Sunday, November 10, 2013

ሰበር ዜና ከሳውዲ አረቢያ – ነቢዩ ሲራክ

በሳውዲ ዋና ከተማ ዛሬ ከረፋዱ ጀምረው እስከ እኩለቀን በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ወጡ! ቤተሰቦቻቸውን እና ሻንጣቸውን ይዘው አውራ መንገድ የወጡት ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ግማሾቹ ወደ ሪያድ ኢንባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት አንድ የፖሊስ መኪና እንደተሰበረ የአይን እማኞች ገልጸውልኛል። ይህንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመፍራት አብዛኛው ተቃውሞ አቅራቢ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት መበተናችው ታውቋል!


ከቀትር በኃላ …

የጭንቅ ጊዜ የማይደረገው ይደረጋል !

የዛሬው የመንፉሃ ተቃውሞ በፎቶ …. ለደህንነት ሲባል ቅርብና ግልጽ ፎቶዎችን ብሎም በእጀ የገቡ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ላለማውጣት መርጫለሁ! ጉዳዩን የሪያዱ አንባሳደር በቅርብ መከታተል መጀመራቸውንና ነዋሪው ተጨባጭ መረጃዎችን በማቀበል ላይ መሆኑን ተጨባጭ መረጃም አግኝቻለሁ ! በአሁኑ ሰአት ሰው ከቦታው የተበታተነ ቢሆንም አድማ በታኝ ሃይል ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሷል የሚል የአይይን እማኝ መረጃዎች ደርሰውኛል! እንደኔ እንደኔ ሁኔታው አቅጣጫውን እንዳይስት ማዕከላዊው መንግስተረ ለዜና ፍጆታ ሳይሆን ህጋዊ አይደሉምነየሚባሉ ዜጎች የመውጫ ሰነድ እየተሰጣቸው በሰላም ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ መንግስታችን አስቸኳይ ልዑክ መላክና ከሳውዲ መንግስት ጋር መነጋገር አለበት እላለሁ ። ወገኖቻችን ለመታደግ ጊዜው አልመሸም! በሃገር ቤት ፣ በአሜሪካ ፣ በአውሮፖ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን የሳውዲን መንግስት ጥቂት ወረበሎችን ለማጽዳት በሚል በመንፉሃና በተለያዩ የሪያድ ክፍሎች እየወሰደ ያለውን ህግን ያልተከተለ እርምጃ በሰላማዊ መንገድ ልትጠይቁልን ይገባል! የሳውዲን ህገ እናከብራለን ፣ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውን ተለይተን ግፍ ሊፈጸምብን አይገባም!

እስኪ ቸር ያሰማን!

No comments:

Post a Comment