተራችን መሰደድ ዕጣ ክፍላችን ሆኖ ቀረ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ወጣት በሀገሩ የመኖር ተስፋው በመሟጠጡ፣ በስደት ወጀብ የሚንገላታ፣ ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ሲናወዝ መሽቶ የሚነጋለት ብኩን ሆኗል፡፡ በሀገሩ እጅግ ከመመረሩም የተነሳ ራሱን ለሻርክ ጥርስ፣ ለእንግልት፣ ለግርፊያና ለበልዓ-ሰቦች አሳልፎ እስከ መስጠት በሚያደርሰው የስደት ጉዞ ለማለፍ የማያመነታ ትውልድ ለመሆን ተገዷል፡፡ ይህ ከድህነት ወለል ስር ያሳደረን የዘመን ግርሻ፣ ይህ ከመንግስት ጋር አይንና ናጫ ያደረገን አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ለዚህ ሁሉ አሳረ-መከራ ዳርጎን፣ ከሀፍረት ጋር አንገታችንን እስደፋን… ውለታን ከማስረሳቱም በላይ ለከፋ በደል አጋልጦ ቁጭት አስታቀፈን፡፡

ሰሞኑን ‹‹የበላችበትን ወጪት…›› ከሰበረችው ሳውዲ አረቢያ የተሰማው አሰቃቂ ዜናም የእዚህ የኢትዮጵያን ስደተኞች ተከታታይ ፍዳ ጉትያ ነው፡፡ እርግጥ አብዛኛው የአረብ ሀገራት መሬቱ ሰለጠነ እንጂ ሕዝቡ ገና ጨለማ ዘመን ውስጥ ነው፤ ሌላ ሌላውን ወደጎን ብለን የሰሞኑን አውሬአዊ ባህሪያቸው እንኳን እንደ አይነተኛ ማሳያ ልንወስደው እንችላለን፤ ይህ ድርጊትም እንሰሳዊ ባህሪያቸው የስነ-ዝግመት ለውጥን ገና አለማገባደዱን ያመለከተ ነው፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒሊክ አድዋ ላይ፣ ያውም ሀገራቸውንና ዙፋናቸውን በጦር ኃይል ለመንጠቅ የጎመዠችው ሮም ያዘመተቻቸው ወታደሮች፣ እልፍ አእላፍ ሠራዊታቸውን ፈጅተው፣ የቅርብ ወዳጆቻቸው የሆኑ የጦር አበጋዞቻቸውን ገድለው የማታ ማታ የሽንፈትን ፅዋ አስጎንጭተው ከማረኳቸው በኋላ በርህራሄ ተንከባክበው እንደያዟቸው የዓለም ታሪክ ያውቀዋል፡፡

በሀገሩ ኑሮ አልቃና ብሎት፣ በሰው ምድር የሰው አደፋ አፅድቶ፣ ቆሻሻ ለቅሞ… ፋታ የማይሰጠውን የእህል ውሃ ጥያቄ ለመሙላት በማሰነ፣ ሆድቃን በሳንጃ መዘርገፍና የዱር አውሬ እንኳ የማይፈፅመው የጋርዮሽ ሴት ደፈራ መፈፀም… ምን አይነት ‹ኢብሊሳዊ› (ሠይጣናዊ) ተግባር ነው? የተቸነፈን መልሶ ማቸነፍ፣ የወደቀን መርገጥስ ‹ከመክፈር› (ፈጣሪን ከመካድ) በምን ይለያል?

አሁንም እደግመዋለሁ፡- ይህ ፖለቲካ አይደለም፤ እየፈሰሰ ስላለ የንፁሀን ደም፣ የወላድ መሀን ስለሆኑ እናቶች፣ ጧሪ ቀባሪ ስላጡ የተራቡ አባቶች፣ አሳዳጊ አልባ ስለሆኑ ህፃናት፣ ያለሚስት ስለቀሩ አባወራዎች፣ ባላቸውን ስለተነጠቁ የቤት እመቤቶች … የሰቆቃ እሪታ ነው፡፡ በወጡበት ሰው ሀገር ላይ ወድቀው ስለሚቀሩ ወገኖቻችን ዋጋ ስለመጠየቅ ነው፤ ለነጋዴው መንግስታችን ኢትዮጵያዊው ዜጋ ዋጋው ስንት እንደሆነ የመሞገት ጉዳይ ነው፡፡

ሀገር ምን ማለት ነው? ‹ሀገር› የሚለውን ቃል የኢህአዴግ መራሹ-መንግስት መዝገበ ቃላት ምን ፍቺ ሰጥቶት ይሆን? ሉዓላዊነትስ በ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ቀዩ መፅሀፍ አንደምታው ምን ይሆን? …ቀለብ ሰፍረን የምናሳድረውን ሠራዊት ሞቋዶሾ ድረስ ልኮ፣ የባራክ ኦባማን ስጋት ማቃለል? በ‹ተባበሩት መንግስታት› ስም የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛ ሆኖ በሱዳናዊያን የውስጥ ችግር ላይ-ታች እንዲማስን ማድረግ? የሕዝብ ደህንነት መ/ቤትስ ኃላፊነቱ የእናንተንና የቅምጦቻችሁን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ ነውን? የአምባሳደሮቻችን የሥራ ድርሻ ፓስፖርት ማደስና የመግቢያ ፍቃድ መስጠት ብቻ ነው? በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ‹ጊንጥ ሰላይ› መሆን? ቦንድ መሸጥ? ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው› እያሉ መስበክ? …ወይስ የዜጎችንም ደህንነት መከታተልና መጠበቅንም ጭምር? …ይህ ነው የወቅቱ ዓብይ ጥያቄ፡፡

የዲፕሎማሲ ግንኙነትስ ምን ማለት ነው? አገዛዙ በአንድ ወቅት ተቀማጭነቱ ኳታር-ዶሀ የሆነው ‹አልጄዚራ› ቴሌቪዥን ‹ስሜን አጠፋ› በሚል የኳታርን ኢምባሲ እንደ ዘጋው አይነት ስራን ብቻ የሚመለከት ይሆን? ከዋነኞቹ ለጋሽ ሀገራት በግንባር ቀደምነት የምትመደበው ኖርዌይስ ኢምባሲዋ የተዘጋው ለማን ትርፍ ነበር? ለብሔራዊ ጥቅም መቆርቆርስ ‹ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አልተከበረም› ብለው ዘገባ ባወጡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያንን ሁሉ አቧራ ማስነሳት ይሆን?

ሌላው ቢቀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለምን እንደ ተመሰረተ ይዘነጋል? አባቶቻችን ኮሪያና ኮንጎ ድረስ የዘመቱት ለዓለም ዜጎች ሰላም መሆኑስ እንዴት ይረሳል? የድርጅቱ አባል ሀገራት የፈረሙት ስምምነትስ የሳውዲ አረቢያን ሽፍትነት እንኳ ለመከላከል አቅም አይኖረውም? በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እልፍ አእላፍ ወታደሮቻችን ካለቁብን በኋላ ከባረንቱ የተመለስነው፣ ባድሜ ላይ የቆምነው፣ በዛላንበሳ የታገድነው… የማንን ሕግ አክብረን ነበር? ያውም ‹በስለላ ስራ ሊሰማሩ ይችላሉ› ተብለው የተጠረጠሩ ኤርትራውያን እንዲያ በክብርና በእንክብካቤ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተሸኙት፣ በጦር ሜዳ የተሸነፈው ሻዕቢያ ተፈርቶ ነበር እንዴ? …ይህ ነው እንቆቅልሹ፡፡

ዛሬስ መንግስታችን የስደተኛ ዜጎችን ደህንነት በምልዓት የማይከታተለውና የድረሱልኝ ጩኸታቸውን ሰምቶ ፈጥኖ እጁን የማይዘረጋላቸው ለምን ይሆን? ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት? ወይስ በለመደው የንቀት መነፅር አይቶ እንዳላየ በቸልተኛነት አልፎት ነውን? በርግጥ ይህንን የበደል ማማ ካለፈው ታሪኩ አንፃር ከገመገምነው ምክንያቱ ሀገራዊ ስሜቱ ደካማና ከሥልጣኑ ሌላ ምንም የሚያሳስበው ነገር ባለመኖሩ ብቻ እንደሆነ ይገባናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሠማያዊ ፓርቲ የአረቦቹን ወደር የለሽ ጭካኔ ለማውገዝ በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ በር አጠገብ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ያገደው ‹ይህ አይነቱ ሀገራዊ መቆርቆር ነገ ደግሞ መስቀል አደባባይን በሕዝብ ሱናሚ ለማጥለቅለቅ መነቃቃት የሚፈጥር ገፊ ምክንያት ሊሆን ይችላል› ብሎ በስጋት ስለተጠፈነገ ይመስለኛል፡፡

የሆነው ሆኖ የመንግስት ህልውናም ሆነ አቅም በእንዲህ አይነቱ ወቅት ነውና የሚፈተነው ኢህአዴግም በዚህ ተግባሩ ዜጎቹን የመታደግ ገት እንዳሌለው አስመስክሯል፡፡ መቼም በሲ.አይ.ኤ ተላላኪነቱ በ‹ዋይት ሀውስ› ማህደረ-መዝገብ ውስጥ ከጊዜ ጊዜ እየዳጎሰ የመጣው የ‹ውለታ›ው ዶሴ ለእንዲህ አይነቱ ፈታኝ ወቅት መሆን ይሳነዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ሼክ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ የሳውዲ ነጋዴዎች፣ ሀገራችን ውስጥ በበርካታ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው አትርፈው ማደራቸው፣ በሰፋፊ እርሻዎች ዘርተው ማጨዳቸውስ እንደምን ተዘነጋ? ይህ ቢያንስ በነፍስ-ውጪ ነፍስ-ግቢ ለተያዙ ወገኖቻችን እንዴት የመደራደሪያ ጉልበት መፍጠር ሳይችል ቀረ? …በርግጥ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከጎራ ፈርዳ ስላፈናቀላቸው አማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በተጠየቀበት ጊዜ ‹‹ደን ጨፍጫፊዎች ናቸው›› ሲል የስላቅ መልስ እንደሰጠው ሁሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም የሳውዲውን እልቂት
በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ ‹‹የማባረር ሥራው በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ተረድተናል›› በማለት መቀለዱ፣ ስርዓቱ ‹አስተዳድረዋለሁ› ከሚለው ሕዝብ ይልቅ ሥልጣኑንና ተያይዘው የሚመጡ ጥቅሞቹን በዜጎች ሕይወት ጭምር ተደራድሮ ከማስከበር እንደማይመለስ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ እንደ መንግስት በሀገር ሀብት እንደአሻው እየተምነሸነሸ፣ ‹ግዴታዬ የባቡር መንገድና ኮንዶሚንየም ቤት መስራት ብቻ ነው› ማለቱ ይህንኑ ይመሰክራል፡፡ አሊያማ ፋሺስቱ ጣሊያን እንዲያ በርካታ ድልድዮች፣ መንገዶች፣ ቤቶች… ገንብቶ ሲያበቃ፣ ‹ሀገር› ማለት ሕዝብ የሰፈረበት ሉዓላዊ ግዛት ማለት ነው ተብሎ ያ ሁሉ መስዕዋትነት ተከፍሎ በኃይል እንዲባረር ባልተደረገ ነበር፡፡

‹ሕዝቤን ልቀቅ!›

በዘመነ-ኦሪት በግብፅ ዙፋን ላይ በተፈራረቁ ፈርኦኖች፣ ለባርነት የተዳረጉ ዕብራዊያንን ነፃ ያወጣ ዘንድ በፈጣሪ ተመርጦ የተላከው ሙሴ ‹‹እግዚአብሄር ‹ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ!› ብሎሀል›› ማለቱ በቅዱሳት መፃህፍት መገለፁ እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ራሱን ‹ኢህአዴግ› ሲል በሚጠራው ‹አምሳለ-ፈርኦን› ለመከራና ለሀፍረት የተዳረጉ ሕዝቦች አርነት ይጎናፀፉ ዘንድ ‹የሙሴ ያለህ!› የሚለው ጩኸታቸው ከተራራ ተራራ እያስተጋባ መሆኑ ሌላ እውነታ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵውያን ደምም ዋይታ እየተበራከተ ነው፤ ስርዓቱ እንዲህ አይነቱ ሰቆቃን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመበት መሆኑንም ሰሞኑን የመንግስት እና ደጋፊዎቹ ሚዲያዎች የሚያሰራጩትን ዘገባ መመልከት በቂ ነው፡፡ መቼም መሬት ልሰው፣ አፈር ቅመው ያፈሩትን ንብረት ተነጥቀው፣ ባዶአቸውን እየተመለሱ ያሉ ስደተኞችን ‹በሀገራችን መስራት ይሻለን ነበር› እንዲሉ ማስገደድ ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ካልሆነ በቀር ሌላ ትርጉም  የለውም፡፡ አስከፊው ድህነታችን ጉርሻ እስከ መግዛት፣ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ቅልጥም እስከ መምጠጥ፣ የወደቀ ምግብ ከውሻ ጋር ተጋፍቶ እስከ መመገብ… በደረሰበት በዚህ የችጋር ዘመናችን ላይ በምን አመክንዮ፣ ከየትኛው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመዝኖ ሊታመን ይችላል ተብሎ ነው ‹ሀገር ውስጥ ሰርቶ በሰላም መኖር ይቻላል› የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነጋ-ጠባ የሚደሰኮረው? ምንድር ነውስ የሚሰራው? እዚህ እኛ ሀገር የማንን መፀዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቅ ይሆን የአረቦቹን ያህል ዳጎስ ያለ ክፍያ ማስገኘት ቀርቶ፣ በቀን ሁለቴ ለመብላት የሚያግደረድረው? ቅጥ አንባሩን ያጣው የግብር ፖሊሲያችን፣ እንጀራ ቸርቻሪዎችን ሳይቀር አሳድዶ የእለት ጉርሻቸውን እየነጠቀና በተንሰራፈው ድህነት ላይ ተጨማሪ እልቂት አውጆ ድሆችን ለማጥፋት ሰይፉን በሚያወናጭፍበት በዚህ ወቅት፣ ወጣቱ እንዴት ብሎ ነው በሀገሩ ሰርቶ መኖር ይችላል የሚባለው? ገና ጀንበር ከማዘቅዘቋ ጎዳናውን የሚያጥለቀልቁት ህፃናት ሴተኛ አዳሪዎችንስ ምን እንበላቸው? የትኛው ተቀጣሪስ ነው በደሞዙ የወር ቀለቡን ሳይሳቀቅ መሸመት የቻለው? …ሁላችንም የመዳፋችንን ያህል አብጠርጥረን የምናውቀው በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ይህ ነው፡፡

እነሆም በመጨረሻ እንዲህ ማለት ወደድኩ፡- ስርዓቱ ሰባኪው እንዳለው ‹የከንቱ ከንቱ፣ ከንቱ› ቢሆንም፣ አቶ መለስ ዜናዊ በኤርትራ የመጀመሪያው የነፃነት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝቶ በአስመራ ሳባ ስታዲዮም ለተሰበሰበው ህዝብ በደርግ የደረሰባቸውን በደል በማስታወስ ‹‹በእናንተ ጀርባ ላይ ያለው ጠባሳ በእኛም ላይ አለ›› ሲል ሀዘኑንና መቆርቆሩን እንደገፀላቸው ሁሉ፣ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆናችሁ ወንድም-እህቶቼ ሆይ! የእናንተ ሰቆቃና በደል፣ በእኛም ግንባር ላይ ተቸክችኮ ሀፍረታችችንና ውድቀታችንን የጋራ እንዳደረገው የታሪክ ፍርድን መጠበቁ አይቀሬ ነው፡፡ እመኑኝ ያች ዕለትም አብረን የምንነሳበት፣ ከፍ ብለን የምንበርበት ትሆናለች፡፡›

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ተቃዉሟቸዉን አሰሙ!!!


ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ወገኖች ዛሬ በተካሄደዉ የ ታላቁ ሩጫ ላይ በሳዑዲ ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸዉን ሲያሰሙና በመንግስትም ላይ ወቀሳቸዉን በመፈክር እዲዲሁም በዜማ አሰምተዋል፡፡ መንግሰት በዚህ ሩጫ ላይ ህብረተሰቡ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ እዳይቀበል በአዘጋጀቹ በኩል ቢያሳስብም(ጥቁር ሪቫን እንዳይደረግ) የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸዉና የወገኖቻቸዉ ጥቃት ያተሰማቸዉተሳታፊዎች ከፍተኛ የፖሊስና የደህንነት ቁጥጥር ከቁብ ሳይቆጥሩ “በሳዑዲ ነገር እንነጋገር የሳዑዲን ነገር ” ሲሉ አርፍደዋል፡፡ ገና ከመግቢያዉ ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ ሲደረግ የነበረ ቢሆንም አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ሪቫኑን ትተዉ በጥቁር ኮፍያና ሱሪዎች ሩጫዉን መካፈል ችለዋል(በተቃዉሞዉ የተሳተፉቱ)፡፡

በሳዑዲ ላይ ተቃዉሟቸዉን ሲያሰሙ በነበረበት ወቅትም ዳር ዳር ላይ ቆመዉ ሁኔታዉን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎችና በእድሜ የገፉ ሰዎች በእልልታ እና በጭብጨባ ያበረታቱዋቸዉ ነበር፡፡ በዚህ አኳኋን የተካሄደዉ ሩጫ(እርምጃ) ወደ መጠናቀቁ ላይ ግን በደህንነቶች የሚነዳዉ(የሚታዘዘዉ) የፖሊስ ሀይል አንድ ቡድን ላይ በማተኮር ከበባ የሚመስል ነገር በማድረግ እየቆራረጡ ወደ ጃንሜዳ ግቢ እዲገቡ በማድረግ በሩ አካባቢ ላይ ሶስት የሚሆኑ ወጣቶችን(በከፍተኛ ሁኔታ መፈክር ሲያሰሙ የነበሩ) አስረዋል፡፡ በዚህ የተደናገጡት ተሳታፊዎችም ጩኸት በማሰማት ወደ ዉስጥ እየተሯሯጡ በመግባት ሩጫዉም ተቃዉሞዉም ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገደለ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የ3ኛ አመት ማርኬቲንግ ተማሪ የነበረው አንተነህ አስፋው መገደሉን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል። ትላንት ምሽት ወደ ዩኒቨርስቲው ከሴት ጓደኛው ጋር ወደዩኒቨርስቲ እየሄደ የነበረው ወጣት፤ ከግቢው ውጭ የዩኒቨርስቲው ጠባቂ ያስቆመዋል። ተማሪውም “ከዩኒቨርስቲ ውጪ ልታስቆመኝ አትችልም” የሚል ክርክር ይገጥማል። በዚህ መሃል ሴት ጓደኛው ተመትታ ራሷን ስታ ትወድቃለች። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግርግር ጥበቃው ተኩስ ይከፍትና ተማሪዎች ይበታተናሉ። በንጋታው ጠዋት ግን ያልተጠበቀ ነገር ገጠማቸው።

ምሽቱን ተማሪዎችን ለመበተን ይሁን ወይም ሆን ተብሎ በተተኮሰው ጥይት አንድ ተማሪ ቆስሎ ኖሮ፤ ጠዋት ወደ ዩኒቨርስቲ ሲመለሱ፤ አንድ ተማሪ ሞቶ ተገኝቷል። ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ነው። በጎንደር ዩኒቨርስቲና በከተማው አካባቢ ይህ ጉዳይ ህዝቡን እያነጋገረ ይገኛል። ይበልጥ ነገሩን ያካረረው ደግሞ፤ የጥበቃውን ተግባር ለመሸፈን ሲባል ፖሊስ “እርስ በርስ በጩቤ ተወጋግተው ነው የተገደለው” ማለቱ ነው። ተማሪዎቹ ግን “የለም። ገዳዩ ምሽት ላይ የተኮሰው የጥበቃ ሰራተኛ ነው” በማለት ላይ ናቸው። እንግዲህ የአስከሬን ምርመራ የሚደረግ ቢሆን፤ የአሟሟቱን ምክንያት ለማወቅ ይቻላል። እስከዚያው ግን ነገሩ እንዳወዛገበ ይቆያል – ማለት ነው።

የሟችን ፎቶ እና ተጨማሪ መረጃዎች ካገኘን ቆየት ብለን እናቀርባለን።

ኢትዮጵያዊው ቢንያም አሰፋ ከነቤተሰቡ ተገድሎ ተገኘ

(EMF) ከከተማው ራቅ ያለ ቦታ ነው የሚኖሩት – የ40 አመቱ ኢትዮጵያዊው ቢንያም አሰፋ፣ ጣልያናዊቷ ሚስቱ እና ልጆቹ። ድንገት በደረሰባቸው ጥቃት ባል እና ሚስቱ ከሶስት ወር ልጃቸው ጋር ሲገደሉ የአምስት አመት ልጃቸው ግን ተደብቃ ለማምለጥ ችላለች። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ፤ የ5 አመቷ ልጅ ከተደበቀችበት ወጥታ ወደ ጎረቤት በመሄድ፤ “ቤተሰቦቼ ተጎድተዋል” ብላ ነገረቻቸው። ከዚያ በኋላ ነው ለፖሊስ የተደወለውና አሳዛኙ ድርጊት ይፋ የሆነው።
ቤን አሰፋ
በመጀመሪያ የሜሪላንድ ነዋሪ የሆኑት የቤን አሰፋ ቤተሰቦች የደረሰው አደጋ፤ የርስ በርስ ግጭት ሊሆን ይችላል፤ በሚል ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቶ ነበር። ሆኖም ፖሊስ ዛሬ እንደገለጸው ከሆነ፤ ግድያው በሌላ ወገን የተፈጸመ ነው ተብሏል።

ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ይፋ አላደረገም። ይልቁንም የሟች (የቤን አሰፋ ሚስት) ቤተሰቦች ከጣልያን አገር ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። እነሱ ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሁለቱም ባል እና ሚስቶች የባዮ ሜዲካል ህክምና ሳይንቲስቶች ነበሩ።

አዜብ ህወሀትን ለመልቀቅ ማመከቻ ማስገበቷ ተሰማ

የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስቴር ባለቤት የሆነችዉና የሙስናዋ እመቤት በመባል የምትታወቀዉ አዜብ መስፍን ከወጣትነት እድሜዋ ጀምሮ የገለገለችዉን ህወሀት ፓርቲ በቃኝ ብላ ለመተዉ ለፓርቲዉ ማ/ኮሚቴ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቷን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች አስታወቁ። ከባለቤቷ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በፓርቲው የነበራት ተሰሚነትና የበላይነት እየተሸረሸረ በመምጣቱ፤ ከኤፈርት ሃላፊነቷ ሳትወድ በግድ በመነሳቷና እንዲሁም ጓግታለት የነበረው የአዲስ አበባ ከንቲባነት ስልጣን በማጣቷ፣ የተበሳጨችዉ አዜብ ተስፋ መቁረጥ መጀመሯ ፓርቲውን ለመልቀቋ ዋና ምክንያት እንደሆነ ምንጮቹ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ አዜብ የምትተማመንባቸዉ አብዛኞቹ የህወሀት ባለስልጣኖች ከስልጣን ተባርረዉ መታሰራቸዉና እንዲሁም በስብሃት ነጋ ቡድን እየተወሰደባት ያለው ፖለቲካዊ የበላይነት መቋቋም ስለተሳናት ከፓርቲው በግዜ መሰናበቷ ሌላ አማራጭ የሌለዉ መሆኑን በቅርብ የሚያዉቋት ሰዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርብ ቀን ዉስጥ ተሰብስቦ የአዜብ መስፍንን ጥያቄ እልባት እንደሚሰጠዉ የጠቆሙት ምንጮች ከዚሁ ጋር አያይዘው ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ አዜብ በሲውዲን ወይም አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ዉስጥ በገዛቸዉ መኖሪያ ቤት ለመኖር ጓዟን እንደምትጠቀልል አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘረኛዉና ለብዙ ሰላማዊ ዜጎች ሞት ተጠያቂ የሆነዉ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከኢታማጆር ሹምነቱ ቦታ ተነስቶ በምትኩ በቅርቡ የሌፍቴናነት ጄኔራልነት ሹመት የተሰጠዉ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀልን ሊተካ እንደሚችል አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ቃል አቀባዮቻችን ገለጹ።

Friday, November 22, 2013

በኢትዮጵያ 38 ሚሊዮን ህዝብ የሚጸዳዳው ሜዳ ላይ ነው ተባለ

ህዳር ፲፫(አስ ሦስት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ዩኒሴፍ ባወጣው ሪፖርት እንደማለከተው ይህን ችግር ለመቅረፍ የኮሚኒቲ አስተባባሪዎች ከፍተኛ  ሚና መጫወት አለባቸው።
ኤርትራ ውጭ ላይ መጸዳዳትን በማስቀረት ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡዋን ዩኒሴፍ ጠቅሷል። በመላው ኤርትራ ውጤታማ ስራ በመሰራቱ አገሪቱ ውጭ ላይ መጸዳዳትን ያስቆመች አገር የሚል ሰርተፊኬት እንደሚሰጣት ድርጅቱ ገልጿል።
በአለም ላይ 34 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ የላቸውም።

መንግስት ከሳዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ኢትዮጵያዊያንን ባለሃብቶች እንዲረዱዋቸው በመማጸን ላይ ነው።

ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያዊያን በአስከፊ ሁኔታ እንዲባረሩ ከተደረገ በኃላ  መንግስት በሳዑዲ ስፖንሰርነት
ያጓጓዛቸውን ከ10ሺ በላይ ተመላሾች በካድሬዎች ማሰልጠኛ በሆነው የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በማሳረፍ ባለሃብቶች እንዲረዱዋቸው በመማጸን ላይ ነው።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለተመላሾቹ ማቋቋሚያ መንግስት 50 ሚሊየን ብር  መመደቡን፣ ገንዘቡ ሊያድግ እንደሚችልና በማቋቋም ረገድ ችግር እንደሌለ ከገለጹ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ባለሃብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ ከዚህ ቀደም ቃል የገቡትም ቃላቸውን እንዲፈጽሙ ትላንት በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የምሳ መርሃግብር ላይ ጠይቀዋል፡፡
አንዳንድ ባለሃብቶቹ በራሳቸው ተነሳሽነት ኮሚቴ በማቋቋም ለተመላሾቹ ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ያስታወሱት ዶክተሩ ሌሎችም ይህንን አርአያነት እንዲከተሉ በመምከር መንግሰት ከነዚህ ባለሃብቶች ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ተመላሾቹ ከህብረተሰቡ ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በከፍተኛ ጥበቃ ስር ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በቀላሉ ተመላሾችን መጎብኘት ባለመቻላቸው አንዳንድ ቤተሰቦች ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
አንድ በሳዑዲዓረቢያ እህት እንዳላት የጠቀሰች አስተያየት ሰጪ እህቴ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ማወቅ
አልቻልኩም፡፡ መጥታ እንደሆነ ውጪ ጉዳይ መ/ቤትን ብጠይቅም መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ገብቶ ለመፈለግም የሚፈቀድ ባለመሆኑ ግራ ተጋብቻለሁ ስትል ጭንቀትዋን ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን ተናግራለች፡፡
ወደ አገር ቤት ለመመለስ በፈቃዳቸው ተመዝግበዋል የተባሉት ኢትዮጽያዊያን ቁጥር ከ23ሺ በላይ ሲሆን ይህ ቁጥር በሕገወጥነት ከተፈረጁት ከ100ሺ በላይ ኢትዮጽያዊያን ቁጥር አንጻር አነስተኛ ነው፡፡ እስከትላንትና በስቲያ ማምሻውን ድረስ 10ሺ707 ሰዎች መመለሳቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ችግሮች እየደረሱባቸው እንደሆነ ለኢሳት ገልጸዋል። የኢትዮጵያን ኢምባሲ አሰራር ክፉኛ የሚተቹት ኢትዮጵያውያኑ፣ ሁሉም ዜጋ ከችግራቸው እንዲታደጋቸው እየተማጹ ነው።
በተመሳሳይ ዜናም በሳውድ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚቃወሙ ሰልፎች ቀጥለዋል። ረቡእ እለት በኦክላንድ ኒውዚላንድ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ አንዱአለም ሀይለማርያም ገልጿል
በተመሳሳይም በፈረንሳይ ፓሪስ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን አስተባባሪዋ     የገለጸች ሲሆን፣ የሳውዲ ኢምባሲ ሰራተኞች ጥያቄያቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ኖቨምበር 29 ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ በሳውዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት እንደሚካሄድ የገለጸችው ወ/ት ማክዳ፣ የፈረንሳይ የመገናኛ ብዙሀን ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በእለቱ ለመገኘት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውንም ተናግራለች።

በሳዉዲ የኢትዮጵያውን ስቃይ ያስነሳዉ ተቃዉሞ

ሕጋዊ ፈቃድ በሌላቸው ኢትዮጵያውን ላይ የሚደርሰውን ችግር እና ጥቃት በመቃወም በተለያዩ ሀገራት ሰሞኑን የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሄዱ ሰንብተዋል። ዛሬም በበርሊን እና በፓሪስ የሚገኙ ዜጎች አደባባይ ወጥተዋል።
Titel: Äthiopien - Demonstration in Paris 
Thema: Äthiopien - Protest gegen Saudi Arabiens Aktion gegen Einwanderer aus Äthiopien 
Autor/Copyright: Haimanot Tiruneh Torode (Paris Korri.) 21.11.2013 
Schlagworte:Äthiopien, Demonstration, Addis Abeba, Saudi Arabien, Einwanderer, Paris
ሳዉድ አረቢያ በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚፈፀመዉን ጥቃት በመቃወም ከመላ ጀርመን የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በበርሊን ከተማ ሰልፍ አካሄዱሰልፈኞቹ የሳውዲ መንግሥት የወሰደውን ርምጃ የሚያወግዙ መፈክሮች በማሰማት ርምጃው እንዲያበቃ ጠይቀዋል። ከሰልፉ አዘጋጂዎች መካከል አንዱ የሆኑትን አቶ በላይነህ ተሾመን ስለሰልፉ በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ። የፓሪሱንም ሰልፍ ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህ ተከታትላዋለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ

ተገን ጠያቂዎች እና የጀርመን የስለላ መስሪያ ቤት

ጀርመን እንድትቀበላቸው ያመለከቱ ተገን ጠያቂዎች ማመልከቻቸው ተቀባይነት እስኪያገኝ ረዥም ጊዜ በሚወስድ ሂደት ውስጥ ማለፍ አለባቸው ። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል ጀርመን የውጭ ዜጎችና የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ባልደረቦች አመልካቾቹን ስለ ሃገራቸው ሁኔታ ና የፖለቲካ ክትትል ይደረግባቸው እንደሆነ ይጠይቋቸዋል ።
Dolmetscher Ahmed Yasser spricht am 10.10.2013 in einem Büro in der Außenstelle des Bundesamts für Migration und Flüchtlinge in Berlin-Spandau mit Asylbewerbern aus Syrien . Foto: Bernd von Jutrczenka/dpa
Beratung für Asylbewerber
በምን ዓይነት መንገድ ወደ ጀርመን ሊመጡ እንደቻሉም ያጣራሉ ። ይህ የተለመደና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታወቅ አሠራር ነው ። ይሁንና በዚህ ሂደት የጀርመን ህዝብ እንኳን የማያውቃቸው ሌሎች ባለሥልጣናት በዚህ ሂደት ውስጥ እንደሚሳተፉ የዶቼቬለው የቮልፍጋንግ ዲክ ዘገባ ያስረዳል ።

መቀመጫውን በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ያደረገው የውጭ ዜጎችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚቆጣጠረው የፊደራል ጀርመን መሥሪያ ቤት በይፋ በመራሄ መንግሥት ጽህፈት ቤት ስር የሚገኝ ተቋም ነው ። ተቋሙ እጎአ ከ 1958 ዓም አንስቶ ለጀርመናውያን ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ለጀርመን የስለላ መስሪያ ቤት የሚጠቅሙ መረጃዎችን ይሰበስባል ። ዙድ ዶይቸ ሳይቱንግ የተባለው ጋዜጣና NDR የተባለው የጀርመን ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በጋራ እንደዘገቡት የዚህ ተቋም የሥራ ባልደረቦች ተገን ጠያቂዎች በሃገራቸው የአሸባሪ ድርጅቶች አባላትን ያውቁ እንደሆነ ወይም ደግሞ የጦር መሣሪያ
Rechtsanwalt Pfaff.
Er ist spezialisiert auf alle Rechtsfragen, die Unionsbürger und Ausländer betreffen, unter anderem: 
EU-Migrations- und Ausländerrecht 
Staatsangehörigkeitsrecht 
Asyl- und Flüchtlingsrecht 
Arbeitsgenehmigungsrecht 
Berufszulassungsrecht 
Strafverteidigung mit ausländerrechtlichem Bezug
Rechte geklärt
ፋፍ
ስለሚደበቁባቸው ቦታዎች የሚያውቁት እንዳለ ይጠይቁዋቸዋል ። በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ እነዚህ መረጃዎች ለጀርመን የስለላ መስሪያ ቤት ተላልፈው አሸባሪዎችን በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ለመግደል ሊውሉ ይችላል ። ጀርመን ውስጥ ለተገን ጠያቂዎች ጥብቅና የሚቆሙ በርካታ ጠበቆች እነዚህን ባለሥልጣናት ያውቃሉ ። ቪክቶር ፋፍ ፍራንክፈርት ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ የተገን ጠያቂዎች ጠበቃ በመሆን ሰርተዋል ። ከበርሊኖቹ ባለሥልጣናት ጋርም በግል ተነጋግረዋል ። ፋፍ እንደሚሉት ሠራተኞቹ ትሁትና ግልፅ ናቸው ። ከፌደራል ጀርመን የስለላ መስሪያ ቤት ጋር ግንኙነት እንደሌላቸውም ነው የሚናገሩት ።

