Thursday, October 31, 2013

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ (ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት)


የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ ሕዝብ ያልተቀበላቸው አንቀጾች እንዳሉት ብንገነዘብም፣ዓለም የተቀበላቸውን የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶች ያካተተ ሙሆኑን እንረዳለን። በሕገ-መንግሥቱ ከተካተቱት አንቀጾች፣አንቀጽ 74 ከንዑስ አንቀጽ(1) እስከ (13) የተዘረዘሩት የእርሰዎ የጠቅላይ ሚነስትሩ ሥልጣንና ተግባሮች እንደሆኑ ያረጋግጣል ። ከሁሉም በላይ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 13 የተገለጸው ሕገ-መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጠው ሥልጣን መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጿል። ይህም ማለት በአገሪቱ ውስጥ ለሚታይ የሕግ መከበርም ሆነ መጣስ ፣ሕግ ያከበሩትን የመሾምና የመሸለም፤ሕግ የጣሱትን ደግሞ ለፍርድ የማቅረብ ከፍተኛ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ያለበዎ መሆኑን ሕገ-መንግሥቱ ያረጋግጣል። በአጠቃላይ፣በሕገ-መንግሥቱ የተጓደሉትንና የተዛቡትን ጉዳዮች በማጥናትና በማስጠናት እንዲሟሉና እንዲቃኑ የማድረግ፣በአግባቡ ያሉትን በሥራ እንዲውሉ የማድረግ ብቸኛው ኃላፊ እርሰዎ እንደሆኑ ሕገ-መንግሥቱ ያዛል። ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ኢትዮጵያዊቷን የማደጎ ልጅ በርሀብ የገደለችው አሜሪካዊት በ37 አመታት እስራት ተቀጣች

Hana’s parents broke down in tears as they get maximum sentences (+video)

የ42 አመቷ ካሪ ዊሊያምስ የ13 አመቷን ታዳጊ ሐና ዊሊያምስን በረሀብና በብርድ በመቅጣት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል።
የገዳዩዋ ባለቤት በ28 አመታት እንዲታሰር ተፈርዶበታል። ሌላው የ10 አመቱ የማደጎ ታዳጊ ኢትዮጵያዊም ለሌሎች አሳዳጊዎች እንዲሰጥ ተደርጓል። ፍርዱን የሰጡት ዳኛ ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ማስተላላፋቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሰዎች ከሁለት አመታት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።

  • Larry and Carri Williams of Sedro-Woolley, Washington were found guilty of neglecting, abusing, and ultimately killing 13-year-old Hana Williams
  • The couple left Hana to die from hypothermia and starvation in their backyard in May 2011
  • Step-brother Immanuel testified he and Hana were beaten with sticks, hosed down, forced to eat frozen food and locked in closets
  • Larry accusing his wife of being the ‘primary actor’ in the abuse
A Washington couple accused of starving, beating and forcing their adopted daughter to stay outside as punishment have been sentenced to spend decades in prison for her death.
Larry and Carri Williams were convicted on September 9 and sentenced on Tuesday for the manslaughter in the death of a teenage girl they adopted from Ethiopia.
Carri Williams was also found guilty of homicide by abuse.
Hana Williams was found dead May 12, 2011, in the backyard of the family home in Sedro-Woolley, about 60 miles north of Seattle.
EMF

ድምፃችን ዛሬም ነገም የጎሹ ወልዴ ነው! (ጌታቸው ረዳ ከኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)


በወያኔ ዘመን የተወለዱ ወይንም ህጻናት የነበሩ ወጣቶች ዛሬ አድገው ባደጉበት የተመረዘ የፖለቲካ ትምህርት በመዋኘት ግንጠላም ሆነ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያስተምሩ እንደ እነ ጃዋር መሐመድ የመሳሰሉት አደገኛ ‘የሰው አንስሳት’፤ ከትግራይ ከመቀሌ ‘አብርሃ ደስታ’ እያለ ራሱን የሚጠራ ወጣት እና የዓረና ድርጅት አባል ‘በፌስ ቡክ’ እና ዘሐበሻ በተባለው ድረገጽ የሚያሰራጨው የነቀዘ ቅስቀሳው ‘ለጃዋር መሐመድ’ (ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ሶማሊያ! ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ! ፈካሪ) በተደጋጋሚ ለሦስተኛ ጊዜ ድጋፍ በመቆም “በጃዋር ላይ የጥላቻ ዘመቻ አራማጆች” በማለት ወንጅሎናል።

Wednesday, October 30, 2013

ኢትዮጵያ- የፖሊስ መንግስት ያንሰራፋባት ሀገር (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም)

October 30, 2013
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገመንግስት በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል፡፡“በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል፡፡ ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን  ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም፡፡ ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡“ ይላል አንቀጽ 19(2)(5)፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለዉም፡፡

ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች “HRW“ የተባለው ዓለም ዓቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ መንግስት “የፌዴራል ፖሊስ ማዕከላዊ ምርመራ” እየተባለ በሚጠራው የፖሊስ ጣቢያ የሚፈጸሙትን አስደንጋጭና አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ዘገባ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ይህ የፖሊስ ምርመራ ማዕከል በጥርጣሬ የተያዙ ዜጎችን በማሰቃየት ይታወቃል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በቁጥጥር ስር ባሉ እስረኞች ላይ በተለይም ያለው መንግስት ይቃወሙኛል በሚላቸው የፖለቲካ እስረኞች ላይ ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም እልህ አስጨራሽ የምርመራ ሂደት በማድረግ እስረኞችን በግድ ወንጀል ሰራን ብለው አንዲአምኑ በማስገድድ፣ እንደሚያሰቃይና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ“ እየፈጸመ እንደሆነ በማረጋገጥ በዘገባው ይፋ አድርጓል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በማያያዝም “ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው ተቋም ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች፣ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች፣ መንግስት የብሄር ግጭት ተንኳሾች ናቸው በሚላቸውና ሌሎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በጅምላ ተይዘው የሚሰቃዩበት የምርመራ ማዕከል” ነው ብሎታል፡፡

ገጣሚው ዊሊያም ኤርነስትን አባባል በመዋስ “ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል”  የሰቆቃ መደብር በለቅሶና በሰቃይ የታጠረ የጭለማ ቤት ነው :: የገዥው መንግስት ተቃዋሚዎች፣ አመጸኞች፣ የሚላቸዉን የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እስረኞች በሙሉ በምርመራ ጊዜ ሰቆቃ ተጠቅሞ አራሳቸዉን አንዲወነጅሉ ያስገደዳቸዋል:: እንዲሁም ብዙዎቹ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች አባባል ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም “አስቀያሚው የአካልና የስነ ልቦና ማሰቃያ እንዲሁም አስገድዶ የማሰመኛ ምሽግ” መሆኑን በመጠቆም በማዕከሉ ከሚፈጸሙ የማሰቃየት ወንጀሎች እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ መሆናቸውን በአጽንኦት ገልጿል፡፡ አኔም በግሌ  ከአስፈሪው ማአከላዊ ምርመራ መዳፍ የተረፉ የቀድሞ እስረኞችን አነጋገሬ አውቃለሁ::

የስሚንቶ ፋብሪካዎች የገበያ ችግር እንዳጋጠማቸው ተዘገበ

ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ በአገሪቱ የሚገኙ ሶስቱ ታላላቅ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በአመት 12 ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም በገበያ ውስጥ የሚገኘው ስሚንቶ ድምር ከ5 ሚሊዮን አይበልጥም።
አብዛኛውን ስሚንቶ የሚገዛው መንግስት ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍ ድርሻ ቀዝቃዛ መሆኑ ተዘግቧል።
የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ደርባን ኩባንያ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በኩንታል 209 ብር እየሸጠ፣ ለደንበኞቹ ቤታቸው ድረስ እያደረሰ ነው። ሙገር ስሚንቶም በተመሳሳይ ለልዩ ደንበኞቹ ምርቶቹን ቤታቸው ድረስ እያደረሰ ነው።
ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የገለጹ ባለሙያዎች ” ብዙም ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የሲሚንቶ ገበያ እየተቀዛቀዘ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በ2006 ዓ.ም 21 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን፣ በ2007 ዓ.ም. 27 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ አገሪቱ እንደምትፈልግ ከአራት ዓመት በፊት የወጣው ጥናት ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡

Friday, October 25, 2013

2 የጎንደር ወረዳዎችን ወደ ትግራይ ክልል ለማካለል ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ


 
የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)
(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል ስር ያሉትና በሰሜን ጎንደር ስር የሚገኙት 2 ወረዳዎችን ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል የፊርማ ማሰባሰብ መጀመሩን ለዘ-ሐበሻ ከስፍራው የደረሰው መረጃ አመለከተ። ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል በጎንደር ስር የነበሩት አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ገበሬዎች በሰፊው የሰፈሩ ሲሆን እነዚሁ የትግራይ ተወላጆች ወረዳዎቹ ወደ ትግራይ ክልል እንዲጠቃለሉ ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረዋል። በአሁኑ ወቅት እነዚህ 2 ወረዳዎን የትግራይ አመራሮች እንደሚቆጣጠሩት የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገበሬዎቹም አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው። ገበሬዎች ከጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ወረዳዎቹ ወደ ትግራይ ክልል እንዲጠቃለሉ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ የጀመሩ ሲሆን ይህን ለማሳካት ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ መዋጮ እንዳዋጡም ተጠቁሟል።
የአማራ ክልል በነዚህ የትግራይ ገበሬዎች በተጀመረው እንስቃሴ ዙሪያ እስካሁን የሰጠው ምላሽ ባይኖርም ክልሉ ፈቀደም አልፈቀደም ገበሬዎቹ እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ድረስ ጉዳዩን ወስደው እነዚህን ሁለት የጎንደር ወረዳዎች ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል የሚመልሳቸው እንደሌለ በመናገር ላይ ናቸው ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳንጃ፣ ጠገዴ፣ ዳባትና አፎኛ ደምቢ ወደራ የሚገኙ ነዋሪዎች የትግራይ ገበሬዎችን ጥያቄ እንደሚቃወሙ ገልጸው የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ በ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

የአንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው

የአንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው ——————————- የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት መምህር አበበ አካሉ ትናንት 14/02/06 ዓ.ም የደህንነት መስሪያ ቤት አባላት ነን ባሉ ሶስት ቅጥረኞች የግድያ ሙከራና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ለፍኖተ ነጻነት ይፋ አድርገዋል፡፡ ሰላማዊው ታጋይ እንደተናገሩት በምሳ ሰዓት ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ ህገ ወጦቹ ያካራክሯት የነበረችን ላንድክሩዘር መኪና የእግረኛ መንገድ እንድትዘጋ በማድረግ አቶ አበበን በሀይል በመኪናው በመጫን ወደማያውቁት ሰዋራ ቦታ በመውሰድ ቤቶች በሚሰሩበት አካባቢ ከመኪናዋ በማውረድ ሺሚንቶ ላይ በማስተኛት በሰላማዊ መንገድ የሚያካሂዱትን ትግል እንዲያቆሙ ይህ ካልሆነም‹‹ በሽብርተኝነት በመወንጀል መንግስትን በሀይል ለማውረድ ትሰራለህ›› በማለት እንደሚወነጅሏቸው በመንገር በቃላት ለምግለጽ በሚቸግር ሁኔታ ድብደባ እየተፈራረቁ እንዳካሄዱባቸው ተናግረዋል፡፡ መምህር አበበ ከቀኑ 6፡30 እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ግለሰቦቹ ሽጉጥ ደግነውባቸውና የማያውቁትን የአልኮል ቃና ያለው ፈሻሽ ነገር በመጋትና ከሲሚንቶ ጋር አጣብቀው በመርገጥ የግድያ ሙከራ ካደረጉበቫቸው በኋላ ከምሽት ላይ በመኪና አውጥተው እንደጣሏቸው ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ነጻነት ፓርቲው አመራሩ በህገ ወጥ መንገድ መያዛቸውንና መደብደቡን በተመለከተ ምን እያደረገ ነው በማለት የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች በመጠየቅ ከአመራሮቹ ‹‹ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንገኛለን፡፡አውሬነት የተሞላበትን አስነዋሪ ድርጊትም በቸልታ የምናልፈው አይሆንም››የሚል ምላሽ አግኝታለች፡፡ መምህር አበበ አካሉ በአሁኑ ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ይገኛሉ፡፡ ሰላማዊው ታጋይ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ናቸው፡፡

ሲኖዶሱ የፓትርያርኩን ውሳኔ አስቀየረ


ቅዱስ ሲኖዶሱ በትናንትናው የስብሰባ ውሎው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በአብላጫ ድምጽ ወስኖባቸው የነበሩት የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ በዛሬው ዕለት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ ‹‹አዲስ አበባ የእኔ ልዩ ሐገረ ስብከት በመሆኑና ማንም ሊያዝበት ስለማይችል ሊቀ ጳጳሱ በቦታቸው እንዲቀጥሉ በመወሰን የትናንቱን ውሳኔ ሽሪያለሁ››ማለታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ከሰዓት በኋላ ቀጣዩን አጀንዳ በማንሳት ከመወያየቱ በፊት ተቃውሞ እንዳላቸው የገለጹ ጳጳሳት ፓትርያርኩ የሲኖዶሱን ውሳኔ በመሻር ሊቀ ጳጳሱን በመንበራቸው እንዲቀጥሉ ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ የቤቱን ውሳኔ እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡
ፓትርያርኩም በመጨረሻ የሲኖዶሱን ውሳኔ የመጨረሻ በማድርግ መውሰዳቸውን በመግለጽ አቡነ እስጢፋኖስ በሲኖዶሱ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ሲኖዶሱ በነገ ውሎው በአቡነ እስጢፋኖስ ቦታ ሌላ ሊቀ ጳጳስ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት?

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።

ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?

በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።

በዚህ ረገድ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች አሉ፤ ለምሳሌ:

ወያኔ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “እንቢ አንጣላልህም” ያሉት መሆኑ የሚያኮራ ነው። ወያኔ ከጠበቀው በተቃራኒ የሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ መታየቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው። አብሮነታችንን ማጎልበትና ይህንን በአደባባይ፣ በአዳራሾች፣ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ውጭ የተጀመረው አገር ቤት መዳረሱ የማይቀር ነው። ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።
ወያኔ በአባይ ግድብ ስም በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን “ከአባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ” “ከአባይ በፊት ሙስና ይገደብ” እያሉ ወዋጮዎቹን እንቢ ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የታየው ጽናት በጣም አበረታች ነው። የወያኔ ሹማምንት በአባይ ጉዳይ እንኳንስ ገንዘብ ስብሰባም ሊሰበሰቡ አልቻሉም። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

ተስፋዬ ገብረአብ–ኢሰብዓዊ እና የሞራል ድሃ! ገላነው ክራር

ጥቂት ቀደም ሲል “አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ በደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ አይን” በሚል ርእስ በለቀቅሁት ጽሁፍ ሳቢያ በርካታ አንባቢያን የተለያዬ አስተያየት ልከውልኛል። አንዳንዱ “ይህን እየወጣ ያለ ደራሲ ወደታች ባትጎትተው ምናለ?” ሲል ሌሎችም “አበጀህ” ብለውኛል።

መጽሃፍትን አነባለሁ ብዬ አስባለሁ–በተለይ የአማርኛ ስራዎችን። አሁን አሁን የሚወጡትን ካልሆነ በቀር ብዙም ያመለጠኝ ስራ አልነበረም። አንድ መጽሃፍ አጀማመሩ ካላስደሰተኝ ለመጨረስ ራሴን አላስገድደውም። ጀምሬ ወዲያ ከወረወርኳቸው መጽሃፎች ውስጥ “የቡርቃ ዝምታ” አንዱ ነው። ይህ ስራው ተስፋዬን ከሞራሊቲ አኳያ እንዳወረደው ይኖራል። ባብዛኛው ሰው ተቀባይነት ያለው የሞራል ድርጊትና ሃሳብን፣ ሰብአዊነትን እና በስነ-ጽሁፍ ውበት ውስጥ ፍቅርን እና ሰላምን መስራትን ደግሞ “አደንቃቸዋለሁ” ከሚላቸው ደራሲያን–ስብሃት ገ/እግዚአብሄር እና በአሉ ግርማ አለመማሩ አሳዛኝ ነው። በተለይ በዓሉ ግርማ ለተስፋየ ሞዴል ሊሆን አይችልም። እኔ ተስፋዬን ብሆን፣ የበአሉን ስራዎች እንደገና አነባለሁ። ፍቅርና ሰላምን፣ እውነትን፣ ስለሰው ልጆች ሁሉ አንድነት ለመጻፍ እሞክራለሁ። የ“ቡርቃ ዝምታ” በወቅቱ የመለስ አገዛዝ ለተስፋዬ የሰጠው የቤት ስራ ነው ለማለት ባልደፍርም፣ በራስ ጊዜ ተነሳስቶ የሰራው ቢሆንም እንኳን፤ እኔ ተስፋዬን ብሆን ኖሮ የመጀምሪያ ስራዬ በ“የቡርቃ ዝምታ” ያደማሁትን ያብዛኛውን ልብ አጠግጋለሁ። ባጭሩ “አጥፍቻለሁ… ይቅርታ ይደረግልኝ” እላለሁ። በዚህ ብቻ አይደለም። ተስፋዬ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን አልበደለም አይባልም። “እፎይታ”ን ሲያዘጋጅ ያኔ በፕ/ር አስራት ወ/የስ ስም የወጣውን ጽሁፍ የሚያስታውስ አለ? ባለፈው ጽሁፌ “ … በ1980ዎቹ አጋማሽ አካባቢ በእፎይታ መጽሄት በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ስም አንድ ጽሁፍ ይወጣል። [ይህን አሁን ከዚህ በላይ እኔ የጻፍኳቸው ሁለት አንቀጾች፣ አንባቢ የየራሱን Nth term (ለምሳሌ እያንዳንዱን አምስተኛ/ስድስተኛ ቃል) እያወጣ በመጣል፣ ቀሪውን ጽሁፍ በምናብ ለማንበብ ይሞክር። ምንም እጅና እግሩ የማያስታውቅ ጽሁፍ ነው የሚሆነው] የሚል ጠቅሼ ነበር። ጽሁፉ በፕሮፌሰሩ ስም ሲወጣ የመጽሄቱ ዋና አዘጋጅ ተስፋዬ ገ/አብ ነበር። ጋዜጠኝነት እና ደራሲነት እንዲህ ዘቅጦ የሚወርድበትን የመለስ አገዛዝ፣ ያኔ እውስጡ እያለ አያውቅም አይባልም። “ያኔ የት ሄዶ ነበር?” ብዬም አልሞገተውም ተስፋዬን። የመለስን አገዛዝ (ኢህአዴግን) ያኔ የተቀላቀለው ወዶ ሳይሆን ተማርኮ ቢሆንም፣ እያደር በአመራራቸው ተመስጦ፣ በርዕዮተ አለማቸው ተማርኮ… ሊሆን ይችላል–እነሱው ጋር የከረመው። ይሁን። ግን እንደዚያ የፕ/ር አስራትን ጽሁፍ በወሮበላ አስቀምቶ ጽሁፋቸውን እንደ ማሳተም ያለ ስራ ሲሰራ፣ ከሞራል አንጻር ተስፋዬን ምን ተሰማው? ያን በፕ/ሩ ስም የወጣውን ጽሁፍ ቆይቼ ደጋግሜ አንብቤያለሁ። እውነት ለመናገር በረቂቅ ደረጃ እንኳን እንደዚያ አይነት ጽሁፍ የሚጽፍ የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሚኖር አይመስለኝም። (ያ ጽሁፍ በአጋጣሚ በእጁ ያለው ሰው እታች ባሰፈርኩት አድራሻየ ቢልክልኝ ወይም አንባቢ እንዲያየው በአንዱ ሳይት ቢያወጣው አገራችን በእነማን እጅ እንደወደቀች እና የተስፋየንም ማንነት ማወቅ ይችላል)።

20 ሚሊየን ብር ፈጅቶ በሃያ ቀን የተገነባው የጂንካ ስታዲየም በሁለት አመቱ ተደረመሰ

በደቡብ ኦሞ ጂንካ ከተማ በ2003 ዓ.ም የተሰራ ሁለገብ ስታዲየም መፍረሱ ተሰማ፡፡ ስታዲየሙ ለ13ኛው የአርብቶ አደር ጉባኤ ወደ ዞኑ ላቀኑት የቀድሞ ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ ጉብኝት እንዲደርስ ተብሎ የተወጠነ እንደ ነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም የዋለው የአርብቶ አደር ቀን በስታዲየሙ እንዲከበር ለማድረግ ስራው ሙሉ በሙሉ በ20 ቀናት ውስጥ እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከተጠናቀቀበት ጥር 13 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ አመት እንዳገለገለ የዛሬ አመት ገደማ ከክቡር ትሪቡኑ በስተቀኝ የሚገኘው ብሎክ እንደወደቀ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ከተከሰተ ከአመት በኋላ ጥላ ፎቁና ክቡር ትሪቢዩኑ ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ለመፍረስ ችሏል፡፡
አደጋው ሲከሰት በጥበቃ ላይ የነበሩ ሶስት ፖሊሶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ እንደሚሉት በእለቱ በስታዲየሙ የአውደ ርዕይ ዝግጅት እንደነበርና አደጋው በቀን ገጥሞ ቢሆን ከፍተኛ እልቂት ይከሰት እንደነበር ገልፀዋል፡፡
ስታዲየሙ ሲሰራ ክቡር ትሪቢዩኑና ጥላ ፎቁ “ይርጋለም ኮንስትራክሽን” በተባለ ተቋራጭ መሰራቱ ታውቋል፡፡ ለስቴዲየሙ ግንባታ 20 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ታውቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የዞኑ የስፖርት ሰብሳቢ አቶ ስጦታው ጋርሾ “በጉዳዩ ላይ አስጠያየት መስጠት አልፈልግም” በሚል ስልካቸውን ዘግተዋል፡፡ የዞኑ አስተዳዳር አቶ ሞሎካ ውብነህ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት በስልካቸው ያለመስራት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

source abugida


Thursday, October 24, 2013

አሸባሪው ማነው?

በቀይዋ ብዕሬ፣ የከተብኩት ሁሉ፤
አንዴ ከኔ ወጥቷል፣ እስቲ ተቀበሉ።

እውነትን ሊናገር፣ አፉን የከፈተ፤
ንቅዘቶችን ነቅሶ፣ ድክመትን ያተተ፤
በዚህች ጉስቁል አገር፣ ምሣር በበዛባት፤
በሚቀጥለው ቀን፣ ለርሱ ወየውለት!!

ለምን!?
ፈራጅ ነው ዘራፊ፤ ተዘራፊው ሌባ
ትችት ያሳስራል፤ በማሸበር ደባ

የታል!?
"ነፃ አውጪው" የታል!?
ሆኗል ጨቋኝ መሪ
"ለምን" ባዩን ፈራጅ፤ "በሽብር ፈጣሪ"
ደፍሮ የሚናገር፣ ዘብጥያ ታሣሪ።

ማነው!?
ፀረ—ሠላም ማነው!? ማነውስ ነፃ አውጪ!?
አሸባሪ ማነው!? ማንኛው ነው ቀጪ!?
ወንጀለኛው ማነው!? ማነውስ ታሳሪ!?
ፀረ—ሠላም ከሣሽ፣ እራሱ መስካሪ፤
"ለምን" ባይ ተከሣሽ፣ ላገር ተቆርቋሪ!!

2004 ዓ. ም.

ኄኖክ ስጦታው
ከ "ሀ-ሞት" የግጥም መጽሐፍ

ወያኔ ወደ ሙኒክ መጥቷልና ወገን ተዘጋጅ!!!!!!!!!

ወያኔን መደገፍ ማለት በወገኖችዎ ላይ የሚደርሰውን ይህን ግፍ መደገፍ መሆኑን ይገንዘቡ!!

Ethiopia 1997

የወያኔን የዘረፋ ጉዞ ተባብረን እንግታ!!

የወያኔ ቁንጮ የነበረው መለስ ዜናዊ ከሚስቱ ጋር በመሆን ከዘረፉት በላይ ለመዝረፍ በነደፉት የአባይ ግድብ እቅድ ሳቢያ በውጭ ሃገር ካለው ወገናችን ጉልበት በዝባዥ የሆነውን የፈረንጅ ሃገር ስራ ተጋትሮ ያገኛትን ለመመንተፍ የመለስ ውሾች የሆኑት ካድሬ ተብዬዎች ላይ ታች ሲንጠራወዙ ሁለት ዓመት ሆናቸው። ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም እነዚህን ተላላኪ አሽከሮች በየደረሱበት እያሳደዱ ስብሰባ ብለው የጠሩትን ሲያከሽፉ፣ እግሬ አውጭኝ ሲያስሸመጥጡ፣ የእነርሱን ባንዲራ እያነሱ እውነተኛ የኢትዮጵያ ባንዲራ ሲሰቅሉ፣ ወያኔዎቹ የተከራዩትን አራሽ ተቆጣጥረው የራሳቸውን ስብሰባ ሲያካሄዱ፣ ወዘተ ወዘተ ብዙ ገድል አይተናል። ካድሬዎቹ ውሾች ግን ወትሮም የሰውነት ክብር የላቸውምና በደረሰባቸው ተደጋጋሚ ውርደት ተሸማቀው አርፈው አልተቀመጡም።

እየተሽሎኮለኩና እያደቡ ከዳያስፖራው የውጭ ምንዛሪ ለመንጠቅ ዛሬም የሞት ሞታቸውን ያገኙትን ሁሉ ከመቧጠጥ አላረፉም። በዚህም መሰረት በመጪው ኖቬምበር 02/2013 በጀርመን ሙኒክ በአባይ ቦንድ ስም ዩሮ ለመሰብሰብ እየተጠራሩ መሆኑ ተደርሶበታል። በመሆኑም በሃገሩ ጉዳይ የሚንገበገብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከቅርብም ከሩቅም ወደ ሙኒክ እንዲከትና የወያኔን ዘረፋ በተለመደው መልኩ እንዲያከሽፍ የተቃውሞ አስተባባሪ ግብረ-ኃይሉ ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

በእለቱ በሚደረገው ተቃውሞ የተለመደው የወያኔን የዘረፋ ተግባር ከመግታት በተጨማሪ ትናንት የወያኔ መንግስት በደል እንደፈጸመባቸው አመልክተው የስደት ተገን ያገኙና ዛሬ ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ለወገኖቻችን ስቃይና ሞት ተባባሪ የሆኑ ለጥቅምና ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎችን ፎቶ በማንሳትና ቪዲዮ በመቅረጽ ስደት ላመለከቱበት ሃገር መንግስት የማጋለጥ ስራ በሰፊው ይሰራል። ሁላችንም በ02/11/2013 ጀርመን ሙኒክ ተገናኝተን የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።

ወያኔን ለምን እንደምንቃወም እናውቃለን።

*     በስርዓቱ ደባ እየፈራረሰች ስላለችው ሃገራችን

*     በየጊዜው ስለሚጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን

*     መሬታቸውና እየተነጠቁ ስለሚፈናቀሉ ወገኖቻችን

*     በየእስር ቤቶቹ ስቃይና መከራን እየተቀበሉ ስላሉ ወንድም እህቶቻችን

*     የካድሬ መፈንጫ ስለሆኑት የሃይማኖት ተቋሞቻችን

*     ታሪክ አልባ ስለተደረገው ሃገራዊ ማንነታችን

*     ስለምንናፍቀውና በወያኔ ስለተዘረፈው የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት

*     ስለተረገጠው፣ ፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነታችን ወዘተ ወያኔንና በስሙ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ያለማቅማማት እንድንቃወም ያስገድደናል።

ለወያኔ ያደሩ ሆድ አደር ባንዳዎችም ወያኔ ለሚያፈሰው እያንዳንዱ የደም ጠብታ አስተዋጽኦዋቸው መቼም የማይረሳ ስለሆነ ለተጠያቂነታቸውም ጠንክረን እንሰራለን!!

በሙኒክ ለተዘጋጀው የወያኔ ዘረፋ ሁኔታዎችን እያመቻቹ ያሉትን በቅርብ ቀን ፎቶዎቻቸውንና ስማቸውን ለኢትዮጵያውያን ይፋ እናደርጋ

ጫልቱ እንደ ሄለን ከቡርቃ ዝምታ የቀጠለው መርዛማ ብዕር


October 24, 2013
ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ተራሮች አንቀጠቀጥኩ ያለው ትውልድ አካል ነኝ ባዩ ወንድማችን በቡርቃ ዝምታው በማር የተለወሰ መርዝ አሰናድቶ አማራና ኦሮሞ ሲተራረድ ዙርያ ከበው በለው! አትማረው! የሚሉትን የአባቱን ሀገር ፖለቲከኞች አስቦ የጻፈው ክታብ መሆኑ ተነግሮ አብቅቶለታል። ተስፋዬ የጦር ሜዳ ዘጋቢነቱን በኢትዮጵያውያን ተምሮ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለው ለሚወጉን ማገልገሉና በደል መፈጸሙ እውነት ነው። ለዚህ ውለታውም የዘመናት ታሪክ ያለውን ድርጅት ያለምንም ክህሎት በአዛዥነት ይዞ እንዳሻው እንዲፈነጭበት ተሰጥቶት ነበር። ቁንጮ ሆኖም የሚበቃውን መረጃ ከክምችቱ እንዲያገኝ ሆኖ መሰየሙንና ክምችቱንም ለፕሮፓጋንዳ መሳርያነት እንዲጠቀምበት ሙሉ መብት ተሰጥቶት እንደነበረም እናውቃለን። ተስፋዬ አገር የለቀቀበትን ጊዜ መለስ ብለን ብንመለከት ለሻዕብያ ያለው ቅርበት ከወያኔ ጋር ለመቀያየም ምክንያቱ መሆኑን መገመት ይቻላል። በተስፋዬ ስራዎች ውስጥ የኤርትራ ጉዳይ ልዩ ቦታ እንዳለውና ከጻፈም ጀግና ብልህና አስተዋይ እንደሚያደርጋቸው የታወቀ ነው።

ስለዚህ ኤርትራዊነት አያደላበትም ወይም ለኤርትራ መረጃ አያቀብልም ብሎ ያለመገመት ከመነሻው የሚገርም ጉዳይ ነው። በቅርብ ድርሰቶቹ ወያኔዎቹን በተመለከተ የአሉባልታ ዶፍ ማውረዱና ይልቁንም ዱላው የጠነከረው ለሻዕብያ ወገንተኛ አይደሉም ባላቸው ላይ መሆኑም የሚያመለክተው ይህንኑ ነው። በማሩ ቃላት አሉባልታዎች ከመገለጻቸው በቀር የፖለቲካ ፋይዳ ያላቸው የማይታወቁ ድብቅ ምስጢሮች የሚባሉ ነገሮችም የሉበትም። ስለዚህ ተሥፋዬ የት እንደሰፈረ የሚሸሽግ አንዳች ነገር ከሌለ ፈቅደን የታለልንለት ድንገት መባነናችንና ምስጢሩ እንደተገኘ ያለማሳወቃችን ለምን በዚህ ጊዜ ሆነ ብለው ለሚጠይቁ ጠርጣሪዎችም የውይይት ማንደርደርያ ቢሆን አይገርምም። የአብርሃ ደስታን ምልከታ እጋራዋለሁ። የተሰጡ አስተያየቶችን አንብቤያለሁ። ጥሩ የሚባል ነገር ሲጻፍ ማመስገን ስህተት ሲኖርም ስህተት እንደመጠቆም የዘር ሀረግ ላይ ተንጠልጥሎ መራገም ውይይታችንን ጤናማ ያደርገዋል የሚል እምነት የለኝም። የቀረበበት ማስረጃ ግን አንዳንድ የዋሆች ለኦሮሞ ካለው ፍቅርና አክብሮት አንጻር የተንገበገበ ሳይሆን የእልቂት ድግሳችንን እያጧጧፈ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ያደርጋል ብዬ አምናለሁ።

