Monday, November 18, 2013

ኢህአዴግን በግልጽ በቃህ የምልበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ አዎ!

beka2-300x168
ኢትዮጵያዊ ባልሆነ መንግስት መገዛት ይብቃን!

አንድ የኢህአዴግ ታጋይ አሊያም ሲቪል ካድሬ ሲሞት በቴሊቪዥን ሳይቀር ይለፈፍለታል፡፡ በሳውዲ እየሞቱ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ግን አንድም ነገር አልተደረገም፡፡ ሌላው ይቅርና መሰሎቹ አጭበርብረው ‹‹ምርጫ አሸነፍን›› ሲሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለማጉረፍ ማንም የማይቀድማቸው እነ ኃ/ማሪያም አሁን ምንም አላሉም፡፡ በተቃራኒው ድምጽ ለማሰማት የወጡትን በጨካኝ ፖሊሶቻቸው አስደበደቡ፡፡

ወደ ጣሊያን ሲያቀኑ ያለቁት የአፍሪካ ስደተኞችን ሞት አስመልክቶ ሰንደቅ አላማው ዝቅ ብሎ ተውለብልቧል፡፡ የኢትዪጵያውያንን ነፍስ ምን ያህል አርክሰው ቢያዩት ነው? ለአንድ ቀን ሀዘን፣ ለአንድ ቀን ሰንደቅ አላማውን ዝቅ ለማድረግ አልፈቀዱም፡፡ ስለዛ አምባገነን መሪያቸው ግን ሁሌም ይቆዝሙብናል፣ ይለምኑብናልም፡፡ ኢትዮጵያን እንደነጠቁን ሰላማዊ ሰልፉን በመከልከል ዳግመኛ አረጋግጠውልናል፡፡ በተቃራኒው ከኤስያ፣ እስከ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ የእኛዎቹ ወገኖች እንደልባቸው ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡፡

እንዲያውም ድጋፍ እየተደረገላቸው፡፡ ትናትና ፌስ ቡክ ላይ እንዳነበብኩት አንድ የአውሮፓ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ የድምጽ ማጉያ የመሳሰሉ መሳሪያዎች ከሌሏቸው ማዘጋጃ ቤቱ ሊያውሳቸው እንደሚችል አረጋግጦላቸዋል፡፡ እንደ ሳውዲ ካሉት ውጭ ለኢትዮጵያውያን አገራቸው ካለው ይልቅ የተሰደዱበት መንግስታት ደግና ርሁሩሆች ናቸው፡፡ ለእኔ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ ላለመሆኑ ከዚህ ውጭ አስረጅ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ የግድ እንደ ግራዚያኒ በየ ቤታችን ገብቶ በቆጨራ እስኪቆርጠን መጠበቅ የለብንም፡፡ ካድሬ ሆነ ተቃዋሚ፣ አማራ ሆነ ኦሮሞ፣ ትግሬ ሆነ ወላይታ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እስካለሰበ ድረስ ከስቃዩ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ መለስ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ኢህአዴግ ገንዘብ ሲያሰባስብ የነበረው እንደ ሳውዲ ባሉ አገራት ከሚገኙት ዜጎቻችን ጭምር ነው፡፡ የልመና ጊዜ በሮ የደረሰው የውጭ ጉዳይ አሁን በቲውተር ከሚቀልደው ያለፈ ሊፈይድ አልቻለም፡፡ ካድሬም ብትሆን አይቀርልህም፡፡


በጊዜያዊ ጥቅም ከሆነማ ጣሊያንም ለባንዳዎቹ ከፍተኛ ጥቅም ሰጥታለችኮ፡፡ እነ ራስ ሀይሉ በወር 175 ሺህ ሊሬ ይከፈላቸው ነበር፡፡ የፋሽስቱን ስርዓት ያልተቃወመ ወጣት አሁን ኢህአዴግ ከሚያደርገው በላይ ተከፍሎታል፡፡ እናቶች፣ ካድሬ ቄሶችና ሌሎችም ኢህአዴግ አሁን ከሚያደርግላቸው በላይ ጣሊያንን እንዳይቃወሙ ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኋላ ግን በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡ እናም ይህን ኢትዮጵያውይ ያልሆነ መንግስት ኢትዮጵያዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ በቃ! ከዚህ በላይ በደል መሸከም አንችልም፡፡ ከዚህ በላይ ባይተዋር መሆን አንፈልግም፡፡ ከዚህ በላይ ማንባት አንሻም፡፡ ኢህአዴግን በግልጽ በቃህ የምልበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ አዎ! ኢትዮጵያዊ ባልሆነ መንግስት መገዛት ይብቃን!

sourse minilik salsawi

No comments:

Post a Comment