«ከፌደራል የስለላ መስሪያ ቤት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ነው የሰማሁት ። ለመራሄ መንግሥት ጽህፈት ቤት ዘገባ እንደሚያቀርቡ ና እዚያ የሚገኙትም ለጽህፈት ቤቱ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው የሚያስቧቸውን አንዳንድ መረጃዎች ለማግኘት መሆኑን ነው በቀጥታ የተነገረኝ ። »
የጀርመን የስለላ መስሪያ ቤትም በመራሄ መንግሥቱት ቢሮ ስር ነው ። ፋፍ እንደሚሉት በ40 ዓመት የአገልግሎት ዘመናቸው ቃለ መጠይቅ በመደረጌ ችግር ገጥሞኛል ያላቸው ተገን ጠያቂ አላጋጠማቸውም ። በተቃራኒው ፋፍ አንዳንዴ የተገን
Asylsuchende vor dem Gebäude der zentralen Aufnahmestelle für Asylbewerber in Berlin.ተገን ጠያቂዎች በበርሊን
ጠያቂዎች ማመልከቻዎች አፋጣኝ መልስ እንዲያገኙ የመስሪያ ቤቱን ባልደረቦች ያነጋግራሉ ። ደንበኞች ለዚህ መሥሪያ ለስለላው መሥሪያ ቤት ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን መስጠት ከቻሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኛሉ ። እንደዚህ ዓይነት ስምምነቶች ላይ የሚደረሰው ግን ሁሌም አይደለም ። መረጃዎችን ሳያሳውቁ መሰብሰብም ሊኖር ይችላል ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ አደገኛ ሊሆንም ይችላል ይላሉ ።
« አደገኛ ሊሆን የሚችለው የውጭ የስለላ ድርጅቶች ተገን ጠያቂዎቹ የሚሰጡትን መረጃ ማወቅ ከፈለጉ ነው ። ይህ ግን ሁሌም የሚሆን አይደለም ። »
ፋፍ እንደሚሉት ይህ የሚደረግ ከሆነ ተገን ጠያቂዎች መጠቀሚያ እንደሆኑ ሊሰማቸው ይችላል ። እነዚህን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መስማታቸውን የሚናገሩት ፋፍ በርሳቸው እምነት ይህን መሰሉ አሰራር አደገኛ ነው ። ምክንያቱም በርሳቸው አስተያየት አሸባሪዎች በክህደት የሚጠረጥሩዋቸውን በዚያው ተገን በጠየቁባቸው ቦታዎች ሊበቀሉዋቸው እና ሊገድሏቸውም ይችላሉ ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

የተቃውሞ ሰልፍ በእሥራኤል

ሳዉድ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያን ላይ የሚፈፀመዉን ጥቃት በመቃወም ሰሞኑን በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያካሂዱ ሰንብተዋል።
Foreign workers wait for a taxi as they leave the Manfuhah neighbourhood of the Saudi capital Riyadh on November 10, 2013, after two people have been killed in clashes between Saudi and other foreign residents the previous day, according to the Saudi police. On November 4, the authorities began rounding up thousands of illegal foreign workers following the expiry of a final amnesty for them to formalise their status. AFP PHOTO/FAYEZ NURELDINE (Photo credit should read FAYEZ NURELDINE/AFP/Getty Images)
ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከመላው እሥራኤል የተሰበሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን መገኘታቸውን ሰልፉን የተከታተለው የኃይፋ ዘጋቢያችን ግርማው አሻግሬ ገልጾልናል። የዛሬውን ሰልፍ አስመልክቶ ያካሄድነውን ቃለ ምልልስ ከታች ያገኙታል።
ግርማው አሻግሬ
ልደት አበበ

የኢትዮ-ኤርትራ ችግር መፍትሄ፣ ድንበር ማስመር ሳይሆን ድንበር ማፍረስ ነው

ኤርትራ ራሷን እያወደመች ነው የኢትዮጵያ ትምህርት ችግሮች ቋንቋና ያለ እቅደ መስፋፋት ናቸው
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ በስዊድን አገር በኡፕስላ ዩኒቨርሲቲ የዘመናዊ ታሪክ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ትምህርት ላይ ከፍተኛ ምርምሮችን ያደረጉ፣ በመስኩም የታወቁ ምሁር ሲሆኑ ከከዓምናው ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ተጋባዥ ፕሮፌሰር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1947 በአስመራ ከተማ ተወልደው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአስመራ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ ተከታትለዋል፡፡ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ በህግ አግኝተዋል፡፡ ከ1972 እስከ 1974 በአስመራ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩት ፕሮፌሰር ተከስተ፤ በለንደን ዩኒቨርሰቲ ከ“ስኩል ኦፍ ኦሪየንታል ኤንድ አፍሪካ ስተዲስ” ማስተርስ ድግሪ ያላቸውን ያገኙ ሲሆን ዶክትሬታቸውን ከስዊድን አገር ኡፕስላ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ሰርተዋል፡፡ የኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ እንዴት ይገልፁታል? እኔ የኤርትራን ጉዳይ መከታተል ካቆምኩ አስራ ሶስት አመት ሊሆነኝ ነው፡፡ ምክንያቱም ልለው የምችለውን ሁሉ ብያለሁ፡፡
“Brothers at war” በሚል ከአንድ የኖርዌይ ተወላጅ ጋር በመሆን በፃፍነው መጽሐፍ፤ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦርትነት የወንድማማችነት ጦርነት ነው፤ ችግሩን ለመፍታት ሁለቱ አገሮች ወንድማማችነታቸውን ማመን አለባቸው ብለን ደምድመናል፡፡ ከዛ በኋላ ምንም ሠላም አልተገኘም፤ በኔ አስተያየት የሚገኝም አይመስለኝም፡፡ እስከአሁን በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ ወንድማማችነቱን ማመን ላይ አልተደረሰም፡፡ የሁለቱ አገራት የወደፊት ግንኙነት ምን የሚሆን ይመስልዎታል? የኤርትራን ጉዳይ ማጥናት የተውኩት ተገድጄ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ነገሮች በጣም በጎ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ ለውጥ እየተካሄደ ነው የሚል አቋም ስላለኝ ሲሆን በሌላ በኩል የኤርትራ ጉዳይ አልቆለታል ብዬ ስላመንኩ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ኤርትራ ራሷን በራሷ እያወደመች ነው፡፡ ኤርትራ ምንም ተስፋ የላትም ብዬ አምናለሁ፡፡
ወደ ጥያቄሽ ስመለስ… የኤርትራና የኢትዮጵያ ሁኔታ እንዴት ይቀጥላል ለሚለው በኔ አስተያየት ከዚህ በኋላ ጦርነት አይካሄድም። ኤርትራ ግን የሶማሊያን አይነት የምትሆንበት፣ በአንድ ልትመራ ወደማትችልበት ደረጃ ልትደርስ ትችላለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ከኢሳያስ አፈወርቂ በኋላ ኤርትራ ሶማሊያን ትሆናለች በሚል የሚሰጡ አስተያየቶችን ይቀበላሉ ማለት ነው? አዎ፡፡ ኢሳያስ እስካለ እሱ የፈጠረው ስርዓት ይቀጥላል፡፡
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋም እና የኢትዮጵያ መንግስት የያዙት አቋምም ለዚህ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ከኢሳያስ በኋላ ግን የኢኮኖሚ ችግር ብቻ ሳይሆን የብሔር ግጭቶች አሉ፡፡ ቆላማው የኤርትራ ክፍል የራሱ አጀንዳ አለው፤ ደገኞቹ ደግሞ እርስበርሳቸው በጣም የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ ይህን መያዝ የሚችለው ኢሳያስ ብቻ ነው፡፡ ከሱ በኋላ አገሪቱን አንድ አድርጐ ወደፊት ሊያራምድ የሚቻል ይመጣል ብዬ አላምንም፡፡ የኤርትራ ጥያቄ ለምርጫ በቀረበበት ወቅት ከነበሩ አማራጮች ዋነኞቹ፤ መገንጠል፣ በፌዴሬሽን መቆየት እና አንድነት የሚሉ ነበሩ፡፡ በውድም ይሁን በግድ ሁሉም አማራጮች ተግባራዊ ሆነዋል፡፡ ኤርትራ ከተገነጠለች 23 አመት ሊሆናት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አንድነት የሚለው አቋም ቅሪት አለ ወይስ ሙሉ በሙሉ ተሸርሽሯል? የደጋው ኤርትራ ባህል በመሠረቱ ኢትዮጵያዊነቱን እንደያዘ ነው፡፡ ኢሳያስ ስልጣን እንደያዘ በሶስተኛ አመቱ ሆላንድ መጥቶ ባደረገው ውይይት፤ እኔም እድሉን አግኝቼ ሰምቼዋለሁ፡፡ እኛ ሠላሳ አመት ሙሉ ታግለን ብዙ ሰው ሞቶብን፣ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ የኤርትራ ህዝብ የከፈልነውን መስዋዕትነት ረስቶ ከኢትዮጵያ ጋር ወዲያ ወዲህ ይላል ብሎ ተናገረ፡፡ ኤርትራ ነፃ ከወጣች ጊዜ ጀምሮ እስከ ጦርነቱ ድረስ የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ተለይተናል የሚል ብዙ ስሜት አልነበረውም፡፡ ደርግ መሸነፉ ላይ ነበር እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር የመለየቱ ብዙ ግንዛቤ አልነበረውም፡፡ ጦርነቱ ሲጀመር ስሜቱ መቀዛቀዙን መናገር ይችላል፡፡
ሌላው በደጋው ኤርትራ ያለው ትግርኛ ተናጋሪ ከጣሊያን ጊዜ የጀመረ የገዢና የተገዢ ግንኙነት ነበረው፡፡ እኛን ጣልያን ነው የገዛን በሚል፣ ትግራይ ያሉትን ትግሪኛ ተናጋሪዎች “እናንተ ከአዲግራት፣ ከመቀሌ፣ ከአድዋ የምትመጡ…” የሚል ነገር ነበር፡፡ ከጦርነቱ በኋላ የትግራይ ህዝብ የራሱን ማንነት ኢኮኖሚ በማሻሻል ላይ ስለሚገኝ በነዚህ ሁለት ትግሪኛ ተናጋሪዎች መካከል ያለው ፉክክር ማን ትግሬን ይወክላል የሚል ነው፡፡ ይህ ለጊዜው ችግር ሊፈጥር ይችላል፤ ግን እኔ እስከምረዳው ድረስ ኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ባህል፣ አስተሳሰብ አለ የምንል ከሆነ በደጋማው ኤርትራ አሁንም አለ። ከዛ ደግሞ ከአፋር ጋር ያለውን ትስስር ማየት ይቻላል፡፡ በኤርትራ ያሉ ቢለኖች አገዎች እንደሆኑ አይጠራጠሩም፤ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ ኩናማዎችንም ካየሽ ተመሳሳይ ነው፡፡ ወቅታዊውን የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ እንዴት ይገልፁታል? በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያን ካየን፣ ለሁለቱም የሚጠቅማቸው የሶማሊያ አንድ መሆን ነው፡፡ አሁን ያለው ሁለት ሶማሊያ በኔ አስተያየት ረጅም የሚጓዝ አይደለም፡፡ ከጥቅም አንፃር ካየነውም፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለሶማሊያ አይጠቅምም፡፡ በኤርትራና በኢትዮጵያ በኩል ስናየው፣ ኤርትራ የምትፈልገው ድንበር ሊኖር አይችልም፡፡ ይህን ደግሞ ሁለቱም አገሮች ያውቁታል፡፡
የኤርትራ ሁኔታ ከኢሳያስ በኋላ አዲስ መልክ ይይዛል፡፡ በአዲሱ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሚና ምን ሊሆን እንደሚችል በሚገባ ማጤን ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጪው ሁለት መቶ ሶስት መቶ አመት ሊያራምድ የሚችል ሆኖ መቀረፅ ይገባዋል፡፡ የኢትዮጵያን የፌደራል አወቃቀር እንዴት ያዩታል? አወቃቀሩ በፌደራል መሆኑ ጥሩ ነው፡፡ በብሔር መሆኑ ግን መጥፎ ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ያደረገው ትልቁ ስህተት ነው፡፡ ፌደራል ስርአት በፊትም የነበረ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የኋላ ታሪክ ካየሽ የፌደራል አወቃቀር አዲስ አይደለም፡፡ ንጉሠ ነገስት ስንል እኮ ንጉሶች አሉ፡፡ ከበላያቸው ንጉሠነገስት አለ ማለት ነው፡፡ አካባቢያዊ ፌደራሊዝም ነበር፡፡ የኤርትራ ህዝብ አሁን ያሉበትን የነፃነት ሁኔታ ከቀድሞው ጋር ሲያስተያዩት ምን ትርጉም ይሰጥዎታል? እኔ እኮ በመጀመሪያም ኤርትራውያኖች ከማን ነው የሚገነጠሉት የሚል አቋም ነው ያለኝ። ማነው ከማን የሚገነጠለው? የደቡብ ወይም የኦሮሞ ህዝቦች እንገነጠላለን ቢሉ ኖሮ ምክንያት ነበራቸው፡፡ የኤርትራ የነፃነት ጥያቄ በተነሳበት ወቅት ኤርትራውያኑና ከላይ የጠቀስኳቸው ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ያገኙትን እድል (Comparative advantage) ስናይ፣ ኤርትራውያኑ በጣም ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ (በጣሊያን፣ በእንግሊዝ፣ በፌዴሬሽኑ ዘመን) በ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ሀብታሞቹ እነሱ ነበሩ። በትምህርት መስክ ሃያ አምስት በመቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች ኤርትራውያን ነበሩ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችንም ካየሽ 25 በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነበሩ፡፡ ከተማረው ሰላሳ አምስት በመቶው ክፍል ኤርትራውያን ነበሩ፡፡
ይህን እድል ያገኙ ሰዎች ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን ሲሉ ምክንያቱን ለማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ምንም ምክንያት አልነበራቸው፡፡ ለነፃነት የተደረገው እንቅስቃሴ 30 አመት ቢፈጅም ስልሳ ሺህ ሰው ቢሞትም በቂ ምክንያት አልነበረውም። የኔ ጥናት የጣልያን ቅኝ አገዛዝ በኤርትራ የሚል ነው። እንዲገባኝ ሞክሬያለሁ፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል እንዳለበት የሚያሳይ ምንም ነጥብ አላገኘሁም፡፡ ነፃ ወጣን አሉ፡፡ ሁለት አመት ሳይቆዩ እኛ የታገልነው ለነፃነት ብቻ አይደለም፤ የኛ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር ነው ማለት ጀመሩ፡፡ ይህን የሚሉት ተገደው ነው፤ ምክንያቱም የኤርትራ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ በራሱ ሊቆም የሚችል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ልዩ አገር ነች፤ ነፃነቷን ጠብቃ የቆየች አገር ናት፡፡ የኤርትራ ቴሌቪዥን በቅርቡ “Ancient Eritreans” (የጥንት ኤርትራውያን) የሚል ዶክመንተሪ አቅርቦ ነበር፡፡ አይተውታል? (ረጅም ሳቅ) አላየሁትም፡፡ ግን ምንም አዲስ ነገር አይፈጥርም፡፡ ወጣቶቹ ኢትዮጵያን አያውቋትም፤ ነገር ግን መንግስት የሚያደርገው አንድ ነገር ነው፣ ህዝቡ የሚያስበው ሌላ ነገር ነው፡፡
መንግስት በቴሌቪዥን የሚየሳየውና ህዝቡ የሚመኘውና የሚያስበው ሌላ ነው፡፡ እስከቅርብ ጊዜ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ብትለያይም በድብቅ ወጣቶቻቸውን ለትምህርት ወደ ቤጌምድር (ጐንደር) ይልኩ ነበር፡፡ የኢሳያስን መረጃ በማየት ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም፡፡ ኤርትራዊውን ማን አገኘው፡፡ የተለየን ነን የሚል አቋም የት ነው ያለው? በኤርትራ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ምን ያህል አለ ለሚለው መልስ ለማግኘት ድንበሩ መፍረስ አለበት፡፡ ለሁለቱ ህዝቦች መፍትሔ የሚሆነው በኤርትራ በኩል እየተጠየቀ ያለው ድንበር ሲሰመር ሳይሆን ከደርግ ሽንፈት በኋላ የተሰመረው መስመር ሲፈርስ ነው፡፡ ትናንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋ፣ እውቀት እና የጋራ ህልውና በሚል የውይይት መነሻ ጥናት አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ትምህርት ላይ ጥናቶችን አድርገዋል፡፡ ዕይታዋ ምንድን ነው? ዋና ጥናቴ እሱ ነው፡፡ ትምህርት በጣም ተዳክሟል፡፡ የተዳከመው በሁለት ምክንያት ነው ብዬ አስቀምጣለሁ፡፡ አንዱ ያለዕቅድ መስፋፋቱ ነው። የሚፈለጉ ህንፃዎች፣ አስተማሪዎች፣ መፃሕፍቶች ሳይሟሉ እንዲሁ ሠፍቷል፡፡ ሌላው ዋነኛ ምክንያት የቋንቋ ጉዳይ ነው፡፡ እንግሊዝኛ ቋንቋ አያዋጣንም፡፡ በራስ ቋንቋ መማር የህልውናና የመበት ጥያቄ ነው፡፡ ዜግነትዎ ከየትኛው ነው? ስዊድናዊ ነኝ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!