Wednesday, October 23, 2013

ብረታ ብረት ኮርፖሬሽንና ሚድሮክን ጨምሮ 20 ድርጅቶች እንዳይፈተሹ ያደረጉ ከፍተኛ የሙስና ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ



-አቶ መላኩ ፈንታ የሦስት ልጆች እናትን አፋተው አግብተዋል ተባለ
-አቶ ጌቱ ገለቴን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌሉበት ክሳቸው ተሰማ
በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ከግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. መጀመሪያ ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ነሐሴ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ክስ ተመሥርቶባቸዋል የተባሉት
ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች፣ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና ሚድሮክን ጨምሮ 20 ድርጅቶች ከውጭ ዕቃ ሲያስመጡ እንዳይፈተሹ አድርገዋል በሚልና በተለያዩ የሙስና ድርጊቶች የተካተቱበት የክስ ቻርጅ፣ ጥቅምት 11 እና 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ከአንድ ወር ከ15 ቀናት ቆይታ በኋላ ተነበበላቸው፡፡
ክሱን የመሠረተው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ሲሆን፣ በተለያዩ ሦስት የክስ መዝገቦች በድምሩ በ55 ተጠርጣሪዎችና በአምስት ድርጅቶች ላይ ያዘጋጀውን የክስ ቻርጅ፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ አሰምቷል፡፡
የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንደዘረዘረው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ፣ የሕግ ማስከበር ሥራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ የአዳማ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊ አቶ ተመስገን ሥዩም፣ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊና በሚሌና አካባቢው ያሉ ፍተሻ ጣቢያዎች ሥራ አስኪያጅ አቶ እሸቱ ግረፍና የአዳማ ቅርንጫፍ የፍተሻ ክፍል ኃላፊና አጠቃላይ የቅሬታ ቡድን አስተባባሪ አቶ ያለው ቡላ በዋና ወንጀል አድራጊነትና የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን በመምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
እንደ ኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ገለጻ፣ ባለሥልጣናቱና ኃላፊዎቹ በመንግሥትና በሕዝብ በተጣለባቸው ከፍተኛ ኃላፊነት የመንግሥት ግብር እንዲሰበሰብ ማድረግ ሲገባቸው፣ በተቃራኒው በመሥራት የመንግሥት ቀረጥና ታክስ እንዳይከፈል አድርገዋል፡፡ የተከለከሉ ዕቃዎች እንዳይገቡ በፍተሻ የሚለይበት ሥርዓት እንዳይፈጠር አድርገዋል፡፡ ሕገወጥ አስመጭዎች እንዳይጠየቁ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እንዲመቻች በማድረግ ድርጅቶች (አስመጪዎች) ተመርጠው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ አድርገዋል፡፡ የተለያዩ አስመጭዎችና ትራንዚተሮች ሕገወጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጉቦና ተገቢ ያልሆነ ጥቅም የመቀበል፣ የመስጠትና የማቀባበል ወንጀል እንዲፈጽም ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠራቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
ከአቶ መላኩና ከአቶ ገብረዋህድ፣ ለባለሥልጣኑ የሚሌ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅና በሚሌ ቅርንጫፍ ሥር የሚገኙትን የጋላፊ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ የሰመራ ደረቅ ወደብ ጣቢያ፣ የሚሌ የዘመናዊ ማሽን መፈተሻ ጣቢያና የአዋሽ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ እሸቱ ግረፍ ትዕዛዝ ይተላለፍላቸው እንደነበር ክሱ ይገልጻል፡፡
በትዕዛዙ መሠረት ከ2003 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ የትራንዚት ፈቃድ ተሰጥቷቸው በጂቡቲ ወደብ በኩል ከውጭ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ሚሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሲደርሱ በአቶ እሸቱ ግረፍ አማካይነት ተመርጠው ሳይፈተሹ ‹‹ተፈትሸዋል›› የሚል ማረጋገጫ እየተሰጣቸው ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውን፣ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡
ሳይፈተሹ ‹‹ተፈትሸዋል›› የሚል ማረጋገጫ እየተሰጣቸው ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ያስገቡት ድርጅቶች ኒያላ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያና መለዋወጫ ዕቃ አስመጪ፣ ፔትራም፣ ሞኤንኮ፣ ጌታስ ትሬዲንግ፣ አልሳም፣ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ አይካ አዲስ (የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ)፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ፣ ሆላንድ ካርስ (ከስሮ ተዘግቷል)፣ ቶታል ኢትዮጵያ፣ ሚድሮክ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን፣ ድሬ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ፣ ኢትዮ ሌዘር፣ ኢትዮ ቆዳ ፋብሪካ፣ ባሰፋ ትሬዲንግ፣ ነፃ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ጌታስ ኢንተርናሽናልና ኮሜት ትሬዲንግ መሆናቸው በክሱ ተዘርዝረዋል፡፡
አቶ ጌቱ ገለቴ የጌታስ ትሬዲንግና ጌታስ ኢንተርናሽናል ባለቤት (በሌሉበት)፣ አቶ ገብረ ሥላሴ ገብሬ (የኮሜት ትሬዲንግ ሀውስ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ) አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር (የባስፋና ነፃ ትሬዲንግ ባለቤት)፣ አቶ ከተማ ከበደ (የኬኬ ድርጅት ባለቤት) ከነድርጅቶቻቸው በክሱ ውስጥ የተካተቱ ሲሆኑ፣ ከላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶችም ሆኑ ባለቤቶቻቸው በክሱ አልተካተቱም፡፡ አቶ ጌቱ ገለቴ ከአቶ መላኩና ከአቶ ገብረዋህድ ጋር ባላቸው ግንኙነት ወደ አገር ውስጥ የተለያዩ ዕቃዎችን ሲያስገቡ በሕግ አግባብ መሠረት ተፈትሸው ተገቢውን ታክስና ቀረጥ መክፈል ሲገባቸው፣ በሕገወጥ ትዕዛዝ አማካይነት ዕቃዎቻቸው ሳይፈተሹ ‹‹ተፈትሸዋል›› የሚል የማረጋገጫ ኢንቮይስ ተስተናግደው ሕገወጥ ጥቅም ማግኘታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በተነበበው ክስ ውስጥ 31 ተጠርጣሪዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ባጠቃላይ 28 ክሶች ቀርበዋል፡፡ በክሶቹ ውስጥ በዝርዝር በተገለጹት በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎችና ከ20 በላይ የሚሆኑ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችና ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎችና ከውጭ ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር በተለያዩ ቦታዎች ጉቦ የተቀበሉ መሆኑን፣ በፍተሻ ወቅት እንደተፈተሸ አድርጎ በማሳለፍና የተሳሳተ ሰነድ በመጠቀም በመንግሥትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ፣ የመንግሥትን ሥራ በማያመች መልኩ በመምራትና በዋና ወንጀል አድራጊነትና የሙስና ወንጀል በመፈጸም ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡
በሦስቱም የክስ መዝገቦች ላይ ተጠርጥረው ስማቸው የተጠቀሰው አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. በተነበቡ ሁለት የክስ መዝገቦች ላይም የመጀመሪያው ተጠሪ ሆነው ተከሰዋል፡፡ 18 ሰዎች የተካተቱበት የክስ መዝገብ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ሹማምንትና ኃላፊዎች የተካተቱበት ሲሆን አቶ አመሐ ዓባይ፣ አቶ ነብዩ ሳሙኤል፣ አቶ አስፋው ወሰን አለነ፣ አቶ ተስፋዬ መርጊያ፣ አቶ አማረ ገብረወልድ፣ አቶ መስፍን አህመድ፣ አቶ ደሜ አበራ፣ አቶ ተስፋዬ ቤተና ወ/ሮ ሃይማኖት ዓለሙ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በክሱ የተካተቱ ቢሆንም ክሱ የተሰማው በሌሉበት ነው፡፡
አቶ መላኩ፣ አቶ ገብረዋህድ፣ የባለሥልጣኑ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላቸው በየነና በሌሉበት የተከሰሱት የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ እንደገለጸው፣ ከታክስ ገቢ ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ማስተናገድ የሚያስችሉ አዋጆችና አጣሪ ኮሚቴ ቢኖርም፣ አቶ መላኩ በአዋጁ መሠረት የቀረቡ አቤቱታዎችን እንደገና መከለስ የሚያስችል ሕገወጥ ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡ ሕገወጥ ድርጊቱን መፈጸም የሚያስችል መመርያም አውጥተዋል፡፡ በዚህም መሠረት ሀዋስ አግሮ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለ ድርጅት በሕገወጡ መመርያ መሠረት አቤቱታ እንዲያቀርብ በማድረግና ሕገወጡ ኮሚቴ እንዲያየው በማድረግ ከ22.3 ሚሊዮን ብር በላይ መንግሥት እንዲያጣ ማድረጋቸውን ክሱ ይተነትናል፡፡ አቶ ገብረዋህድም ለዚሁ ድርጅት በሕገወጥ መንገድ ድጋፍ በማድረግና ካልተያዙት ተጠርጣሪዎች (የሕገወጥ ኮሚቴ አባላት ናቸው) ጋር በመተባበር የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ሼባ ስቲል ሚልስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የንግድ ትርፍ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና  ከተከፋዩ ሒሳብ የሚቀነስ ግብር ኦዲት ተደርጎ 101.4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ከተወሰነበት በኋላ፣ ለሕገወጡ ኮሚቴ አቤቱታ እንዲያቀርብ በማድረግ፣ አቶ ገብረዋህድ እንዳይከፍል ማድረጋቸውን ክሱ ይጠቅሳል፡፡ ለሌሎችም በርካታ ድርጅቶች ላይ ግብር እንዳይሰበሰብ ማድረጋቸውን ክሱ በዝርዝር ያብራራል፡፡
17 ክሶችን በያዘው መዝገብ ውስጥ አቶ መላኩ ፈንታ የሦስት ሕፃናት እናትን ከትዳራቸው በማፋታት እንዳገቧት የሚገልጽ ክስም ተካቷል፡፡ የዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያብራራው፣ አቶ ደምሴ ዓለማየሁና ወ/ሮ መቅደስ ለማ ከኅዳር 8 ቀን 1993 ዓ.ም. ጀምሮ ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ ሦስት የዘጠኝ፣ የአምስትና የሁለት ዓመት ሕፃናትንም አፍርተዋል፡፡ ወ/ሮ መቅስና አቶ ደምሴ ሳንክቹሪ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለ ድርጅት አቋቁመው እስከ 2001 ዓ.ም. ድረስ ሠርተዋል፡፡ በ2001 ዓ.ም. አቶ ደምሴ ግብር ለመክፈል ሲሄዱ 144,000 ብር እንዲከፍሉ ይነገራቸዋል፡፡ ግብሩ የበዛባቸው አቶ ደምሴ ቅድሚያ ይከፍሉና ለምሥራቅ አዲስ አበባ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡ ጉዳዩ መፍትሔ ሳያገኝ ከአንድ ዓመት በላይ በመፍጀቱ ባለቤታቸው ወ/ሮ መቅደስ ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ያቀረቡትን አቤቱታ ለአቶ መላኩ በግልባጭ ሊሰጡ ወደ ቢሮአቸው ያመራሉ፡፡ አቶ መላኩ በወቅቱ የነበራቸውን ሥልጣን መከታ በማድረግ በሚያዝያ ወር 2002 ዓ.ም. አካባቢ ከተገመተባቸው ግብር ላይ 100 ሺሕ ብር እንዲቀነስ ማድረጋቸውንና ወ/ሮ መቅደስን ማማገጥ መጀመራቸውን፣ በተለያዩ ጊዜያት በሾፌራቸው አማካይነት ወደ ባህር ዳር በመውሰድ ሰመርላንድ ሆቴል ለሦስትና ለሰባት ቀናት መቆየታቸውን፣ እንዲሁም በመንግሥት ተሽከርካሪና ነዳጅ በመጠቀም ሴትየዋን ሲያዝናኑ መክረማቸውን ክሱ ዘርዝሯል፡፡ በመጨረሻም ወ/ሮ መቅደስን ከትዳራቸው በማፋታትና ልጆቻቸውን ያለአሳዳጊ በመበተን አግብተዋቸዋል፡፡ በመሆኑም በፈጸሙት የማፋታት፣ ልጆችን ያለ አሳዳጊ እንዲቀሩ የማድረግና በፈጸሙት የሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡
በአጠቃላይ የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ሹማመንትና ኃላፊዎች ግብር እንዳይሰበስብ በማድረግ፣ በመቀነስ፣ ፍተሻ እንዳይኖር በማድረግ፣ በተለያየ ቦታ መጠኑ የተለያየ ጉቦ በመቀበልና ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በመጨረሻ ያነበበውና 93 ክሶችን ያካተተው የክስ መዝገብም ከአቶ መላኩ፣ ከአቶ ገብረዋህድና ባለቤታቸው ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ በተጨማሪ፣ ምክትል ዋና ዓቃቤ ሕግ የነበሩትን አቶ መርክነህ ዓለማየሁ፣ አቶ አስመላሽ ወልደማርያም፣ አቶ ስማቸው ከበደ (የኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ባለቤት)፣ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአገር ውስጥ ኃላፊ የነበሩትን አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤልን ጨምሮ በድምሩ 24 ተከሳሾችን በክሱ አካቷል፡፡
አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ በአቶ ከተማ ከበደ ላይ ቀርቦ የነበረን የአራጣ ማበደር ወንጀል ክስ በማቋረጥ፣ አቶ በላቸው ደግሞ አቶ ስማቸው ከበደ ለኢንተርኮንቴንታል ሆቴል ከቀረጥ ነፃ የ9.9 ሚሊዮን ብር ዕቃዎች ከውጭ አስገብተው ለተፈለገው ዓላማ አለማዋላቸው እየታወቀ በድጋሚ እንዲቆጠር፣ ድርጅቱ በምርመራ እንዳይጣራና በወንጀል እንዳይከሰስ ሁኔታዎችን በማመቻቸታቸው፣ የመንግሥትን ሥራ በማያመች ሁኔታ በመሥራት የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ይተነትናል፡፡ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩም ከአቶ መላኩና ከአቶ ገብረዋህድ ጋር በመመሳጠር ተከሰው ተመሥርቶባቸው የነበረውን ክስ እንዲቋረጥላቸው ማድረጋቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡
አቶ ገብረዋህድ ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ሃይማኖት ጋር በጋራ በቀረበባቸው ክስ፣ አቶ ገብረዋህድ ከ1978 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ በመንግሥት ሠራተኝነታቸው ከ247 ብር እስከ 5,700 ብር ይከፈላቸው ነበር፡፡ ኮሎኔል ሃይማኖት ደግሞ ከ1989 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ በመከላከያ ተቀጥረው ሲሠሩ ከ790 ብር እስከ 2,145 ብር ደመወዝ ይከፈላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በተደረገ ብርበራ በተለያዩ ባንኮች የተቀመጠ ከፍተኛ ገንዘብ፣ ተሽከርካሪዎች፣ መቀሌና አዲስ አበባ ውስጥ ቤቶች፣ የተለያዩ አገሮች ገንዘቦች፣ ሰባት ሽጉጥና ሁለት ታጣፊ ክላሽ መገኘቱን ክሱ ይዘረዝራል፡፡ አቶ መርክነህ ዓለማየሁም ምርመራ እንዲቋረጥ፣ ከአቶ ባህሩ አብርሃ (ብስራት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር) 100 ሺሕ ብር ጉቦ መቀበልና ከተከሰሱበት ክስ በነፃ በማሰናበት፣ ከ1987 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ ከ2,535 ብር እስከ 10,234 ብር ያገኙ የነበረ ቢሆንም፣ ከደመወዛቸው ጋር የማይመጣጠን ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ አካብተው በመገኘታቸውና ሌሎችም ክሶች ተመሥርተውባቸዋል፡፡
በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል ከግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. እስከ የካቲት ወር 2005 ዓ.ም. ድረስ ይከፈላቸው የነበረው ደመወዝ ከ1,600 እስከ 6,000 ብር ደርሶ እንደነበር ክሱ ጠቅሶ፣ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን በ175 ካሬ ሜትር ላይ ባለሦስት ፎቅ ቤት ገንብተው በ50 ሺሕ ብር ማከራየታቸውን፣ የመንግሥት ይዞታ የነበረና የሊዝ ግምቱ 2.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 375 ካሬ ሜትር ቦታ በሕገወጥ መንገድ አጥረው ቤት የገነቡበት በመሆኑ፣ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘትና ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ ይገልጻል፡፡ ባለሰደፍ አንድ ክላሽ፣ ስታር ሽጉጥና አንድ የጭስ ቦምብ ያለፈቃድ ይዘው በመገኘታቸው ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባቸውም ዓቃቤ ሕግ በክሱ አክሏል፡፡
በክስ መዝገቡ በተካተቱ 24 ተከሳሾች ላይ ዝርዝር ተደጋጋሚ ክሶች በተናጠልና በጋራ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ አቅርቧል፡፡
ነሐሴ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. መሥርቻለሁ ያለውን ክስ ከ40 ቀናት ቆይታ በኋላ ጥቅምት 11 እና 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አቅርቦ ያሰማው የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ፣ ባቀረበው ክስ ላይ ከተከሳሾች ተቃውሞ ቀርቦበታል፡፡ የተቃውሞው ምክንያትም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ (20) ንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት አንድ ተከሳሽ ክስ ሲመሠረትበት፣ ክሱና የማስረጃ ዝርዝር አብሮ እንዲሰጠው የተደነገገው ሕገ መንግሥታዊ መብት በኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ተሟልቶ ባለመቅረቡ ነው፡፡ በመሆኑም የተከሳሽ ጠበቆች ከፍተኛ ተቃውሞ በማቅረብ በዕለቱ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ ሌላው ያነሱት ጥያቄ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸው ነው፡፡ ተጠርጣሪዎች በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤት የወሰነውን ትዕዛዝ በመተላለፍ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች ወደ ፖሊስ ማቆያ ቦታ መወሰዳቸውን በመግለጽም ጠበቆች ተቃውመዋል፡፡
ሌላው በራሳቸው ጠበቆች ባይሆንም በአቶ ከተማ ከበደ ጠበቃ የተነሳው ተቃውሞ፣ የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ማየት የሚችለው ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንጂ የሁለተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አለመሆኑን በመጥቀስ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ በጠበቆች አስተያየት ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ሲያዘው፣ የማስረጃ ሰነድ ያላያያዘው ከቅድመ ክስ መግለጫ ጋር የሚቀርብ መስሎት በሌላ ቀጠሮ ለማቅረብ መሆኑን አስረድቷል፡፡ የዋስትና መብት ጥያቄን በሚመለከት የአብዛኛዎቹ ክስ ከአሥር ዓመት በላይ የሚያሳስር አንቀጽ መጠቀሱን ጠቁሞ፣ ዋስትና እንደሚከለክል ተናግሯል፡፡ የሦስት ተከሳሾችን የዋስትና ጥያቄም እንደማይቃወም ገልጾ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠውም ብይን ጠበቆች ያነሱት ከክሱ ጋር የሰነድ ማስረጃ መቅረብ እንደነበረበትና ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን በመጠቆም፣ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. እንዲያቀርብ አዟል፡፡ ዋስትናን በሚመለከት ተጠርጣሪ ተከሳሾች አቶ ሰመረ ንጉሤ፣ አቶ ማርሸት ተስፋዬና አቶ ዳዊት መኮንን እያንዳንዳቸው 15 ሺሕ ብር አስይዘው እንዲለቀቁ አዟል፡፡ በማረሚያ ቤት ይቆዩ የተባሉ ተጠርጣሪዎችም በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ በማዘዝ ለጥቅምት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በአቶ መላኩ ፈንታ የፍርድ ቤት የሥልጣን ጉዳይ ምላሽ ሳይሰጥ ፍርድ ቤቱ አልፎታል፡፡ የዋስትና መብት የጠየቁ ተከሳሾች ቢኖሩም፣ የተጠቀሰባቸው የሕግ አንቀጽ ዋስትና እንደሚከለክል በመግለጽ አልፎታል፡፡
በመጨረሻ ፍርድ ቤቱ ያልተያዙ ተከሳሾችን የኮሚሽኑ ሰርቪላንስ ድጋፍ ሰጭ ቡድን በቁጥጥር ሥር አውሎ እንዲያቀርባቸው አዟል፡፡ እስከ መስከረም 2006 ዓ.ም. አጋማሽ ድረስ የጊዜ ቀጠሮ ሲጠየቅባቸው የነበሩት የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ ምሕረት አብርሃም ላይ ግብር ባለመክፈል ወንጀልና የተሳሳተ ሰነድ በማቅረብ ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡
ethiopian reporter

ህወሓትና ስብሃት! Abraha Desta



አንድ የድሮ የህወሓት ታጋይ ነው። አሁንም መከላከያ (ሰሜን ዕዝ) ነው የሚሰራው። ስለ ህወሓት ወቅታዊ ሁኔታ ሲጀነጅነን ነበር። የህወሓት ‘ጥሩነት’ ይሰብከናል። ስብሃት ነጋ የድሮ ታጋዮች እያሰባሰበ ‘ህወሓት የማዳን ዘመቻ’ መጀመሩ ነገረን።
ስብሃት እንዴት ህወሓትን እንደሚያድናት ብዙ ጥያቄዎች ሰነዘንርለት። በመሃል አቋርጦ … “ኤጭ ስብሃት’ኮ ግን እባብ ነው። በ 70ዓም በሽሬ ገበሬዎች (ገባር ሽረ) ዶሚኔት (dominate) ተደርገናል በሚል ሰበብ ሆን ብሎ ‘ሕንፍሽፍሽ’ (ዉስጣዊ ብጥብጥ) በመፍጠር ህወሓት የግሉ (የቤተሰቡ) ያደረገ ሰው ነው” አለን።
የድሮ ታጋዩ በዉስጡ ሐዘን እንዳለ ከስሜቱ ይነበባል። ይቺ የሽሬ ገበሬዎች የምትለዋን ነገር ራሳቸው ህወሓቶች ባዘጋጁት ። “ሙሴ” የተሰኘ ፊልም በደንብ ይንፀባረቃል። በፊልሙ ገበሬዎቹ ‘የሙሁራን ፎብያ’ እንደነበራቸውና ‘ሙሁራን ዶሚኔት አድርገውናል’ ብለው ማመፃቸው፣ በኋላም መሸነፋቸው ያሳያል።
እውነታው ግን ብጥብጡ (ሕንፍሽፍሹ) ያቀናበሩት እነ ስብሃት ነበሩ። ምክንያታቸውም በሽሬ ገበሬዎች (ገባር ሽረ) ዶሚኔት ተደርገናል የሚል ነበር። እነ ስብሃት ‘እኛ ሙህራን ነን። የፓርቲው አመራር በሙሁራን እጅ መሆን አለበት’ በሚል ሰበብ ፓርቲው ተቆጣጠሩት። በዚህ መንገድ የሽሬ ገበሬዎች ከቁልፍ ቦታዎች ተወገዱ። ገባር ሽሬ በጦርነቶች (ግንባር) እንዲዋጋ ሆነ፤ የነ ስብሃት ነጋ ቤተሰብም ወደ መሪነት መጣ። ሽሬዎች በጦርነቱ አለቁ። ስብሃቶች መሪዎች ሁነው ቤተመንግስቱ ተቆጣጠሩ።
አሁን እስቲ ስብሃት ነጋ ህወሓት ማዳን አለብን ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ይሆን? የሚወገዱስ እነማን ይሆኑ? ግን አትድከሙ በአሁኑ ሰዓት ህወሓትን ማዳን አይቻልም። ግን ህወሓት ተወልዶ እስኪያድግ ድረስ ግዜ የወሰደበትን ያህል ሞቶ እስኪቀበር ድረስም ግዜ ይወስዳል።
(ለማንኛውም በሐየሎም አርአያ የትግል ታሪክ የሚያጠነጥን መፅሐፍ በቅርቡ ይወጣል። ከመፅሓፉ የምናገኘው ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ።)
It is so!!!Abraha Desta

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለ7 ሰዓታት በመብራት እጦት ሥራ አቁሞ ነበር

  

October 23rd, 2013

 October 23rd, 2013
black_lion_hospital
የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት እንዴት ይጠየቃል? ከመሐመድ አሊ መሀመድ የገዥው ፓርቲ ልሳን እንደሆነ የሚታወቀው ፋና FM ሬዲዮ በቀትር የዜና እወጃው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከትናንት 10 ሠዓት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የሆስፒታሉ ታክሚዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አረዳን፡፡ ሬዲዮው የሆስፒታሉ ዲዝል ጄኔሬተርም

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8601

ስብሃት ነጋ በመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ተገለጸ !



(ዘ-ሐበሻ) አዛውንቱ የሕወሐት መስራች ስብሃት ነጋ በመርሳት በሽታ (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ለአዛውንቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገለጹ። ምንጮች በተለያዩ ሁኔታዎች እንደገለጹት ስብሃት በየመድረኩ አንድ ጊዜ የተናገሩትን በሌላኛው ጊዜ የማይደግሙት፣ ወይዘሮ አዜብን ጨምሮ ከተለያዩ የኢሕአዴግ ሰዎች ጋር የሚላተሙት ወይም ጥያቄ ሲጠየቁ አላስታውስም የሚሉት የዳመንሺያ ተጠቂ በመሆናቸው መሆኑን የህክምና ባለሙያዎችን ጥናት ያሰባሰቡት እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል። 
ስማቸው እንዳይገለጽ የሚፈልጉት እነዚሁ ምንጮች አቶ መለስ በሞቱበት ወቅት 33 ጀነራሎች ከተሾሙ በኋላ መሾማቸውን በሰሞኑ ቃለምልልሳቸው ላይ አላውቅም/አላስታውስም/ ማለታቸውንና ሌሎችንም በመጥቀስ፤ እነዚሁ ምንጮች ከህክምና ባለሙያዎች እንዳገኙት ጥቆማ “የመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) ምንድን ነው?” የሚለውን ሲያብራሩ፦
“ከባድ  የመርሳት    ችግር  ይህ   ነው   የሚባል   በሽታ     አይደለም።   ይልቁንም     አእምሮን  በሚያውኩ የተለያዩ እክሎች   ምክንያት     የሚፈጠሩ   የህመም   ምልክቶች አጠቃላይ  መገለጫ     ነው፡፡  የከባድ    የመርሳት  ችግር ተጠቂዎች    አእምሯዊ    አተገባበራቸው  እጅጉን    በመስተጓጎሉ  የእለት     ተለት     ተግባራቸውና    ከሰዎች ጋር    ያላቸውን    ግንኙነት  ይጎዳል፡፡    እንዲሁም ግልፍተኝነት፣   የቀን   ቅዠት እና     በሌለ  ነገር    ማመን የመሳሰሉት   ሁኔታዎች     ስለሚያጋጥሟቸው  ለከባድ    ባህሪያዊ   ችግሮች   ሊዳረጉና     ማንነታቸውን   ሊያጡ  ይችላሉ።  የማስታወስ   ችሎታ    መቀነስ     የዚህ   ህመም    የተለመደ  ምልክት ቢሆንም የማስታወስ ችሎታው የቀነሰ ሰው በሙሉ የከባድ የመርሳት ችግር ተጠቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡” ይላሉ።
እነዚህ ችግሮች በስብሃት ላይ በየጊዜው እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት እነዚሁ የቅርብ ምንጮች ”በሽታውን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ሲያብራሩም “ለከባድ የመርሳት ችግር የመጋለጥ እድልን ከፍ ሊያደርጉ  ከሚችሉ ሁኔታዎች ውስጥ ቀጥሎ የተጠቀሱት ይገኙበታል፡-
• ከዘር የመጣ ከሆነ
• በአንጎል ውስጥ የሚከሰቱ እክሎች ካሉ
• የደም ዝውውርንና ወደ አንጎል የሚያመራውን ጤነኛ የደም ዝውውርን የሚያውክ በሽታ ከተከሰተ
• የኤችአይቪ ቫይረስ በደም ውስጥ መኖር (በተለይ ኤችአይቪ በደሙ ያለበት ሰው የኤድስ ታማሚነት ደረጃ ከደረሰ)” በማለት ይጠቅሳሉ።
የህክምና ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ የሚገልጹት እነዚሁ ምንጮች “የከባድ መርሳት ችግር ምልክቶች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ሲገልጹም “አብዛኛውን ጊዜ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ከባድ የመርሳት ችግር ቀዳሚና በጉልህ የሚታይ ምልክት ነው፡፡
የሚከተሉትም ሌሎች ምልክቶች ናቸው፡-
• የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ማስታወስ ማዳገት • በደንብ የሚያውቋቸውን ሰዎችና ቦታዎች መዘንጋት
• ሀሳብን ለመግለጽና ቁሶችን በስማቸው ለመጥራት ትክክለኛ ቃላትን ለማግኘት በእጅጉ መቸገር
• የሂሳብ ስሌቶችን መስራት ማዳገት
• እቅድ ለማውጣትና ስራን ለመፈጸም መቸገር
• ለመወሰን መቸገር፥ ለምሳሌ በአጣዳፊና አደገኛ ሁኔታ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባ አለማወቅ
• የራስን ባህሪይና ስሜት ለመቆጣጠር መቸገር፤ለምሳሌ ግልፍተኛ ወይም ቁጡ መሆን
• አዘውትሮ መደበት
• ራስን አለመንከባከብ፤ ለምሳሌ የግል ንጽህንናን አለመጠበቅ” ናቸው ይላሉ።
“በአንድ ሰው ላይ ቀደም ሲል የተገለጹት ምልክቶች የሚታዩና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ የሚንጸባረቁ ከሆነ ያለምንም ማመንታት በቶሎ ወደ ሆስፒታሎችና የጤና ማእከላት መሄድና የባለሙያ የህክምና አገልግሎትና እንክብካቤ ማግኘት ይኖርበታል፡፡” ሲሉ የባለሙያዎችን ምክር የሚጠቅሱት እነዚሁ ምንጮች  በሽታውን እንዴት ማስታመም ይቻላል? የሚለውን ሲገልጹ ደግሞ
“የታዘዘላቸውን ህክምናና የሀኪም ምክር በአግባቡ እንዲከታተሉ ማገዝ፦
ከባድ የመርሳት ችግር ካልታከመ ወደከፋ ደረጃ ሊደርስ ይችላል። ሆኖም ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች የሀኪምን ምክር በመከታተልና የታዘዘላቸውን ህክምና በአግባቡ በመከታተል ጤናማ ህይወት መምራት ይችላሉ። ለዚህም የጓደኛና የቤተሰብ ድጋፍ ወሳኝ ነው።
• ከባድ የመርሳት ችግር ላለባቸው ሰዎች ድጋፍ ማድረግ፦
- ከባድ የመርሳት ችግር ያለባቸው ሰዎች ራሳችውን ወይም ሌሎችን ለጉዳት እንዳይዳርጉ
- ለመከላከል ከቤተሰብና ከጓደኞች ቋሚ እንክብካቤና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ለዕለት ተዕለት ተግባሮች ለምሳሌ ሲመገቡ፣ ሲታጠቡም ሆነ ሲለብሱ እርዳታ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡
- በመኖሪያ አካባቢ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ማሸሽ፦
- አደጋ ሊያስከትሉባቸው የሚችሉ ነገሮችን ከፊታቸው ዞር ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ ለምሳሌ እንደስለት ፣ አደገኛ ኬሚካሎች፣ ሹል ነገሮችንና መሳሪያዎችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
• ሊረብሹ የሚችሉ ሁኔታዎችን መቀነስ፦
በአንዳንድ ድርጊቶች ወይም በሚረብሹ ድምጾች ምክንያት ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ሊፈሩና ግራ ሊጋቡ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም አላስፈላጊ ድርጊቶችን ማስቆም፣ ሊጠይቁ የሚመጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ ቴሌቪዥንና ሌሎች የሚረብሹ ድምጾችን መቀነስ አስፈላጊ ነው፡፡
• ከባድ የመርሳት ችግር ያለባቸው ሰዎች እንዲዝናኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፦
የተለመዱ የመዝናኛ ተግባራቶቻቸውን መፈጸም   እንዲቀጥሉ ሊበረታቱ ይገባል፡፡ ለምሳሌ፤ የእጅ ስራዎች፣ ጨዋታ፣ ሙዚቃ የመሳሰሉት አዕምሮን ለማነቃቃትና ስሜታቸውን ሊያሻሽሉ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡” ይላሉ።
እነዚሁ የቅርብ ሰዎች ምናልባት አቶ ስብሃት ይህን ችግር እንዳለባቸው በሃኪም አልተነገራቸው ከሆነ በአስቸኳይ ህክምናውን እንዲከታተሉ ይመክራሉ።
source:(ዘ-ሐበሻ)

