ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራሩ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 18 ለህዝብ አገልግሎት በሚል የተሰራው ጤና ጣቢያ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የእስረኞች ማጎሪያ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሆን መደረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የአካባቢው ነዋሪ በቂ የህክምና ቦታ አጥቶ በሚቸገርበት ጊዜ ፣ መንግስት ጤና ጣቢያውን ፖሊስ ጣቢያ ማድረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የክፍለ-ከተማውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment