“ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ!”
“ኢትዮጵያ የምትመራው ከትጥቅ ትግል ጀምሮ እስካሁን ድረስ በኤርትራውያንና በትውልደ ኤርትራውያን ነው እኔም ኤርትራዊ ነኝ” ስብሃት ነጋ ከሀገር ፍቅር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ንጉሴ ወልወደማርያም በዋሽንግተን ዲሲ ከተናገሩት የተወሰደ”። *ደብረጺዮን ገብረሚካዔል፣ቴዎድሮስ አድሃኖም፣በረከት ስምኦን፣…እና ሌሎችም ኤርትራውያን “ከሥልጣን ይውረዱ !! የህወአት/ሻቢያ ቅጥረኖች ሆድአደር፣ አድርባይ ደደብ የብሄር ብሔረሰብ ወካይ ነን የሚሉ ከፊት አስቀምጠው የሚጋልቧቸው ሽመልስ ከማል፣ሬድዋን ሁሴን፣ዲና ሙፍቲ ኀይለማርያም ደስአለኝ፣ ሸፈራው ሽጉጤ፣ ሸፈራሁ ተ/ማርያምን በመተካካት ከኋላ ቂጣቸውን እየገረፉ በገዛ ብሔረተኞቻቸው እያስቀጠቀጡ ኢትዮጵያውያኑን ተበቀሏቸው።ሀገራቸውን፣ ወደባቸውን፣ መሬታቸውን፣ ሕጻናት ልጆቻቸውን፣ ወጣት ሴቶቻቸውን፣ባህልና አብሮ መኖርን ገፈው በማኅበር ተደራጅተው ሸጧቸው፡፡ ተው ብለናል!
*ለመሆኑ መንግስት ምንድነው? ገድሎ ሬሳህን አሞራ እንዳይበላው የሚጠብቅ ወታደር ያለው ማለት ይሆን?
*ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ አንድ ሀገር ሳትሆን በወሮ በላ ተከፋፍላ በክልል ታጥራ እንድትኖር በህወአት ማኒፌስቶ(ሕገመንግስት) ፅሑፍ ተረቆላት፣ ህዝቦቹ በፊት ያልነበሩ፣ እንደአዲስ ተፈጥረው ለመሬት፣ ለወደብ፣ ለዳርድንበር፣ ለቋንቋ፣ ለባሕልና ለታሪክ፣ ለአንድነትና አብሮ መኖር እሴት ላይናገሩ እንኳንም በቁማቸው ስለሚኖሩበት መሬትና መብት ፣ሞተውም ኪራይ የሚከፍሉባት የመጤዎች መስፈሪያ ስትባል ህዝቡ ፣ባርኔጣውን ደፍቶ፣አንገቱን በሻርብ አስሮ፣ በቀን በቀን ዘፈን እየነገደ እንደከብት ሲፈነጥዝ ፳፪ ኣመት አለፈ። የሚበላው ሌላ የሚያገሳው ሌላ እንዴት ይጨፍራል ይህ ህዝብ ሳይበላ? አያት.. ቅድም አያቶች ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በክብር ያቆዩለትን በሀገሩ በወንዙ በቀዬው ለመብታችን አንናገርም እንቢኝ አንልም! እንገረፋለን፣ እንታሰራለን፣ እንገደላለን፣ ሴቶች እህቶቻችን ይደፈራሉ።ለመሆኑ በሰው ሀገር ሄዶ ክብር ስጡኝ ማለት አግባብ ነውን? ባለቤቱ እራሱ የጣለውን ማንነት አሰው ደጅ ኢከበርልኝ ማለት መሃይምነት….!?
