Tuesday, May 20, 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።

በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።



ትኩረት በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ላይ ይሁን!!!

ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች። በአንድ በኩል ህወሓት እና አገልጋይ ድርጅቶቹ በተለይም ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ የተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለመሸፈን የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ ለመጫር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎችና ጥቃቶች እንዲኖሩ በካድሬዎቻቸውና በቅጥረኞች አማካይነት እየጣሩ ነው። በዚህ እኩይ ተግባር ውስጥ ባለማወቅ በስሜት ብቻ የሚነዱ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ ወገኖችም እየተሳተፉበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በዘውግም ይሁን በአገር ደረጃ የተደራጁ የፓለቲካ ድርጅቶች መሪዎች የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና ግብረአበሮቹ ስለመሆናቸው የጠራ አቋም እየያዙ ነው። ወያኔና ግብረአበሮቹን ለማስወገድ በጋራ መታገል የሚያስፈልግ መሆኑ እና ከወያኔ አገዛዝ በኋላ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አገር የመገንባት የጋራ ኃላፊነት ያለብን መሆኑ ሰፊ ግንዛቤ እያገኘ መጥቷል።

ይህ መንታ መንገድ በሁሉም ቦታ በባሰ ኦሮሚያ ውስጥ ጎልቶ እየታየ ነው። በኦሮሚያ አካባቢዎች የሚደርሰው ጥቃትና መፈናቀል ያስቆጫቸው ወጣቶች የሚያደርጉት ፍትሃዊ ተቃውሞ ቀጥሏል። በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጊምቢ፣ በሀረር፣ እና ሌሎችም አካባቢዎች በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥርዓቱን በመቃወማቸው ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል። በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ የእንተባበር ጥሪዎች ጎልተው እየተሰሙ ነው። በኦሮሚያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎች ከጎናቸው እንዲቆሙ የኦሮሞ ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥሪዎችን አቅርበዋል። የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎችም ከኦሮሞ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን ቆመዋል። ይህ ተስፋ የሚሰጥ እና መበረታታት ያለበት ነገር ነው። ሆኖም ግን ከዚሁ ጎን ለጎን ህወሓትና ኦህዴድ የሕዝቡን ጥያቄ ወደ ዘር ግጭት ለማዞር እየሠሩ ነው። በተማሪዎች መፈክሮች ውስጥ ዘርን ለይተው የሚያንቋንሽሹ መልዕክቶች ሰርገው እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ኦሮሞ ባልሆኑ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው። የወያኔ ጆሮ ጠቢዎችና ካድሬዎች በስሜት የተገፋፉ ወጣቶችን ወደ ዘር ግጭት እየመሯቸው ነው።ይህ እጅግ አሳሳቢና በአስቸኳይ መቆም የሚኖርበት ነገር ነው።

ከመንታ መንገዶቹ ለአገርና ለወገን እንዲሁም ለወደፊቱ ትውልድ ደህንነት የሚበጀውን የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እና የመተባበርን መንገድ መርጠን እርምጃችንን ካላፋጠንን አሁን የደረስንበት ደረጃ እጅግ አስጊ ነው። ማሰብ፣ ማስተዋል እና ጠላትን መለየት በሚያፈልግበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው የምንገኘው። ድሃ አማራ ለድሃ ኦሮሞ ወገኑ ብቻ ሳይሆን የትግል አጋሩ ነው። ኦህዴድ ውስጥ ያሉ የወያኔ አገልጋዮች ደግሞ ኦሮሞች ስለሆኑ የድሃ ኦሮሞ ወዳጆች አይደሉም። እነሱ የወያኔ ተቀጥላዎች ናቸው። የትውልድ መንደራቸውን ሳይቀር አዘርፈው የሚዘርፉ ስግብግቦች ናቸው።

የኦሮሞ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ በአማራና በኦሮሞ ወይም በኦሮሞና በትግሬ ሕዝብ መካከል አይደለም። የአማራ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ ከማንኛውም አካባቢ ሕዝብ ጋር አይደለም። ወደ እርስ በርስ ቅራኔ ሊዘፍቁን የሚፍጨረጨሩትን ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን ከሕዝብ መነጠል መቻል አለብን። እዚህ እኩይ ኃይሎች ሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ፍትህና ሰላም ማግኘት አንችልም። እዚህ እኩይ ኃይሎች እርስ በርሳችን ሊያጫርሱን እየሠሩ መሆኑን አውቀን ኃይላችንን በማስተባበር እንመክታቸው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም የኢትዮጵያ ግዛት የሚደርስን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በፍጹም ቁርጠኝነት በጋራ እንታገል፤ በስሜት ከተሞሉና ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ ነገሮች እንቆጠብ፤ አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ የጋራ ጠላቶቻችን በሆኑትን በህወሓት እና አጫፋሪዎቹ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ ላይ በጋራ እንነሳ ሲል ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!