Tuesday, October 22, 2013

ተገዥነታችን ለሕዝብና ለሕግ እንጅ ለአምባገነኖች ማስፈራሪያ አይደለም!!! – ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገራችን ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና ፍትሃዊነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየታገለ ይገኛል፡፡ በትግሉ ውስጥም ፓርቲያችን የተጋረጡበትን ፈተናዎች እየተወጣና የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈለ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት እያረጋገጠም ነው፡፡

ፓርቲያችን በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አደረጃጀት በመጠቀምና ሕዝቡን በማሳተፍ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሰላማዊ ትግል ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት አካሂዷል፡፡ ወደፊትም ይህንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ኢህአዴግና መሪዎቹ መንግስት እንደመሆናቸው መጠን በሰላማዊ መንገድ ለምንንቀሳቀስ ፓርቲዎች ድጋፍና ትብብር ማድረግ ሃላፊነታቸው ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀስን ያለን ፓርቲዎችን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ልክ ከዚህ በፊት ሲያደርጉት እንደነበረው ባልዋልንበት ዋሉ፣ ባልተገኘንበት ተገኙ… በማለት ህዝባዊ መሰረታችን ጥርጣሬ ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ አባባላችን ጥሩ ማስረጃ የሚሆነን ባለፈው ሳምንት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴችንን እሳቸው ከፈለጉት አካል ጋር በማገናኘት ስም ለማጥፋት መሞከራቸው ነው፡፡

አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ መንግስት የሆነው ፓርቲያቸው ለሚነሱ ሀገራዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄ አቅራቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት የምናውቀውና የነበረ አሮጌ መንገድ ነው፡፡

ፓርቲያችን ህዝባዊ ንቅናቄ ያደረገው ህጋዊ አግባቡን ጠብቆና የራሱን አጀንዳ ቀርፆ ነው፡፡ ጠ/ሚንስትሩ የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፤ የሻዕቢያ መልክት አድራሾች ናቸው ወዘተ ያሉበት ድፍረት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን ጠፍቷቸው ሳይሆን ሆን ብለውና አቅደው ስም ለማጥፋት፣ ህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ ለመጫር በመፈለጋቸው ብቻ ነው፡፡ እኛ ተላላኪነታችን ለኢትዮጵያ ህዝብና ይጠቅማል ብለን ለቀረፅነው የፖለቲካ ፕሮግራም ብቻ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱን ስም ማጉደፍም ፓርቲያችን በቸልታ አይመለከተውም፡፡ ስለዚህ አቶ ኃይለማርያም ከባለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አጥብቀን እንመክራለን፡፡

የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ በተመለከተ ፓርቲችን ያለው አቋም ግልፅ ሲሆን አሁንም ጥያቄያችው በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ መመለስ፤ ዜጎች የመብት ጥያቄ ሲያነሱ መፈረጁ ይቁም፤ ካላግባብ የሃማኖት ነፃነት ጥያቄ ስላነሱ ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ዜጎች ባስቸኳይ ይፈቱ የሚል ነው፡፡ በተጨማሪም ስርዓቱ ካላግባብ ያሰራቸው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ባስቸኳይ ይፈቱ ብለን እንጠይቃለን፡፡ ወደፊትም ይህንን ጥቄያችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ እኛ እያልን ያለነው ከኢ-ፍትሃዊነት ጋር አንደራደርም፤ አንቀበለውም ነው፡፡ ስለዚህ ፓቲያችንን ከሙስሊም ወገኖች ጥያቄ ጋር በማያያዝ ትርፍ ፍለጋ መሯሯጥ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡

አቶ ኃይለማርያም በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ የጨፈለቀው ንግግራቸው ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ ነው፡፡ በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ተልካሻ ሰበብ የዜጎችን መብት መንጠቅ አይቻልም፡፡ በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጅ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም በማለት መዛት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ድርጊት ነው፡፡

ስለዚህ ፓርቲያችን አንድነት አሁንም ተገዥነቱን ለህዝቡና ለህግ አድርጎ በአምባገነኖች ዛቻ ሳይበረግግ፤ ዘር፣ ፆታ፣ ሀይማኖት፣ ቀለም ሳይለይ ዜጎች የሚያነሱት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ፤ የመንግስት በሐይማኖት ጣልቃ ገብነትም እንዲቆም ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያረጋግጣል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲያችን የአፍሪካ መሪዎች ብዙ መፍትሄ ፈላጊ ችግሮች ባሉባት አፍሪካ ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም መከሰስም የለብንም በሚል የያዙት አቋም አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ሕግ እየጣሱ በህግ አለመጠየቅ አይቻልም፡፡ ዘር እያጠፉ ያለመታሰር መብት አይኖርም፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ የመሆን መብት የለውም፡፡

የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው ማለት ያለባቸው አይሲሲ ሊከስሰን አይገባም ሳይሆን የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ ነው፡፡ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ መጣር ነው፡፡ መሳሪያና ጉልበት የችግሮች መፍቻ መሆናቸው እንዲያበቃ የሰለጠነ መንገድ መከተል ነው፡፡ የሚያስከስሳቸውና የሚያሳስራቸው ስራቸው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፓርቲያችን አሁንም ሆነ ወደፊት በዜጎቻቸው ላይ ግፍና ሰቆቃ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በተመለከተ የሚያራምዱት የአትክሰሱን አቋም ፓርቲያችን አይቀበለውም፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)UDJ
   abugida

ወያኔና አሸባሪነት ምንና ምን ናቸው

የወያኔ ጉጅሌ ሰሞኑን የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ በእጅጉ ሊያስቅ የሚችል ቧልት ላይ ተጠምዷል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሳይቀር ህብረተሰቡን በየተቋሙና በየመኖሪያው እየሰበሰበ ስለሽብርተኝነት ማብራሪያና ገለፃ በመስጠት ዜማ ላይ ተጠምዷል።

የወያኔ የሽብረተኝነት ገለፃ ዘመቻ ሚስጥር ደግሞ ብዙ ምርምር የሚሻ አይደለም። የሀገራችን ሰዎች ዶሮ ጭራ ልታወጣው የምትችል የሚሉት አይነት ሚስጥር ነው። አላማው ነጻነት አማረኝ፣ እምቢ ዘረኝነት እና ቢያንስ መሰረታዊ ሰበአዊ መብቴ ይገባኛል በማለት መብቱን እየጠየቀ የመጣው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ታይቶታል።

የማእበሉ የመጀመሪያ ንቅናቄዎች ከወዲያ ወዲህ መታየት ጀምረዋል። የገለፀው ሽርጉድ ዋና አላማ ይህ መብቱን የሚጠይቅና አጎንብሶ መኖር የሰለቸው ህዝብ ለመብቴ የማደርገውን ትግል ሽብርተኛ ያስብለኛል ብሎ እንዲፈራና ይበልጥ እንዲያጎነብስ መሆኑ ነው። ይህን ደግሞ ህዝቡ አውቆታል። ሰሞኑን በአለምያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለገለፃው ለመጡ ካድሬዎች የሰጧቸው አጸፋዊ ገለጻ ይህንኑ ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያ እና የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ


ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ጣቢያ ሶስት የተለመዱ ስፍራዎች አሉ።አንደኛው ሰዎች ያለመብራት የሚታሰሩበት እና ጭለማ ቤት የሚባለው ነው።ሁለተኛው ለግርፋት የተመቻቸው ጣውላ ቤት የሚባለው ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ በተሻለ ደረጃ የሚታሰሩበት እና ከዚሁ የተነሳ በሌስሊ ኣባባል «ሸራተን» ተብሎ የሚታወቀው ነው።
self
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እስረኞችን ይገርፋሉ፥ ይደበድባሉ በተለያየ መንገድ እያሰቃያሉ በማለት ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች አጋለጠ።ሑዩማን ራትስ ዋች ዛሬ ባወጣዉ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች በተለይ አዲስ አበባ ዉስጥ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራዉ የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚደርጉት የምርመራ ዓይነትና ሒደት ሕገ ወጥ ብቻም ሳይሆን ሰብዓዊነትም የጎደለው ነው።የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዱ ዘንድም ሂዩማን ራይትስ ዎች አሳስበዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን የሑዩማን ራይትስ ዋችን ወቀሳና ጥያቄ አጣጥለዉታል።ጅዓፈር ዓሊ ሁለቱንም ወገኖች አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለን።
በዚሁ ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ እስር ቤት የሚታሰሩት እና የሚመረመሩት ደግሞ በሪፖርቱ መሰረት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አባላት እና ደጋፌዎችን ጨምሮ ጋዜጠኞች የተቃውሞ ሰልፍ ኣደራጆች እንዲሁም የእምነት እና የብሄር ተቐማት ደጋፌዎችም ጭምር ናቸው።
0,,16530143_404,00
በማዕከላዊ እስር ቤት የሚታየው የእስረኞች እያያዝም ሆነ የምርመራው ስልት በተለይም እ ጎ አ ከ 2010 ዓ ም ወዲህ እጅግ እየከፋ መምጣቱን የጠቀሰው የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ በእስር ቤቱ ውስጥ ሲገረፉ የነበሩ 35 የቀድሞ እስረኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ይህ ሁሉ የሚካሄደው እስረኞችን አስፈራርቶ አሰቃይቶ እና አደናግሮ መረጃ ለማወጣጣት ወይንም የሐሰት ሰነድ ለማስፈረም መሆኑን አውስቷል።
«ከተጭበረበረው» የ2005ቱ ምርጫ ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ በማዳፈን ላይ መሆኑንም ሪፖርቱ ያትታል።
አንዳንድ የቀድሞ እስረኞች ይላል ሪፖርቱ በጥፊ በእርግጫ በዱላ በጠመንጃ ሰደፍ እና በተለያዩ ነገሮች መደብደባቸውን ተነጥለው መታሰራቸውን እና ተዘቅዝቀው ከጣሪያ ወደታች መሰቀላቸውን ለሂማን ራይትስ ዎች አስረድተዋል።አንድ ከኦሮሚያ አካባቢ የተያዘ የኦሮሞ ተማሪም በማዕከላዊ እስር ቤት ለወራት በእግር ብረት እና በእጅ ካቴና መታሰሩን እና ከምግብ ጀምሮ ለመጸዳዳት ጭምር በእስረኞች እርዳታ ብቻ መክረሙን በምሬት ያስታውሳል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቀዋል።
በሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ጉዳዮች ም/ዳይሬክተር የሆኑት ሚስ ሌስሊ ሌፍኮቭ እንደሚሉት በዚህ ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ጣቢያ ሶስት የተለመዱ ስፍራዎች ኣሉ። አንደኛው ሰዎች ያለመብራት የሚታሰሩበት እና ጭለማ ቤት የሚባለው ነው። ሁለተኛው ለግርፋት የተመቻቸው እና ጣውላ ቤት የሚባለው ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ በተሻለ ደረጃ እስረኞች እየተንቀሳቀሱ በጋራ የሚታሰሩበት እና ከዚሁ የተነሳ በሌስሊ ኣባባል «ሸራተን» ተብሎ የሚታወቀው ነው።
ከዚህም ሌላ ይላሉ ሌስሊ በማዕከላዊ እስር ቤት በእሳቸው ኣባባል ማጎሪያ ቤት እስረኞች ከዘመዶቻቸው እና ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር እንዳይገናኙ የሚደረግበት ሁኔታም ኣለ ከእትዮጵያ መንግስት በኩል የጠ/ሚ/ሩ ቃል ኣቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግን ይህ ከእውነት የራቀ እና የተለመደ የሂዩማን ራይትስ ዎች ተራ ድራማ ነው ይላሉ።የጸረ ሽብር ህግ ተብሎ የሚታወቀው የኢትዮጵያ ህግም መንግስት ተቃዋሚዎችን የሚያፍንበት ሰላማዊ እንቅስቃሴን የሚያሽመደምድበት እና በኣጠቃላይ ሰብዓዊ መብትን ለመጣስ የሚጠቀምበት ተጨማሪ መሳሪያ ነው ሲል የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ይተቻል።
ጅዓፈር ዓሊ
አርያም ተክሌ
ሊንኩን በመንካት ዝርዝር ዘገባውን ያዳምቱ

“ኢትዮጵያነቴን ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ” አቶ ተስፋዬ ገ/አብ


11ቀደም ብዬም ተናግሬያለሁ። ማንም ሊከለክለኝ አይችልም። ማንም ሊሰጠኝ አይችልም። አገር ውስጥ እንዳልገባ ልከለከል እችል ይሆናል። የልብ ስሜቴን መንጠቅ የሚችል አንድም ሰው የለም። ይህንን ስሜቴን ነው ባጭሩ ማነገር የምፈልገው።ማንም አይቻለውም። ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼ ሚሊዮኖች አሉ።በተለያዩ ምክንያቶች አገር ቤት መግባት አይችሉም። ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ግን እንደጎርፍ ነው ወደ አገራችን የምንገባው።ይህንን ነው ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው። / አበባ ይበተንለታል/ ለከለከሉኝ ክፍሎች ማን ነው ያ ከልካይ በመሰረቱ? ከየት ነው የመጣው? ያ ሰው ምን አደረገ ለአገሪቱ?እኔ የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ። ይህንን መከልከል የሚችል ማንም የለም።ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ። እስከመጨረሻው … (ተስፋዬ ከኢካድኤፍ የመወያያ መድረክ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)
ከሰነዱ ከተገኙት መረጃዎች መካከል ተስፋዬ በእጁ የጻፈው ይህ መረጃ ይገኛል፡-
“ኢትዮጵያዊያን የኤርትራ ታሪክ በትክክል እንዲያውቁ ይረዳል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለኛል። ለዚህ ሥራም የናንተ መ/ቤት ሆነ ህገደፍ (ሻዕቢያ) ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ። እነዚህ መጻሕፍትን ጽፌ እስከምጨርስ ሁለት ዓመት ይፈጅብኛል። ቢያንስ በቢሮና በጽሕፈት መሣሪያዎች እንዳልቸገር ብደረግ እመኛለሁ።” …
“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻዕቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” …
“አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።” …
“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: 3 ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”
golgule.com

የብኣዴኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከግድያ አመለጠ::



የብኣዴኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከግድያ አመለጠ:: #Ethiopia #Ogaden #eprdf #ONLF የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ሰራዊት በቀብሪደሃር አየር መንገድ (AIRPORT) የወያኔ ባለስልጣናትን አጠቁ:: ብዛት ያላቸው የወያኔ ወታደሮች ሲገደሉ 2 መኪናዎች ተቃጥለዋል:: በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የወያኔ ባለስልታናት የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እና ወታደራዊ መኮንኖች የያዘ የልኡካን ቡድን በኦጋዴን ክልል እንደደረሰ በኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ሰራዊት በተከፈተበት ቶክስ በርካታ ወታደሮች ሲገደሉ ባለስልጣናቱ ማምለጣቸው ታውቋል:: ዋናው አላማችን ወደ ባለስልጣናቱ ማነጣጠር አልነበረም ሆኖም የህንን የወያኔ ባለስልጣናት ጉብኝት ማደናቀፍ እና ለአሻንጉሊቱ አስተዳደር መልእክት ማስተላለፍ ነበር ሆኖም በተገኘው አጋጣሚ አየር መንገዱን አጥቅተን የወያኔ ወታደሮችን ፈጅተናቸዋል::ወታደሮቹ ለእንግዶቹ ጥቃት እየተፈጸመ ስለሆነ መረጃ በመስጠት እንዲያመልጡ ቢያደርጓቸውም ባለስልጣናቱ አብረዋቸው ላሉት የህንን ጉዳይ ለማድበስበስ ሞክረው ነበር::ሆኖም አላማችን ተሳክቷል ወያኔንም አስደንግጠናል ብለዋል የግንባሩ ቃል አቀባይ:

