የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታሰሩ፡፡ ከጽ/ቤታቸው ተነስተው ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ቦታ ሲሄዱ 4 ኪሎ የኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጎን በሚገኘው ወታደራዊ ገራዥ መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ከቦታው አድርሶናል፡፡ ከመታሰራው ቀደም ብሎ ከፖሊስ ጋር እንሂድ አትሄዱም በሚል ጭቅጭቅ ላይ እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ ሌሎች የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተበታትነው ወደ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ እየሄዱ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡
ዘግየቶ በደረሰን ዜና ደግሞ በኤምባሲው በተገኙ ሰዎች ላይ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ማድረሱ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም በሰልፉ ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትም መታሰራቸው ታውቋል፡፡
በተለይ አንዲ ሴት ክፉኛ በመመታቷ ለህይወቷ እንዲያሰጋ ለማወቅ ችለኛል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው “በሰው አገር ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ለመቃወም ወጥተን ተመሳሳይ ስቃይ አስተናገድን” ብለዋል፡፡
No comments:
Post a Comment