Tuesday, May 6, 2014

ሂውማን ራይትስ ወች በተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ አወገዘ

ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወሰዱት ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ በአስቸኳይ ሊያቆሙ ይገባል ብሎአል።
የመንግስት ባለስልጣናት በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን መፍታት እንደሚገባቸው ፣ ድርጊቱን የፈጸሙት የጸጥታ ሃይሎችና ባለስልጣናት አስፈላጊው ምርምራ እንዲካሄድባቸው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ጠይቋል።
የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሌስሊ ሌፍኮ  የአዲስ አበባን መስፋፋት ተከትሎ በከተማዋ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶአደሮች እጣ ፋንታ አሳስቧቸው ተቃውሞ የወጡትን ንጹሃን ዜጎችን ከማጥቃት ይልቅ ፣ መንግስት ከተማሪዎች ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር መፍትሄ መፈልግ ነበረበት ብለዋል።
ተማሪዎች በአምቦ፣ ነቀምት፣ ጅማ እና ሌሎችም ከተሞች ተቃውሞ ማድረጋቸውን የገለጸው ሂውማን ራይትስ ወች፣ የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ጥይቶችን በመተኮስ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን ገድለዋል። መንግስት በአምቦ 8 ሰዎች እንደተገደሉ ቢናገርም፣ የአይን ምስክሮች ግን ቁጥሩ ከዚህ በላይ እንደሚሆን መግለጻቸውን ድርጅቱ  አክሎ ገልጿል።  የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃውን የወሰድኩት ዘረፋ እና ንብረት ማውደም ስለነበረ ነው የሚል ምክንያት መስጠቱንም ድርጀቱ ገልጿል።
መንግስት የነጻውን ፕሬስ እና የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን በማዳካሙ በኦሮምያ የደረሰውን ጉዳት በትክክለኛ ለማጣራት አለመቻሉን ፣ ወደ አካባቢው የተጓዙ የውጭ አገር ጋዜጠኞችም በጸጥታ ሃይሎች እንዲመለሱ መደረጉን ድርጀቱ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ጋዜጠኖች ከሚታፈኑባቸው አገራት መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑዋን ሂውማን ራይትስ ወች አስታውሷል።
 መንግስት ሚዲያውንና የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን ቢያፍንም ከተጠያቂነት ያመልጣል ማለት አለመሆኑን ምክትል ዳይሬክተሯ ሌስሌይ ሌፍኮው ገልጸዋል።

Sunday, May 4, 2014

ኢትዮጵያ በህግ አምላክ የሚባልባት ሀገር መሆኗ ቀርቷል

ግፈኛውና ዘራፊው የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ መሬት ከሚሰራቸው ትልልቅ ወንጀሎች አንዱና ምናልባትም ዋነኛው በህግና ሕገ-መንግስት ላይ የሚያካሄደው ቀልድና ጭዋታ ነው። ሕገ-መንግስት ህዝብን ከእብሪተኛ መንግስት መጠበቂያ መሳሪያ መሆኑ ቀርቷል። ህግና ሕገ-መንግስት ለወያኔ ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በጣት የሚበላ ነገር ነው። ወያኔና አፋኝ ስርአቱ ህግ የሚጠቅሱት ለራሳቸው ይጠቅመናል ባሉበት ሰዓት ነው። ህግ ለነሱ ካልተመቻቸው ተቀዶ የሚጣል ቆሻሻ ወረቀት ነው።