የኢህአዴግ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

October 22, 2013

የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ ‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ ብሎ ለማለፍ የማያስችሉ ሶስት ምክንያቶች አሉ፤ የመጀመሪያው በሀገሪቱ ለአንድ የሥራ መደብ አራት ሚንስትር ተሹሞ አለማወቁ ሲሆን፤ ሌላው ተሿሚዎቹ፣ ኢህአዴግን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች በኮታ የተወጣጡ መሆናቸው ነው፡፡ ሳልሳዊውና አስገራሚው ደግሞ ሰዎቹ ፖለቲከኞች እንጂ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን አለመሆናቸው ነው)Journalist Temasegan Dasaleg
እነዚህ ሁሉ በግልፅ የሚታወቁ የዓመቱ መጀመሪያ ክስተቶች ናቸው፡፡ ለስርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ መሠረት፣ በቅርቡ ‹ሚዲያ›ን እና ‹የይቅርታ ስነስርዓት›ን የተመለከቱ አዳዲስ አዋጆች በተወካዮች ም/ቤት ለመፅደቅ ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለይም ‹ሚዲያው›ን የሚመለከተው አዲሱ ህግ፣ ከአምስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለውን የ‹‹ፕሬስ አዋጁ››ን የአፋና ጉልበት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበረው አንፃራዊ ጭላንጭል ጭራሽ ሊዳፈን እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ‹‹የይቅርታ አዋጁ››ም ቢሆን ጥቂት የአገዛዙ ጉምቱ ባለስልጣናት ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትና አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች ብንታሰርም በይቅርታ እንፈታለን በሚል ግንባሩን እየተፈታተኑ ነው›› ሲሉ ደጋግመው መደመጣቸውን፣ ከአዲሱ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥ እና አፈፃፀም ሥነ-ሥርአት አዋጅ›› ጋር ካያያዝነው፣ አንቀፆቹ ሊኖራቸው የሚችለውን አንድምታ መገመቱ ብዙ ከባድ አይሆንም፡፡
ለማንኛውም ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጉልበታም በመሆን ቀጣዩን ምርጫ በስኬት ለማለፍ፣ በያዝነው ዓመት የተለያዩ አፋኝ ህጎችን በማውጣት ፓርቲዎቹን የማዳከም ስራ ለመስራት በተለየ መልኩ መዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡ በአናቱም ኃ/ማርያም ደሳለኝ-ከመንግስት፣ ከፓርቲውና ከውስን የግል ጋዜጠኞች፤ ደመቀ መኮንን-ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ ሽመልስ ከማል -ከኢዜአ ጋር ያደረጓቸው ቃለ-መጠይቆችም ይህንን መረጃ የሚያጠናክር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም አገዛዙ በቀጣይ ሊኖረው የሚችለውን ባህሪ እና ‹አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ›ን አስቀድሞ ለማሸነፍ እየቀመረ ያለውን ሴራ መጠቆም ነው፡፡
የባለስልጣናቱ አንደበት
ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያምና ምክትሉ ደመቀ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ፣ በስሱም ቢሆን ከጀርባቸው ያደፈጡትን አንጋፋ ታጋዮች ቀጣይ ‹‹የፖለቲካ ሴራ›› (Political Conspiracy) አርድተውናል ብዬ አስባለሁ፡፡
ሁለቱ መሪዎች በዋናነት እንዲያተኩሩ የተደረገው በአራት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ በግንባሩ ውስጥ ክፍፍል መፈጠሩን መካድ፣ አመቱን ሙሉ ‹የመለስ ራዕይ› እየተባለ የተዘመረለትን ‹እሳት ማጥፊያ› ፕሮፓጋንዳ ማስተባበል፣ የሙስና ክሱን ሂደትና ውጤት መሸፋፈን እንዲሁም ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ማስፈራራት የሚሉ ናቸው፡፡ በአዲስ መስመርም እነዚህን አራት አጀንዳዎች ነጣጥለን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
ክፍፍሉን በተመለከተ
ከመለስ ህልፈት ማግስት አንስቶ በግንባሩ ግልፅ ክፍፍል መከሰቱ የአደባባይ ሀቅ ቢሆንም፣ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ‹‹ፓርቲዎ ውስጥ ክፍፍል አለ ይባላል፤ የኃይል አሰላለፍ እየተጠበቀ ነው የሚኬደው የሚባሉ አሉባልታዎች ይሰማሉ፣ የፓርቲዎ ጤናስ እንዴት ነው?›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብለት፡-
‹‹በፓርቲዬ ውስጥ ክፍፍል አለ የሚለው ጥያቄ የምኞት ነው፤ ብዙ ምኞቶች ሲሰሙ ነበር፤ ምኞት አይከለከልም፡፡ ስለዚህም ምኞት ይኖራል የሚል ሃሳብ ከማቅረብ በዘለለ እውነት ስለሌለው ምኞት ነው ብሎ ማለፍ ነው›› በማለት አስተባብሎ ሲያበቃ፤ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ተገልብጦ ‹‹አሁን በቅርቡ እንደደረስንበት አንዳንድ ጊዜ በየቦታው ደባ የሚሰሩ ጥቂት የመሥሪያ ቤት ሰራተኞች አሉ›› ብሎ የራሱ ሰዎች በመንግስቱ ላይ እያሴሩበት እንደሆነ በመግለፅ ከላይኛው ንግግሩ ጋር መጣረሱ፣ በርግጥም የተጠቀሰው ችግር መኖሩን ለመረዳት አያዳግትም፡፡
ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተም ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ አጠንክሮ ጠይቆት ያስተባበለበት መንፈስም ለመሸሸግ የፈለገው ጉዳይ እንዳለ የሚያሳብቅ ይመስላል፡፡
‹‹አንድ ግልፅ መሆን ያለበት እንደ አቶ መለስ ያለ ታላቅ መሪ፣ ታግሎ የሚታገል ጠንካራ መሪን ማጣት ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ ጉድለቱ እንዲሁ ዝም ተብሎ እዚያና እዚህ በዘመቻ የሚሞላ ጉዳይ አይደለም፡፡ …ስለዚህም ሁለት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ኃላፊዎችን በመሰየም ክላስተር እንዲያስተባብሩ ማድረግ ያለመተማመን መገለጫ አይደለም፡፡››
የሁለቱ ሚኒስትሮችን ያልተጠበቀ ቃለ-መጠየቅ መግፍኤ ለመረዳት በተለይ ደመቀ መኮንን ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሾች በጥልቅ መፈተሽ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ተከስቶ የነበረውን መከፋፈልም ሆነ ‹ፓርቲው በጥቂት የህወሓትና የብአዴን ታጋዮች ነው
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
የሚሽከረከረው› መባሉን ለማስተባበል የሄደበት መንገድ፣ ከዚህ ቀደም ኢህአዴግ የሚከራከርባቸውን እምነቶቹን ጭምር እስከመናድ የደረሰ ነውና፡፡ ወይም እንዲንድ ታዝዟል ያስብላል (በነገራችን ላይ ከምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ እነአባይ ፀሀዬና በረከት ስምዖንም ከመጋረጃው ጀርባ የሚሰራ ኃይል መኖሩን ማስተባበል ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ‹‹በነፃነት እንዲሰሩ አመቻቹላቸው›› እያሉ የሚወተውቷቸውን ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ማሳመኑ ከባድ ሥራ እንደሆነባቸው ሰምቻለሁ፡፡
የሰሞኑ የቃለ-መጠይቅ ጋጋታም ይህንኑ የሚያጠናክር ይመስላል፡፡ ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣም ለደመቀ መኮንን ያቀረባቸው ጥያቄዎች ከቀደመው ታሪኩ አኳያ ሲመዘን የግል እምነቱ አለመሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡ ‹‹ጋዜጣው እስከአሁን ያልነበረውን ‹የኤዲቶሪያል ነፃነት› ዛሬ አግኝቶ ነው ሰውየውን እንዲህ ያፋጠጠው›› የሚል ተከራካሪ ካልቀረበ ማለቴ ነው፡፡ ምናልባትም ጉዳዩን በሌላ አውድ እንየው ከተባለ ደግሞ የሚያያዘው፣ የድርጅቱ አመራሮች አልፎ አልፎ ህዝብ ዘንድ የደረሱ እውነታዎችን፣ በራሳቸው ጋዜጠኞች እንዲጠየቁ በማድረግ ለማስተባበል ከሚሞክሩበት የቆየ ልማዳቸው ጋር ብቻ ነው፡፡ በመስከረም 22፣ 23 እና 24 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው የ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ በተስተናገደው የደመቀ መኮንን ቃለ-መጠይቅ ላይ የተነሱትን ጥያቄዎች ብንመለከት ይህንኑ ያረጋግጡልናል፡፡ ‹‹ፓርቲው በጥቂት ሰዎች ስር ስለመውደቁ፣ ከመንግስት ኃላፊነት የተነሱ ባለስልጣናት በፓርቲው ውስጥ ስራ-አስፈፃሚ ሆነው ስለመቀጠላቸው፣ መተካካቱ የቦታ መቀያየር ብቻ ስለመሆኑ፣ ሥራ የማይሰሩ ደካማ መሆናቸውን በተወካዮች ም/ቤት ጭምር የተረጋገጠባቸው ከፍተኛ አመራሮች ዛሬም በኃላፊነት ቦታ ላይ ስለመቀመጣቸው፣ በብልሹ አሰራር /በሙስና/ የተጠየቁ ባለስልጣናት ጥቂት ብቻ መሆናቸው፣ በአቅም ማነስ የሚነሱ ኃላፊዎች ወይ ከነበሩበት የተሻለ አሊያም ተመጣጣኝ በሆነ ደረጃ ስለመመደባቸው፣ አንድ ጊዜ የላይኛውን የስልጣን እርከን የተቆናጠጠ ባለስልጣን ከፓርቲው ቁልፍ አመራሮች ጋር ካልተጋጨ በቀር አቅም ባይኖረውም እንደማይሻር፣ ለፓርቲው መስራቾችና እስከአሁንም ወሳኝ ለሆኑት አመራሮች ታማኝ የሆነ ኃላፊ ምንም አይነት ድክመትና ወንጀል ቢፈፅምም በስልጣን መቆየት መቻሉን፣ የሁለቱ ተጨማሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት በአራቱ የብሔር ድርጅቶች መካከል ያለውን አለመተማመን ስለማሳየቱ፣ ሁሉም ፓርቲዎች እኩል አለመሆናቸውን፣ መለስ በሃያ ሁለት የሥልጣን ዓመታቱ ተተኪ ማፍራት አለመቻሉን፣ ‹የመለስ ራዕይ› የሚባል ነገር አለመኖሩን…›› እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ባልተለመደ ድፍረት የጠየቀው መንግስታዊው ዕድሜ ጠገብ ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ነው)
ቃለ-መጠየቁ ከእነዚህ በተጨማሪም ቀጣዩን የኢህአዴግ አቅጣጫ አመላክቷል፡፡ የሆነው ሆኖ ክፍፍሉንና ከጀርባ ሆነው ያሽከረክራሉ የሚባሉትን አንጋፋ የአመራር አባላት አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ ከሰጠው ምላሽ ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡-
‹‹ፓርቲው አንድ ሰው፣ ሁለት ሰው፣ ሶስት ሰው እጅ ጠምዝዞ ‹ይሄን አድርጉ› በሚል አንዳችም ጉዳይ የሚያስፈፅምበት አይደለም፡፡ …ኢህአዴግ በጥቂቶች የሚመራ ድርጅት አይደለም፡፡ …ጥቂት ግለሰቦችን በተለየ ሁኔታ የሚያይ፣ በእነርሱም ስር የሚሆን አይደለም፡፡ የጥቂቶች ነው የሚለው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ …ማንም በራሱ ተቆጥሮ በተሠጠው ሥራ ሊወስን፣ ሊመራና ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በድርጅታዊ ዲሲፒሊንና አሰራር፣ የግልና የጋራ አሰራር በሚዛን ተቀምጦ በንቅናቄ የሚመራ እንጂ በግለሰቦች አይደለም የሚለው ቢሰመርበት ጥሩ ነው፡፡››
በርግጥ ይህንን ያነበበ ‹‹ሰውየው ስለየትኛው ኢህአዴግ ነው የሚያወራው?›› ቢል ላይፈረድበት ይችላል፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ የታሪክ ንባብም ሆነ የቀድሞዎቹ ስዬ አብርሃ፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ ሀሰን አሊ፣ አልማዝ መኩን የመሳሰሉት የአመራር አባላት የነገሩን ‹ድርጅቱ በጣት በሚቆጠሩ ሰዎች ፍቃድ የሚያድር› መሆኑን ነው፡፡ ለነገሩ ራሱ ደመቀም ቢሆን ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ህወሓት በር ዘግቶ ብቻውን መምከሩንም ሆነ የግንባሩን አባል ድርጅቶች ነፃነት እንዳሻው መጋፋቱን አምኖ መቀበል ባይፈልግ እንኳን፣ በ1999 ዓ.ም መጨረሻ ከሱዳን ጋር የሚዋሰነው የጎንደር መሬት ላይ የተላለፈው ውሳኔ በምን መልኩ እንደነበረ ሊክደው አይችልም (በነገራችን ላይ በወቅቱ የአማራ ክልል አስተዳዳሪው አያሌው ጎበዜ ምክትል የነበረ በመሆኑ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጎንደርና ትግራይ አካባቢ፣ የሚወራበትን ውንጀል በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)
የሰውየው መከራከሪያ ግን እውነት አለመሆኑን ‹ፍትህ›ና ‹ልዕልና› ጋዜጦች፤ ‹አዲስ ታይምስ›ና ‹ፋክት› መፅሄትን ጨምሮ የምዕራብ ሀገራት ብዙሃን መገናኛ እና ድርጅቱን በቅርብ የተከታተሉ ምሁራን በተለያየ ጊዜ ማስረጃ በማጣቀስ ደጋግመው ስላቀረቡ ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልገዋል ብዬ አላስብምና ወደ ቀጣዩ ጉዳያችን አልፋለሁ፡፡
‹‹መተካካት›› ሲባል…
በአንድ ወቅት አቶ መለስ ብዙ ብሎለት የነበረው የመተካካት ዕቅድ ‹‹ቦታ ከመቀያየር ያለፈ አዲስ ፊት አላመጣም›› መባሉን በተመለከተ፣ ደመቀ መኮንን የሰጠውን ምላሽ፣ ከተለያየ አውድ ካየነው ከላይ የተጠቀሰውን ክፍፍል በሌላ በኩል ይነግረናል፡፡ ምክንያቱም መለስ በህይወት በነበረበት ዘመን ጉዳዩን አስመልክቶ የነገረን ‹መተካካቱ ከላይ ያሉትን ነባር የአመራር አባላት፣ በየተራ በጡረታ በማሰናበት አዲሱን ትውልድ (አዲስ ፊት) ወደመሪነት ማምጣት ነው› የሚል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ደመቀ መኮንን ደግሞ በግልባጩ እንዲህ ይላል፡-
‹‹አዲስ ፊት ሲባል የማናውቀው ሰው ከጨረቃ ይምጣ? የሚመራው እኮ አገር ነው፡፡ አንድ ሰው አንድ ቦታ ላይ ሆኖ ሥራውን እየተወጣ፣ ሌላውንም እያበቃ ሥርዓቱ መቀጠል አለበት፡፡ በጣም የሚታወቅ ህዝባዊ አገልግሎት ላይ ያለ ሰው፣ ከያዘው ኃላፊነት ሌላ፣ በሌላ ጊዜ ሌላ ተክቶ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አዲስ ፊት የለም፤ የማናውቃቸው ሰዎች ይምጡ ማለት፣ ሀገር የሙከራ ቦታ ይሁን ማለት ነው፡፡››
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚደክመው በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ሽፈራው ጃርሶ፣ ካሱ ኢላላ፣ ሙላቱ ተሾመን… የመሳሰሉ አንጋፋ መሪዎች ከዚህ ቀደም ለአባላቶቻቸው የገቡትን ቃል ጠብቀው በክብር ከመሰናበት ይልቅ ስልጣን መቀያየራቸውን ለማስተባበል ይመስለኛል፤ በርግጥ ጉዳዩን ከለጠጥነው ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአንጋፋዎቹ መካከልም ሊሆን ይችላል እያለን ይሆናል፡፡ ይሁንና ሰውየው ያስተባበለበት መንገድ ግን በውስጡ ካለው እውነታ ጋር የተቃረነ በሚመስል መልኩ
የመተካካቱ አንድምታ የተቀየረው በመካከል የተፈጠረውን የኃይል ልዩነት አርግቦ፣ ስርዓቱ ከገጠመው መንገራገጭ ወጥቶ በሁለት እግሩ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ፍንጭ ይሰጣል፡፡
‹‹መተካካት ግለሰብን አይደለም የሚተካው፤ የስርዓት ቀጣይነትን ማረጋገጥ ነው!››
ይህ ሁናቴ በደንብ የሚፍታታው አቦይ ስብሃት ነጋ በተለይ ህወሓት ውስጥ የተካሄደው መተካካት ከተፈጠረው ልዩነት ጋር ተያይዞ መሆኑን ለ‹‹ውራይና›› መፅሄት የሰጡትን ቃለ-መጠየቅ ስናነብ ነው፡-
‹‹ጉባኤው ከማዕከላዊ ኮሚቴ ለተሰናበቱ ሰዎች ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው፣ አሰራር ለምን እነሱን በሌሎች መተካት እንዳስፈለገ፣ ተራ በተራ እየጠቀሰ አስተያየት (ማብራሪያ) መስጠት ነበረበት፡፡ ይህ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ከተሰናባቾቹ መካከል ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መቆየት (መቀጠል) የሚገባቸው በተገኙ ነበር፡፡ ከተመረጡት ውስጥ ደግሞ መሰናበት (በሌላ መተካት) የሚኖርባቸው ሊገኙ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አካሄዱ ስህተት ስለሆነ ውጤቱም እንደዚያው ሊሆን ችሏል፡፡ እነማን መሰናበት፣ እነማን መቆየት እንደነበረባቸው በዝርዝር ስም ጠርቼ መናገር እችል ነበር፡፡ ግን ምንም ለውጥ ስለማያመጣ ስም መዘርዘሩ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡››
የ‹‹ራዕዩ›› ጉዳይ…
በፋክት መፅሄት ቁጥር 5 ላይ ኢህአዴግ ‹የመለስ ራዕይ› እያለ ይደሰኩርለት የነበረውን አጀንዳ በወራት ጊዜ ውስጥ ገልብጦ በማጠቋቆር ሊቀየረው መዘጋጀቱ ተጠቅሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በደመቀ መኮንን ቃለ-መጠይቅ ላይም፣ መለስ ሥልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ተገምግሞ መንግስታዊ ተቋማትንና የልማት ዕቅዶችን በአግባቡ መከታተልና መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል፡፡
‹‹ያለፉት ዓመታት ሥራዎቻችንን ስንገመግም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብዙ ሥራ ተሸክመው ይሰሩ በነበረበት ዋና ዋና የልማት ሥራዎቻችን ላይ በማተኮር አንዳንድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የልማት መስኮችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሽ፣ በዝርዝር ዕቅድ ግምገማና ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተቶች እንደነበሩ እንደ ችግር በጋራ ያገኘናቸው ነጥቦች አሉ፡፡››
እንዲያ ሀገር-ምድሩ ‹ካልዘመረለት ተደፍረናል!› ሲሉለት የነበረው ‹‹የመለስ ራዕይ››ም ቢሆን የኢህአዴግ እንጂ የመለስ አለመሆኑን እየነገሩን ነው፡፡ አቶ ደመቀም፣ መለስ የነበረው ‹‹ራዕይ›› ሳይሆን ኃላፊነት ነው ወደ ማለቱ አዘንብሏል፡፡
‹‹ይሄን የዕድገት መንገድ ከኢህአዴግ አባላትና ከመሪዎቹ ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት የመሪነት ቁልፍ ሚና የተጫወቱ መሪ ናቸው፡፡››
በጥቅሉ በወቅታዊው የድርጅቱ ፖለቲካዊ አተያይ ‹‹የመለስ ራዕይ›› የሚለው ሀረግ ከየት እንደመጣ የተተነተነበትን አውድ ለመረዳት ከጋዜጣው ላይ አንድ ተጨማሪ ጥያቄና መልስ እንደወረደ ልጥቀስ፡-
‹‹አዲስ ዘመን፡- በየዘርፉ ራዕያቸው ተብለው የሚነገሩት መልእክቶችና መሪ ቃሎች ጋር በተያያዘ የተለጠፈባቸው ራዕይ እንዳለ ነው የሚነገረው፤ አገሪቱን ከመሩበት 22 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ምናልባት አንድ ጊዜ በንግግር መሀል የተናገሯት ወይም ለጋዜጠኞች የሰጡት ምላሽ ራዕይ ተደርጎ እየቀረበ ነው ስለሚባለውስ?
‹‹አቶ ደመቀ፡- እነዚያ መልዕክቶች ያንን ራዕይ የሚገልፁ፣ የሚያስታውሱ ምልዕክቶች ናቸው፡፡ ከማንኛውም ጉዳይ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚያ ያንን ትልቁን ራዕይ የሚመግቡ መልዕክቶች እንደሆኑ አድርጎ መመልከት ይቻላል፡፡››
ይኸው ነው፤ በቃ፡፡ መለስ ራዕዩን በጥሩ ቋንቋ ከመግለፅ ባለፈ የብቻው የሆነ ነገር የለውም፡፡ በክፍፍሉ ወቅት ከ‹አዲስ አበባው-ህወሓት› ጎን የተሰለፉት አቦይ ስብሃት ነጋ በጉባኤ፣ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች እንዲሁም አርከበ እቁባይ በህወሓት ጉባኤ ላይ የመለስ ‹ራዕይ› የሚባል ነገር አለመኖሩን በመግለፅ፣ በወቅቱ በአሰላለፍ የተመሳሰሉት ‹የመቀሌው-ህወሓት› እና ብአዴን በ‹ራዕይ› ስም ኃይል የማጠናከር እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ለመተቸትና ለማደናቀፍ መሞከራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ሁናቴም ልዩነቱ ከተገለፀባቸው ምልክቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ሌላው እዚህ ጋ መነሳት ያለበት ጉዳይ በዚህ ዓመት በዚሁ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ፅሁፍም ‹‹የመለስ ራዕይ››ን የማይቀበለው ቡድን እያሸነፈ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብ-አባይ ወልዱ ህወሓትን አዳክሞ፣ የእነ በረከት-ብአዴንን ከጎኑ ማሰለፍ መቻሉን የተተነተነበትን ጉዳይ የሚያጠናክር መሆኑን ነው፡፡
የሆነው ሆኖ አሁን መለስን የሚያመልኩት ሄደዋል፤ በቦታውም እርሱ የሚያርቃቸው፣ እነርሱም ይፈሩት የነበረ ተተክተዋል፡፡ እናም በህልፈቱ ማግስት ድጋፍ ማሰባሰቢያ እና ኃይል ማጠናከሪያ ከመሆን አልፎ ሀገሪቱን ወደ ብልፅግና ሰማይ የሚያከንፍ፣ መና የሚያዘንብ ተደርጎ የነበረውን ‹‹የመለስ ራዕይ›› ታሪክ በማድረጋቸው፣ አርቀው መስቀል ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ አነጋገር በፋውንዴሽኑ አጥር ክልል ተወስኖ ይቀመጥ ዘንድ በይነዋል (በነገራችን ላይ ይህን ጉዳይ በዚህ ደረጃ ያነሳሁት የስርዓቱ መሪዎች ‹‹እንመራዋለን›› የሚሉትን ህዝብ በአደባባይ ሲዋሹ ቅንጣት ያህል ሀፍረት እንደማይሰማቸው ለማሳየት እንጂ፣ በግሌ መለስም ሆነ ጓደኞቹ ለስልጣናቸው ካልሆነ በቀር ሀገር የሚጠቅም ራዕይ አላቸው ብዬ አላምንም)
የ‹‹ሙስና››ውን ክስ ሂደት መሸፋፈን:
የእነ መላኩ ፈንቴን እስር ተከትሎ ‹‹ሙስና›› ዋነኛ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያምም ‹ጉዳዩን ራሴ እከታተለዋለሁ› የምትል ፉከራ ብጤም ሞካክራው ነበር (ቀደም ሲል በዚሁ መፅሄት የ‹ሙስና›ው ክስ በፖለቲካው የኃይል አሰላለፍ ላይ የበላይነትን ለመጨበጥ በአዲስ አበባው ህወሓት የተመዘዘ ‹‹ካርድ›› እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል)
ባለሥልጣናቱ የታሰሩ ሰሞን ‹‹የመለስ ራዕይ›› ገና አልከሸፈም ነበርና ‹‹የፀረ-ሙስና ኮሚሽን›› ኮሚሽነር አሊ ሱለይማንም ጉዳዩን አቶ መለስ ራሱ ጀምሮት ለሁለት ዓመት ያህል ሲከታተለው ከቆየ በኋላ፣ በመጨረሻ ህይወቱ እንዳለፈ እያለቃቀሰ ነግሮን ነበር፡፡
ይሁንና
ከእስራ አምስት ቀን በፊት ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ባደረገው ቃለ-መጠይቅ፣ የታሰሩትን ሰዎች አስመልክቶ ከጊዜ ቀጠሮ ያለፈ ቁርጥ ያለ ነገር አለመኖሩ፣ በሌሎች ላይ ስጋት ስለመፍጠሩ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ‹ገድሉ›ን ከመለስ ወደራሱ (ከኋላው ወደአሉ ሰዎች) መልሶታል፡፡
‹‹በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል በሙስና የተጠረጠሩ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና በሙስና ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት ተዘርግቶ የመንግስት አካል የሆነው የፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቷል፡፡››
ጥያቄውም ይህ ነው፡፡ ‹‹የአሊ ሱሊማንን ‹መለስ የጀመረው…› መግለጫንስ ምን እናድርገው?››
…ደመቀ መኮንንም ‹‹እዚያም እዚያም ከኃላፊነት የማውረድ፣ በሕግ የመጠየቅና ሕጋዊ እርምጃዎች ደረጃቸውን ጠብቀው ይቀጥላሉ›› ቢልም በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ግን የሚያሳየው ሙስና የተዘጋ አጀንዳ መሆኑን ነው፡፡ የ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ የፊት ገፆችም ‹‹ሚኒስትር እገሌ…››፣ ‹‹ዳይሬክተር እገሌ… በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ›› ከሚል ዜና በብርሃን ፍጥነት ‹‹በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የዲዛይንና ግንባታ ፍቃድ ጽ/ቤት፣ የግንባታና ዕድሳት ባለሙያ የነበረችው ግለሰብ መስከረም 21 ቀን 2006 ዓ.ም አራት ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል በፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ተያዘች›› ወደሚል ቧልት ተቀይረዋል፡፡
አቦይ ስብሃት ነጋ ከላይ በጠቀስኩት መፅሄት የሙስናውን ጨዋታ የገለፁት እንዲህ በማለት ነበር፡-
‹‹አሁንም ድረስ ያልተፈቱ የአካሄድ (የአሰራር) ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ‹ሙስና አለ› ብትል፣ ሙስና በስርዓቱ ላይ በሚያደርሰው አደጋ ላይ ከማተኮር ይልቅ ‹አንተስ ከሙሰኛነት ነፃ ነህ ወይ?› በማለት ዋናው ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የሚቸልሱ ሰዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁንም ቢሆን ይህንን የከፋ ድርጅታዊ ጉዳይ (ችግር) በመጋረጃ ሸፋፍኖ ለማለፍ ‹ስብሃት ለምን በጊዜው ጉባኤው ላይ አላቀረበውም ነበር› የሚሉ አይጠፉም የሚል ግምት አለኝ፡፡ በበኩሌ ይህ ነገር በሌላ ላይ ጊዜው ሲደርስ የሚነሳ ይሆናል ነው የምለው:፡››
በርግጥ የአቦይ ወቀሳ እውነት ነው፡፡ ይሁንና ጉዳዩን በጉባኤው ላይ ያላነሱበት ምክንያት ‹‹በሌላ ላይ ጊዜው ሲደርስ የሚነሳ ይሆናል›› በሚል እንደሆነ ለመናገር መሞከራቸው ግን የክፍለ ዘመኑ አስቂኝ ቀልድ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም፤ ባይሆን ‹‹አንተስ ከሙሰኛነት ነፃ ነህ ወይ?› ይሉኛል ብዬ ተውኩት›› ቢሉን፣ ቢያንስ ለግልፅነታቸው ባርኔጣ እናነሳ ነበር፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የኢህአዴግ ሰዎችን የሙስና ወንጀል በህግ የሚያስጠይቅ ከሆነ አቦይ ስብሃት ከፊት መስመር መሰለፋቸው አይቀርምና፡፡ ሌላው ቀርቶ አርከበ እቁባይ ለጊዜው ገለል እንዲል (ከሀገር እንዲወጣ) የተደረገው ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቼ ነግረውኛል፡፡ አርከብ፣ አቦይን ጨምሮ ከታሰሩት ባለሀብቶች ውስጥ ጥቂቶቹ በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩት የመሆኑ ጉዳይ ይመስለኛል ‹ማዕበሉ እስኪረጋ› ከዕይታ እንዲርቅ የተደረገበት ምስጥር፡፡ በተቀረ አርከበ ሀገር ጥሎ ኮበለለ፣ ኢህአዴግን ከዳ… ጂኒ ቁልቋል የሚሉት የፒያሳ ወሬዎች፣ አንድም ወቅታዊውን የኢህአዴግ አሰላለፍ ካለመረዳት ሊሆን ይችላል፤ አሊያም የጉዳዩ ባለቤቶች ስራዬ ብለው የተሳሳተ መረጃ በሚያስተላልፉበት በተለመደው ሰርጥ ያሰራጩት ማስቀየሻ ነው የሚሆነው፤ አርከበ የሄደው አቦይ እንዳሉት ‹‹አንተስ ከሙስና ነፃ ነህን?›› የማለቱ አቅም ያላቸውን አጉረምራሚ ሰዎችን ለማለዘብ ነው፡፡ ምናልባት የመቀሌው ህወሓት አሸንፎ ቢሆን ኖሮ እውነትም አርከበ ከቃሊቲ ይልቅ አሜሪካ ይሻለዋል ማለታችን አይቀርም ነበር፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በእጁ ላይ ካቴና ለማጥለቅ አያመነቱም፡፡ ግና! የሆነው በተገላቢጦሹ ነው፡፡ …ማን ነበር ‹‹አባቱ ዳኛ…›› ያለው? (በነገራችን ላይ ኢህአዴግ የሙስና አዋጁንም በዚሁ ዓመት የማሻሻል ዕቅድ አለው፡፡)
የአፈናው ዝግጅት:
ስርዓቱ በሚቀጥለው ዓመት የሚደረገው አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን ከወዲሁ ‹የቤት ስራን በማጠናቀቅ› ካልተዘጋጀንበት፣ ያልተጠበቀ አደጋ ሊያመጣብን ይችላል ወደሚል ጠርዝ የተገፋው አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በተለያየ ጊዜ በጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ ቁጥር አሳስቦት ብቻ አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ያለ መለስ ዜናዊ የሚጋፈጠው የመጀመሪያው ምርጫ በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ እንደሚታወሰው አቶ መለስ ሁሉንም የሥልጣን ምንጮች ጠቅልሎ የያዘ ‹ጠንካራ ሰው› (Strong Man) በመሆኑ፣ በእንዲህ አይነት ወቅት የሚመጡ ድንገቴ አደጋዎችን ለመቋቋም ብዙም ሲቸገር አይስተዋልም ነበር፡፡ ይሁንና በቀጣዩ ምርጫ አንድም በድርጅቱ ውስጥ የእርሱ አይነት ተተኪ ሰው አለመኖሩ፣ ሁለትም ምንም እንኳ ከህልፈቱ በኋላ የተፈጠረው ልዩነት በአንፃራዊነት የተረጋጋ ቢመስልም፣ ለሌላ ዙር የክፍፍል አደጋ አለመጋለጡ አስተማማኝ ባለመሆኑ ስጋት መፍጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በአናቱም ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የተከሰተው አለመግባት እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ ተፅእኖ ለማድረግ የመሞከሩ ጨዋታም ለተቀናቃኞች ያልተጠበቀ ኃይል ሊሆን የሚችልበት ዕድል ቢፈጥርስ የሚል ስጋት አለ፡፡
የባለሥልጣናቱ በአደባባይ የማስፈራራት መግፍኤም ይኸው ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም በቃለ-መጠይቁ ላይ ተቃዋሚዎችን (አንድነትና ሰማያዊን) እና የሀይማኖት ማህበራትን ለማስፈራራት ከሰባት ጊዜ በላይ የመለስን ‹‹ቀይ መስመር›› አገላለፅ ተጠቅሞበታል፡፡ በተለይም ሁለቱ ፓርቲዎች የያዙት በሠላማዊ ሠልፍ ተፅዕኖ የመፍጠር መንገድ ተከታዮቻቸውን እያበዛ እና የፈዘዘውን የፖለቲካ ተሳትፎ እያነቃቃው መሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ የተረዳው ይመስለኛል፡፡ በኃ/ማሪያምም በኩል ያስተላለፈው መልዕክትም ቀጣዩን የፖለቲካ ሴራ አመላካች ነው፡-
‹‹መታወቅ ያለበት አንድ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚጠየቅ ከሆነ፣ እኛም አንድ ቦታ ስንደርስ ‹ለዚህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ መልስ ሰጥተናል፤ ጥያቄው ይህ ከሆነ የሠልፍ ትርጉም ምንድነው?› ብለን የምናቆምበት ደረጃ እንደርሳለን፡፡ ምክንያቱም ሠልፍ ለዘላለም የሚካሄድበት ሀገር ያለ አይመስለኝም፡፡››
በተመሳሳይ መልኩ የሃይማኖት ማህበራት የሚያነሱትን የመብት ጥያቄም ወዴት ሊገፋው እንደሚችል ጥቁምታ ሰጥቷል፡-
‹‹የሀይማኖት ግብንም አክራሪዎች በምድር ላይ ሊሰሩ የሚፈልጉትን ግብ ሁለቱን የሚያምታቱ ሰዎች አሉ፤ የሌላውን ግብ በምድራዊ ዓለማዊ ማሳካት ስለማይቻል፣ እነዚህ ፖለቲከኞች ይዘዋቸው እንዳይነጉዱ፣ ከህዝብ እንዲነጠሉ ምክር ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ የሚታወቁ ስላሉ፡፡ በተለይ ወጣቶች፣ ከወጣቶችም ወጣት ሴቶች በአሁኑ ወቅት በዚህ ውስጥ ተሳትፈው የሚጓዙ እንዳሉ በግልፅ ይታወቃሉ፡፡ መንግስት በዚህ ደረጃ ለእነዚህ አካላት መልዕክት ማስተላለፉ ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡››
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚመራው ሽመልስ ከማልም ከ‹‹ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)›› ጋር ያደረገውና ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ላይ በወጣው ቃለ-ምልልስ እንደተለመደው ጉዳዩን በተመለከተ ጠንከር ያለ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ለማስተላለፍ የፈለገ (የታዘዘ) መስሎ አግኝቸዋለሁ፡-
‹‹አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጉን እናሰርዛለን፣ ሕጉ ሰብዓዊ መብት የሚጥስ ነው ብለው በአደባባይ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰሙ የሚታዩና በተዘዋዋሪ መንገድ ከሽብርተኞች ጋር ለሽብርተኞች የሞራል ድጋፍ ሲሰጡና ሲቸሩ የምናያቸው አንዳንድ ወገኖች ሳያውቁ፣ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በቀና መንገድ ተሳስተው ነው የሚል ግምት ሊኖር የሚገባው አይመስለኝም፡፡
እነዚህ ወገኖች አውቀው ነው ይህንን ሥራ የሚሰሩት፤ በስሌት ነው ይህን የሚከናውኑት፡፡››
በእርግጥም የስርዓቱ የሴራ ቀማሪዎች ‹‹አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የፈጠሩት መነቃቃት፣ በጊዜ ካልተቋጨ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ‹ባልታወቀ ስፍራ የተኛ ሰይጣን ቀስቅሶ፣ ድንገቴ ማዕበል ሊያስነሳ ይችላል›› የሚለው ትንተናቸው ይመስለኛል ቀድሞም የጠበበውን ምህዳር ይበልጥ ለማጥበብ (ለመድፈን) ከወዲሁ እላይ-ታች እንዲሉ ያስገደዳቸው፡፡
እንደ መውጫ:
ስርዓቱ በብዙ መልኩ ያለ ስኬት ከሃያ ሁለት ዓመታት በላይ መጓዙ እርግጥ ነው፡፡ በተቃውሞ ሰፈርም ይህንን ሁናቴ ለመለወጥ አብዛኛውን ዓመታት የበረዶ ያህል ቢቀዘቅዝም፣ አልፎ አልፎ እየጋመ ለውጥ ለማምጣት ያደረገው ሙከራ፣ አገዛዙ ካከማቸው ኃይል ጋር ባለመስተካከሉ ደጋግሞ መምከን አሳዛኝ ዕድል ፈንታ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመት የተያዘው ዕቅድም ከቀድሞ በባሰ መልኩ፣ ለመደራጀት የሚውተረተረውን ኃይልም ሆነ ተበታትኖና ተከፋፍሎም ቢሆን ለውጥ የሚጠይቀውን ህዝብ በተለያየ መንገድ ማቀዝቀዝ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ጉዳዩን በደንታቢስነት ማየቱ ይህ እውን ሆኖ የ2002ቱ የምርጫ ድል፣ በ2007 ዓ.ምም ይደግም ዘንድ ፍቃድ የመስጠት ያህል ነው የምለው፡፡
አሁንም አረፈደም፡፡ ነገር ግን ፈረንጅኛው እንደሚለው ‹‹እውነቱ ግድግዳው ላይ ተፅፏል›› የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ለውጥ ፈላጊ ዜጎች… ስርዓቱ ለህዝብ ፍላጎት ይገዛ ዘንድ ከዚህ ቀደም ያልተሞከሩ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) አማራጮችን ከመተግበር ውጪ ጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ ተጨማሪ ‹የዕድል ቁጥር› አለመኖሩን መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

