አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከመላው ኢትዩጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ለመዋሃድ በምክር ቤቱ በማስወሰን በጽህፈት ቤቱ አማካኝነት ለመኢአድ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ሁለቱ ፓርቲዎች ለመዋሃድ በሚያስችሏቸው ሂደቶች ዙሪያ ለመነጋገር ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ለመዋሀድ ለመዋሀድ የሚበቁበትን ሃላፊነት በመውሰድ የኮሚቴው አካል የተደረጉት ፓለቲከኞች በመጀመሪያው ቀን የውይይት ስብሰባቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የውህደት ውይይቱን ለማድረግ መስማማታቸውም ሂደቱን በመግባባት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረጉን አንድነትን በመወከል የኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ሙላት ጣሰው ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡
የመኢአድን የፐለቲካ ፕሮግራምና ደንቡን ለማጥናት በአንድነት በኩል ሻለቃ አርጋው ሀብታሙ የሚመሩት ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን መኢአድ የአንድነትን የፖለቲካ ፕሮግራምና ደንብ ለማጥናት በአቶ ተስፋዬ ታሪኩ የሚመራ ቡድን ማቋቋሙ ታውቋል፡፡
አቶ ሙላት የተቋቋመው ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደርስበትን ውሳኔ እንዲያቀርብና ውህደቱ ረዘም ያለ ጊዜ ሳይወስድ ወደ ቀጣይ ስራ እንዲገባ ትዕዛዝ መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡ በኢትዩጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ በዛ ያሉ ጥምረቶች፣ውህደቶችና ቅንጅቶች ከዚህ ቀደም ተፈጥረው እንደታሰበው ውጤታማ ሳይሆኑ መቅረታቸው አሁን ለሚመሰረተው ውህደት እንቅፋት አይሆንም? ተብለው የተጠየቁት አቶ ሙላት ‹‹አሁን በዋናነት ያተኮርነው በመነሻ የድርጅቶቹ ፕሮግራምና ደንብ ላይ ጥናት ለማከናወን ነው በቀጣይ ግን የቀደሙት ውህደቶች ለምን ውጤታማ ሳይሆኑ እንደቀሩ በዝርዝር በመመልከት ትምህርት ንወስድበት በሚገባን ነጥብ ዙሪያ እንወያያለን››ብለዋል፡፡
source abugida
No comments:
Post a Comment