በኢትዮጵያ ምድር ዋናው ሕገወጥ ተቋም ራሱ ላወጣው ሕግ የማይገዛው ወያኔ/ህወሃት ነው። ለዚህ ነው “ለሚመለከተው አካል ከማሳወቅ ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ፈቃድ አይጠየቅም” የሚለውን ራሱ ያወጣውን ህግ ጥሶ ሰሞኑን ተቃዋሚዎችን ቁም ስቅላቸውን የሚያሳያቸው። ለዚህም ነው ሃሳብን በጽሁፍና በቃል ለመግለጽ ቅድመ ምርመራ እና እገዳ አይኖርም ብሎ ጽፎ፣ አለም አቀፍ የሰበአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዳሉ ተቀብያለሁ ብሎ የተናገሩና የጻፉ ሰዎችን የሚያሳድደውና በሽብርተኝነት የሚከሰው።

ኢትዮጵያ “በሕግ አምላክ” የሚባልባት ሀገር መሆኗ ቀርቷል። ወያኔ ይህን ለህግ ትልቅ ክብር ያለውን የህዝባችንን የዘመናት እምነት ድራሹን በማጥፋት ላይ ይገኛል። ፍትህ በወያኔ አፋኞች መዳፍ እጅ ወድቃለች።

በዚያ አስከፊ የደርግ መንግስት ስርአት እንኳን ዳኞችን “እንዲህ ብላችሁ ፍረዱ” የሚል ትእዛዝ አልነበረም።

ዛሬ በየፍርድ ቤቱ አለም እየታዘበ የሚከናወን አይን አውጣ አሰራር እና የህወሃት የንጹሃን ዜጎችን የፖለቲካ መቀጣጫ ቤት ሆኖ ተለምዶል። ፍትህ እና ፍርድ ቤት እንዲዋረድ ሆኗል። ፍትህና ዳኝነት ራሱ በህወሃት የታሰረበት ጊዜ ነው።

ባለፈው ሳምንት ወያኔ አፍሶ ማእከላዊ በማስገባት የሚያሰቃያቸው የዞን 9 የኢንተርኔት ፌስቡክ ተጠቃሚዎች በሀገሪቱ ህገ መንግስት ከተለመደው መሰረታዊ መብታቸው ውጪ ያደረጉት ቅንጣት ወንጀል የለም። ወያኔ በፈራ እና በደነገጠ ቁጥር ሺህ ህግ ይጥሳል፡፡ ወያኔ ደግሞ ጥላውን የሚፈራ ድንጉጥ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ጠላት እንጂ እንደ አብሮ ኗሪ ዜጋ ማየቱን ከተዎ የሰነበተውም ለዚህ ነው።

ዛሬ ራሱ ወያኔም እኛም በሕግና በሕጋዊነት ላይ ያለን ተስፋ ተሟጧል። ስለዚህም ነው ምርጫችን ይህን ህገ ወጥ የወንበዴ መንግስት በትጥቅ አልባም ይሁን በታጠቀ ሁለገብ አመጽ ማስወገድ ብቻ ነው የምንለው።

ግንቦት 7 የወያኔን አያያዝ አይተን የሁሉአቀፍ የአመጹን መንገድ ተከትለናል። ፈልገን ሳይሆን ተገደን በወያኔ ምርጫ የተመረጠልንን።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወያኔ የህግና የሰላም በሩን ሁሉ ዘግቶ የተወልህን እና ሊከለክልህ የማይችለው ምርጫ የራስህን የነጻነት ትግል የአመጽ ሃይል ብቻ ነው። በየአለህበት በእምቢተኝነት ተነሳ!! መብትህንና ክብርህን ከወያኔ መጠበቅ የዋህነት ነውና ተነስ ተቀላቀል! ራስህን ነጻ አውጣ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!



Thursday, May 1, 2014

አገር እንዲህ ኾናም አትቀርም (ሊያነቡት የሚገባ)

ጽዮን ግርማ -

ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ በምታዝበት ሬዲዮ ጣቢያ ጓደኞቿን ሰብስባ ወደ ስቱዲዮ የገባችው ሚሚ ስብሃቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስለታሠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ሰባት ጦማሪዎች ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ጠቅሳ ስታወራ ነበር። ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከሚሠራው አርቲክል ዐሥራ ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ሲሠሩ ነበር፣ትልልቅ ሆቴል እየተገናኙ ይወያዩ ነበር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ያደራጁ ነበር፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና ከአምነስቲ እንዲሁም ከግብጽና ከኤርትራ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር፤ የሚሉ ውርጅብኞችን በማውረድ እነርሱን የኢትዮጵያ ጠላት እራሷን ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጋ በመሳል ውንጀላዋን ስታዥጎደጉደው ነበር።


በወሬዋ መካከልም ‹‹ይህ ሞያ ሠላሣ ዓመት ያገለገልኩበት ነው፡፡ ታአማኒነት ያለኝ ጋዜጠኛ ስለመኾኔ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስክር ይኾነኛል›› ስትል ነበር።

እንዳለችው ሠላሳ ዓመት በማገልገል ተአማኒነት የሚገኝ ቢኾንማ ዛሬ ጋዜጠኝነት በዚህ ደረጃ አይዘቅጥም ነበር። ሚሚ ዛሬ እንኳን ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ዜና አድርጋ ለማቅረብ አልፈለችገም፡፡ ከእርሷ በዕድሜ በጣም የሚያንሱትን በአስተሳሰብ ግን በእጅጉ የሚልቁትን ወጣቶች አገር ሊያተራምሱ ስትል ወቀሰቻቸው። ኢትዮጵያ እኮ የአንድ ግለሰብ መኖሪያ አይደለችም፡፡ የሁላችንም ናት፣ሁላችንም ባለመብቶች ነን። እነዚህ ወጣቶች እዚሁ አገር ቤተሰብ አላቸው አገሪቱ ስትተራመስ ቤተሰቦቻቸው ይተራመሳሉ ቢያንስ እርሱ ያሳስባቸዋል፡፡ በአመለካከት እና በአስተሳሰብ ስለተለዩ አገር ያተራምሳሉ ማለት ትንሽ እንኳን ጉሮሮን ያዝ አያደርግም?

ተስፋለም በዕድሜም በጋዜጠኝነት ልምድም በቁጥር ከእርሷ በእጅጉ ያንሳል፡፡ በአስተሳሰብ፣በጠንካራ ሞራሉ፣ለሞያው በሚሰጠው ትልቅ ክብር ደግሞ ከእርሷ በእጅጉ ይለያልም ይልቃልም፡፡እርሱ የሞያው ሥነምግባር በሚፈቅድለት ልክ ‹‹ጋዜጠኛ›› ነው። እርሱ የተቀደደ ጫማ አድርጎ ይሄዳታል እንጂ ለገንዘብ ሲል እስኪሪፕቶውን አያንሻፍፍም። እንደርሱ ቢኾንማ በጣም ቀላል ነበረለት እኮ እርሷ እንዳለችው ምን አርቲክል 19 ድረስ አስኬደው እርሷ የምታደርገውን ከእርሷ በላይ ማድረግ ይችል ነበርኮ ያውም ከእርሷ በተሻለ። እርሱ ግን የእዚህ ሰው አይደለም የእርሱ ፍላጎትና ጥረት ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኝነት በራሱ ኃይል እንዲቆም የሚጥር፣ለሞያው ሥነ ምግባርና ክብር አንገቱን የሚሰጥ በማንኛውም መልኩ ትክክለኛ ዘገባ ለማቅረብ የሚጥር ጋዜጠኛ ነው።
ለነገሩ ሚሚ ጋዜጠኞችን ለመወንጀል ስትሽቀዳደም ዛሬ የመጀመሪያዋ አይደለም። እኔም ከዛሬ በስተቀር ለዚች ሴት ቦታ ሰጥቼያት አላውቅም። ከእሥረኞቹ አንዱ ማንነቱን አበጥሬ የማውቀው ጋዜጠኛ ተስፋለም ነውና በእንደርሷ ያለች ጋዜጠኛ ተብዬ ‹‹ጋዜጠኛው ተስፋለም›› ሲወነጀል እየሰማኹ ግን መቻል አቃተኝ፡፡ እናም ወ/ሮ ሚሚን እንዲህ ልላት ፈለኩ፤ ‹‹ይቺ አገር የእሷና የጓደኞቿ ብቻ አይደለችም፣ይቺ አገር እንዲህ ኾናም አትቀርም፤ምናልባት ነገ እርሷ በተስፋለም ቦታ እርሱ ደግሞ በእሷ ቦታ ይኾኑ ይኾናል፤ ዕድሜ ይስጣት እንጂ ያኔ ተስፋለም የጋዜጠኝነትን ሁሁ ጥሩ አድርጎ ያስተምራታል››

አበቃሁ

ክብርነቶ በተናገሩበት ሳመንት?

May 1, 2014

ከዳዊት ዳባ

ሰኞ መያዚያ 13 2006 ባሌ ውስጥ የሁለት ንፁሀን ዜጎችን መገደል በመስማት ሳምንቱን ጀመርነው። አገዳደላቸው ወንጀላችሁን ከባድ ያደርገዋል። የመጀመርያው ልጅ በቁጥጥራችሁ ስር ነበር። በህግ አግባብ መጠየቅ ስትችሉ ነው በነጻ እርምጃ የገደላችሁት። አፉ ውስጥ ሽገጥ አስገብታችሁ ተኩሳችሁ። በሚቀጥለው ቀን ይህን ግፍ ዜጎች ስለተቃወሙ ሌላ ዜጋ ደግሞ በቀን ብረሀን ገደላችሗል።

ማክሰኞ መያዝያ 14 2006 አፋር ውስጥ አስር ንፁሀን ተገለዋል። ከቦታው ያንድ እህት ምስክርነት።” እኔ አራሴ የቆምኩት ስምንት እሬሳ ላይ ነው። ይህ የመጀመርያ አይደለም። በየቀኑ አምስት ልጅ፤ ስድስት ልጅ፤ ሰባት ልጅ፤ ስምንት ልጆች እየቀበርን ነው። ገዳዬች ፌደራል ፖሊሶች ናቸው። እጅግ ለጆሮ በሚከብድና በሚያሳዝን ሁኔታ ልጆ መገደሉ ሳያንስ ነብሰ ጡር እህትም በጽኑ ተጎድታለች። ይህቺ እህታችን ሳትሞትም አልቀረችም’”። በዚሁ ቀን ጋንቤላ ዲማ ላይ መከላከያ ሰራዊት አባለት አስገድደን ፍቶወት ካልፈጸምን ብለው ባስነሱት አንባጓሮ ከመከላከያ ሶስት ከፌደራል አንድ ሞተዋል። “ጋዜጠኛ መሳይ ዝሆኖች ሲጣሉ” ብሎ እንደገለጸው ይህ ገጠመኝ ቁጥሩ ከራት በላይ የሆኑ ንፁሀን ዜጎች ሂወት ያለአግባብ እንዲጠፋ አድርጓል ። ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ አስራ ስምንት አባላቱ ምንም ወንጀል ሳይሰሩ በዚሁ እለት ታስረውበታል። የአገሪቷ ህግ ተቃውሞ ለማድረግ ፍቃድ የማያሻ መሆኑን ቢደነግግም በዚሁ እለት አንድነት ፍቃድ ከለከልንህ ብላችሁታል።

እሮብ መያዝያ 15 ካመት በፊት ዴሬደዋ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በተያያዘ የታሰረ ዳንኤል ጎሳ የሚባል ዜጋ አሰቃይታችሁ ገድላችሗል። ይህ ወገን ደብደባ ሲፈፀምበት ነበር። ለእሬሳ ምርመራ ፖሊስ ከቤተሰቡ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተልኳል። የተላከው ፖሊስ ገዳዩ እራሱ አለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። የሬሳ ምርመራው አምስት ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ተጠናቋል። ሐኪምቤቱ የሬሳ ምርመራ ውጤት ቅጂውን እንኳ ለቤተሰቡ አልሰጥም ነው ያለው። ባንፃሩ አባት አበበ ጎሳ ልጄን ገድሏል ብለው ከጠረጠሩት አካል ነው የምርመራውን ውጤት ያገኛሉ የተባሉት። አቶ አበበ ያላቸው አንድ ልጅ ብቻ ነው። እሱኑ ነው የገደላችሁባቸው። ልጅ የሙት ልጅ ነው። አባት በወንድ አቅማቸው ብቻቸውን ሆነውና መከራ አይተው ያሳደጉት መሆኑን ተናግረዋል። እናንተ እንዳላችሁት እራሱንም ያጥፋ ወይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይገደል በናንተ እጅ እያለ ስለሞተ መንግስቶት ተጠያቂነት አለበት።

ሐሙስ መያዚያ 16 ጎንደር ጪንጋ ላይ ዜጎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የመብት ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ ቀናቶች ተቆጥረዋል። ይህን ምክንያት አድርጋችሁ አራት ዜጎችን ገድላችሗል። እንዲሁ አንድ ፖሊስ ሞታል ሌላ ቆስሏል። ነዋሪው ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረው መሳርያ ሳይዝ ስለነበር ህዝብ ፖሊሶቹ እርስ በእራሳቸው ተጋዳድለዋል እያለ ነው። እነዚህ ፖሊሶች የሞቱትም ሆነ የቆሰሉት በየትኛውም መንገድ ይሁን ወናው ጉዳይ እናንተ በተሸነፋችሁ ጊዜ ወይ ከዛም በሗላ አልቻልንም ብላችሁ ስልጣን ስላለቃቅችሁና ሁሌም ችግሮችን ሁሉ በምትፈቱበት የሀይልና ግጭት ያለበት መንገደ ምክንያት ስለሆነ አሁንም ለነዚህም ዜጎች ሞትም በቀጥታ ተጠያቂ ናችሁ። በዚሁ እለት የቆሰሉት ዜጎች ብዙ መሆናቸውና ባህር ዳር ሆስቢታል ልህክምና መግባታቸውን ሰምተናል። አስራ ስድስት ተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ማታሰራቸውንም በዚህ ቀን ነው የሰማነው።

አርብ መያዚያ 17 የሰላማዊ ፓርቲ ሰላሳሶት አባላት ሊቀመንበሩን ጨምሮ መታሰራቸውን ሰምተናል። እነዚህ ዜጎች ያለምንም ጥፋት የታሰሩት ለሰላማዊ ሰልፍ ህዘብን ሲቀሰቀሱ በነበረበት ጊዜ ነው። የጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ዘግናኝና ልታፍሩበት የሚገባ ግብራችሁን የሰማንበትም ቀን ነው። የዞን ዘጠኝ ስድስት አባላትም መታሰራቸውን የሰማነው በዚሁ ሳምንት ነው። መብራት አገልግሎት ለረጅም ጊዜ እያገኘን አይደለም ያሉ የሽሮ ሜዳ አካባቢ ነዋሪዎችን አፍሳችሁ አስራችሗል።

ቅዳሜና እሁድ ዜና ሰለሌ ነው እንጂ ግድያው፤ እስሩ፤ ማንገላታቱ ይኖራል። ግፋችሁን በማጋለጥ እንኳ እኩል ልንራመድ አልቻልንም። ጨርሼ ሳለቀው ሌላኛው ሰኞ መጥቶ ይህም ሳምንት እንዲሁ በመገደል በማሰር በማሸበር መጀመሩን እየሰማው ነው። በቀጣይ ያንድነት ሰላማዊ ተቃውሞ አለ። የስልምና እምንት ተከታይ ወንድሞቻችን ጥያቄያቸውን ለማስመለስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ። አስተዳድራችሁ አድሏዊ ሆኖ እያለ አዲስ አበባን እናስፋፋለን በሚል ደሀ ዜጎችን ከመሬታቸው ለማፈናቀልና ለማኝ ለማድርግ የዘየዳችሁት እቅድ መረረ ተቃውሞ ከዜጎች እየስነሳ ነው። ጎንደር፤ ጋንቤላ ባጠቃላይ በመላ አገሪቱ የለውጥ ፍላጎት እየተንቀለቀለ ነው። ሰንቱን ገድላችሁ፤ ስንቱን አስራችሁና አሰቃይታችሁ እንደምትወጡት የምናየው ይሆናል።

ይህን እንዳስብ ያደረገኝ ሰባቱንም ቀን በየቀኑ በግፍ ስለተገደሉ እንሰማባቸው የነበሩ ሳምንታት እጅግ ብዙ መሆናቸውን ስለታዘብኩ ነው። በሳምንት አምስቴ፤ ሶስቴ ወይ አንዴ መስማት የተለመደ ነው። የታሰረውን፤ ግፍና ስቃይ የተፈፀመበትን ወይ ያሰደዳችሁትን ዜጋ ጨምረን እንይ ካልን ይህን አይነቱ ወንጀል ሳይፈፀምና እኛም ሳንሰማ ያሳለፍነው ቀን ማግኘት አይቻልም። ይህ እንግዲህ የመገናኛ ሽፋን ለማግኘት የቻለው ብቻ ተወስዶ ነው።

በእርግጥ ንፁሀን ዜጎችን መግደል ማሰር ማሰቃየት ማሰደድ ትግል ላይ እያሉም ያለቆቾ ዋና ሞያቸው እንደነበረ ብዙዎች መስከረዋል። ሚኒልክ ቤተ መንግስት ከገባችሁ ሀያ ሶስትኛ አመታችሁ ላይ ናችሁ። ታዲያ ከሀያ ሶስት አመት በሗላ ዛሬስ ነጻ እርምጃን ማቆም ቻላችሁ ወይ ነው ጥያቄው?። የለመግባባቶችን፤ ልዩነትን ሳትገድሉን ዜጋውን ሳታሸብሩ መፍታት ትችላላችሁ ወይ ነው ጥያቄው?። ከላይ እንዳዩትና ልትክዱት የማያችላችሁ ይህ ችግር ከአመት አመት የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ በጭራሽ አልሆነም። ስለዚህ መልሱ ባጭሩ አልቻላችሁም ነው። በእርግጥም ይህን የሀያሁለት አመት እብደት ላየ መግደልና ግፍ መፈፀም እንዳትችሉ እስክናደርጋችሁ ወንጀላችሁ አይቆምም ብሎ ድምዳሜ ዜጋው ላይ ባይደርስ ሲፈጥረው ጅላንፎ ሆኖ ነው ማለት ይቻላል። እርሶ እራሶ ዘላለማዊ ከብርና ሞገስ ብለው ማሀላ ፈፅመው ስልጣን ከያዙ በሗላ እንኳ ብዙ ንፅሀን ዜጎች በነጻ እርምጃ ተገለዋል። ያለጥፋታቸው ዜጎች በገፍ እየታሰሩና ስቃይ እየተፈፀመባቸው ነው። የታዘለች ህፃንም አልቀረላትም። ይህን አይነት መንግስታዊ ሽብር በሚፈፀምበት አገር ለአፍ ካልሆነ ፖለቲካ ማህደሩ ስፍቷልም ጠቧልም ብሎ መከራከር ልብ ድክም ማድረግ ነው።

በጠቅላላው የስልጣን ዘመናችሁ የፈፀማችሁት ፍጅት ቢወዳደር ከደርጉ የሚብስ ይመስለኛል። ምክንያቱም በዚህ ደረጃና በማያባራ ሁኔታ በየቀኑ በግፍ ስለሚገደሉ ስለሚታሰሩ ሰቆቃ ስለሚፈፀምባቸው ንፁሀን ዜጎች በኔ እድሜ ያኔ አይሰማም ነበር። በርግጠኛነት ግን እስቲ ቦንብ አፈንድተን ሀያ ሰላሳ ሰው እንግደልና የዜጋውን ስሜት እናጥና ወይ ፖለቲካ እንስራበት ብለው ፍጅት የሚፈፅሙ መሪዎች አልነበሩም።” ጦርነት ሰርተን” የምትባለው አለቆቾ የሚወዷት የጫወታ አይነትን ማለቴ ነው።

ደርጉም አንባገነን ስርአት ስለነበር ሰፈራ የመሳሰሉ ግብታዊና ጎጂ እቅዶችን ተግባራዊ አድርጓል። ዜጎች ያልተስማሙባቸውና አምርረው የተቃወሟቸው ቢሆንም እንደናንተ ያጉረመረመውን ሁሉ በገፍ መግደል ወና የቅዱ ማስፈፀሚያ ግን አልነበረም። ሰበብ አይሁን ለማለት ነው። ህንፃ ለመግንባት፤ መንገድ ለመስራት፤ አበባ ለመትከል የንፁሀን ሂወት እስርና ስቃይ የግንባታዎቹ ሁሉ መሰረቱ እኮ ነው የሆነው። ይህ የባህሪያችሁ ከመሆኑም በተጨማሪ ሁላችሁም ጋር ከፍተኛ የማስተዳደር እውቀት አለ ማለት ብቻ ነው የሚቻልው።

ክብር የሆነው ለሰው ልጅ ሂወት የሚሰጠው ዋጋ ከፍተኛ በነበረበት ዘመን ዜጎች ግዛው ለምን ለምን ሞተ? ማርታ ለምን ለምን ሞተች ብለው ጉሮሮ ሊይዙ ይደርሱ እንደነበር ያውቃሉ። ዛሬ ከአንድ እስከ አስር ዝም ብሎ ዜናችን ነው። ለምን ተብሎ መጠየቅ አይደለም ገደሏቸው እኮ ተብሎም በቀጣይ አናወራበትም። ሀምሳ፤ መቶና ሶስት መቶ አዲስ ቁጥር አየደለም። ከዚህ በፊት አድርጋችሁታላ። ያዋጣል ካላችሁ ግን ለወደፊቱም በርቱ። ይህን በሚመስል እውነታ ውስጥ ጊዜና ሁኔታ ይመቻቻል። ያኔ ገደላችሁ አይደለም ገላመጣቸሁ የስልጣናችሁን ፍፃሜ እንደሚያደርገው እነግሮታለው። ማወቅ ያለቦት የተለወጠ ነገር የለም ያው ኢትዬጵያዊ ነው።

በግሌ ስልጣኑ የያዙ ለት ያደረጉትን ንግግሮትን ካዳመጥኩበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌም ሳዮትም ሆነ ስሰማዎት አብሮአደጌን ሞዘዘኝን ነው የሚያስታወሱኝ። በዛኑ ሰሞን በፃፍኩት ፅሁፍ ስለዚሁ ጉዳይ ልነግሮት ነበር። ሰው ናቸው የሚሉ ሲበዙ አልቸኩል ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ተውኩት። ይህን ክፍል ጎርጄ በሌላ ገፅ ላይ አኖርኩት። ዛሬ ኮፒ ፔስት ነው ያደረኳት። በርግጥ ሰበአዊነት ያለበትና ልጆቼ ተቆጡኝ። ፀለይኩኝም የምትለዋ ቃለ መጠይቆት አጭበርብራኝለች።

ልጆች ሆነን ከልጅነቱ ጀምሮ የመጨረሻ ገንገበት የነበረ ልጅ ነበር። ለዚህ ልጅ የሆነ ጊዜ ላይ ይህን ባህሪውን ያየ ሌላኛው አብሮ አደጌ ሞዘዘኝ ብሎ የቅጥል ስም አወጣለት። ገንገበቶች ገገማ ስለሆኑ እንደተጠመቀበት ወይ እንደሰለጠኑበት ጉዳይ ነው ለመሀበረሰቡ ጠቃሚም ጎጂም የሚሆኑት። አክራሪ የእምነት ሰው፤ ወይ ገገማ ቀልደኛ፤ ጨካኝ መርማሪ ወይ ለእውነት የሚሞት ዳኛ ወይ የሚያናድድ ሊስትሮ ጠራጊ ሊሆኑ ይችላሉ። ሞዘዘኝ ከፍ ሲል የሰፈር የጠብ ቡድን አገኘው። ከዛ አንዷን ጡቷ ላይ በጩቤ ወጋት፤ እትዬ እንትናን በድንጋይ ፈነከታቸው። የዛን ሰፈር ልጅ በብረት ሰንሰለት ቀጠቀጠው። ብቻ ስሙ ባንዴ ዝነኛማ ተፈሪም ሆነ። የጠብ ቡድን ውስጥ ደግሞ ድርሻቸው ማካበድና ማሟቅ የሆነ አሉ። ሀይ ሀይ ስለበዛበት ሞዘዘኝ እስታ ሊል አልቻለም። ቆያይቶ ተገደለ።

እርሶን ሳይ ትግሬ ተጋዳላዮች ምርጥ መጠቀሚያ ነው ከመንጋው መዘው ያወጡት እላለው። ገንገበቶችን እንዲሞቃቸው በማድረግ ብቻ እንደፈለጉ ሊነዷቸው መቻላቸውን አውቀዋል። የዚህ አይነት ሰዎችን ምንም አይነት ወንጀል ማሰራት ቀላል ነው። የሚፈልገው ጎሽ አበጀህ፤ አቤት ድፍረት፤ ለርሶ ሲሆን ባለእራዩም እንዲህ ሊያሳምረው አይችልም ነበር። እስከዛሬም ተሳስተናል አይነት ሙገሳን መጨመር ነው። በርግጠኛነት ከበቀደሙ የፓርላማ ውሎዎ መልስ ብዙዎች ይህን አይነት አስተያየት ሰጥተዎታል። ከዋኖዎቹ ለዚሁ ጉዳይ ተደውሎሎታል። ሙገሳ ያለበት ተመሳሳይ ነገርን ብለዎታል። ለሁሉም መልክቴን ጠቅላይ ሚንስትሩ ሞዝዘውኛል። ብዬ አቆማለው።