Saturday, November 2, 2013
በረከት ስምኦን የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ቦርድ ኃላፊነቱን ቦታ ለሬድዋን ሁሴን አስረከበ
የወያኔዉ ፓርላማ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ያቀረበዉን ሹመት ተቀብሎ ማጸደቁ ተሰማ። ይህ አንቅልፋምና ከአገዛዙ የቀረበለትን ነገር ሁሉ ከማጽደቅ ዉጭ ሌላ ምንም አይነት አማራጭ እንዳለዉ እንኳን የማያዉቀዉ ፓርላማ የኢትዮጵያን ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት የመራዉ በረከት ስምኦን በሬድዋን ሁሴን እንዲተካ የቀረበለትን ጥያቄ እንዳለ ተቀብሎ አጽድቋል። ሹመቱ በአማካሪዎችም ሆነ በካቢኔ ደረጃ ምንም አይነት ዉይይት ሳይካሄድበት በድንገት የተደረገ ሲሆን በዚሁ ሬድዋን ሁሴን በሚመራዉ ቦርድ ዉስጥ በቅርቡ ለረዥም ጊዜ ካገለገለበት የብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃላፊነቱ ተነስቶ በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የሕዝብ ተሳትፎ አደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆነው የተሾመዉ ደስታ ተስፋውና አማኑኤል አብርሃም፤ ዓቢይ መሐመድ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል፣ አቶ ገበየሁ በቀለ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አባል፣ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ ከእምነት ተቋማት ፣ አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከኢቲቪ የቦርዱ አባላት በመሆን ተሹመዋል። የፓርማዉ አባልና በተሰናባቹ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ በአባልነት ያገለገሉ አንድ ስማቸዉ እንደነገር ያልፈለጉ ግለስብ የፓርላማዉን ሹመቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ሹመቱ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን በመጥቀስ ማብራሪያ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል። እንደእሳቸው አባባል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተጠሪ የሆኑ የመንግሥት የሚዲያ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሆናቸውን በማስታወስ ለሁለቱ ተቋማት 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሹመት መስጠቱን አስታውሰዋል። ይህንኑ ማብሪያያ ይሰጠኝ በሚል ከፓርላማዉ የተነሳዉን ጥያቄ የፓርላማዉ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ጠ/ሚኒስትሩ በማንኛውም ጊዜ ሚኒስትሮችን ሲያነሱ ማብራሪያ እንደማይጠየቁ ሁሉ የቦርድ አባላትንም ሲሰየሙ ማብራሪያ ለመስጠት እንደማይገደዱ በመናገር አግባብ ያለዉን ጥያቄ በተለመደዉ የቃላት መዶሻዉ ደብድቦት አልፏል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment