Wednesday, November 13, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ አርብ ለሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ


ህዳር (አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ለኢሳት እንደገለጸው ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍል ፣ የሰላማዊ ሰልፍ መጠየቂያ ደብዳቤውን እንደማይቀበል ቢገልጽም፣ ፓርቲው ተቃውሞውን በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ለማድረግ ወስኖ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ተባብሮ ተቃውሞ ማዘጋጀት ሲገባው፣ ፓርቲው እንዳያዘጋጅ መከልከሉ እንዳስገረመው ወጣት አሬድ ገልጿል።
ኢትዮጵያውያን ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍም በጥሩ ሁኔታ እየደገፉ መሆኑን አክሎ ገልጿል በሳውዲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ ተከትሎ በአገር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment