Wednesday, November 13, 2013

አምባሳደር ሙሴ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሠላምና በግጭት አፈታት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሰፊ ሥራዎችን በማከናወን የሚታወቁት አምባሳደር ሙሴ ኃይሉ ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት ጀምሮ በቀድሞ ማዕከላዊ ፖሊስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ተጠቆመ።
የሰንደቅ ጋዜጣ ምንጮች እንደተናገሩት አምባሳደር ሙሴ በአዲስ አበባ በመደበኛ ሥራቸው ላይ እያሉ በፖሊስ ቁጥር ሥር ከመዋላቸው በስተቀር ስለታሰሩበት ምክንያት የታወቀ ነገር የለም።
አምባሳደር ሙሴ ባለፈው ሣምንት ረቡዕ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ትላንት ከሰዓት በኋላ ድረስ አለመፈታታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
 
አምባሳደር ሙሴ ኢንተርፌዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢንሸየቲቭ የተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ይህ ድርጅት በተለይ በሠላምና በግጭት አፈታት ዙሪያ ከ12 ዓመታት በላይ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። በተጨማሪም አምባሳደር ሙሴ በእነፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ የሚመራ የሽማግሌዎች ቡድን ውስጥ በቀጥታ በመሳተፍ አንዳንድ አገራዊ አለመግባባቶች በዕርቅና በሠላም እንዲፈቱ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ከቆዩ የአገር ሽማግሌዎች አንዱ መሆናቸውን ምንጫችን አስታውሷል።
source: ሰንደቅ ጋዜጣ 
posted by Aseged Tamene

No comments:

Post a Comment