ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘግይቶም ቢሆን ችግረኛ ኢትዮጵያውያንን ከሳውድ አረቢያ ማስወጣት የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት፣ እስካሁን ድረስ የተመላሾችን አሀዝ በተመለከተ የሚሰጠው መግለጫ ግን ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ መጣሉን የኢትዮጵያው ዘጋቢያችን ገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በቲውተር ወደ አገር ቤት የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 10 ሺ 707 ነው በማለት ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ የእርሳቸው ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የተመላሹን ቁጥር በ6 ሺ በማሳነስ 4 ሺ 961 ሰዎች መግባታቸውን ለጀርመን ራዲዮ ተናግረዋል። ሁለቱም ባለስልጣናት መግለጫዎችን የሰጡት በአንድ ቀን ውስጥ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ይህን ያክል ቁጥር ያለው ልዩነት እንዴት ተፈጠረ ሲሉ ጠይቀዋል።
No comments:
Post a Comment