የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት ሁለት አባላት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ቀደም ሲል በቅንጅት ለአድንነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) በተለያዩ ደረጃዎች ሲታገሉ የቆዩና አሁንም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እየታገሉ የነበሩት ሻምበል ጥላሁን ተክለመድህን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ሻምበል ጥላሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትና እኩልነት ሲታገሉ የነበሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁርጠኛ ታጋይም ነበሩ፡፡ ሻምበል ጥላሁን ከቅንጅት በኋላ በአንድነት ፓርቲ ምስረታና አደራጅ በመሆን በምርጫ 2002 ዓ.ም መድረክን በመወከል በአማራ ክልል በአንኮበር የምርጫ ክልል ተወዳዳሪ ነበሩ፡፡ ባደረባቸው ህመም ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡
አቶ ዘውዴ ክፍሌ በበኩላቸው የባህር በር ባለቤትነት መብት እንዲከበር የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ኢህዴፓን በመወከል ለወረዳ 15 ምክር ቤት፣ ቅንጅትን በመወከል በቀድሞ ወረዳ 15 ተመራጭ የነበሩ፡፡ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሲመሰረትም በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባል በመሆን ጠንካራ ተሳታፊ የነበሩና እስከ ዕለተ ሞታቸውም ድረስ የወረዳው አመራር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ ፅኑ የኢትዮጵያ ታጋይ አባት ነበሩ፡፡ ባደረባቸው ህመም ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡
No comments:
Post a Comment