Thursday, November 7, 2013

ይድረስ ለጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግሩም ተ/ሀይማኖት

ይድረስ ያልኩት በቀጥታ ባይደርሶትም መስማትዎ እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ሰላም የምሎት ሰላምታ የእግዚአብሄር በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ ጫንቃችን ላይ ተጎብራችሁ የዜግነት ክብንርን አውርዳችሁ የዜግነት ክብር የምታዘምሩ በሆናችሁ፣ በብሄር ፣በጎሳ ከፋፍላችሁ…ሰብዓዊ መብታችንን ገፋችሁ..ኑሮን መቋቋም እንዳንችል አድርጋችሁ ለስደት ስለዳረጋችሁን ሰላምስ ማለት አይገባም ነበር፡፡ ለስምም ሆነ አልሆነ በአሁኑ ሰዓት ለሀገሪቷ ጠ/ሚኒስትር በመሆንዎ ነው ይድረስ ያልኩት ለእርሶ ይሁን እንጂ ለሚመለከታቸው ባለስልጣኖች ሁሉ ይድረስ ማለቴ አይቀርም፡፡ ጥቂት ጥያቄዎችንም መሰንዘሬም አይቀርም፡፡


ለኢትዮጵያዊነት ክብር ሳትሰጡ የምታስተዳድሯት ኢትዮጵያ ያለ ህዝብ ባዶ መሬቷ ትርጉሙ ምንድን ነው? ህዝቡን ጠልታችሁ በኑሮ እንዲማረር ከማድረግ ጀምራችሁ ፍትህ ነፍጋችሁታል፡፡ ገበሬ ቦታውን ይነጠቃል፡፡ ኢንቨስተር ከተገኘ ግነት ገደል ይግባ ውስጣዊ መርሃችሁ ነው፡፡ ግን እስከመቼ? ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ መሆኑ ቀርቶ እጅ አፍ ጋር ሳይደርስ ተንጠልጠሎ ሲቀር ስደት ተመረጠ፡፡ ስደቱም በገፍ እንዲወጣ ከማድረግ ጀምሮ በየሀገሩ ለምን ዜጋዬን ብሎ የሚጠይቅ ባለመኖሩ ዜጎቻችንን በማሰርና መግረፍ ተጀምሮ ለምን ባይ ባለመኖሩ በየአደባባዩ እንደፈለጉ መግደል ተዘውትሯል፡፡ ማነው ለኢትዮጵያዊያን መብት መጠየቅ የሚችለው? የሀሪቷን ፖለቲካ ምህዳር የምታሽከረክሩት እናንተ ስለሆናችሁ ለዜጋው ምን እየሰራችሁ ነው? የትኛውን መብት አስከበራችሁ? ኢትዮጵያዊያ በአረብ ሀገራት ጠያቂና ተቆርተቋሪ የሌለው ሆኖ እንዲህ በየቦታው እየረገፈ ዝምታችሁስ ምንድን ነው? ኤምባሲ ብላችሁ በአረብ ሀገራት የከፈታችሁት ጸ/ቤቶች ሁሉ ስራቸው ምንድን ነው? መጀመሪያ ደረጃ ዜጋውን እንደ ዜጋ ተቀብለውስ ያስተናግዳሉ? ኢትዮጵያዊነት ትርጉም ያጣው በእናንተ ጊዜ መሆኑንስ አለመረዳታችሁ አውቆ የተኛ አያሰኝም?

በህጋዊም ሆነ በህገ-ወጥ መንገድ የሚሰደደው ኢትዮጵዊ ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ነው፡፡ የምታወሩት ባለ ሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ እድገት እውን ይሁንም አይሁንም በወሬ ብቻ ሆኖ መሮት የሚሰደደው ቁጥር በስድስት ዲጂት ማደጉን ልብ ማለት አልቻላችሁም፡፡ ታዲያ የእርሶ ጠ/ሚኒስትርነት ለየትኛው ህዝብ ነው፡፡ ከሀገር የወጣው ኢትዮጵያዊ ለእርሶ ኢትዮጵያዊ ሆኖ አልታዮትም ወይስ እንደሚባለው አድርግ ተብሎ የሚታዘዙትን ብቻ ነው ማድረግ የሚችሉት፡፡ ከሆነ እንኳን እባኮት ሪሞቱን ለያዙት ሰዎች ዜጎቻችን ስደት ላይ በየቦታው እየረገፉ ነው እና አይናችሁን ላክ አድርጉ ይበሏቸው፡፡ እስኪ እነዚህን ፎቶዎች እዩዋቸው፡፡ የደህንነት አባሎቻችሁ ድረ-ገጾችን ማፈን ላይ በርትተው ከሚሰሩ መፍትሄ ይስጡ፡፡ እውነታውን ይቀበሉ፡፡

ያለበለዚያ ግን የደህንነት ስራቸው ስልጣን የማራዘም ብቻ ሆኖ አለም የሚጮኸውን፣ አለም አቀፍ የተለያየ መገናኛ ብዙሀን የሚያሰሙትን ጥሪ እንኳን ካልሰሙ የደንቆር ስብስብ ነው ማለት ነው፡፡ ዛሬ እንኳን እስኪ እውነታውን እዩ…ህዝቡ ምን ይላል? ዜጎቻችን ላይም ምን እየደረሰ ነው፡፡

ሌላውን ትተን በቤይሩት በዚህ አንድ ወር ውስጥ ብቻ ሰባት ሰው ላይ የመኪና አደጋ እንደደረሰ በመረጃ የተደገፈ እውነት ነው፡፡ ወገኖቻችንን ከማሰቃየት ባለፈ በመኪና መድፋትንም ሆን ብለው በሚመስል መልኩ ገፍተውበታል፡፡ ጠያቂ፣ ሀይ! ባይ የሌለው ዜጋ ተገኝቷል..ኧረ!…ወገን ድምጻችንን እናሰማ…. እናንተም ለመስማት እና ዜጋችሁን ለማስታወስ ያብቃችሁ፡፡

No comments:

Post a Comment