November 22, 2013
ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ይህንን ጥሪ እንደሚቃወሙት እና በፕሮግራሙም ላይ ጥቁር ሪቫን ያሰረ ተሳታፊን እንደተሳታፊ እንደማይቆጥሩ መናገራቸው ፓርቲያችንን እጅግ አሳዝኖታል፡፡ ፓርቲያችን ይህንን ጥሪ ሲያስተላልፍ አላማው ፍጹም ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለው ሲሆን ጥያቄውም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ግድያ እንዲቆም እና ፍትሃዊ እርምጃም እንዲወሰድ ለመጠየቅ ብቻ እና ብቻ እንጂ ሌላ አላማ እንደሌለው እየታወቀ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ግን ጉዳዩ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው የሚያስተዛዝብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡

ስፖርት ሰላማዊ ነገር የሚሰበክበት እንዲሁም እኩይ ተግባራት የሚወገዙበት መድረክ ነው፡፡ በአለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ አሰቃቂ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ ሲወገዙ እንዲሁም ለሰለባዎች ሃዘን የመግለጽ ስነ ስርዓትና የህሊና ጸሎት ሲደረግ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ እናት ልጆችዋ ፊት እንዲሁም ሴት ልጅ ቤተሰቦችዋ ፊት ስትደፈር ከማየት የዘለለ ምን እኩይ ተግባርስ ሊኖር ነው? ታዲያ ስፖርት ይህንን ካላወገዘ ምንን ሊያወግዝ ነው?
በመጨረሻም የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች የፓርቲውን ጥሪ መቃወማቸው ፓርቲያችንን ያሳዘነ እና ያስቆጣ መሆኑን እየገለጽን አሁንም ፓርቲያችን በድጋሜ በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ እየጠየቀ ጥቁር ሪቫኖችን ማግኘት ለማትችሉ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተገኝታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ክብር ለዜጎቻችን ይሁን!!

Thursday, November 21, 2013

የስዊድን የጦር ፍርድ-ቤት አቃቢ-ህግ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ፡

ህዳር ፲፩(አስ አንድ )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የጦር ፍርድ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቅርቡ በኦጋዴን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበርና የፕሬዚዳንቱ የግል ዌብሳት ማኔጀር እና አማካሪ የነበረው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በኦጋዴን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።
የጦር ፍርድ ቤቱ ዋና አቃቢ ህግ ክሪስተር ፒተርሰን በ10 የኦጋዴን ክልል ባለስልጣናትና የመከላከያ አዛዦች ላይ የቅድመ መርምራ እንዲካሄድ የወሰኑ ሲሆን ከተመርማሪዎች መካከል የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመርና ምክትሉ አብዱላሂ ዌረር እንደሚገኙበት ወጣት አብዱላሂ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ገልጿል።
ውሳኔው ለኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ድል ነው ያለው አብዱላሂ፣ ምርመራ መጀመሩንም ገልጿል።
ምርመራው እንደተጠናቀቀ ሁለት አማራጮች ሊኖሩ እንደሚችል ተናግሯል። አንደኛው አማራጭ ጉዳዩን በስዊድን የጦር ፍርድ ቤት ማየት ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ወደ አለማቀፉ የወንጀል ፍርድቤት መላክ ነው።
በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃዎችን በመላክ እንዲሁም የምስክርነት ቃላቸውን በመስጠት እንዲተባበሩ ወጣት አብዲ ገልጿል።
በሌላ በኩል በተለያዩ የአለም ክፍሎች  የሚገኙና በኢትዮጵያ መንግስት በደል  የደረሰባቸው ሰዎች መረጃዎቻቸውን እንዲሁም የምስክርነት ቃል ለመስጠት የሚፈልጉ የስልክ ቁጥራቸውን በ0031 68 71 54 530 ወይም በ editor@ethsat.com ቢልኩ  ኢሳት ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉ ወገኖች ጋር የሚያገናኛቸው መሆኑን ለመግልጽ ይወዳል።

በሚኒስትር ማእረግ የሚለው ሹመት ውዝግብ እያስነሳ ነው

ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድቤት ይታይ የሚለውን ጉዳይ ፥ የህገመንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ለሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤ መምራቱ አንዳንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንትን እንዳላስደሰተ ታውቋል።
ሰኞ ህዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም በነበረው የችሎት ውሎ አቶ መላኩ ፈንታበሚኒስትር ማዕረግ ተሸመው ሲያገለግሉ እንደነበሩና በወቅቱም የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል መሆናቸውን በመግለፅ በፍርድቤቶች መቋቋሚያ አዋጅ 25/88 መሰረት እኔ በሚኒስትር ማእረግ የተሾምኩ ስለሆነ ፥ ጉዳዩ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳይሆን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው ሊታይ የሚገባው በማለት መከራከሪያ ማቅረባቸው ይታወሳል።
የኮሚሽኑ አቃቤ ህግም በሚኒስትር ማዕረግ መባላቸው ጥቅማ ጥቅማጥቅሞችን በሚኒስትር ደረጃ እንዲከበርላቸው ተብሎ ነው የሚለውን መከራከሪያና ሌሎችንም በመዘርዘር ተቃውሞ አቅርቦ ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይሆን በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊታይ ይገባዋል ሲል ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ችሎቱ በትላንትነው እለት ጉዳዩ በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ሊያገኝ የሚገባው ነው በማለት ወደዚያው ጉዳዩን በመምራት ለታህሳሱ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በሚኒስትር ማዕረግ በሚል በአማካሪ ስም ጭምር ለሚቀመጡ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ሹመት መስጠት የጀመሩት አቶ መለስ ዜናዊ ሲሆኑ በአቶ ኃይለማርያምም የስልጣን ጊዜ ይህንን ሹመት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግም ጭምር በመስጠት በተለይ በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ በርካታ ሹማምንት እንዲከማቹ ተደርጓል፡፡ ሹመቱ በሚኒስትር ማዕረግ ሲሰጥ አንድ ሚኒስትር የሚያገኘውን ጥቅማጥቅም ከማግኘት ባሻገር በሚኒስትሮች ም/ቤት በአባልነት እንደሚሳተፉ ይታወቃል፡፡ የፌዴራል የስነምግብርና የጸረ ሙስና ዐቃቤ ሕግ ይህ በማዕረግ የተባለው ሹመት የተሠጠው ለጥቅማጥቅም ብቻ ነው ብሎ ክርክር በፍ/ቤት ማቅረቡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ለሕገመንግስት አጣሪ ጉባዔ መምራቱ አንዳንድ ከፍተኛ ሹማምንትን እንደላስደሰተ ታውቋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ ትልልቅ ሹማምንት በሚኒስትር ማዕረግ እየተሾሙ ከቀድሞ ሃላፊነታቸው እየተነሱ መሆኑን ያስታወሰው ምንጫችን እነዚህ ጎምቱዎች አንዱ ማባበያ የነበረው የቀድሞ ማዕረጋችሁ ትቀጥላላችሁ መባላቸው እንደነበር ያስታውሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህን ማዕረግ ዝቅ የሚያደርግ ክርክር መነሳቱ በቀጣይ የማዕረጉ አስፈላጊነት ጥያቄ ጭምር የሚያስነሳ መሆኑን ጠቅሶ በክርክሩ ጥቅት የማይባሉ ከፍተኛ ካድሬዎች መበሳጨታቸውን አመልክቶአል፡፡

በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን የመብት ጥሰት ለመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች እንደቀጠሉ ነው

ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሰኞ ኖቬምበር 25፤ 2013 ከ ጠዋቱ 8:30 ጀምሮ ሚድራንድ በሚገኘው ፓን አፍሪካ ፓርላማ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያዘጋጁ ለኢሳት ተናግረዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ተማጽነዋል።

ከሳውድ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር በተመለከተ የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት መግለጫ ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል

ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘግይቶም ቢሆን ችግረኛ ኢትዮጵያውያንን ከሳውድ አረቢያ ማስወጣት የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት፣ እስካሁን ድረስ የተመላሾችን አሀዝ በተመለከተ የሚሰጠው መግለጫ ግን ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ መጣሉን የኢትዮጵያው ዘጋቢያችን ገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በቲውተር ወደ አገር ቤት የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 10 ሺ 707 ነው በማለት ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ የእርሳቸው ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የተመላሹን ቁጥር በ6 ሺ በማሳነስ  4 ሺ 961 ሰዎች መግባታቸውን ለጀርመን ራዲዮ ተናግረዋል።  ሁለቱም ባለስልጣናት  መግለጫዎችን የሰጡት በአንድ ቀን ውስጥ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ይህን ያክል ቁጥር ያለው ልዩነት እንዴት ተፈጠረ ሲሉ ጠይቀዋል።

በአቶ መለስ ትእዛዝ በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ንብረት ተወርሶ ኢምባሲና የአምባሰደሩ መኖሪያ ቤት እንደተሰራበት ታወቀ

ህዳር ፲፪(አስ ሁለት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ኢሳት በደረሰው አስተማማኝ መረጃ መሰረት   በሳውድ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት ቤት መገንቢያ እና ለችግር ግዜ ይሆነናል በማለት ከግል ኪሳቸው እያወጡ በደረግ ዘመን ሲያጠራቅሙት የነበረውን ገንዘብ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሰጡት ትእዛዝ ገንዘቡ ተወርሶ በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲና የአምባሳደሩ መኖሪያ እንዲሁም ጅዳ የሚገኘው የቆንስላ ጽህፈት ቤት እንዲሰራበት ተድርጓል።
ኮሚኒቲው በወቅቱ 50 ሚሊዮን ሪያል ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ከ13.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ነበረው። የኮሚኒቲው መሪዎች ገንዘቡ እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑና ምናልባትም የሳውዲ መንግስት አይን ሊያርፍበት ይችላል በሚል ምክንያት በኢትዮጵያ ኢምባሲ አካውንት እንዲቀመጥላቸው እና ገንዘቡን ሲፈልጉ ከአምባሳደሩ ጋር በጋራ በመሆን እንዲያንቀሳቀሱ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ስምምነት በማድረጋቸው፣ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኢምባሲ አካውንት እንዲቀመጥ ተደርጓል። ገንዘቡም በኮሚኒቲው ሊቀመንበር እና ተቀማጭነቱ ጅዳ  በነበረው ቆንሲላ ጄኔራሉ ፊርማ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ ገንዘቡን ለመጠቀም በመፈለጉ የኮሚኒቲ መሪዎችን በጥቅማጥቅም ለመደለል ዘመቻ ጀመረ። ለኮሚኒቲ መሪዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ መሬት እንደሚሰጣቸውና ቤቶችን ሰርተው እንደሚኖሩ ፣ መንግስት መሪዎቹ ለሚያቀርቡት ጥያቄ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተነግሮአቸዋል። ይሁን እንጅ የስደተኞች ተወካዮች ገንዘቡ የህዝብ በመሆኑና ትምህርት ቤት ለመስሪያ እንዲሁም ለችግር ጊዜ የሚቀመጥ በመሆኑ፣ ገንዘቡን መንግስት እንዲጠቀምበት አንፈቅድም የሚል መልስ ሰጡ።
በጉዳዩ ላይ እጃቸውን ያስገቡት አቶ መለስ ለአንዳንድ የኮሚኒቲው መሪዎች ” መሬት እንኳ ባይኖር መስቀል አደባባይን ሸንሽኜ አከፋፍላችሁዋለሁ” በማለት ቃል እስከመግባት ደርሰው ነበር። የኮሚኒቲ መሪዎች የአቶ መለስን ማባበያ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲታወቅ አቶ መለስ ገንዘቡ ለግንባታዎች እንዲውል ቀጥተኛ ትእዛዝ ሰጡ።
በዚህ የተበሳጩት የወቅቱ የኮሚኒቲው መሪ አቶ እርቁ ገዳ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ቢፈልጉም፣ ኢምባሲው ግትር ናቸው የተባሉት ሊቀመንበሩ በሌላ የኢህአዴግ ደጋፊ እንዲተኩ በማስደረግ ክሱ እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል።
አንዳንድ የኮሚኒቲው መሪዎችም ምንም ማድረግ አለመቻላቸውን ሲያዩ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ቃል የተገባላቸው ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ይሁን እንጅ የጠየቁትን ቦታ ካለማግኘታቸውም በላይ አንዳንዶች መንግስት በጠየቃችሁ ጊዜ ግትር አቋም አሳይታችሁዋል በሚል የተለያዩ ችግሮች እንዲደርስባቸው ሆኗል።
አንዳንድ ሰዎች ገንዘቡን የኢትዮጵያ መንግስት ባይጠቀምበት ኖሮ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙና ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ሰዎችን ለመርዳት ሊውል ይችል እንደነበር አስተያየት ሰጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን አስተያየት ለማግኘት በመስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም፣ ስብሰባ ላይ ነኝ የሚል መልስ በመስጠታቸው ሊሳካልን አልቻለም።
ጉዳዩን በቅርቡ ከሚያውቁ ሰዎች ጠይቀን እንደተረዳነው በወቅቱ መንግስት የሳውዲ አረቢያን የኢትዮጵያ ኪሚኒቲ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም የገልፍ አገሮች የኮሚኒቲ ገንዘቦችን በመውሰድ ለግንባታው አውሎአል።
የሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ካቋቋሙዋቸው ኮሚኒቲዎች ሁሉ ጠንካራው ነው። ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ በመላክ ቅድሚያ ሲናራቸው በአደጋ ጊዜ በተለይም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁትን ሰዎች ያነጋገርን ሲሆን፣ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

November 21, 2013
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡

እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

እ.ኤ.አ 2011 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ (Human Rights Watch) ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ “ህገወጥ ስብሰባ በሚል ሰበብ 35 የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያወያንን/ትን“ “በአንድ ኢትዮጵያዊ የክርስትና እምነት ተከታይ የግል መኖሪያ ቤት በእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ጸሎት በማድረግ ላይ እንዳሉ” በፖሊስ ቀጥጥር ስር ውለዋል” ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በሚፈልጉ እና ሌሎች ስደተኛ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኖች ላይ በሚደረገው ሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ምንጊዜም የማያቋርጥ ትችት እየተደረገ መሆኑን መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በዕየለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎችና ተራ የሳውዲ ዜጎች በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ያድናሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩ የሚያሳየው የቪዲዮ ቅርፅ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሳውዲዎች ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ የማባረር ሁከት፣ ጥቃት የመሰንዘርና የመግደል ድርጊት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያሳየው የፎቶግራፍ ምስል አስደንጋጭና ከሰለጠነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ በእጅጉ የዘለለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር 200 ሺ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን/ት ለማገዝ ምን እያደረገ ነው? ምንም!!! እራሱ አምኖ በተቀበለው መሰረት ገዥው አስተዳደር ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደሚኖሩ እንኩዋን አያውቅም፣ ሆኖም ግን ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሳውዲ አረቢያ ሙሉ በሙሉ በተቻለ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለለሁ የሚል ቃል ገብቷል፡፡

የወባ ተመራማሪው “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር”፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ መንግስት በግዛቱ በሚገኙት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ የኃይል እርምጃ “መንግስቱ አውግዘዋል፡፡ ይኸ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህን ጉዳዩ የሳውዲ መንግስት እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ በክብር መያዝ የነበረባቸውን ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ደስተኞች ነን፡፡ ተቀባይነት የለውም” የሚለውን አባባል ገዥው አስተዳደር እንደ አስፈሪ የጭካኔ ድርጊቶች፣ ያለመሰልጠንነትና ዘግናኝ ጨካኝነትና ወንጀለኛነት የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀምበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ አልጄዚራ እንደዘገበው ከሆነ በተፈጸመው ድርጊት ተበሳጭተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን/ት አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሄዱበት ጊዜ የገዥው አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር በማዋል  ድብደባ ፍጽሞባቸዋል፡፡ “ፖሊሶች ከመጡ በኋላ ደብድበውናል፣ እና በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ” በማለት የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ነባር አባል ጌትነት ባልቻ ገልጿል፡፡ ጌትነት በመቀጠልም “የፓርቲው ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል” በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡

ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን/ት በሀዳር ወር መጎዳትና መጎሳቀል ለምን ይደንቀን? እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 ያለው የገዢ አስተዳደር ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የጭካኔ ድርጊት በአትዮጵያኖች ላይ ፈፅሞአል:: በዚያው ዓመት የፓርላማውን ምርጫ ተከትሎ በግንቦት ወር በጠራራ ፀሐይ የተዘረፈውን የህዝብ ድምጽ በመቀወም ድምጻቸውን ባሰሙ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች እራሱ መለስ ዜናዊ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን 193 ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአዲስ አበባ መንገዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጻቸውና እና ሌሎች በከፍተኛ ደህንነት በእስር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ሆን ተብሎ በጥይት ደብድበዋል፣ ሌሎች 763 የሚሆኑት በጽኑ ቆስለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በየጊዜው በህዳር ወር እ.ኤ.አ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋና ያልታጠቁ ሰልፈኞች ተኩስ በመክፈት ገደሏቸው፣ አካለ ጎደሎ አደረጓቸው፡፡ እኔም ያንን ጊዜ ለማስታወሰ ስል መጻፌን ቀጥየ ነበር፡፡

በመጀመሪያው የማሰታወስ ጽሁፌ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 እና በጁን 2005 የተከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም ይታወሳል! ለአንባቢ ዎቼም ሳስታዉስ በህይወት ላሉትና ለሞቱት ምስክርነት መስጠት እንዳለባችሁ የሞራል ግዴታ ተጥሎባችኋል ብዬ ነበር፡፡ ኤሊ ዌይሰል የዕልቂቱ ተራፊና የኖቬል ተሸላሚ በክብር እንዳስቀመጠው “ማስታዋስ አለብን ምክንያቱም የጋራ ትውስታችን የሆኑትን ያለፉ ድርጊቶች የወደፊቱን ትውልድ መብት መከልከል ስለማንችል ነው መርሳት መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን ስድብም ነው፡፡ የሞቱትን መርሳት ሁለተኛ ከመግደል እኩል ነው፡፡”

በ2005 ያለቁትን መርሳት ማለት በእነርሱ ላይ የተፈጸሙትን ግፎች መርሳት እንዲህም ያሉትን አረመኔአዊ ወንጀል መርሳትማለት ነው፡፡ እልቂቱን መርሳት ማለት ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የልብ ልብ መስጠት ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሳት ማለት በስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች እንደገና እና እንደገና የወንጀል ደረጃውን ከፍ በማድረግና ተጠያቂነት የሌለበትን ሁኔታ በመፍጠር ወንጀል እንዲሰሩ ማበረታታት ማለት ነው፡፡

አስታውሳለሁ! በምንም አይነት አልረሳምም፣ በፍጹም!!!