Monday, October 21, 2013

የስዊድን የጦር ኮሚሽን በኦጋዴን ስለተፈጸመው ወንጀል አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጥ አስታወቀ

ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦጋዴን የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል የሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ዛሬ አርብ፣ የስዊድን የጦር ኮሚሽን ማስረጃዎችን ተረክቧል።
ማስረጃዎችን ለኮሚሽኑ ያስረከቡት ሂደቱ ዋና ተወናይ የሆነው ወጣት አብዱላሂ የሱፍና የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ናቸው።
የጦር ኮሚሽኑ የቀረበለትን ማስረጃ በማየት አፋጣኝ ውሳኔ እንደሚሰጥ መግለጹን ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት ተናግሯል።
ይህ በእንዲህ እንደላ በስልጣን ላይ የሚገኙ የአፍሪካ መሪዎች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲከበር  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠየቁ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአፍሪካ ህብረት 15ኛው አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባ ላይ በጉዳዩ ላይ በመምከር ያስተላለፈው ውሳኔም ተግባራዊ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

“ኢትዮጵያነቴን ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ” አቶ ተስፋዬ ገ/አብ

ቀደም ብዬም ተናግሬያለሁ። ማንም ሊከለክለኝ አይችልም። ማንም ሊሰጠኝ አይችልም። አገር ውስጥ እንዳልገባ ልከለከል እችል ይሆናል። የልብ ስሜቴን መንጠቅ የሚችል አንድም ሰው የለም። ይህንን ስሜቴን ነው ባጭሩ ማነገር የምፈልገው።ማንም አይቻለውም። ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼ ሚሊዮኖች አሉ።በተለያዩ ምክንያቶች አገር ቤት መግባት አይችሉም። ከጥቂት ጊዜያት  በሁዋላ ግን እንደጎርፍ ነው ወደ አገራችን የምንገባው።ይህንን ነው ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው። / አበባ ይበተንለታል/ ለከለከሉኝ ክፍሎች ማን ነው ያ ከልካይ በመሰረቱ? ከየት ነው የመጣው? ያ ሰው ምን አደረገ ለአገሪቱ?እኔ የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ። ይህንን መከልከል የሚችል ማንም የለም።ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ። እስከመጨረሻው … (ተስፋዬ ከኢካድኤፍ የመወያያ መድረክ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)

ከሰነዱ ከተገኙት መረጃዎች መካከል ተስፋዬ በእጁ የጻፈው ይህ መረጃ ይገኛል፡-

“ኢትዮጵያዊያን የኤርትራ ታሪክ በትክክል እንዲያውቁ ይረዳል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለኛል። ለዚህ ሥራም የናንተ መ/ቤት ሆነ ህገደፍ (ሻዕቢያ) ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ። እነዚህ መጻሕፍትን ጽፌ እስከምጨርስ ሁለት ዓመት ይፈጅብኛል። ቢያንስ በቢሮና በጽሕፈት መሣሪያዎች እንዳልቸገር ብደረግ እመኛለሁ።” …

“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻዕቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” …

“አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።” …

“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: 3 ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”

Source; golgule.com

Sunday, October 20, 2013

ኢትዮጵያ፡ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የማሰቃየት ድርጊት ይፈጸማል

በግዳጅ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።

(ናይሮቢ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2006 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዋና የማሰሪያና የምርመራ ጣቢያ ውስጥ በፖለቲካ ሳቢያ የተያዙ እስረኞችን እንደሚያሰቃዩ እና ለጎጂ አያያዝ እንደሚያጋለጡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ፡፡ ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ተግባራትን ለማስቆም እንዲሁም የሚፈጸሙትን በደሎች በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እና አጥፊዎቹንም ተጠያቂ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

74 ገፆች ያሉት እና “ ‘የሚፈልጉት የእምነት ቃል ነው’ ፡ ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ” በሚል ርዕስ የወጣው ይኸው ሪፖርት ከ 2002 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከላዊ የተፈፀሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ በህገ ወጥ መንገድ የሚካሄድ ምርመራን እና በዚያ ያለውን አስከፊ የእስር ሁኔታ ይዘረዝራል። በማዕከላዊ ከሚታሰሩት መካከል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ጎሳን መሰረት ያደረገ ትግል የሚያካሂዱ አማፂያንን ይደግፋሉ የሚባሉ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ከ35 የሚበልጡ የቀድሞ ታሳሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ያነጋገረ ሲሆን እነሱም የማዕከላዊ ሃላፊዎች መረጃ እና የእምነት ቃል ለማግኘት ሲሉ እንዴት መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንደከለከሏቸው፣ እንዳሰቃዩአቸው፣ በተለያየ መልኩ ያልተገባ አያያዝ እንደፈጸሙባቸው እና የቤተሰብ አባላትን እና የሕግ ጠበቃ እንዳያገኙ እንደከለከሏቸው በዝርዝር ገልጸዋል፡፡

በሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ “መረጃ ለማግኘት ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋና ከተማዋ እምብርት በየጊዜው ጥቃት ይፈፅማሉ” ብለዋል፡፡ ሌፍኮ እንዳሉት “ድብደባ፣ ማሰቃየት እና በማስገደድ ቃል መቀበል ለጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የተገባ አይደለም።”

ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው በኢትዮጵያ ከ1997ቱ አወዛጋቢ ምርጫ በኋላ በሰላማዊ ተቃዎሞ ላይ የሚደረገው ጫና ተባብሷል። በማዕከላዊ ተይዘው ምርመራ የሚካሄድባቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች ጥብቅ በሆነው የሀገሪቱ የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ መሠረት መከሰስን ጨምሮ የዘፈቀደ እስር እና ፖለቲካን መሠረት ያደረገ ማሳደድ ይፈጸምባቸዋል።የማዕከላዊ ሃላፊዎች በዋናነትም መርማሪ ፖሊሶች እስረኞቹን በተለያየ መንገድ ያሰቃያሉ፤ ጎጂ አያያዝም ይፈጽማሉ፡፡ በተለይ በምርመራ ጊዜ ታሳሪዎቹ በጥፊ፣ በእርግጫ እንዲሁም በብትር እና በሰደፍ በተደጋጋሚ እንደተመቱ ለሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጸዋል፡፡ እስረኞቹ ሰውነታቸውን ለህመም በሚዳርግ ሁኔታ እንዲሆኑና በተለይም እጆቻቸውን ከግድግዳ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ ተደርጎ ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ እንደሚደበደቡ ተናግረዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመጣ አንድ ተማሪ ብቻውን ተነጥሎና በሰንሰለት ታስሮ ለበርካታ ወራት እንዲቆይ እንደተደረገ ተናግሯል፡፡ “ለመቆም ስሞክር እቸገራለሁ፡ ለመቆም ጭንቅላቴን፣ እግሮቼን እና ግድግዳውን መጠቀም ነበረብኝ ፡፡ ምግብ ስመገብ እንኳ በሰንሰለት ታስሬ ነበር። ስመገብ እጆቼ በፊት ለፊት በኩል እንዲታሰሩ ይደረጋል ስጨርስ ደግሞ መልሰው ወደ ኋላ ያስሩኛል።”

በማዕከላዊ በሚገኙት አራቱ ዋና የማሰሪያ ብሎኮች ያለው ሁኔታ አስከፊ ነው። ሆኖም በየብሎኩ ያለው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይለያያል፡፡ ‘ጨለማ ቤት’ በመባል በሚታወቀው በጣም የከፋ ብሎክ የቀን ብርሃን እና የመፀዳጃ አገልግሎት ማግኘት በእጅጉ የተገደበ መሆኑን የቀድሞ ታሳሪዎች የገለጹ ሲሆን ‘ጣውላ ቤት’ በሚባለው ብሎክ የታሰሩት ደግሞ ወደ ደጃፍ ለመውጣት ያለውን ገደብ እና የክፍሎቹን በተባይ መወረር ገለጸዋል። እስረኞቹ ለመርማሪዎቹ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ትብብር መሰረት በቅጣት ወይም በማበረታቻ መልኩ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውንና ሌሎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሊከለከሉ ወይም ሊፈቀዱላቸው ይችላል፡፡ ይህም ታሳሪዎቹን ከአንዱ ብሎክ ወደ ሌላ ማዘዋወርን ይጨምራል፡፡ ከዓለማቀፉ ሆቴል ስያሜውን ወዳገኘው እና ‘ሸራተን’ በመባል ወደሚታወቀው ብሎክ መዛወር የተሻለ የመንቀሳቀስ እድል ስለሚያስገኝ ከመፈታት ቀጥሎ እስረኞች እጅግ የሚናፍቁት ነገር ነው።

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!

ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።

ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።