*የአፍሪካን ፳፭ከመቶ ድራጎት የሚቀማው የህወአት መንግስት፣ መሬት፣ ወደብ፣ ግድብ፣ ለውጭ ዜጋ የሰጠ ወንበዴ ፣ ፲፩ከመቶ ለ፰ዓመት ያላቋረጠ ዕድገት፣ የዳቦ ዕጥረት፣ የውሃና መብራት ዕጦት፣ ያጎናፀፈ ራዕይ ደረት ሲደቃለት፣ ንፍሮ ሲወቃለት፣ ባነር ሲወጠርለት፣ ሆድአደር አድርባይ ሲወጠርበት፣ዲያስፖራ ለሀጭና ንፍጡን ያዝረከረከለት ፤ታማኝ ካድሬ ፎቶ የሸጠበት፤አጋፋሪ አርቲስት ያሽቃበጠበት፣ሻማና ጧፍ የባከነበት፣ የብሄር ብሄረሰብ ለቅሶ ትዕይንት፣(የፍትወት) የሴክስ ቱሪዝም የተከፈተበት፣ ዜጋ(ግብረሰዶም) የተስፋፋበት፣ሃይማኖት እንደአሸን የፈላበት፣የህጻናትና ሴቶች ልጆች ንግድ የተከፈተበት፤ ፵፻በሚበልጡ መንግስታዊ ባለሀብት የሰው ልጆች የመሸጫና መለወጫ የንግድ ድርጅቶች በወታደራዊ ባለሀብቶች ሲቋቋም፣ወጣቱ ሌት በብርድና በዝናብ ድንጋይ ላይ ተኝቶ አድሮ ፓስፖርት በጉቦ ገዝቷል።የወያኔን ባለሀብት አድርጎ ሀገሩን አስረክቦ በፍቃደኝነት የሌባ ተባባሪ መሆን የኢትዮጵያዊያን የቀን ከቀን ሕይወት ነው! ዓይኖቻችን በርካታ ግፎችን ተመልክተዋል! እኛው ፈቅድን ህወአት አዋረደን! በለው!
**በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ በሱዳን፣ በኬንያ፣ታንዛኒያ፣በጋና፣ሊቢያ፤በየመን ፣በግብፅ፣በደቡብ አፍሪካ፣ ኢሰብዓዊ የሆነ ድርጊት ተፈፅማል። ሴቶች እህቶቻችን ከባሎቻቸው ተነጥለው ተወስደው አንዳንዶቹም በሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ፊት በብዙ የአረብ ጎረምሶች ተደፍረዋል። በዚሁ የተነሳ ህይወታቸው አልፏል፣ ብዙዎች በአደባባይ ደማቸው ፈስሷል፣ በግፍ ተገድለዋል፤ የተረፉትም በአሰቃቂ ሁኔታ ምግብና ውሃ በሌለባቸው ማጎሪያዎች ተወርውረዋል ሆድ ዕቃቸው ተቀንሶ ተሸጧል በዱር በገደሉ የአውሬ እራት ሆነዋል፣ በበረሃ አሸዋ ውስጥ በጅምላ ተቀብረዋል፣ ባሕር ተወርውረዋል። በኢትዮጵያም ከዋና ከተማው አዲስኣበባ እና በአራቱም ማዕዘን ላለፉት ፳፪ዓመታት ግፉ ነበር አለ ይቀጥላል።እንዲያውም በውጭ ኢንቨስተሮች የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት እረገጣ ስድብና ዱላ፣በገዛ ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እጅጉን የከፋና የከረፋ ነው። ከዚህ የተነሳ ሌሎች በሀገራቸው ቢንቁን ቢገድሉን ማን ጠያቂ አለባቸው? ወያኔ እንጂ ወኔ ያለው የለም!።
**እኛ የሞቱ ጠ/ሚኒ “ሀገር ማለት ወንዙ፣ ተራራው፣ ሽንተረሩ፣ አደለም ‘ሕዝቡ’ ነው” አሉ፡ ለመሆኑ ይህ ብሔር ብሄረሰብ ሕዝብ አደለም እንቨስተር ብቻ ነው ሰው(ህዝብ) ማለታቸው ይሆን?ለመሆኑ እነኝህ ብሄር ብሔረሰቦች ታስረው፣ ተደብድበው፣ ተሰደው፣ ተገለው፣ እንደሚያልቁ ተጠንቶበታል ማለት አደለምን?አለበለዚያ ሀገር አልባ ናቸው መሬቱ በኮንትራት የሚሰፍሩበት ስለሆነ እንደሀገራቸው አይቆጠርም ማለታቸው ነው?ለዚህም ይሆን መንግስት(ህወአት) ለመሬት ከፍተኛ ፍቅር ያደረበት? ከሚናገሩት ይልቅ የሚሰሩትን ማየት ተገቢ ነው።