አስታውሳለሁ ምክንያቱም እኔ ካላስታወስኩ ማን ያስታዉሳል? አስታውሳለሁ ምክንያቱም የምረሳ ከሆነ ወንጀሎችና ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ የምረሳ ከሆነ ታሪክ እንዴት ሊያስታውስ ይችላል? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው ሌላ ሊያስታውስ የሚችል ሰው ሲኖር ነው:: በህዳር፣ በታህሳስ፣ በጥር፣ በየካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ… ዛሬ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ነገ ለሚወለዱ ህጻናት አስታውሳለሁ፡፡

የእኔን ስራ በማድነቅና ለበርካታ ዓመታት ሲደግፉ ሲቆዩ ሌሎች ደግሞ ሲተቹ ሲቃወሙ የሚኖሩ አሉ። እኔ በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ ነው ይሉኛል:: በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ መሆን ለኔ ታላቅ ክበር ነው::

የ2005 ዕልቂትን አስታውሳሁ፡፡ እያንዳንዱን በግፍ የተገደሉትን አስታዉሳለሁ፡፡ አስታውሳለሁ ወጣት ሴቶች ወደፊት እናት ላይሆኑ፣ ወጣት ወንዶችን የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም  ወደፊት አባት ላይሆኑ፣ ወላጅ የሌላቸውን ወላጆቻቸው የተገደሉባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን እናቶችንና አባቶችን አስታውሳለሁ::

ወንጀለኞችን አልረሳም፣ ተንኮል የሰሩትን 237ቱን የፖሊስ አባላት አስታውሳለሁ፣ የወንጀለኞችን ቁንጮና መሪ የነበረዉን አራዊትን  አልረሳም:: የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም::

አስታውሳሁ፣ መቼ ረሳለሁ: ሁልጊዜ  ህዳርን፣ ታህሳስን፣ ጥርን፣ የካቲትን፣ መጋቢትን፣ ሚያዝያን…. አልረሳም፡፡

ተ.ቁ

ስም

ጾታ

እድሜ

ስራ



መግለጫ

1

ሬቡማ ኢርጋታ


34

ግንበኛ

2

መለሳቸው አለምነው


16

ተማሪ

3

ሀድራ ኦስማን


22

አይታወቅም

4

ጃፋር ኢብራሂመ


28

ቢዝነስ

5

መኮንን


17

አይታወቅም

6

ወልደሰማያት


17

7

ባህሩ ደምለው


አይታወቅም

8

ፈቀደ ነጋሽ


25

መካኒክ

9

አብርሀምይልማ


17

ታከሲ ነጂ

10

ያሬድ እሸቴ


23

ቢዝነስ

11

ከበደ ገ/ህይወት


17

ተማሪ

12

ማቴዎስ ፍልፍሉ


14

ተማሪ

13

ጌትንት ወዳጆ


48

ቢዝነስ

14

ቃሰም ራሽድ


21

መካኒክ

15

ሸውሞሊ


22

ቢዝነስ

16

አሊየ ኢሳ


20

የቀን ስራ

17

ሣምሶን ያዕቆብ


23

የህዝብ ማመላ

18

አለባለው አበበ


18

ተማሪ

19

በልዩ ዛ


18

ትራንስ. ረዳት

20

ዩሱፍ ጀማል


23

ተማሪ

21

አብርሃም አገኘሁ


23

ትራንስ.ረዳት

22

መሀመድ በቃ


45

አርሶ አደር

23

ረዴላ አወል


19

የታክሲ ረዳት

24

ሀብታሙ ኡርጋ


30

ቢዝነስ

25

ዳዊት ፀጋዬ


19

መካኒክ

26

ገዛኸኝ ገረመው


15

ተማሪ

27

ዮናስ አበራ


24

አይታወቅም

28

ግርማ ወልዴ


38

ሾፌር

29

ደስታ ብሩ


37

ቢዝነስ

30

ለገሰ ፈይሳ


60

ቢዝነስ

31

ተስፋዬ ቡሽራ


19

ጫማ ጠጋኝ

32

ቢንያም ደገፋ


18

ስራ አጥ

33

ሚሊዮን ሮቢ


32

ትራንስ.ረዳት

34

ደረጀ ደኔ


24

ተማሪ

35

ነብዩ ሃይሌ


16

ተማሪ

36

ምትኩ ምዋለንዳ


24

ዶመስቲክ ሰራተኛ

37

አንዋር ሱሩር


22

ቢዝነስ

38

ንጉሴ ዋብግነ


36

ዶመስቲክ ሰራተኛ

39

ዙልፋ ሀሰን


50

የቤት እመቤት

40

ዋስይሁን ከበደ


16

ተማሪ

41

ኤርሚያስ ከበደ


20

ተማሪ

42

00428


25

አይታወቅም

43

00429
26

አይታወቅም

44

00430
30

አይታወቅም

45

አዲሱ በላቸው


25

አይታወቅም

46

ደመቀ አበበ


አይታወቅም

47

00432
22

አይታወቅም

48

00450
20

አይታወቅም

49

13903
25

አይታወቅም

50

00435
30

አይታወቅም

51

13906
25

አይታወቅም

52

ተማም ሙክታር


25

53

በየነ በዛ


25

አይታወቅም

54

ወሰን አሰፋ


25

አይታወቅም

55

አበበ አንተነህ


30

አይታወቅም

56

ፈቃዱ ኃይሌ


25

አይታወቅም

57

ኤሊያስ ጎልቴ


አይታወቅም

58

ብርሃኑ ዋርካ


59

አሸብር መኩሪያ


አይታወቅም

60

ዳዊት ሰማ


አይታወቅም

61

መርሀጽድቅ ሲራክ


አይታወቅም

62

በለጠ ጋሻውጠና


አይታወቅም

63

ብኃይሉ ተስፋዬ


20

አይታወቅም

64

21760
18

አይታወቅም

65

21523
25

አይታወቅም

66

11657
24

አይታወቅም

67

21520
21

አይታወቅም

68

21781
60

አይታወቅም

69

ጌታቸው አዘዘ


45

አይታወቅም

70

21762
75

አይታወቅም

71

11662
45

አይታወቅም

72

21763
25

አይታወቅም

73

13087
30

አይታወቅም

74

21571
25

አይታወቅም

75

21761
21

አይታወቅም

76

21569
25

አይታወቅም

77

13088
30

አይታወቅም

78

እንዳልካቸው ገብርኤል


27

አይታወቅም

79

ኃይለማርያም አምባዬ


20

አይታወቅም

80

መብራቱ ዘውዱ


27

አይታወቅም

81

ስንታየሁ በየነ


14

አይታወቅም

82

ታምሩ ኃይለሚካኤል


አይታወቅም

83

አድማሱ አበበ


45

አይታወቅም

84

እቴነሽ ይማም


50

አይታወቅም

85

ወርቄ አበበ


19

አይታወቅም

86

ፈቃዱ ደግፌ


27

አይታወቅም

87

ሸምሱ ካሊድ


25

አይታወቅም

88

አብዱዋሂደ አህመዲን


30

አይታወቅም

89

ታከለ ደበሌ


20

አይታወቅም

90

ታደሰ ፌይሳ


38

አይታወቅም

91

ሶሎሞን ተስፋዬ


25

አይታወቅም

92

ቅጣው ወርቁ


25

አይታወቅም

93

ደስታ ነጋሽ


30

አይታወቅም

94

ይለፍ ነጋ


15

አይታወቅም

95

ዮሀንስ ኃይሌ


20

አይታወቅም

96

በኃይሉ ብርሀኑ


30

አይታወቅም

97

ሙሉ ሶሬሳ


50

አይታወቅም

98

የቤት እመቤት
አይታወቅም

99

ቴዎድሮስ


23

አይታወቅም

100

ጫማ ሰሪ


ጫማ ሰሪ

101

በኃይሉ ብርሃኔ


30

አይታወቅም

102

ሙሉ ሶሬሳ


50

የቤት እመቤት

103

ቴዎድሮስ ኃይሌ


23

ጫማ ሻጭ

104

ደጄኔ ይልማ


18

መጋዝን ጠባቂ

105

ኡጋሁን ወልደገብርኤል


18

ተማሪ

106

ደረጀ ማሞ


27

አናጺ

107

ረጋሳ ፈይሳ


55

ላውንድሪ ሰራተኛ

108

ቴዎድሮስ ገብረዎልድ


28

የግል ንግድ

109

መኮንን ገ/እግዚአብሄር


20

መካኒክ

110

ኤሊያስ ገ/ጊዮርጊስ


23

ተማሪ

110

አብርሀም መኮንን


21

የቀን ሰራተኛ

111

ጥሩወርቅ ገ/ጻድቅ


41

የቤት እመቤት

112

ሄኖክ መኮንን


28

አይታወቅም

113

ጌቱ ምሀትተ


24

አይታወቅም

114

ክብነሽ ታደሰ


52

አይታወቅም

115

መሳይ ስጦታው


29

የግል ንግድ

116

ሙሉአለም ወይሳ


15

አይታወቅም

117

አያልሰው ማሞ


23

አይታወቅም

118

ስንታየሁ መለሰ


24

የቀን ሰራተኛ

119

ጸዳለ ቢራ


50

የቤት እመቤት

120

አባይነህ ሰራሴድ


35

ልብስ ሰፊ

121

ፍቅረማርያም ተሊላ


18

ሾፌር

122

አለማየሁ ገርባ


26

አይታወቅም

124

ጆርጅ አበበ


36

የግል ትራንስፖርት

125

ሀብታሙ ዘገየ


16

ተማሪ

126

ምትኩ ገ/ስላሴ


24

ተማሪ

127

ትዕዛዙ መኩሪያ


24

የግል ንግድ

128

ፈቃዱ ዳልጌ


36

ልብስ ሰፊ

129

ሸዋጋ ወ/ጊዮርጊስ


38

የቀን ሰራተኛ

130

አለማየሁ ዘውዴ


32

የቴክስታይል ሰራተኛ

131

ዘላለም ገ/ጻድቅ


31

የታክሲ ሾፌር

132

መቆያ ታደሰ


19

ተማሪ

133

ሀይልየ ሁሴን


19

ተማሪ

134

ፍስሀ ገ/ጻድቅ


23

የፖሊስ ተቀጣሪ

135

ወጋየሁ አርጋው


26

ስራ ፈላጊ

136

መላኩ ከበደ


19

አይታወቅም

137

አባይነህ ኦራ


25

ልብስ ሰፊ

138

አበበች ሆለቱ


50

የቤት እመቤት

139

ደመቀ ጀንበሬ


30

አርሶ አደር

140

ክንዴ ወረሱ


22

ስራ ፈላጊ 141

141

እንዳለ ገ/መድህን


23

የግል ንግድ

142

አለማየሁ ወልዴ


24

መምህር

143

ብስራት ደምሴ


24

መኪና አስመጭ

144

መስፍን ጊዮርጊስ


23

የግል ንግድ

145

ወሎ ዳሪ


18

የግል ንግድ

146

በሀይሉ ገ/መድህን


20

የግል ንግድ

147

ሲራጂ ኑሩ ሰይድ


18

ተማሪ

148

እዮብ ገ/መድህን


25

ተማሪ

149

ዳንኤል ሙሉጌታ


25

የቀን ሰራተኛ

150

ቴዎድሮስ ደገፋ


25

የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ

151

ጋሻው ሙሉጌታ


24

ተማሪ

152

ከበደ ኦርቄ


22

ተማሪ

153

ለሊሳ ፋጤሳ


21

ተማሪ

154

ጃገማ ባሻ


20

ተማሪ

155

ደበላ ጉታ


15

ተማሪ

156

መላኩ ፈይሳ


16

ተማሪ

157

እልፍነሽ ተክሌ


45

አይታወቅም

158

ሀሰን ዱላ


64

አይታወቅም

159

ሁሴን ሀሰን ዱላ


25

አይታወቅም

160

ደጀኔ ደምሴ


15

አይታወቅም

161

ዘመድኩን አግደው


18

አይታወቅም

162

ጌታቸው ተረፈ


16

አይታወቅም

163

ደለለኝ አለሙ


20

አይታወቅም

164

ዩሱፍ ኡመር


20

አይታወቅም

165

መኩሪያ ተበጀ


22

አይታወቅም

166

ባድሜ ተሻማሁ


20

አይታወቅም

167

አምባው ጌታሁን


38

አይታወቅም

168

ተሾመ ኪዳኔ


65

የጤና ባለሙያ

169

ዮሴፍ ረጋሳ


አይታወቅም

170

አብዩ ንጉሴ


አይታወቅም

171

ታደለ በሀጋ


አይታወቅም

172

ኤፍሬም ሻፊ


አይታወቅም

173

አበበ ሀማ


አይታወቅም

174

ገብሬ ሞላ


አይታወቅም

175

ሰይዴ ኑረዲን


አይታወቅም

176

እንየው ጸጋዬ


32

እረዳት ትራንስፖርት

177

አብዱራህማን ፈረጅ


32

የእንጨት ስራ ባለሙያ

178

አምባው ብጡል


60

የቆዳ ፋብሪካ ሰራተኛ

179

አብዱልመናን ሁሴን


28

የግል ንግድ

180

ጅግሳ ሰጠኝ


18

ተማሪ

181

አሰፋ ነጋሳ


33

አናጺ

182

ከተማ ኡንኮ


23

ልብስ ሰፊ

183

ክብረት እልፍነህ


48

የጥበቃ ሰራተኛ

184

እዮብ ዘመድኩን


24

የግል ንግድ

185

ተስፋዬ መንገሻ


15

የግል ንግድ

186

ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ


58

የግል ንግድ

187

ትንሳኤ ዘገየ


14

ልብስ ሰፊ

188

ኪዳና ሹክሩ


25

የቀን ሰራተኛ

189

አንዷለም ሺበለው


16

ተማሪ

190

አዲሱ ተስፋሁን


19

የግል ንግድ

191

ካሳ በየነ


28

ልብስ ሽያጭ

192

ይታገሱ ሲሳይ


22

አይታወቅም



የጸጥታ ኃይሎች እርስ በእርስ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በጥይት የተገደሉ ሰዎች፣



193

ነጋ ገብሬ


194

ጀበና ደሳለኝ


195

ሙሊታ ኢርኮ


196

የሃንስ ሶሎሞን


197 አሸናፊ ደሳለኝ


198

ፈይሳ ገ/መንፈስ


በመቶዎቹ የሚቆጠሩትን የግድያ ሰለባዎች፣ አካለ ጎደሎዎች፣ ቁስለኞች፣ በኃይል የተመቱትንና ሰውነታቸው በጥይት የተበሳሱትን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡

እ.ኤ.አኖቬምበር 2/2005 ከቃሊቲእስርቤትለማምለጥሲሞክሩበታጣቂዎችበተከፈተተኩስበጥይትተደብድበውያለቁሰዎችስምዝርዝር፣

ተ.ቁ

ስም

ጾታ

የተከሰሱበት ጥፋት፣

1

ጠይብ ሸምሱ መሀመድ


ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
2

ሳሊ ከበደ


ምንም ዓይነት ክስ አልተጠቀሰም
3

ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ


በአስገድዶ መድፈር
4

ዘገዬ ተንኮሉ በላይ


በዝርፊያ ወንጀል
5

ቢያድግልኝ ታመነ


የተወነጀሉበት ያልታወቀ
6

ገብሬ መስፍን ዳኘ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
7

በቀለ አብርሃም ታዬ


በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
8

ጉታ ሞላ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
9

ኩርፋ መልካ ተሊላ


በማስፈራራት ወንጀል
10

በጋሻው ተረፈ ጉደታ


የህዝብን ሰላም በማደፍረስ ወንጀል
12

አብደልወሃብ አህመዲን


በዘርፊያ ወንጀል
13

ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ


ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
14

አዳነ ቢረዳ


በነፍስ ማጥፋት ወንጀል
15

ይርዳው ከርሴማ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
16

ባልቻ አለሙ ረጋሳ


በዝርፊያ ወንጀል
17

አቡሽ በለው ወዳጆ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
18

ዋለልኝ ታምሬ በላይ


በአስገድዶ መድፈር
19

ቸርነት ኃይሌ ቶላ


በዝርፊያ ወንጀል
20

ተማም ሸምሱ ጎሌ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
21

ገብየሁ በቀለ አለነ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
22

ዳንኤል ታዬ ለኩ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
23

መሀመድ ቱጂ ቀኔ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
24

አብዱ ነጂብ ኑር


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
25

የማታው ሰርቤሎ


በአስገድዶ መድፈር
26

ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ


በማስፈራራት ወንጀል
27

ሙኒር ከሊል አደም


በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
28

ኃይማኖት በድሉ ተሸመ


ጽንፈኝትን በማራመድ
29

ተስፋዬ ክብሮም ተኬ


በዥርፊያ ወንጀል
30

ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
31

ሲሳይ ምትኩ ሁነኛ


በማጭበርበር ወንጀል
32

ሙሉነህ አይናለም ማሞ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
33

ታደሰ ሩፌ የኔነህ


በማስፈራራት ወንጀል
34

አንተነህ በየቻ ቁበታ


ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
35

ዘሪሁን መርሳ


በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንወጀል
36

ወጋየሁ ዘሪሁን አስፋው


በዝርፊያ ወንጀል
37

በከልካይ ታምሩ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
38

የራስወርቅ አንተነህ


በማጭበርበር ወንጀል
39

ባዝዘው ብርሀኑ


ግብረሰዶም በመፈጸም ድርጊት
40

ሶሎሞን እዮብ ጉታ


በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
41

አሳዩ ምትኩ አራጌ


በማስፈራራት ወንወጀል
42

ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ


በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
43

ማሩ እናውጋው ድንበሬ


በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
44

እጂጉ ምናለ


በግድያ ሙከራ ወንጀል
45

ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ


የተቀደሰን ቦታ በማራከስ
46

ጥላሁን መሰረት


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
47

ንጉሴ በላይነህ


በዝርፊያ ወንጀል
48

አሸናፊ አበባው


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
49

ፈለቀ ድንቄ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
50

ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው


በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
51

ቶሎሳ ወርቁ ደበበ


የዝርፊያ ወንጀል
52

መካሻ በላይነህ ታምሩ


የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
53

ይፍሩ አደራው


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
54

ፋንታሁን ዳኘ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
55

ጥበቤ ዋቀኔ ቱፋ


ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
56

ሶሎሞን ገብረአምላክ


የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
57

ባንጃው ቹቹ ካሳሁን


በዝርፊያ ወንጀል
58

ደመቀ አበጀ


በግድያ ሙከራ ወንጀል
59

እንዳለ እውነቴ መንግስቴ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
60

አለማየሁ ጋርባ


እ.ኤ.አ በ2004 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር የዋሉ
61

ሞርቆታ ኢዶሳ


የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
ለምዘገባ፣ በዚህ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ 237 የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ዝርዝርን የያዘ ሰነድ ተቀምጧል፡፡

የኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ!

Yenesew Gebre from Dawro-Waka Ethiopia
የኔሰው ገብሬ
እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የተባለ የ29 ዓመት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ መሰብሰቢያ ዳራሽ ፊት ለፊት እሳት በመለኮስ እራሱን በእሳት አያይዟል፡፡ ለሶስት ቀናት ቆስሎ ከቆየ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት የኔሰው ከህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ ለተሰበሰበ ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፣ “በእኩልነት ላይ ባልተመሰረተ አስተዳደር እና ፍትህ በሌለበት እንዲሁም የሰብአዊ መብት በማይከበርበት አገር ውስጥ እራሴን ለመስዋዕትነት አቀርባለሁ፣ ይህንንም በማድረጌ ወጣቱ ትውልድ ነጻ ይወጣል፡፡” የአትዮጵያ ጀግናዉ የእኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ…

“ገዳዮችን አስታውሳለሁ፣ የግድያ ሰለባዎችንም አስታውሳለሁ፣ ለትግሌ የሚያግዙ አንድ ሺ እና ከዚያ በላይ ያሉ አሳማኝ ምክንያቶች እና ተስፋ ቢኖረኝም፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ተስፋየ ይሟጠጣል፣ ያንን ድርጊት ባስታውስኩ ቁጥር ደግሞ ተስፋቢስነቴን የማስወገድ ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘበላሁ፣ ተስፋ ከተስፋቢስነት በላይ ነው፡፡“ ይላል ኤሊ ዊሴል!

**ለጥቃቱ ሰለባዎች ተጨማሪ መረጃ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ያሬድ ኃ/ማርያም እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 “በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ  ወንጀል በኢትዮጵያ፣ የጁንና ኖቬምበር 2005 የአዲስ አበባው ዕልቂት“ በሚል ርዕስ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ለልማትና ውጭ ጉዳዮች እና ለሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አስቸኳይ ጥምር ጉባኤ የቃረቡትን ምስክርነት ይመለከቷል፡፡

***የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባዎችን ነጻ ሲያወጣ አጠቃላይ ኃላፊነቱን ግን በፖሊስና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ መርማሪ ኮሚሽኑ አስተያየቱን በመቀጠል እንደሚከተለው አጠቃሎታል፣ “በተቃዋሚዎቹ የተጎዳ ንብረት የለም፣ በመንግስት በሞኖፖል በተያዘው መገናኛ ብዙሀን እንደተለፈፈው ጥቂት ተቃዋሚዎች የእጅ ቦንቦችንና ጠመንጃዎችን ታጥቀዋል እንደሚለው ሳይሆን በተቃራኒው የእጅ ቦንብ እና ጠብመንጃ የታጠቀ አንድም የተቀዋሚ አባል የለም፣ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የተከፈተው ተኩስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ሳይሆን በተቃራኒው የሰልፈኞችን ጭንቅላትና ደረት ለመበርቀስ ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡” የመርማሪ ኮሚሽኑ የ193 የእልቂቱ ሰለባዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚያካትተው እ.ኤ.አ ከጁን 6 – 8 እና ከኖቬምበር 1- 4/2005 በዚህ ጊዜ ብቻ ያለውን ድርጊት እንዲያጣራ ለአጣሪ ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ነበር፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ግን በፓርላማው ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ከህግ ውጭ በመንግስት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ስም ዝዝዝር ያገኘ ቢሆንም እነዚህ ግድያዎች ኮሚሽኑ እንዲያጣራ ተለይቶ ከተሰጠው ጊዜ ውጭ በመሆናቸ ለህዝብ ይፋ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