አሁን በውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ላይ የሚደረግ ጩኸት ዋጋ ያስከፍላል፡በህወአት መንግስት ላይ መነሳት ግን ዘላቂ ጥቅም አለው በለው! “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን”ለዚያውም ሕግን ባልተከተለ የጉልበት ፉከራና ዛቻ መዘዙ ከባድ ነው። ምን አልባት ሌሎች አረብ ሀገሮችም ተመሳሳይ አጻፋና ከሀገራችን ውጡልን አመፅና የጉልበት እርምጃ ወስደው የከፋ ችግር በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ እንዳይደረስ መጠንቀቅ ነው። ግዜውን ጠብቆ ግን በሀገር ውስጥ ማንነትን ማሳየት ተገቢና ሕጋዊ የዜግነት በመብት ነው።!!ይህንን አብሮ መቆምና መታገል መብት ማስከበርን ከ፳፪ኣመት በፊት ብለነው ቢሆን ከ፵ዓመት በፊት ስለሰው ልጅ ክበር ተሟግተው ቢሆን ዛሬ እንኳን አረብ ሀገር አደለም አውሮፓና አሜሪካ አንሰደድም ነበር።እስልምና ሃይማኖት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድሮ ቀረ አሁን አላህዋክበር ቀልድ ሆኗል። አሁንም ጃዋር መሀመድና ተስፋዬ ግብረእባብ ከህወአት ጋር በመተባባር ይህንኑ በሜንጫ መተላላቅ ሀገርህ ድረስ ያመጡልሃል አፍክን ከፍተህ ጠብቅ!!ቂጥህን ገልበህ ከመጨፈርና በራዕይ ከማረር ተነስ እንቢኝ በለው!!
*በዚሁ አጋጣሚ “ነብዩ ሲራክ…ግሩም ተክለሃይማኖት የተባሉ ግለሰቦች ለዘመናት ሲጮሁ፤ሲያለቅሱ፣ ሲጣሩ፣ ያዳመጠ፣ የረዳቸው የለም..አሁን የሚታየው ግርግር የውሸትና ለትንሽ ቀን ነው። እያንዳንዱ መዝሙርና ዘፈን በማውጣት በተጎዱ ወገኖች ሥም የችሎታ መለማማጃ ባያደርጋቸው የተሻለ ነው። ኢህአዴግ ሻቢያን ከሥልጣን ያባር ኀይለመለስ ደስአለኝ ከሥራው ይውረድ! መንግስት እንደዕቃ የሸጠውን ወጣት በራሱ ወጪ ይሰበስባል ማለት ውሸት ነው!። ይህ ወጣት በሰው ሀገር በነፃነት መኖር አለብኝ ሀገሬን ለህወአት ቤተሰቦች ሰጥቻለሁ ማለት የለበትም። አሁን ይህ ትውልድ መጠየቅ ያለበት ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ ልጆችና ቤተሰቦች የት ናቸው?።ቻይና፣ ሕንድ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ በወር ፭ሺህ ዶላር ይላክላቸዋል፣ ቤት ተገዝቶላቸዋል፣ይነግዳሉ፣ ወደፊት በመተካካት የሚቀጥለውንም ትውልድና መሬት ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ የማናት? ይህ የተበሳቆሉትን የተገረፉትን የተበደሉትን ለኢህአዴግ ቤተሰቦች በተግባር ማሳየት አለባቸው። ያለቀሱለት የመልስ ራዕይ እዚህ ላይ ለመድረስ ነበርን? ሁለት ወር ሙሉ ደረት መድቃት፣ረግዶ፣ ሻማና ጧፍ ማቃጠል፣ ትርፉ ይህ ነው ልመናቸውና ራእዩ ተፈፅሟል።በሰላም ሀገር በቀን አበል አጉል የፈሰሰን እንባ እግዝሐብሄርን አስቀይሟል… ቤተክርስቲያን ማቃጠል፣ ሰው በሜንጫ መግድልና ከእነነፍሱ ገደል ጨምረው አላህዋክበር!የሚሉ ሁሉ ልብ ይግዙ! ዋነኛው ጉዳይ ለዚህ ሁሉ ስደትና ውርደት ግድያና ሰቆቃ የዳረገንን የህወሃት አገዛዝ እና አስተሳሰቡን ጭምር ነቅለን መንግስት አልባ የሆነችውን አገራችንን የህዝብ መንግስት ባለቤት ለማድረግ የሚካሄደውን ዕልህ አስጨራሽ ትግል በመቀላቀል የድርሻችንን እንወጣ። “ኢትዮጵያ እጆቻን ዘርግታ የተበታተኑ ቅን አሳቢ ልጆቻን ትሰበስባለች! ሀሴትም ታደርጋለች! በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ
No comments:
Post a Comment